ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች አደራ የመስጠት መርሐ ግብር ተካሄደ
መስከረም ፭ /፳፻፲፰ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጋር በመተባበር በ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተፈትነው ውጤት በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች አደራ የመስጠት መርሐ ግብር በትናንትናው ዕለት መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት በጽርሐ ተዋህዶ ተካሄዷል።
በመርሐ ግብሩ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሰዋሰው ብርሃን የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ አባል፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሰብሳቢ አቶ ኤልያስ አበበ፣ የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢና የአዋሽ ካፒታል ባንክ ፕሬዝዳንት በትረ ትጉሃን ዲያቆን ዶ/ር አንዱዓለም ኃይሉ ፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሰብሳቢ አቶ ኤልያስ አበበ የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ስለ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አደረጃጀት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሰብሳቢው አክለውም ተማሪዎች ዩንቨርስቲ በሚኖራቸው ቆይታ ግቢ ጉባኤን እንዲሳተፉ ያሳሰቡ ሲሆን በዚህም ማኅበረ ቅዱሳን እና አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት አብረው እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

❤40🙏4👏1🤔1
ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ አባል በበኩላቸው ”እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ሐሳቡንም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንደሚደረግ እናውቃለን” (ሮሜ ፰፥፳፰) የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መነሻ በማድረግ ትምህርት ያስተማሩ ሲሆን ተማሪዎች በውጤታቸው መሠረት በመንግሥትና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም በኮሌጆች ቢመደቡም በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ነውና ይህንን ለበጎ እንደተደረገ በማመንና በመቀበል በተመደቡበት በየትኛውም ሥፍራ በኦርዶክሳዊ መንገድ ሕይወታቸውን መምራት እንዲችሉ ተናግረዋል።
በኩረ ትጉሃን ዲያቆን ዶ/ር አንዱዓለም ኃይሉ የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢና የአዋሽ ካፒታል ባንክ ፕሬዝዳንት ተማሪዎች ወደ ዩንቨርስቲ በሚገቡበት ወቅት ሊገጥማቸው የሚችለውን ነገሮችና የአገልግሎት ምቹ ሁኔታዎች በተመለከተ ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን ተማሪዎች በዓለማዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምህርታቸው በርትተው መሥራት እንዲችሉ መልእክት አስተላልፈዋል።
አቶ አምደሥላሴ ሙሉጌታ በማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት የቅድመ ግቢ ጉባኤ ኃላፊ ማኅበረ ቅዱሳን ከሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጋር በጋራ በመሆን በርካታ ሥራዎችን መሥራታቸውን ገልጸው ተማሪዎች በቀለም ትምህርት ውጤታማ እንዲሆኑ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት ራሳቸውን ጠብቀው በግቢ ጉባኤ አገልግሎት እንዲሳተፉና የተዘጋጀላቸውን ኮርሶች አጠናቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የሰዋሰው ብርሃን የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትና አባታዊ ቡራኬ ሰጥተዋል።👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤49🙏1
ለመመዝገብ እና የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ👉👉https://forms.gle/jkjeZnNBunzKHvp69 ማሳሰቢያ መጠይቆችን ሞልተው ሲጨርሱ Submit የሚለዉን መጫንዎን እንዳይረሱ
❤40👍22🙏4👏2🤔1
" ጳጕሜን ቢቀር በኢትዮጵያዊ ማንነት ፣ ታሪክ፣ እምነት እና ባህል ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ይኖረዋል"#መጋቤ ብሉይ # ወሐዲስ አባ አትናቴዎስ፡- ሐመር መጽሔት መስከረም በ፳፻፲፰ ዓ.ም የጥያቄዎቻችሁ ዐምድ ✍️
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦# መስከረም ፳፻፲፰ ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፱ # መስከረም ፳፻፲፰ ዓ.ም መልእክት #ዘማኅበረ ቅዱሳን " #እርሱ ጊዜያትንና #ዘመናትን ይለውጣል"በሚል በመልእክት ዐምዷ ታስነብባለች።
.#ዐውደ ስብከት ሥር”#የምነቅፍብህ ነገር አለኝ" በሚል ርእስ ዛሬ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምንማረው እንዳንሳሳት፤ የምንመከረው በክፉ ሥራችን እንዳንጎዳ እንደሆነ ሁሉ የምንነቀፈውና የምንገሠፀው ደግሞ በክፉ ሥራችን ምክንያትከሚመጣብን ከእግዚአብሔር ተግሣፅ እንድንድን ፣ዛሬ ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎታችን ያራቀንን ምክንያት ስንጠየቅ ሥራ በዝቶብኝ፣ከምኖርበት አካባቢ ርቄ፣አዲስኑሮ መስርቼ፣የማጠናው ትምህርት ፋታ አልሰጥ ብሎኝ እያልን እንናገራለን እንጂ ቤተ ክርስቲያንን እንዴት ማገልገል እንደሚገባው ለምን እንደሚያገለግል ለተረዳ ሰው እነዚህ ነገሮችከቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ከአገልግሎትም አይለዩትም፡፡ ከክርስቲያኖች ኅብረት፣ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎትየመራቃችን ምክንያቱ ልንገልጠው ያልወደድነው ልንለየው ፈቃደኛ ያልሆንበት ደካማ ጎናችን እንደሆነ ታስነብባለች።

❤23🙏4
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#የዘመኑ ዑደት " በሚል ዐቢይ ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ #ደጀኔ #ሺፈራው አዲሱን ዓመት እንዴት ማክበር እንዳለብን ሰፊ ትምህርት ቀርቦበታል። እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍስሓየሚሰጠን ትምህርተ ሃይማኖትሐመር መስከረም ፳፻፲ ዓ.ም. የትናንቱን ስሕተታችን አርመን በጎ ምግባርእንድንሠራበትነው፡፡ የተጣላን እንድንታረቅበት የበደልን እንድንክስበት ነው። የታረዘን እንድናለብስበት የተጠማን እንድናጠጣበት የተራበንእንድናበላበት መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቀስ ትምህርት ይሰጣል ።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “# የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአኃት አብያተ ክርስቲያን ምን ትማር? በሚል በዲ/ን ዶ/ር #ታደለ ኦርቶዶክሳዊነት ምንድነው? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ጉዞዋ ምን ገጠማት? አኀት አብያተ ክርስቲያን የሚባሉት እነማን ናቸው?ስለምን አኃት ተባሉ? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያን ምን ታስተምር? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአኀት አብያተ ክርስቲያን ምን ትማር? የሚሉ ተያያዥ ነጥቦችን በዝርዝር ያሳያል ።
• #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በክርስትና ሕይወት:
ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች _ክፍል ፩
"በሚል ርእስ ማኅበራዊ ሚዲያ ይዞት የመጣው እጅግ በርካታ ጥቅም ቢኖርም የራሱ የሆነ አሉታዊ ጎኖችም እንዳሉት በአመክንዩ ያሳያል ፡፡ ከእነዚህ አሉታዊ ጎኖች የመጀመሪያው የአእምሮ ጤና መታወክ ነው፡፡በማኅበራዊ ሚዲያ እና በአእምሮ ጤንነት መካከል ያለው ግንኙነት ውስብስብ ነው፡፡ በዘርፉም ብዙ ጥናቶች ተካሂደዋል፡፡
ማኅበራዊ ሚዲያ በተለይ በወጣቶች ላይ ዘርፈ ብዙ የሥነ ልቡነ ቀውስ ሊያሰከትል ይችላል፡ የመንፈስ ጭንቀት፣ ድብርት፤ ራስን ከሌሎች ጋር አላስፈላጊ ውድድር ውስጥ ማስባት፣ ሁልጊዜ ራስንትክክል አድርጎ የማሰብ፤ ወዘተ በዋናነት የሚጠቀሱ የሥነ ልቡና ቀውሶች እንደሚጠቀሱ በአጽንዖት ታሰተምራለች።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “ ቅዱስ ማማስ " በሚል ርእስ ልደትና ዕድገቱን፣በመጨረሻም በሰይፍ ተቆርጦ በሰማዕትነት ማረፉን ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “ "ኦርቶዶክሳዊ ወጣትነት "ክፍል ሁለት በሚል ርእስ ስለ ሃይማኖት በሚገባ ለማወቅና መልስ ለመስጠት የወጣትነት ዕድሜ ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ታስነብባለች።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "# ሲሳይ የመጨረሻው ክፍል "በሚል ታስነብባለች ።
• #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “ወርኃ ጳጉሜን # ክፍል ፩ " በሚል ርእስ #“«ወርኃ ጳጕሜን»በተመለከተ ለተነሡ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠበትን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔት የ፬ቱ ጉባኤያት የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህርና የዝዋይ ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የቦርድ አባል የሆኑትን መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ #አትናቴዎስን ጋር የተደረገ ጥያቄና መልስ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፱ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
━━━━━༺✞༻━━━━

❤48🙏15👍6
በማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማእከል በመካከለኛው ማስተባበሪያ የዲያቆናት ጉባኤ ተካሄደ ።
ጉባኤው በመካከለኛው ማስተባበሪ እና በአትላንታ ንዑስ ማእከል ተተኪ ትውልድ ክፍል ትብ ብር የተዘጋጀ ነው ፥፥
በጉባኤው ከ፸ በላይ የሚሆኑ ዲያቆናት የተሳተፉ ሲሆን በዲያቆናት የቤተክርስቲያን አገልግሎትና ፈተናዎች ፥ መንፈሳዊ ሕይዎትና እውቀት ዙሪያ ውይይቶች ተካሂደዋል ፥፥
በውይይቱ በአሁኑ ሰዓት የዲያቆናቱን አገልግሎት እየፈተኑ ያሉ ተግዳሮቶች እና የተፈጠሩ መልካም አጋጣሚዎች እንዲሁም የአገልግሎት ዓላማ እና ግብ ፥ በቀጣዩ ዘመን የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ጉዞ የዲያቆናቱ ድርሻ ምን መሆን አለበት የሚሉ እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ተነስተዋል።
ዲያቆናቱ የቀጣይ የቤተክርስቲያኗ ተረካቢ እንደመሆናቸው መጠን ለሌሎች አርኣያ ሁነው ማገልገል እንደሚገባቸውም በውይይቱ አጽንኦት ተሰጥቶታል ።
በአትላንታ መካነ ሕይዎት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ካቴድራል የተካሄደው ይህ ጉባኤ በመካከለኛው አሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች የሚያገለግሉ ዲያቆናት ትውውቅ እና ቅርርብ እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ማሳሰቢያ ተሰጥቶበታል።

❤77👍12🙏3

❤43🙏12👍3