Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ አገልግሎቱን በማጠናከር በግቢ ጉባኤያት ላይ ውጤታማ ሥራ ለመሥራትና ብቁ አገልጋዮችን ለማፍራት ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቶቹን ለማስፈጸም ይረዳው ዘንድ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ትኬት ሽያጭ ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በማሠራጨት ላይ ይገኛል፡፡
እርስዎም ትኬቱን በመግዛት ትውልድን ለመቅረጽ በሚደረገው ጥረት ውስጥ አሻራዎን ያኑሩ፡፡
94🙏19👏15
የማኅበረ ቅዱሳን የ2017 ዓ.ም ሁለተኛ መንፈቀ ዓመት የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ መከናወን ጀመረ።

ማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ሂደቱን ከሚገመግምባቸው ጉባኤያት መካከል አንዱ የሆነው እና በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከናወነው የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በዋናው ማእከል ተጀምሯል።

በጉባኤው ላይ የማኅበሩ የሥራ አመራር አባላት፣የሥራ አስፈጻሚ አባላት፣የማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ በአገር ውስጥ ከሚገኙ ማእከላት የተወከሉ የማእከላት ሰብሳቢዎች በአካል የተገኙ ሲሆን የውጭ ማእከላት ተወካዮች ደግሞ በበይነ መረብ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው የማኅበሩ የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በ6ወራት ውስጥ የተከናወኑ አገልግሎቶች እንዲሁም በመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት የሥራ አመራር ጉባኤ ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች አፈጻጸምን የተመለከቱ ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።

በአሁኑ ሰዓትም የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛሉ።
66🙏10👍5👏4
ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ለገዳማት፣ ለአብነት ት/ቤቶች እና ደቀ መዛሙርት ድጋፍ እንዲሁም ለገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች በበጀት ዓመቱ ማውጣቱን ማኅበረ ቅዱሳን አስታወቀ።

ዛሬ ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በተጀመረው የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ የበጀት ዓመቱን እቅድ አፈጻፀም አቅርበዋል። ከእነዚህም አንዱ የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገልግሎት ይገኝበታል።

በሪፖርታቸውም ከተለያዩ አህጉረ ስብከት ለተመረጡ 169 የአብነት ት/ቤቶች፣ ለ229 መምህራንና 2020 የአብነት ደቀ መዛሙርት እና ለ27 የአባ ጊዮርጊስ ነጻ የትምሕርት እድል ተጠቃሚዎች 12,444,872.00 ብር ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በሁሉም አካባቢ በጦርነት እና በድርቅ ለተጎዱ 22 ገዳማት እና 65 አብነት ትምሕርት ቤቶችም 3,085,540.00 ብር የተገዛ የቀለብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

8,870,407.125 ብር ወጪ የተደረገበት የምሥራቅ ወለጋ ሀ/ስብከት አዳሪ አብነት ት/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ትግበራ በማጠናቀቅ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ መመረቁም በሪፖርቱ ተጠቅሷል::

የደብረ ሐዊ ቅ/ያሬድ አንድነት ገዳም የገቢ ማስገኛ ግንባታ ፕሮጀክት ማኅበሩ ማከናወን ከሚጠበቅበት ድርሻ ከ75% በላይ የተከናወነ ሲሆን እስከ አሁን 25,218,432.06 ብር ወጪ መደረጉን መምህር ዋሲሁን አስታውቀዋል፡፡

23,705,832.46 ወጭ የተደረገበት የማኅበረ ቅዱሳን በደሌ የገቢ ማስገኛ ሕንጻ ፕሮጀክት ግንባታ 15% ላይ መድረሱም ተጠቅሷል ፡፡
29🙏7
የአሶሳ ሀገረ ስብከት አምባ አራት ሐ/ኖኅ ቅ/ኪዳነ ምሕረት ገዳም አብነት ትምህርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክት እየተተገበረ 55% ላይ የደረሰ ሲሆን እስከአሁን 6,726,558.00 ብር ወጪ ተደርጓል።

በካፋ ሀገረ ስብከት የቦንጋ አብነት ትምሕርት ቤት ግንባታ ፕሮጀክት በተመሳሳይ እየተተገበረ 35 ፐርሰንት የደረሰ ሲሆን 5,374,054  ብር ወጪ ሆኗል።

ከተመረጡ ገዳማትና የአብነት ት/ቤቶች መሪ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ለማፍራትም ማኅበረ ቅዱሳን ለ525 መነኮሳት፣ መምህራንና ደቀ መዛሙርት የዓቅም ማሳደጊያ ሥልጠና መሰጠቱን ዋና አስፈጻሚው አብራርተዋል፡፡
27👏3🙏3
ማኅበረ ቅዱሳን በያዝነው የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ50 ሺህ በላይ አዳዲስ አማንያንና የጠፉትን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መመለሱን አስታወቀ።

ማኅበረ ቅዱሳን እያካሄደ ባለው የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤው በያዝነው የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት 52,609 ነፍሳትን ማስጠመቁን አስታውቋል።

በዚህም 47,116 ኢ አማንያንን የሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ እና 5493 ጠፍተው የነበሩትን እንዲመለሱ አድርጓል።

ይህን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመፈጸምም ለመመለስ እና ለማስጠመቅ 87 ጉባኤያት ተዘጋጅተዋል።

በተጨማሪም በተመረጡ 4 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ትምህርቶችን በድምፅ ወምስል በማዘጋጀት ለምእመናን አድርሷል።

የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚሰጡ መምህራን በደረጃ አንድ ከ1597 እና በደረጃ ሁለት ከ259 መምህራን ማሠልጠንና ማሰማራት መቻሉም እያካሄደ በሚገኘው የ2017 ዓ.ም የሁለተኛው መንፈቀ አመት ጠቅላላ ጉባኤ በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል።

ለአዳዲስ አማንያንም መገልገያ እና ሐዋርያዊ ተልእኮ ለማስፋፋት የሚያገለግሉ 7 አብያተ ክርስቲያናት ተሠርተዋል፡፡

ለቅድመ ጥምቀት እና ድኅረ ጥምቀት አገልግሎት የሚውሉ 3 መካነ ስብከት አዳራሾች ተሰርተዋል፡፡

በካህናት እጥረት ለተዘጉ 34 አብያተ ክርስቲያናት ካህናት መቅጠር እና አገልግሎት እንድሰጡ ተደርጓል ሲል በዋና ሥራ አስፈጻሚው መምህር ዋሲሁን በላይ አማካኝነት አስታውቋል፡፡
146🙏26👍7🥰6👏2
2025/09/15 20:08:43
Back to Top
HTML Embed Code: