Telegram Web Link
በአሜሪካ የሚገኙ ግቢ ጉባኤያት ጠቅላላ ጉባኤ በአትላንታ ከተማ እየተካሄደ ነው!

በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ክፍል በማእከሉ የሚገኙ 22 ግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን በአንድነት ያሰባሰበ ጠቅላላ ጉባኤውን በጂዮርጅያ ግዛት በአትላንታ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ጉባኤው በአካል ለሁለተኛ ጊዜ በአጠቃላይ ደግሞ ለሰባተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ከ 250 በላይ ወጣቶች የታደሙበት ነው። ጉባኤው ዐርብ ሐምሌ 11 ቀን በመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ቤተክርስቲያን እንግዶችን እግር በማጠብ እና በጸሎት የተከፈተ ሲሆን እንግዶች በተዘጋጀላቸው የጂዮርጂያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መኖሪያ አርፈዋል። የቅዳሜ ሐምሌ 12 መርሐግብርም በዩኒቨርሲቲው ትልቅ የስብሰባ አዳራሽ በጸሎት ተጀምሮ በተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች በድምቀት ሲካሄድ ውሏል። የአትላንታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ በመርሐግብሩ በመገኘት ቃለ ቡራኬ እና በዚህ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ እና የክፍተኛ ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል። ጉባኤው እሑድ ሐምሌ 13 ቀንም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን ተማሪዎች በከተማው በሚገኙ የተለያዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በቅዳሴ ጸሎት የሚሳተፉ ይሆናል። የእሑዱ መርሐግብር እስከምሽቱ ድረስ በተለያዩ መንፈሳዊ መርሐግብራት በመቀጠል የቀጣይ ዓመቱን ጉባኤ አዘጋጅ ንዑስ ማእከል በመምረጥ በምስጋና እና በዝማሬ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
41👍8🙏5
2025/09/16 12:59:46
Back to Top
HTML Embed Code: