ዱራሜ ማእከል 19ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ እንደሚገኝ አስታወቀ
ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኀበረ ቅዱሳን ዱራሜ ማእከል 19ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ጉባኤው ከሀገረ ስብከት፤ ሰ/ት/ት/ቤቶች ኅብረት ተወካይ፣ የተለያዩ ደብራትና አጋር አካላት ተወካዮች፤ የማእከሉ አባላት፣ የወረዳ ማእከላትና ግንኙነት ጣቢያ ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ የማእከሉን ዓመታዊ ዕቅድ ክንውን የገመገመ ሲሆን በዕለቱም የከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ቆሞስ አባ ሚካኤል ታደሰ መልእክት አስተላልፈዋል።
ሥራ አስኪያጁ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ሐሣብ የሰጡ ሲሆን በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የሚሆኑ ጉዳዮችን በማገዝ በአገልግሎት ሁሉ ከጎን እንደሚሆኑ ቃል ገብተዋል።

❤33🙏4
አውስትራሊያ ማእከል 6ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ እንደሚገኝ ገለጸ
ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
ከተመሠረተ 11ኛ ዓመት የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን አውስትራሊያ ማእከል 6ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በቨርቿል እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጿል።
በጠቅላላ ጉባኤው የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች፣ የአድባራትና አስተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች፣ የመንፈሳዊ ማኅበራት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
መርሐግብሩ በመጋቢ ምሥጢር ቀሲስ ስንታየሁ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን በመምህር አርክቴክ አንተነህ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል።
በዛሬ መርሐ ግብሩም የማእከሉ የ2017 ዓ.ም ሥልታዊ ዕቅድ አፈጻጸምና የኦዲት አገልግሎት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በዋናው ማእከል ልዑክ በአቶ ግርማ መታፈሪያ የማኅበረ ቅዱሳን መልእክትና እና የማእከሉ መልእክት ደግሞ በሰብሳቢ በዶ/ር ትንሣኤ መኮንን በንባብ ቀርቧል።

❤27🙏4
25ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አውሮፓ ማእከል አስታወቀ
ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል 25ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በፍራንክፈርት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት ሐምሌ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
በጉባኤው የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ መዊዕ ልሣነ ወርቅ ውቤ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች እና ከመላው አውሮፓ የተውጣጡ አባላቱ በተገኙበት ተገኝተዋል፡፡
" እነሆኝ ጌታዬ እኔን ላከኝ " በሚለው መሪ ቃል የተጀመረው 25ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ከመደበኛው የሪፖርትና እቅድ አፈጻጸም ውይይት በተጨማሪ የተለያዩ አጀንዳዎች ተካተዋል።
“አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳይደለ ዛሬ ዕወቅ።” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር መነሻ በማድረግ ትምህርተ ወንጌል በፕሮፌሰር ሰሙ ምትኩ ተሠጥቷል፡፡
በጉባኤው መክፈቻ ላይ የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የማእከሉ ሰብሳቢ ዲ/ን ዶ/ር መኳንንት ሙሉጌታ ማእከሉ በዓመቱ ውስጥ በሀገር ቤት እና በአውሮፓ ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ዋና ማእከሉም በዓመቱ ውስጥ ያከናወናቸውን አጠቃላይ ሪፖርት በቀሲስ ዶ/ር ሄኖክ ፍቅሬ ቀርቧል፡፡
መርሐ ግብሩ በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን የማእከሉን ዓመታዊ አፈጻጸም እንደሚገመግም እና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ላይም እንደሚወያይ ይጠበቃል፡፡

❤26🙏3🥰2
ጉባኤው በአውሮፓ የምትገኘው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮዋን ከዳር ማድረስ ትችል ዘንድ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ የሚወያይ ሲሆን በዋናነትም ተተኪውን ትውልድ ከማስተማር አንጻር የእስከ አሁን ጉዞ መገምገም እና ቀጣይ ሂደት ላይ አቅጣጫ ማመላከትን በሚመለከት ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ምክክር የሚደረግበት ይሆናል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተተኪው ትውልድ ለኃላፊነት እንዲዘጋጁ ፣ በሚኖሩበት ዓለም እንዲሁም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ሰንቀው እንዲኖሩ ከማድረግ አንጻር የወላጆች ሚናን በሚመለከት በሠፊው ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡
ጠቅላላ ጉባኤው ከአባላት በተጨማሪ ለሕጻናትና አዳጊዎች የተለያዩ አስተማሪ ዝግጅቶች ተሰናድተዋል፡፡

❤34🙏3🥰2
የባሌ ሮቤ ማእከል 27ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ እንደሆነ አስታወቀ
ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ባሌ ሮቤ ማእከል 27ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ እንደሆነ አስታውቋል።
በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሀገረ ሰብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣የሀገረ ስብከቱ መምሪያ ኃላፊዎች አንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻና አጋር በተገኙበት ተገኝተዋል።
ጉባኤው በመጀመሪያው ቀን ውሎው የዋናው ማእከልን ሪፖርት ጨምሮ የ2017 ዓ.ም የማእከሉን ልዩ ልዩ አፈጻጸም ሪፖርቶች አድምጦ አጽድቋል።
የቀሩ አጀንዳዎች በነገው ዕለትም የሚቀጠሉ ይሆናል።

❤55🙏14🥰6