ማኅበረ ቅዱሳን ለሁለት ወራት ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ
ጳጉሜን ፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት በነቀምቴ ምሥካበ ቅዱሳን ዑራኤል ወሳሙኤል ገዳም ለሁለት ወራት ያስተማራቸውን ከ17 ወረዳዎች የተውጣጡ 32 ደቀ መዛሙርት ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ በሁለት ወራት የትምህርት ቆይታቸው 21 ደቀ መዛሙርት የቅስና ማእረግ የተቀበሉ ሲሆን 11 ዲያቆናት ደግሞ ለአገልግሎት ብቁ የሚያደርጋቸውን ትምህርት መማራቸው ተጠቁሟል።
ማኅበረ ቅዱሳን ባስገነባውና ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተመረቀው አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት ውስጥ ሊጦን ፣ መስተበቁዕ፣ ኪዳንና የትምህርተ ሃይማኖት ኮርሶችን ደቀ መዛሙርቱ መማራቸውን የተገለጸ ሲሆን ይህም ለተሻለ የክህነት አገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን ትምህርት በመማር የነበራቸውን እውቀት እንዲያጠናክሩ ያስችላቸዋል ተብሏል።
በማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ዳይሬክተር ዲ/ን ደረጀ ጋረደው በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት በማስተላለፍ ''በዚህ ወቅት መማራችሁ ሰፊው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚጠብቃችሁ በመሆኑ የተመረጣችሁበትን ዓላማ በውል በመረዳት በእምነት መጠበቅ እና መወሰን ይጠበቅባችኋል።" በማለት ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም "እስከ ምድር ዳርቻ ምሥክሮች ትሆናላችሁ" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በመጥቀስ ተመራቂ ደቀ መዛሙርቱ ቃለ እግዚአብሔርን ለተራቡ በተለይ በጠረፋማ አካባቢ ለሚገኙ ምእመናን ተደራሽ ማድረግ እንዲችሉ አሳስበዋል።

❤22👍3🙏2
የምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ላእከ ወንጌል ቀሲስ ገረመው በቀለ በበኩላቸው " ዛሬ የተመረቃችሁ 21 ካህናት የተዘጉ 21 አብያተ ክርስቲያናትን የምትከፍቱ ናችሁ" በማለት ቤተ ክርስቲያን የጣለችባቸውን አደራ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አደራ ብለዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም ማኅበረ ቅዱሳን የአገልጋይ እጥረት ለመቅረፍ እያደረገ ያለውን በጎ ተግባርም በማመስገን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
በማኅበረ ቅዱሳን የነቀምቴ ማእከል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በኩረ ትጉሐን አሰፋ ጉደታ ማኅበሩ ባስገነባው አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን አስተምሮ ማስመረቁ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤቱ የተገነባበትን ዓላማ ጅማሮ የሚያሳይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ዛሬ አስተምረን ማስመረቃችን ልዩ ትርጉም አለው ያሉት ኃላፊው በሀገረ ስብከቱ 480 አብያተ ክርስቲያናት ያሉ ሲሆን አብዛኛዎቹ በአገልጋይ እጥረት የተዘጉ በመሆናቸው የዛሬዎቹ ተመራቂዎች የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን በመክፈትና አገልግሎቱን በማስቀጠል የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
በማኅበረ ቅዱሳን የነቀምቴ ማእከል ከዋናው ማእከል ባገኘው ድጋፍ እና የአካባቢውን ምእመናን እንዲሁም ማኅበራት በማስተባበር ከ438,720 ብር በላይ የመምህራን፣ የሠራተኞችና የደቀ መዛሙርቱን ወጪ በመሸፈን ሲያስተምር መቆየቱን ተጠቁሟል።
በመጨረሻም ማኅበሩ ከምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ጋር በጋራ በመሆን ደቀ መዛሙርትን ከተለያዩ ወረዳዎች በመመልመልና በማስተማር ለአገልግሎት የማሠማራቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።

❤37👍19🙏2
✝️ከአንድ ቤተሰብ፣ ለአንድ ተማሪ✝️
++++
ማኅበረ ቅዱሳን በየዓመቱ እንደሚያደርገው በማኅበራዊ ቀውስ ጉዳት የተነሣ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ በገንዘብና በዓይነት እያሰባሰሰበ ይገኛል።
ድጋፍ ለማድረግም፡-
#በገንዘብ
በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000309803648
2. በአቢሲኒያ ባንክ 37235458
3. በወጋገን ባንክ 0837331610101
4. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
#በዓይነት
ደብተር፣እስክርቢቶ፣ እርሳስና ቦርሳ ለበለጠ መረጃ
• 09 84 18 15 44
• ማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ 1ኛ ወለል
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት

❤42🙏6👍2
ማኅበረ ቅዱሳን ለምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ያስገነባውን የአብነት ትምህርት ቤት ማስረከቡ ተገለጸ
ጳጉሜን ፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት በምስካበ ቅዱሳን ዑራኤል ወሳሙኤል ገዳም አዳሪ አብነት ት/ቤት ገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል።
ይህ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት ታኅሣሥ ወር 2016 ዓ.ም ተጀምሮ ታኅሣሥ 2017 ዓ.ም በአንድ ዓመት ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል።
የአብነት ት/ቤት ፕሮጀክቱ ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ርክክብ ተፈየተደረገ ሲሆን በርክክብ መርሐ ግብሩ የምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ላእከ ወንጌል ቀሲስ ገረመው በቀለና በማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገትና መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገልግሎት ዳይሬክተር ዲ/ን ደረጀ ጋረደው በመፈራረም ርክክቡን ፈጽመዋል።
ከ8.8 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት አዳሪ አብነት ት/ቤቱ የሁለት መምህራን ማደሪያ፣ የምግብ ማብሰያና መመገቢያ አዳራሽ፣ የመማሪያ ጉባኤ ቤትና የንጽሕና መጠበቂያ እንዲሁም 32 ተማሪዎችን ማስተናግድ የሚችል ደረጃቸውን የጠበቁ ማደሪያዎች ከነሙሉ ቁሳቁሳቸው ያካተተ ነው ተብሏል።
የአዳሪ አብነት ት/ቤቱ መገንባት በአካባቢው ያለውን የካህናት አገልጋይ እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችል ከመሆኑም በተጨማሪ ማኅበረ ቅዱሳን አብነት ት/ቤት ባልተስፋፋባቸው አካባቢዎች ለሚያደርገው አብነት ት/ቤቶችን የማስፋፋት እንቅስቃሴ ማሳያ ነው።

❤37🙏8👍3👏3
ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንዲሆን በሀገር ውስጥ የሚገኙ ምእመናን፣ በሀገረ አሜሪካ ሚኒሶታ፣ ኢንዲያፖሊስ፣ ሚያፊስና ፖርትላንድ ንኡስ ማእከል፣ በካናዳ እና አውሮፓ ማእከላት እንዲሁም በእንግሊዝ ሀገር የሚኖሩ በጎ አድራጊ ምእመናን ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።
አዳሪ አብነት ት/ቤቱ ለመጀመሪያ ግዜ ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ/ም 21 ቀሳውስትና 11 ዲያቆናትን በአጠቃላይ 32 ደቀ መዛሙርትን አስተምሮ አስመርቋል።

❤58👏16👍7🙏4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሳችሁ!
ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያስገነባው የልህቀት ማእከል ድጋፍ የሚውል የበረከት ዕቁብ ይሳተፉ! አንድ ዕጣ በወር 500ብር ብቻ።
ለመሳተፍ-https://forms.gle/jkjeZnNBunzKHvp69
ለበለጠ መረጃ-0966636363 ይደውሉ።
ማኅበረ ቅዱሳን።

❤30🙏6👍5🥰3
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የአዲስ ዓመት አባታዊ መልዕክት ማስተላለፋቸው ተገለጸ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን መግባት አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል ።
የቅዱስነታቸው ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው።
++++++++++++++++
ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዐውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰንመቱ ዓመተ ምሕረት፤
በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሐዱ ኣምላክ ኣሜን!
• በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
• ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
• የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
• በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣
• እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣
ኣምላክነቱን ኣውቀን እንድናመልከው ዕድሜንና ዘመናትን የሚሰጠን እግዚብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስምንት ዓመተ ምህረት የርእሰ ዐውደ ዓመት በዓል ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
‹‹ወገብረ ኵሎ ኅቡረ ወኵሎ ኣሕዛበ እምአሐዱ ዕጓለ እመሕያው ከመ ይንበሩ ዲበ ኵሉ ገጸ ምድር፤ ወሠርዐ ዕድሜሁ ወዓመታቲሁ መጠነ ይነብሩ በዘየኃሥዎ ለእግዚአብሔር፤ እመ ይረክብዎ፤ ወያደምዕዎ፤ ወኢኮነ ርሑቀ እምኵልነ፡-

❤28🙏7