Telegram Web Link
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳፬ ~ (24 )

ጊዜው ለአይን እየነሳ ነው። ፅሀይዋ ሌት ግርዶሿን ዘርግታ ከተሰወረች ስአታት አልፈዋል። ወይዘሮ አትጠገብ ቀዳማዊይን እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ እየጠበቀች ነው። ነገር ግን እስካሁን አልመጣም። እነ ማለፊያም " እስካሁን ምን ሆኖ ነው ያልመጣው?አጅሬ እስካሁን አይቆይም ነበር!"አለች። " እኔ ምን አውቃለሁ ይሄ የማይረባ የመናጢ ልጅ አሁን ብቻ ይምጣማ የማደርገውን እኔ ነኝ የማውቀው!የት እንደደበቀው ይናገራል።" አለች ማለፊያም ግራ በመጋባት የምን መደበቅ ነው?ምንድነውየደበቀሽ?"አለች " አንችው ይሄ ንፍጣም የሆነ ልጅ ሰርቶልኛል። ወይኔ ቆይ አሁን አንገቱን ስይዘው ይናገራታል " አለች። " ኧረ ምንድን ነው?ነገሩ ንገሪኔ እንጅ ምንድን ነው ያደረገው?"አለች " የ የተረገመ ልጅ ካርዱን ተቀብሎ ሸሽጎታል መጥቼ ሁሉንም የሱን ጓዝ የሚያስቀምጥበት ቦታ ሁሉ ብፈልግ አጣሁት። ወይ የሆነ ቤት አለዚያ ደግሞ አኔዱ ጋ ሸሽጎት ነው እንጅ እዚህ ቢያኖረው ኖሮ አገኘው ነበር።" አለች። ማለፊያ ራሷን እየነቀነቀች " የሆነ ነገር አስቧል ማለት ነው።" አለች " ምን ሊያስብ ይችላል?"አለች ወይዘሮ አትጠገብ " ለመጥፋት ነዋ መቼም ለመጥፋት ባያስብ ኖሮ ይሄን ያህል ባልደበቀው ነበር። የደበቀው ወደሌላ ሀገር ሄዶ ለመማር ስላሰበ ነው።" አለች " እኮ እንዴት በእግሩ ሊሄድ?መሄጃ ገንዘብ ከየት ያገኛል?" አለች ወይዘሮ አትጠገብ " አዎ እሱም ደግሞ አለ መቼም ቅርብ ቦታ ለመሄድ እነደዚህ አያደርግም ራቅ ብሎ ለመሄድ ደግሞ ብር ያስፈልገዋል። " አለችና " ለማንኛውም እስኪ ገንዘቦቹንም እስካሁን አላመጣም ጓደኛው ሙሉቀንም ቢሆን እስካሁን አልመጣም።ስለዚህ ሙሉቀን እስኪመጣ መጠበቅ አለብን" ብላ ተናግራ ሳትጨርስ ሙሉቀን " ማለፊያ ማለፊያ " ብሎ ተጣራ ማለፊያም የሙሉቀንን ጥሪ እንደሰማች ወጣች። ስትወጣም ሙሉቀን " እንቺ ገንዘቦቹን " አላት " ቀዳማዊይስ?"አለች " አላውቅም አብረን ልናግድ ተስማምተን ነበር የነዳነው ከዛ እሱ ግን ከነዳን በኋላ በየተራ ገንዘቦቹን እየመለስን ስንጫወት ቆይተን እሱ ሊመልስ እንደሄደ በዛው ቀረ። በእጁ ግን ከጧት ጀምሮ የሆነ ወረቀት ነገር ይዞ ነበር። ከዛ እኔም ከአሁን ከአሁን ይመጣል ብየ እየጠበኩ ገንዘቦቹን ስጠብቅ ውይ ይዣቸው መጣሁ" አለ " እና ምንም ነገር አላለህም?" አለች ማለፊያ " ኧረ በጭራሽ ምንም አላለኝም። እኔም በጣም ግራ ገብቶኛል።" አለና የራሱን ገንዘቦች ይዞ ወደ ቤቱ ሄደ። " እናቴ ልጅሽ ጠፍቷል።" አለች " ምን የት ወደየት ነው የሚጠፋው ምንም ልብስ እንኳ አልበሰም አዲሱን ልብሱን እንኳ አልያዘም ያነኑ የክቱን እንደለበሰ ነውኮ" አለች ወይዘሮ አትጠገብ " እሱንማ ያልለበሰው እኛ እንዳናውቅበት ነው። ደግሞ ጥሩ አድርጎ ሸውዶናል ተሳክቶለታልም። ግን ይሄን ሁሉ ነገር ሲያስብ በእርግጠኝነት ለሙሉቀን ያማክረዋል። ሙሉቀን እየደበቀን ነው እንጅ ሁሉንም ነገር ያውቃል።" አለች ማለፊያ ወይዘሮ አትጠገብ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ወደ እነ ሙሉቀን እናት አባት ሄደች። እንደደረሰችም ሙሉቀን ከብቶቹን አስሮ ጨርሶ ወደ ቤት ሊገባ ሲል ደረሰችበት " ልጄን የት ጥለኸው ነው የመጣኸው?ንገረኝ እ የት ነው ያለው?ሁሉንም ነገር እንደሚነግርህ አውቃለሁ አሁን ሁሉንም ነገር ንገረኝ " አለች እየተቆጣች " እኔ በምን አውቃለሁ " አለ ሙሉቀን " የኔ ሌጅ ወደ ሌላ አገር የመሄድ ሀሳብ የለውም ቢኖረውም ኪሱ ላይ ስሙኒ ሳንቲም እንኳ የለውም ስለዚህ ከአንተ ጋር ሳይማከር ምንም ነገር አያደርግም " አለች " አላውቅም ምንም ነገር አለሠማከረኝም ኤጁ ላይ ብቻ የሆነ ወረቀት ነገር ይዟል ።ምንድነው ብየ ላየው ስል አላሳይህም ብሎ አላሳየኝም በቃ ይሄን ነው የማውቀው እቴወይ " አለና ትቷት ወደ ቤት ገባ " ኧረ ወይዘሮ አሰለፈች እያየሽ ነው የልጅሽን ጥጋብና ስርአተቢስነት እኔ ትልቋ ሴትዮ እያወራሁት እረግጦኝ እኮ ገባ ።እንደው ከመቼ ወዲህ ነው አቶ ዲህ የሆናችሁት። አቤት አቤት እናንተ ከፍ ስትሉማ ዱላ ታነሳላችሁ።" አለች ወይዘሮ አትጠገብ በንዴት ፊቷ እየተጨማደደ " ቆይ አታስቢ እኔ አናግረዋለሁ ወይዘሮ አትጠገብ " አለችና የሙሉቀን እናት ወይዘሮ አትጠገብን ሸኘቻት። ወይዘሮ አቴጠገብም በንዴት እየተምሰለሰለች" እንደው ይሄ የፈየል ጨቅላ የሆነ ልጅ ትላንት ተወልዶ እንዲህ ረግጦኝ ይግባ?ፈጣሪ ይርገጥህ" እያለች ሙሉቀንን እያማረረችና እየረገመች ወደ ቤቷ ተመለሰች። ምንም አዲስ ነገር ይዛ እንዳልመጣች የተረዱት እነ ማለፊያ " እናቴ እኔ ግን አንድ ሀሳብ አለኝ መቼም ያ መምህር ደረጄ ከዚህ ቢባረርም እንኳ አርፎ እንደማይተኛና አይኑን ቀዳማዊይ ላይ እንደማይነቅል እናውቃለን ።እናም የሚኒስትሪ ካርድ የሚቀበሉበትን ጊዜ እዚህ በሚያስተምሩት መምህሮቹ አማካኝነት በማጣራትና በማወቅ መጥቶ የሚሳፈርበትን ብር ሰጥቶት ደግሞ ካርዱን እሱ ይዞ ሄዶለት ቀዳማዊይ ደግሞ እንዳይታወቅበት አንድ ሁለት አድሮ እንዲወጣ ተስማምተው ነው የሚሆነው" አለች ማለፊያ " አወ ልክ ናት ማለፊያ " አሉ ሁሉም ።ይሄኔ ወይዘሮ አትጠገብ በጣም እየተናደደች " ርንደው አፈር ብሉ እናንተንስ በደፋችሁ አሁን እናንተ የዛ ጎበዝ ተማሪ የቀዳማዊ እህቶች ናችሁ?"አለችና በንቀት እየተመለከተቻቸው" አይይ ይሄን እንኳ ማስተዋል ያቅታችሁ?ሙሉቀን ያለውን አልሰማችሁም እንዴ?በእጁ ወረቀት ነገር ይዟል ። አሳየኝ ስለውም አላሳይህ አለኝ አለ እያለን እንዴት ጭፍን ብላችሁ አንድ ነገርን ብቻ ታስባላችሁ እንደው አይይ እኔ ያልተማርኩት እንኳ አስተዋልኩ። እንደው እየሄዳችሁ ኤንገር ነው እንዴ እያላችሁ የምትውሉት?በሉ እናንተን በየተራ ብድር ነው የሚሻለኝ ትምህርቱንስ አታውቁትም " አለች
*
" እኔ እምልህ የኔ ልጅ ግን አትጠገብን ዋሽተሀታል አይደል። መቼም እኔን እናትህን አትዋሽም አይደል?ቀዳማዊ ጋር ምንም ያወራችሁት ነገር የለም?" አለች የሙሉቀን እናት ሙሉቀንም ራሱን እያሻሸ " አይ ያለኝ ነገርማ አለ እናቴ ቀዳማዊ ጠፍቷል። ብታይው ያሳዝን ነበር በቃ ሁሉም ነገር ሰልችቶታል። እኔም ሂድ ወደፈለክበት አልኩት " አለ ። ወይዘሮ አሰለፈች የሙሉቀን እናት ትኩር ብላ ተመለከተችውና " መሄጃ ብር ከየት አገኘ ታዲያ " አለች ።ይሄኔ ሙሉቀን ራሱን እያሻሸ ዝም አላት። ወይዘሮ አሰለፈች የሙሉቀን ሁኔታ ስላላማራት ቀስ ብላ ብድግ አለችና የሙክቱን ብር ያስቀመጠችበትን ቦታ አየች። ብሩ የለም ደነገጠች። " ሰጥተኸው ነው?እ አይይ መከራየ አሳፍራ ላከችው ልታስብለኝ ነው። እንደው ምን ይሻለኛል አሁን ሰንበቴና ማመር ልታሳግደኝ ነው ይሄን ያደረከው " አለይና ቀጭን ለበቅ አንስታ ሙሉቀንን እስኪበቃት ገረፈችው ።ሙሉቀንም እንደምንም ቻለው። " እታተይዬ በቃ ኤያየሁኮ ስላልቻለኝ ነው። እኔስ መቼም ግን እሱ በቃ ሕይወት አይደለም እኮ የሚኖረው ስቃይ ነው እንጅ" አለ ሙሉቀን " ደግሞ ዝም በል አታውራ ስራህን አንዴ ሰርተሀል። ይሄን ስርቆትህን ለአባትህ እነግርልህና በደንብ አድርጎ ይገርፍሀል። አንተ ልጅ በጣም እየተበላሸህ ነው ከቀን ወደ ቀን ብለህ ብለህ ደግሞ ከዛች ነገረኛ ሴትዮ ጋር ታነካካኝ። እንደው ምን አድርጌህ ነው ልጄ?አሁን ይሄን ሁሉ ብታውቅ የምታስቀምጠኝ ይመስልሀል?እድሜ ልኳን ልጇን እንደወሰድኩባት ነው የምታምነው ለዚህም ደግሞ መከራየን ነው የምታበላኝ" አለች ወይዘሮ አሰለፈች። " ማን ይነግራታል ምንም አታውቅም እኮ " አለ ሙሉቀን " እንደው ዝም
Corss @BINCJ90
:) ሀና

ምን መሰለህ…አንዳንዴ የወደድናቸው ሰዋች ከእኛ በላይ እሚወዳቸው እና እሚወዱት ሌላ ሰው ይኖራቸዋል…

🥀 @monhappy 🥀
🍂 @BINCJ90 🍂
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳፭ ~ ( 25 )

" እኔ እምልህ የኔ ልጅ ግን አትጠገብን ዋሽተሀታል አይደል። መቼም እኔን እናትህን አትዋሽም አይደል? ቀዳማዊ ጋር ምንም ያወራችሁት ነገር የለም? " አለች የሙሉቀን እናት ሙሉቀንም ራሱን እያሻሸ " አይ ያለኝ ነገርማ አለ እናቴ ቀዳማዊ ጠፍቷል። ብታይው ያሳዝን ነበር በቃ ሁሉም ነገር ሰልችቶታል። እኔም ሂድ ወደፈለክበት አልኩት " አለ ። ወይዘሮ አሰለፈች የሙሉቀን እናት ትኩር ብላ ተመለከተችውና " መሄጃ ብር ከየት አገኘ ታዲያ " አለች ።ይሄኔ ሙሉቀን ራሱን እያሻሸ ዝም አላት። ወይዘሮ አሰለፈች የሙሉቀን ሁኔታ ስላላማራት ቀስ ብላ ብድግ አለችና የሙክቱን ብር ያስቀመጠችበትን ቦታ አየች። ብሩ የለም ደነገጠች። " ሰጥተኸው ነው? እ አይይ መከራየ አሳፍራ ላከችው ልታስብለኝ ነው። እንደው ምን ይሻለኛል አሁን ሰንበቴና ማመር ልታሳግደኝ ነው ይሄን ያደረከው " አለይና ቀጭን ለበቅ አንስታ ሙሉቀንን እስኪበቃት ገረፈችው ።ሙሉቀንም እንደምንም ቻለው። " እታተይዬ በቃ ኤያየሁኮ ስላልቻለኝ ነው። እኔስ መቼም ግን እሱ በቃ ሕይወት አይደለም እኮ የሚኖረው ስቃይ ነው እንጅ" አለ ሙሉቀን " ደግሞ ዝም በል አታውራ ስራህን አንዴ ሰርተሀል። ይሄን ስርቆትህን ለአባትህ እነግርልህና በደንብ አድርጎ ይገርፍሀል። አንተ ልጅ በጣም እየተበላሸህ ነው ከቀን ወደ ቀን ብለህ ብለህ ደግሞ ከዛች ነገረኛ ሴትዮ ጋር ታነካካኝ። እንደው ምን አድርጌህ ነው ልጄ? አሁን ይሄን ሁሉ ብታውቅ የምታስቀምጠኝ ይመስልሀል? እድሜ ልኳን ልጇን እንደወሰድኩባት ነው የምታምነው ለዚህም ደግሞ መከራየን ነው የምታበላኝ" አለች ወይዘሮ አሰለፈች። " ማን ይነግራታል ምንም አታውቅም እኮ " አለ ሙሉቀን " እንደው ዝም በል የሰው ጅል አሁን ይሄ ጉዳይ ጠፍቶ ሊቀር ነው? ነገ ጠዋት ትደርስበታለች ሴትዮዋ እንዴት አይነት ነገረኛና አነፍናፊ እንደሆነች የማውቀው እኔ ነኝ" አለችና ዝም አለች። ሙሉቀንም እናቱ እንደተናደደችበት እንዳዘነችበት ሲያውቅ አንገቱን ደፋ።
*****
ቀዳማዊ አልጋ ይዞ ያደረባት ሴትዮ በጠዋት ቀስቅሳው ወደ አውቶብስ መነሀሪያ ወስዳ የአዲስ አበባ አውቶብስ አሳፍራው ልትመለስ ስትል ቀዳማዊ " እትዬ እንደ እናት ነው የተንከባከቡኝ እግዚአብሔር ይስጥልኝ። በጣም ነው የማመሰግነው " አለ " ችግር የለውም ልጄ አንተ ብቻ ይቅናህ አዲስአበባም ከዚህ አገር የበለጡ ዱርየወች ስለሆኑ ያሉት በጣም ተጠንቀቅ ከቻልክ ትልቅ ሰወች ጋር ጠጋ ብለህ እደር" ብላው ሄደች። ቀዳማዊ እኒህን ደግ እናት በአይኖ ሸኛቸው።
ረዝሙ የህዝብ አውቶብስ የመሀል አገር ተሳፋሪዎቹን ሞልቶ። ሾፌሩ ቦታውን ይዞ የመኪናውን ሞተር አብርቶ መውጫ ሊቆርጥ የሄደውን ረዳቱን መጠባበቅ ጀመረ።ረዳቱም እየተካለበ መጣና " ትላንት መቁረጥ ነበረብኝ በጣም ነው ያጠፋሁት" እያለ በራሱ ይናደዳል።" እና ይሄን ለእኔ ለምን ትነግረኛለህ? ይሄ የኔ ጉዳይ አይደለ ምን አገባኝ" ብሎ ሾፌሩ ይበልጥ እንዲናደድ በነገር ወጋ አደረገውና ሳቀ። ያው የረዳትና የሹፌር ብሽሽቅና መሰዳጀብ የተለመደ ቢሆንም ለቀዳማዊ ግን እንግዳ ነበር። የሚጣሉም መስሎት ሁለቱን እያፈራረቀ ይመለከታቸው ነበር። መኪናው መንገድ ጀመረ። አንዳንዶች ያማትባሉ ገሚሶቹ አይናቸውን ጨፍነው ይፀልያሉ። ቀዳማዊ ደግሞ መስኮቱን ከፍቶ መንገዶቹን የሚታየውን ተፈጥሮ ፍዝዝ ብሎ ማየትን ከሀረጎ ጎዳና ጀመረ። ከደሴ ኮምቦልቻ እነዛ የጦሳ ታናናሾች አስፈሪዎቹ ጠመዝማዛ መንገዶችን አልፈው ብዙም ሳይቆዩ ኮምቦልቻ ደረሱ። የፍቅር ተምሳሌቷ የወሎዎች የውበት ኮከብ ኮምቦልቻ ከብዙ ኢንዱስትሪ ፓርኮቿ ጋ ሆና ገና በማለዳው ተውባ ደምቃ ትታያለች። ከሀርቡ ኬሚሴ አጣዬ ሸዋ ሮቢት ደብረሲና ደብረ ብርሀን እያለ ጠመዝማዛውን መንገድ ጨርሶ አመሻሽ 12 ስአት ላይ አዲስ አበባ ላም በረት የአውቶብስ መናሀሪያ ደርሶ ተሳፋሪዎቹን አወረደ። አዲስ አበባ በምሽት መብራቶቿ አሸብርቃ ልክ እንደ ኒዮርክ፣ ሞስኮ፣ ለንደን፣ ፓሪስ፣ ቤጅንግ፣ ከተሞች እንቁጣጣሽ መስላለች። ቀዳማዊ የሚያያት አዲስ አበባ የተለየች ከተማ ሆነችበት እጁኔ አፉ ላይ ጭኖ ዝም ብሎ በመገረም ይመለከታል። መኪኖች ከሰው በላይ ይርመሰመሳሉ። ሰው ከሰው ላይ እንደ አንደ አዳል በግ እየተላተመ ይተላለፋል። ቀዳማዊይ የሚያደርገው ጠፍቶት ግራ ገብቶት የመኪናው መንገድ ህዳግ ላይ ቆሞ ይታዘባል። አንዳችም ቅያሪ ልብስ ያልያዘው ቀዳማዊ የአዲስ አበባ የመስከረም ነፋስ ብርድ ከወዲሁ ጀመረው። ወደየት ይሂድ የቱንም መንገድ አያውቀውም። ማንንም አያውቅም ። በዚህ ሁነት መሀል ስአቱ እየሄደ በምሽቱ ፈንታ መብራቶች እየደመቁ ሄዱ። ፊት ለፊቱ የታክሲ ረዳቶች ይጠራሉ ። መገናኛ፣ ሾላ፣ ቀበና አራት ኪሎ ፣ ፒያሳ ሌላኛው ደግሞ ሰሚት በአቋራጭ፣ ሌላኛው ደግሞ አያት ጉርድ ሾላ ይላል የቱ ቦታ መሄድ እንዳለበት ግራ ገባው ።ከዛ በመጨረሻ በመጀመሪያው በቀበና አድርጎ ፒያሳ ወደሚሄደው ታክሲ ተሳፈረ ። ታክሲው ምሽት ላይ ስለሆነ ሰው በሰው ላይ ደራርቧል። መገናኛ የሚወርደውን እያስወረደ በሚወርደው ምትክ ሌላ ሰው እየጫነ ታክሲው ጉዞውን ቀጠለ። የእንግሊዝ ኤምባሲን አልፎ የሩሲያ ኤምባሲ ላይ ሲደርስ አንድ ሰው አውርዶ ትንሽ እጅ ዳለፈ ድልድዩ ሳይደርስ ኮከበ ፅባአ ትምህርት ቤት አንድ ሰውየ ታክሲውን አስቆመው " እ የት ነህ አራት ኪሎ ፒያሳ?" አለው ረዳቱ አንገቱን ብቅ አድርጎ ሰውየውም " አወ "ብሎት ገባና የጋቢናው ጀርባ ባለች ወንበር ባልሆነች መቀመጫ ረዳቱ የሚቀመጥባት ቦታ ተቀመጠ። ቀዳማዊይም ብድግ ብሎ " ጋሼ እዚህ ይቀመጡ " አለና ቦታውን ለቀቀለት ።ሰውየውም " አመሰግናለሁ " አለና የለቀቀበት ቦታ ላይ ተቀመጠ። ሰውየውም ቀዳማዊይን ትኩር ብሎ ሲያየው ቀዳማዊ በመስኮቱ አንገቱን ብቅ አድርጎ ይመለከታል።
@BINCJ90
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳፮ ~ ( 26 )


ፒያሳ አያሌው ጋ " ይሄው መጨረሻው አለና "ረዳቱ የመውጫውን በር ስቦ መታ መታ አደረገው ቀዳማዊይም ወጥቶ ዙሪያውን ሲያይ መኪናና ሰው ነው። ሱቆች ካፌዎች ናቸው ። መንገድ ዳር ተኮልኩለው ልብስ ጫማ ልብስ ወደሚሸጡት ሰዎች ጠጋ ብሎ በመቶ ብር ጫማ በ 80 ሱሪ በ30 ብር ደግሞ ቲሸርት በ 90 ብር ደግሞ ሹራብ ነገር ገዝቶ ገጠሬ ላለመምሰል ራሱን አሳመረ። ነገር ግን በልብስ ይደበቅ እንጅ አተያዩ አካሄዱ አነጋገሩ የገጠር ልጅ እንደሆነ ያሳብቃል። ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ካፌዎች የሚገኙባት ፒያሳ አራዳ በየጉራንጉሩ ምግብ ቤት የማይጠፋባት የአራዳዎቹ መነሀሪያ ፒያሳ ምሽቱን አስመልክታ ቀዝቀዝ ብላለች። ምሽቱ ለአይን እየነሳ ሄደ። የሚያድርበትንና የሚበላበትን ማፈላለግ ስለነበረበት ዝም ብሎ ይሄድ ጀመር። በሲኒማ አምፒር ታጥፎ በትሬን ሀውስ ስቴሽን አድርጎ ወደ ላይ ቀጭን መንገዷን ይዞ እንደሄደ አንዲት ጠባብ ቤት ውስጥ ብዙ ባላገር የሚመስሉ የቀን ሰራተኞች ምግብ እየበሉ ሲወጡ አየና ገብቶ ምግብ አዘዘ። በያይነቱን በልቶ ሂሳብ የሚቀበለውን ሰውየ " እዚህ አካባቢ ቤርጎ ይኖራል ወንድሜ?" አለ ቀዳማዊ " አወ አለ ከፍ ስትል የሆነ መጠጥ ቤት አለ እዛ ውስጥ ገብተህ ጠይቃቸው" አለው " እግዚሃብሄር ይስጥልኝ " አለና ቀዳማዊ እሱ ወዳለው አቅጣጫ ሄዶ እንዳለው ገብቶ ጠየቀ ለአንድ አዳር " 50 " ብር ሲለው በጣም ደነገጠ " ወንድሜ መጨረሻ የለውም?" አለ ልጁም ስቆ " ወንድሜ ይሄ እኮ ግብይት አይደለም አልጋ ቤት ነው የሚቀንሰውን ነው የነገርኩህ እምቀንስ ከሆነ ለምን ቀድሜ እጨምርብሀለሁ ዋጋው ይሄው ነው።ከተመቸህ ቁልፍ ልስጥህ ካልፈለክና ካላመንከኝ ደግሞ ሂድና ሌላ ቦታ መጠየቅ ትችላለህ " አለ ቀዳማዊይም ልጁ እንደዛ ሲለው ስላመነውና ደግሞ ስአቱም እየመሸ ስለሆነ በዛ ላይ ያቺ ሴትዮ ያለችው ትዝ ብሎት በዋጋው ተስማምቶ ብሩን ከፍሎ ቁልፍ ተቀብሎ ገብቶ ተኛ። የስፕሪንግ አልጋው ልዩ የሆነ ምቾትን ሰጠው።" ወይ አዲስ አበባ ይቺ ናት? እህ አይ ፈጣሪየ ቸርነትህ እኮ ከዛ ሁሉ መአት አውጥተህ እዚህ አደረስከኝ አይደል? ተመስገን አሁን በዚህ ስአት ከትላንት ጀምሮ እነዛ ሰይጣኖች እያበዱ ነው የሚሆነው። መቼም ሙሉቀንን መቀመጫ ያሳጡታል ግን ደግሞ ምንም አያደርጉትም። ጀግናና አዛኝ ልብ ያላቸው እናትና አባቶች አሉት። ህ እኔ ላይ የሚከፍቱትን አፋቸውን እሱ ላይ እንከፍታለን ቢሉ የሚከተላቸውን ያውቁታል መቼም! ግን ሙሉቀን በምን ቀን ነው አንተን ፈጣሪየ የሰጠኝ? በምን ቀን ይሆን ያንተን ውለታ መቼ ይሆን የምመልሰው ፈጣሪ አደራህን አድለኝ!" አለ ቀዳማዊ ሌሊቱን ሙሉ በሀሳብ እየባነነ አልፎ አልፎ ደግም ተኝቶ እያሸለበ ሊሊቱ ነግቶ በጠዋት ጮራ ተተክቶ ጨለማው ተገፈፈ። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ከየት መጣ ያልተባለ ዝናብ ዘነበ። የመስከረም የአዲስ አመት ስጦታ የሆነው የአዲስአበባ ዝናብ ያለቅጥ መዝነቡን ቀጠለ። ቀዳማዊይም በዝናቡ ምክንያት ከአልጋው ክፍል መውጣት ስላልቻለ ዝናቡ እስኪያባራ ድረስ የቀጣይ ሁኔታውን ቁጭ ብሎ ማሰብ ጀመረ፡ " ብሬ ከማለቁ በፊት ስራ መስራት አለብኝ ምን መስራት እችላለሁ? ትምህርቴስ? ላቋርጥ ነው ማለት ነው? ለነገሩ ምን ማድረግ እችላለሁ? መጀመሪያ ሰርቼ ብር ካጠራቀምኩ በኋላ ያኔ እማራለሁ እስከዛው ግን ጠንክሬ መስራት አለብኝ" አለ ።በዚህ ጊዜ በሩ ተንኳኳ ቀዳማዊ ተነስቶ ሲከፍተው ማታ አልጋ ያስያዘው ልጅ ካሸሪው ነበር። " ደህና አደርክ ወንድም ያው አልጋ መያዝ የሚፈቀደውና በከፈልክበት ብር እስከ አራት ስአት ስለሆነ የሚቻለው አሁን ክፍሉ ሊፀዳ ስለሆነ ወይ ጭማሪ ከፍለህ ያዝ አለያም ያው አልጋው ክፍት መሆን አለበት።" አለው ቀዳማዊይም አይኖቹ እየተርገበገቡ " እ እ እሽ በቃ እለቃለሁ ወንድሜ አሁኑኑ " አለ " ግን ስራ አታገኝልኝም አገሩን አላውቀውም ገና ትላንት መምጣቴ ነው።" አለ " አይይ ወንድሜ አንተ እኮ ገና ልጅ ነህ ለአንተ ምን አይነት ስራ ሊገኝልህ ይችላል? ወይ አስተናጋጅ ምናምን እንዳትሆን እንኳ ገና ህፃን ነህ በዛ ላይ ልምድም የለህም ስለዚህ ዝም ብለህ የሚያስተምርህ ሰው ብታገኝ ጥሩ ነው።" አለ ልጁ እንዴት ማግኘት እችላለሁ? " አለ ቀዳማዊ " እሱማ የትምህርት ቤት ካርድህን ይዘህ የሆነች ወረቀት በኮምፒውተር አፅፈህ ይዘህ ካርድህንና ወረቀት ስታሳያቸው በብርም በምንም ይረዱሀል እንደዛ ብታደርግ ለአንተም የተሻለው ይሄ ብቻ ነው። ለእንደ እኔ ግን አኔተ የፈለከውን ማድረግ ና መምረጥ ትችላለህ!" አለ። ቀዳማዊ ልጁ ያለው ነገር ከብዶታል። እምቢም እሽም ሳይል ዝም አለ።
ቀዳማዊ ብዙ ካወጣና ካወረደ ካሰበ ካሰላሰለ በኋላ እየፈራም እያፈረም የዚህኛውን አመት ትምህርቱን ላለማቋረጥ ሲል ወደ ልመና ውስጥ ልጁ እንዳለው የሆነች የእርዳታ ማሰባሰቢያ ሀሳብ ከወረቀቷ ላይ አፅፎ በየ ቢሮዎች በየ ሱቆች እየገባ መለመን ጀመረ። የአዲስአበባ ሰው ደግና አዛኝ ነው። እንኳን እንዲህ አይነቱን ህፃን ልጅ ልመና ወጥቶ ይቅርና መስራት የሚችል ወጠምሻ ራሱ ለልመና ወጥቶ ሲለምን ያላቸውን ሳይሰስቱ ይሰጣሉ። ካላቸው ወደ ኋላ አይሉም ለዚህም ይመስለኛል የአዲሰ አበባ ጎዳናዎች በለማኝ ተጨናንቀው የሚታዩት " ለማኝና ዝናብ አዲስአበባን አያጣትም ይባላል። ታዲያ ይሄን የአዲስ አበባን ሰው ድክመት እና አዛኝነትና የዋህነት በመገንዘብ አንዳንዶች ያልታመመ ሰው ነጭ ልብስ አልብሰው በየጎዳናውም ይለምናሉ። ታዲያ እውነቶቹ ተረጅወች ተጎጂዎችን ጥርጣሪ የሚጥል ና ለጋሾችንም ሆነ ማህበረሰቡን እንዲጠረጥርና ከእርዳታው እንዲቆጠብም እያደረጉ ነው። በዚህ ሁነት መሀል ሆኖ ቀዳማዊ ለልመና እጆቹንና የልጅነት አይኑን በሰዎች አይን ላይ አንከራቶታል። አንዳንዱ በልጁ ልመና በመናደድ በዚህ እድሜህ ለምን ትለምናለህ አቡሽ? እያሉ እየጠየቁ በሚነግራቸው ነገርም እያዘኑ የቻሉት እየሰጡት አንዳንዶቹ ደግሞ እግዚአብሔር ይስጥህ፣አሏህ ይስጥህ እያሉ ይሸኙታል። ልመና እጅግ ቅስም ሰባሪ ነው። ሰውነትህን አንተነትህን ያሳንሰዋል በራስህ እንድታፍርም ያደርግሀል። ቀዳማዊይም አንገቱን ሰብሮ የያዘውን ማስረጃና የልመና ወረቀቱን ለባለ ሱቆች እያሳየ አስርም አምስትም ሲሰበስብ ውሎ። ያችን የለመናትን ብር ደግም ዱርየ እንዳይወስድበት እየተጠነቀቀ ኪሱ ላይ ያስቀምጣል። በዚህ አካሄድ ውሎውን ሙሉ በፒያሳ አራዳ ህንፃ ሰራተኛ ሰፈር፣ ዶሮ ማነቂያን ሲለምን ውሎ አመሻሽ ላይ አልጋውን ይዞ አደረና በጠዋትም ይህንኑ ስራ ቀጠሎ ዋለ።

@monhappy
@monhappy

@BINCJ90
​​. የፍቅር እምባ
~~

ሁሌም እማስብሽ የፍቅር ንግሥት ነሽ
በአይኔ መስኮት ገብተሽ በልቤ ውስጥ ቀረሽ
ኧረ አኔስ አቃተኝ የፍቅርሽ ክብደቱ
መቀነስ አስቤ ብሮጠው ዳገቱ
ቀንሶ አገኘሁት ስጋየ ውፍረቱ
ቢወርድም ስጋየ በእሙ ፍለጋ
ልቤ ቢታመም በፍቅርሽ አለንጋ
ተስፋ ግን አልቆረጥም ቢመሽም ቢነጋ
ልንገርሽ እማየ የፍቅሬን ብዛት
ጆሮሽን አውሽኝ ለጥቂት ሰአት
አይኖችሽ ያምራሉ ጥርስሽም እንደዛው
የከንፈርሽን ግን መፃፍም አይበቃው
ከሁሉም ከሁሉም እኔን የገዛኝ
የውስጥሽ ውበት ነው ለዚ ያበቃኝ
ውስጥሽ ነው ያሰረኝ ይሄን ሁሉ አመት
አሁንም እኖራለሁ በፍቅሬ ፅናት
እያልኩኝ በተስፋ ሳፈቅርሽ እኖራለሁ
እስክትሆኚ የሌላ ሰው እንከባከብሻለሁ።

@monhappy
@BINCJ90
👨‍💻ስለ ምን ማወቅ ይፈልጋሉ🛰🛰
❤️👄 ስለ ፍቅር💘💍
👅🔞ስለ ወሲብ🔞🔞
🏟⚽️ስለ sport🏆🤾‍♀
🎮🎰ስለ game🎲🎳
🎧🎼ስለ ዘፈን🎙💽
🇺🇸🇯🇵ስለ ፖለቲካ🗼⛲️
🇪🇹🇪🇹ስለ እትዮጰያ🇪🇹🇪🇹
🦍🦃ስለ ተፈጥሮ🦍🦑🐢
⛪️🕌ስለ ሃይማኖት
💻📲ስለ ቴክኖሎጂ🕦🖥
🌋🏔ስለ አስደናቂ ነገር🗿🗽
🍔🍽ስለ ምግብ🍰🍞🍉
👗🎩ስለ ፋሽን👖👚
JOIN
👇👇👇👇👇
@monhappy
@monhappy
@monhappy
ጆ ባይደን አሸነፉ‼️

በ2020 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን አሸንፈዋል፡፡

በዚህም መሰረት ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በአሜሪካ ምርጫ ፕሬዝዳንት ለመሆን ከሚያስፈልገው 270 የመራጮች ድምፅ፣ ጆ ባይደን ከአራት ቀናት በኋላ ነው ዶናልድ ትራምፕን በመብለጥ አሸናፊ መሆናቸው ይፋ የተደረገው፡፡

ዲሞክራቶችን የወከሉት ጆ ባይደን በቀጣይ ለአራት አመታት አሜሪካን በፕሬዚዳንትነት የሚመሩ ይሆናል፡፡
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳፯ ~ ( 27 )


ለአራት ቀናት ያህል እየለመነ ቆይቶ እንደለመደው በአምስተኛው ቀን በጠዋት ተነስቶ ልመናውን በሰባራ ባቡር ከአንድ ትልቅ ህንፃ ውስጥ ገብቶ ጀመረ። ወደ አራት ሱቆች ለምኖ አምስተኛው በር ላይ አንኳኩቶ ገባ። ሲገባ አንድ ጎልማሳ ሰውየ እድሜው ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ ያለ አገኘ ከባለቤቱ ጋ ነበር። ቀዳማዊይም የእርዳታ ወረቀቱን ዘረጋለት " ምንድን ነው? " አለ ሰውየው ቀዳማዊይም አንገቱን አቀርቅሮ " የሚያስተምረኝ ወላጅ ስለሌለኝ የሚረዳኝ ሰው እየፈለኩና ስራ እስካገኝ ድረስ ለማደሪያም ለምግብም እንዲሆነኝ እየለመንኩ " አለ ሰውየውም ቀና ብሎ ቀዳማዊይን ተመለከተው። ባለቤቱ ወረቀቱን ተቀብላ አነበበችው ያው ቀዳማዊ ያለውን ነበር የፃፈው " ሌላ ማስረጃ አለህ?" አለችው። ይሄኔ ቀዳማዊ ፈጠን ብሎ ካርዱን አውጥቶ አሳያት። ካርዱን ተቀብላ ስታየው ደነገጠች። " ኧረ እንካ እየውማ " አለችና ካርዱን ለባለቤቷ ሰጥታው ቀዳማዊይን እንዲቀመጥ በእጇ ምልክት ሰጠችው። ቀዳማዊም ተቀመጠ ። የቀዳማዊይን የሚኒስትሪ ካርድ እየተቀባበሉ ካዩ በኋላ ተደነቁ ።ሰውየውም ስራውን አቁሞ " ማን ወደዚህ አመጣህ" አለ " ማንም ብቻየን ነው የመጣሁት " አለ ቀዳማዊ " ቆይ እናት አባት የለህም?" አለ ሰውየው ።በዚህ ጊዜ ቀዳማዊ እንባው በአይኑ ሞላ ትንሽ ከቆየ በኋላ አለቀሰ። " አይዞህ በቃ አታልቅስ እሽ እኛ እኮ የጠየቅንህ በዚህ እድሜህ መማር ሲገባህ እንዴት በሰው አገር ትንከራተታለህ። ብለን አስበንልህ ነው እንጅ ልናስለቅስህ ወይም ህመምህን ለማስታወስ አይደለም እሽ " አለች " አዎ አንተ ልጅ ነህ እንዴት ወላጅ በዚህ እድሜህ እንድትንከራተት ያደርጉሀል? ብለን ተጨንቀን ስለ አንተ አስበን ነው የጠየቅንህ " አለ ቀዳማዊይም " እኔ መማር ነው የምፈልገው የሚያስተምረኝ ሰው ነው ያጣሁት አባቴ ሞቷል። እኔ አባት የለኝም ብቸኛ ነኝ ምንም ለእኔ የሚያስብ ቤተሰብ የለኝም " አለ እያለቀሰ " እሽ በቃ ገባኝ አታልቅስ እኛ ምን እንድናደርግልህ ትፈልጋለህ?" አለ " እኔ ሌላ አልፈልግም በትርፍ ስአቴ እየሰራሁ በትርፍ ጊዜየ ደግሞ መማር ነው አላማየ እናም የሚሰራ ሰጥታችሁኝ በፈረቃ እየሰራሁላችሁ እንድታስተምሩኝ ወይም የሚያስተምሩ ሰዎች ካሉ እንድታገናኙኝ ነው! " አለ " እምም እሽ በቃ ተረጋጋ እንፈልጋለን " አለውና ቀዳማዊይን ትኩር ብሎ ተመለከተው። እነዛ ነገ የተሻለ ቦታ መድረስ ተስፋ ማየትን የሚመኙ ቡቃያ አይኖችን በስስት ተመለከታቸው። አይኖቹ ላይ እልህና ህልም ጎልተው ይታያሉ።" በል ቁርስ መቼም አልበላህም ቁርስ እስኪ እዘዥለት ሔዋን " አላት አቶ ሙሉ ሰው። ወይዘሮ ሔዋንም አጠገባቸው ከሚገኝ ሬስቶራንት ምግብ ይዛለት መጣች። ቀዳማዊይም ምግቡን በልቶ ሲጨርስ አመስግኖ ትሪውን አስቀመጠ። " በቃ እኔ ቤት ይዤው ልሂድ " አለች ወይዘሮ ሔዋን " አይሆንም ጎረምሳውማ እኔ ጋ ነው የሚሆነው። እኔ ብቻየን ስለሆንኩ ያጫውተኛል። " አለ ሳቅ ብሎ ቀዳማዊይን እየተመለከተ ። " ኧረ? ይሻላል? ጥሩ ።ለምሳ ኑ በቃ ደግሞ ርሳው አሉ። መቼም ምሳ መርሳት ብርቅህ አይደለም። ለነገሩ ዛሬ እንኳ እንግዳ ስላለብህ አትረሳውም" ብላ እየሳቀች ሄደች ።ወይዘሮ ሔዋን በሰላሳዎቹ መጀመሪያ እድሜ ላይ ትገኛለች። ተጫዋችና ሳቂታ ለመሆኗ እንዲሁ ስትታይ ታስታውቃለች። " እሽ ጎረምሳው ታዲያ አዲስአበባን እንዴት አየሀት?" አለ አቶ ሙሉሰው ኮምፒውተሩን እየነካካ " ኧረ ሸጋ አገር ናት ግን መኺናው ሽር ሽር ሲል ያስፈራል እንደው ለሰከንድ እንኳ መንገዱ መች መኺና ይመትራል!" አለ ቀዳማዊ አቶ ሙሉሰውም ሳቅ አለና " ከመጣህ ብዙ ቆየህ እንዴ?" አለ አቶ ሙሉሰው " ኧረ ገና ዛሬ አምስት ቀኔ ነው።" አለ እየተቅለሰለሰ " ኣ በጊዜ ነዋ የተዋወቅነው ማነው ግን ይሄን የተረገመ ልመና እንድትለምን ያነሳሳህ?" አለ " ወዲያው ተገጠር እንደመጣሁ አልቤርጎ ይዤበት የነበረው ቤት ልጅ ነው ተቸግሬ ሲያየኝ ጊዜ ወይ የሚረዳህ ሰው ታገኝበታለህ ወይ ደግሞ ብሩን አጠራቅመህ ትምህርትህን ትማርበታለህ ብሎ ነው" አለ ቀዳማዊ " አይ ቢሆንም ልመና እኮ ጥሩ አይደለም የሰው አይን እንደ እሳት ነው። ሁሌም የማይሽር ጠባሳ ነው የሚሆነው። ከኋላ ሆኖ እንደ ጥላ ነው የሚከተልህ። በዛ ላይ ልጅ ነህ ገና በዚህ እድሜህ የዚህን ሁሉ ሰው እዳ ተሸክመህ እንዴት ብለህ ትዘልቀዋለህ? ስለ ህይወት ብዙ አታውቅም ምክንያቱም ልጅ ነህ አንዱን መንገድ ብቻ ነው የምታየው። ሌላኛውን ሌሎቹን መንገዶች ለመመልከት እድሜህም ገና ነው። የማሰብ ብቃትህም በልጅነትህ ይወሰናል። ያደረጉልህ ሰዎች በኋላ ከአንተ እንደሚወስዱ እንደሚጠብቁ አታውቅም እንጅማ ብታውቅ ኖሮ ወደዚህ አትገባም ነበር። ግን ብቻ እንኳን ብዙም አልቆየህ ምስኪኑ ምንም የማታውቀው ልጅ ሕይወትህ ጥሩ አይሆንም ነበር። ለማንኛውም አይዞህ አሁን ለጊዜው እኛ የምንበላትን እየበላህ የምንጠጣትን እየጠጣህ ከእኛ ጋር ሁነህ መፍትሔ እናፈላልጋለን። ትምህርትም ትመዘገባለህ። ከዛ ቀሪውን ደግሞ የጎደለውን ደግሞ እያየን የምንሞላ ይሆናል። " አለ አቶ ሙሉሰው ቀዳማዊ የሚለው ጠፋበት ነፍሱ በደስታ ተሞላች። " ኧረ ጋሼ ትምህርቴን ብቻ ከተማርኩ ይበቃኛል። ሌላ ምንም አያስፈልገኝም ምንም እንዳትቸገር " አለ ቀዳማዊ " ሃሃሃሃ ምኑን እንቸገራለን ብለህ ነው? ያው ትምህርት ለመማር እኮ ደብተር እስክርቢቶ ምግብ ልብስ ምን ያስፈልጋል። ያው እነዚህ ለአንድ ተማሪ መሟላት ያለባቸው ነገሮች ናቸው። ስለዚህ አታስብ " አለ ሳቅ ብሎ እየተመለከተው " ይኸው ይሄን አራት ቀን ብዙ ሰው ረድቶኛል " አለና የሰበሰበውን ብር እንዳለ አውጥቶ የአቶ ሙሉሰው ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው። አቶ ሙሉ ሰው ቀዳማዊ በምን አይነት የመንፈስ ውጥረት ጭንቀት ሀፍረት እንዳለ በቅፅበት ባደረገው ድርጊት ተገነዘበና ሆዱ ተንሰፈሰፈ በዚህ ህፃን ልጅ እጣፈንታም ከልቡ አዘነለት።
ይቀጥላል

አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ርዳታችሁ ያስፈልገኛል እስኪ በቻላችሁት መጠን ለሌሎች ሼር አድርጉ!
@monhappy
@monhappy
@BINCJ90
:)
የሆነ ቀን እመኚኝ ዝም ብዬ እሄዳለው…ቻው እና ወደዚህ ነው የሄድኩት ሳልልሽ በአንቺም ተስፋ ማድረግ አቁሜ እሄዳለው…እዛኔ ግን ለዘላለም ነው…ለዘላለም…እመቤቴን ያኔ እኔ ተመልሼ አልመጣም…ብትደውይልኝ እና ብትፈልጊኝም አታገኚኝም…ያ ቀን መቼ ነው?…ምን አልባት ነገ…ወይ ከነገ ወዲያ…አልያም የሆነ ቀን…

እንዲህ ይሰማኛል…
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳፰ ~ ( 28 )


ምሳ ስአት ላይ ቀዳማዊይና አቶ ሙሉ ሰው በመኪና ደጃች ውቤ ወደ ሚገኘው ቤታቸው ሄዱ። ገና የመኪናውን ድምፅ ሲሰሙ ሁለቱ ሴት ልጆቹ እየሮጡ ሄደው አቀፉት። አንዷ የሶስት አመት ትልቋ ደግሞ የ ስምንት አመት ልጅ ናት። እየተቀያየሩ ሳሙት " ኧረ ቀስ ጉንጨ እንዳያልቅባችሁ " እያለ ይስቃል። ልጆቹ ግን ዝም ብለው ይሞጨሙጩት ይዘዋል። ቀዳማዊ ቆሞ በፈገግታ ይመለከታቸዋል። ሁኔታቸው ያስቀናል። " በሉ አሁን ደግሞ እሱን ሂዱና ሳሙት" አለ አቶ ሙሉሰው " ትልቋ ልጅ " ማነው እሱ አባየ ዘመዳችን ነው?" አለች ። "አዎ ልጄ የቅርብ ዘመድ ነው ከእኛ ጋር ለመኖር ነው የመጣው።" የሚል ምላሽ ሰጥቷቸው በአባታቸው ትዕዛዝ መሠረት ቀዳማዊይን ሳሙት ና እጁን ይዘው " ና ከእኛ ጋር ግባ " እያሉ ይዘውት ገቡ። ወይዘሮ ሔዋን " መጣችሁ ልክ ምሳ ተዘጋጅቶ ሲያልቅ ነው የመጣችሁት" አለች ። ሰራተኛዋ አሰለፈች የእጅ ውሃ መታጠቢያ አቅርባ ካስታጠበቻቸው በኋላ ጠረንጴዛው ላይ ቁርጥ እንጀራ እንዲሁም የተለያየ አይነት ቀርቦ ሁሉም የሚበቃውን ያህል አንስቶ ከሁሉም ወጥ እየጨመሩ የቀዳማዊ ሳህን ላይ ቁርጥ እንጀራም ወጥም እየጨመሩለት በሉ። በልተው ከጨረሱ በኋላ ቀዳማዊ ተነስቶ እጁን ለመታጠብ ከሳሎን ወጥቶ ወደ ቧንቡሀው ሄደ። በዚህ ጊዜ ትልቋ ልጅ ተከተለችውና " ከዚህ በኋላ የኛ ወንድም ልትሆን ነው አይደል?" አለች " አዎ " አላት " ውይ ታድየ ታጫውተኛለህ ወክ ይዘኸኝ ትሄዳለህ ታስጠናኛለሃ? እንደ እነ አትናሲያ ፣ ሜላት ፣ ምህረት " አለች የጓደኞቿን ስም አንድ በአንድ እየዘረዘረች " አዎ አታስቢ ሁሉንም እናደርጋለን። ጋሼን እያስፈቀድን" አለ ቀዳማዊ " ምን ጋሼ ነው ያልከው? " አለችና እየሮጠች ወደ ቤት ገባችና " አባየ ይሄ ዘመዳችን ማን እንደሚልህ ታውቃለህ?" አለች " አላውቅም ልጄ ማን አለኝ?" አለ እየሳቀ " ጋሼ ነዋ!" አለች እየሳቀች " እና ምን ችግር አለው እኔ እኮ የመስሪያ ቤት ስሜ ጋሼ ነው " አላት " አይደለም የማላውቅ መሰለህ አቶ ሙሉሰው አይደል የሚሉህ ደግሞ ስ ጋሼ የሚባሉት ብዙ ነጭ ጠጉር ያላቸውና ትልልቅ ሰዎች አይደሉ?" አለች " አይ እንደዛ ብቻማ አታስቢ ልጄ ጋሼ ለትልቅ ሰው ብቻ ሳይሆን ሰው ለማክበርም ጋሼ ተብሎ ይጠራል!" አለ " እና እኔም ጋሼ እያልኩ ልጥራህ?" አለች " አይ አንቺማ አባትሽ ስለሆንኩ አባዬ እያልሽ ነው እንድትጠሪኝ የምፈልገው ኧረ አባዬ ብዬ አልጠራህም የምትይ ከሆነ ደግሞ ሌላ አባየ የምትለኝ ልጅ አመጣለሁ" አለ " ኧረ በቃ እልሀለሁ አባዬ የኔ ብቻ አባት እንድትሆን ነው የምፈልገው!" አለች።
ቀዳማዊ ውጭ የቤቱ መናፈሻ ላይ ተቀምጦ እጆቹንና አይኖቹን ወደ ላይ ዘርግቶና አሻቅቦ እየተመለከተ ንፁህ አየር እየተነፈሰ ፀጥ ብሎ ነፋሱን ይቀበላል።
" እና ወሰንክ በቃ እኛ እናስተምረው?" አለች ወይዘሮ ሔዋን " አዎ ውዴ ይሄ ልጅ ሒወቱ በልመና ሊመሰረት ሲል ነው እግዚአብሔር ወደ እኛ የላከው። ትንሽ ቢቆይ ኖሮ ይሄን የልመና የጎዳና ሒወት ለምዶ የሚያስተምረውም ሰው አጥቶ አሁን መንገድ ላይ እንደምናያቸው ልጆች ይሆን ነበር። ምን አልባት እግዚአብሔር ወደ እኛ የላከውና እኛ ጋ ያመጣው እኛን ለመልካም ነገር አጭቶን ይሆናል። እና ልጁን ለማንም ሳንሰጥ እራሳችን እናስተምረው ። በጣም ጎበዝ ልጅ ነው። ህፃን ቢሆንም ግን ምን እንደሚያስፈልገው ያውቃል። ልቡ ንፁህ ነው። ትልቅ ህልም ያለው ልጅ ነው። ስለዚህ ነገውኑ ወስደን ምዘገባ ሳያልቅ ይመዝገብ ቤተልሔም ትምሀርት ቤት ይማር" አለ " እሽ በቃ ሁሉንም አንተ ታውቃለህ" አለች ወይዘሮ ሔዋን " አዎ አውቃለሁ ግን ደግሞ አንቺም ታውቂያለሽ ሌላ ሀሳብ ካለሽ ከአንቺ ሀሳብ አልወጣም። ይሄን ጉዳይ ብቻየን የምወስነው ውሳኔ አይደለም። የአንቺም እሽታና አወንታ መጨመር አለበት።እኔ ያልታየኝ ነገር ካለ ደግሞ ንገሪኝ አስተካክላለሁ " አለ አቶ ሙሉሰው " ኧረ በጭራሽ ከአንተ የተለየ ሀሳብ የለኝም እኔም የአንተን ሀሳብ ነው የምጋራው።እንዳልከው ልጁ ከእኛ ጋ ይሁን እንዲህ ሁኖ ብንተወውና ሂወቱ ቢበላሽ እኛም ይፀፀተናል።ያለንን ተካፍሎ ይደግ ለልጆቻችንም ጥሩ አነጋጋሪ ያገኛሉ። ያጫውታቸዋል ያስጠናቸዋል። ጥሩ ወንድም ይሆናቸዋል። " አለች " መልካም የኔ ማር ለቀናነትሽ አመሰግናለሁ! በይ አሁን ተመልሼ ወደ ስራ ልሂድ " አለ " ቀዳማዊይንም ይዘኸው ሂድ እዚህ እንዳይጨንቀው ከሴት ጋር ከሚውልኮ ከወንድ ጋር ቢውል ይሻለዋል። በዛውም ዘወርወር አድርገው" አለች ወይዘሮ ሔዋን " " ኧረ ይሻላል እኔ ደግሞ እዚህ ከእነ ሔመን ጋር ቢጫወት አሪፍ ነው እሱም አረፍ ይላል። ብየ አስቤ ነበር " እሽ በቃ እንዳልክ በል ደህና ዋል ደህና አምሽ!"ብላ ጉንጩን ስማ ሸኘችው። ሊወጣ ሲል ቀዳማዊይን ሲያየው ከሔመን ጋር ደክሞት እስኪያለከልክ ድረስ እየተጫወቱ አያቸው። ሔመን ያላትን መጫወቻ በሙሉ አውጣት አንዱን ከአንዱ እየደባለቁ ይጫወታሉ። አቶ ሙሉሰውም ደስታው እጥፍ ሲሆን ተሰማው። " ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! እግዚአብሔር በምክንያት ያመጣል በምክንያትም ይሞላል በምክንያትም ያጎላል ። አሁን ቤቱ ሙሉ ሲሆን ተሰማው። ወደ ስራ ሊሄድ ሲል ካልወሰድከኝ ብላ እሪ ብላ ብላ የምታለቅሰው ልጁ ሔመን አሁን እያየችው ከቀዳማዊ ጋር በደስታ እየተጫወተች ነው። አንድ በአንድ ነገሮች እየተፈቱ ያሉ መሰሉት። ይሄን ልጅ ሳስገባ እግዚአብሔር እጥፍ አድርጎ ሌላ ሲሳይ እንደሚያስገባልኝ አምናለሁ። በሱ በረከት ቅንጣት ታህል አልጠራጠርም " እያለ በሆዱ መኪናውን አስነስቶ ወጥቶ ሄደ። አቶ ሙሉሰው ስራውን ሲሰራ ውሎ ማታ ላይ ወደ አንድ የልብስ መሸጫ መደብር ቡቲክ ገብቶ የተወሰኑ ልብሶችን ጫማዎችን ሸምቶ ወጣ። ማታ ላይ ቤት ሲገባ የገዛቸውን ሱሪዎች ሹራቦች ቦዲዎችና እንዲሁም የዝናብ ጃኬቶችን ለቀዳማዊ አለበሰው። ሁሉም ልብሶቹ ጫማው ሳይቀር ራሱ ሄዶ ለክቶ የገዛቸው ነበር የሚመስሉት።ሁሉም ልኩ ሆኑ እየቀያየረ ለብሶ። ገጠር ላይ አዲስ ልብስ ሲገዛ የእናት አባት ጉልበት እንደሚሳመው ባህል። ቀዳማዊይም ልብሱን ለብሶ ተነስቶ የአቶ ሙሉሰውን ጉልበት እንዲሁም የወይዘሮ ሔዋንን ጉልበት ሊስም ሲል " አይሆንም አይቻልም ይሄ ቀላል ነገር ነው" ብለው ሁለታቸውም አንገቱን አንስተው አቅፈው ሳሙትና " እንኳን ወደ ቤታችን በሰላም ተቀላቀልክ።" አሉት።



ሼር @monhappy
@monhappy
👇👇👇👇
@monhappy
@monhappy
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳፱ ~ ( 29 )

ራስ አምባ፦
ይቺን የገጠር ቀበሌ የመስከረም ወር ውበቷን አጉልቶታል። ተራራዎቿ በአደይ አበባ አሸብርቀው ምድሯ ደግሞ በአተር ፣ በቆሎ ፣ እንዲሁም በባቄላ አሸት ተጥለቅልቋል። ሌሎች የደረሱት ሰብሎችም የውበቷ አጋፋሪዎች ናቸው። ገበሬው እሸቱን እየነቀለ እንዲሁም እየጠበሰ ይበላል።
ወይዘሮ አትጠገብ ቀዳማዊ ከቤት ከለቀቀበት ቀን ጀምሮ ሌሊት በቅዥት ቀን ደግሞ በንዴት እያሳለፈች ነው። አሁንም ግን ተስፋ የቆረጠች አትመስልም። ቀዳማዊ ወደ ቤት ይመለሳል ብላ ስለምታስብ ሲመጣ ምን እንደምታደርገው እያሰበች ነው። ቤቷ ድረስ ማህበርተኛዋ መንደርተኛው እየመጣ እያፅናናት ነው። ነገር ግን እሷ አሁንም ቢሆን የጠፋ አልመሰላትም የተከፋችው ደግሞ ስለልጇ አስባ ሳይሆን ሳታስበው እንደዚህ ያደርገኛል ብላ ስላላሰበች ተናዳ ነው። አንድም ቀን ትቶኝ ይሄዳል ብላ አታውቅም ነበር። አሁን ታዲያ ብቻዋን ማውራት ሁሉ ጀምራለች። ሁኔታዋን የተመለከቱ አንዳንድ ጎረቤቶች ቀዳማዊ ላይ ያደረገችውን ስለሚያውቁ " አሁን ሲያይዋት ያዘነች ትመስላለች። ይች አስመሳይ ጨካኝ እናት የማትመስል። ወልዶ ነካሽ " "ደግሞ እኮ በእሷ ምክንያት ነው ወደ ሰው አገር የሄደው። አፈር ትብላ ይቺ እርኩስ " እያሉ ያሟታል።
እነ ማለፊያ ርብቃ አድና እንደ ወትሮው ደስታቸው ከፊታቸው ከጠፋ ዋል አደር ብሏል። ሁላቸውም በሀሳብ ለብቻቸው ይሄዳሉ። ቤቱ ቀዝቀዝ ብሏል። እና ይሄን ነገር የታዘበችው ማለፊያ ታዲያ " ምንድን ነው ግን ይሄን ያህል የምንቆዝመው። በቃ እሱ እንደሁ ሄዷል ተመልሶ አይመጣም ከዚህ በኋላተገላግለነዋል ተመስገን ነው። አሁን በነፃነት መኖር እንችላለን። የምንፈልገው ይሄኑ ነበር " አለች " ከእንግዲህ በኋላ ቀዳማዊይን አናየውም። መቼም ቢሆን ይሄን ደግሞ እርግጠኛ ነኝ። አሁን እርሻውን መከፋፈል ትችላላችሁ። አሁን ሁሉንም ትቶት ሄዷል።" አለች ወይዘሮ አትጠገብ " አንድ ቀን የመጣ እንደሆነስ? መቼም በዛው አይቀርም ። ብዙ አመት ቆይቶም ቢሆን ይመጣል። ያኔ ምን ልናደርግ?" አለች ሲሳይነሽ " በጭራሽ አይመጣም ሊመጣ የሚሄድ ሰው ያስታውቃል። በጣም ነው የሚጠላን ዞሮም አያየን! በእርግጥ ይሄ እኔን አያስጨንቀኝም እሱ ወንድ ነው የትም ቢሆን ሄዶ በልቶ ያድራል እናንተ ሴቶቹ ልጆቼ ናችሁ እንጅ የምታሳዝኑኝ" አለች ወይዘሮ አትጠገብ
የመስከረም ወር ላይ ከሚከበሩ ክብረ በዓል አንዱ የመስቀል የደመራ በዓል ነው። ይሄን በዐል ለማክበር መንደርተኛው ሽር ጉድ እያለ ነው። መስቀልን መንደርተኛው አንድ ላይ ነው የሚያከብረው። ጠዋት ላይ ደመራው ተለኩሶ መሀል ላይ ተተክላ የነበረችው እንጨት በየትኛው አቅጣጫ እንደምትወድቅ ሰው በጉጉት ይጠብቃል። ይቺ እንጨት የምትወድቅበት አቅጣጫ ምርት ይበዛበታል ተብሎ ይታሰባል። ይህ የመስቀል ደመራ ታሪካዊ ዳራ ከንግስት ኤሊኒ የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ተራራ ለማግኘት የተጠቀመችበት መንገድ ነው። ደመራ ደምራ የደመራው አቅጣጫ እንዲሁም እንጨቷ በወደቀችበት አቅጣጫ ተመልክታ ነው። ተራራውን አግኝታ ስታስቆፍር ግማደ መስቀሉን ያገኘችው ይባላል። እና መስከረም ፲፯ [17] የደመራ በዐል ሆኖ የሚከበረው። በዚህ ምክንያትና መስቀሉን ለማግኘት ቁፋሮ የተጀመረበት ቀን ነውም ይባላል።
****
አዲስአበባ
አዲስ አበባ ከወትሮው ለየት ብላ አሸብርቃለች ከተለያዩ የአለም ክፍል ወደ ኢትዮጵያ አዲስአበባ የመስቀል ደመራን በዐል ለመታደም ከመጡ ሰንበትበት ብለዋል። በዐሉን በድምቀት የምታከብረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዝግጅቷን አጠናቃ ትዕይንቱን እያሳየች ነው። የአዲስ አበባ ነዋሪ ከያለበት እየተመመ ነው። መንገዶች ተዘግተዋል ከእስጢፋኖስ ወደ ቦሌ ከፒያሳ ሳሪስ ከአምባሳደር መገናኛ እንዲሁም የተለያዩ መንገዶች ተዘግተዋል። ፍተሻውና ጥበቃውም አይሏል። አያሌ ፌዴራል ይህን ባዕል ያለ ፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ መንግስት በሰጠው ተልዕኮ መሠረት እየታተረ ይገኛል። ህዝበ ምዕመናኑ የተለያዩ ቲሸርቶችን አሳትመው ለብሰው በዝማሬና በእልልታ ክርስቶስን መላእክትን ቅድስት ድንግል ማርያምን እያነሱ ይዘምራሉ። ይህን በአለም አቀፍ በዩኔስኮ የተመዘገበውን ቅርስ ለማየት የውጭ አገር ዜጎች ገብተው በካሜራቸው ትዕይንቱን እያስቀሩ ነው። አሁንም አሁንም ፎቶ ያነሳሉ። ቄሶች ዲያቆኖች እንዲሁም ዘማርያን ፀኣዳቸው አንድ አይነት ነው። ቄሶቹ ዲያቆኖቹ እንዲሁም መርጌቶች አቋቋማቸው፣ እና ዝማሬያቸው ያሬዳዊ ዜማ ስልት ያለው ሲሆን በአንድ አይነት ዜማ በአንድ አይነት አካሄድ አቋቋምና ፅናፅል አያያዝ አለባበስ ወደ ምስራቅና ምዕራብ እየዘመሙ ያዜማሉ። ዜማቸው በሀሴት ነፍስን የገነት አፀድ ላይ ያስቀምጣል። እጅግ ለየት ያለ ውብ የሆነ ከያሬዳዌ ማህሌታይ የተቀዳ የዜማ ድምፅ ስርአቱን የተከተለነ የዜማ ስልታቸውን ያማከለ የከበሮ አመታት የፅናፅል አያያዝ። ይህ ሁሉ ትዕይንት በመስቀል አደባባይ ነው የሚካሄደው። ይህን ሁሉ አስገራሚ የበዐል ስነስርአት ቀዳማዊ ከአቶ ሙሉሰው ጋር ሆኖ ወደ መሀል ሳይገቡ ጊዮን ሆቴልን አለፍ ብለው ድልድዩ ስር በእርቀት እየተመለከቱ ነው። ልክ አመሻሽ አንድ ስአት ሲል ደመራው ተለኮሰ። ህዝቡም አኔድ ላይ ጧፍ አበራ ያሁሉ ህዝብ ጧፍ ሲያበራ የሆነ የሚገርም ታዕምር ነው የሚመስለው! ስነስርአቱ እንዳለቀ ቀዳማዊይና ሙሉ ሰው ቀስ እያሉ እያወሩ መኪናቸውን ያቆሙበት ቦታ ሄዱ። " እና በዐሉን እንዴት አየኸው? እናንተ አገር እንደዚህ ነው የሚከበረው?" አለ አቶ ሙሉሰው " ኧረ ትንሽ ሰው ነን የተወሰነ የእኛ ጎረቤት የሆነው ነን በአንድ ላይ የምናከብረው ትንሽ ነን" አለ ቀዳማዊ " እየውልህ እኛ አገር ላይማ እንደዚህ ነው የሚከበረው" አለ አቶ ሙሉሰው " ኧረ ይሄ ነው ደስ የሚለው በጣም ነውኮ የሚያምረው " አለ ቀዳማዊ ትንሽ እንደሄዱ ደመራ የሚሸጥበት ቦታ ሲያገኝ አቶ ሙሉሰው መኪናውን አቁሞ ደመራ ገዝቶ መጣ " እነ ሄሚ ቤት ያው ደመራ ስለሚሰሩ እዛም እናከብራለን " አለ " እሽ " አለ ቀዳማዊ ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ለውጦችን አሳይቷል። ነቃ ብሏል ፍጥነትም እንደዚሁ ጨምሯል። ቤት ደርሰው ችቧቸውን ይዘው የተሰራውን ደመራ ከለኮሱ በኋላ እዛው ዳቦ ተቆርሶ እነ ሄመን ደግሞ የሆነ መዝሙር እየዘመሩ ከእናታቸው ከአባታቸው ብር ሰብስበው ቀዳማዊይንም እንደዚሁ አስር ብር ተቀብለው ብራቸውን ተከፋፍሉ መጫወቻ ልትገዛ ወደ ውጪ ወደ ሱቅ ልትወጣ ስትል ። አቶ ሙሉሰው " መሽቷል እኮ ኄሚ ነገ ትገዣለሽ የኔ ቆንጆ መቼም አሁን ብትገዥውም አሁን ስለመሸ አትጫወቱም ነገ በጠዋት ገዝታችሁ ትጫወታላችሁ! " አለ " እሽ በቃ አባዬ ነገ ግን ራሴ ነኝ ሄጄ የምገዛው " አለች " እሽ ግን ትምህርት አለብሽኮ ረሳሽው እንዴ?" አለ ሙሉሰው " አዎ ረስቼው ነበር በቃ ከትምህርት ስመለስ " አለች ኄመን " ኧረ ተይ አንቺ ልጅ ይሄን ትምህርት አትርሽ ጎበዝ ሁኝ አጥኚ " አለ አቶ ሙሉሰው " እሽ በቃ አጠናለሁ አባዬ " አለችና ወደ ውስጥ ገባች። " እንደው ይቺን ልጅ ምን ላድርጋት " አለ

ሼር
@monhappy
@monhappy

በቻናሏ ላይ ወይም በድርሰቶቼ ላይ አስተያየት ካላችሁ
@BINCJ90 ላይ አድርሱኝ
:)
…ትዝታ…

"ልጄ ሆይ ከአንግዲህ ሚስትህን ጠብቃት እስከዘላለሙም የአንተ ናት"…ብለውኝ ነበር ያኔ አዎ ያኔ ሚስቴን ሳገባት …አሁን ግን የለችም …ምን አልባት እኔ ከዘላለሙም ቡኋላ እየኖርኩ ይሆን…

🤵🏽 @monhappy 👰🏽
👫 @BINCJ90
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፴ ~ ( 30 )


ራስ አምባ፦
በዚህ የመስቀል ደመራ በዐል ታዲያ አንዳንድ አዝማሪዎች እየመጡ ማህበርተኛውን ባለ አመትባሉን ሰው እያዝናኑ እየዘፈኑ ትልልቆቹን በትዝታ እያስጋለቡ ህፃናቶችን ደግሞ በእስክስታ እያስወረዱ ሳይሰስቱ የፈረስ ጭራቸውን ይገርፋሉ። ታዲያ እነዚህ አዝማሪዎች በማሲንቋቸው ሲዘፍኑ ውለው በሽልማት መልክ የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ነገር ተቀብለው የተሰጣቸውን እህልም ሆነ ብር ይዘው ወደ መጡበት ይሄዳሉ። እናም ታዲያ ይሄን ተጫዋችነታቸውን ያዩ እረኞች እና ህፃናት " ምነው ባደረገኝ የአዝማሪ ዲቃላ፣ ማሲንቆየን ይዤ በኋላ በኋላ። ብለው የግጥሟን ስንኝ ያዜሟታል። በዚህ ጊዜ አንድ ትልቅ ሰው የሰማ እንደሁ " ምን እነዚህ የማይረቡ አሁን ደግሞ ምኑን ነው የተመኛችሁት? አሁን እነዚህ ሀሚና ዘዋሪ ቀላዋጮች ምናቸው ነው የሚያስቀናው? እ ደግሞ እነዚህ ዘረ ሰባራዎች " ብሎ ይሳደባል። አዝማሪዎች ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ስለሆነ የሚኖሩት በብዛት ቤት የላቸውም ቤታቸው የድግስ ታዛና የሰርግ ዳስ ነው" ይባላል። ለዚህ ነው ድግስህንና ሰርግህን የፈለከውን ያህል ምስጢር ብታደርገው ወይም ብትደብቀው ከአዝማሪ ግን ልታመልጥ አትችልም ይባላል። ለአዝማሪዎች የሆነ ሹክ የሚላቸው አለ። ከየት መጡ ሳይባሉ በድንገት ብቅ ሲሉ ያስገርማሉ። በዛው ልክም ደግሞ ተፈላጊ ተናፋቂ ናቸው። ጨዋታ ዘዋሪ ናቸው። የጨዋታ ነፍስ መዝራት ይችላሉ። በቃ ሁለት ዝልል ጠላ የጠጡ ጊዜ ማሲንቋቸውን ብድግ ነው የሚያደርጉት። ታዲያ በዚህ የመስቀል እለትም አንድ ሊቀ መኳስ እያሉ የሚጠሩት መንደርተኛው የለመደው አዝማሪ መጣ " እንዲያ ነው እንጅ በስአቱ መምጣት ጀግናው ሊቀ መኳስ በል አስቲ እሷን ጭራ አስለቅሳት" አለው አንድ ሲሳይ የሚባል ሰውየ በውል እንኳ መሬት ሳይዝ ሳይቀመጥ። " እስኪ መጀመሪያ ሞቅ ይበለኝ እኔ ልሙላና ነው እንጅ በባዶ ሆድ ሆኖ ምን ጨዋታ ይመጣል ብለው ነው አያ ሲሳይ" አሉና ከመጫወቱ በፊት ጠላና ምግብ እንደሚፈልግ በምሳሌ አስረዳ።በትዕዛዙ መሰረትም የሚበላ ና የሚጠጣ መጣለት። ሊቀመኳስ ከበላ ከጠጣ በኋላ ሞቅ አለው በዚህ ጊዜ ነበር ፈገግ እያለ ማሲንቆውን ማጫወት የጀመረው።
አስይዙኝ አስታጥቁኝ ዝናር በልጅጌን፣
ደፍሮ ለመጣ ሰው መመከቻየን። " አለ አዎ እንደዛ በልማ አንተው እ አንተ እኮ ስትመጣ ነው ሁሉ ነገር የሚታየኝ እስኪ እንደው ሊቀ መኳስ በነካ አፍህ እስኪ በሰሜን ገብተህ በደቡብ ውጣ" አለ አያ ሲሳይ
" እሽ ምን ገዶኝ ይሄማ ስራየ አይደል " አለና አዝማሪው የማሲንቆውን ቅኝት አስተካክሎ
ኧረ አገሬ አድዋ~ አክሱምና አዲግራት~ ሸንበቆው ማማሩ፤
ኧረ አገሬ ጎንደር ~ ሸዋ ፣ወሎ፣ጎጃም~ሸንበቆው ማማሩ፤
ኧረ አገሬ ናዝሬት ~ አምቦ፣ ጅማ፣ ባሌ ~ ሸንበቆው ማማሩ፤
ኧረ አገሬ አሶሳ ~ የቤንሻንጉል ጉምዝ ~ ሸንበቆው ማማሩ፣
ኧረ ወንዜ ባሮ ~ አገሬ ጋምቤላ ~ ሸንበቆው ማማሩ፤
አገሬ ሶማሌ ~ ጂጂጋ ኦጋዴን~ ሸንበቆው ማማሩ፤
ኧረ አገሬ ሀረር ~ ሸንበቆው ማማሩ
ኧረ አገሬ ድሬ አሰበ ተፈሪ ሸንበቆው ማማሩ፤
ኧረ አገሬ አሳይታ~ አዋሽአርባ ሚሌ~ ሸንበቆው ማማሩ፤
ኧረ አገሬ ጂንካ ~ ሀመር ኮንሶ አርባምንጭ~ ሸንበቆው ማማሩ፤
ኧረ አገሬ ደቡብ
ወላይታ ሲዳሞ ~ ቡታጅራ ሀላባ ~ ዲላ ሆሳዕና~ ሸንበቆው ማማሩ፤
የዘላለም ህያው ~
የአንዲት ኢትዮጵያ~ ዋልታ ማገር ሆነው ዝንታለም ሲኖሩ፣
አየሁ የአገሬን ሰው
እንደ ማር ከቀፎ ሲቆረጥ በጠዋት መውደድና ፍቅሩ።"
አለና ሊቀመኳስ ማሲንቆውን በደንብ መታው " ኧሯ እንደው ለአንተማ ምንም ያንስብሀል አይይይ አንጀቴን እኮ ነው ያራስከው በልማ እንካ " አለና አያ ሲሳይ 10 ብር ሸለመው። አዝማሪውም አንድ ጊዜ ፉት ብሎ ከእንደገና የተሸለመውን ብር ወደ ኪሱ እያስገባ ማሲንቆውን ማጫወት ጀመረ። ቀጠሎም እንዲህ ብሎ ተቀኘ፦
"እግዚአብሔር ታረቀኝ ይሄው እርሻዬ ላይ በልግ ዝናብ ጣለ፣
ነገር ግን አጣሁት...
ላሳድግ ብነሳ ቢተካኝ ያልኩት ዘር ቡቃያው የታለ፣"
ጎተራው ሙሉ እህል ቅምባው እያመለ፣
ያ የደጃዝማች ልጅ ደጀን ቢያጣ ጊዜ ወቶ ኮበለለ፣
መቼም የጊዜ እንጅ የሰው ጀግና የለም በእሱ አዘነበለ።"
አለ ። ይሄኔ ሁሉም ድንግጥ ድንግጥ አሉና እርስ በእርስ መተያየት ጀመሩ። ከዛ ሁላቸውም አንድ ላይ ወደ ወይዘሮ አትጠገብ ዘወር አሉ። ወይዘሮ አትጠገብ ደግሞ አዝማሪውን ደንግጣ ተመለከተችው። " እንዴ እንዴ እንዴት አውቆ ነው? ኧረ ጉድ ነው " አለ አያ ሻምበል " አየ ማህተብ አዝማሪማ መቼም አይረሳም ነፍሱን ይማረውና ያ ሟች አቶ ታረቀኝ ይሄን አዝማሪ በጣም ነበር የሚወደው እንደውም አንድ ጊዜ አንዲት ፍየል ሰጥቶት ነበር። እና ሁሌ ወደዚህ መንደር በመጣ ቁጥር አይ አቶ ታረቀኝ ሳይል ስሙን ሳያነሳው አይሄድም እጅግ በጣም እንደሚውደው አስታወሰኝ። ይሄው ደግሞ አሁን በስንት መከራ ያገኘውን ልጁን ድንገት እዚህ ሲያጣው እሱንም ከፍቶት ኖሮ ይሄው እንጉርጉሮውን መከፋቱን በማሲንቆው መግለፁ እኮ ነው" አለ አያ ሲሳይ " እውነቱን ነው ወንድ ልጅ ለማግኘት እግዚአብሔርን ስንቴ ወድቆ እየተነሳ ለምኖታል በስተመጨረሻ ቢሰጠውም እሱ ግን ሳያየው ሄደ። በስንት ልመናና ስለት የተወለደው ልጅም ይሄው መከራውን ሲያይ ኑሮ መጨረሻ ላይ መቼም ወንድ ልጅ ከፍቶት ከፍቶት አይቀርም ይሄው ብን ብሎ ጠፋ። የት እንዳለ እንኳ አይታወቅም። ምፅፅፅ አሁን እንደው የደጃዝማች ገዛኸኝ ወልዴ ዘር የጀግናው የፊታውራሪው የአቶ ታረቀኝ ልጅ ከፍቶት ተሰደደ ቢባል ማን ያምናል" አለ " አዎ እንግዲህ ምን ታደርገዋለህ? የጊዜ እንጅ የሰው ጀግና የለው " ብሏል እኮ አዝማሪውም አለ ሌላኛው እየቆዘመ " ብቻ ባለበት ሰላም ይሁን እኛም ምንም አላደረግንለትም " አለ አያ ሲሳይ
ወይዘሮ አትጠገብም .....

ክፍል ፴፩ ( 31 ) ምሽት 12:00 ይቀጥላል

ታሪኩን ከወደዳችሁት ለጓደኞቻችሁ አጋሩ
@monhappy
@monhappy

ለአስተያየት
@BINCJ90
ተጀመረ ተጀመረ ተጀመረ !!!!!!!!

🌺🌺🌺ማክ🌺🌺🌺

እመኑኝ ትወዱታላቹ🥀 ከ15 አመት በላይ ለሆናቹ እጅጉን 🌺አስየማሪ እና ምርጥ ታሪክ ርዕሱ🌹🌹ማክቤል🌹🌹 እውነተኛ የሴትን ልጅ ታሪክ ምናይበት ከናተ የሚተበቀው መቀላቀል ብቻነው ትደሰቱበታላቹ
👇👇👇👇👇👇👇👇
@monhappy
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፴ ፩~ ( 31 )

በንዴትና በጥላቻ አይን አዝማሪውን እየተመለከተች " እንዴት አውቆ ነው ይሄ ሀሚና አዝማሪ እንዲህ ሊል የቻለው?" አለች " እንጃ እኔም ገርሞኛል። ግን ያው ሰዎች ሲያወሩ ሰምቶ ሊሆን ይችላል " አለች ማለፊያ።አዝማሪው ሊቀ መኳስ እነ ማለፊያ ሲሰድቡት ስድባቸውን የሚሉትን ወደ ኋላ እየተወ እንዳልሰማ እያለፈ በጣም ብዙ ሰም ለበስ ቅኔዎችን በማሲንቆው እያንቆረቆረ ማጫወቱን ቀጥሏል። አንዱ " ተቀበል እስኪ ሊቀመኳስ " አለ " እሽ " አለና ማሲንቆውን ገታ አድረገ " አባይ ሞልቶ እሳት ይዞረዋል " በል አለው " ሊቀመኳስም አለው " በል ድገመው " አለ ሰውየው " አባይ ሞልቶ እሳት ይዞረዋል፣ " አለ " ሊጠፋው ነው እንጅ መች ይሻገረዋል።" ብለህ ጨርሰውማ "" እሱም በማሲንቆው እያሽሞነሞነ ደግሞ ደጋግሞ አለው ሌላኛው አስከተለና " ወንድ ልጅ ሲከፋው ምነው ውጪ ይመኛል፣ ከዚህ ያልተገኘ እዛስ ምን ይገኛል?" በልማ ሊቁ አለ"" ሊቀ መኳስም የሰጡትን እያለ ራሱም እየጨመረ እያጫወታቸው ውሎ ወደ አመሻሽ ላይ የዋሹለትን ፍየልም ሪዝም በግም እህልም ብቻ የተቻላቸውን የሰጡትን ተቀብሎ ወደ አካባቢው ሳይመሽበት ሄደ። " ይሄ ሰውየ ዛሬ አኔድ ቀን የዋለ አልመስልሽ አለኝ ውሎ ያደረ የሰነበተ ነውኮ የመሰለኝ። እንዴት ነው የሚያስጠላው ዝም ብሎ የተሰጠውን ይዞ ለምኖ አይሄድም እንዴ ምን በማያገባው ጥልቅ ይላል? "አለች ማለፊያ " ያው የአባትሽ ወዳጅ ስለሆነ ነዋ አባትሽን ስለሚወደው። እሱ ከሞተ በኋላ ደግሞ እኛ ምንም አላደረግንለትም! እ ለዚያ እኮ ነው ይሄ ውሻ እኛ ማሳፈሩ ነው በኤሱ ቤት" አለች ዘይዘሮ አትጠገብ።
" ሰው እንዴት የወለደ ሰው በአብራኩ ክፋይ እንዲህ ይጨክናል? ምንም በማያውቅ ህፃን ልጅ መፍረድስ ምን ይሉታል? በጣም ነው የሚገርመው። አባቱ የፈለገ ቢያድርግስ ልጁ ጥፋተኛ ሆኖ መቀጣት ይገባዋል? ነገ ጠዋት ይሄ ልጅ አድጎ የበቀል ጥዋውን ማንሳቱ የማይቀር ነው። እነሱ የነካኩትን ቁስል በደንብ አርጎ እየገለጠ ዋጋቸውን ይሰጣቸዋል። ብቻ በደንብ አድርጎ ይበቀላቸዋል።" አለ አንደኛው ሰው " የእኔ ግን ጥያቄ ይሄ አይደለም ቆይ ይሄ ልጅ ልጇ ባይሆንስ?" አለ ሌላኛው " ተው እንጅ የእብድ ጥያቄ አትጠይቅ ጃል " አለ ሌላኛው " እንደው ምን ላድርግ ክፋቷ ቢብስብኝ ገርሞኝም እይደል የምለውን ሳላውቅ እስከመናገር የደረስኩት " አለ " እኔ በበኩሌ ከዚህ በኋላ ከእሱ ጋር ቁጭ ብየ ባዕል አላከብርም። ባየኋት ቁጥር እየተሸማቀኩ ነው። ባለቤቴም ቢሆን ከዚህ በኋላ ከእሷ ጋር ማህበር ላለመጠጣት ወስናለች። እኔም እቀበላታለሁ እንዴትስ ከዚች መናጢ ጋር አብሮ ተቀምጦ የቅዱስ ፅዋ ይጠጣል። " አለ " ምንድን ነው? ያበዛችሁት አልመሰላችሁም። እንዲህ አድርጎ የማግለል ስራማ ጥሩ አይደለም። ምንድን ነው አንዱ የሆነ ነገር ሲል ተቀብሎ አብሮ መሄድ። አዎ እኔም አልዋሽም ሴትዮዋ ልጇ ላይ ያደረገችው ነገር እጅግ የሚያስጠላ ነው ግን ደግሞ ይሄን ያህል ማግለል ጥሩ አይደለም። እሱ ፈጣሪ እንደፈጠራት በክፋቷ ልክ ይቅጣት እንጅ እኛ የማግለልም ሆነ በመጥላት የምንሰጣት ነገር መኖር የለበትም። ይሄን ፈጣሪም አይወደውም። በእሱ ስራ መግባት ነው። እና እባካችሁ በፈጣሪ ስራ ባንገባና እኛ የተለመደ ኑሯችንን ብንቀጥል። በአመት አንድ ጊዜ ለምናከብረው የመስቀል በዐል በወር አንድ ጊዜ ለሚደርስብን የማህበር ዝክር ይሄን ያህል መሆን የለብንም። እስኪ አስቡት ልጁ አድጎ ይቅርታ ቢያደርግላትና ባይበቀላት እኛ ያኔ ምን ልንል ነው? አያችሁ በድርጊታችን እናፍራለን። ስለዚህ ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል ባንናገር" አለና ተነስቶ ሄደ " በሉ እንግዲህ እኔም እየሄድኩ ነው! የወይዘሮ አትጠገብን ጉዳይ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንዲሁ እየጠጣን እንመክርበታለን።" ብሎ ሌላኛው አባወራ ተነስቶ ሔደ።
**
አዲስአበባ፦

" እንግዲህ ሕይወት እንዲህ ናት ትላንት የሆነ ቦታ ላይ ዛሬ ሌላ ቦታ ነገ ደግሞ ትላንት ከነበርክበትም ዛሬ ካለህበትም ውጪ! በቃ ሕይወት የሚጨበጥ የሚወሰን ነገር የላትም። አንተ ትኖራታለህ እንጅ እሷ አትኖርህም! አይዞህ አትጨነቅ አትፍራ! ሁሌም የራስህ የሆነ አንድ ሕልም ይኑርህ ከዛ እሱን ሕልም ለመኖር የቻልከውን ያህል ጣር እግዚአብሔር በጥረትህ ልክ ነው ወደ ምኞትህ የሚያቀርብህ። ነገር ግን አንተ ቁጭ ብለህ ምንም ነገር ሳትሰራ የሆነ ነገር ብትጠይቀው ከምኑ ላይ ይጨምርልሀል? ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ፈጣሪ በምክንያት ነው የሚያስወጣህ ፈጣሪ የሚወደውን ሰው ነው የሚፈተነው። አንተ ደግሞ ገና በጠዋት ነው የፈተነህ። ምክንያቱም ወርቅ ስለሆንክ ሊያነጥርህ ፈልጎ ነው። " አንድ ነገር ልንገርህ ልጄ አሁን ከምነግርህ ንግግር ብዙ ትምህርት ታገኝበታለህ።
በሆነ ጊዜና ቦታ ነው አሉ ንጉስ አማካሪዎቹን ጠራና የዘመናትን ጥበብ እንዲፅፉለትና እንሱም ለቀጣዩ ትውልድ ይህን እንዲያስተላልፍ ጠየቃቸው:: አማካሪዎቹም የንጉሱን ትዕዛዝ በመቀበል ከብዙ ድካም በኋላ ሰዎቹ በጥበብ የተሞሉ በርካታ ቅፆችን አመጡና ለንጉሱ አስረከቡት:: ንጉሱም መልሶ ጠራቸውና ''ይህማ እጅግሰፊና ረዥም ነው:: ትውልዱም ቢሆን ይሄን ሁሉ ገፅ ትዕግስት ኑሮት አያነበውም:: እናም በደንብ አሳጥሩት::'' አላቸው::
እነርሱም መልሰው ፃፉና ወደ አንድ ቅፅ ብቻ አሳንሰው መለሱለት:: አሁንም ንጉሱ አማካሪዎቹ አሻሽለው ያመጡትን ሀሳብ ውድቅ በማድረግ ረዝሟል አሁንም አሳጥሩት አላቸው ። አነርሱም ለ3ተኛ ጊዜ አሳጥረው አንድ ምዕራፍ ብቻ አድርገው አመጡ:: ''አሁንም ቢሆን ረዝሟል አይደለም አንድ ምዕራፍ አንድ ገፅ ራሱ ረዥም ነው:: እንደገና አሳጥሩት::'' አለ አለ ንጉሱ
አማካሪዎቹም ሳይሰለቹ ዳግም ተመልሰው ከብዙ ጥረት በኋላ በመጨረሻም ንጉሱን ደስ ያሠኘ ነጠላ ዓረፍተ ነገር ይዘው ተመለሱ:: ንጉሱም ፈገግ ብሎ ''ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላልፈው ብቸኛ ጥበብና እውቀት ቢኖር ይህ ነው-እርሱም " ነፃ ግብዣ የለም!!!/No free lunch"አላቸው::
አሁን ይሄ ሀሳብ ምን ማለት ነው? እንታገል... እንጣር... ምናልባት ጥረታችን... ትግላችን ረዥም ጊዜና ትዕግስት የሚጠይቅ ይሆናል:: ግን ተስፋ አንቁረጥ:: የሚገጥመንን መሠናክል ካላለፍን የመጨረሻውን የአሸናፊነት መስመር አንረግጥም:: ጥሩ ከዘራን... በትጋት የዘራነውን ለፍሬ ካበቃን... በመኸር ወቅት መልካም ምርትን የሰበሰበ ገበሬ እንሆናለን! በደከምነው ልክ እናገኛለን:: የዘራነውን እናጭዳለን። ምክንያቱም ነፃ ግብዣ ስለሌለ " because there is no free lunch!

ከወደዳችሁት ለወደዳችሁት
👇
@monhappy
@monhappy

ለአስተያየት
@BINACJ90
:)
…ችግር የለውም…

አንዳንዴ መጥላት ያለብንን ወደን…መውደድ ያለብንን ደሞ እንጠላለን…እኔ ደሞ ቶሎ ነው እማምነው…ወሸት እሚባል ያለ እስካይመስል አምናለው…መመኔን አልጠላውም…ግን እማምንበት መንገድ ያናደኛል…

ብዙ ጊዜ…አዋ በጣም ብዙ ጊዚያትን ይህን ቃል እልሽ ነበር…ችግር የለውም…ግን ችግር ሳይኖረው ቀርቶ እንዳይመስልሽ…ችግርማ አለው…ግን አንቺ ከችግሩ ትበልጫለሽ…ለዛም ነው…

…ችግር የለውም…

ሰው እሚናደደው በሚወደው እና ግድ በሚሰጠው ሰው ነው…ምን አገባኝ በምንወደው ሰው ላይ አንልም… እኔ ለአንቺ ብቻ የነገርኩሽን እና እንቺ ብቻ እምታውቂያቸውን ሚስጥሮች ነበሩኝ…ሚስጥሮቼን ግን ከሌላ ሰማሁዋቸው…ግን ችግር የለውም…

…ችግር የለውም…

እናም ችግር የለውም ስልሽ ችግር እያለው ነው…ግድ የለምም እምልሽ ግድ እያለው ነው…

…ችግር የለውም…

እየተበደሉ ይቅር በሉኝ ማለት ግን ምን ያህል ብፁዕነት ነው…እየተከፉ መሳቅስ…መውራት ፈልጐ ዝም ማለትስ…እኔጃ…ብቻ ውስጤን ዛሬ ድረስ ብዙ ነገር ይለኛል…ቢለኝም ግን ችግር የለውም…

…ብቻ ውስጤ እንዲህ ይለኛል…

ችግር የለውም😔😊
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_1

...🖊ሃና ትባላለች ተወልዳ ያደገችው እዚው ከተማችን አዲስ አበባ ልዩ ስሙ መገናኛ አካባቢ ነው። የምትኖረው ከእናቷና ከእንጀራ አባቷ ጋር ሲሆን ለእናቷ የመጀመሪያ ልጅ ነች ታድያ የሃና ውስብስብና አሳዛኝ ታሪኮች
የጀመሩት ገና በለጋ እድሜዋ ነው ሃና ከእናቷ ከአፀደ ጋር
እስከ ስምንት አመቷ ድረስ የኖረች ሲሆን ከዛ ቡሃላ ነበር
እናቷ ቴድሮስን አግብታ መኖር የጀመሩት በእርግጥ የሀና
እናት ልጇ ሃናን የወለደቻት ከአንድ ባለፀጋ ቢሆንም
ሰውየውን ግን ለሀና ሳታስተዋውቃት ይኸው ሀና የ10
አመት ልጅ ሆናለች... አፀደም ልጇ ሃናን በጣም ተቸግራ
ልብስ አጥባ ቀን ስራ ሰርታ ልጇን ግን እጅግ አሳምራ
ነበር ያሳደገቻት...
የሀና እናት አፀደ ከሀና አባት ጋር የተዋወቀችው እሷ ሰው
ቤት በምትሰራበት ወቅት ነበር ይሁንና ገና የ15 አመት
ታዳጊ ስለነበረች ምንም አይነት ፆታዊ ግንኙነትን
አታውቅም ለዚም ነበር አፀደ በሀና አባት ተደፍራ ሀናን
ለመውለድ የተገደደችው ይሁና ግን አፀደ ልጇ ሀናን
ከማንም እና ከምንም በላይ እጅግ በጣም ትወዳታለች
እናት ልጇን ባትጠላም የነሱ ፍቅር ግን እጅግ በጣም
ያስቀና ነበር ለዚም ነው አፀደ የኔ የምትለው ዘመድ
ስለሌላትና ሀናም እድሜዋ ከፍ ሲል "አባቴ ማነው?"
አያለች ስታስቸግራት የቀድሞ ወዳጅዋን ቴድሮስን
አግብታ ለመውለድ የወሰነችው...
ታድያ ሀና ቴዎድሮስን እንደ አባቷ ስለምታየው በጣም
ትወደው ነበር ይህ በንዲህ እንዳለ አፀደ አረገዘች ሀናም
ይሄን ስታይ እጅግ በጣም ነበር የተደሰተችው እህት
ሊወለድልኝ ነው ብላ ለክፍል ጓደኞቿና ለመንደሩ ልጆች
ሳይቀር በየግዜው ትነግራቸዋለች ... ቀናት በሳምንታት
ሳምንታት በወራት ተተካክተው ዘጠኝ ወር ሞልቷት ለአፀደ
ሁለተኛ ወንድ ልጇን ለሀና ደግሞ ወንድም ተወለደላት ....
ሀና አሁን ደስተኛ ናት ወንድም አላት አባትም እንዲው ....
ታድያ አፀደ አራስ በመሆኗ ምክንያት ሀናና የእንጀራ አባቷ
ቴዲ መሬት ላይ ፍራሽ አንጥፈው መተኛት ጀመሩ በዚ
ጊዜ ነበር የሀና ፈተና ሀ ብሎ የጀመረው ሀና ገና የ3ኛ
ክፍል ተማሪ ናት እድሜዋም ገና 10 ነው ይሁን እንጂ
ቴድሮስ አብራው ስትተኛ ስሜቱ ይፈታተነው ጀመር
ይህችን ህፃን ሀናም በእንቅልፍ ልቧ ስስ የለሊት ሱሪዋን
በማውለቅ አይታው ቀርቶ ሲያወሩ ሰምታው
የማታውቀውን ድርጊት ይፈፅምባት ጀመር ... በርግጥ
ሀይል ተጠቅሞ ትክክለኛ ወሲብ የሚባለውን
አልፈፀመባትም ምክንያቱም ህፃን ስለሆነች ብትጮህስ
ብሎ ይፈራ ነበር ቢሆንም ግን በየእለቱ ይህን አስነዋሪ
ድርጊት ቀጠለ ሀናም ይሄን እንግዳ ድርጊት ለማንም
ትንፍሽ ሳትል 1 አመት ሞላት ከቀን ወደቀን ተጫዋችና
ፍልቅልቋ ሀና እናቱ እንደሞተበት ህፃን ትካዜ አበዛች ...
አፀደም ባልዋና ልጇ ሀና እንደ አባትና ልጅ እንዲተያዩላት
ስለምትፈልግ ብዙ ግዜ አብረው ሲተኙ ደስተኛ ትሆን
ነበር ቴድሮስም አልጋ ላይ ከመተኛት ይልቅ ከሀና ጋር
መሬት መተኛት እንደሚመቸው በመናገር በድርጊቱ ፀና
...
ሀና የ14 አመት ልጅና የ8ኛ ክፍል ተማሪ ሆነች ይሄኔ
የእንጀራ አባቷ የሚያደርጋት ነገር አይምሮዋን
ይበጠብጣት ጀመር ይህን ነገር ለእናቷ ብትነግራት እናቷ
ባልዋን ከመፍታትም አልፋ እንደምትታመምባት ማሰብ
ጀመረች ስለዚህ የሚሻለው ዝምታ ነበርና ሀና የእንጀራ
አባቷንና የተወለደውን ህፃን አልፎም ወንድ የሚባል
ፍጡር ጠላች በትምህርቷም እጅግ በጣም በመቀዝቀዝ ከዱርዬ ሴት ጓደኞቿ ጋር ከትምህርት በመፎረፍ አጓጉል ቦታ መዋል ጀመረች...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_ሁለትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_2

...🖊ሀና ገና በ14 አመቷ ወደ ሺሻና ጫት ቤቶች ጎራ ማለት
ጀምራለች ክፍል ውስጥ ገብታም እንደተማሪ ትምህርት
ከመከታተል ይልቅ የተለያዩ የፍቅር ልብ ወለድ ታሪኮችን
ማንበብ ታዘወትራለች ጓደኞቿ ስለፍቅርና ፍቅረኛ ካወሩ
የምታስታውሰው የእንጀራ አባቷ የሚያደርስባትን ጥቃት
ነው ለዚም እነሱ ሲያወሩ በፍጥነት ካጠገባቸው
በመነሳት ብቻዋን ጓሮ ሄዳ ታለቅሳለች እነሱም ችግሯን
ስለማያውቁ "እይዋት ሚጢጢዋ ልጅ ስታፍር " ይሉና
"....ካካካካ" ብለው ይስቁባታል ሁሌም እራሷን እንደ
እርካሽና እንደማይፈለግ እቃ ነው የምትቆጥረው የሀና
እናት ምንም እንኳ የልጇ ከለት ወደለት ፀባይ መቀየር
ቢያሳስባትም ምክንያቱን ባለማወቋ ምንም ልትላት
አልቻለችም...
የክረምት ወቅት በመሆኑ ትምህርት ተዘጋ ይሄኔ ሀና
በግንብ ሞያ ከሚተዳደረው የእንጀራ አባቷ ጋር ቀን ስራ
ለመስራት ወሰነች ይህንም የምታደርገው ለመጪው
አዲስ አመት ትምህርት ሲከፈት ለደብተርና ዩኒፎርም
እንዲሁም ለልብስ መግዣ ገንዘብ ለማግኘት ነበር ሃና
ለሷ ብላ እንጀራና ዳቦ በመሸጥ ቤተሰቡን ለምታግዘው
እናቷ ከልቧ ታዝናለች ለዚም ነበር ስራ ካልሰራው ስትል
ቴድሮስ(የእንጀራ አባቷ) "ከኔ ጋር ትስራ" ብሎ ሀናን
ያሳመናትና ...
ይህን ስትወስን ቴድሮስ በደስታ ነበር የተስማማው እናቷ
ግን "ልጄ ገና በ14 አመቷ ቡለኬትና ባሬላ ብትሸከም
ትጎዳለች" ብላ ተቃወመች ሆኖም ቴድሮስ "ልጄ ማለት
አደለች እንዴ ደስ እንዲላት ብቻ ትዋል እንጂ ከባድ ስራ
አላሰራትም " በማለት አሳመናት... ይሄኔ ሀና በልጅነት
ልቧ ገንዘብ ማግኘት መቻልዋን ብቻ እያሰበች ስራዋን
ጀመረች ያያት ሰው ሁሉ ያዝንላት ነበር ቴድሮስም
ከምድር ጀምሮ አራተኛ ፎቅ ድረስ 4 ቡለኬት ያሸክማታል
እዛ ላያቸው እንኳን የልጁ እህት የሚያቃትም
አይመስል... ሁሌም ቅስም የሚሰብር ንግግር
ይናገራታል በተለይ ሁሌም ከስራ ሲመለሱ "ቀን ስራ ደስ
ይላል አይደል በይ ልመጂው መቼስ ከዚ የተሻለ ህይወት
አይኖርሽ" ይላታል...
ሀና ግን ካለፈውና አሁን እያየች ካለችው የፈተና ህይወት
የባሰ ውስጧን የሚያቆስል ነገር ገጠማት... ቴድሮስ
በእናቷ ላይ ሲማግጥ በአይኗ ማየት ጀመረች በዛ ላይ
ምንም አታውቅም ብሎ ስለሚንቃት በፊትዋ አብረውት
ከሚሰሩት ሴቶች ጋር ቦታ ይቀጣጠራል ከሁሉም በደሎች
ይልቅ ደግሞ ይህን መቋቋም ከበዳት ... ለእናቷ ሁሉንም
ነገር ልትነግራት ትወስንና "እናቴ በንዴት አንድ ነገር
ብትሆንስ ?..ወንድሜስ እንደኔ ያላባት ወይ ያለእናት
ቢቀርስ ?" ትልና ብቻዋን አልቅሳ ትተወዋለች...
ክረምት አልቆ በአል ደረሰ ሀና ድሮ ቢሆን በአልን በጉጉት
ጠብቃ በፍቅር ነበር የምትቀበለው አሁን ግን ቅፍፍ
ብሏት ነበር... ከእናቷ ጋር ሽር ጉድ ስትል ውላ አመሻሽ
ላይ አፀደ ጎረቤት ቡና ተጠርታ ሄደች ሀናም ቤት
ያፈራውን ቀማምሳ እጅግ ልቧን የሚነካውን "የጭን
ቁስል" የተሰኘ ልብ ወለድ ታነባለች ይሄኔ ገርበብ ብሎ
የተዘጋው የቆርቆሮ በራቸው ተከፍቶ አንድ መጠጥ
ያደከመው ሰው ገባ ... ቴድሮስ ነበር
... ፈገግ ብሎም ተጠጋትና "ዛሬ የእውነት እናድርግ
ላንዱ ዱርዬ ድንግልናሽን ሳትሰጭው እንደጀመርኩ
ልጨርስሽ..." አላት ሀናም በድንጋጤ ወደ አልጋው ጥግ
እየሸሸች ለቅሶ በተቀላቀለበት ድምፅ ትለምነው ጀመር...
በዚ ቅፅበት የውጭው በር በሀይል ተንኳኳ...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_ሶስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት # @BINCJ90 ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90
2025/07/13 13:25:34
Back to Top
HTML Embed Code: