Telegram Web Link
#በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “"ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነት "ክፍል ሦስት በሚል ርእስ በወጣትነት ዘመን የሚያጋጥሙ ፈተናዎች ፣ ታስነብባለች።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "# የኢትዮጵያ ድኖኳኖች ሲጨነቁ አየሁ" "በሚል ታስነብባለች ።
#የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “ወርኃ ጳጉሜን # ክፍል_፪ " በሚል ርእስ #“«ወርኃ ጳጕሜን»በተመለከተ ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠበትን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔት የ፬ቱ ጉባኤያት የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህርና የዝዋይ ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የቦርድ አባል የሆኑትን መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ #አትናቴዎስን ጋር የተደረገ ጥያቄና መልስ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፲ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
━━━━━༺✞༻━━━━
29🙏6
ማኅበረ ቅዱሳን ዜማና ኪነ ጥበባት ማእከል ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ጋር በመተባበር "ዜማ ወጥበብ" የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ አዘጋጀ

መተግበሪያው ማኅበሩ እስካሁን በተለያዩ የሕትመት ውጤቶች ለመላው ዓለም ምእመናን ሲያደርስ የነበረውን የመዝሙርና የኪነ ጥበባት ውጤቶችን በተሻለ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ዜማና ኪነ ጥበባት ማእከል አባላቱን በማስተባበር በ2017 ዓ.ም ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ጋር በመተባበር ሲሠራ ቆይቶ በመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአገልግሎት ውሏል።

ማእከሉ ይህን የስልክ መተግበሪያ (Mobile Application) በመላው ዓለም የሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን የማኅበሩ መዝሙራዊና ኪነ ጥበባዊ ሥራዎችን ማለትም የማኅበሩን የመዝሙር ጥራዞች፣ በተለያየ ጊዜያት የተዘጋጁ የመዝሙር ካሴቶች፣ የዜማ መሳሪያዎች መዝሙራት፣ የልዩ ልዩ ቋንቋ መዝሙራት፣ የኪነ ጥበብ ሥራዎችና የመዝሙራዊና ኪነ ጥበባዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ማሠልጠኛዎችን የያዘ ሲሆን ከዚህ ወር (መስከረም 2018 ዓ.ም) ጀምሮ ከፕላይ ሰቶር (Play store) ዜማ ወጥበብ ብሎ በመፈለግ ማውረድና መጠቀም ይቻላል።

ለማንኛውም ሐሳብና አስተያየት አፕሊኬሽኑ ላይ በተቀመጠው የአስተያየት መስጫ ወይም በተቀመጡት የኢሜይል አድራሻዎች ማድረስ ይቻላል።

አፕሊኬሽኑን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ👇👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eotcmk.zemawetibebzmk
93👏18🙏9👍6🥰3
መርሐግብሩን - Join Zoom Meeting
meeting ID: 849 6710 2865
‎Passcode: 825584
‎ወይም ደግሞ 
https://www.tg-me.com/+e_alNr2w1RpmNDY0 ቴሌግራም ላይ ይከታተሉ።
27🙏7👏6👍1🤔1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ማኅበረ ቅዱሳን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሥነ-ልቡና የተረዱ፣ ብቁና በቂ ኦርቶዶክሳውያን መምህራንን ለማፍራት ለመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅትና ኅትመት፣ እንዲሁም የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የመምህራን ሥልጠና መስጠት የሚያስችል የሥልጠና ማእከል ማቋቋምና ሌሎችም አገልግሎቶች ተግባራዊ ለማድረግ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ የዕጣ ትኬት አዘጋጅቶ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በሥርጭት ላይ መሆኑ ማኅበሩ ባሉት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ሲገለጽ ቆይቷል፡፡
እርስዎም በአንድ በኩል ዕድሎዎን እየሞከሩ ማኅበረ ቅዱሳን ዘመኑን የዋጀ ንቁ ኦርቶዶክሳዊ ትውልድ ለማፍራት በሚያደርገው ጥረት ውስጥ ፕሮጀክቶቹን ለመደገፍ የድርሻዎን ይወጡ፡፡
93🙏14👍5🤔2
መርሐግብሩን ለመከታተል- Join Zoom Meeting
meeting ID: 849 6710 2865
‎Passcode: 825584
‎ወይም ደግሞ
https://www.tg-me.com/+e_alNr2w1RpmNDY0 ቴሌግራም ላይ ይከታተሉ።
20🙏6👏1
በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት በዳዉሮ ሀገረ ስብከት ዛባ ጋዞ ወረዳ የተገነባው የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በተገኙበት መመረቁ ተገለጸ

ጥቅምት ፫/፳፻፲፰ ዓ.ም
    
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት  ቤቶች ማዳራጃ መምሪያ ማኀበረ ቅዱሳን ዋናዉ ማእከል በዳዉሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት በዛባ ጋዞ ወረዳ ቤተ ክህነት በዱጋ ያስገነባዉን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን አስመረቋል፡፡

የዳዉሮ፤ ኮንታ፣ ካምባታ፣ ጣምባሮ እና ሀላባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በመስከረም 30/2018 ዓ.ም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ባርከዉ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበረ ክብሩ መግባቱን የተገለጸ ሲሆን  ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም ብፁዕነታቸዉን ጨምሮ የዳዉሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ክንፈ ገብርኤል፣ የየመምሪያዉ ኃላፊዎች፣ የዛባ ጋዞ ወረዳ ምክትል አስተዳዳር፣ እንዲሁም የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የወረዳዉ የየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ካህናት አባቶች፣ ከሁሉም ወረዳ ማእከላት የተሳተፉ ምእመናን፣ የዋናዉ ማእከል ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ምእመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡

የዳዉሮ፤ ኮንታ፣ ካምባታ፣ ጣምባሮ እና ሀላባ አህጉረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ እና የቅዱስ ስኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በንግግራቸዉ ”ይህን የመሰለ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ተገንብቶ እንዲህ ደምቀን፣ በዝተን በክብር ላቆመን እግዚአብሔር ምስጋና አቅርበዉ″ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
22👏3🙏1
ብጹዕ አቡነ ጢሞቴዎስ  አክለውም ይህን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ለገነባዉ ማኀበረ ቅዱሳን እና የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ግለሰብ ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያን ይዞታ ጋር ተያይዞ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ለተባበሩ ለወረዳ መንግሥት፣ ለዱጋ ማዘጋጃዊ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት እና የአካባቢን ሕዝብ በማመስገን አያይዘውም በሀገር ስብከቱ ያሉ ችግሮችን በመፍታት እንደዚህ በቅንጅት መሥራት የሚያስፈልግ በመሆኑ የማኀበረ ቅዱሳን ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ይህ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሕዝቡ እንዲገለገልበት፣ እንዲባረክበት፣ እግዚአብሔር እንዲከብርበት፣ለአካባቢ ሰላም፣ በረከት እንዲመጣ የሚፀለይበት በመሆኑ ሕዝበ ምእመናን መበርታት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

የዛባ ጋዞ ወረዳ ምክትል አስተዳዳር አቶ ተመስገን ሳዊሮ የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሀገር ባለዉለታ በመሆኗ እንደዚህ ዓይነት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በወረዳችን መገንባቱ ለአካባቢ በረከት በመሆኑ የወረዳዉ መንግሥት ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን መሆኑን በንግግራቸዉ ገልጸዋል፡፡

አቶ ዳዊት ዳና የወረዳዉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸዉ ቤተ ክርስቲያኒቷ የሰላም፣ የአንድነት እና የፍቅር ተመሳሌት መሆኗን በማዉሳት በማንኛዉም ጉዳዮች ድጋፋቸዉ እንደማይለይ በማረጋገጥ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማእከል ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል ኃላፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ነጋ በበኩላቸው ይህ ቤተ ክርስቲያን የአካባቢ ነባራዊ ሁኔታውን መሠረት በማድረግ በቀረበው ጥናት ማእከሉ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እንዲገነባ በመፍቀድ በየካቲት ወር 21/2017 ዓ.ም ግንባታው በይፋ ተጀምሮ በነሐሴ 2017 ዓ.ም በስድስት ወራት ውስጥ የህንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለምረቃ መብቃቱን ገልጸዋል፡፡

የግንባታው አጠቃላይ ወጪ 6.4 ሚሊዮን ብር የፈጀ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ይህ ግንባታን ከጅምር እስከ ፍጻሜ ድረስ አባታዊ ስምሪት በመስጠት ክትትልና ድጋፍ ላደረጉ ለብጹዕነታቸዉ፣ ለዳዉሮ ሀገረ ስብከት፣ ለማኀበረ ቅዱሳን ታርጫ ማእከል፣ ለወረዳ መንግሥት፣ ግንባታዉን ላካሄደ ኮንትራከተር እና ለአካባቢው ምእመን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በስተመጨረሻም በሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ በዳዉሮ ሀገረ ስብከት፣ በማኀበረ ቅዱሳን ታርጫ ማእከል እና በወረዳ ቤተ ክህነት የተዘጋጀዉን የእዉቅና ሰርተፍኬት የተሰጠ ሲሆን በዕለቱ ስድሳ/60/ አዳዲስ አማኒያን ተጠምቀዉ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደተቀላቀሉ ተጠቁሟል፡፡
44👏13🙏3
፵፬ኛው የሰበካ ጉባኤ ዓለም አቀፍ መደበኛ ስብሰባ በቅዱስ ፓትርያሪኩ ቡራኬ መከፈቱ ተገለጸ

በጉባኤው ከመላው ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት ተወካዮች እየተሳተፉበት ይገኛል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው
23🙏3
"ያለምንም ደመወዝ በራሳቸው ዓቅም በግብርና እየተዳደሩ ቤተ ክርስቲያንን በጥሩ ሰብእና በንጽሕና እና በቅድስና ጠብቀው ያስረከቡ እልፍ አእላፍ አበው እንዳልነበሯት ዛሬ የተሻለ ኑሮና ደመወዝ እያገኘን እግዚአብሔርን እንደቀኖናው በጥንቃቄ ማገልገል አቅቶናል" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ


ጥቅምት ፬/፳፻፲፰ ዓ.ም

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርከ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
የአዲስ አበባና ሐድያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የየመምሪያውና የየድርጅቱ ኃላፊዎች ፣
ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የመጣችሁ የየሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጆችና የየክፍሉ ተወካዮች፣
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኃላፊዎች፣
የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ተወካዮች
የምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች፣
በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ ጉባኤ የተገኛችሁ ክቡራና ክቡራት
እግዚአብሔር አምላካችን ዓመቱን ጠብቆ በከፍተኛ ጉጉት ለምንጠብቀው 44ኛው የሰበካ ጉባኤ አጠቃላይ መንፈሳዊ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ስላደረሰን ክብርና ምስጋና ለእርሱ እናቀርባለን፡፡ እናንተንም እንኳን በደኅና መጣችሁ እንላለን፡፡
20👏2👍1🙏1
2025/10/16 10:22:37
Back to Top
HTML Embed Code: