ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የተወለዱት በመስከረም ፯ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ፍቼ ከተማ ነው። ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ በጎሐጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከፊደል እስከ መዝሙረ ዳዊት የተማሩ ሲሆን ከዚያም በመንፈሳዊ ሕይወት እንዲጎለብቱ ወላጆቻቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ ታዋቂ መምህር ለነበሩት ለባሕታዊ ተድላ እንደሰጧቸው ይነገራል።
ብፁዕነታቸው የወላጆቻቸውን ሕልም ለማሳካት በንፁሕ አእምሮአቸው የልዩ ልዩ መጽሐፍትን ንባብ፣ ጸዋትወ ዜማ ና ቅኔ ፣ የገዳሙን ሥርዓት እየተማሩ በመንፈስ፣ በጥበብና በጸጋ አደጉ።
ብፁዕነታቸው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከባሕታዊ ተድላ የቀሰሙትን የዕውቀት ጣዕም እጅግ ስለጣፈጣቸው ዕውቀት ለመቅሰም ከሀገር ሀገር መዘዋወር ጀመሩ፤ በዚህም በምእራብ ጎጃም ወደሚገኘው ወደ ቅኔ መድብል ዋሽራ በማምራት የቅኔ መምህር ሆኑ። ከዚያም ወደ ወሎ በመጓዝ ከታዋቂው መምህር አካለወልድ ክፍሌ ቦሩ ሜዳ ላይ የመጻሕፍተ ብሉያትን፣ መጽሐፍተ ሐዲሳትን፣ መጽሐፍ ሊቃውንትንና መጽሐፍተ መነኮሳትን በከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ደረጃ አጠናቅቀው በመምህርነት ተመረቁ። እንዲሁም በነገረ መለኮት ሚሥጢርና በቅዱሳት መጻሕፍት ምርምር የታወቁም ሆኑ።
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በወሎ አማራ ሳይንት በተባለ ስፍራ በሚገኘው ምስካበ ቅዱሳን ገዳም መንፈሳዊ ዕውቀት የተጠሙ ደቀ መዛሙርትን ወንበር ዘርግተው ማስተማር የጀመሩ ሲሆን ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅሙ ደቀ መዛሙርትን በትምህርት አንጸው ማበርከት ችለዋል።

❤51🙏9
በዚያው ገዳምም ከማስተማሩ ጎን ለጎን አመክሮ ያደረጉ ሲሆን ብፁዕነታቸው የድንግልና ሕይወት መርቷቸው በ፲፱፻፱ ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጸሙ። አያይዘውም ማዕረገ ቅስናም ከብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ ተቀበሉ።
ብፁዕነታቸው በ፲፱፻፲ ዓ.ም በወላይታ ሶዶ የደብረ መንክራት ተክለሃይማኖት ገዳም አስተዳዳሪ፣ በ፲፱፻፲፩ ዓ.ም በዝዋይ ደሴት የገዳሙ መምህር፣ በ፲፱፻፲፱ ዓ.ም በአዲሰ አበባ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን የደብሩ አስተዳዳሪ በመሆን አገልግለዋል።
የግብጽ ቤ/ክ ኢትዮጵያዊ ኢጲስ ቆጶስ እንዲሾም ተጽዕኖ ብታደርግም የእግዚአብሔር ፈቃድ በትምህርታቸው፣ በአባትነታቸውና በጠባያቸው ተመርጠው ግንቦት ፳፭ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ.ም አራት ቆሞሳት የጵጵስና ማእረግ ከግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ ፲፱ኛ ተቀብለው ከተመረጡት መካከል አንዱ “አቡነ ጴጥሮስ” የሚል ሢመት ጵጵስና ክብር ተቀዳጁ።
ብፁዕነታቸው በዚሁ ጵጵስና ዘመን ሐዋርያዊ አገልግሎት፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነትና አደራ ለመወጣት ምእመናንን በትምህርታቸው በማነጽ፣ በጸሎታቸው በመደገፍ፣ አዳዲስ አማንያንን በማስጠመቅ በርካታ አገልግሎቶችን አከናውነዋል።
የኢጣሊያ ፋሺስት በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን በማወጅ ሕዝቡን በግፍ ይገድል ጀመረ፤በየገዳማቱም በርካታ ካህናትና መነኮሳት ተገደሉ፣የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ተዘረፉ፤ አቡነ ጴጥሮስም ይህንን ግፍ በማየታቸው ከሀገራችን አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎታቸው ሊዋጉት ተነሡ፡፡ ፋሺስት በማይጨው በመርዝ የተደገፈ ጦርነት ከማድረጉ የተነሣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበታተንም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው ለሀገርና ለነጻነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሰላሌ አርበኞች በሚገባ አስተምረዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ‹‹የሀገሬን ሕዝብ ለጠላት እንዳይገዛ በአደባባይ አውግዤ ጠላትን ረግሜ በሰማዕትነት ባልፍ ይሻለኛል›› ብለው ራሳቸውን ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት ወሰኑና የፋሺስት ኢጣሊያ እንደራሴ ለሆነው ለራስ ኀይሉ ሄደው እጃቸውን ሰጡት፡፡ በዚህም ለግራዚያኒ ሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ግራዚያኒም ግማሽ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲገደሉ ወሰነባቸው፡፡
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በፈቃዳቸው እጃቸውን አሳልፈው ከሰጡ በኋላ ወደ ችሎት ቀረቡ፡፡ በቀረበባቸውም ወንጀል ‹ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ራስዎም ዐምፀዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምፁ አድርገዋል› የሚል ነበር፡፡ ዳኛውም ‹ካህናቱም ሆኑ የቤተ ክህነት ባለሥልጣኖች ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የጣሊያንን መንግሥት ገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን ዐመፁ? ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ?› ብለው ተጠየቁ፡፡
ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱም፡- ‹‹አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፣ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፣ እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ኀላፊነትም ያለብኝ በመሆኔ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡ ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም፡፡ ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ፡፡ እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ» አሉ፡፡
በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲመለከት ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ የሚከተለውን ሕያው መልእክት አስተላለፉ፡- ‹አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው እንጂ በጎ ለመሥራት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፡፡ ስለ ውድ ሀገራችሁ፣ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ፡፡ ነጻነታችሁ ከሚረክስ ሞታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ፣ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን፡፡ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን› ብለው አወገዙ፡፡
ቀጥሎም ብፁዕነታቸው በፍጥነት ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለ እርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ፡፡ ከዚያም እንዲገደሉ ከተወሰነ በኋላ ከመካነ ፍትሑ ዐሥር ሜትር ርቆ ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያ ተወሰዱ፡፡ ከገዳዮቹም አንዱ ‹ፊትዎን ለመሸፈን ይፈልጋሉን?› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ‹ይህ ያንተ ሥራ ነው› ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ፡፡
ከመግደያውም ቦታ እንደደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ አድርገው እንዲቀመጡ ሆኑ፡፡ ከዚያም በኋላ ስምንት ወታደሮች በስተ ጀመርባቸው ሃያ ርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ፣ ወዲያው አዛዡ ‹ተኩስ!› በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቱዋቸው፡፡ ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ፡፡ መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ፡፡ ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ፡፡ ከዚያም በኋላ አንድ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው፡፡
ፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል በሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ሰማዕቱን አቡነ ጴጥሮስን ገድሎ አስክሬናቸው አደባባይ ላይ ጥሎ ከዋለ በኋላ ቀብራቸው በምሥጢር መፈጸሙ የሚነገር ሲሆን በሐምሌ ፳፪ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለሀገር እና ለቤተ ክርስቲያን ሲሉ ሰማዕት ሆነዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ፲፪ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም እኚህን ሰማዕት ‹‹አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ›› ተብለው እንዲጠሩ ወስኗል፡፡ በወቅቱ በሰሜን ሸዋ የሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡ ቀውስጦስ ለብፁዕነታቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በተወለዱበት ስፍራ የመንፈስ ልጆቻቸውን በማስተባበር በስማቸው ቤተ ክርስቲያን አሠርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ነጻነቷን ካገኘች በኋላ መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት አሳሳቢነት ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ.ም በአዲስ አበባ መሐል ከተማ ላይ ሐውልት ቆሞላቸዋል፡፡
ምንጭ፡- የሐመር መጽሔት ግንቦት ፩ ቀን 2001 ዓ.ም

❤52🙏13👍4
«ልጆቼ ዓላማዬን ተከተሉ!»
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ (1932 ዓ.ም— 1982 ዓ.ም)
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ከአቶ ገበየሁ እሰዬና ከወ/ሮ አሰለፈች ካሣ በ1933 ዓ.ም በስእለት የተወለዱ ሲሆን ወደ ተቀደሰው የእግዚአብሔር ጎዳና ያመሩት ገና በሕፃንነታቸው ነበር። ዝናቸው ከታወቀው የተለያዩ ኢትዮጵያ ገዳማትና ብቃታቸው ከተመሰከረላቸው ሊቃውንት ዘንድ ዜማ፣ትርጓሜ መጻሕፍት፣ባሕረ ሐሳብ እና ቅኔ ተምረው ተመርቀዋል።
በዘመናዊ ትምህርታቸውም በየደረጃው ከአቴና ዩኒቨርስቲ በቲኦሎጂ (ነገረ መለኮት ) በማስትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል እንዲሁም ፈረንሳይኛና ዐረብኛ ቋንቋ አጥንተዋል።
በመንፈሳዊ አገልግሎታቸው፣በትምህርታቸው፣በምርምር፣በሥነ ጽሑፍ እና በማስተማር ዘዴያቸው ባለተሰጥኦ እንደነበሩ ይነገራል።
የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በነበሩት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እንብሮተ እድ በ1971 ዓ.ም ጳጳስ ሆነው ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ ሕይወታቸው በመኪና አደጋ እስካለፈበት ቀን ድረስ በጣም ድንቅና በርከታ ሥራዎችን አከናውነዋል።
በተለይም የዝዋይን የከህናት ማሠልጠኛ በገዳም ሥርዓት እንዲተዳደር አስወስነው በሺህ የሚቆጠሩ ካህናት እንዲሠለጥኑ፣ አባትና እናት የሌላቸው ሕፃናት እንዲያድጉበት ከማድረጋቸውም በላይ፣ አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽና በዚሁ ሥፍራ የተለያዩ የልማት አውታሮችን በመዘርጋት አርአያነት ያለው ተግባር ፈጽመዋል።
ትምህርታቸው ልቡናን ሰብሮ የሚገባ፣በምሳሌዎች የተደገፈ እና ጥልቀት ያለው ነበር በአጠቃላይ «ትምህርታቸው እንደ ዐባይ ውኃ የሚፈስ ነበር» ።

❤56🙏10
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በአስተሳሰበቸው ሀገራቸውን፣ሕዝባቸውን የሚወዱ፣ በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑ፣እናት ለልጅዋ እንደምታስብ ሀገራቸውን የሚወዱ፣ሥጋዊ ጥቅም የማያታልላቸው፣በሃይማኖትም ሆነ በሀገራቸው ጉዳይ አድርባይነት የሌለበቸው፣ፍርሀት የሌለባቸው፣ እውነት የሚናገሩ እንደነበሩ ብዙዎች ይመስክራሉ፡፡
ለወጣቶች የተለየ ፍቅርና እንክብካቤ ያደርጉ የነበሩ፣በአቀራረባቸው የሚወደዱ እና ወጣቶችን “እናንተ የቤተ ክርስቲያን የስስት ልጆች ናችሁ፣የሰንበት ተማሪዎች የቤ ተክርስቲያን ችግኞች ናችሁ» በማለት በሃይማኖታዊ ፍቅር ይኮተኩቱ ነበር፡፡
ብፁዕነታቸው በዓለም መድረክ የቤተ ክርስቲያን መልእክተኛ የነበሩ ሲሆን ሦስት ጃማይካውያንን በዝዋይ አስተማረው ለማዕረገ ቅስና አብቅተዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ራብዕ፣ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ካልዕ፣ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሣልስ፣ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ ከብፁዕነታቸው ፍሬዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
አቡነ ጎርጎርዮስ የሃይማኖትና የታሪክ ተመራማሪም የነበሩ ናቸው፡፡ በሕይወት ዘመናቸው ስምንት መጻሕፍት ጽፈዋል። እነርሱም፡- መሠረተ እምነት፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፣ትምህርተ ሃይማኖት (ዶግማ)፣የስብከት ዘዴ( ኦርቶዶክሳዊ)፣ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ፣ሥርዓተ ኖሎት እና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሲሆኑ እነዚህም መጻሕፍቶቻቸው በምርምር ላይ የተመረኮዙ፣ጥልቅ ምሥጢር ያካተቱ እና በውብ አገላለጽ የተሞሉ ናቸው።
በጻፉት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ መጽሐፋቸው ኢትዮጵያ በዘመነ ኦሪት፣ኋላም የክርስትናን እምነት ከተቀበለችበት ወቅት አንስቶ እስከ አሁን የተጓዘችባቸውን የታሪክ ሂደቶች የሚያሳይ፣በሥዕላዊ ቃላትና ጥልቅ ሐሳቦችን የሚገልጽ ድንቅ መጽሐፍ ነው።
በተጨማሪም መጽሐፉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት(ዶግማ)፣የታበት፣የሥዕልና የመስቀልን ክብር፣የአማላጅነት ምስጢር፣የቤተ ክርስቲያን ትውፊት እና ሥሪትን የሚያብራራ ነው።
ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ.ም ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ተኩል ወደ መቂ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ሲሄዱ በድንገተኛ የመኪና አደጋ በተወለዱ በሃምሳ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡
ብፁዑነታቸው ከተናገሯቸው ድንቅ አባባሎች ውስጥ ስለ እመቤታችን መናገር የምንችለው ስለሰውና ስለ እግዚአብሔር ስናውቅ ብቻ ነው፣ የቤተ ክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ነውና ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠናክሩ፣ሰው ፍላጎቱን ካላሸነፈ የእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም፣ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው፣ኢትዮጵያ ለእግዚአብሔር የምሥጢር ሀገር ናት፡፡
ለሠሩት እና ላበረከቱተት አስተዋጽኦዎች ትምህርት ቤቶች፣አዳራሾች፣ቤተ መጻሕፍት እና ሐውልት በስማቸው ተሰይሞላቸዋል፡፡
ምንጭ፡- የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ

❤120🙏17🤔3