Telegram Web Link
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት 623 መሆኑ ተገለፀ።
---------------------------------------------
በሁለት ዙር በተሰጠው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት 623 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር ፈተና የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 563 ሲሆን በሁለተኛው ዙር የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደግሞ 623 መሆኑ ነው የተነገረው።

ከፍተኛ ውጤቱም በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ የተመዘገበ መሆኑም ታውቋል።

ፈተናው በመጀመሪያው ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ 600፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ 500 የተያዘ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ 600 መያዙ ታውቋል።

አጠቃላይ ፈተናውን በሁለት ዙር 598ሺ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 287ሺ223 ተማሪዎች 50% እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

@minesterofeducation
#MoE

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ታማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል።

ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንዲያደርጉ ጠይቋል ፦

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ የተባለ ሲሆን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ማሳሰቢያ የተላለፈ ሲሆን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሚኒስቴሩ የማናስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር

@minesterofeducation
''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየጠበኩ ነው'' የአበክመ ት/ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ሚኒስቴር መሰሪያቤቱ በዛሬው ዕለት ተገቢው ማብራሪያ እንዲማሰጥ ገልጾልኛል ሲል አስታውቋል።

ቢሮው ''ብሔራዊ ፈተና በሁለቱም ዙር በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጥ የሚፈለግብንን ሁሉ አድርገናል። ከ12ኛ ክፍል ፈተና አኳያ የክልሉ ድርሻም ይሄው ነው።'' ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው።

''የአንደኛው ዙር ፈተና እንደተጠናቀቀ በሚቀጥለው ቀን ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በወቅቱ ፈተና ተሰርቋል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሲስራጭ በነበረው የተለያየ መረጃ ምክንያት የፈተና ውጤት ትንተናው በጥንቃቄ እንዲታይ በፅሁፍ ጥያቄ አቅርበናል። ሌሎች ጠቃሚ ሀሳቦችንም በወቅቱ አቅርበናል።'' ሲል ዛሬ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

አክሎም በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በኩል አስፈላጊው ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ በትምህርት ቢሮው በኩል የሚፈለጉ መረጃዎች ካሉ መረጃዎችን ሳልደብቅ ገልጻለሁ ብሏል።

''የተማሪዎች ውጤት ለዞኖች፣ ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በግልፅ የተላለፈ ስለሆነ ለመሸፋፈን የሚፈልግ አካልም የለም መሸፋፈንም አይቻልም።'' ማለቱን ከቢሮው ገጽ ተመልክተናል።

@minesterofeducation
በአማራ ክልል የዘንድሮው የማትሪክ ማለፊያ ነጥብ ሁኔታ ❗️❗️👇👇

🔵በዋግኽምራ ጋዝጊብላ ወረዳ 229 ተፈትነው ያለፉት 29 ብቻ ናቸው፣

🔵በዳባት ወረዳ 1166 ተፈትነው ያለፉት 37ቱ ናቸው፣

🔵በምንጃር ወረዳ 350 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 5ቱ ብቻ ናቸው፣

🔵ሰሜን ወሎ ጋዞ ወረዳ 350 ተፈትነው ወደ ዩንቨርስቲ ያለፉት 5ቱ ብቻ ናቸው፣

🔵ሰሜን ሸዋ መንዝ ቀያ ወረዳ ከተፈተኑት 500 ተማሪዎች ያለፉት 30 ብቻ ናቸው፣

🔵ደቡብ ወሎ ለገሀዲ ወረዳ 275 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 2ቱ ናቸው፣

🔵ጃናሞራ ወረዳ 805 ተፈትነው ያለፉት 120 ተማሪ ብቻ ናቸው፣

🔵ታች ጋይንት ደቡብ ጎንደር 1720 ተፈትነው ያለፉት ያለፉት 22 ተማሪዎች ብቻ ናቸው፣

🔵ሲዳማ ክልል ሎካ አባያ ወረዳ 444 ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት 5ቱ ናቸው፣

🔵ጉራጌ ዞን ኤገር ወረዳ ሁሉም ተፈታኞች አላለፉም፣

🔵ከፋ ዞን ገዋታ ወረዳ ካሉት 6 ት/ቤቶች አንድም ያለፈ የለም።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት
@minesterofeducation
ከ20ሺህ በላይ የተማሪዎች ቅሬታዎች ላይ ምላሽ መሰጠቱን የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
---------------------------------------------
የፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ከፈተና እርማት እና ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው የፈተናው እርማት ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በጥንቃቄ የተከናወነ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ፈተና እርማት ላይ የቴክኒክ ችግር ማጋጠሙን እና እርማት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የእርማት ችግሩ የተፈጠረው በ 559 ባልበለጡ ተማሪዎች ላይ እንደሆነ እና ዳግም ምልከታ ተደርጎ መሰተካከል እንደተደረገም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የፈተና እርማት ችግር ማጋጠሙ የተገኘውም የፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ምርመራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቅሬታዎችን በተመለከተም ተማሪዎች ሳይጉላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው ቅሬታቸውን ለመፍታት የ ሚያስችል ስርዕት ተዘርግቶ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

በስርዓቱም ከ 20ሺህ በላይ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ መሰጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡

በተደጋጋሚ የሚነሱ የፆታ እና የስም ስህተቶች በትምህርት ቤቶች አካባቢ የተፈጠረ ክፍተት እንጂ የፈተናዎች አገልግሎት ክፍተት አለመሆኑን ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው አመት የተፈታኝ ተማሪዎች መብዛት እና በአገራችን ውስጥ ካሉት 47 ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ አሁን 43 ቱ ከፍተኛ የት/ት ተቋማት ብቻ የሚቀበሉ ስለሆነ ይህም የዩኒቨርስቲ ቅበላ አቅም አነስተኛ እንዲሆን በማድረጉ መግቢያ ነጥቡን ከፍ እንዳደረገውም ተገልጿል፡፡

በዚህም ምክኒያት በዘንድሮው አመት ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 25 ፐርሰንት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡
@minesterofeducation
#Update

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 25 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ ካሉት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 43ቱ ብቻ ተማሪዎች የሚቀበሉ መሆኑ የዩኒቨርስቲዎችን የቅበላ አቅም ዝቅ ማድረጉ ተነስቷል።

በተጨማሪም ዘንድሮ የተፈታኝ ተማሪዎች ብዛት የጨመረ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ነጥብ ከፍ እንዲል እንዳደረገው ተገልጿል፡፡

በሁለት ዙር የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 598 ሺህ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን 287 ሺህ 223 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወሳል።

@minesterofeducation
#Update

ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጠ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከ " 12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ውጤት እና ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ " ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍል ከ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ጋር ተያይዞ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የ12ኛ ክፍል ፈተና በ2 ዙር እንዲሰጥ መደረጉንና በመጀመሪያው ዙር የስነ-ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ከፈተናው ቀን ቀድሞ በመውጣቱና የውጤት ግሽበት በመምጣቱ እንዲሰረዝ መደረጉን ተናግረዋል።

በመጀመሪያ ዙር ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው በመጀመሪያው ዙር ፈተና ከወሠዱት 544ሺ 682 ተማሪዎች ውስጥ 44 ከመቶዎቹ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል።

በሁለተኛው ዙር ከተፈተኑት 53ሺ 997 ተማሪዎች ውስጥ 28 ከመቶዎቹ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ሲሆን ከመጀመሪያው ዙር 554 ሺ 682 ተፈታኞች ውስጥ ደግሞ 25 ከመቶዎቹ ይመደባሉ ብለዋል።

የ10 ክፍል የማትሪክ ፈተና በመቅረቱ ምክንያት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች በዘንድሮው አመት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ወስደዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው አራት ዩኒቨርሲቲዎቻችን መቀበል በማይችሉበት ሁኔታ ከአምናው የተሻለ ቁጥር ያለው ተማሪ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉን አብራርተዋል።

በትግራይ ያሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውና ዘንድሮም ይመደቡ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉ 48ሺ ተማሪ የቅበላ አቅም አጥተናል ብለዋል።

ነገር ግን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር በ43 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 152 ሺ 14 ተማሪዎች እንዲመደቡ መደረጉና ይህም ከአምናው የቅበላ አቅም ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል።

ፀጥታ ችግር ያጋጠማቸው አከባቢዎች በተመለከተ የተለየ መቁረጫ ነጥብ ለመወሰን የሚያስገድድ የውጤት ትንተና ስላልተገኘ በበመደበኛው የመቁረጫ ነጥብ ተስተናግደዋል ብለዋል።

በባለፈው አመት በ47 ዩኒቨርሲቲዎች 147 ሺህ ተማሪዎች ምደባ የተደረገ ሲሆን ዘንድሮ በ43 ዩኒቨርሲቲዎች 152ሺ 014 ተማሪዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@minesterofeducation
በዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ እንደማይደረግ ተገለፀ‼️

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ( ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ የጸጥታ ችግር አጋጥሞ በነበረባቸው አካባቢዎች የተገኘው ውጤት ከሌላው ጊዜ የተለየ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ዘንድሮ በ43ቱ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከ187 ሺ በላይ ተማሪዎች ይገባሉ ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ በበኩላቸው በእርማት ወቅት የነበሩ ስህተቶችን በወቅቱ አስተካክለናል፡ የሚሻሻል የነገር የለም ብለዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት

@minesterofeducation
ዩኒቨርስቲ ጥሪ ከሚያዝያ 30 በሗላ‼️

ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ ተብላቹሃል።

የፍሬሽማን ኮርሶችን ከሁለት ሴሚስተር ትምህርት በኋላ በበቂ መረጃና በዋናነት በመምህራኖቻችሁ ምክር ላይ የተመሰረተ የትምህርት ፕሮግራም እንደየአቅማችሁና ፍላጎታችሁ መርጣችሁ በመማር ብቁና በቂ ባለሙያ ሆናችሁ ለመመረቅ እንድትበቁ እንመኛለን።

#MOSHE
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት

@minesterofeducation
" .. የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው ይራዘምልን " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ጠየቀ።

ቢሮው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ በትምህርት አመራሩና በትምህርት ማህበረሰቡ ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ በመሆኑ ቢሮው የተማሪዎች ውጤት በአግባቡ ተፈትሾላቸው ተገቢው መተማመን እስኪፈጠር ድረስ የተማሪዎች መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቋል።

ቢሮው ይህን ጥያቄ ያቀረበው ለትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ ነው።

@minesterofeducation
#Update

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ጊዜ እንዲዘገይ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።

የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ መጋቢት 09 እና 10/2014 ዓ.ም በባሕር ዳር ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ነው ጥሪውን ያቀረበው።

"ከ12ኛ ክፍል አገር ዐቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ከተማሪዎችና ወላጆች አልፎ የማህበረሰባችን ጥያቄ በመሆኑ አገር ዐቀፍ ፈተናዎች ድርጅት እና ትምህርት ሚኒስቴር አስቸኳይ እልባት እንዲሰጡት" ሲል ፓርቲው አሳስቧል።

"እስከዚያው ድረስ ግን የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንዲዘገይ በአጽንኦት እንጠይቃለን" ብሏል ፓርቲው በመግለጫው።

@minesterofeducation
#ኢሰመጉ

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እንደገና እንዲፈተሽላቸው ጥያቄ ላቀረቡ ተማሪዎች መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ጠይቋል።

"የፈተናው ውጤት ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሽላቸው ለሚመለከተው አካል ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኙ" ጉባኤው ገልጿል።

"በመሆኑም የሚመለከተው ክፍል የተማሪዎቹን ጥያቄ በመመርመር አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው" ጉባኤው አሳስቧል።

በፈተናው ውጤት ዙሪያ "ከተለያዩ አካላት የሚሰነዘሩ ሃሳቦች ማኅበረሰቡን ግራ እያጋቡ እና የተማሪዎቹንም ስነ ልቦና እየጎዱ በመሆናቸው የሚመለከተው አካል ተገቢውን ማብራሪያ እንዲሰጥ እና የእርምት እርምጃ እንዲወስድ" ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪውን አቅርቧል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት

@minesterofeducation
የትምህርት ሚኒስቴር ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን
እንዲያስተካክሉ የሰጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ ተጠናቋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃጻጸም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ መጋቢት 08/2014 ዓ.ም ማሳወቁ አይዘነጋም።

ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወሳል።

በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላይ በርካታ ቅሬታዎች በተለይ ከአማራ ክልል መነሳታቸው ይታወቃል።

ሚኒስቴሩ በቅሬታዎቹ ላይም ሆነ በዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያው ላይ ያለው አዲስ ነገር የለም።

@minesterofeducation
የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ከ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ በኢፌዲሪ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የቀረበበትን አቤቱታ እንደማይቀበለው ማምሻውን አስታውቋል።

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ማምሻውን ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ከ12ኛ ክፋል ፈተና ጋር ተያይዞ የፈተናው እርማት ላይ ችግር ተፈጥሯል በሚል የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የለውም። ይህንንም በተጨባጭ ያረጋገጥነው በመሆኑ አስተራረም ላይ የተፈጠረ ሥህተት የለም ብለዋል።

ስህተት የተፈጠረው ፈተናው በሁለት ዙር የተሰጠ ከመሆኑና የመረጃ ቋቱም አንድ ላይ የተቀመጠ ስለሆነ ውጤት አገላለጽ ላይ መረጃ ሲወሰድ የተወሰነ ሥህተት ተፈጥሯል። ይህንንም በቀረበ ቅሬታ መሰረት ኤጀንሲው ማስተካከሉን ነው አቶ ተፈራ የገለጹት። ከ20 ሺህ በላይ ቅሬታ በኦንላይ እና በአካል ተቀብሎ የማጣራት ሥራ መስራቱን የጠቀሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ በኦንላይን የቀረቡ አቤቱታዎች አልታዩም የሚለውን ክስም ሥህተት ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ከመግቢያ ነጥብ ጋር በተያያዘ ያለው ቅሬታ እንደማይመለከታቸውና ጉዳዩ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑንም አቶ ተፈራ ገልጸዋል።

የኢፌዲሪ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከተማሪዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ ባደረገው ማጣራት ስህተት መፈጠሩን፤ ቅሬታ አመላለስ ላይም ችግሮች መኖራቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል። #ኢትዮመረጃ

@minesterofeducation
#Update

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ጉዳይ የከፍተኛ የፖለቲካ አመራር ውሳኔ እንደሚያስፈልገው ተጠቆመ።

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን ጉዳይ ለመፍታት የከፍተኛ ፖለቲካ አመራሩ ውሳኔ እንደሚያስፈልገው የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላት በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች ጉዳይ ላይ ተወያይቷል።

የክልሉ ተማሪዎች በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በስነ ልቦና ለፈተናው ዝግጁ ሳይሆኑ በጦርነት ውስጥ ሆነው ለፈተና መቀመጣቸው በውጤታቸው ላይ ተጽዕኖ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲ መግቢ የመቁረጫ ነጥብ ከተጠበቀው በላይ ከፍተኛ መሆኑ ተማሪዎችን፣ የተማሪ ወላጆችን፣ መምህራርን እና የትምህርት የሥራ ኃላፊዎችን መጉዳቱ በመድረኩ ተነስቷል፡፡

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የሥራ ኃላፊዎች የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን ጉዳይ ለመፍታት የከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ ውሳኔ ያስፈልጋል ብለዋል። #WMCC

@minesterofeducation
#የሕዝብ_ዕንባ_ጠባቂ_ተቋም

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ቅሬታ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊወስደው እንደሚችል አሳውቋል።

"ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ጉዳዩን በአግባቡ በመመርመር ለተማሪዎቹ ቅሬታ አሳማኝ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ጉዳዩን ለሕዝብ እንደራሴዎች እንደሚያቀርበው" ተቋሙ ገልጿል።

በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከአስተራረምና ከውጤት መቁረጫ ነጥብ ጋር በተያያዘ ያበረቡትን ቅሬታዎች ኤጀንሲው እያስተናገደበት ያለው መንገድ ኢ-ዲሞክራሲያዊ መሆኑን ዋና ዕንባ ጠባቂ እንዳለ ሀይሌ (ዶ/ር) ለቪኦኤ ተናግረዋል።

"ዜጎች ለሚያቀርቡት ቅሬታ ተገቢ ምላሽ የማያገኙ ከሆነ የሕግ አውጪው አካል ጣልቃ እንዲገባና እልባት መስጠት እንዲችል ጉዳዩን በልዩ ሪፖርት መልክ ለም/ቤት እንደሚቀርብ" ዋና ዕንባ ጠባቂው ገልጸዋል።

"አቤት ባዮች አጥጋቢ ምላሽ እስከሚያገኙ ድረስ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አቤት ባዮችን ወክሎ እንደሚሟገት" አስረድተዋል።

"የአቤት ባዮች መብት እስከሚከበር መሄድ ያለብን ድረስ እንሄዳለን። ይሄ የግለሰብ ወይም የተቋም ጉዳይ አይደለም። የሀገር ጉዳይ ነው" ብለዋል።

በስልክ፣ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት እና በአካል አቤቱታቸውን ለተቋሙ ያቀረቡ ተማሪዎችና ወላጆች ከፈተናዎች ኤጀንሲ ጋር በተያያዘ ሦሥት መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዳሏቸው ዋና ዕንባ ጠባቂው ይገልጻሉ።

"ለምናቀርበው አቤቱታ በአግባቡ እየተስተናገድን አይደለም፣ በፈተናው አስተራረም ላይ አጠቃላይ ቅሬታ ስላላቸው በድጋማሜ ቢታይልን እንዲሁም ጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች የተፈተንን ተማሪዎች ውጤት አንጻራዊ ሰላም በነበረባቸው አካባቢዎች ከተፈኑ ተማሪዎች ጋር በእኩል ባይታይ" የሚሉ ጥያቄዎችን ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

@minesterofeducation
⚠️⚠️ምደባን በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተማሪዎች

-እስከ የካቲት 30 የተባለው ምድብ እስካሁን አለመለቀቁ አጃኢብ ነው ወገን።ከተለያዩ ቤተሰቦች እየደረሰን ያለው መረጃ ልጆቻችን mentally በጣም እየተጎዱ ነው ሚሰሩት ከማጣቸው የተነሳ

-የተለያዩ የ12+ ተኛ ክፍል ተማሪዎች ልጆቻችን ወዳልሆነ ሱስ እና ጭንቀት ውስጥ እየገቡ ነው።መንግስት ስለነሱ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል።


-ወይም ድምጻችሁ እንዲሰማ የsocial media ዘመቻ በማድረግ የረሳችሁን መንግስት ማስታወስ ይኖርብናል።

-ተማሪዎች depression ውስጥ ገቡብን እያሉ የሚጮሁ እናቶች ስትሉ እንኳን በአፋጣኝ ምላሽ እንጠብቃለን።

ለተለያዩ ጥያቄዎች @marcilas3bot

@minesterofeducation
የ2013 ዓ/ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሂደት ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን እንዲያጣራ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው ኮሚቴ ምንድነው ያለው ?

የ2013 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት አስመልክቶ የአማራ ክልል ትምህርት ባቀረባቸው ቅሬታዎች ላይ የተደረሰበት ሂደት ኮሚቴው ለህዝብ አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ፤ በጦርነት አውድ ውስጥ ቆይተው ፈተና እንዲወስዱ የተደረጉ በክልሉ የሁሉም ዞን ተማሪዎች በውጤታቸው ላይ የተለየ ተፅዕኖ የተፈጠረ መሆኑ እና ጉዳዩ በልዩ ሁኔታ መታየት እንዳለበት #ከትምህርት_ሚኒስቴር ጋር አስፈላጊው መግባባት መፈጠሩን ገልጿል።

በትምህርት ቢሮው በኩል በጦርነት ተጽዕኖ ምክንያት ውጤታቸው የቀነሰባቸው ተማሪዎች ዝርዝር መረጃ እና አስፈላጊ ማስረጃዎች ሁሉ ለትምህርት ሚኒስቴር መቅረቡን ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴርም በቀረበለት መረጃ እና ማስረጃ መሰረት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እያየው እንደሆነና ውሳኔውን #በቅርብ_ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን ኮሚቴው ለህዝብ አሳውቋል።

ሌላው ኮሚቴው የተለያዩ መረጃዎችን አደራጅቶ ወደ ፈተናዎች ኤጀንሲ በመሄድ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምርመራ ያደረገ ሲሆን የደረሰበትን በዝርዝር አሳውቋል ፤ (በዚህ ያንብቡ https://telegra.ph/Amhara-Education-Bureau-04-15)

ተማሪዎች ፣ ወላጆች እና መላው ማህበረሰብ የትምህርት ሚኒስቴርን የመፍትሄ ሃሳብ በትግስት እንዲጠብቅ ኮሚቴው ጥሪውን አቀርቧል፡፡

በሌላ በኩል ፤ የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በተፈጠረው ችግር ሳይዘናጉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲዘጋጁ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥሪውን አቅርቧል።

@minesterofeducation
#የዩኒቨርሲቲ_ምደባ

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፤ ከተያዘው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ የ2013 ዓ.ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች የዩኒቨርሲቲ ምደባቸውን ማወቅ ይችላሉ ሲል አሳውቋል።

መቼ ? በየትኛው ቀን ? ስለሚለው ጉዳይ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ቁርጥ ያለውን ቀን ለማሳወቅ እየተሰራ መሆኑን እና ሚኒስቴሩ ቀኑን እንደሚያሳውቁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

@minesterofeducation
" ከ4 ክልሎች ተጨማሪ 8,080 ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ "

የትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ይፋ ካደረገው ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ ካላቸው 152,014 ተማሪዎች በተጨማሪ 8 ሺህ 80 የሚሆኑ ተማሪዎችን ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚመድብ አሳውቋል።

ምንም እንኳን ጦርነት ሁሉንም ክልሎች በተወሰነ ደረጃ ተፅእኖ ቢያሳድርባቸውም ነገር ግን በተለየ ሁኔታ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የነበረው ሁኔታ በልዩነት እንዲታይ ተደርጓል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተጠቀሱት አራቱ ክልሎች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያቸው ፥ " የጦርነት ስሜት የፈጠረው ነገር ተማሪዎችን ጎድቷቸው እንደሆነ አስተያየት የሚደረግበት መንገድ እንፈልግ በሚል የክልል ትምህርት ቢሮዎች ተስማምተው ለትምህርት ሚኒስቴር የሰጡት ስራ አስተያየት የሚደረግበት ሁኔታ ካለ እንዲፈለግ " የሚል እንደነበር አስረድተዋል።

በዚህም ፥ በፊት ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ከተቆረጠው ቁጥር 152 ሺ ተጨማሪ የሚገኝ ቁጥር ካለ ታይቷል ሲሉ ገልፀዋል።

በተለይም ፥ ከትግራይ ክልል መጥተው አራተኛ ዓመት ጨርሰው የሚወጡ ተማሪዎች ስለሚኖሩ የቅበላ ቦታዎችን ማግኘት ይቻላል በሚል ስራ ላይ ያሉት 43 ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን አቅም አሟጠው ወደ 8,080 ተማሪዎች የቅበላ ቦታ እንዳሳወቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የተገኘውን የተማሪ ቅበላ አቅም በፍትሃዊነት ለ4ቱ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት በተጎዱ ተፈታኞች መጠን እንዲከፋፈል መወሰኑንም አሳውቀዋል።

ምንም እንኳን የተገኘው የቅበላ ቦታ ለ4ቱ ክልሎች ይከፋፈላል ቢባልም በምን አግባብ እና መንገድ ተማሪዎቹ እንደሚለዩ እስካሁን በግልፅ የተብራራ ሆነ የታወቀ ነገር የለም።

@minesterofeducation
2025/06/30 19:23:21
Back to Top
HTML Embed Code: