ሐረር ማእከል በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሐረር ጤና እና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ የህክምናና የጤና ተማሪዎች ማስመረቁ ተጠቆመ
ሰኔ 15/2017 ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ሥር ከሚገኙ አምስት ግቢ ጉባኤያት መካከል አንዱ የሆነው የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በሐረር መካነ ሥላሴ ካቴድራል ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም አስመርቋል።
በምርቃ መርሐ ግብሩ የሐረር መካነ ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ፣ ካህናት አባቶች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል አባላት፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል አባላት፣ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ተካሂዷል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል ተመራቂ ተማሪዎች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅሯን ጠብቀው እንዲያገለግሉ ፣ በኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ አገልግሎት ንቁ ተሳታፊ ሆነው ያስተማራቸውን ማኅበረሰብ በእኩልነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉ መልእክት አስተላልፏል።
በካቴድራሉ አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ጥበቡ የአደራ መስቀል ለተማራቂ ተማሪዎች ያበረከቱ ሲሆን በግቢ ጉባኤውና በክፍላት ሲያገለግሉ ለቆዩ የስጦታ መርሐ ግብር ተከናውኗል::

በማኅበረ ቅዱሳን የአሶሳ ማእከል 574 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን ማስመረቁ ተጠቆመ
ሰኔ ፲፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን አሶሳማእከል በአሶሳ ዩንቨርስቲና በአሶሳ ከተማ መንግስት ና ግል ኮሌጆች በመደበኛ ግቢ ጉባኤያት ከዓለማዊ ትምህርታቸዉ ጎን ለጎን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲያስተምራቸዉ የነበሩ 574 ተማሪዎችን ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም አስመርቋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ትምህርተ ወንጌል በመምህራን እና ወረብ በተመራቂ ተማሪዎች ቀርቦ የአደራ መስቀል ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

ሀዋሳ ማእከል በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ፣ ግብርና ኮሌጅና ሪፈራል ግቢ ሲያስተምራቸው የነበሩ 250 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡
ሰኔ ፲፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳ ሀዋሳ ማእከል በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ፣ ግብርና ኮሌጅና ሪፈራል ግቢ ሲያስተምራቸው የነበሩ 250 ተማሪዎችን ሀዋሳ ደብረ ምጥማቅ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስመርቋል።
በማኅበ ቅዱሳን ደቡብ ማእከላት ማስተባበርያ ጽ/ቤት ኃላፊ ቀሲስ እንጅነር አሰፋ ቦረና እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና አግኝቶ ከተመሠረተ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በኀላፊነት የተሰጡትን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን በግቢ ጉባኤያት የማስተባበር፣ የማስተማር አገልግሎቱን ትናንትም ዛሬም እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
“ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት” የሚለውን የማኅበሩን ርእይ እውን ለማድረግ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳውያን ተመራቂ ተማሪዎች እንዲመጣ የፈለገው ውጤት በእናንተ ሕይወት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግና የቤተ ክርስቲያንን ችግሮች ለመፍታት የመፍትሔው አካል ከመሆን አንጻር ከምሩቃን የምንጠብቀው አደራ ቀላል የሚባል አይደለም በማለት ተመራቂዎች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል።
የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ስብሐት ቀሲስ ኪነ ጥበብ ያለው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም በአብነት እና በአስኳላው ትምህርት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በከሚሴ ሀገረ ስብከት በከሚሴ ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ሰበካ ጉባኤ የሚመራ ኦርቶዶክሳዊ የምክክር ተቋም ተቋቋመ ።
ሰኔ ፲፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ማኅበራዊ ቀውሶች የሚፈጥሩትን የሥነ ልቦናና አእምሯዊ ችግር ለማቃለል በዘርፉ የሚሠሩ አመካካሪዎች ለማፍራትና ተቋማትን ለማስፋፋት ሰፊ ሥልታዊ ተግባራትን በሁሉም ማእከላት እየፈጸመ ይገኛል።
በዚሁ መሠረት በማኅበረ ቅዱሳን ከሚሴ ማእከል አስተባባሪነት በሁሉም ወረዳ ማእከላት ከሀገረ ስብከቱና ከሁለቱም ወረዳ ቤተ ክህነት ከከሚሴ ፣ ባቲና ጨፋ ሮቢት ወረዳ ማእከላት ጋር ሲሰጥ የነበረው ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን በሁሉም ዘርፍ የማጠናከርና የማማከር አገልግሎትን ሊያሰፋ የሚያስችል የአመካካሪነት ክህሎት፣ ትምህርተ አበ ነፍስ፣ ኦርቶዶክሳዊ የልጆች አስተዳደግና ጋብቻ፣ ሱስን ለመከላከል የኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ መፍትሔዎች፣ የምክክር አገልግሎት በሰፊው ሥልጠና ከተሰጠ በኋላ ተቋሙ የተቋቋመ መሆኑ ተገልጿል።
በተቋም ምሥረታውም ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ገነት ደጀን ተስፋዬ፣ የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች፣ የሁለቱም ወረዳ ቤተ ክህነት ሊቃነ ካህናትና ሠራተኞች፣ የከሚሴ ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና የሰበካ ጉባኤ አባላት፣ የማኅበረ ቅዱሳን ከሚሴ ወረዳ ማእከል ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም ሥልጠናውን ሲያሳልጡ የነበሩ አሠልጣኞች ተገኝተዋል።
ይህን ተቋም ሊያስቀጥሉ የሚችሉ ከሁሉም ባለሙያ ስብጥር ያላቸው አካላት የተመረጡ ሲሆን የተመረጡት አካላትም ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና ከሁሉም ተቋማት ጋር በመናበብ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ሥራ መሥራት እንዳለባቸው አጽንኦት ተሰጥቶበታል ።

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አሰኪያጅ መልአከ ገነት ደጀን ተስፋዬ ቀጣዩን ትውልድ በምን መንገድ ነው መምራት ያለብን ዝም ብሎ በማየትና በመመልከት አንድነትን ያወቀ፣ በእውቀት የመጠቀ፣ በአዕምሮ የተራቀቀ፣ እውቀትና ክህሎት፤ እምነትና ምግባርን አጣምሮ የያዘ ትውልድ መፍጠር ለሀገርም ሆነ ለቤተክርስቲያን ወሳኝ መሆኑን አውቆና ተረድቶ ለዚህም ደግሞ ሳይሰላቹ በድካም ውስጥም ሆኖም ቢሆን መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በመጨረሻም ሥልጠናውን በትጋትና በቅንነት ሲሰጡ ለነበሩ አሠልጣኞችም የምሥጋናና እውቅና ምሥክር ወረቀት ተሰጥቷል ።