Telegram Web Link
በ2017ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽኝት መርሐ ግብር ተከናወነ።
በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማዕከል በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው ወደ ክፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ ላስመዘገቡ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች የሽኝት እና የአደራ መስጠት መርሐ ግብር ተከናወነ፡፡
መስከረም 18/2018 ዓ.ም በና/ደ/መ/መድኃኔዓለም ገዳምና ካቴድራል ፈ/ጥ/ሰ/ት/ቤት አዳራሽ በተከናወነው የሽኝት መርሐ ግብር ፤ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ት/ት ተቋም ሲገቡ ስለሚጠበቅባቸው አካላዊ እና መንፈሳዊ ዝግጁነት ሰፋ ያለ ሥልጠና የተሰጠ ሲሆን ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ 4ኛ ዓመት ተማሪዎች የልምድ ልውውጥ ተደርጎላቸዋል፡፡ማዕከሉ በአዳማ ከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች የእውቅና እና ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡
በመጨረሻም በከፍተኛ ት/ት ተቋም በሚኖራቸው ቆይታ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው እና ጎን ለጎን በግቢ ጉባኤ የሚሰጠውን መንፈሳዊ ት/ት በመከታተል በሁለት መልኩ የተሳለ ሰይፍ መሆን እንዲችሉ የአዳማ ማዕከል የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት ሙለታ በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡
94🙏19👍7👏5🥰2
የኒቂያ ጉባኤ
መስከረም ፳፪፤፳፻፲፰ ዓ.ም.

የአርዮስ ክህደት በተስፋፋበት በ፫፻፳፭ ዓ.ም የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት የማይቀበሉ መናፍቃን ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ጊዜውም ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ስለነበር ንጉሡ በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሄድ በየአገሩ ለነበሩ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡https://eotcmk.org/a/https://eotcmk.org/a/
33🙏5
The Assembly of the Ecumenical Council at Nicea

At the year 325 A.D., 318 fathers assembled in the city of Nicea, in the days of Emperor Constantine, the righteous Emperor. Among them were the heads of the four Sees and they were: Anba Alexandros, the 19th Pope of Alexandria, who was accompanied by Athanasius, his Archdeacon and private secretary; Estasius, archbishop of Antioch; Macarius, Archbishop of Jerusalem. Sylvestros, archbishop of Rome, because of his old age did not attend and sent two priests in his place.The reason for their assembly was to judge Arius who was a priest in Alexandria. He blasphemed against the Son of God, the Lord Jesus Christ by saying that he was not equal in essence to God, His Father, and there was a time when the Son did not exist.https://eotcmk.org/e/
42🙏4
ማኅበረ ቅዱሳን ለመማር አቅም ለሚያንሳቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

መስከረም ፳፫/፳፻፲፰ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ለመማር አቅም ለሚያንሳቸው ተማሪዎች 1.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የኦርቶዶክሳውያንን ማኅበራዊ ተሳትፎ የሚያጎለብት የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት፣ በማኅበራዊ ግንኙነት የጠነከረ እና የሚደጋገፍ ማኅበረሰብ መፍጠር ማኅበረ ቅዱሳን በሙያ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ዘርፍ ትኩረት አድርጎ ከሚሠራባቸው ግቦች አንዱ ነው፡፡

በዚህም መሠረት ማኅበሩ በየዓመቱ ለመማር አቅም ለሚያንሳቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በያዝነው ዓመትም 1.9 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፉ ከ11 ማእከላት ማለትም ሰቆጣ፣ ወልድያ፣ ደሴ፣ ግልገል በለስ፣ ነቀምት፣ ወላይታ ሶዶ፣ ጂንካ፣ ሻሸመኔ፣ ፍቼ፣ደብረ ብርሃንና አዲስ አበባ ለተመረጡ 2262 ተማሪዎች የተደረገ ሲሆን ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸርም የተሻለ ተደራሽነት ያለው ነው ተብሏል ፡፡

በድጋፍ ርክክብ ወቅት በየማእከላት የሚገኙ የሀገረ ስብከት፣የወረዳ ቤተ ክህነት፣የማኅበረ ቅዱሳን እና የመንግሥት መስሪያ ቤት ተወካዮች በመገኘት ምስጋና እና መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ማኅበሩ ከዚህ ባለፈ ወላጆቻቸውን በሃይማኖታቸው ምክንያት ላጡ ተማሪዎች ወርኃዊ የትምህርት ድጎማ እያደረገ ሲሆን በተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ቀውስ ምክንያት በችግር ላይ ላሉ ወገኖች ጊዜያዊ ማኅበራዊ ድጋፎችንም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
35👍10🙏5
ማኅበሩ ከዚህ ባለፈ ወላጆቻቸውን በሃይማኖታቸው ምክንያት ላጡ ተማሪዎች ወርኃዊ የትምህርት ድጎማ እያደረገ ሲሆን በተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ቀውስ ምክንያት በችግር ላይ ላሉ ወገኖች ጊዜያዊ ማኅበራዊ ድጋፎችንም አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ለዚህ ድጋፍ የተባበሩ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ በጎ አድራጊ ምእመናንን እያመሰገነ ቀጣይ ድጋፎችን ለማድረግ በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
+ ለበለጠ መረጃ ፡- 0984181544/0948506072 መደወል ይችላሉ፡፡
46🙏6👍5👏2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለመመዝገብ እና የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ👉👉https://forms.gle/jkjeZnNBunzKHvp69 ማሳሰቢያ መጠይቆችን ሞልተው ሲጨርሱ Submit የሚለዉን መጫንዎን እንዳይረሱ
28👍12
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአኃት አብያተ ክርስቲያን ምን ትማር?
ሐመር መጽሔት ጥቅምት በ፳፻፲፰ ዓ.ም ዐቢይ ዐምድ ✍️
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦#ጥቅምት ፳፻፲፰ ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በሚዲያ አገልግሎት ተቋም በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት ፴፪ ኛ ዓመት ቁጥር ፲ #ጥቅምት ፳፻፲፰ ዓ.ም መልእክት #ዘማኅበረ ቅዱሳን " #የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች አፈጻጸም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል"በሚል በመልእክት ዐምዷ ታስነብባለች።
.#ዐውደ ስብከት ሥር”#እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ "በሚል ርእስ ታስነብባለች።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#ከብሉይ ኪዳን " በሚል ዐቢይ ርእስ ቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቀስ ትምህርት ይሰጣል ።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “# የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአኃት አብያተ ክርስቲያን ምን ትማር? ክፍል -፪ በሚል በዲ/ን ዶ/ር #ታደለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከአኃት አብያተ ክርስቲያን ምን ትማር? የሚሉ ተያያዥ ነጥቦችን በዝርዝር ያሳያል ።
#ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በክርስትና ሕይወት:
ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች _ክፍል- ፪
"በሚል ርእስ ምን እናድርግ ??
ማኅበራዊ ሚዲያን ለምን ዓላማና እንዴት መጠቀም እንዳለብን በአጽንዖት ታሰተምራለች።
#በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “ሊቁ ቅዱስ ዲዮናስዮስ " በሚል ርእስ ልደት ፣ ዕድገቱና ትምህርቱን ታስቃኛለች ።
28🙏4
2025/10/15 20:14:15
Back to Top
HTML Embed Code: