ከወላይታና ከዳውሮ አህጉረ ስብከት የመጡ 31 ተተኪ ሰባኪያነ ወንጌል በጀሞ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እየሠለጠኑ እንደሚገኝ የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት አስታወቀ
ሐምሌ ፳፩/፳፻፲፯ ዓ.ም
የጀሞ ደብረ ሰላም ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ከሰበካ ጉባኤውና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ከወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት የተወጣጡ 31 ተተኪ ሰባኪያነ ወንጌል በማምጣት ለሁለተኛ ዙር እያሠለጠነ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የፈለገ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሊቀ መንበር አቶ ኃይለ መስቀል ጋሻው እንደገለጹት ስብከተ ወንጌልን በጠረፋማውና በገጠራማው አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ ሠልጣኞችን እያሠለጠኑ እንደሚገኙ ገልጸው በዚህም በ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ያሠለጠኗቸው ደቀ መዛሙርት ከ450 በላይ አዳዲስ አማንያንን በማስጠመቅ፣ አብያተ ክርስቲያናትን በመገንባት፣ ሰንበት ትምህርት ቤትና የስብከት ኬላዎችን በማቋቋም በርካታ ሥራዎችን በመሥራታቸው የዘንድሮውን የሥልጠና መርሐ ግብር ለማዘጋጀትና ለመስጠት እንደጠቀማቸው ተናግረዋል።
አቶ ኃይለ መስቀል ጋሻው አክለውም ይህን አገልግሎት በስፋት ተደራሽ ለማድረግ ሌሎች ሰንበት ትምህርት ቤቶች ተሞክሮዎችን ሥልጠናውን ከሚሰጡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በመውሰድ እና ተናቦ በመሥራት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዲችሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

❤40👏1🙏1
መልአከ አርያም ዓለማየሁ ዘውዴ የጀሞ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በበኩላቸው እንደገለጹት ሠልጣኞች ሠልጥነው ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ ስብከተ ወንጌልን በቋንቋቸው ተደራሽ ለማድረግ እንዲያስችላቸው የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ ያሉ አካላትን አመስግነው ይህንን ተግባር ለመደገፍ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችም ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ለአሠልጣኞች ሥልጠና ከሚሰጡት መምህራን መካከል አንዱ የሆኑት መምህር ተመስገን ሥራህ ብዙ እንደተናገሩት “ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ስበኩ” በማለት ክርስትናን ጀማሪው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባሳሰበው መሠረት የወንጌል አገልግሎት ባልተስፋፋባቸው አካባቢዎች ለማድረስ ሐዋርያዊ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል በማለት በዚህም እየሠለጠኑ ያሉ ሠልጣኞች የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎች በመሆናቸው አካባቢያቸውን ለማገልገል ሥልጠናው እንደሚረዳቸው ተናግረዋል።
ሠልጣኞች እንደገለጹት በአካባቢያቸው ያለውን የስብከተ ወንጌል በቋንቋቸው ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ሥልጠና እየወሰዱ መሆናቸውን ገልጸው ሥልጠናው የሄዱትን ለመመለስ፣ ያሉትን ለማጽናት፣ አዳዲስ አማንያንን ለማስጠመቅ እንደሚጠቅማቸው ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ትውልድን የሚያንጽ፣ ክርስትናን የሚያጠነክር፣ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ተቆራኝቶ እንዲኖር የሚረዳውንና የሚያግዘውን ማኅበረ ቅዱሳንን እናመሰግናለን ያሉት ደቀ መዛሙርቱ አክለውም በሥልጠናው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ የሚገኙትን ሁሉ ምስጋናን ችረዋል።
በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዳሬክተር ዲያቆን ሙሉጌታ ነጋ እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን በገጠራማውና በጠረፋማው አካባቢ ከሚሠራቸው ሥራዎች መካከል ስብከተ ወንጌል ተደራሽ ባለሆነባቸው ስፍራዎች ለማደረስ ተተኪ መምህራንን እያመጣ ከባለድርሻ አካላት ጋር እያሠለጠነ ይገኛል በማለት ተናግረዋል።
ዳሬክተሩ አክለውም ከማእከላትና ከወረዳ ማእከላት፣ ከወረዳ ቤተ ክህነት፣ ከሀገረ ስብከት ጋር በማስተሳሰር የሠለጠኑ ደቀ መዛሙርትን ወደ አካባቢያቸው በመላክ ከዚህ በፊት ከሠለጠኑ ሠልጣኞች ፣ ከካህናት፣ ከአጥቢ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር ሆነው በቅንጅት እንዲሠሩ በማድረግ የጠፉትን የመመለስና ቅዱስ ወንጌል ያልደረሰባቸው አካባቢዎች እንዲያደርሱ በማድረግ የማስተማርና የማስጠመቅ ሥራ እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ይህንን አገልግሎት በስፋት ተደራሽ ለማድረግ ማኅበራትና ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለሠለጠኑ ሰባኪያን ደመወዝ የመክፈል፣ጉባኤያትን የማከናወን፣ሌሎች ሠልጣኞች ካልመጡባቸው ቦታዎች በማምጣት በጋራ መሥራት፣ ማስተማርና ለተልእኮ መላክ ቢቻል ነፍሳትን የማዳን ሥራ ማከናወን እንደሚቻል መልእክት አስተላልፈዋል።

❤38👏1🙏1
በአሜሪካ ማእከል የመካከለኛው ማስተባበሪያ 2ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ!!
በአሜሪካ ማእከል መካከለኛው ማስተባባርያ በሚኒያፖሎስ ከተማ በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄዳ፡፡ በሚኒያፖሊስ ርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል አርብ በጸሎተ ወንጌል የተከፈተው ጉባኤ ቅዳሜ እና እሑድ ቀጥሎ ውሏል::
በጉባኤው ከ150 በላይ አባላት የታደሙ ሲሆን የ2017 ዓ/ም ዓመት የሥራ ክንውን እና የቀጣይ ዓመት እቅድን ጨምሮ ክርስቲያናዊ ቤተሰብ እና የልጆች አስተዳደግን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሁፎች ለጉባኤው ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ::
በጉባኤው ማጠቃለያ እለት የተገኙት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሚኒሶታ እና አካባቢው እንዲሁም የኮለራዶ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ማኅበሩ በሌሎች ዘርፎች ያሳየውን አስደናቂ ውጤት በተተኪ ትውልድ ማፍራት ላይ ጠንክሮ እንዲሰራ ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል::
በመካከለኛው ማስተባበሪያ ሥር የሚገኙ 4 ንዑሳን ማእከላትና 6 ግንኙነት ጣቢያዎች አባላት በጉባኤው ተሳታፊ ሁነዋል:: የሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ ማኅበራት ተወካዮችም በጉባኤው ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል::
በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል ለአገልግሎት ቅልጥፍና ና አመችነት ሲባል ተቋማዊ ለውጡን ተከትሎ በሶስት ማስተባበሪያ ከተዋቀረ በኋላ ማስተባበሪያዎቹ በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ አካሄደውል፡፡ በዚህ ሳምንት መጨረሻም አጠቃላይ የአሜሪካ ማእከል ሁሉንም አባላት የሚሳተፉበት ቨርቸዋል ጠቅላላ ጉበኤ የሚካሄድ ይሆናል ::

❤33🙏3👏2