በምናያት ሀገር ጀርባ የሁላችንም #ማንነት አለ።
ሀገር የምታድገው በህንፃና በመንገድ ሳይሆን #በአስተሳሰብ ነው። ወደድንም ጠላንም ሀቁ ይህ ነው፤ #የከፋ_አስተሳሰብ_እንጂ_የከፋ_ዘመን_የለንም! ዘመን ክፉ አደለም እኛ ስንከፋ ግን ዘመኑ ይከፋል፡፡
መጀመርያ የሰው አስተሳሰብ ይገንባ! (ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር ) ማለት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጲያን ዘለዓለም የሚያኖራትን #ሐሳብ ማምጣት የተሻለች ዓለም፣ የተሻለ የደግነት ሰንሰለት መፍጠር ያስፈልጋል፥ ያኔ ነው ኢትዮጵያ 'ዘለዓለም' ያልነውን ኑሮ የምትኖረው።
- አሁንም አስተሳሰባችን ካልተስተካከለ ዘመኑ ያው ካለፈው ዘመን የተለየ ዘመን አይደለም። አከተመ!!!

መምህራችን ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው ሁለተኛ መልእክቱ ምዕራፍ 13 ውስጥ የጠቀሰልንን ሁልንም የፍቅር ዓይነቶች ተግባራዊ እናድርግ።
➡️"ፍቅር ሁልን ይታገሳል፣" ሰዎችን ሁሉ በትዕግስት ቻል።
➡️"ፍቅር አይቀናም፣" በሌሎች ላይ ላለመቅናት እንለማመድ።
➡️"ፍቅር ራሱን አያስመካም፣" አንድ ሰው ሌሎች ሰዎች ሊያገኙት በሚችሉት ነገር ላይ ሊመካባቸው አይገባም።
➡️"ፍቅር አይታበይም፣" እግዚአብሔር አምላክ ትዕቢተኞችን ስለሚቃውምና ለትሑታን ጸጋን ስለሚሰጥ ትዕቢት አደገኛ ማነቆ ነው።
➡️"ፍቅር ክፉ ነገር አያሳስብም፥" ሰውን የሚወድ ሰው በክፋት አይናገርም በትሕትና እንጂ ልክ ጣፋጭ ውኃ እንደሚያመነጭ ንጽህ ምንጭ።
➡️" ፍቅር ብቻየን ይድላኝ አይሰኝም፣" ሰዎች የሚወድ ሰው ራሱን ወዳድ አይደለም ሌሎችን ይወዳል እንጂ፡እርሱ ለእነርሱ መሥዋዕት ይሆናል ያለውን ሊሰጣቸውም ዝግጁ ነው ራስ ወዳድነት የብዙ ችግሮች ምክንያት ስለሆነ እርሱን ከእናንተ አርቁ።
➡️"ፍቅር አይበሳጭም፣" ብስጭት(ቁጣ) የእግዚአብሔርን ጽድቅ ስለማይሰራ አትበሳጩ።
➡️"ፍቅር ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፣" ሌሎች ሰዎችን የሚጎዳ ውድቀት አይመኝም። ሕሊናቸው ንጹህ ለሆኑ ሰዎች ሁሉም ነገር ንጹህ ነው። ንጹሓን ሰዎች ከራሳቸው ይልቅ ሌሎች ሰዎችን ያስቀዳማሉ።
➡️"ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል ፣"ፍቅር ያለው ሰው ሰዎች ስኬት ወይም ሀብት ወይም ደስታ ወይም ልጆች ወይም በሌሎች እግዚአብሔር በሚሰጣቸው በረከቶች ይደሰታል ።ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ከምያለቅሱም ጋር አልቅሱ።"ሮሜ11፥15
➡️"ፍቅር ሁሉን ይታገሳል ፣" ታጋሽ ሰው ለመሆን ተለማመድ። እጅግ ከባድ የተባሉ ስሕተቶች ላይ ብትወድቅም እንኳን ቁጣህ ፈጥና አትቀጣጠል የሰዎችን ፍቅርና ክብር ታጣለህና። ለመታገስ የሚቻለው ለማፍቀር ሲቻል ነው። ስለዚህ ሁሉንም ነገሮች ሁሉንም ሁኔታዎችና ሁሉንም ሰዎች ያለ ምንም ማማረር ታገሡ።
➡️"ፍቅር ሁሉንም ያምናል፥" ፍቅር ቀላል ነው እንጂ አታላይ አይደለም ፍቅር ጠቢብና አርቆ አሳቢ ነው።ተስፋ የሚያደርገው ለሌሎች ሰዎች መልካምነት ነው ።
➡️" ፍቅር በሁሉ ይጸናል ፣" ከእርሱ ጋር የሕይወት አክሊል ስለሚመጣ ትዕግስትን ተለማመድ። ሌሎች ሰዎችን መቻልም ተለማመድ እነዚህ ሰዎች ችግር ፈጣሪዎች ቢሆንም እንኳ ይህን ስታደርግም ትዕግስትህ መልካም ነገር እንደሚያሰገኝልህ በማወቅ ይሁን።
➡️"ፍቅር ለዘላለም አይወድቅም ፥" የተለያዩ ፈተናዎችና መከራዎች ቢገጥሙም እውነተኛ ፍቅር ፈጽሞ አይወድቅም፡በማንኛውም ፈተና ፊት በጽናት ይቆማል እንጂ: -"ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና ፥........ብዙ ውኃ ፍቅርን ይጠፋት ዘንድ አይችልም ፈሳሾችም አያሰጥሟትም ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይንቁታል።"ምሳ 8፥6-7
#ጸሎት_ንሰሐና _ተምስጦ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
#አቡነ_ሺኖዳ_ሳልሳዊ

📖ኦሪት ዘፍጥረት 2፥1-3📖
1.“ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ።”
#ሠራዊቶቻቸውም : - በውስጣቸው ያሉት ፍጥረታትንም ሁሉ ፈጥሮ ጨረሰ።
🌍 @yemetshaf_qdus_tinat 🌌
2.“እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።”
#ሰባተኛው_ቀን : - ብርሃንና ጨለማ የተለያዩበት ከስነ ፍጥረት የመጀመርያው ቀን(እሁድ) አንስተን አዳም እስከ ተፈጠረበት(አርብ) ያለውን የብርሃንና የጨለማ ዑደት(ዙር፣መፈራረቅ) ብንቆጥር 6ቀን ይሆናል ስለዚህ ሰባተኛዋ ቀን ቀዳሚት ሰንበት (የመጀመርያዋ ሰንበት) በአይሁድ "sabbath" የምትባለዋ ናት።የመጀመርያዋ ሰንበት ወይም ቀዳሚት ሰንበት (በተለምዷዊ አጠራር ቅዳሜ) የመባልዋ ምክንያት #እሁድም ሁለተኛዋ ሰንበት(የክርስቲያን ሰንበት፣ሰንበት ዓባይ፣የጌታ ቀን) ተብላ ስለምትጠራ ነው።ስለዚህ እግዚአብሔር ከመፍጠር ያረፈው በሰባተኛይቱ ቀን ቀዳሚት ሰንበት ላይ ነው።
⏩ @yemetshaf_qdus_tinat ⏪
#ዐረፈ : -በስድስቱ ቀናት ከፈጠራቸው ፍጥረታት ተጨማሪ መፍጠርን #አቆመ #ተወ ማለት ነው እንጂ ፈጣሪ ውጣ ውረድ ድካም የለበትም!!።ይህ ቃል እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ያለው ግንኙነት መገለጫም ነው። እንዴት? በሰባተኛይቱ ቀን ከስራው ሁሉ ዐረፈ ካለ በኋላ ማታም ሆነ ጠዋትም ሆነ አይልም አንድ የዕረፍት ቀን ላይ ነው።ፍጥረቱ የሆነው የሰው ልጅ ደግሞ ወደእርሱ እንዲመጣ(እርሱን እንዲያውቅ) በቃሉም እየኖረ እንዲያመልከው ከፈጣሪው ጋር ህብረት እንዲያደርግ ይፈልጋል።
📜 @yemetshaf_qdus_tinat 📜
እስራኤል ከግብፅ ሲወጡ ለአብርሃም ወደ ማለለት ምድር ይገቡና እርሱን እያመለኩ በመንፈሳዊ ሐሳብ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንዲኖራቸው ነበረ ዓላማው ይህም ለዘለአለማዊው ከእግዚአብሔር ጋር የመኖርን ምሳሌ ነው።በእምነት ቃሉን ሰምተው እየታዘዙት መኖር በመንፈስ ዕረፍቱን መውረስ መካፈል ነው።ነገር ግን ከግብፅ የወጡት ቃሉን ሰምተው አላመኑም ባለመታዘዝ አሳዘኑት ፈጣሪም ከኔ ጋር አንድነት ዕድል ፈንታ የላቸውም አለ።
@yemetshaf_qdus_tinat
⚠️“ነገሬንም ስላልሰሙ፥ በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም፤ ከእነርሱም የናቀኝ ሰው ሁሉ አያያትም፤”— ዘኍልቁ 14፥23
⚠️መዝ94(95)፥10-11 “ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተቈጥቻት ነበር፦ ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ።ወደ #ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ።”
💠ቅዱስ ጳውሎስም ይህን ዕረፍት በዕብራውያን መልእክቱ ሲያብራራው እንዲህ ይላል
👉“ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር #በእምነት_ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ምንም እንኳ ቢፈጸም፦ እንዲህ፦ ወደ #ዕረፍቴ አይገቡም ብዬ በቁጣዬ ማልሁ እንዳለ፥ እኛስ ያመንን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን።ስለ #ሰባተኛው_ቀን በአንድ ስፍራ፦ እግዚአብሔርም በሰባተኛው ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ብሎአልና፤በዚህ ስፍራም ደግሞ፦ ወደ #ዕረፍቴ አይገቡም።እንግዲህ አንዳንዶች በዚያ እንዲገቡ ስለ ቀሩ፥ ቀድሞም የምስራች የተሰበከላቸው ባለመታዘዝ ጠንቅ ስላልገቡ፦ #ዛሬ_ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደ ተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ #በዳዊት ሲናገር፦ ዛሬ ብሎ #አንድ_ቀን እንደ ገና ይቀጥራል(ይወስናል)።” ዕብ4፥1-7
🛐 @yemetshaf_qdus_tinat 🛐
3.“እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።”
#ባረከው_ቀደሰውም : - መልካም ነገር እንዲያስገኝ መልካም እንዲሆን መረቀው ለራሱም ለየው።
#በረከቱም እስራኤላውያን በነቢዩ ሙሴ መሪነት ከባርነት ወጥተው አምላካቸውን አውቀው ህግም በተሰጣቸው ጊዜ ከባርነት ወጥተው ብቻ ሳይሆን ከስጋ ስራም በእግዚአብሔር ስራና ዕረፍት ምሳሌ 6 ቀን ሰርተው በሰባተኛይቱ ቀን እንዲያርፉ ሲታዘዙ፤ከሰማይ ይዘንብላቸው የነበረው መና ለነገው ማሳደር አልተፈቀደላቸውም ለቀኑ በቅቷቸው ካደረ መናው ይበላሻል ለየቀኑም አዲስ የዘነበ ይበሉ ነበር በስድስተኛይቱ ቀን ግን ከዘነበው መና የሁለት ቀን ይሰበስቡና በሰባተኛይቱ ቀን መናም አይዘንብም ያደረውም አይበላሽም አርፈው ይመገቡት ነበር (ዘጸ16)።
📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎📖🕎
ዕብራውያን 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።
¹⁰ ወደ ዕረፍቱ የገባ፥ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፥ እርሱ ደግሞ ከሥራው አርፎአልና።
¹¹ እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።

#ትሕትና
ልቡ አብዝቶ የጸለየውን ያህል በዚህ መጠን ልብ ትሑት ይሆናል፡፡ ትሑት ቢሆን እንጂ ትሑት ካልሆነ የሚለምን፣ የሚማልድ የለም፡፡ ፈጣሪ ጽኑ፣ ክቡር፣ ትሑት፣ ኅዙን፣ ልቡና የጸለየውን ጸሎት አልቀበልም አይልምና፡፡
ልቡናም በመከራ ትሑት ካልሆነ ትዕቢትን መተው አይቻለውም፡፡ ትሕትና መከራን ያርቃልና፤ ሰው ትሑት በሆነ ጊዜ ይቅርታን ያገኛል፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር እንደተሰጠችው ያውቃል፡፡ ያድነኛል ብሎ በማመን ዕውቀት ገንዘብ ያደርጋል፡፡
ሰው ረድኤተ እግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠችው ያወቀ እንደሆነ ያድነኛል ብሎ ያምናል፡፡ የድኅነት መገኛ እንደሆነች፣ የሃይማኖት መገኛ እንደሆነች፣ ከመከራ ማዕበል ሞገድ ከውስጧ የሚያድን ወደብ እንደሆነች፣ በመከራ ድንቁርና ላሉ ዕውቀታቸው እንደሆነች፣ የድኩማን መጠጊያ በመከራ ጊዜ የሚያርፉባት ክንፍ እንደሆነች፣ በጽኑ ደዌ ጊዜ የሚድኑባት ረድኤት እንደሆነች፣ በጭንቅ ጊዜ የሚያርፉባት የሕይወት ተክል እንደሆነች፣በጠላት ፊት የተቃጣ ፍላጻ እንሆነች ያውቃል፡፡
(#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ)

✝ ጋብቻና የሰው ጥንተ ተፈጥሮ - ፩ ✝
አሁን የምናውቀው ዓይነት የመዋትያን ጋብቻ በገነት ውስጥ በነበረው የሰው ልጅ ሕይወት አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ምንም እንኳን ለወደቀው የሰው ልጅ ድጋፍ እንዲኾን እግዚአብሔር የመሠረተው ቢኾንም፥ ከውድቀት በፊት ግን አልነበረም፡፡ እንዲህም ማለታችን በገነት ውስጥ የነበረው ድንግልና አሁን ከምናውቀው ዓይነት ድንግልና እንደሚለይና እጅግ እንደሚልቅ ኹሉ፥ በገነት ውስጥ የነበረው የአዳምና የሔዋን አንድነትም አሁን ከምናውቀው የባልና የሚስት አንድነት የሚለይና እጅግ የሚልቅ ነበር፡፡ በገነት ውስጥ የነበረው የአዳምና የሔዋን አንድነት ምሥጢራዊ አንድነት ነው፡፡ ሔዋን ለአዳም ረዳት ኾና ስትሰ’ጠው፥ አሁን በጋብቻ ውስጥ የምናውቀውን ዓይነት ረዳትነት እንድትሰጠው አልነበረም፡፡ አሁን በምናውቀው ዓይነት ጋብቻ ውስጥ ሚስት ለባሏ ረዳት ከምትኾንባቸው ነገሮች ዋናው ነገር፥ ፍትወት ሲበረታበት በዝሙት እንዳይወድቅ ሸክሙን ማቅለል ነው፡፡ ባልም እንደዚሁ ለሚስቱ! በገነት ውስጥ ከውድቀት በፊት የነበረው የሔዋን ረዳትነት ግን እንደዚህ አልነበረም፡፡ የተሰጠችው እንድታወራው፣ እንድታጽናናው፣ እኩል ክብሩን እንድትጋራ፣ በኹለንተናዋ እርሱን እንድትመስል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በእንተ ድንግልና” በተባለ ተወዳጅ መጽሐፉ ይህን ሲያብራራውም እንዲህ ይላል፡-
“እግዚአብሔር ይህን ዓለም ለጥቅማችን ፈጥሮ ከፈጸመና ዝግጁ ካደረገ በኋላ፥ በመጨረሻ ይህ ዓለም ለእርሱ የተፈጠረለትን ሰውን ፈጠረ፡፡ ከተፈጠረ በኋላም የሰው ልጅ በገነት ኖረ፤ ለጋብቻ የሚኾን ምክንያትም አልነበረም፡፡ ሰው ረዳት ያስፈልገው ነበር፤ ወደ መኖርም መጣች (ተፈጠረች)፡፡ ያን ጊዜም ቢኾን [አሁን የምናውቀው ዓይነት የመዋትያን] ጋብቻ አልነበረም፡፡ ገና [አሁን በምናውቀው መንገድ] አልተገለጠም ነበር፤ ከዚህ ይልቅ ጋብቻ እንደማያስፈልጋቸው ኾነው ይኖሩ ነበር፡፡ የሩካቤ ፍላጎት፣ ፅንስ፣ ምጥ፣ ልጅ መውለድና ኹሉም ዓይነት ሙስና ከነፍሶቻቸው ውስጥ አልነበሩም፡፡ ከንጹህ ምንጭ ጽሩይ ወንዝ እንደሚፈልቅ፥ እነርሱም (አዳምና ሔዋንም) በገነት በድንግልና ውበት ተጽደልድለው ይኖሩ ነበር፡፡”
ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆም እንዲህ ይላል፡-
“ያን ጊዜ [አሁን የምናውቀው ዓይነት] ጋብቻ አልነበረም፡፡ ገና [አሁን በምናውቀው መንገድ] አልተገለጠም ነበር፤ ከዚህ ይልቅ ጋብቻ እንደማያስፈልጋቸው ኾነው ይኖሩ ነበር፡፡ የሩካቤ ፍላጎት፣ ፅንስ፣ ምጥ፣ ልጅ መውለድና ኹሉም ዓይነት ሙስና ከነፍሶቻቸው ውስጥ አልነበሩም፡፡”

✝† ጋብቻና የሰው ውድቀት - ፪ ✝
የሰው ልጅ ከመበደሉ የተነሣ፥ በአዳምና በሔዋን መካከል የነበረው አንድነት ፍጹም ታውኮ ስለ ነበር፣ አዳም “ረዳት ትኹንህ ያልከኝ አሳሳተችኝ” እንዳለው ሔዋንን ዝቅ ሊያደርጋትና ሊተዋት ተቃርቦ ስለ ነበር፥ በቀድሞ ዐዋቂነቱ በመካከላቸው መሳሳብ የሚችሉበትን ተፈጥሮ አብሮ ፈጥሮላቸው ስለ ነበረ አሁን ከውድቀት በኋላ በዚህ መልኩ እንዲሳሳቡና በኪነ ጥበቡ አንድነታቸው እንዲያጸኑበት አደረገላቸው፡፡ አዳም ሚስቱን ሔዋንን የሚወቅሳት የሚነቅፋት ሳይኾን የእርስዋ ባሪያ የሚኾንበት፣ በእርስዋ የሚማረክበት መንገድ አዘጋጀላቸው - አሁን የምናውቀው ዓይነት ጋብቻ! መጽሐፍ ቅዱስ፡- “ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ በሚስቱም ይጣበቃል” የሚለውም ለዚህ ነው (ዘፍ.2፡24)፡፡
ወደ ሰዎች ባሕርይ ዘልቆ የገባው ፍትወት ጨርሶ እንዳያጠፋቸውና እንደ ማረፊያ ደሴት እንዲኾናቸው ብሎም ለአዳምና ለሔዋን ብቻ ሳይኾን ከዚያ በኋላ ተፈጥረው ለሚጋቡ ሰዎች ኹሉ ሩካቤውን አግባብ ባለው መንገድ እግዚአብሔር ባዘጋጀላቸው ደሴት ላይ ዐርፈው ጾራቸውን እንዲያቀሉበት፣ ከማዕበሉ እንዲድኑበት፣ እንደ አዳምና ሔዋን የድንግልና ሕይወታቸውን ጠብቀው መኖር ሳይችሉ ሲቀሩ እንደ እሪያ በቆሻሻ እንዳይወድቁ፣ ባልተፈቀደና ወደ ቀደመ ክብራቸው እንዳይመለሱ በሚያደርጋቸው ቦታ - በዝሙት - ላይ እንዳያከናውኑና ድኁን በኾነ ቦታ (Safe Zone) ላይ እያከናወኑ በሃይማኖት በምግባር እንዲጸኑበት ጋብቻን ሰጣቸው፡፡
ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊም፡-
“የእግዚአብሔር የመጀመሪያ አሳብ እኛ [አሁን በምናውቀው የመዋትያን] ጋብቻና ጥፋት እንድንበዛ አልነበረም፡፡ አዳም በዓመፃ ሥራው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ተላለፈና ስለ አቃለለ ግን [የመዋትያን] ጋብቻ መጣ፡፡ ስለዚህ ከአዳም የተወለዱ ኹሉ በአባታቸው በደል ምክንያት ‘በኃጢአት የተፀነሱ’ ናቸው” በማለት ይህን ይበልጥ ግልፅ ያደርግልናል (መዝ.50፡5)፡፡
ስለዚህም መዋቲነት በገነት ውስጥ ስላልነበረ፥ የመዋትያን ጋብቻም በገነት ውስጥ አልነበረም፡፡ ከኃጢአት የተነሣ ሞት እንደ መጣ ኹሉ ግን፥ ጋብቻም ከሞት የተነሣ መጣ፡፡ “ጋብቻ የመጣው ካለመታዘዝ፣ ከርግማንና ከሞት ነው፡፡ ሞት ባለበት ጋብቻ አለና፡፡ አንዱ የሌለ ከኾነ ሌላውም አይኖርምና” እንዲል፡፡ ከሞት የተነሣ መጣ ማለት ግን ኖስቲካውያን እንደሚሉት “ርኵስ ነው” ማለት አይደለም፡፡
ስለዚህ ጋብቻ፥ የፍትወት እሳት ለሚለበልባቸውና ይህን መቋቋም ለማይችሉ ሰዎች የሩካቤን ፍቃድ የሚሰጣቸው ድኁን ስፍራ ነው፡፡ በምሳሌ ለማስቀመጥ ያህል የዚህ ዓለም ሕይወት በተቀጣጠለ የፍም እሳት እንደ ተነጠፈ ነው፡፡ ስለዚህም ተጋቢዎች በዚህ በተቀጣጠለ የፍም እሳት ላይ እየተራመዱ ቃጠሎውን መቋቋም ተስኗቸው ሊወድቁ ሲሉ ጋብቻ ላይ ያርፋሉ፤ ባል በሚስቱ ሚስትም በባልዋ ዐርፈው ሰማያዊ ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ደናግል ግን ይህን እሳት ተቋቁመው የሚጓዙ ናቸው፡፡
ወዳጄ ሆይ! አንተም ስታገባ፣ አግብተህ ከኾነም ያገባኸው፥ ወደ ቀደመ ልዕልና፣ ወደ መልአካዊ ሕይወት እንድትነሣበት ስለኾነ በአግባቡ ልትኖረው ይገባሃል፡፡ ትነሣበት ዘንድ የተሰጠህን ነገር እንደ ቅቡልና እንደ ዘለዓለማዊ የደስታ ምንጭ አድርገህ የማታየው ከኾነ፥ ትዳርህን በአግባቡ መምራት ይሳንሃል፡፡ በኾነ ባልኾነ ትጨቃጨቃለህ፤ የጽድቅ መንገድህን ታወሳስበዋለህ፡፡

✝† ጋብቻና በብሉይ ኪዳን ዘመናት የነበረው እድገቱ - ፫ †
* በአምስቱ የሙሴ መጻሕፍት - በብሉይ ኪዳን የጋብቻ ትልቁ ዓላማ ኾኖ የምናየው ልጅ መውለድን ነው፡፡ በተለይ አርእስተ አበው በነበሩበት ዘመን ልጅ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ነበር፡፡ ከሦስቱ አርእስተ አበው መካከል በአብርሃምና በያዕቆብ የምናየው ይህንን ነው፡፡
የታሪክ መጻሕፍቱ ላይ ግን ምንም እንኳን በዘመኑ የነበሩት ሰዎች አብዛኞቹ ባይችሉትም ጋብቻ በአበው ከነበረው ደረጃ ጥቂት ከፍ ብሎ በአንድ ባልና በአንዲት ሚስት መካከል ብቻ እንዲከናወን ይፈለግ ነበር፡፡
* በጥበብ መጻሕፍት ደግሞ ልጆችን ከመውለድና ብዙ ሚስቶችን ካለማግባት በተጨማሪ፥ አሁንም ከፍ ብሎ ልጆችን በአግባቡ ማሳደግ የጋብቻ ዓላማ ኾኖ መጥቷል፡፡
**** ጋብቻ በእግዚአብሔርና በእስራኤል ዘሥጋ መካከል ላለው ፍቅር ትእምርት መኾኑ በግልፅ ማስተማር የተጀመረው በነቢያት ዘመን ነው፡፡ በዚህ ዘመን ጋብቻ “ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም” ከሚለውና ልጆችን ከመውለድና በአግባቡ ከማሳደግ በተጨማሪ (ኢሳ.1፡2)፥ እግዚአብሔር እንደ ሙሽራ እስራኤልም እንደ ሙሽሪት ኾነው ቀርበዋል፡፡
ከዚህ ኹሉ ማጠቃለል የምንችለው፥ የመዋትያን ጋብቻ ራሱ ምን ያህል (እስከ ሰዶማዊነት ድረስ) እየወደቀ እንደ ኼደ፣ እስራኤላውያን ትርጕሙንና ለምን እንደ ተሰጣቸው እንዲያውቁት ብዙ ክፍላተ ዘመናት እንደ ወሰደባቸው ነው፡፡ በርግጥ ይህ የኾነበት ዋና ምክንያት ምን እንደ ኾነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የሮሜ መልእክትን በተረጎመበት ዓሥራ አንደኛው ድርሳኑ ላይ እንዲህ ያስረዳናል፡-
“ከክርስቶስ መምጣት በፊት ሰውነታችን ኃጢአት በቀላሉ የሚያጠቃው ነበር፡፡ በሰው ልጆች ላይ ሞት ከተፈረደ በኋላ ቊጥር የሌላቸው ፍትወታትም አብረው ወደ ባሕርዩ ዘልቀው ገብተዋልና፡፡ ከዚህ የተነሣም ምግባር ትሩፋትን ለመያዝ መፋጠን ቀላል አልነበረም፡፡ የሚረዳ መንፈስ ቅዱስ ወይም ኃይል የምትኾን ጥምቀት ገና አልነበሩምና፡፡ በታሰረለት ልጓም መሠረት የማይጓዝ ፈረስ እንዲሁ ወደ መራው እንደሚኼድና ደጋግሞ እንዲወድቅ፥ ምን መሥራት እንዳለባቸውና ምን መሥራት እንደሌለባቸው ይነግራቸው ዘንድ የተሰጠው ሕግም በቃላት ደረጃ ምክር ከመስጠት የዘለለ ኃይል አልሰጣቸውም ነበር፡፡”

ሙሴ ፀሊም ምንኩስናን በጀመረበት ወቅት የአጋንንት ፆር ይበረታበታል ።ወደ አባ መቃርስም ሄዶ አባ አልቻልኩም አላቸው ። አባ መቃርስም የበቁ አባት ናቸውና ከፍ ወዳለ ተራራ ወስደው ወደ ቀኝ እይ ምን ይታይሀል ? አሉት ብዙ መላዕክት አላቸው ። አሁን ደግሞ ወደ ግራ እይ ምን ይታይሀል ? አሉት ብዙ አጋንንት አላቸው ።አየህ ልጄ አንተ ከበረታህ መላዕክቱ ይረዱሀል አጋንንቱ ይሸሹሀል ድል ታደርጋለህ ። ከደከምክ ደግሞ መላዕክቱ ይርቁሀል አጋንንቶቹ ድል ያደርጉሀል አሉት ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ሙሴ ፀሊም በታላቅ ተጋድሎ ተጋድሎ ታላቅ አባት ለመሆን በቃ። ዛሬ እኛም እንደዛው ነን ከበረታን እናሸንፉለን ከደከምን እንሸነፉለን ። ዛሬ ህይወት በትሯን እኛ ላይ በተደጋጋሚ ብታሳርፍብን እኛን ቅርፅ ለማስያዝ ነው ።አስታውስ አንድ የድንጋይ ሀውልት ያንን ቅርፁን የያዘው አናፂው በመዶሻ ስለቀጠቀጠው ነው። አንድ ጠጠር አንስተህ ተራራ ላይ ብትወረውረው ተራራው ምንም አይሆንም ያንን ጠጠር ግን መስታወት ላይ ብትወረውረው መስታወቱ ይሰባበራል። ጠጠሩን በችግር ብንመስለው ችግሮች ወዳንተ ሲመጡ እንደ ተራራው ተቆጣጠራቸው እንጂ እንደ መስታወቱ አትድቀቅላቸው አትሰባበርላቸው ። አንድ የተለኮሰች የክብሪት እንጨት ጭድ ላይ ብትጥላት ጭዱ ይቀጣጠላል ። ያቺን እንጨት ግን ውሀ ላይ ብትጥላት ውሀው ያጠፋታል። ወዳጄ አቃጣይ ነገሮች ወደ ህይወትህ ሲመጡ እንደ ጭዱ አትቀጣጠልላቸው እንደ ውሃው አጥፉቸው ። አንድ ካፒቴን ብቃቱ የሚታየው ማዕበል ሲመጣበት ነው ። አንተም ብስለትህ የሚታየው በህይወትህ ውስጥ በሚመጣብህ መከራ ነው ። ችግሮች እንደ ኮፍያ ካንተ በላይ አታርጋቸው ይልቁንስ እንደ ጫማ ሶል ከእግርህ በታች አድርጋቸው ። መከራ ፈጣሪ ሰውን ወደ ራሱ የሚጎትትበት ገመድ ነው ። እግዚአብሔርን ይዞ ያፈረ የለም። "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው" ተብሎ ነው የተፃፈው ። ደሞም አስታውስ እንዲህም ተብሎ ተፅፏል "እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላቹ " ። ስለዚህ ወዳጄ በርታ
አባ ጳኩሚስ በሚኖሩበት ገዳም የሚኖር አንድ መነኩሴ ነበር ። ያ መነኩሴም በተደጋጋሚ በዲያቢሎስ ፆር እየተሸነፈ ተቸገረ ። በአንድ ሀጢያት ሲወድቅ ሄዶ ለገዳሙ አበምኔት ይነግራቸውና መክረው ይሉኩታል ። አሁንም ይወድቅና ሄዶ መክረው ይልኩታል። አሁንም ሲወድቅ ተቆጡት እንዴት እንዲ ትሆናለህ ብለው ገሰፁት ። ያም መነኩሴ እንደውም ለምን ምንኩስናውን ትቼ በአለም አልኖርም ብሎ ገዳሙን ለቆ ልብሱን ይዞ ሊወጣ ሲል አባ ጳኩሚስ ያገኙትና ምነው ልጄ አሉት ። እሱም የተፈጠረውን ሁሉ ይነግራቸዋል ። እሳቸውም በል ተመለስ በአሁኑ ታሸንፈዋለህ ይሉታል። እሱም እሺ ብሎ ተመለሰ። አባ ጳኩሚስም ወደ ባዕታቸው ገብተው ጌታ ሆይ የዚን መነኩሴ ፆርና ህመም ወደኔ ገልብጠው ብለው ይፀልያሉ ። የአንድ ቀፎ ንብ ከአንድ ቀፎ ወደ ሌላ ቀፎ እንዲገለበጥ እንዲሁ የሱ ፆርም ወደሳቸው ይገለበጣል። አባ ጳኩሚስም አጋንንቶቹን አሁን የፀሎት ሰአት ነው እንፀልይ እያሉ ሲፀልዩ ምንጣፍ አንጥፈው ደግሞ አሁን ደሞ የስግደት ሰአት ነው እንስገድ እያሉ ሲሰግዱ አጋንንቶቹ እራሳቸው በቃን እንሂድ አሉ ። ጳኩሚስም ምነው አትቆዩም ሲላቸው የአዳምን ስጋ ለብሶ እንዳንተ በትህትና ድል ያረገን የለም ብለው ጠፉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያ መነኩሴ በተደጋጋሚ የወደቀበት ፆር ጠፉለት። እስቲ ዛሬ እኛ እራሳችንን እንይ በጓደኛችን ፣ በወንድማችን ፣ በስራ ባልደረባችን ፣ በጎረቤታችን ፆር ሲወድቅ እንዴት ብለን ተቆጪ ነን ወይስ በሱ ድክመት ላይ ወደ ፈጣሪ እንፀልይለታለን ? አንተ ማትፈተንበት ነገር አንዱ ይፈተንበት ይሆናል ። አንተ ያለፍከውን አንዱ ይወድቅበት ይሆናል ፡ ላንቺ የቀለለሽ ለሷ ከብዷት ይሆናል ፡ ላንቺ ምንም የሆነው ለሷ ተራራ ሆኖባት ይሆናል ። አንዳችን በአንዳችን ድክመትና ውድቀት ከምንወጋገዝ ድካማችንን በፀሎት ብንተጋገዝ መልካም ነው ። ፈጣሪ ለሁላችንም የሰውን ድካም የምንረዳበት ልቦና ይስጠን።
በመፅሀፈ መነኮሳት ላይ ታሪካቸው የሚገኝ አንድ አባት የበቁ አባት ነበሩ። ከሰውነታቸው ብርሃን ይወጣ ስለነበር ሰው ፀጋቸውን አወቀ ። እሳቸው ግን በዚ ደስተኛ አልነበሩም ።ስለዚህ ፀጋቸውን ለመደበቅ ሰው እንዳያገኛቸው ቀን ቀን መውጣት አቁመው ማታ ማታ ለመውጣት ወሰኑ ።ከዛ ሰው ሲተኛ እኩለ ለሊት ላይ ሲወጡ ከሳቸው ላይ ከሚወጣው ብርሀን የተነሳ ሰው ነጋ እያለ መውጣት ጀመረ ። እግዚአብሔር እንዲ ነው እኛ ትሁት ስንሆን እሱ ፀጋውን ያበዛልናል ። ዝቅ ስንል ከፍ ያረገናል። እኔ እንዲ ነኝ እኔ የእከሌ ልጅ ነኝ ፣እከሌ የተባለው ባለስልጣን ወዳጄ ነው ፣ ካዝናዬ ሙሉ ነው ብሬን ይጭነቀው ምናምን እያልን በብር በባለስልጣን እንዲሁም በሌላ ስንመካና ስንታበይ እንወድቃለን። የዲያቢሎስም የውድቀቱ መጀመሪያ ትዕቢት ነበረች ። ነገር ግን መፅሀፍ እንደሚል ማንም የሚመካ ቢኖር በእግዚአብሔር ይመካ ።አባ ቢሾይ የበቁና ክርስቶስ የሚያናግራቸው አባት ነበሩ። ከእለታት በአንዱ ቀን የገዳሙ መነኮሳት አባ ቢሾይን ክርስቶስ ለኛም ይገለጥልን ዘንድ ንገሩልን ይሏቸዋል ። እሳቸውም እሺ ይላሉ። ማታ ሲፀልዩ ክርስቶስ መጣ ከዛ እሷቸው ጌታ ሆይ ለወንድሞቼ መነኮሳት ተገለጥላቸው አሉት ። ጌታም ቢሾይ ልጄ ነገ በተራራው ላይ በ6 ሰዓት እንደምገለጥላቸው ንገራቸው አላቸውና ተሰወረ ። ቢሾይም ለመነኮሳቱ ነገሯቸው ። ከቀኑ 6 ሰዓት በሆነ ጊዜም መነኮሳቱ ክርስቶስን ለማየት ወደ ተራራ ሲሮጡ አንድ አቅመ ደካማ ሽማግሌ ተራራው ስር ቁጭ ብለው ፡ልጆቼ እባካቹ ጌታን ላየው እሻለውና እኔንም ውሰዱኝ እያሉ ለመኗቸው ። መነኮሳቱ ግን አንተን ይዘን ታዘገየናለህ ሳናየው ታሳልፈናለህ እኛ ቸኩለናል እያሉ እያለፏቸው ሄዱ ። መጨረሻ ላይ አባ ቢሾይ ሲመጡ እነዛ ሽማግሌ አባ ቢሾይን እባክህ ውሰደኝ አሏቸው ። አባ ቢሾይም አቅፈዋቸው ጉዞ ጀምሩ ትንሽ ቆይተውም ሽማግሌው ሰውዬ ከበዷቸው ዝቅ ብለው ቢያዩዋቸው ሽማግሌው ወደ ወጣትነት ተቀየሩእጁና እግሩን ሲያዩት ችንካር አለው ። ደነገጡ ።ክርስቶስ ነው ። ቢሾይ ልጄ እንዳከበርከኝ አከብርሀለው ። ለመነኮሳት ወንድሞችህ ተገልጬ እንደነበርና በንቀታቸው ምክንያት እንዳለፍኳቸው ንገራቸው ። አጠገባቹ ያለውን ሳትወዱና ሳታከብሩ እኔን እንወድሃለን እናከብርሀለን ብትሉ ፍቅራቹ ውሸት ነው በላቸው ብሎ ክርስቶሰ ተሰወረ ።ሰውን ስናከብር ፈጣሪ ያከብረናል ሰው የፈጣሪ አምሳል ነውና ።
† የጋብቻ እድገት በሐዲስ ኪዳን - ፬ †
በብሉይ ኪዳኑ እድገት ላይ እንዳየነው ጋብቻ በዘመናት ኺደት እያደገ መጥቷል፡፡ ሐዲስ ኪዳን ሲቃረብ ደግሞ የበለጠ እጅግ ከፍ አለ፡፡ የሐዲስ ኪዳን ምልክት ኾነው የመጡት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና መጥምቁ ዮሐንስ ደናግል ናቸውና፡፡
ጌታችን ኃይለ ጥምቀትን ከሰጠ በኋላ ደግሞ ፍጹም ተለወጠ፡፡ ቀድሞ በብሉይ ኪዳን ኃይለ ጥምቀት ስላልነበረች በአንዲት ሚስት መጽናት ያቅት የነበረው፥ አሁን ግን አንዲት ሚስትም መተው ወደሚቻልበት ዓቅም አደገ፡፡ እስኪ በዘመናት ከፋፍለን እንየው፡-
ሀ) በመጀመሪያው ክ.ዘ.፡-
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር መጀመሪያ የኼደው ወደ ገዳም ነበር፡፡ በሌላ አገላለፅ የመጀመሪያው የቅድስና መንገድ አድርጎ ያሳየን ድንግልና (ምንኵስና) ነበረ (ማቴ.4፡1)፡፡ ዳግማዊ አዳም እንደ መኾኑም፥ ቀዳማዊ አዳም ሊኖረው ይገባው የነበረውን ሕይወት ኖረ፡፡
በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከቆየ በኋላም፥ አገለግሎቱን የጀመረው በሰርግ ቤት ነው (ዮሐ.2፡1-11)፡፡ በዚህም የድንግልና ሕይወትን መኖር ለማንችል ሰዎች የጋብቻ ሕይወትን ሲባርክልን ነው፡፡
መባረክ ብቻ ሳይኾን ሲያስተምርም እነ ረቢ ሒለልና ረቢ ሻማይ የተለያዩበትን ትርጓሜ ለጠየቁት ፈሪሳውያን አማናዊ ትርጕሙን ሰጣቸው፡፡ ሰዎች በጋብቻ ላይ የነበራቸው እምነት እየተስተካከለ እንዲኼድና እግዚአብሔር ጋብቻን ለሰዎች የሰጠበት ዋና ዓላማ ዓላማቸውን አድርገው እንዲኖሩበት አስተማራቸው፡፡ እንዲህ በማለት፡- “ሙሴ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም” (ማቴ.19፡8)፡፡ “ስለ ልባችሁ ጥንከሬ” ማለትም ስለ በደላችሁ ስለ ኃጢአታችሁ ከዚሁ የተነሣም ስለ መድከማችሁ ሲል ነው፡፡ ባል ሚስቱን ሲጠላት ልቧን እያሸ የሚገድላት ስለ ኾነ ሴቲቱም ባሏን ስትጠላው መርዝ አጠጥታ ሥራይ አብልታ የምትገድለው ስለ ኾነች፥ ከሚገዳደሉ እንዲለያዩ ፈቀደላቸው፡፡ አሁን ግን ይህ ተከለከለ፡፡ ፍቺ፣ ዝሙት ፈጽሞ የማይቻል ኾነ፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ መልእክታትን በተለይም የቆሮንቶስንና የኤፌሶን መልእክትን ስናያቸው ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ቢቻል ቢቻል ሰው ኹሉ እንደ እርሱ ድንግል እንዲኾን አስተማረ፡፡
ራሱን መግዛት የማይችል፣ የዝሙት ጠንቅ ያለበት ግን እንዲያገባ ፈቀደለት፡፡ ይህ ያገባ ሰውም ግን ቢያገባም አንድ ሰው ሳይርበው እንደማይበላ፣ ሳይጠማው እንደማይጠጣ፣ እንቅልፉ ሳይመጣ እንደማይተኛው ባለ ትዳርም ምንም እንኳን የሚያርፍበት አስተማማኝ ቦታ ያለው ቢኾንም፥ ፈቃዱ ሳያስቸግረው እንዲሁ እንዳገኘው ሩካቤ እንዳይፈጽም አስተማረው፡፡ ለጸሎት ሲተጉ፣ ሲጾሙ ይህን እንዳያደርጉ በስምምነት እንዲከላከሉ አዘዛቸው፡፡ ጸሎት የሌለበት ጊዜ ስለሌለም በተዘዋዋሪ ቢቻል ቢቻል አግብተውም ቢኾን ወደ ድንግልናዊ ሕይወት እንዲያድጉ መከራቸው፡፡ ሚስት ያለችው ሚስት እንደሌለቺው ይኹን አለ፡፡ ዝሙትንና ፍቺንም እጅግ አጥብቆ ተጸየፋቸው፡፡
ለ) ከ2ኛው-5ኛው መ.ክ.ዘ.
በዚህ ዘመን ውስጥ ጋብቻ እጅግ ከፍ ወዳለ ደረጃ ያደገበት ነው፡፡ ከኹለተኛው ሦስተኛው ከሦስተኛውም አራተኛው መ.ክ.ዘ. ጋብቻ እጅግ ከፍ ወዳለ ደረጃ ያደገበት ነው፡፡ ድንግልናና ጋብቻና ኹለቱ የቅድስና መንገዶች - በቅዱስ አትናቴዎስ አጠራርም “ኹለቱም ጸጋዎች” - በተለይም በአራተኛው መ.ክ.ዘ. እጅግ የተመነደጉበት ነው፡፡ የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት ጥንቱንም የነበረ ቢኾንም በቀጰዶቅያ አባቶች ይበልጥ እንደ ተብራራ ኹሉ፥ የድንግልናና የጋብቻ ትምህርትም ይበልጥ የተብራራው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ የድንግልና ሕይወት ወደ ምንኵስና ያደገው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ የድንግልና ሕይወት መምራት ያልቻለው ደግሞ የጋብቻ ሕይወቱን ትንሽዋ ቤተ ክርስቲያን በማለት በትንሽዋ ቤተ ክርስቲያን በሚያደርጋቸው አገልግሎቶች ድኅነቱን እንዲፈጽም የተደረገው በዚህ ጊዜ ነው፡፡
ለዚህ ዋና ምክንያት ተብሎ የሚጠቀሰውም ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ስለ አባ እንጦንስ የጻፈው ገድል ነው፡፡ ገድሉ በጊዜው ወደ ሌሎች ቋንቋዎች መተርጐሙም ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
ሐ) ከ6ኛው-15ኛው መ.ክ.ዘ.
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ የተለያየ ቊጥር የነበረ ሲኾን፥ ለምሳሌ እስከ ሦስተኛው መ.ክ.ዘ. ድረስ ጥምቀትና ቊርባን በይፋ ምሥጢራት ተብለው ይቈጠሩ ነበር፡፡ በአምስተኛው መ.ክ.ዘ. ደግሞ በቅዱስ ዲዮናስዮስ ስም በተጻፈ ጽሑፍ ላይ፥ ከምሥጢረ ጥምቀትና ምሥጢረ ቊርባን ጋር ምሥጢረ ሜሮን ተጨምሮ እናገኘዋለን፡፡ ጥቂት ቆይቶ ደግሞ ምሥጢረ ክህነትን አካትቶት እናያለን፡፡ አሁን ያለውና ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሰባት መኾናቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ የምናገኘው ዓሥራ ኹለተኛው መ.ክ.ዘ. ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ዘመን በታወቀ በተረዳ መልኩ ጋብቻ ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ የኾነበት ጊዜ ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ፥ አሁንም ጋብቻ ወደ ምን ያህል ደረጃ እንዳደገ የሚያስረዳን ነው፡፡
በተለይም እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እነ ዘርዓ ያዕቆብ ስለ ቤተሰብ ሕይወት ያስተማሯቸው ትምህርቶችና ያወጧቸው ዐዋጆች እጅጉን ተጠቃሾች ናቸው፡፡

✝† ጋብቻ ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ - ፭ †
ተደጋግሞ እንደ ተነገረ አሁን የምናውቀው ጋብቻ የሞት ልጅ ነው፡፡ ስለዚህ የኋለኛው ጠላት ሙሉ ለሙሉ ሲወገድ፥ የመዋትያን ጋብቻም አብሮ ያልፋል፡፡
ጋብቻ የተሰጠው ድኅነትን ለመፈጸም፣ በሰዎች ዘንድ ፍጹም አንድነትን ለማምጣት፣ የክርስቲያን ዘር እንዲቀጥልና ይህን ለመሰለ ኹሉ ስለ ኾነና እነዚህ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት ከገባን በኋላ የሚያስፈልጉ ስላልኾኑ፥ ጋብቻ አይኖርም፡፡ ድኅነቱ ስለሚፈጸም፣ አንድነቱ ስለሚመጣና ፍቅሩም ጸንቶ የሚኖር ስለ ኾነ ይህን ለማምጣት ተብሎ የመዋትያን ጋብቻ አይኖርም፡፡
ጋብቻ ብቻ ሳይኾን ከጋብቻ ጋር የተያያዙ ሩካቤ፣ እርግዝናና አምጦ ልጅ መውለድም አይኖሩም፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ ይህን ሲያስረዳንም፡-
“በዚያ ያገቡት ኹሉ በወሊድ ምክንያት ካገኛቸው የርግማን ውጤት ጽኑ ሥቃይ፣ ልጆች በማስገኘት መከራን ከተሳተፉ በኋላ ዕረፍትን ያገኛሉ፡፡ አሁን እነዚያ እያለቀሰች የቀበረቻቸው ሕፃናት እንደ ጠበቶች በኤደን ገነት ተሰማርተው ትመለከታቸዋለች፡፡ በማዕርጋቸው የተመሰገኑ ናቸው፡፡ በውበታቸውም የተደነቁ ናቸው፤ ፍጹም ንጹሃን የኾኑት የመላእክት ወገኖች ይመስላሉ” ይላል፡፡
ያን ጊዜ የሚኖረው ጋብቻ የዳኑ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር የሚኖራቸው ረቂቅና ምሥጢራዊ ጋብቻ ነው፡፡ ያን ጊዜ የሚኖረው ጋብቻ በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን (በምእመናን) የሚደረገው ጋብቻ ነው፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ላይ፡- “የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ፡፡ ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል፡፡ ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና፡፡ እርሱም ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ አለኝ፡፡ ደግሞም፥ ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው አለኝ” ብሎ የገለጠው ይህንን ነው (ራዕ.19፡7-9)፡፡
ለዚህ ሰማያዊ ሰርግ ሲያዘጋጀን የነበረው የመዋትያን ጋብቻ ያልፋል፡፡ ከክርስቶስ ጋር የሚደረገው የኢመዋትያን ጋብቻም ይተካል፡፡ ባለ ትዳሮች በዚህ ምድር በትዳራቸው ውስጥ የተለማመዷቸው ነገሮች፥ ለምሳሌ የቅድስና ሕይወት፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ መዋደድ እጅግ ጥልቀት ይጨምሩና ለዘለዓለም ጸንተው ይኖራሉ፡፡ በዚህ ምድር ላይ እንዲዋሐዱባቸው የተሰጧቸው እነዚህ ነገሮች በላይ በሰማይ ግን ከፍትወት ነጻ ኾነው ተዋሕዶውባቸው ይኖራሉ፡፡ እዚህ በሥጋ ሲዋሐዱ የነበሩ ባለትዳሮች በላይ በሰማይ ግን በነፍሳቸው ይዋሐዳሉ፡፡ የሚዋሐዱት ግን ጥንዶቹ እርስ በእርሳቸው ብቻ ሳይኾን ርስት መንግሥተ ሰማያትን ከሚወርሱት ኹሉ ጋር ነው፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምስት ዓመት በትዳር ከእርስዋ ጋር የነበረው ባሏ ባረፈ ጊዜ መበለት ለኾነችው ሴት መኝታዋን ንጹህ አድርጋ እንድትጠብቀውና ጋብቻዋን እንድታጸና የመከራት፡፡
ወዳጄ ሆይ! ትዳርህ ለዚህ ሕይወት ዝግጁ ካላደረገህ - የሚያድን ሳይኾን ወደ እሳተ ገሃነም የሚወረውር ትዳር ነው፡፡

✝† የኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ዋና ግብ - ፮ †
እስከ አሁን ከውድቀት በፊት ከነበረው የሰው ኹኔታ አንሥተን ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላ እስካለው ጊዜ ድረስ ከጋብቻ አንጻር በጣም በጥቂቱ ተመልክተናል፡፡ ስለዚህስ ከዚህ ተነሥተን የጋብቻ ዋና ግቡ ምንድን ነው ልንል እንችላለን?
ብዙዎቻችን ዘር ለመቀጠል፣ ለመረዳዳትና ከዝሙት ለመጠበቅ ተብለው ስለ ሦስት የጋብቻ ዓላማዎች ሰምተናል፤ አንብበናልም፡፡ ጋብቻ ከተሰጠበት ዋና ዓላማ አንጻር ስናያቸው ግን እነዚህ ያንሱብናል፡፡ ጋብቻ የተሰጠን ወደ ጥንተ ተፈጥሮአችን እንድንመለስበት፥ ከዚያም በላይ እግዚአብሔርን መስለን እንድናድግበት የድኅነት መንገድ ኾኖ ነውና፡፡ ጥንቱን በገነት ውስጥ መባዛት አልነበረም፡፡ ከትንሣኤ ዘጉባኤ በኋላም በመንግሥተ ሰማያት “ብዙ ተባዙ” የለም፡፡
ዳግመኛም፥ ዘር መቀጠል የጋብቻ ዋና ዓላማ ቢኾን ኖሮ በዙሪያችን እንኳን የምናውቃቸው ብዙ መካን ክርስቲያኖች አሉ፡፡ አንዲት ሴት የማረጥ ጊዜ ላይ ስትደርስ በተአምር ካልኾነ በቀር ብዙውን ጊዜ አትወልድም፡፡ ምናልባትም ባል ወይም ሚስት በተለያየ የጤና ችግር ምክንያት ልጅ መውለድ ላይችሉ ይችላሉ፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ፥ በዚህ ዓለም ኑሮ መረዳዳት የጋብቻ ተቀዳሚ ዓላማ ቢኾን “ድኾች” ክርስቲያኖች ምንኛ ምስኪናን ናቸው? አንድ ለአንድ ተወስኖ ሩካቤ መፈጸም የጋብቻ ተቀዳሚ ዓላማ ቢኾን ኖሮስ ከአንዳንድ ክርስቲያን ካልኾኑት ብቻ ሳይኾን ደበኔ ከተባለው ርግብ መሰል ወፍ ምን ብልጫ አለን?
ጋብቻችን በርግጥም ኦርቶዶክሳዊ ነው የሚባለው እነዚህ ኹሉ በዋናው ዓላማ ማለትም ጽድቅን በመፈጸም ሥር ሲኾኑ ነው፡፡ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ፡- “እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው?” ይላል (ሮሜ 3፡1)፡፡ ይህም ከያዝነው አሳብ ጋር አስተሳስረን ስናየው፡- “ክርስቲያን የመኾናችን ብልጫው ምንድን ነው? ክርስቲያን ኾነን የማግባታችንስ? ትዳራችን እንደዚህ ዓለም ሰዎች ልጅ መውለድ ከኾነ ምንድን ነው? ዘማውያንስ እንኳን ይወልዱ የለምን? ደግሞስ ልጅ መውለድ የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ የምናደርግ ከኾነ፥ በተቀደሰ መኝታ ሳይቀር ልጅ ካልተወለደ ሩካቤ ማድረግን እንደ ኃጢአት እንደሚቈጥሩት እንደነ አውግስጢኖስ ትምህርት ማስተማራችን አይደለምን? ልጅ ያልተሰጣቸው ባለትዳሮችስ የትዳርን ዓላማ አይኖሩም ማለት ነውን? ስለ ሰዎች የምናገረውስ ለምንድን ነው? እንስሳት ስለሚወልዱ የትዳርን ዓላማ ተግብረው ይኖራሉ ሊባል ነውን? ከእንስሳት ምንድን ነው ብልጫችን? ከአሕዛብ ከመናፍቃን ምንድን ነው ብልጫችን?” ማለት ነው፡፡
ይልቅስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን፥ ጋብቻን በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ አትማ የምትመሠርትበት ዋና ምክንያት፥ ተጋቢዎች ጋብቻቸው ድኅነታቸውን እንዲፈጽሙበት፣ አንድነታቸውን ወደ መንፈሳዊ አንድነት እንዲያሳድጉበት፣ ኦርቶዶክሳዊ ዘርንም እንዲቀጥሉበት ለማድረግ እንደ ኾነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
በዚህ ፍኖት እንድንጓዝ የአባት እናቶቻችን አምላክ ይርዳን!

✝† ኦርቶዶክሳዊ ትዳር እንዲኖረን የትዳር አጋርን እንዴት እንምረጥ? - ፯ †
የምንኖረው ወይም ለመኖር የምንጥረው ሕይወት በእምነታችን ላይ የተመሠረተ ስለ ኾነ፥ ከዚህ በፊት ባሉት ክፍሎች የተመለከትነው በጋብቻ ላይ ያለን አተያይ ወይም እምነት ኦርቶዶክሳዊ እንዲኾን ማድረግና ኦርቶዶክሳዊ ያልኾኑትን እንድንሰነግል ማድረግ ነው፡፡
በዚህ ክፍል ደግሞ ኦርቶዶክሳዊ ትዳር እንዲኖረን፣ ራሳችንንም የትዳር አጋራችንንም ኾነ ልጆቻችንን የሚያድን በአጭሩ የዘላለም ሕይወትን ማእከል ያደረገ ሕይወት እንድጓዝ ከትዳር አጋር አመራረጥ ጋር ተያይዞ ምን ልናደርግ እንደምንችል እናያለን፡፡
ሀ) ፈቃደ እግዚአብሔር፡-
ፈቃደ እግዚአብሔር ስንል እግዚአብሔር ወድዶና ፈቅዶ እንዲኾን የሚያደርገውንና የሚፈቅደውን ነው፡፡ በባሕርዩ ቸር፣ ደግና ሰውን ወዳጅ እንደ መኾኑም ፈቃዱን ለእኛ መግለጥ ይወድዳል፡፡ ከሥነ ፍጥረቱ አንሥቶ በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በቅዱሳን ሰዎች፣ በአንድያ ልጁ፣ በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንና በሌላው ለእኛ ያደረገውን ኹሉ ያደረገው ለሌላ ሳይኾን ፈቃዱ ምን እንደ ኾነ ለእኛ ለመግለጥ ነውና፡፡ ዋናው የእግዚአብሔር ፈቃድም፥ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ፡- “ሰዎች ኹሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው”እንዳለው፥ የሰው ልጆች ኹሉ መዳንና የዘለዓለም ሕይወት ማግኘት ነው (1ኛ ጢሞ.2፡3-4)፡፡ ከጋብቻ አንጻር ስናየውም፥ የትዳር አጋር አመራረጥ ላይ የምናስቀምጠው መመዘኛና መለኪያ ስሜታችንና ፍላጎታችን ሳይኾን መዳን ነው፡፡
ስለዚህ አንድ ሰው የትዳር አጋር ከመምረጡ በፊት እግዚአብሔርን መጠየቅ ይገባዋል፡፡ የምታድነውን፣ የሚያድናትን የትዳር አጋር እንዲሰጣቸው መጠየቅ ይገባቸዋል፡፡ በመጽሐፈ ጦቢት እንደምናነበው ጦቢያ ሊያገባት የነበረችው ሣራ፡- “ከጥንት ጀምሮ እርሷን አዘጋጅቶልሃል” የተባለላት ናት፡፡ ስለዚህ ወደ ትዳር መግባት ስናስብ ከዘለዓለም አንሥቶ የምንድንባትን፣ የምንድንበትን የትዳር አጋር ያዘጋጀልንን እግዚአብሔርን አጥብቆ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ እኛ በራሳችን መመዘኛ መርጠን እርሱ እንዲያረጋግጥልን ከመለመን ይልቅ እርሱ መጀመሪያ መርጦ እንዲሰጠን ልንጠይቀው ይገባናል፡፡
ለ) ለምን ማግባት እንደምንፈልግ በውል መረዳት
ብዙዎች ወጣቶች ለምን ማግባት እንደሚፈልጉ ሲጠየቁ፡- “እግዚአብሔር ይመስገን! አሁን ትምህርቴን ጨርሻለሁ፤ ጥሩ ሥራም ይዣለሁ፡፡ እንግዲህ ምን ቀረ? ዕድሜዬም እየኼደ ነው፡፡ ስለዚህ ላግባ” ይላሉ፡፡ ይህ ግን የማኅበረሰቡ እይታ እንጂ የእግዚአብሔር እይታ አይደለም፡፡ ማግባት ያለብን ማግባት ካለብንና እንደ እግዚአብሔር አሳብ በዚያ ለመዳን እንጂ ልማዳዊ በኾነ መንገድ መኾን የለበትም፡፡
ሐ) ኃሠሣ
እንደ ዓቅማችን እግዚአብሔርን ከጠየቅንና ለምን ማግባት እንደምንፈልግ በውል ከተረዳን በኋላም መቀጠል የሚኖርብን ወደ ኃሠሣ ነው፡፡ ኃሠሣ ማለት በውስጡ ወደ ጋብቻ የሚያደርስ ዓላማን የያዘና ለዚህም ዓላማ እውን መኾን በተገቢ መንገድ ግንኙነት መመሥረት ማለት ነው፡፡ የዚህ ግንኙነት ዋና ግብ ጋብቻን በማሰብ የሚኾን መጠናናት እንጂ እንዲሁ ወዳጅነትን ለመፍጠር የሚደረግ አይደለም፡፡
ስለዚህ #መጀመሪያ የሚያድን የትዳር አጋርን ለመፈለግ ኦርቶዶክሳውያን ወዳሉበት ቦታ መኼድ፤ መጽሐፍ መግዛት ስንፈልግ ኳስ ሜዳ እንደማንኼድ ኹሉ፥ ኦርቶዶክሳዊ የትዳር አጋርንም ኦርቶዶክሳዊ ባልኾነ ከባቢ ማግኘት አይቻልምና፡፡
ቀጥሎም #በጓደኝነት መጀመር፤ ምክንያቱም ይህ ደረጃ መተጫጨት ስላልኾነ፥ በአንድ ጊዜ ወደ ጋብቻ የሚያደርስ ግንኙነትን መምሥረት አይገባም፡፡ ልናያቸው የሚገቡ ነገሮችን ማየት ይገባልና፡፡
በጓደኝነቱ ያየናቸው ነገሮች ጤናማ ከኾኑም ከዚያ በኋላ በአግባቡ ወደ #መጠየቅ መሸጋገር ይኖርብናል፡፡
የእሺታ መልስ አግኝተን አሁንም በዚህ ደረጃ ልናያቸው የሚገቡን ነገሮች፥ ማለትም ግንኙነታችን ወደ መዳን የሚያደርስ መኾኑን በጥንቃቄ እያስተዋልን አሁንም ጤናማ ከኾነ ግንኙነትን ወደ #ዕጮኝነት ማሳደግ ይገባል፡፡
መ) ልናስወግዳቸው የሚገቡ ነገሮች
አንዳንድ የተሳሳቱ የዕጮኝነት መንገዶች መኖራቸውን ማስታወስ ይገባል፡፡ ለምሳሌ ወላጆቻችን ልጄን ለልጅህ ተባብለው ቃል በመጋባታቸው ቃላቸውን ለማስጠበቅ የሚደረግ፣ በቸገረን ጊዜ የተለያየ እርዳታ ስላደረጉልን ለዚያ እንደ ውለታ ሊያገቡን ሲፈልጉ በውለታ ታስረን መግባት፣ ምናልባት ጥያቄው በምንወዳቸው ሰዎች በኩል ሲቀርብና እኛም እነርሱን ላለማሳፈር ብለን መቀበል፣ “እኔም በሃይማኖቴ አንቺም በሃይማኖትሽ” በሚል የሞኝ ይትብሃል ተይዘን፣ ብዙውን ጊዜ እንደምናስተውለው ወንዱ በሴትዋና በቤተሰብዋ ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል በመዛት “በራሴና በቤተሰቦቼ ላይ ችግር ከሚመጣ እርሱ እንደሚፈልገው ብኾንለት ይሻላል” በሚል፣ ወንዱና ሴትዋ ብቻቸው እንዲሁ ሳይዘጋጁ በዘፈቀደ በመቊረብ፥ ኹለታቸውም በስሜት በሚያደርጉት መሐላ፥ እንዲሁ በዕጣም ጭምር ቃል መግባት፥ እነዚህ ኹሉ ኦርቶዶክሳዊ የዕጮኝነት መንገዶች አይደሉም፡፡ ኃሠሣችንን ወደ ዕጮኝነት ማሳደግ ያለብን እግዚአብሔርን ጠይቀን፣ የትዳር ዓላማ ገብቶን፣ በትዳር ውስጥ ያሉትን ኃላፊነቶች ለመሸከም በሥነ ልቡናም በአካልም በገንዘብም ብቁዎች መኾናችንን መርምረን ሊኾን ይገባል፡፡

✝† እግዚአብሔርን ጠይቄ የትዳር አጋር ካላገኘሁስ? - ፰ †
በመጀመሪያ ደረጃ መረዳት የሚኖርብን፥ ከያዝነው ርእስ አንጻር ወደ ድኅነት የሚያደርሱ መንገዶች ኹለት ብቻ ናቸው - ድንግልናና ጋብቻ! እግዚአብሔር ደግሞ ከድንግልናና ከጋብቻ ሕይወት የትኛው እንደሚያድነን ያውቃል፡፡ “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ ዐውቃለሁ” እንዲል (ኤር.29፡11)፡፡
ስለዚህም አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ካዘጋጀልን መንገድ በተቃራኒ ልንኼድ እንችላለን፡፡ ራሳችንን የመግዛት ችግር ሳይኖርብን እንዲሁ ሰው ሲያገባ ስላየን ወይም ሌላ ሰው ለምን አታገባም/ አታገቢም ስላለን ከሚጠቅመን መንገድ ፈቀቅ ልንል እንችላለን፡፡ በድንግልና የሚድነው ማግባት ከፈለገ፥ በጋብቻ የሚድነውም ከመነኰሰ በራሱ ላይ ዘርፈ ብዙ መከራዎችን ያመጣል፡፡
ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር የሚጠብቀንና የሚጠቅመንን የሚያደርግልን ከቸርነቱ የተነሣ እኛ ሳናውቀው ነው፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚኾነንም ቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ቅዱስ ጳውሎስ የሥጋ መውጊያ ተሰጥቶት ነበር፡፡ ይህ እንዲርቅለትም እግዚአብሔርን ሦስት ጊዜ ለምኖታል፡፡ የእግዚአብሔር መልስ ግን አይኾንም፤ ትታበያለህ የሚል ነበር፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዚሁ በተሰጠው የሥጋ መውጊያ ደስ መሰኘት የጀመረው እግዚአብሔር ምክንያቱን ሲነግረው ነው፡፡
ስለዚህ እኛም ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀን፣ በምክረ ካህን ተጉዘን ሳለ አንዳንድ ጊዜ የትዳር አጋር ያጣን ሊመስለን ይችላል፤ ተስፋም ልንቆርጥ እንችላለን፡፡ ኾኖም ግን ከላይ እንደ ተጠቀሰው እንደ አሳቡ እስከ ተጓዝን ድረስ ካላገኘሁ ብለን መጨነቅ አይኖርብንም፡፡ እግዚአብሔር ያደረገልን የበለጠውን ሊኾን ይችላልና ይህን በአግባቡ አዳምጠን በዚያ መንገድ ንጽህ ጠብቀን ከሴት / ከወንድ ርቀን መኖር ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔርን በአግባቡ እስከ ጠየቅነውና በዚያ እርሱ በሚመራን መንገድ ለመጓዝ እስከ ፈቀድን ድረስ፥ አምላካችን በሚያመለክተን መንገድ መጓዝ ያስፈልጋል፡፡
ምናልባት መመንኰስ ላንፈልግ እንችል ይኾናል፡፡ መረዳት የሚያስፈልገን፥ ምንኵስና ከድንግልናዊ ሕይወት ውስጥ አንደኛውንና ከፍተኛውን እንደ ኾነ፣ ይህን መርጠው የሚኼዱ ክርስቲያኖችም ድንግልናቸውን በልዩ ምልክት - ማለትም በቆብ - ገልጠው አስታውቀው ለሚኖሩት መናንያን መጠሪያ መኾኑን ነው፡፡
በዚህ ረገድ ትልቅ አብነት የሚኾነንም በዓሥረኛው መቶ ዓመት ላይ የነበረው ስምዖን ጫማ ሰፊው ነው፡፡ ስሙ እንደሚያመለክተው ቅዱስ ስምዖን በዚህ ዘመን አነጋገር በጫማ ፋብሪካ ውስጥ ይሠራ የነበረ ሠራተኛ ነው፡፡ ሕይወቱም፥ በድንግልና ያጌጠ፣ በትሕትና ያሸበረቀ፣ የዚህን ዓለም ክብር የናቀ፣ ያለ ማቋረጥ በመጸለይ የተጠመደ፣ ሥራ የሚሠራ ኾኖ ሳለ ነገር ግን ድኾችንንና ጦም አዳሪዎችን በመርዳት በስውር የሚረዳቸው፣ ዕለት ዕለት ቅዱሳት መጻሕፍትን እየተመገበ የሚኖር ኾኖ እናገኘዋለን፡፡
እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ዛሬም ጭምር አሉ፡፡ ከውጭ ለሚያያቸው ሱፍ ለብሰው፣ ከረባት አድርገው የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ከሱፋቸውና ከከረባታቸው ውስጥ ግን የወንጌላዊው ዮሐንስ መታጠቂያ አላቸው፡፡ ሰው ኹሉ ጋሼ፣ አቶ፣ ዶ/ር፣ ኢንጅነር፣ ዲ/ን እያለ ነው የሚጠራቸው፡፡ እነርሱ የሚኖሩት ሕይወት ግን ሌላ ሕይወት ነው፡፡ ቀን ቀን ሲሸከሙ የሚውሉ፥ ማታ ማታ ግን ተሸክመው ያገኙትን ለጦም አዳሪዎችና ለተቸገሩ የሚሰጡ ስዉራን ደናግል ብዙ ናቸው፡፡
ስለዚህ ከአበ ነፍስ ጋር እየተመካከሩ ይህን ሕይወት ለመኖር መጣር እንጂ፥ ዕድልን እያማረሩ መኖር አያስፈልግም፡፡ የሰው ሙሽራ ወይም ሙሽሪት ከመኾን የክርስቶስ ሙሽራ መኾን እጅግ የሚበልጥ፥ ንጽጽር ውስጥም የማይገባ ነውና፡፡

✝† የዕጮኝነት ጊዜዬን እንዴት ላሳልፍ? - ፱ †
ብዙዎቻችን ግንኙታችንን ወደ ዕጮኝነት ስናሳድግ የትዳር ሕይወታችን እጅግ ስኬታማና እንከን የለሽ አድርገን ልንሥለው እንችላለን፡፡ ትዳር በተለይም ኦርቶዶክሳዊ ትዳር ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ አሁን በወጣትነት ዕድሜያችን ላይ ኾነን በልምድም በዕውቀትም የተገደብን ስለምንኾን በስሜት ተወስደን ዋናውን ዓላማ ማእከል ያላደረገ አሳብ ላይ ልናተኩር እንችላለን፡፡ ለዚህ እንደ አንድ ማሳያ የሚኾነውም ለምሳሌ ብዙዎቻችን በዕጮኝነት ጊዜያችን አብዛኛው ጊዜ፣ አብዛኛው ጉልበትና ገንዘብ የሚወጣው ስለ ሰርግ ቀን በማሰብ ነው፡፡ በርግጥ እንዲህ እንድንኾን የሚያደርጉ ብዙ ተፅዕኖዎች አሉ፡፡ ዘመኑ ራሱ ያመጣው የሰርግ አብዮት ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ስለ ኾነ ሰርግ የፋሽን ትርኢት ወደ መምሰል ስላደገ፣ እኛ ተጋቢዎቹ ሳንኾን የካሜራ ቀረፃ የሚያከናውን ሰው የሚመራው ወደ መኾን ስለ መጣ፥ ከዚህ የተነሣ በተለይ እኅቶች ቀረፃው ስለሚከናወንበት ስቱድዮ፣ ስለሚለብሱት ልብስ፣ ስለሚጫሙት ጫማ፣ ስለሚቀቡት ሽቶ፣ ስለሚያደርጉት ሜክአፕ፣ ስለሚኳሉት ኩል፣ ስለሚሠሩት የፀጉር ዲዛይን፣ ስለሚጠሩ ሰዎች ብዛትና ይህን ስለ መሰሉ ነገሮች ነው እጅግ የሚጨነቁት፡፡ ኹላችን ባንኾንም አብዛኞቻችን ወንዶችም ፍቅረኞቻችንን ላለማስኮረፍ ብለን ወደማይወጣበትና ከጋብቻ ዓላማ ፈጽሞ ወደማይገናኝ ምስቅልቅል እንገባለን፡፡ ስለዚህ እንደ ኦርቶዶክሳውያን በዕጮኝነት ጊዜያችን ስለሚከተሉት ነጥቦችና ተያያዥ አሳቦች ብንነጋገር ትዳራችንን ውጤታማ ያደርጓል፡፡
1. ስለ ጋብቻና ምንናቱ፡- ስለ አምስቱ አዕማደ ምሥጢር መማርና በዚያ መሠረት መኖር እንደሚያድን ኹሉ ስለ ጋብቻም አንድ ኹለት ብለን በአግባቡ መማር፣ ማንበብ፣ መወያየት ይገባል፡፡
2. አንዳንድ መንፈሳዊ ተግባራትን በጋራ መለማመድ፡- ለምሳሌ በየቤታችን ኾነንም ቢኾን መጸለይን፣ ምሥጢራት መካፈልን፣ የምግባር የትሩፋት ሥራዎችን መሥራት!
3. ትዳር የሚፈልገውን ኃላፊነት መመርመር፡- በሥነ ልቡና ለምሳሌ ቤተሰብን ወደ ድኅነት ለመምራት፣ ልጅ ሲወለድ አባት እናት ለመኾን፣ ቤተሰባችንን ለማስተዳደር ዓሥራት ለማውጣት የትሩፋት ሥራዎችን ለመሥራት ወላጆቻችንን ለመርዳት በገቢ ረገድ ምን ያህል ዝግጁዎች እንደ ኾንን ማየት ያስፈልጋል፡፡ በእነዚህ ነገሮች ዝግጁዎች እስክንኾን ድረስ የሰርግ ቀን መቁረጥ አያስፈልግም፡፡ መጀመሪያ እኛ መሠራት አለብን፡፡ “ፍቅር ካለ” ተብሎ ዘው ተብሎ የሚገባበት አይደለም ትዳር! “ፍቅር ካለ” የሚባልለትም ብዙውን ጊዜ እውነተኛው ፍቅር ሳይኾን ስሜት ነው፡፡ ስሜት ደግሞ ያው ስሜት ነው፡፡ የረሃብ ስሜት በመብላት እንደሚጠፋ የፍቅር ስሜትም እንደዚያ ነው፡፡
4. በትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ቅራኔዎችን እንዴት ልንፈታቸው እንደምንችል መነጋገር ይገባል፡፡ የቤተሰብ የጓደኛ ጣልቃ ገብነት ቢኖር፣ የሩካቤ አለመጣጣም ቢያጋጥም፣ አንዳችን ላይ የጤና እክል ለምሳሌ አካል ጉዳተኝነት ቢያጋጥም፣ ልጅ ባንወልድ፣ የገንዘብ አያያዝ፣ የትዳር አጋርን አመል አያያዝ፣ ስለ ተግባቦት… ስለ በጣም ብዙ ነገሮች በዚህ ጊዜ ልናወራባቸው የሚገቡን ናቸው፡፡
5. ዕጮኝነት ጋብቻ ስላልኾነ ከሥጋዊ ፈቃዳት እንዴት ራሳችንን ልንጠብቅ እንደሚገባን መነጋገር መተግበር፣ ከአበ ነፍስ አለመራቅ ያስፈልጋል፡፡ ተመራጩ መንገድም ለፈተና በማያጋልጥ ጊዜና ቦታ እየተገናኙ ትንሽዋን ቤተ ክርስቲያን ለማነፅ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
ስለ እነዚህና እነዚህን ስለ መሳሰሉ ነገሮች የምር አሁን የማንነጋገር ከኾነ በኋላ የምር ወደ ትዳር ስንገባ አፍጠው አግጠው የሚመጡ ናቸው፡፡
ስለዚህ ከኃሠሣ ጊዜ አንሥቶ በዕጮኝነት ጊዜ የምር መነጋገር፣ የምር መወያየት፣ የምር መቀራረፅ፣ የምር መደማመጥ ያስፈልጋል፡፡ መጋጨት ያስፈልጋል፡፡ ስንጋጭ ቅራኔያችንን የምንፈታበት መንገድ በኋላ በትዳር ውስጥ ተመሳሳይ ቅራኔ ውስጥ ስንገባ ልምድ ነውና፡፡ ትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ቅራኔዎች ደግሞ ብዙ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከ85 ከመቶ በላይ ጥንዶቹ ብቻቸውን በመነጋገር የሚፈቷቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ በዚህ ረገድ ምርጥ ጊዜ ማሳለፍ ያስፈልጋል፡፡

± መጽሐፍ ቅዱስ ሥዕላትን ይፈቅዳልን ? ±
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ የሚመለከት ሰው እጅግ የተዋቡ የጌታችን ፣ የድንግል ማርያም ፣ የመላእክትና የቅዱሳን ሰዎች ሥዕላት ቤተ መቅደሱን ሞልተውት ያገኛል፡፡ ኦርቶዶክሳዊያን በሥዕላቱ ፊት ዕጣን ሲያጥኑ ፣ መብራት ሲያበሩ ፣ ሲሳለሙና ሲሰግዱ ኦርቶዶክስ ያልሆኑ ደግሞ ‹ይኼ እኮ ጣዖት አምልኮ ነው!› ‹‹በላይ በሰማይ ካለው ፤ በታች በምድርም ካለው ከምድርም በታች በውኃ ካለው የማናቸውንም ነገር ምሳሌ ለአንተ አታድርግ አትስገድላቸው አታምልካቸውም›› ተብሎ በዐሠርቱ ትእዛዛት ላይ ተጽፎ የለምን? ብለው ይከራከራሉ፡፡ (ዘጸ. 20፡4)
በእርግጥም እግዚአብሔር በሰማይም ፣ በምድርም ፣ ከምድርም በታች ባሉ በማናቸውም ነገር የተቀረጸ ምስል አታድርግ ብሎ በግልጥ ማዘዙ ማስተባበያ የሌለው እውነት ነው፡፡ ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይህ ትእዛዝ በግልጥ ተጽፎ ካለ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሰማይ ካሉ የመላእክትን ፣ በምድር ካሉ የቅዱሳን ሰዎችን ሥዕላት ለመቅረጽም ሆነ ለመሳል እንዴት ደፈረች? እውነት ይኼንን በግልጥ የተቀመጠ ሕግ እያየች ሥዕላትን ለማዘጋጀት ምን አነሣሣት? የሚለው ጥያቄ የግድ መመለስ ያለበት ነው፡፡
በቀጥታ ወደ ምላሹ ከመግባታችን በፊት ከዚያው ከኦሪት ዘጸአት ሳንወጣ ጥቂት ምዕራፎችን እንሻገርና እናንብብ፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለው ፡-
‹‹ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ … አንደኛውን ኪሩብ በአንድ ወገን ሁለተኛውን ኪሩብ በሌላ ወገን አድርገህ ሥራ … ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘርጉ ፤ የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ ፤ ፊታቸውም እርስ በእርሱ ይተያያል … እኔም በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ አነጋግርሃለሁ›› (ዘጸ. 25፡18-22)
ልብ አድርጉ ፤ ከአምስት ምዕራፎች በፊት ‹ከሰማይ ፣ ከምድርና ከባሕር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ› ብሎ ለሙሴ ያዘዘው እግዚአብሔር አሁን ደግሞ በሰማይ ካሉ መላእክት መካከል የሆኑትን የኪሩቤልን ሁለት ምስል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ ፣ ክንፎቻቸውን እንዲዘረጉና እንደሚናተፍ ዶሮ እንዲተያዩ አድርጋቸው ፣ እኔም በእነርሱ መካከል አነጋግርሃለሁ አለው፡፡
ከዘጸአት ሳንወጣ እግዚአብሔር አሁንም ለሙሴ እንዲህ አለው ፡-
‹‹መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ አድርግ ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ ይሁኑ›› በማለት ከወርቅ ከተቀረጹት ሁለት ኪሩቤል በተጨማሪ በመጋረጃ ላይ በጥልፍ መልክ ኪሩቤል እንዲሣሉ አዘዘው፡፡ (ዘጸ. 26፡30-31) እግዚአብሔር በሰማይ ካሉት የማንንም ምሳሌ አታድርግ ብሎ ያዘዘውን ትእዛዝ ራሱ የሚጥስ አምላክ ነው ሊባል ይችላልን? ኪሩቤል ‹በሰማይ ካለው ማናቸውም ነገር› ውስጥ አይደሉምን? የተቀጠቀጠ ወርቅስ የተቀረጸ ምስል አይደለምን? ይህን ጥያቄ እንደ ዋዛ መተው እንዴት ይቻላል?
መጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘጸአት ብቻ ቢሆን ሁለት ማስረጃ ጠቅሰን እንተወው ነበር፡፡ ሆኖም መጽሐፉ በዚህ አላበቃም ፤ እግዚአብሔር ‹‹እጅግ ብዙ ጥበብና ማስተዋል በባሕርም እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋት ሠጠው›› ተብሎ የተነገረለት ጠቢቡ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ሲፈጽም ይህንን አደረገ ፡-
‹‹በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ ፤ የኪሩብም አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሌላኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ … ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው›› ይላል፡፡ (1ነገሥ. 6፡23-28)
ጠቢቡ በዚህ አልበቃውም ፤ የቤተ መቅደሱን ግንብ ዙሪያውን ባዶ እንዲሆን አልተወውም ‹‹በቤቱም ግንብ ዙሪያ በውስጥና በውጪ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ›› ይላል፡፡ (1ነገሥ. 6፡29) በአጭሩ ጠቢቡ ሰሎሞን እንደ ሙሴ በመጠን ያነሡ ሳይሆኑ ዐሥር ክንድ የሚረዝሙ ኪሩቤልን ከወይራ ሠርቶ በወርቅ ሲለብጥ ከምድርም አበባና ዘንባባን በቤተ መቅደሱ ምስል አድርጎ ቀረጸ፡፡
‹የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ› የሚለው ቃል የመላእክትን ሥዕልና ቅርጽ የሚከለክል ከሆነ ይህ ሕግ ክብር ይግባውና ሕጉን ባወጣው በእግዚአብሔርና በባሪያዎቹ በሙሴና በሰሎሞን ተጣሰ ማለት ነው፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔር ሕግ ስለእነዚህ ዓይነቶቹ የቅዱሳን ሥዕላት የወጣ ሕግ አልነበረም፡፡ ሕጉ የሚጠናቀቅበት ‹አትስገድላቸው አታምልካቸውም› የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር የከለከላቸው የተቀረጹ ምስሎች አምላኬ ነህ ተብለው ለፈጣሪ የሚገባ የአምልኮ ስግደት የሚሰገድላቸው ጣዖታትን እንደሆነ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ለማንኛውም በእግዚአብሔር የሚያምን ሰው ከሰማይ ከምድር ከባሕር ያሉ ፍጥረታትን በምስል ቀርጾ አምላኬ አንተ ነህ ብሎ እንዳይሰግድ የተከለከለው ክልከላ እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳን መላእክት መቅረጽ አይገባም ለማለት ማስረጃ አድርጎ ማቅረብ የተሳሳተ መሆኑን ራሱ ባለቤቱ ሕጉን ከሠራ በኋላ በዚያው ዘመን የመላእክቱን ሥዕልና ቅርጽ በማሠራት አሳይቶናል፡፡
እዚህ ላይ አንድ ነገር እናስተውል ፤ ከላይ ባየናቸው የቤተ መቅደሱ ውስጥ ሥዕላት በተደጋጋሚ የተሣሉት መላእክት ብቻ ከመላእክትም ኪሩቤል ብቻ ናቸው፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን እንደምናየው ከሙሴ በፊት የነበሩ እንደ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያሉ ቅዱሳን ሥዕላቸው በቤተ መቅደሱ ለምን አልተሣለም? ምናልባት ለቅዱሳን ሰዎች ሥዕል አይገባ ይሆን? ያሰኛል፡፡
አይደለም ፤ እንደሚታወቀው ቤተ መቅደሱ የሰማያት ምሳሌ ሲሆን በሰማያት በልዕልና የሚኖር አምላክ ከሕዝቡ መካከል በረድኤት የሚገለጥበት ሥፍራ ነው፡፡ በቤተ መቅደሱ ያሉት ነገሮች ሁሉም በሰማያት በእግዚአብሔር መንግሥትና ከእግዚአብሔር ጋር ያሉትን ነገሮች የሚወክሉ ናቸው፡፡ ቅዱሳን ሰዎች ሁሉ ጽድቃቸው እንደ መርገም ጨርቅ ሆኖ ወደ ሲኦል በወረዱበት በዚያ በብሉይ ኪዳን ዘመን ከእግዚአብሔር ረድኤት ርቀው በሞት ጥላ መካከል ናቸውና የእግዚአብሔር መንግሥት ምሳሌ በሆነው መቅደስ ውስጥ አልተሣሉም፡፡ በዚያ ቤተ መቅደስ የተሣሉት መላእክት ከመላእክትም ለታቦቱ ዙፋንነት ምሥጢር የሚቀርቡት በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋኑን የሚሸከሙት ኪሩቤል ናቸው፡፡
± ሥዕላት ለምን ይጠቅማሉ? ±
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ሥዕላትን የሰማይ መስኮቶች ይላቸዋል፡፡ በቤተ መቅደስ ቆሞ የመላእክቱን ሥዕል ፣ የሥላሴን ዙፋን ፣ የቅዱሳኑን ኅብረት የሚመለከት ሰው ለአፍታ በሕሊናው ወደ ሰማያት መመሰጥና የላይኛውን ነገር ማሰብ ይችላልና ሥዕላት የሰማይ መስኮቶች ናቸው፡፡ የሚያስደንቀው ሥዕላት ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚበልጡ የእግዚአብሔር ቃል መማሪያዎች ናቸው፡፡ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ሊገነዘብ የሚችለው ወይ ሊያነበው በሚችለው ቋንቋው ተተርጉሞ ሲቀርብለት ነው ፤ አለዚያም ደግሞ ማንበብ የሚችል ፊደል የተማረ ሰው ከሆነ ብቻ ነው፡፡
ሥዕላት ግን ከዚህ መድልዎ የጸዱ አስተማሪዎች ናቸው፡፡ የየትኛው ቋንቋ ተናጋሪ ያለ አስተርጓሚ ሥዕላትን አይቶ ሃሳባቸውን ለመረዳት ይችላል፡፡ ምንም ፊደል ያልቆጠረ ሰው ቢሆንም ሥዕላትን አይቶ መማርና መጠቀም ይችላል፡፡ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ከጌታችን የዕለተ ዓርብ መከራ ሥዕላት ፊት ብናቆማቸው ሁለቱም የጌታችንን ሥቃይ ፣ መውደቁን መነሣቱን ፣ መገረፉንና መሰቀሉን አይተው ያለቅሳሉ፡፡ ያለ ቋንቋ እንቅፋትነት አብረው ሊማሩ የሚችሉት ስብከት የሚገኘው ሥዕላት ላይ ብቻ ነው፡፡ ያልተማረ ሰውም ከሌሎች የማነስ የበታችነት ሳይሰማው እኩል መረ

ዳት የሚችልበት አስተማሪው ቅዱሳት ሥዕላት ናቸው፡፡
የቤተ ክርስቲያን ሐኪሞች (Doctors of the Church) ከሚባሉት አባቶች አንዱ የሆነው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የጌታችንን ስቅለት የሚያሳይ ሥዕልን ባየ ጊዜ የተሰማውን ሲገልጥ ‹‹ይህንን ሥዕል በተመለከትሁ ጊዜ ያለ ዕንባ ልመለከተው አልችልም ፤ ምክንያቱም ሰዓሊው በጥበባዊ መንገድ ታሪኩን ፊቴ ላይ ስላመጣብኝ ነው›› ብሏል፡፡ ይህንን የጎርጎርዮስን ምስክርነት ያየው ዮሐንስ ዘደማስቆ ደግሞ በእንተ ሥዕላት አምላካዊያት (On the Divine Images) በተባለው ጥንታዊ መጽሐፉ ‹‹ሥዕላት እንዲህ ዓይነቱን የቤተ ክርስቲያን ሐኪም እንዲያለቅስ ከረዱት ለአላዋቂ የዋሐንማ ምን ያህል ይረዳቸው ይሆን?›› ብሎ አድንቋል፡፡
ውድ አንባቢ ፤ ሁሉም ሰው እግዚአብሔርን የሚያገለግለው በጸጋው እንደሆነ መቼም ታምናለህ፡፡ የመዘመር ጸጋ ያለው ሰው የክርስቶስን መከራውን የሚገልጽ ዝማሬን ሲዘምር ሰዎች ዝማሬውን ተጠቅመው ከፈጣሪ ጋር በተመስጦ ይገናኛሉ፡፡ ጥሩ የመስበክ ጸጋ የተሠጠው ሰው ደግሞ የጌታን መከራ በርቱዕ አንደበቱ በመግለጽ ሰዎች በሕሊናቸው ወደ ቀራንዮ እንዲገሰግሱ ያደርጋል ፤ ጸሐፊው ደግሞ በብዕሩ መሣሪያነት ሰዎች የጌታን መከራ እንዲያስቡ ያደርጋል፡፡ ሠዓሊስ?
ጥሩ የመሣል ጸጋ ያለው ሰው እንደ ዘማሪው መዘመር ፣ እንደ ጸሐፊው መጻፍ ፣ እንደ ሰባኪው መስበክ ባይችል በተሠጠው ጸጋ የጌታችንን በደም የተለወሰ ፊት ፣ በመስቀል እንደ ቆዳ የተወጠረ ሰውነት በቀለምና በብሩሹ ተጠቅሞ በመሣልና በማሳየት ምስል መከሰትና ሰዎች የተዋለላቸውን ውለታ እንዲረዱ ማድረግ ይችላል፡፡ እንግዲህ ለቤተ ክርስቲያን ሥዕል አያስፈልግም የሚሉ ሰዎች በተዘዋዋሪ እያሉ ያሉት ‹‹ሠዓሊያን በተሠጣቸው ጸጋ አያገልግሉ›› ነው፡፡ (ይኼን ጉዳይ የሠዓሊያን ማኅበር ቢያስብበት ሳይሻል አይቀርም)
የሰባኪ ዓላማው ክርስቶስን በሰዎች ልቦና እንዲሣል ማድረግ ነው፡ ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ‹‹ልጆቼ ሆይ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል›› ብሎ ነበር፡፡ አክሎም ‹‹የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር ፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ ማን አዚም አደረገባችሁ›› ብሎም ገሥፆአቸው ነበር፡፡ (ገላ. 4:19 ፣ 3፡1) ይህ ሁሉ ጥረቱ ሰዎች ክርስቶስንና የመሰቀሉን ነገር በልባቸው እንዲሥሉ ማድረግ ነበር፡፡ በዚህ የሐዋርያው ንግግር ሁለት ነገሮችን መረዳት እንችላለን፡፡ አንደኛው ምጥ እስኪይዘው በሰዎች ልብ በስብከቱ ለመሣል የሞከረውን የክርስቶስ መከራ ሠዓሊ ቢሆን ኖሮ ሥሎ ከማሳየት እንደማይመለስ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በጳውሎስ ትምህርት ሰዎች ጌታን እንደተሰቀለ ሆኖ በልባቸው መሣል (imagination) ከተፈቀደላቸው በልባቸው የሣሉትን የመስቀሉን መከራ የሥዕል ችሎታ ኖሯቸው በወረቀት ላይ ሲያሠፍሩት ኃጢአት ሊሆን አይችልም የሚለውን ነው፡፡
ሥዕልን መከልከል የሠዓሊነትን ጸጋ ለጣዖት አምልኮ እንጂ ለክርስትና የማይሆን ጸጋ ነው እንደማለት ነው፡፡ ‹ሥዕላት ከማስተማሪያነት ያለፈ እግዚአብሔርን ለማምለክ ይውላሉ ወይ?› ከተባለ መልሱ ስብከትና መዝሙር ለአምልኮ አይውልም ወይ ነው፡፡ ሥዕላት ማለት የተሣሉ ስብከቶች ፣ የተሣሉ መዝሙራት ናቸው፡፡ ሠዓሊያንም በቡሩሽ የሚሰብኩና የሚዘምሩ ድምፅ አልባ ሰባኪያንና ዘማርያን ናቸው፡፡
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን በሥዕላት አማካይነት ፈጣሪዋን ታመልካለች ፣ ቅዱሳንን ደግሞ ታከብራለች እንጂ ሥዕላቱን አታመልክም፡፡ በመዝሙር ፈጣሪን ማምለክ ማለት መዝሙርን ማምለክ እንዳልሆነ ሁሉ በሥዕል ፈጣሪን ማምለክም ሥዕሉን ማምለክ አይደለም፡፡ በሥዕላቱ ፊት የምናደርገው ስግደትና አክብሮትም ለሥዕሉ ሳይሆን ለሥዕሉ ባለቤት ነው፡፡ በድርሳነ ሚካኤል ‹አኮ ዘንሰግድ ለረቅ ወለቀለም ወለ ግብረ ዕድ› ‹የምንሰግደው ለወረቀቱ ለቀለሙ ወይም ለሰው የእጅ ሥራ አይደለም› ተብሎ እንደተጻፈው በሥዕሉ ፊት የምናደርገው ነገር ሁሉ የሚመለከተው በሥዕሉ የተወከለውን አካል እንጂ ሥዕሉን አይደለም፡፡
በዓለም ታሪክ እንደሚታወቀው በስምንተኛው ክፍለ ዘመን በክርስትናው ዓለም የሥዕላት ውዝግብ (Icon controvercy) ተነሥቶ ብዙ ደም አፋስሶ ነበር፡፡ ክርስቲያኖች ሥዕላትን የሚያመልኩ (iconolatrilism) እና ሥዕላትን የሚጠሉ (iconoclasm) ሆነው በሁለት ጎራ ተከፍለው ነበር፡፡ በወቅቱ ሥዕል ጠሎቹ ከቄሣሩ ጋር ተመሣጥረው መተኪያ የማይገኝላቸውን ጥንታውያን ሥዕሎች ሲያቃጥሉና በመዶሻ ሲያፈርሱ ነበር፡፡ ቄሣሩም የክርስቶስን ሥዕል በመሬት ላይ አስነጥፎ እየረገጠ ‹እኔ ክርስቲያን ነኝ ይኼን ሥዕል ግን ጌታ ስላልሆነ እረግጠዋለሁ›› እስከማለት ደርሶ ነበር፡፡
የኒቆማድያው እስጢፋኖስ የተባለ አባት በቄሣሩ ፊት ታስሮ በቀረበ ጊዜ በወቅቱ የቄሣር ምስል ይታተምበት የነበረውን መገበያያ ገንዘብ ከመሬት ላይ ጥሎ ረገጠው፡፡ ወታደሮቹ ነገሩን ሳያስተውሉ ‹እንዴት የቄሣርን ምስል ትረግጣለህ› ብለው ሊመቱት ሲቃጡ ‹‹ይህ ቄሣርን የሚወክል ምስል እንጂ ቄሣር አይደለም ስረግጠው ግን ተቆጣችሁኝ ፤ የሰማይና ምድር ንጉሥ የክርስቶስ ምስልን ግን ቄሣራችሁ ሲረግጠው እያያችሁ ክርስቶስ አልተነካም ብላችሁ ዝም ትላላችሁ›› ብሎ ገሥፆአቸዋል፡፡
በዚህ በምዕራቡ ክርስትና የሁለት ጎራ ውዝግብ ያልተሳተፈችው ምሥራቃዊቷ ቤተ ክርስቲያናችን በዚያ ብትኖርም ኖሮ ሁለቱንም ጎራ አትደግፍም ነበር፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያናችን ሥዕላትን አትጠላምም ፤ አታመልክምም፡፡ በሥዕላት የሚከበረው የሥዕሉ ባለቤት ነውና የሚሠጠውም ቦታ እንደተወከለው ባለቤት ማንነት ይወሰናል፡፡ ይህ ውዝግብ ያበቃው በታሪክ ሰባተኛው የአብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ (The seventh ecumenical council) ተብሎ በሚታወቀው ጉባኤ ላይ ቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆን የመሳሰሉ አባቶች ባቀረቡት ሚዛናዊው ኦርቶዶክሳዊ አቋም ነው፡፡
ስለ ሥዕል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረትና አስፈላጊነት ይህችን ታህል ካየን በሥዕላት ተአምር ይፈጸማል ወይ? የሚለውን አጭር ጥያቄ ተመልክተን እንቋጭ፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልሱ ‹‹ጳጳሱ ቅስና አላቸው ወይ›› ብሎ ለጠየቀው ‹‹ተርፏቸው ይናኙታል›› የተባለው መልስ ትዝ አለኝ፡፡ ሥዕላት ተአምር እንደሚሠሩ ከማስረዳት መልሱ ኪሩቤል የተሣሉባት ታቦተ ጽዮን ተአምር ሠርታለች ወይ ብሎ መጠየቅ ይቀልላል፡፡
የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላው ያረፈባቸውን ሕሙማንን ይፈውስ ነበር፡፡ (ሐዋ. 5፡15) የጴጥሮስ ጥላው ያለ ብሩሽ በብርሃን ረዳትነት የተሣለ ሥዕሉ አይደለምን? የጳውሎስስ ልብስ አልፈወሰምን? (ሐዋ. 19፡11) ልብሱስ የጳውሎስ በረከት ያደረበት ጨርቅ አይደለምን? በፈጣሪና በቅዱሳኑ ስም የተሣሉ ሥዕላትም በራሳቸው ኃይል የላቸውም፡፡ በሥዕላት የተወከሉት ቅዱሳን ግን ከፈጣሪ በተሠጣቸው ሥልጣን በሥዕሉ ላይ ተአምር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ከጥቅስ ይልቅ ወዝ የሚፈስሳቸውን የእመቤታችንን ሥዕላት ፣ በሀገራችን ዓመት ጠብቆ በማሕሌት መካከል በከበሮው ምት ትክክል በሥዕሉ ላይ ያለው ፈረስ የሚዘልለው የቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕልን እንድትጎበኙ እንጋብዛለን፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ