Telegram Web Link
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፲፯ ~ ( 17 )

ቀዳማዊ ጋመን ጋመን አላት በጣም ሞቋል። እንደሞቀና እንዳመመው ስታውቅ ወጣ ብላ ለእነ ማለፊያ " በሉ ዛሬ እናንተ ናችሁ እረኞች ገንዘቦቹን የምታግዱት ቀዳማዊ አሞታል።" አለች።" አይደለም መታመም እና ለምን አይሞትም። እና እኔ ምን አገባኝ እኔ ዙሮ አላግድም።" አለች ማለፊያ " በይ መቼም ባልረባ ነገር እኔና እናንተ አንጣላም። እንዲሁ ሳልናገር የምትሰሙኝና የምትረዱኝ ይመስለኛል። አሁን ዙሮ ያልኳችሁን አድርጉ " አለች አትጠገብ " ኧረ ነው እንዴ?" ብላ ማለፊያ የነገር ነጋሪቷን መጎሰም ጀመረች። " በይ ልጄ ያልኩሽን ብቻ አድርጊ አሁን እንደዚህ አሞት ብንልከው በዛው ነው የሚቀረው!" አለች " እና ቢቀርስ ስላለ አይደል እንዴ ደስታችንን የተነጠቅነው ። ሞቶ ለምን አይገላገለንም። " አለች ርብቃም እጇን ወደ እናቷ እያወራጨች። ሁሉም " ቢሞት ይሻለናል። ምን ኖሮም አይጠቅመን በኋላ እያሳደደ ነው የሚያሰቃየን " አሉ። ወይዘሮ አትጠገብ ግን ያለችውን ብላ ምንም ሳትመልስላቸው ወደ ቤት ገባች። እነ ማለፊያም እያጉረመረሙ አማራጭ እንደሌላቸው ሲረዱ እናታቸው ባለችው መሰረት ገንዘቦቹን ለማገድ ወሰኑ።በዚህ መልኩ በማግሱትም እየተማረሩና የቀዳማዊ ሞት በቅርቡ እንዲሆን አጥብቀው እየተመኙ ለሁለተኛ ቀን ገንዘቦቹን አገዱ።ቀዳማዊይም ለሁለት ቀን ታሞ ከቆየ በኋላ በሶስተኛው ቀን ትንሽ ሲሻለው ወደ መጀመሪያው የእለት ተእለት ኑሮው ተመለሰ። ከትምሀርት ቤት እንደተመለሰ ለመጠበቅ ሄዶ ከአንደኛይቱ እህቱ ጋር ይተካል። የበልጉ ዝናብ መዝነቡን ተያይዞታል። ይህ የበልግ ዝናብም ገበሬውን ከተኛበት እንዲነቃ የሰቀለውን ሞፈርና ቀንበር እንዲያወርድ፣ ድግሩን እንዲጠርብ ፤ ማረሻውን እንዲያስል፤ እርፉን እንዲቆርጥ፣ ጅራፉን እንዲፈትል፤ የሚዘራውን ዘር እንዲያፈላልግ ያደረገ ደወል ሆኗል። በዚህም መሰረት ገበሬው ዝግጅቱን ጀምሯል።እርፉን ከማረሻው ጋር ማዋደድ፣ የቀንበሩን ቁርበት በበሬው ትከሻ ልክ ማስተካከል፤ የምናር ገመዶችን ማስተካከል ጀምረዋል። አልፎ አልፎም በሬዎቹ እርሻ ማረሱን እንዳይረሱት በባዶ ቅብቅብ ወይም ጥንጫ መሬት ላይ ጠምደው ያዞሯቸዋል። ያልቀኑ ወይፈኖች ካሉም ተጠምደው እንዲቀኑ ይደረጋሉ። ይሄ የሚያዚያ ወር የፆም ወር እንደመሆኑም በብዛት ዝናብ አያጣውም። አሁን ግን ፆሙ የማብቂያ ሳምንት ላይ ደርሷል። ሀሙስ ደግሞ በተለምዶ ፀሎተ ሐሙስ ባዕል ነው። ዳቦ ተቆርሶ የሚበላበት። ታዲያ በዚህ የመጨረሻ የፆም ሳምንት ሰው ሰላም ማለት አይቻልም እ ሌላው ደግሞ በስመአብ ተብሎ አይቆረስም ኪራላይሶ እየተባለ ነው የሚባረከው የሚቆረሰው። ሀሙስ ታዲያ ይህ የፀሎተ ሐሙስ በዐል የታላቁ የትንሳኤ በዐል ማዳረሻ በዐል ነው። አርብ ስቅለት ቅዳሜ አክፍለት እሁድ ደግሞ ትንሳኤ ብርሃን። የትንሳኤ በዐልን ታዲያ ለብቻ ስለማይከበር ማለትም ልጆች ተጠርተው ካሉበት መጥተው ስለሆነ ወይዘሮ አትጠገብም ከወዲሁ ከርብቃ በታች ቀድመው ያገቡትን ሴት ልጆቿን ምላሽ ለመጥራት ሽር ጉድ እያለች ነው። ጠላም ለመጥመቅና ለማዘጋጀት ደረቆቱን ፈጭታ አብሽሎውንም እየጋገረች ትገኛለች። እነ ማለፊያ ደግሞ ለበዓል የሚሆን እንጨት እየለቀሙ በዛውም ቀዳማዊይን ገንዘቦቹን ከሚያግድበት ስፍራ ድረስ በመሄድ በነገር እየጎነተሉ ይመለሳሉ። ታላቁ የሁዳዴ የአብይ ፃም አልቆ ትንሳኤም ደረሰ። በዚህ የትንሳኤ በዓል ታዲያ ከአገር ውጪ ያሉ ወደ አገራቸው ገብተው፣ ወደ ሌላ ቦታ ለትምህርት የሄዱም ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው የሚያከብሩት ልዩ በዐል ነው። የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ራሳቸውን በፆም በፀሎት ከቆዩ በኋላ ትንሳኤ የሚፈስኩበት እለት ። በዚች የገጠር ቀበሌም ያገቡ ሴት ልጆች ባሎቻቸውን ይዘው ወደ እናት አባታቸው ቤት በጥሪ ይሄዳሉ። አንዲት ሴት ልጅ አግብታ በቤተሰቦቿ የትንሳኤ በዐል ለምላሽ ካልተጠራች በባሏ ወገንም ሆነ በባሏ ትነወራለች። ትንቋሸሻለች። ስለዚህ ይህን ባህል ስለሚያዉቁ የሴቷ ቤተሰቦች ባይኖራቸውም እንደምንም ብለው ቢያንስ አንዴ ሙክት አርደው የልጃቸውን ባል ምላሽ መጥራት አለባቸው። ባልየውም ምላሽ ተጠርቶ ሙክት ቀፍፎ አቅማዳ ማልፋት ካልቻለ በሴቷ ቤተሰቦች በኩል ይነወራል " ምን ይሄ ሶላቶ ሴት አውል " ይባልና ይናቃል። ምን አልባትም ልጃቸውን ሊነጥቁት ማለትም ሊያፋቱት ይችላሉ። በዚህም መሠረት የልጅቱ ባል ተጠንቅቆ የሙክቱን ቆዶ ገፍፎ አቁማዶ ማድረግ ይጠበቅበታል። አቁማዳው ለብዙ ስራዎች ይጠቅማል። በተለይ እህል በሚወቃበት ወቅት እህል ተቋጥሮበት ወደ ቤት የሚጓጓዘው በአቁማዳ ነው። ስለዚህ በጣም ሰፊ ጥቅም ስላለውና አቁማዳ ለማድረግም ከባድ የሆነ ጉልበት ስለሚያስፈልግ ነው በብዛት አማቾች እንዲያለፉ የሚደረገው።
የወይዘሮ አትጠገብ ልጆች ሰላምና ዘውዲቱም በዚህ የምላሽ ጥሪ መሠረት ባሎቻቸውን አስከትለው ለበዓል ቤት ተገኝተዋል። ከታላቅ እህታቸው ከርብቃ በፊት ያገቡት እንጨት ለመስበር በሄዱበት ተደፍረው ዲቃላ ስለያዙና በዛው ደፋሪዎቹ እንዲጠቀልሉ በሽምግልና በመወሰኑ ነው።
እረኞች በፋሲካ በዓል በቤታቸው ያለውን ሽር ጉድ ማን ቤት እንደመጣ፤ ምን እንደታረደ የታረደውን የፍየልም ሆነ የበግ ስም ሳይቀር ለባልንጀሮቻቸው ያወራሉ። ሌላው በዚህ የፋሲካ በዐል በጉጉት የሚጠበቀው በምላሽ የተጠሩት ያገቡት ሴቶችም ሆነ ገና ያልተዳሩት ልጃገረዶች ሳዱላዎች፣ ኮበሌዎች፣ ህፃናቶች፣ በጉጉት የሚጠብቁት "እሽው ላሌ" የተሰኘውን ባህላዊ ጨዋታ ነው። ይህ እሽው ላሌ የተሰኘው ጨዋታ በመንደሩ ያሉ ሴቶች ገመድም ሆነ ጠፍር አዋጥተው ብዙ ገመድና ጠፈር ተሰብስቦ ከዛ ለሁለት እኩል እኩል ይካፈልና ከአንድ ትልቅ ዛፍ ላይ በሁለት ረድፍ ታስሮ ይወርዳል ከዛ ከታች ከመሬት የተወሰነ 50ሳንቲ ሜትር ከፍ ብሎ ይዋልና ማለትም ይቋጠራል። አንድ ሰው ወጥቶ ቁጭ ይልበታል።መያዝ እንደቻለና እንዳልቻለ ይፈተንና በደንብ ታስሮ ከዛ በተራ በተራ እየወጡ ገመዱ ላይ ቁጭ ብለው በአንደኛው ረድፍ ያለውን በአንድ እጃቸው በሌላኛው ገመድ ደግሞ ሌላኛውን እጃቸውን አስይዘው ቂጣቸውን ገመዱ እንዳይበላው ጨርቅ ነገር ተጎዝጉዞ ከኋላ እየተገፉ እሽው ይላሉ።ታዲያ ይሄን እሽው ላሌ ጨዋታ ለእንግድነት የተጠሩት ሳይቀር ከትንሽ እስከ አዋቂ የሚታደሙት አዝናኝ ጨዋታ ነው። እሽው ለማለት ገመዱ ላይ የተቀመጠችው ሴት " እሽው ላሌ የሚለውን ዜማ የማውጣት ግዴታ ይኖርባታል። ዜማው ይጣምም አይጣምም ይነስም ይብዛም እታች ያሉት የመቀበል ግዴታ አለባቸው።እሽው ባይዋ ልጅም ........

እንደተለመደው ሼር ይደረግ
@monhappy
@monhappy
ለአስተያየት
@BINCJ90
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፲፰ ~ ( 18 )

እሽው ባይዋ ልጅም ባላት ድምፅ ፍርሃቷን እንደምንም በመቋቋም
" እሽው ማለት
የፋሲካ እለት "
እያለች ኮረዳዋ ታወጣለች በአንድ ላይም " እሽው " አያሉም ይቀበሏታል።በዚህ ሁኔታ እያወጣች ደክሟት ልውረድ ካላለች ማንም ውረጅ አይላትም። እሷም ልውረድ ስትል ዝም ብለው እንደማያወርዷት ጠንቅቃ ስለምታውቅ ያው አስጋሪዋን ኮበሌ ክንዱን ለማድከም ለመቆየት ትጥራለች ነገር ግን ካልቻለችና ደፍራ ልውረድ ካለች ታዲያ "ማነው ባልሽ? " የሚለውን ጥያቄ የመመለስ ግዴታ አለባት። ይህን ጥያቄ ታዲያ ያገቡት ከሆኑ የባላቸውን ስም ይናገራሉ ያላገቡት ልጃገረዶች ግን ጥያቄው ስለሚያሳፍራቸው ይሽኮረመማሉ። ግን ካልተናገሩ ደግሞ ይበልጥ ስለሚሰግሩ " ባላችን አውራ ደሮ ነው" እያሉ ለመውረድ ሲሞክሩ አስጋሪው ኮበሌ ታዲያ " ስራ አጥቶ አውራ ደሮ አፈሩን መጫር ትቶ አንቺን ሲጭር " ይልና " ይልቅ ተናገሪ " ይላታል። ይሄኔ ሳትወድ በግዷ የአንዱን ኮበሌ ስም ትጠራና ትወርዳለች። በዚህ ጊዜ አስጋሪው ልጅ የተጠራው ኮበሌ ልጅ ካለ ዘወር ብሎ አይቶ " ና ሚስትህን አውርድ ይለውና " ቦታ ይለቃል። የሰፈሩ እረኛም ታዲያ ቀበል አድርጎ " እንትና የእንትና ሚስት ፣ የእንትና ሚስት እንትና የእንትና ባል " እያሉ ስሟን እየጠሩ የጠራችውን ልጅ ባሏ አድርገው እየጠሩም ያበሽቋታል። ይሄው ተናፋቂ በዓልም በዚህ አመት ተጀምሮ ሁሉም እየተዝናና ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ።ያው እንደ ደንቡ ኮረዳወችም በግድ ባላቸውን እየተናገሩ እየወረዱ ነው። ጨዋታው ደርቷል። ይህን ሁሉ ትዕይንት ራቅ ብሎ የሚመለከተው ቀዳማዊ በሀሳብ ተውጦ በአይኑ ብቻ እያያቸው በልቡ ብዙ ሀሳብ እያጠነጠነ ያ~ድራል። በዚህ ጊዜ ነበር ከህልም አለም ከሚመስል የተመስጦ ቅፅበት እረኞች ሲጠሩት የነቃው " ምንድነው?" ብሎ የጠሩትን እረኞች ጠይቆ ተነሳ " ና ሚስትህን አውርድ አየተባልክ ነው " አሉት። እሱም ባህሉን ስለሚያውቀው ያቺን መልከ መልካም ደመ ግቡ ኮረዳ በህጉ መሠረት ለማውረድ ወደ ገመዱ ጠጋ ብሎ አንድ ሁለት ጊዜ ቀስ አድርጎ ከገፋት በኋላ አወረዳት። ወዲያው እንደወረደች አፍራ አይኗን በክርኗ ሸፍና እየሮጠች ሄዳ ለብቻዋ ቁጭ አለች። እረኞቹም ቀድመው እንደሚሉት " ዳሳሽ የቀዳማዊ ሚስት ቀዳማዊ የዳሳሽ ባል " እያሉ ይጮሁ ጀመር።" አስተማሪ ሲሆን ነው የሚያገባት " እያሉ ይሳሳቃሉ። ዳሳሽም አይኖቿን በእጆቿ እንደሸፈነች ማልቀሱን ተያያዘችው። ሴቶቹ ይሳሳቃሉ። ኮበሌዎቹም " ቀዳማዊይን አግኝተሽ ተጎድተሽ ነው? በወር አንድ ሺህ ብር ደመወዝ ሲበላ ያኔ ደስ ትሰኝ የለ? " ይሏታል። አንደኛው ደግሞ " ምን ይቺ ትነፋረቃለች እኛ በግድ ቀዳማዊይን ጥሪ አላልንሽ አንቺ ራስሽ ስለፈለግሽው ነው እንጅ የጠራሽው እንጅማ ስንት ኮበሌ ሞልቶ አልነበር?! " አለ " እውነቱን ነው ተሁሉም የተማረው እሱ ስለሆነ አይደል የመረጥሽው አንቺው?" አላት ሌላኛው " ደግሞም ጥሩ ጠርተሻል ይዞሽ ኸተማ ይኸዳል። ተዚያ አብራችሁ ትተኙና ኸተሜ ልጆችም ትወልዳላችሁ። ተዚያ ኑሮሽ ሁሉ ጥድት ያለ ይሆናል ማለት ነው።" አለ ሌላኛው። ብቻ የዳሳሽን ማልቀስ በመመልከት ይበልጥ ተረባረቡባት። እሷም በደንብ ማልቀሷን ቀጠለች።
ቀዳማዊ ጠጋ ብሎ ዳሳሽን ሊያባብላት ቢፈልግም ለእረኞቹ ይበልጥ መንገድ መክፈት እንደሆነ ና እንደሚስቁ እንደሚቀልዱባት እንዲሁም እንደሚያነዷት ስላወቀ ትቷት ከሙሉቀን ጋር ከእዛ አካባቢ ተሰወረ።ከሙሉቀን ጋር የተወሰነ ረጅም መንገድ ከተጓዙ በኋላ " ግን ባልንጀሬ ደስ አላለህም?" አለ ሙሉቀን " በምኑ ?" አለ ቀዳማዊ በግርምት ሙሉቀንን እየተመለከተው። " ያው ዳሳሽን የማይመኝ የእኔ ብትሆን የማይል የለም ከዛ ሁሉ አንተን ስትጠራ እኔ በበኩሌ በጣም ነው ደስ ያለኝ።" አለ ሙሉቀን ቀዳማዊ እንደመሳቅ አለና " ልጅቱ ለመውረድ ብላ እኔን ብትጠራ አንተም እንደሌሎቹ ልታመር ባልሆነ ? በል አረጋጋው ጓደኛየ እኔን በበኩሌ በዚህ ስአት ስለ እሷ እኔን መጥራት ሳይሆን የማስበው ስለሚመጣው የ ፰[8]ኛ ስፍል ማጠቃለያ ፈተና ነው። ይሄን ፈተና በብቃትም ሆነ በስለት የግድ ጥሩ ውጤት በማምጣት ላልፍ ይገባል። " አለ " ልክ ነህ ቀዳማዊ ወንድሜ እሱስ " አለ " እነዛ ሰይጣኖች መሰናክል ካልሆኑብህ አንተ እንኳ እንደምታመጣ አልጠራጠርም " አለ ሙሉቀን በሆዱ
እነ ቀዳማዊ ጋራውን ዙረው እንኳ እረኞቹ ዳሳሽን ከማብሸቅ አላረፉም። ከእነዚህ ኮበሌዎችና ወጣቶች መሀል ግን አንድ ልጅ ዳሳሽን በንቀት ይመለከታታል። ለጓደኛውም እኔ ጀግናው የደጃዝማች ፍቅሩ ናደው የልጅ ልጅ እያለሁ የማንንም ውልንፍጥ የአስኮላ ተማሪ ትጠራለይ? "ፐ አለ ብትሩን ወደ ላይ ወደ ታች እያደረገ መሬቱን እየመታ " እሱን እንኳ ተወው ቀዳማዊይስ የዋግሹም ጎበዜ ዘር እንዳለበት አጣኸውን ይሄን ተወውና ግን ምን ታደርገዋለህ እንግዲህ ዘመኑ የተማሪ ነው። ሁሉም ነገር የሚቀለው ለተማረ ነው ደግሞ እኮ እንዳለ ሴቱን የፈጀው የአስኮላ ተማሪ ነው። ነይ ላስተምርሽ ነይ ላስቀዳሽ እያለ ስንቱን ሴት ነው ያባለጉት ይችስ እንደው ገና ከአሁኑ ልቧ ወደ ቀዳማዊ በምን እንደሸፈተ እናውቃለን?" አለ ጓደኛው " ኧረ ተው ባልንጀር እሱን እንኳ ተወው እንደው ነገሯ አናዶኝ ነውይ ቀዳማዊይ እንኳ ሴት የሚተናኮልበት እድሜ ላይ አይደለም። እንደው ሌላ ቢሆንስ መቼም " አለ " ኧረ ባክህ ማነው ያለው? ቀዳማዊ ስንት አመቱ ነው?" አለ ቱግ ብሎ " አስራ ሶስት ነዋ ጓዴ " " እና አስራ ሶስት ትንሽ ሆኖ ነው? ለወንድ ልጄ እኮ በቂ ነው" አለ " ለምኑ ነው የሚበቃው አንተ ደግሞ ገና ነው ስልህ በዛ ላይ አላየኸውም እንጅ ዘወር ብሎም አላያት ።ምን አልባት እሷ ከጅላው ይሆናል እንጅ እሱ በጭራሽ ተቀልቡም አይዶላት። እሱ ለራሱ ብዙ አውታታ አለበት ። " አለ " እንግዲህ አንተ መቼም አንዴ ታልህ አልህ ነው። ጥሩ " ግን ታልሆነ ተማሪ ቤት ልግባ እንዴ " አለ " ኧረ በእስተርጅና አሁን ብትገባማ የማንም መሳቂያ ነው የምትሆነው በዚያ ላይ የትምህረርት እድሜው ስለተላለፈህ ቶሎ አይገባህም ትምህርትኮ በልጅነት ነው " አለና ሳቀ " አንተው እገባለሁ የግድ መግባት አለብኝ " አለ " ገና ለገና የዳሳሽን ይሁንታ ለማግኘት ብለህ የማንም መሳቂያ ትሆን ሚዜዬ ? ኧረ ባክህ ቀልብ ግዛ " ብሎት ትቶት ሄደ።
ሙሉቀንና ቀዳማዊይም በእለተ ፋሲካ ሲያግዱ ውለው እንደወትሮው በበልግ ዝናብ ተመትተው ወደ ቤት ተመለሱ። ቀዳማዊ ቤት ሲደርስ ለብዙ አመት ሲሞከት የነበረው ሙክት ታርዶ እነ ማለፊያ ሽርጉድ እያሉ ምላሽ የተጠሩት እህቶቹን ደግሞ ከነባሎቻቸው ተቀምጠው አገኛቸው። ባሎቻቸውን እጅ ነስቶ እህቶቹን ደግሞ ተገናኝቶ ተቀመጠ። ወይዘሮ አትጠገብም........


ያው በቅንነት ሼር አድርጉ
@monhappy
@monhappy
ለአስተያየት
👇
@BINCJ90
:)
ይቅርታ ሂወቴ😔

ሂወቴ ምንም እንኳን እኔ ያንተ አንተ የኔ ባትሆንም ስላወኩህ ግን በጣም ደስተኛ ነኝ....



💐 @monhappy 💐
🛋 @BINCJ90 👫
:)
ሁላችንም…ነገ ምን ይዞ እንደሚመጣ አናውቅም…ግን ሁላችንም ያን ነገ እንጠብቃለን…ከእስከ ዛሬውም የተሻለ ነገ ይሆናል ብለን እናምናለን…

አዋ እኛ ኢትዬጵያኖች ደሞ… የመጣንበት መንገድ አድክሞናል…ደስታንም ፍለጋ በብዙ ኳተናል…እኛ ያላየነው መከራ የቱ ነው?…እኛ ያላነባነው የቱን እንባ ነው?…እኛን ዝቅ ያለረገንስ መንገድ የቱ ነው?

ጌታ ሆይ በቃቹህ በለን 🇪🇹😔
ሀዘናቹን አሰብኩት🙏🏽
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፲፱ ~ ( 19 )


ወይዘሮ አትጠገብም የቀዳማዊይን መምጣት በተመለከተች ጊዜ ዱለት በጥርኟ ሰጥታው ተቋድሶ ተቀመጠ። ራት እስኪደርስም ሁሉን የራሱን የልጅነት ታሪክ ገጠመኝ እያወሱ ይጫወታሉ።የልጅነታቸውን ገድል ስንፍና እንደ ማስረጃነት እያቀረቡ እየተሳሳቁ እንደ ቄብ ደሮ ሲያሽካኩ አመሹ። ወይዘሮ አትጠገብም ሁሉም ልጆቿ ስላሉ ፊቷ በደስታ እንደ መስከረም አደይ አበባ ፈክቶ ይታያል።በዚህ የሳቅና የጨዋታ ግርግር መሀል ራት ደርሶ ሁሉም በእድሜያቸው በማዕድ ተሰየሙ። መጀመሪያ ትልልቅና እንግዳ ስለሆነ የሚበላው እነ ርብቃና እህቶቿ በሉ። ቀዳማዊይም ሻማ ይዞ ታላላቆቹንና እንግዶቹን አብልቶ ማዕድ ስመው ሲጨርሱ የነሱን ትራፊ እናቱ አስጠግታ እንዲበላ ምልክት ስትሰጠው ወደ ራሱ አስጠግቶ በላ ። በዚህም የጡንቻ አጥንቱን ወይዘሮ አትጠገብ ለሁለቱ አማቾቿ ና ለባሏ አከፋፍላ ለቀዳማዊይም የጎን አጥንት ሰጠችው። ቀዳማዊይም የነካካ እንጀራውን በልቶ አጥንቱንም ግጦ ሲጨርስ በጣም ስለጠገበ ብቻም ሳይሆን ምግቡንም ያለምንም ነገር በልቶ ከሆዱ ስለተቀመጠ ደስ አለው።በሙሉ ሀሴት ተሞልቶም ፈገግ በማለት የውስጡን የደስታ ብርሃን ገለጠ። ማዕዱንም ብዙ ጊዜ ስሞ አንስቶ ከድኖ አስቀመጠ።ወይዘሮ አትጠገብም ሆነ እነ ማለፊያ ፊቱ ላይ ያለውን ደስታ ሲያዩ ግራ የተጋቡ ይመስላሉ ። ነገር ግን ቀዳማዊይን የደስታው ምንጩ ምን እንደሆነ ለመጠየቅ አልሞከሩም።
****
መምህር ደረጀ ከቀዳማዊ ጋር በአካል ከተለያዩ የተወሰኑ ቀናቶች ተቆጥረዋል። ቀዳማዊ ባደረገው ድርጊት ከትምህርት ቤቱ ከተባረረም ሶስት ቀን አልፎታል።ባለቤቱ ትህትናም እያፅናናችው ነው። እሱ ግን የሚያዝነው ባጣው የመምህርነት ስራው ሳይሆን ገና በለጋነቱ ባልበረቱ ክንዶቹ ባልደነደኑ ልቦቹ መከራና ስቃይን ተቀብሎ ለማሳለፍ እየተነሳ እየወደቀ ስላለው ትንሹ ቀዳማዊ ነበር። መምህር ደረጄ የወለደው ልጁ የአብራኩ ክፋይ እስኪመስለው ድረስ ነው አንጀቱ የሚንሰፈሰፍለት የሚያዝንለት ግን ደግሞ ልቡ ቀዳማዊ አንድ ቀን ትልቅ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ያምናል። አሁን ግን ሌላ ትምህርት ቤት ተቀጥሯል። ወደ ትውልድ ቦታው አቅራቢያ የሚሆን ከቀዳማዊ መኖሪያ የገጠር ቀበሌ የተወሰኑ ቀናትን ማለትም የ2 ቀን ብቻ የሚርቅ። ነገር ግን እዛ ቀዳማዊ የሚማርበት ትምህርት ቤት ላሉት የአስተማሪዎች ጓደኞቹ ስለ ቀዳማዊ አደራ ብሏቸዋልና የቀዳማዊይን የእያንዳንዷን የውሎ ተግባሩን ምን እንደሚመስል ይነግሩታል። ሁሉም ይጠይቃቸዋል። ስለ ነገውም ጥሩ ነገር እንዲገጥመው እዛ አካባቢ እንዲወጡና ህይወቱን ሌላ ቦታ እንዲኖር ይመኝለታል ይፀልያልም። የትንሳኤ በዐል አልፎ ከሳምንት በኋላ የተከበረው የግንቦተ ማርያም በዐልም አልፎ የ ፰[8]ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ደረሰ። ቀን ከበጎቹ ጋር ጫካ ውሎ ማታ ከእናቱ ምሬትና ከእህቶቹ ስድብና ግልምጫ እያስተናገደ አብዝሃኛውን የትምህርት አይነት ለመዳሰስ ሞክሯል።ነገር ግን በጥልቀት የሚያነብበት የጥሞና ጊዜ አላገኘም።ያነበበው እንዲመጣለት እየፀለየ ባለው ቀሪ ጊዜ እያነበበ ለፈተና ደረሰ። አስፈሪውና አስጨናቂው የፈተና ጊዜም በብዙ የፖሊስ አጃቢዎች ታጅቦ የፈተናው ቀን ሀ ተብሎ ተጀመረ። ቀዳማዊይም የመጀመሪያውን ፈተና ጨርሶ ወጥቶ ሲመለስ እንደሌሎቹ " አይዞህታና መልካም ምኞት የሚሰጠው እናትም ሆነ እህቶች ባይኖሩትም፦ በዛ እድሜው አንድና አንድ ትምህርትን ብቻ በማለም እራሱን እያጀገነ እያበረታ ከፈተና መልስ ገንዘቦቹን እንዲጠብቅ የተሰጠውን ትዕዛዝ ተቀብሎ በአንድ እጁ የመቅረቢያ ለበቁን በአንድ እጁ ቀጣይ የሚፈተነውን ትምህርት ደብተር ና መፅሐፍ ይዞ እያነበበ። በብዙ ፈተና ተሞልቶ ይህኛውን ፈተናም እንደምንም ጨርሶ ከፈተናው በኋላ ከክፍል ከጓደኞቹ ጋር የመልካም ዕድል ምኞት ተመኛኝተው ተለያዩ። የአመቱ ማብቂያ መጨረሻ የወላጆች በዐል ላይም እንደተለመደው የአመቱ ጎበዝ ተቀዳሚ ተሸላሚ ተማሪ "ቀዳማዊ" ተባለ። ዝምተኛው ኮከብ እንደከዚህ ቀደሙ ከሁሉም የሱ ክፍል ተማሪዎችና ከሁሉም ክፍል የተሻለ በመሆን የሽልማት አክሊልን ተቀዳጀ። መምህራኖች፣ የተጠሩ ወላጆች ለቀዳማዊ ከመቀመጫቸው ተነስተው አድናቆታቸውን ቸሩት።
ቀዳማዊ በደስታየ እንባውን ዘለላዎች ጣል ጣል አደረጋቸው። ለደስታ አስመስሎ ፈገግ ቢልም የሀዘን እንደሆነ ግን በስሱም ቢሆን ያስታውቅበታል። ዙሪያ ገባውን ቀስ ብሎ ዞሮ አማተረ። ብዙ መምህራን የወላጅ ቤተሰቦች አሉ። ሁልጊዜም ለመሸለም ወደ መድረክ ሲወጣ አንዳቸውንም የቤተሰቡ አባልም ሆነ እናቱን አያይም። ግን መምህር ደረጄ ቢኖር ይህን ሁሉ ማስተዋል ባልቻለ ነበር። እሱ ባለመኖሩ ቅር እየተሰኘ ሽልማቱን ተቀብሎ ከመድረክ እስኪወርድ ድረስ ጭብጨባው አልተቋረጠም ነበር። ቀዳማዊይም ምን .........
ሼር
@monhappy
@monhappy
ለአስተያየት
@BINCJ90
:)
ከሁሉም በፊት ግን ፈጣሪህን ፈልግ !

ፈጣሪን ፈልጋቹ ዘንድ ምኞቴ ነው…እኔ ግን አልፈርድም…

🎍 @monhappy 🎍
🌹 @BINCJ90 🌹
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳ ~ ( 20 )


ቀዳማዊይም" ምን አለ ከእነዚህ ሰዎች መሀል ሆና እንደ ሁሉም ሰው የደስታ ጭብጨባውን ብትሰጠኝ ልጄ ገበዝ እደግ በልልኝ ብላ ብታቅፈኝ። አኔም እናቴ ይሄው እኔ ያንቺ ልጅ አላሳፍርሽም መቼም ቢሆን ብላት " አለና ወደ መቀመጫ ወንበሩ እየሄደ አለቀሰ።
" አይይ በስተማታ ልጅ መውለድ ትርፉ ለሌላ ሰው ልጅ ማድረግ ነው። አሁን ምን አለ ትንሽ ቆይቶ ቢሆን " እያሉ ስለ አቶ ታረቀኝ ሞት መፍጠን ፈጣሪን እየተቃወሙ ቀዳማዊይን በሀዘን ይመለከቱታል። " ደግሞ ራሱን ቁጭ አይደል እንዴ ያደረገው ወቸው ጉድ ቁጭ እሙር አቶ ታረቀኝን አሁን ይሄን ልጅ አይቶ ማን ዝም ብሎ አልፎ ይሄዳል ማንስ ይሳሳታል? " እያሉ ያወራሉ። ቀዳማዊ ከሽልማት ስነስርዓት ማብቂያ በኋላ ወደ ቤት ሲመለስ ያው የተለመደው ፊት ነው የተሰጠው እንደውም ማታ ላይ ሁሉም በተሰበሰቡበት " ከዚህ በኋላ የማስተማር ግዴታ የለብኝም ራስህን መቻል አለብህ ለዚህም ደግሞ መስራት ግዴታ አለብህ ። እኔ አንተን ቁጭ አድርጌ ልጠወር አልችልም። ከዘንድሮው ክረምት ጀምሮ ማረስ፣ ማረም ማጨድ ይሆናል ስራህ ይሄ ሰውየ እናንተን ለማሳደግ ነው ቦታውን ለቆ የመጣው፣ አባታችሁ እንደ ቆሎ ደፍቷችሁ ሲሄድ እኔ በሴትነቴ ሳልችል ስቀር ይሄ ሰውየ ነው መጥቶ ከተደፋችሁበት የለቀማችሁ ያቃናችሁ ስለዚህ መታገዝ አለበት። በተለይ የውጩን ስራ አንተ እየሰራህ ታግዘዋለህ።" አለች ወይዘሮ አትጠገብ ቀዳማዊ ወትሮም ይሄን እንደምትለው አላጣውም። ይችን አመት እስኪጨርስላት ድረስ ስትጠብቀው እንደቆየች ያውቃልና ። አሁን ሁሉም በሮች እየተዘጉበት ነው። ገና በጠራራት ፀሀይ ጨልሞ እንደሚታየው ሰው ተሰማው ከአንድ አካሉ የሆነ ነገር ሲገነጠል ተሰማው ። ሀሳቧንና ውሳኔዋንም ሳይደግፍ በዝምታ ተቀበለ።
****
ክረምቱን እንደ አስራ አራት አመት ልጅ ሳይሆን እንደ ትልልቅ ጎልማሳ ሲያርስ፣ ሲዘራ፣ሲያርም፣ሲጎለጉል፣ በባዕል ቀን ደግሞ እረኝነት ሲሰራ የገበያቀን እህል ይዞ ወደ ገበያ ሲሄድ ሽጦ በምትኩ የተባለውን ሸምቶ እየተመለሰ። ጉንብስ ቀና እያለ በውል እንኳ እንቅልፍ ሳያገኝ ክረምቱን ጨርሶ የጷግሜ ወር ገባ። መስከረም አራት የ፰(8)ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ካርድ እንደሚመጣ ስለተነገረ ውጤቱን በጉጉት ይጣባበቅ ጀመር። በገጠር የቅዱስ ዩሐንስ ማለትም የአዲስ አመት ጠዋት ማለዳ የአዲስ አመት ልጆች ከእንቅልፋቸው በመነሳት የመልካም ምኞት መግለጫ በጠዋት አደይ አበባ ነቅለው በየመንደሩ እየዞሩ ማንም ሳይቀድማቸው እየሰጡ እየተመረቁና ብር እየተቀበሉ ያረፍዳሉ። ቀዳማዊይም ይህን ስነስርዓት ለማካሄድ ከማታ ጀምሮ ሲያስብ ስለሆነ ያደረው በጠዋት የመጀመሪያው ዶሮ ሲጮህ ተነስቶ አደይ አበባውን ነቅሎ ገና ወፍ ጭጭ ሳይል አበባውን በየቤት እየዞረ ማደሉን ተያያዘው። መንደርተኛውም " እድግ በልልን ይህ አመት አንተም ሰላም የምትሆንበት የሚቀናህ የእድል አመትህ ይሁን። አባትህን ለማስጠራት ያብቃህ፣" እያሉ እየመረቁ እናቶች የብር ማስቀመጫ ሙዳያቸውን ባሎች ( አባዎራዎች )ደግሞ የሱሪ ኪሳቸው እየፈተሹ ለቀዳማዊ አስር ብርም ሀያ ብርም አምስት ብርም ብቻ ደስ እንዳላቸው እየሰጡ ይሸኙታል።እስከ ጠዋት ድረስ አበባ እየሰጠ ምርቃትና ብር እየሰበረበ አርፍዶ ወደ ቤቱ ሲመለስ ወይዘሮ አትጠገብ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ጠበቀችው። ልክ ቤት እንደገባ በሌሊቱ ችግር ያለህ አስመስለህ ልመና የወጣህልኝ ማንን አፍ ውስጥ ለማስገባት ነው። ቀጭ የሌለው አባት የሌለው ልጅ ወትሮም እንደዚህ ነው ልታስብለኝ ነው? አንተ የመናጢ ልጅ እንደው በምን ቀን ነው አኔተን የወለድኩት ምነው ያኔ እንግሬ ልዥ የሽንት ውሃ ሆነህ ብትቀር " እያለች ትረግመውና ትመታው ያዘች። ለቅሶውን የሰሙ ና የቀዳማዊይን ሰርክ ለቅሶ የሰለቻቸው ጎረቤቶች ታግሰው ኑረው ወደ እነ ቀዳማዊይ ቤት መጥተው ወይዘሮ አትጠገብን ገላገሏት " እንደው አትጠገብ ምነው ምን ሆነሽ ነውእዚህ ልጅ ላይ ክንድሽ በረታ እንደው ምን አይነቱ ሰይጣን ቢቆራኝሽ ነው።እንደው ምን አለ በአውዳመቱ እንኳ ብትተይው። ደግሞስ የማንም ልጅ የሚያደርገውን እኮ ነው ያደረገው። ደግሞስ ከአመት አመት አደረሳችሁ ብሎ ማንም ሳይቀድመው ቢመረቅ ምን ችግር አለው ምርቃት ቀላል ነገር ሆኖ ነው? ዋ በኋላ ይሄን ልጅ እንዳታጭው ኧረ ጉድ ሲበዛም ጡር አለው።
የሚያድግ ልጅ አይጥላህ፣
የሚወርድ ውሃ አይውሰድህ " ነው የሚባለው " አሏትና በተወሰነ መልኩ እንደመቆጣት ብለው ቀዳማዊይን ከዱላ ሩምታ ለጊዜውም ቢሆን አድነውት ሄዱ። ቀዳማዊ ለቅሶውን ጨርሶ ቀና ሲል ተኮሳትራ በጥላቻና በንዴት አይን ሆና የምታየውን እናቱን በደንብ ተመለከታት።እናቱ አልመስለው አለች።ከእግር እስከራሷ ከእንደገና አያት " ይች ሴትዮ የእኔ እናት አይደለም ቀርቶ የስጋ ዝምድና ለንም ምኔም አይደለችም። ስለዚህ ከዚች ሴትዮና ከነዛ መናጢ ሰይጣን ሴቶች ጋር መኖር የለብኝም።" ሲል ለራሱ ነገረው። ይህንን ሀሳቡንም ለጓደኛው ለሙሉቀን አሳወቀው።" ጓደኛዬ አሁን ሁሉም ነገር በቅቶኛል ከነገ ዛሬ ይተውኛል ከዛሬ ነገ መልካም ፈገግታቸውን አያለሁ ብየ ነበር ግን አሁን በጭራሽ እናቴም እናት አልመስልህ ብላኛለች። ነጋ ጠባ ዱላ ነው ስድብ ነው እኔን አይወዱኝም አብሪያቸው እንድኖር አልፈለጉም። እስኪ እይ የመቱኝን ሰውኔ እኮ እንዳለ ለምፅ ሆኗል። " ብሎ ገልጦ አሳየው። ሙሉቀን ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።" አሁን ሌላ ሰው ጋም ቢሆን እረኝነት ተቀጥሬ በትርፍ ጊዜየ እማራለሁ እንጅ ከእነሱ ጋር መኖር በቃኝ" አለ ቀዳማዊ " አይ እንደዛማ አይሆንም በቅርቡ እንዳለህ ካወቁ ሄደው ያመጡሀል ስለዚህ የሚሻለው ራቅ ብለህ ብትሄድ ነው ደሴ ባሄርዳር አዲስ አቨቫ.ወደ ሚባሉት ትልልቅ ኸተማ ብትሄድ ኤነሱም ፈለገው አያገኙህም ። በያ ላይ አንድ ለነፍሴ ያለ ሰው ያስተምርሀል። የኸተማ ሰውም አዛኝ ነው ሲባል ሰምቻለሁ። አንተሜ ጎበዝ ተማሪ ስለህንህ ደስ ይላቸዋል።" አለ ሙሉቀን " እና እዛ የምሄድበት ብር እኮ የለኝም ከየትስ አገኛለሁ?" አለ ቀዳማዊ በሀሳቡ ተስማምቶ ግን ብሩን የሚያገኝበት መንገድ እያስጨነቀው። " ለሱ መላ እንዘይዳለን አሁን ካርዱን የምትቀበለው መቼ ነው?" አለ ሙሉቀን " የሚመጣው ሀሙስ " አለ ቀዳማዊ " ጥሩ እንግዲህ ካርድህን የምትቀበለው ........



እንደተለመደው ሼር አድርጉ በእናታችሁ እንዴ ጊዜ አትፈጁ ምናለ በአንድ ጊዜ ሼር ሼር ሼርሼር ብታደርጓት

@monhappy

@BINCJ90
:) 🌷🌹🎋🍁

የእሱን ልፍለፍ መስማት ሰልችቶኛል እንዳልሽ ሰማሁ…አዋ ለአንቺ ለፍላፊ ነኝ…ልብ ወለድህም ደስ ይላል አልነበር ያልሺው…ግን እውነት አንቺ እንዳስብሺው አደለም…እኔ ብዙ ጊዜ ጥሩ ሰው አልነበርኩም…

🍂 @monhappy
🌺 @BINCJ90 🌷
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳፩ ~ ( 21 )


"" ጥሩ እንግዲህ ካርድህን የምትቀበለው ........ማንም ሳያውቅ ነው። በጠዋት ተነስተን ገንዘቦቻችንን ወደ በረሃ ለመንዳት እናስወጣና እኔ የአንተን ገንዘቦይ እጠብቅልሀለሁ። አግድልሀለሁ። ከዛ አንተ ሄደህ ወደ ትምህርት ቤት ካርድህን ታወጣና በዚህ በበረሃ አንዱ ዋሻ ላይ እናስቀምጠዋለን።ከዛ ብር ስናገኝ ገንዘቦቹን እንደምታግድ አስመስለህ ትወጣና በዚሁ ትሄዳለህ። እነሱ እንዳያውቁብህ" አለ ሙሉቀን ቀዳማዊይም የሙሉ ቀን ሁኔታ ልክ እንደራሱ ጉዳይ ይዞ እያሰበው እያወጣ እያወረደ እነደሆነ አሰበና " ሸጋ ሃሳብ ነው ሙሌዋ ግን እንደ አንተ አይነት ከወንድም የበለጠ ባልንጀራ ባይኖረኝ ምን እሆን ነበር?" አለ ቀዳማዊ " እሱን እንኳ ተወው ምን አደረኩልህና ነው? " አለ ሙሉቀን " ተወው እሱን ወንድሜ ያደረክልኝን እኔ ነኝ የማውቀው። ብቸኝነት ሲሰማኝ የቦሶቴ መውጫ ነህ ፅሀይ ሲመታኝ እንደ ዶረት ጥላ ትከልለኛለህ። ለእኔ በጣም ትጨነቃለህ ብቻ ወንድሜ የአንተን ውለታ ከፍየ አልጨርሰውም። " አለ ቀዳማዊ " በልማ ዝም በል አታዳንቅ ይልቅ በኋላ ተምረህ የመንግስት ሰሪ ስትሆን የኸተማ ሱሪ ቦላሌ ቦላሌ ኮት የወታደሩን ጫማ ትገዛልኝና ከዛ እኔ በየሰንበቴውና በየቤተክርስቲያኑ በየማህበሩ ልብሼ እኮፈስበታለሁ። " አለና ሳቀ ቀዳማዊ ሳቅ ብሎ " ፈጣሪ ያድለኝ ለዚህ ክብር አንተው " አለ
***
እነ ማለፊያ ሁሌም እየተጫወቱ ቆይተው ማታ ላይ ቀዳማዊ ሲመጣ ጨዋታቸውን ገታ አድርገው እሱን የሚያሽሟጥጡበት የሚያፌዙበት ነገርን ሲያይ ቀዳማዊ በጣም ይገረማል። አንድም ቀን እንኳ በጎነታቸውን ለማየት አልቻለም። እንደሌሎቹ ጎረቤት ሴቶች ወንድሞቻቸውን እንደሚንከባከቡት እንደሚወዱት " ከቶ ግን ለምን ይሆን እንደዚህ የሚሆኑት? ለገንዘብ? እውነት ከእኔ ገንዘቡ በልጦባቸው ነው?" እያለ ራሱን ይጠይቀዋል። ዛሬም የተለመደውን ሁኔታ ሲያይ ብዙም አልተገረመም። ከቀናቶች በኋላ ታዲያ ከሙሉቀን ጋር በተባባለው መሠረት ካርዱን አውጥቶ ከዳንታሮ ዋሻ ውስጥ ዝናብና ፀሀይ እንዲሁም እረኞችም በዝናብ ወቅትም ስለሚጠለሉበት እንዳያገኙት ሰወር ያለ ቦታ ፈልጎ ላዩ ላይ በካርዱ ልክ ጠፍጣፋ ድንጋይ ጭኖ ደብቆ አስቀመጠው። ያመጣውን ውጤት ደግሞ እንደ ወንድሙ ለሚያየው ጓደኛው ሙሉቀን ነገረው። 94 ነጥብ ነበር ያመጣው። የክልሉን ፈተናም ከሶስቱ ወረዳዎች የበለጠው የሱ እንደሆነ ካሬዱን ለመቀበል በሄደበት ጊዜ ርዕሰ መምህሩ እንደነገረው ለሙሉቀን ነገረው። ሙሉቀን በደስታ አቀፈው " እና ከዚህ ሁሉ ህብ ልይ ኑሮ ደልቷቸው ምንም ስራ ሳይሰሩ መግብ በስአቱ እየተመገቡ ሲያጠኑ የነበሩትን ሁሉ በልጥካቸው? ኧረዳ እንኳንም ጓደኛየ ሆንህ አሁን ነው ይበልጥ ያኮራኸኝ ኧህ እንዲህ ነውይ። እስኪ አስበው የአቶ ታረቀኝ ልይ ሲባል አባትህ ሲጠራ ወትሮም በአንተ አላፍርም እተማመንብሀለሁ እኮራብሀለሁ። " ብሎ ትንሽ እንደማሰብ አለና " በል ነገ በጠዋት በተለመደው ስአት ገንዘቦቻችንን እንነዳለን " አለውና ተለያዩ።ቀናቶች በዚሁ መልክ አልፈው እለተ ሰንበት እሁድ ደረሱ። እንደተለመደው በጠዋት ቀዳማዊይና ሙሉቀን ገንዘቦቹን ወደ ጫካው ነዱ። ቀዳማዊይም በዛው ሲያልፉ ካርዱን የደበቀበት ቦታ አውጥቶ ለሙሉቀን አሳየው። ካርዱን አይቶ ደስ አለውደ የሙሉቀን ፊት ላይ ከፀሀይ የላቀ ብርሃን የሰታይ ነበር። " እንደ አንተ ተማሪ ብሆንና ጎበዝ ብሆን ደስ ይለኝ ነበር። ግን እኔ ገና ሁለተኛ ክፍል ሳለሁ ነው ሶስት ጊዜ የወደኩት። ከዛም እኔ ለትምህርት ሳይሆን ለግብርና ነው የተፈጠርኩት ብየ ወደ ባላገርነቴ ተመለስኩ እልሀለሁ። ግን ልጆቼን እንዳንተ ጎበዝ ተማሪ ነው የማደርጋቸው።" አለውና " በል ወንድሜ ይሄን ይዘህ ወደ ፈለከው አገር ሄደህ ተማር አንተ እንጀራህ ትምህርት ነው። እዚህ የጭቃ ህይውት የገበሬነት ስራ አይመጥንህም አንተ ለኸተማ ነው የተፈጠርከው። በጭራሽ እንዳትሳቀቅ ይህ የወንድምነቴን ነው ያደረኩት። ሁሉንም ኤችለዋለሁ። አንድ ቀን ብቅ ብለህ እንገናኝ ይሆናል። ፈጣሪ ለዚያ ጊዜ ያብቃን መቼም በአካል ብንለያይም በቀልብ በልብ አብረን ነን። አሁን ሳታቅማማ ይሄን ብር ይዘህ ሂድ ፈጣሪ ከአኔተ ጋር ይሁን " አለ ሙሉቀን " ግን እኮ ብዙ ነው። እንዴት ነው ይሄን ሁሉ ብር ይዤብህ የምሄደው? ብሩንስ የት አገኘኸው?" አለ ቀዳማዊ እንባው እየቀደመው " ብሩን ከእናቴ ነው የሰረኩት ትላንት ቅዳሜ ሙክቱን ሽጠውት ነበር። ከዛ ማታ ያስቀመጠችበትን ቦታ ስላየሁት ጧት ላይ አነሳሁት። ትክክሉ ይሄ ነው እንግዲህ ዝም ብለህ ይዘክ ሂድ ቤተሰቦቼ የሆነ መጥፎ ነገር የሚያደርጉኝ መስሎህ እንዳታስብ እኔን ምንም አያደርጉኝም። በዛ ላይ የእኔ እናት እንደ አንተ እናት መናጢ ስላልሆነች አትመታኝም ስድብ ደግሞ አይጣበቅብኝም። በዛ ላይ ደግሞ ቢቆጡኝና ቢመቱኝ አንድ ቀን ነው ከዛ ይረሱታል። አንድ ሙክት እኮ ለእኛ ምንም ማለት አይደለም። ደግሞ ብድር ነው። ተምረህ ስራ ስትይዝ በወለድ ትከፍላለህ " አለና ሳቅ ብሎ " በሄድክበት ሁሉ ሰላም ይግጠምህ ወንድሜ" ብሎ አቀፈው። ቀዳማዊ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰና ምንም ሳይመልስለት አቀፈውና " ቸር እንገናኝ ወንድሜ መቼም አልረሳህም። ሰላም ሁንልኝ ክፉ አይንካህ ወንድማለም" አለ ቀዳማዊ ሙሉቀንም አይኖቹ በእንባ እንደተሞሉ ቀዳማዊይን እንደልብ ወንድም የሚያየውን ጓደኛውን " መልካሙ ነገር ሁሉ ይግጠምህ " ብሎ በለሆሳስ እየመረቀው አልቅሶ ሸኘው። ቀዳማዊይም እያለቀሰ ፈጠን ፈጠን እያለ ከሄደ በኋላ ከእንደገና ወደ ኋላ ዞሮ ሙሉቀንን ተመለከተው። እጁን አንስቶም አውለበለበለት። በዚህ ጊዜ ሙሉቀን እየሮጠ ሄደና አንገቱ ላይ እናቱ ከሰይጣን ከአጋንንት ከክፉ መንፈስ እንዲጠብቀው ብላ በቆዳ አድርጋ ውስጡ ላይ የተለያዩ የስዕለ አድኖ የያዛውን ቁርበቱ አንገቱ ላይ አውጥቶ የቀዳማዊ አንገት ላይ አሰረለት " በል በሄድክበት ሁሉ ፈጣሪ ይጠብቅሀል ይሄን እናቴ ከቄስ አስመርቃ ነው ያመጣችልኝ ይጠብቃሀል እሽ " አለውና ለመጨረሻ ጊዜ አቅፎት በመጣበት ተመለሰ።
***
ቀዳማዊ የራስ አምባ ቀበሌን ለመልቀቅ አራት ስአት ፈጀበት። ሰው እንዳያየው በየጥሻው በየዛፉ እየተደበቀ በዛ ላይ ከኋላው ሰው የሚከተለው ስለሚመስለው በረጫ ነበር የሄደው።ወደ ስምንት ስአት ገደማ ከአንዲት የማያውቃት ከተማ ደረሰ። ወደ አቅራቢያዋ ወደ ሚገኘው የአውቶብስ መነሀሪያ ሄደና። የመኪኖቹን ረዳት ጠየቀ። በእርግጥ መኪኖቹ ወደየት እንደሚሄዱ ይጠይቅ እንጅ የሚሄድበትን አያውቀውም። " ቆይ አንተ የት ነው የምትሄደው?" ሲለው አንድ የመኪና ረዳት ቀዳማዊይም ግራ እየተጋባ " እ ደሴ ባህርዳር አዲስ አበባ ነው የምሄደው" አለ ቀዳማዊ ረዳቱም በረጅሙ ሳቀና ቀዳማዊይን ከእራሱ እስከ እግር ጠጉሩ እየተመለከተ "......

ሼር
@monhappy
@monhappy
ለአስተያየት
@BINCJ90
Corss @BINCJ90 ኤሴቅ yekxel ??????
@BINCJ90
:)
ያልሆንኩቱን ነኝ ብዬ ያወራሁ… እማልኖረውን የሰበኩ…የውሸት ወደድኩ ብዬ የማልኩ…እኔ እንጂ እማይገባኝን የተመኘሁ…አምኜ የከዳሁ…አዋ እኔ እንጂ…

💐 @monhappy 🌷
🌷 @BINCJ90 💐
👇👇👇
@monhappy
@monhappy
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳፪ ~ ( 22 )


ረዳቱም በረጅሙ ሳቀና ቀዳማዊይን ከእራሱ እስከ እግር ጠጉሩ እየተመለከተ "ኧረ ይቺ ባላገር ቁምጣዋን ልትሰቅል ነው። ኧረ በለው አታያትም የገጠር ላይፍ (ሕይወት) በቃኝ ብላ እኮ ወደ ከተማ መመነኗ ነው። ከዚያ ደግሞ ከተማውን ስታርፍ(ስታውቅ) ውጪ አሜሪካ ሎሳንጀለስ ምናምን ያምራታል።" አለ ሌላኛው በሳቅ አጀበው።" በይ ለማንኛውም እኔ የትም ቢሆን እወስድሀለሁ። ግን እነዚህ የጠቀስሻቸው ከተሞች ይዤህ እንድሄድ ነው የምትፈልገው?" አለ በሹፈት ረዳቱ ሌላኛው ረዳት መጣና " ኧረ ይደብራል ገና ለገና አዲስ ገጠሬ አገኘሁ ብለህ እንዲህ ጥሩ አይደለም። አንተም እኮ የገጠር ልጅ ነበርክ ምን ራስህን እንደከተማ ልጅ ትቆጥራለህ " አለና ረዳቱን ገልምጦ ቀዳማዊይን " በአንድ ጊዜ ያልካቸው ከተሞች አይኬድም ከአንዱ ወደ አንዱ ነው የምትችለው አሁን ወደ አዲስአበባ መሄድ ከፈለክ ከዚህ ደሴ ሄደህ ነው እንጅ ከዚህ ቀጥታ አታገኝም። ስለዚህ ና ወደ ደሴ ይዤህ እሄዳለሁ ። ከዛ በኋላ ከፈለክ ደሴ ትኖራለህ ካልፈለክ ደግሞ ኸደ አዲስ አበባ የሚሄድ መኪና አሳፍርሃለሁ። ግን እባክህ ነቃ በል እንደዚህ ሆነህ ሲያዩህ ዱርየወች ሊዘርፉህ ይችላሉ ያለህን ብር ሙሉ ይወስዱብሀል። ስለዚህ ብር ስታወጣ የያዝከውን ሁሉንም ሳይሆን የሚያስፈልግህን ቀንሰስ ለብቻ በአንደኛው ኪስህ ትይዝና ሌላኛውን ደግሞ ደብቀህ አስቀምጥ" አለውና ወደ መኪናው አስገብቶ የፊት ወንበር ላይ አስቀመጠው። ቀዳማዊይም መኪና ውስጥ ሰው ስላልነበረ ረዳቱ ባለው መሰረት የተወሰነ ብር በአንደኛው ኪስ ይዞ በሌላኛው ደግሞ ቀሪውን ብር አስቀመጠ። ብሩን ያስቀመጠበትን ቢፈቸሽ አይገኝም በብዙ ቁራጭ ጨርቅ ከተጣፈ ሱሪው ላይ ነበር የደበቀው። ረዳቱም ከብዙ ጥሪ በኋላ እንደምንም መኪናውን ሞልቶ ጉዞ ጀመረ።
*****
እለተ ሰንበት እሁድ የራስ አምባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ነጭ በለበሱ ምዕመናን ተጨናንቋል። የጠዋቱ ቅዳሴ አልቆ ታዕምረ ማርያም ተነቦ ስብከተ ወንጌል ከተነገረ በኋላ ህዝቡ ወደ ቤቱ ከእነዚህ ዲሄድ በፀሎት ተዘግቶ ማህበርና ሰንበቴ ያለበት እዛው ተቀመጠ። ወይዘሮ አትጠገብም እንደ ሁሉም ኪዳን አድራሽ ምዕመናን የግል ፀሎቷን ጨርሳ ለሰንበቴ ወደሚጠጡበት ትልቅ የዛፍ ስር እያመራች ሳለ ከኋላዋ የሆነች ሴትዮ ጠራቻት ወይዘሮ አትጠገብም ዞረች። ስታያት ታውቃታለች " ደህና አረፈድሽ ወይዘሮ አትጠገብ?" አለች ሴትዮዋ " ደህና እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አረፈድሽ" ብላ አፀፋዋን መለሰችላት ወሬ ውስጥ ገቡ ሴትዮዋ ጋር ሲጨዋወቱ በመሀል የልጅ ወሬ ሲነሳ " እንደው ምን አይነቱን ልጅ ነው የወለድሽው ፐ እውነት አንቺ ነሽ እንጅ እድለኛ " አለች ሴትዮዋ ይሄኔ ወይዘሮ አትጠገብ ጆሮዋን ይበልጥ እየሰጠች የምትለውን ማዳመጥ ጀመረች። " እናም የአንቺ ልጅ " የሰው ቤት ሁሉ ወሬ ሆኗል በአንቺ ጎበዝ ልጅ ምክንያት እኛ የወለድናቸውን ልጆች እስከመጥላት ደርሰናል። በጣም ሰናይ ልጅና ለአገር ለወገን የሚበቃ ልጄ ነው ያለሽ በዛ ላይ ከልጅ ጋር አይጣላ እንደው እንዴት ብታሳድጊው ነው?" አለች ሴትዮዋ። ወይዘሮ አትጠገብም የቀዳማዊ ወሬ ሲነሳ ባይላትም ነገር ግን በሰው ፊት ደስ እንዳላት ታስመስላለች።" አይዬ የኔ ልጅ ደግም ምን ሰርቶ ይሆን እኔ ኮ የእሱ ነገር መቼም ጉድ ነው። በየሄድኩበት ስለሱ ነው የምሰማው በአሁኑ ደግሞ ምን አድርጎ ይሆን የኔ ጀግና ልጅ ብዙውን እኮ ደግሞ አልሰማም " አለች በምፀት። ሴትዮዋም የምታውቀን ልትነግራት በመጓጓት " ይሄ ሰኔ ላይ የተፈተኑት ምንትሴውን ፈተና ተበላይ ተክልል የሚመጣውን ፈተና እንደውም በፎሊስ ሆነው የተፈተኑትን የአንቺ አልጀርስ እንድቅትዮን ዳለ ሞልቶ ሞልቶ ነው ያመጣው። ተሶስቱ ወረዳ የአንቺ ልጅ ነው አንደኛ የሆነው። ጉድ ነውኮ አሁን ተገጠር ለዛውም ከእኛ ቀበሌ የወጣ ልጅ አንደኛ ሲሆን የፈጣሪ ታዕምር መች ያልቅበታል። " አለች ወይዘሮ አትጠገብም ግራ በመጋባት " ኧረ ይሄን አላውቅም ካርድ ተቀብለዋል እንዴ ሰሞኑን ተጣልተን ስለነበር አኩርፎኝ ነው መሰል አልነገረኝም " አለች ወይዘሮ አትጠገብ ያው በሰወቹ ፊት ላለመወቀስና ላለመነወር " አዎ ትላንት ካርድ እኮ ተቀብለዋል። እንዴት እስካሁን አልነገረሽም አይ የልጅ ነገር ምንስ ብታስከፊው ታዲያ ይሄ የደስታ ጉዳይ ይደበቃል?" አለች ሴትዮዋ " ምን ታደርጊዋለሽ የዛሬ ልጆች እኮ ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። ምን በረባውም ባልረባውም ቂም መያዝ ነው ስራቸው።" አለች ወይዘሮ አትጠገብ በውስጧ በንዴት እየተብሰለሰለች።
....
ወይዘሮ አትጠገብም በሰማችው ነገር በጣም ተናዳ የሰንበቴውን መጠጥ ና ዝግጅቴ እንኳ በረጋ መንፈስ ከቀልቧ ሆና ሳትጠጣ ሚስጥሯን እሷ ሳታውቅ የዌጭ ሰው እንዳወቀባት ተሸማቃና አፍራ ጠቁራ ወደ ቤቷ ተመለሰች። " ለምንድነው ካርዱን ይዞ ያላየሁት? የት ጥሎት? ለማን ሰጥቶት? ነው ወይስ ሳላየው ደብቆት ይሆን? " እያለች ራሷን እየጠየቀች ቤቷ ደረሰች ። እንደደረሰችም ቀጥታ ቀዳማዊ ደብተሩን መፅሐፉን የሚያስቀምጥበትን ከማዳበሪያ የተሰራ አኮፋዳውን በረበረች። ነገር ግን ካርዱን አላገኘችውም። የሚተኛበትን መደብ የባዶ ሞሰቦችን ቂጥ እንዲሁም ጎታውን ቅንባውን እህሉ ውስጥ ደብቆት ይሆናል ብላም እህል ያለበትን ቦታ ሁሉ ፈተሸች ነገር ግን ምነም ነገር አላገኘችም። ግራ ተጋባች "ቆይ ቤት ውስጥ ካልደበቀው የት ሊደብቀው ይችላል? ይሄ ሰይጣኔ የሆነ ልጅ ተንኮልም ለመደ ማለት ነው? አዎ መህኑ ነው ቆይ ዋጋህን እሰጥሀለሁ ጭራሽ እኔ ላይ እንዲህ ማድረግ ጀመርክ። ጥሩ ካዋጣህ ጥሩ ነው ነገር ግን አያዋጣህም። ልክ አስገባሀለሁ እስኪ ስትመጣ የት እንደደበከው ትናገራለህ " አለችና ፍለጋውን አቆመች።.....

ሼር ሼር
@monhappy
@monhappy
ለአስተያየት
@BINCJ90
:)
የሆነ ቀን ደሞ በምን ትዝ እንዳልሺኝ እኔጃ ግን ትዝ ብለሺኝ ነበር…አዋ የእውነቴን ነው…ትዝ ብለሺኝ ነበር…እንዴት አትይኝም…

መንገድ ላይ እየሄዱክ ሳለ ነበር…ከብዙ ሰዋች መሀል አንድ የክልል ባንዲር ብቻ የየዘ ሰው አይቼ ያስታወስኩሽ…ምንድን ነው እሚዘባርቀው ትይኝ ይሆናል…ግን አዋ እሱ እና አንቺ አንድ ናቹህ…ደሞ ስድብ አደለም…አንቺ እኮ መጥፎ ጐንሽን ሲነግሩሽ ስድብ ነው እሚመስልሽ…

አንቺም እንደሱ ነሽ…ለምን ካለሽ…እሱ ሀገር እያለው እንዴት ክልል ያስቀድማል?…ሀገር ይበልጥ የለ…አንቺም የልቤን ሀገር ነበር የሰጠሁሽ…ግን ክልል አስበልጠሽ ሀገሩን ልቤን ናቅሺው…
•➫ ✰ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለም ‼️


🔑•✰ @monhappy •✰🔑
━━━━━━━━━━━━
🏷 JOIN 🏷
:)
ሜላት እና ቡናዋ ☕️
( ክፍል አንድ )

ምንም አላልኳትም…በሁለት እማልደራደርባቸው ነገሮች ነው የያዘቺኝ…በቡና እና በእማ…

☕️ @monhappy 🌾
🎋 @BINCJ90 *☕️
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፳፫ ~ (23 )


ቀዳማዊይ መኪና ላይ ሲወጣ የመጀመሪያው ነው። አይደለም በመኪና ከአንዱ ወደ አንዱ ቦታ በፈረስ ራሱ ሂዶ አያውቅም። የተቀመጠበት ወንበር አጠገብ ያለውን የመኪና መስኮት ከፍቶ አንገቱን እንደ አንቴና መዞ የመጣበትን ጫካ ተመለከተው። ለመጨረሻ ጊዜ እንደሆነ አያሰበ ቀዳማዊይም በለሆሳስ " እስካሁን ብዙ መከራ አይቻለሁ። በእራሴ እናት በገዛ እህቶቼ ከዚህ በኋላ ግን ቢያንስ ይሄ መከራ ተግ ይልልኛል። ብሰቃይ እንኳ በባዳ ስለሆነ እቀበለዋለሁ። " እያለ ያዳገበትን ስፍራ የተወለደበትን ቦታ ለክፉ መስተንግዶዋ እየረገማት ተሰናበቶ ሲያበቃ ያ እንደ ወንድም የሚንሰፈሰፍለትን ጓደኛው ሙሉቀን ውልብ አለበት። ከእናቱ መቀነት ለእሱ ሲል የሰረቀውን ወንድሙን፣ እሱ ከመከራና ከእንግልት ኤንዲላቀቅ ብሎ የማይደፈረውን የቤተሰብ ንብረት የደፈረው ሙሉቀን አይኖቹ ላይ ተደቀኑበት።" ከቶ መቼ ይሆን የአንተን ውለታ የምከፍለው!እውነት አምላክ እድለኛ አድርጎኝ ውለታህን ለመክፈል ያበቃኝ ይሆን?"አለ ቀዳማዊ ከእንደገና ደግሞ በምናቡ " አሁን በዚህ ስአት ምን እያደረግሽ ይሆን?ከአንቺ ግልምጫና ስድብ ተላቀኩ ፈጣሪ ይመስገን። አንቺ መቼም እናቴ ልትሆኝ አትችይም አይደለሽም። በጣም ነው የምጠላሽ። እድሜ ልኬን ሙሉ እንደጠላሁሽ እኖራለሁ። እናንተንም ቢሆን እህቶቼ ለእኔ ልክ እንደ አባቴ ሞታችኋል። መኖራችሁ ካላኖረኝ ገድያችሁ እኖራለሁ ከዛሬዋ ጊዜ ጀምሮ እኔ እህት፣ ወንድም፣ እናት ፣ አባት የለኝም። እንደ አባቴ ሞታችኋል። መቼም ቢሆን ያደረጋችሁኝን አልረሳም!"እያለ ከንፈሩን ነክሶ የሆነውን ማሰላሰሉን ቀጠለ። " ጋሽ ደረጄ የት ይሆን ያለኸው?ይሄው ኸተማ ወጥቻለሁ ተቀበለኝ" እያለ በአይኖቹ ውልብ እያሉ የሚልፉትን ቁርቁር ከተማዎችን ይመለከታል። ደረጄ መንገድ ላይ ቆሞ የሚጠብቀው ይመስለዋል። መኪናው ያለ ቅጥ እየሰገረ ነው ቀዳማዊ አሻግሮ ተፈጥሮንና ከተሞችን ማየቱን ተያይዞታል። መዳረሻውን ደሴ ያደረገውና እነቀዳሚዊይን ያሳፈረው መኪና ከብዙ ስአታት ጉዞ በኋላ ደሴ የአውቶብስ መነሀሪያ ደርሶ ተሳፋሪዎችን አወረደ። ምንም ተቀያሪ ልብስም ሆነ እቃ ያልያዘው ቀዳማዊይም ወርዶ ዙሪያ ገባውን ሲያማትር ፊት ለፊቱ የጦሳ ተራራ በማን አለብኝነት ተጀብኗል " ኧረ የተራራ ትልቀት ፐ አሁን ቢደረመስ ይሄ ሁሉ ፎቅ እኮ አፈር ነው የሚሆን ሰው ግን ምን አይነት ነው እንዴት ከተራራ ስር ተራራን አምኖ ቤት ይሰራል?ወይ የኸተሜ ሰው አሁን ከተራራው ወጥቼ መርግ የሚያህል ድንጋይ ብጥል እኮ ቤት ያፈርሳል። ይሄን ሁሉ እነዴት አያስቡም" እያለ ። " ልጄ ወደየት ነህ የት ልትሄድ ነው?"ብላ ከጦሳ ተመስጦው አባነነችው። ቀዳማዊይም እየተቅለሰለሰና አንገቱን እየደፋ " እንጃ እትዬ ምኑን አውቄው የከፋው ሰው ዝም ብሎ አይደል የሚሄደው ግን አዲስ አበባ ብሄድ እፈቅዳለሁ።" አለ " አዬ ልጄ አዲስ አበባ እኮ ለእንደ አንተ አይነቱ የዋህ የገጠር ልጄ አትሆንም ። ደግሞስ ዘመድ አለህ?"ብላ ጠየቀችው" ኧረ የለኝም ግን ያገኘሁትን መስራት እችላለሁ " አለ " አዬ ልጄ እንኳን ዘመድ ሳይኖርህ ዘመድ ኖሮህም አዲስ አበባ መኖር ከባድ ነው።ብዙ ህገወጥ ድርጊቶች የሚደረጉባት የህፃናትን አይን እያወጡ እጃቸውን እየቆረጡ ለልመና የሚዳርጉባት ከተማ ናት። በርግጥ በዛውም አላህን ፈጣሪን የሚፈሩ ደግ አዛኝ ሰዎችም ያሉባት ከተማ ናት። ብቻ እንግዲህ እሄዳለሁ ካልክ ሂድ " አለች " አዬ እትዬ እንግዲህ ፈጣሪየ ያውቃል በብዙ ፈተና ነው ከዚህ የደረስኩት ስለዚህ በደንብ መራቅ አለብኝ። ራቅ ብዬ ለመኖር ነው ያሰብኩት " አለ ቀዳማዊ " እሽ እንዳልክ እንግዲህ አሏህ በምህረቱ ያስብህ። ከክፉ ሁሉ ይጠብቅህ። እሱ ከአንተ ጋር ይሁን ። ሌላ ምን እልሀለሁ ልጄ" አለች። ቀዳማዊይ ምራቃቱን አሜን ብሎ ከሴትዮዋ ጋ ተለያዩ
የውበት መናኻሪያዋ፣ የቆነጃጅቶች መፍለቂያ፣ ሙስሊምና ክርስቲያኑ አንተ ትብስ እኔ እብስ ብሎ በመተሳሰብና በፍቅር አብሮ የሚኖርባት ከተማ የድሮዋ ላኮመልዛ የአሁኗ በተራራዎች ተከባ አንቱታነቷን ያተረፈችው ደሴ ከተማ ቀዳማዊይን በጦሳ ተራራ ኩታ ሽንጡን ደርባ በቀዝቃዛ ነፋሷ ተቀበለችው። ቀዳማዊይም እዛው አውቶብስ ተራው እንዳለ ብሩንንና ካርዱን ከሌባ እየተጠነቀቀ ዙሪያ ገባውን አሁንም አሁንም እያየ ሳለ ፡ ከመኪና ወደ ሚወርዱ ተሳፋሪዎች ጠጋ እያሉ " አልጋ አልጋ " ወደ ሚሉት ሰዎች ጠጋ አለና " አልጋ እፈልጋለሁ " አለ " እሽ ብራዘር ይዤሽ እሄዳለሁ። አልጋውን ብታየው በቃ በምቾት ተኝተህ አድረህ ተኝተህ ትውልበታለህ። አሁኑኑ እንሄዳለን ትንሽ አኔዴ ሁለት ሰው በዛውም ለሌላኛው ክፍል ሰው ልያዝ " አለና ለአንድ ልጅ አስይዞት እሱ እንደገና ሰው ፍለጋ " አልጋ አልጋ የትም የማይገኝ አልጋ በጥራትም ከማንም ጋር የማይነፃፀር እያለ" እየጮኸ ሄደ። በዚህ ጊዜ ያ ልጅ ቀዳማዊይን ይዞት ሊሄድ ሲል፦ አንዲት እናት ሩጣ ቀዳማዊይን እጁን ይዛ ሳብ አደረገችውና " እናንተ መናጦች ሁሌም ድሃን እንዳስለቀሳችሁ ደግሞ እንደለመዳችሁት ልትወርሱት ነው?ግን ፈጣሪን አትፈሩም?አሁኑ ፖሊስ ሳልጠራ ከዚህ አካባቢ ጥፋ ያኛው ሌላ የሚዘረፍ ለማምጣት ሲሄድ አንተ ደግሞ ትጠብቃለህ። እናንተ የማትረቡ መናጢ ርጉሞች እንደው እንጀራ አይውጣላችሁ። መውጣትስ አይወጣላችሁም እንዴት ብሎ ይወጣላችኋል የስንቱ እንባና ርግማን እያለባችሁ " አለችና ቀዳማዊይን " በል ልጄ ና ከእኔ ጋ እነዚህ መናጢዎች ያለህን ሊወስዱብህ ነበረ። እንዴት እንደሚወስዱብህ እንኳ እንዳታውቅ በመድኃኒት ያፈዙሀል።" አለችና ወደ እሷ ቤት ወረደችው። ያው ይሄን ስራቸውን የምታየው እሷም አሌጋ ስለምታከራይና ለማከራየት እዛ በወጣችበት ወቅት አልጋ ርናስይዛችሁ ብለው ወስደው ልጆቹ ሰዎቹ እያለቀሱ ሲመለሱ ኤንደምታይ አጫውታው ለአኔድ ለሊት 20 ብር አስከፍላ አልጋ አስያዘችው። በጠዋት ተነስታም አዲስ አበባ የሚሄደው አውቶብስ እንደምታሳፍረው ቃል ገብታ " ያው ለአልጋ ስለከፈልክ እራቱን ደግሞ እኔ ልቻልህ" አለችና ራቱን አቀረበችለት። ቀዳማዊይም በደግነቷ እየተገረመ ያቀረበችለትን ምግብ በደስታ በላ።

ክፍል #24 ነገ ምሽት 12:00 ይቀጥላል

ሰላረፈድኩኝ ይቅርታ ይደረግልኝ 🙏

@monhappy
ለአስተያየት
@BINCJ90
:)
እምዬ እናቴ!

እማ ለዎልሺው ውለታ እሚከፍል ምግባር ባይኖረኝም ግን አንድ ቀን አኮራሻለው አንድ ቀን እሚያስጨንቁሽን ነገሮች አርቅልሻለው ይሄ ቃሌ ነው….ቃል ደሞ አይታጠፍም።

🌷 @monhappy 🌷
💐 @BINCJ90 💐
:(
ኮሌጅ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እያለሁ ነበር…እሷን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁዋት…ሀና ነው ስሟው…ምን መሰለህ…አንዳንዴ…እኛ እምንወዳቸው ሰዋች ከእኛ በለይ እሚወዳቸው እና እሚወዱት ሌላ ሰው አላቸው…ሀናም ምን አይነት ልጅ መሰለችህ…ሀና ማለት እሩቅ የሆነች ቅርብ ናት…

ሙሉ ትረካው ነገ ማታ ይለቀቃል🙏🏽
@monhappy
@BINCJ90
2025/07/13 03:15:58
Back to Top
HTML Embed Code: