Telegram Web Link
በዓለ ቅዱስ ሚካኤል
የቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን የመላእክት ሁሉ አለቃ የሆነ የቅዱስ ሚካኤል በዓልን ሰኔ ፲፪ ቀን በየዓመቱ እንድናደርግ አዘውናል፡፡ ይህም በመጀመሪያ እስክንድርያ በምትባል ከተማ አክላወ ባጥራ የተባለች ንግሥት የንጉሥ በጥሊሞስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ባሠራችው ታላቅ ምኵራብ በየዓመቱ ሰኔ በባተ በዐሥራ ሁለት ቀን በምኵራቡ ሕዝቡ ተሰብስቦ ታላቅ ክብረ በዓል ለረጅም ዓመት ሲያደረጉ ከኖሩ በኋላ አባ እለእስክንድሮስ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ፣ ጻድቅ ቆስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ የክርስትና ሃይማኖት አስፋፍተው ጣዖቱ እንዲሰበር አዝዞ፣ ጣዖቱን ያከብሩ የነበሩትን ሰዎች መክሮና ገሥጾ ጣዖቱን ያጠፋበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡
ምኵራቡንም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አድርገው ሰይመው በዚያ ዕለት ክብረ በዓል አደረጉ፤ እስላሞችም እስከ ነጉሡበት ዘመን ኑራ ከዚያ በኋላ ቢያፈርሱትም ያ በዓል ተሠራ፤ እስከ ዛሬም ጸንቶ ይኖራል፡፡
የከበረ የመልአክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ተአምራቱ ብዙ ናቸው፡፡ በከበረች በሰኔ ዐሥራ ሁለት ቀን የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ምሥራች የቀየረ እና ቅድስት አፎሚያን ከሰይጣን እጅ ያስጣለ ይህ መልአክ ነው፡፡ (ሙሉ ታሪኮችን መጽሐፈ ስንክሳር ዘሰኔ ፲፪ ላይ ያግኙ) በእኛ ሕይወት ውስጥም ድንቅ ታሪክ የሚያደርግ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነውና የእርሱን ጸሎት፣ ምልጃና ተረዳኢነት ተስፋ ልናደርግ ይገባል፡፡
የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጸሎት፣ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ ከበዓሉ በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ አሜን!
Feast of Saint Michael
Our forefather saints, ordered us to celebrate the festivity of Archangel Saint Michael on Sene 12 every year. This was primarily due to the eradication of an Idol in Alexandria a great temple which Queen Cleopatra, the daughter of Ptolemy, King of Egypt, had built in the name of the star Zuhal. (Venus), they use to celebrate a festival in its honor on the twelfth day of the month of Sane.
However, at the reign of the righteous Emperor Constantine whilst the appointment of Abba Alexander Archbishop of Alexandria, the True Christian Faith spread abroad and the King ordered the break of the star Zuhal. He then built the church of Archangel Saint Michael instead of it on the temple. “That temple became known as the “Church of Caesarea,” and it continued to stand until the Muslims reigned in Egypt. But then they destroyed it.
The miraculous of this angel of God is numerous. Then again on Sene 12, Saint Michael saved a boy named “Bahiran,” from a death sentence and also Saint Euphemia from the hands of the devil, Satan. (you can find the whole stories on Ethiopian Synaxarium of Sene 12) This angel might also do many miraculous in our lives and so we shall believe in his prayer, intercession and mediation.
May Archangel Saint Michael’s prayer, intercession and mediation be with us; Amen!
የግቢ ጉባኤያት ደረጃ ሁለት ተተኪ አመራር ሥልጠና መሰጠቱ ተጠቆመ

ሰኔ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም

የሰሜን ምእራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከ86 በላይ ከባሕር ዳር፣ ከደብረ ታቦር፣ ከእንጅባራ ማእከል ሥር ካሉ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የደረጃ 2 ተተኪ አመራር ሥልጠናዎችን ከሰኔ 01 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሰባት ቀናት ሲሰጥ መቆየቱ ተጠቁሟል።

የሥልጠናው ዓላማ በቤተ ክርስቲያን መደበኛ ወዋቅር ገብተዉ ዘመኑ የሚጠይቀዉን አገልግሎት መፈጸም የሚችሉና ሐዋርያዊ አገልግሎቷን የሚያስቀጥሉ ብቁ አገልጋዮችን በልዩነት ከግቢ ጉባኤያት ማፍራት የሚቻልበትን መንገድ ለመጠቆም፤ በእምነት እና በሥነ ምግባር በአርዓያነት የሚኖሩ፣ በተለያዩ በጎ በሆኑ ማኅበረሰባዊ ጉዳዮች ላይ ቀዳሚ ተሳታፊ በመሆን የቅድስት ቤተክርስቲያንን ተልዕኮ የሚያስፈጽሙ ብቁ አገልጋይችን ከግቢ ጉባኤያት በማብቃት ማዉጣት እንደሚገባ ለማስገንዘብ እንደሆነ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያን በሀገር እና በዓለም አቀፍ በሚኖራት ተሳትፎ የሚወጡ ድንጋጌዎች፣ህጎች እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ከአስተምህሮዋ ጋር ለመጣጣማቸዉ እና ለምእመኗ መንፈሳዊ አኗኗር የሚኖራቸዉን አዎንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖዎች በመመርመር በተሻለ እሳቤ ሙያዊ ሓላፊነቱን መወጣት የሚችል፣ እንዲሁም ለመንፈሳዊ አገልግሎቷ መፋጠን የሚረዱ አዳዲስ የፈጠራ ሥራ የሚሰሩ ምእመናንን ከግቢ ጉባኤያት ማፍራት እንደሚገባ እና መንገዶችን ለማመላከት እንደሆነ ተገልጿል።
የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የመሪነት ሚና፣ ኦርቶዶክሳዊነት ሕይወቱና ክህሎቱ፣ የአኃትና ምሥራቅ አብያተክርስቲያናት ተሞክሮ እና የወጣቶች አገልግሎት፣የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት፣ የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን መሪ አገልጋዮች የሕይወት ተሞክሮ፣ የቡድን መሪነት፣ተግባቦት የሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ተዳሰውበታል።

ስለ ነገረ ቤተ ክርስቲያን በቂ ዕውቀት፣ የተሻለ ክርስቲያናዊ አኗኗር፤ ተልዕኮ እና ዓላማ ያለዉ ሰዉ መሆን፤ የላቀ የተግባቦትና ግንኙነት ክህሎት፤ ከተለያዩ አካላት ጋር ጥሩ ሙያዊ ግንኙነት፤ የፈጠራ እና የንባብ ክህሎት፤ የቡድን ምሥረታ ፣ የማስተባበር ና የግጭት አፈታት ክህሎት፤ የተሻለ የመረጃና የዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ችሎታ፤ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊና መጻኢ ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤ፤ የተለያዩ አርዓያነት ባሏቸዉ ማኅበራዊ ተቋማት ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ፍላጎት እና አቅም እና የመሳሰሉት፡፡ በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ የተሻለ እዉቀት ለመግኘት የሚረዷቸዉን መንገዶች የለዩ እና ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸዉ፤ ጥናት እና ምርምር አሰራር ላይ የተሻለ ግንዛቤ እና ክህሎት ከሠልጣኞች ይጠበቃል ተብሏል።
የማኅበራዊ ድጋፍ ጉባኤ ጥሪ
+++
ማኅበረ ቅዱሳን በሀገራችን ኢትዮጵያ በማኅበራዊ ቀውሶች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እያሰባሰበ በማድረስ ላይ ይገኛል።
እርስዎም፡- ድጋፍ በማድረግ ኃላፊነትዎን እንዲወጡ ተጋብዘዋል።
በዙም ለሚካሄድ የድጋፍ መርሐ ግብር ለመሳተፍ
• Date: June 21st, 2025
• Time: 21 - 22:30 CET, 20 - 21:30 UK, 22 - 23 :30 Helsinki
ድጋፍ ለማድረግም፡-
1. በአውሮፓ ለምትገኙ -
• Mahibere Kidusan in Europa e.V.
• IBAN: DE14 3704 0044 0307 8037 00
• BIC: COBADEFFXXX
• Reason: Code 007 (Social support)
Phone for What Sapp/Telegram/Imo: +421950741387
2. በዩኬ ለምትገኙ ፡-
Mahibere Kidusan in UK
Banking: Nat West
Sort code 601251
Acco. No: 36425591
• Reason: Code 007 (Social support)
3. በስዊድን ለምትገኙ ፡-
Swish Number
123 054 28 29
Market Name
Mahibere Kidusan I Sverige
• Reason: Code 007 (Social support) Join Zoom Meeting 👉👉👉
https://us06web.zoom.us/j/83102898301?pwd=Zv3iBrniV5cszclCqONqYrE0C4kI4N.1
Meeting ID: 831 0289 8301
Passcode: 121921
ኦርቶዳካሳዊ እሳቤ በማጎልበት ዓላማ ያለው ሰው  ማፍራት እንደሚገባ ተገለጸ

ሰኔ ፲፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን ደሴ ማእከል ለግቢ ጉባኤያት የደረጃ ሁለት ተተኪ አመራር ሥልጠና እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ሥልጠናው ለተከታታይ 7 ቀናት የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የነበራት፣ ያላትና ሊኖራት የሚገባ የመሪነት ሚና ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየተሰጠ ያለው ሥልጠናው የሴኩላሪዝም ተጽእኖ ከኦርቶዳካሳዊነት እሳቤና ኑሮ አንጻር በሥልጠናው  የተዳሰሰ እንደሆነም ተመላክቷል።

የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት ፣ የአኃትና የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ተሞክሮ ኦርቶዶክሳዊ ሕይወትና ክህሎት በሥልጠናው ትኩረት የተደረገባቸው ርእሰ ጉዳዮች ሲሆኑ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን በማጎልበት ዓላማ ያለው ሰው  ማፍራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የቤተክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳዮች  ፣ የቡድን መሪነት እንዲሁም ማኅበራዊ አገልግሎት በሥልጠናው ትኩረት  የተደረገባቸው ጉዳዮች እንደሆነም ተገልጿል።
#የሰኔ ወር ሐመር #መጽሔት በሁሉም የማኅበረ ቅዱሳን ሱቆች በሥርጭት ላይ ትገኛለች ።!
#የሰኔ ወር ሐመር #መጽሔት ሥርጭት ላይ መሆኗን ያውቃሉ ?? #በውስጧ ምን ይዛለች ? ሙሉውን #ሐመሯን መጽሔቷ በቅርብ ባሉ ሱቆች ገዝተው ያንብቡ ያስነብቡ!

የሰኔ ወር ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን "#ሁሉም የክርስቶስን እውነት #በቋንቋቸው ይሰሙ ዘንድ እንትጋ ››
.#ዐውደ ስብከት ሥር” #የንስሓ አባትና ልጅ ግንኙነት ከየት ወደ የት?
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ክፍል _፪

#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “# የቅዱሳን ኅብረት
"#ማኅበራዊ በክርስትና _#ኦርቶዶክሳውያን በማኅበረሰብ ውስጥ ቦታችን የት ነው _ክፍል _፪"
#በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የደብረ ብርሃን ደብረ ገነት ቅዱስ ዑራኤልና አኔቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን _ክፍል ፪"

#በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “ "ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ህልውና #ምንጩን ማጥራትና መጠበቅ "
ክፍል _፪
#በኪነ ጥበብ ዐምድ #ከፍቅረኛህ ጋር ታረቅ " በሚል ታስነብባለች ።
#የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “#ቤዛና ቤዛነትን” በተመለከተ ክፍል _፪ ላይ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ አዘጋጅተናል።
ሐመር መጽሔት #፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፮ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

Magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
በደቡብ ማእከላት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት በወላይታ ሀገረስብከት በሚገኘው ካህናት ማሠልጠኛ  ለስድስት  ተከታታይ ቀናት  ሲሰጥ የቆየው የደረጃ ሁለት ተተኪ አመራር ሥልጠና  መጠናቀቁ ተገለጸ።

ሰኔ ፲፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን ደቡብ ማእከላት ማስተባበሪያ አዘጋጅነት ከተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ለተዉጣጡ ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ለስድስት  ተከታታይ ቀናት  እየተሰጠ የቆየው የደረጃ ሁለት ተተኪ አመራር   ሥልጠናና ውይይት በዛሬው ዕለት ብፁዕ  አቡነ ይስሐቅ የወላይታ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ በተገኙበት  የማጠቃለያ መርሐ ግብር በርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት  ገዳም መከናወኑ ተገልጿል ።

ሠልጣኞች  ከአርባ ምንጭ ፣ ከወላይታ ፣ ከጂንካ  ፣ከሆሳዕና ማእከላት የተወጣጡ ቁጥራቸው ከ50  በላይ እንደሆኑ ተጠቁሟል ።

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የመሪነት ሚና ትላንት፣ ዛሬና ነገ ፣ ኦርቶዶክሳዊነት ሕይወቱና ክህሎቱ ፣የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ተሞክሮ፣ ሴኩላሪዝም ከኦርቶዶክስ እሳቤና ኑሮ አንጻርና ሌሎች ሥልጠናዎች እንደሰጠም ተመላክቷል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው  በማጠቃለያ መርሐግብር የወላይታ ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ  " የተካሄደው ሥልጠና እጅግ ጠቃሚ የሆነና ሊበረታታ የሚገባው መሆኑን ጠቅሰው   " የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው በማለት ሠልጣኞች በተሰጠው ሥልጠና  እግዚአብሔርን በመፍራት፣ ሕይወታቸውን በመምራት፣   መክሊታቸውን በማትረፍ በሚሄዱበት ሁሉ ቅድስት  ቤተ ክርስቲያንን፣ ወላጆቻቸውንና አገራቸውን እንዲያገለግሉ የአደራ መልእክትና አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።
2025/07/01 01:57:17
Back to Top
HTML Embed Code: