ደብረ ማርቆስ ማእከል በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
ሰኔ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ማርቆስ ማእከል በመደበኛውና በማታው መርሐ ግብር በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።
የማእከሉ ሰብሳቢ ድረስ እንዳላማው ተመራቂ ተማሪዎችን “የድካማችሁን ፍሬ ለማየት ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ያሉ ሲሆን የማኅበሩ ርእይ ቤተ ክርስቲያን የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት እንደመሆኑ መጠን እናንተም የሚጠበቅባችሁን በማድረግ፣ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር በመግባት፣ በጉልበታችሁ፣ በገንዘባችሁና በዕውቀታችሁ ማገልገል እንዲሁም ከማኅበሩ ጋር በጋራ መሥራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ ተማሪዎች በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ ሆነው ለመውጣት በግቢ ቆይታቸው የተሻለ ትጋት ለነበራቸውና በዓለማዊ ትምህርታቸው የሜዳሊያ ተሸላሚ ለሆኑ የግቢ ጉባኤ ፍሬዎች በምሥራቅ ጎጃም ሃገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ መልአከ ምሕረት መ/ር ይትባረክ ክንዴና በሃገረ ስብከቱ ሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ፍቅረሥላሴ አማካኝነት ከግቢ ጉባኤው ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመጨረሻም ተመራቂ ተማሪዎች "ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽ ምላሴ ከትናጋየ ጋር ትጣበቅ" ብለው ቃል በመግባት የአደራ መስቀል ተቀብለዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን እንጅባራ ማእከል 496 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን አስመረቀ።
ሰኔ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን እንጅባራ ማእከል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን እንዲሁም በተለያዩ ኮሌጆች በጥምር ግቢ ጉባኤ ከዓለማዊ ትምህርታቸዉ ጎን ለጎን የቤተክርስቲያን ትምህርት ሲያስተምራቸዉ የነበሩ 496 ተማሪዎችን ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም አስመርቋል።
ከተመራቂዎች መካከል 11 ተማሪዎች ከፍተኛ ዉጤት በማምጣት 10 የሜዳልያና 1 የዋንጫ ተሽላሚ እንደሚገኙ ተጠቁሟል።
በመርሐ ግብሩ ትምህርተ ወንጌል በመምህራን፣ ወረብና የበገና መዝሙር በተመራቂ ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመጨረሻም የእንጅባራ ማእከል ሰበሳቢ በሆኑት በአቶ ይበልጣል አበጀ የማኅበረ ቅዱሳን መልእክት የተላለፈ ሲሆን ለተመራቂ ተማሪዎች የአደራ መስቀል በየኔታ ፍሬዉ ስሜነህ ተሰጥቷል።

ደብረ ታቦር ማእከል 106 የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን ማስመረቁ ተገለጸ፡፡
ሰኔ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ታቦር ማእከል ከ4 እስከ 5 ዓመት ሲያስተምራቸው የነበሩ 106 የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ማስመረቁ ተገልጿል።
በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ታቦር ማእከል ሰብሳቢ የሆኑት ዲ/ን ዶ/ር ለማ ጉልላት እንደገለጹት ጠቢቡ ሰሎሞን በተግሣጹ ‘’በለሱን የጠበቀ ፍሬውን ይበላል’’ እንዳለ ከብዙ የልፋት ዓመታት በኋላ የድካማችሁን ፍሬ ላያችሁበት ለዚህች ዕለት ልዑል እግዚአብሔር እንኳን በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
ሰብሳቢው አክለውም ‘’ጢሞቴዎስ ሆይ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ‘’ ብሎ አባቱ ቅዱስ ጳውሎስ የመከረውን ምክር ተቀብሎ ለአደራ እንደበቃው እንደ ጢሞቴዎስ እናንተም በዚህ የመከራ ወጀብ መካከል የወላጆቻችሁን ምክር፣ የአገራችሁንና የቤተ ክርስቲያናችሁን አደራ ጠብቃችሁ ለዚህ የምረቃ ክብር በመብቃታችሁ እግዚአብሔርንና እርሱ ያከበራቸውን ሁሉ ልናመሰግን ይገባናል በማለት ተናግረዋል።
አያይዘው ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት መልእክት በቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት መዋቅራት ማለትም በሰበካ ጉባኤ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት፣ በማኅበረ ቅዱሳን መዋቅር በመግባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በገንዘባችሁ፣ በጉልበታችሁ እና በዕውቀታችሁ በማገልገል፣ በእውነተኛ ትምህርቷ ጸንታችሁ በመኖር በዘር እና በቋንቋ ለተፈተኑ የቤተ ክርስቲያን አካላት አርአያ እንድትሆኑ፣ በመንፈሳዊ ሕይወታችሁ ዕድገት ለማሳየት እንድትተጉ እና ችግሮቿን ለመፍታት ከጎኗ እንድትሆኑ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም የአደራ መስቀል በመስጠት መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

ሐረር ማእከል በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሐረር ጤና እና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ የህክምናና የጤና ተማሪዎች ማስመረቁ ተጠቆመ
ሰኔ 15/2017 ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ሥር ከሚገኙ አምስት ግቢ ጉባኤያት መካከል አንዱ የሆነው የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በሐረር መካነ ሥላሴ ካቴድራል ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም አስመርቋል።
በምርቃ መርሐ ግብሩ የሐረር መካነ ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ፣ ካህናት አባቶች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል አባላት፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል አባላት፣ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ተካሂዷል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል ተመራቂ ተማሪዎች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅሯን ጠብቀው እንዲያገለግሉ ፣ በኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ አገልግሎት ንቁ ተሳታፊ ሆነው ያስተማራቸውን ማኅበረሰብ በእኩልነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉ መልእክት አስተላልፏል።
በካቴድራሉ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ጥበቡ የአደራ መስቀል ለተማራቂ ተማሪዎች ያበረከቱ ሲሆን በግቢ ጉባኤውና በክፍላት ሲያገለግሉ ለቆዩ የስጦታ መርሐ ግብር ተከናውኗል::