በማኅበረ ቅዱሳን መቱ ማእከል በሁለት ግቢ ጉባኤያት ያስተማራቸውን ተማሪዎች ማስመረቁ ተገለጸ።
ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን መቱ ማእከል በመቱ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ እና በጥምር ግቢ ጉባኤ ሲያስተምራቸው የቆዩ ከ500 በላይ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በቦቶ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ማስመረቁ ተገልጿል።
በማኅበረ ቅዱሳን የመቱ ማእከል ሰብሳቢ መ/ር ጌትነት ሰይፉ እንደገለጹት ተመራቂዎች ከግቢ ወጥተው ወደ ተለያዩ ቦታዎች ሲሄዱ ቤተ ክርስቲያን የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣ በሚችሉት ሁሉ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ማገዝ ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም ተመራቂዎች በአባቶች ቡራኬና የአደራ መስቀል ተቀብለዋል።

ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን መርሐ ግብር መከናወኑ ተገለጸ
ሰኔ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት አዘጋጅነት ዓለም ዓቀፍ የግቢ ጉባኤ ምሩቃን መርሐ ግብር በትናትናው ዕለት ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም መካሄዱ ተገልጿል።
በጉባኤው ከተለያዩ ግቢ ጉባኤያት የተዉጣጡ ከ300 በላይ ተሳታፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የመርሐ ግብሩ ዓላማ የሚመረቁ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ተልእኮ ተኮር አገልግሎት ይዘው የሚሠሩበትን ዕድል ማሳደግና ከግቢ ጉባኤ በኃላ ወደ ቤተክርስቲያን መዋቅር ገብተው እንዲያገለግሉ ለማስቻል የተዘጋጀ እንደሆነ ተጠቁሟል።
በዕለቱ የልምድ ልውውጥ፣ መዝሙር የተከናወነ ሲሆን ትምህርተ ወንጌል በመጋቤ ሐዲስ መምህር እንዳልካቸው መሰጠቱ ተመላክቷል።
በመርሐ ግብሩ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ተገኝተው ያላቸውን ልምድ እና ተሞክሯቸውን ለወጣቶች ያጋሩ ሲሆን “ከልጅነቴ ጀምሮ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በፈሪሐ እግዚአብሔር ያደግሁ መሆኔ ለስኬቴ መሰረት ነው ብለዋል።
የሁለት ኦሎምፒክ የድል ወርቆቼን የሰጠሁት ለእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ነው ያሉት አትሌቱ በየወሩም እንደማይቀሩና እሷ ለእኔ ብዙ ነገሬ ናት ብለዋል።
እኔ በሰከንድ ሚሊዮኖችን እንዳገኘሁ ሁሉ በሰከንድም ብዙ ሚሊዮን የሚያወጣ ሀብት አጥቻለሁ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር በመሆኔ ሁሌም አሸንፋለሁ ሲሉም ገልጸዋል።
ሻለቃ ኃይሌ በመርሐ ግብሩ ወጣቶች እግዚአብሔርን በማመን የትኛውንም መሰናክል በቀላሉ ማለፍ፣ጠንካራ የማሸነፍ ስሜት ሊኖራቸው እንደሚገባ ከልምዳቸው ተነስተው በመግለጽ በተለይ ከሥራ ፈጠራ እና ከባሕል አንጻር ጽናትና ብርታትን ለማግኘት ከፊት ይልቅ አሁን መጠንከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

አትሌቱ አክለውም በተሰማራችሁበት የሥራ መስክ ታማኝ መሆንና ሥነ ምግባር መላበስ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በመጨረሻም የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ማእከልን ጎብኝተዋል።
በመጨረሻም የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ማእከልን ጎብኝተዋል።
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ግቢ_ጉባኤ ያስተማራቸዉን ተማሪዎች ብፁዕ አቡነ እንጦንስ በተገኙበት አስመረቀ
ሰኔ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ለአራትና አምስት አመታት ያስተማራቸዉን 225 ተማሪዎችን የምዕራብ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ በተገኙበት አስመርቋል።
ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ቃለ እግዚአብሔርን መሰረት በማድረግ ፣ ህገ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ ቤተ ክርስቲያንንና ሀገርን ማገልገል ይጠበቅባችኋል በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
አክለውም አገልግሎታችሁም ሁሉ በፍቅር መሆን አለበት ያሉ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚገኙ ወጣቶች ላይ ሥራ እየሠራ በመገኘቱም አመስግነዋል።
የጭሮ ማእከል ሰብሳቢ ዲ/ን ዳንኤል ሞገስ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገኙ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እደሚገኝ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ለተመራቂ ተማሪዎች የአደራ መስቀል የሰጡ ሲሆን ከተመራቂዎች መካከል ከፍተኛ ነጥብ በማምጣት በሜዳሊያ ለተመረቁ አራት ተማሪዎች ዕዉቅናና ሽልማት ተበርክቷል።