Telegram Web Link
ሶስቱ ሳታስቡት የተቆጣጠሯችሁ ሰዎች

በሕይወታችሁ በሰዎች አጉል ቁጥጥር ስር ሆናችሁ እንድትኖሩና ነጻነታችሁን እንድትቀሙ ከሚደርጓችሁ አጉል ልምምዶች መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

1. ለመቆጣጠር የምትሞከሯቸው ሰዎች

የት እንደገቡ፣ ምን እንዳደረጉ፣ ከማን ጋር ወዳጅነት እንደጀመሩ፣ ምርጫቸው ምን እንደሆነና የመሳሰሉትን ነገር ካላወቃችሁና በጉዳዩ ላይ እናንተ ከሌላችሁበት ቅር የሚላች ሰዎች እናንተ የተቆጣጠራችኋቸው ይመስላችኋል እንጂ የተቆጣጠሯችሁ እነሱ ናቸው፡፡ እነሱን መከታተል፣ ሳታስቡት ጊዜያችሁን፣ ስሜታችሁንና ጉልበታችሁን ስሚወስደው ቀስ በቀስ በእነሱ ቁጥጥር ስር እንዳላችሁ አትርሱ፡፡

2. ቂም የያዛችሁባቸው ሰዎች

በቂምና በጥላቻ የምታስቧቸውን ሰዎች እነሱ በሚሄዱበት መንገድ ላይ ማለፍ፣ እነሱ በሚውሉበት አካባቢ መገኘትና እነሱ በሚሳተፉበት ነገር ላይ መሳተፍ ስለማትፈልጉ ብትወዱም ባትወዱም በእነሱ ቁጥጥር ስር ናችሁ፡፡ በተጨማሪም እነሱን ባሰባችሁ ቁጥር በስሜት ስለምትንተከተኩ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ከዋናው ዓላማችሁ ስምትገቱ በእነሱ ቁጥጥር ስር ናችሁ፡

3. የምትቀኑባቸው ሰዎች

በፍቅር ጓደኝነት ሆነ በሌሎች ዘርፎች በጣም የምትቀኑባቸውን ሰዎች ካሉ የእነሱን ውሎ፣ ስኬትና የመሳሰሉትን ነገር ከመከታተል ማረፍ ስለማትችሉ እነዚህ ሰዎች በተዘዋዋሪ መንገድ ሕይወታችሁን ተቆጣጥረው እንደያዙት አትዘንጉ፡፡ ትኩረታቸውን ከእናንተ ይልቅ ለሌላ ሰው እንደሰጡ፣ ስኬትና ዝናቸው ከእናንተ የበለጠ እንደሆነና የመሳሰሉት ስሜቶች ካልተገቱ እጅጉን የወረደና በቁጥጥር ስር የዋለ ሕይወት እንዳላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡

የምትቆጣሯውን ሰዎችን ትንሽ ለቀቅ አድርጉ፣ በሰዎች ላይ ያላችሁን ቂምና ጥላቻ ተወት አድርጉ፣ በሰዎች የመቅናታችሁን ጉዳይ ጣል አድርጉትና ራሳችሁን ከቁጥጥር ነጻ አድርጉ!


@mindset12
Morning Questions to Ask Yourself:

1. What good will I do today?
2. What bad habit can I avoid doing?
3. What am I grateful for in my life?
4. How can I improve today?
5. What challenge might I face today and how can I overcome it?
GOOD MORNING ☀️
እየቻላችሁ እንደማይችል ሰው አትኑሩ!

አንድ ንስር እንደዚያ ነፋሱን የሚቀዝፉና ወደ ከፍታ የሚያወጡ ክንፎች እያሉት፣ ልክ መብረር እንደማይችል አድርጎ ቢያስብና መሬት ላይ ቢከራርም ምን የሚሆን ይመስላችኋል? . . .

አንድ ፈረስ እንደዚያ የፈረጠሙ እግሮች እያሉት፣ ልክ መጋለብ እንደማይችል ቢያስብና ቁጭ ብሎ ቢውል ምን የሚሆን ይመስላችኋል? . . .

አንድ አሳ የምድር እንስሳት ለደቂቃዎች መቆየት በማይችሉበት የውኃ ማእበል ውስጥ ወዲህና ወዲያ እንዲዋኝና እንዲተነፍስ የሚደርገው አካል እያለው፣ ልክ እንደሌለው ቢያስብና ከውኃ ውስጥ ወጥቶ ቢሞክረው ምን የሚሆን ይመስላችኋል?

በተፈጥሮ፣ በስልጠናም ሆነ በብዙ የውጣ ውረድ ልምምድ በእናንተ ውስጥ የሚገኙና ሌላው ጋር የሌሉ አቅሞችም እንደዚሁ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች እያሏችሁ ልክ እንደሌለው ሰው ብትተውት ምን እንደምትሆኑ ገምቱና ድረሱበት፡፡

----------------------------
© Dr. Eyob

**** @mindset12
በእኛ የዳሰሳ ጥናት ለመሳተፍ ይህን ሊንክ ይከተሉ ፡፡ ለ 2ደቂቃ ጊዜዎን ስለሰጡን እናመሰግናለን ፡

https://www.tg-me.com/maseroinsightbot?start=i602f8b10382c9205c1328e6b
😢የምፈልገው አልሆነም አትበል! ሞክሬ እኮ አልተሳካም አትበይ! እስኪሆን መታገስ አቃተኝ በል። ጥግ ድረስ መሞከር ከበደኝ በይ። እንደዚህ ስንል መፍትሄው ግልፅ ነው....መፍትሄው ወይ መታገስ ነው ወይ ስትራቴጂ ቀይሮ በአዲስ መንፈስ መሞከር ነው! ማቆም የሚባል ነገር የለም!

@mindset12
If any one interested in telecom jobs join
2025/07/04 20:32:20
Back to Top
HTML Embed Code: