"ጀግናዋ ቤርናዴትና የተከላካዩ አበሳ"
"The greatest untold Love Story Ever!"
ቤርናዴት ማልዳ ትነሳለች። አንድ ሰዓት እንኳን ሳይሞላ ቀኗ ይጀመራል።ቁርሷን ትበላለች፣ባለቤቷን ለመንከባከብ ራሷን ታዘጋጃለች ልብስ ትቀይርለታለች። ምግብ ታበስልለታለች።ወደ መፀዳጃ ቤት ትወስደዋለች። ቆሻሻውን ሁሉ ታፀዳለታለች። ጡንቻውን ታፍታታለታለች። ይህ የአንድ ቀን ብቻ ልማዷ አይደለም። ላለፉት 38 ዓመታት አድርጋዋለች። በየዕለቱ ደጋግማዋለች። እስከ መጨረሻው ላታቋርጥ ለራሷ ቃል ገብታለች... ፈረንሳይ በጄኔራል ሻርል ደጎል አመራር ስር ሳለች፣ የመንግስት ወግ አጥባቂ አስተዳደር እያደር የህዝብ ቅሬታ ሲያስነሳ ዘመኑ በ1960ዎቹ ነበር። ጥቁሮች ከነጭ ፈረንሳዊያን ጋር በጋብቻ ከተጣመሩ ጉድ የሚባልበት ያ የዘረኝነት ዘመን… ጥቁሩ ዣን ፒዬር አዳምስ ግን ከነጯ ቤርናዴት ጋር በፍቅር ወደቀ። ወደደችው፣ ወደዳት። ሃገር ጉድ ይበል ብለው ፍቅራቸውን እስከ ጋብቻ አደረሱት። ገና አማተር ተጫዋች ሳለ ነበር የተዋወቁት። በፍቅር ሲኖሩም ወንድ ልጅ ወለዱ። 1970ዎቹ ለጥንዶቹ አስደሳች ዘመናት ነበሩ። አዳምስ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጥቁር ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ዝና፣ ገንዘብ፣ መሽቀርቀር፣ መደሰት የአዳምስ የዕለት ተዕለት ልማድ ነበር። ቀልድ ያውቃል። ፈገግታ ከፊቱ አይጠፋም። ዝና ሲጨመርበት ደግሞ… አለ አይደል… አብሮ የሚስቅም አይጠፋም።
34 ዓመቱ ላይ ጫማውን ሰቅሎ፣ ለቀሪው ህይወቱ ህፃናትን ለማሰልጠን ለትምህርትና ልምምድ ወደ ዲዦ ከተማ አቀና። እዚያም በልምምድ ላይ ሳለ በጉልበቱ ላይ ጉዳት ደረሰበት። የሊጋሜንቱን ህመም ለመገላገል በሊዮን ከተማ በሚገኘው ኤድዋርድ ሄሪዮ ሆስፒታል ምርመራ አደረገ። ጉዳቱ ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልገው በማረጋገጡ ለኦፕሬሽኑ ቀን ተቀጠረ።
የቀን ጎዶሎ፣ ማርች 17 ቀን 1982… አንድ የማደንዘዣ ባለሙያ ብቻ ስራ ላይ ነበረች።ተለማማጅ ተማሪዎችም አሉ። አዳምስ ተራው ደርሶ አሸለበ። ግን እንደተጠበቀው አልሆነም። ጉልበት ላድን ያለው ህክምና እጅና እግሩን ጨምሮ መላው አካላቱን ከጥቅም ውጭ አደረጋቸው። ከአይኖቹ ሽፋሽፍት በስተቀር ቢጠሩት እንኳን ፊቱን ዞር ማድረግ ተሳነው። አንደበቱ ተዘጋ፣ በድጋሚ መናገር አልቻለም።
የማደንዘዣው ሂደት የህክምና ስህተት ነበረው።
ተለማማጆቹ ወደ ሰውነቱ ያስገቧቸው ትቦዎች እንኳን በቅጡ አልተሰኩም። ወደ ሳንባው የተላከው ትቦ የአሰካክ ስህተት ስለነበረው ሳምባዎቹ በቂ ኦክስጅን ባለማግኘታቸው የልቡ ስራ ተስተጓጎለ። አንጎሉ በቂ ኦክስጂን ባለማግኘቱ ለአደጋ ተጋለጠ። ያ ፈርጣማ ተከላካይ ሰውነቱ ከዳው። መላወስ አቃተው። በዚያች እርጉም ቀን ያለ ድጋፍ ወደ ሆስፒታል ቢገባም፣ በራሱ አቅም ወደ ቤቱ መመለስ አልቻለም።
ቤርናዴት ለአምስት ቀን በሆስፒታል እየዋለች፣ እያደረች ጠበቀችው። ፍቅሯ፣ የልጇ አባት፣ የህይወቷ ጓድ ከተኛበት ሳይነሳ ቀረ። ከእንግዲህ በሰው ድጋፍ እንጂ በራሱ አቅም መንቀሳቀስ እንደማይችል ቁርጡን ነገሯት። የህክምና ኃላፊዎች ለአረጋዊያን መንከባከቢያ ማዕከል እንድትሰጠው መከሯት። ለቤርናዴት ይህ የሰነፎች ምክር ነበር። አልተቀበለቻቸውም። "ወደ ቤታችን እወስደዋለሁ፣ እዚያም እስከመጨረሻው እንከባከበዋለሁ" ብላ ወሰነች። በደግ ዘመን ፍቅርን ወዳዩበት ቤታቸው አመጣችው።
2021…፣ ዣን ፒየር አሁንም በህይወት አለ። ዕድሜው 72 ደርሷል። ቤርናዴትም አልሰለቸችም። ዕድሜ ተጭኗት ቆዳዋ ተሽብሽቧል። የዚያ ዘመን ውበቷ ረግፏል። እርጅና ቤት እየሰራባት ነው። ዘመናት ቢያልፉም ታማኟ ሴት ግን ሰው ሰራሽ ስህተት አልጋ ላይ የጣለውን ሸበላ አይኗ እያየ ልትጥለው አልፈቀደችም። ከአደጋው በኋላ በእያንዳንዷ ቀን እንዳደረገችው ሁሉ ዛሬም ማልዳ ትነሳለች። ታጥበዋለች፣ ታለብሰዋለች፣ ትመግበዋለች ከመተኛት ብዛት ጎኑ እንዳይላላጥ ታገላብጠዋለች። አልታከተችም፣ አልሰለቸችም።
@monhappy
@BINCJ90

'ሚስተር ሀራም'
በኑዕማን ኢድሪስ
ክፍል አንድ (1)
... የፈጅር ሶላት ጥሪ ሚናራዉ ላይ ከተሰቀሉ ድምጽ ማጉሊዎች ጥርት ብሎ ይሰማል። 'አላሁ አክበር.. አላሁ አክበር.... አሽሀዱ አንላ ኢላሀ ኢለሏህ....."። አለም ላይ ካሉ ጥሪዎች ዉቡና አማኞች በጉጉት የሚጠብቁት የሶላት ጥሪ (አዛን) ነዉ። ሁሉም መስጅዶች በተመሳሳይ ሰአት ጥሪዉን ስለሚያስተጋቡ የደሴ ከተማ በብስራት ጥሪ ተናጣለች። በተለይ ከሸዋ በር መስጅድ የሚሰማዉ ጥሪ አራዳ፣ ሰኞ ገበያንና የሸዋበርን አከባቢ የሌሊቱን ጨለማ አስወግዶ የንጋቱን ብስራት ያዉጃል። "አሶላቱ ኸይሩን ሚነ ነዉም...."
... ብርዱና ዉርጩ ሳይበግራት ቀዝቃዛዉን ዉሀ በእጆቿ፤ በፊቷና በእግሮቿ ላይ አዋለችዉ። ኢማን የሱብሂን ሶላት ለመስገድ የሶላት ትጥበት (ዉዱዕ) እያደረገች ነዉ። እለቱ ሰኞ በመሆኑ ከስግደት በኃላ የሚጠብቋት ብዙ ስራዎች አሏት። ቁርአንን ማንበብ፤ ቁርስ ማዘጋጀት፤ በተለይ ደግሞ ከሳምንት በፊት በሒሳብ መምህራቸዉ የተሰጣቸዉን የቡድን ስራ የማስረከቢያ ቀኑ ስለሆነ በስነ ስርአት ማዘጋጀት ይኖርባታል።
አረማመዷን በትምህርት ቤት ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሁሉ ያዉቁታል። ገና ኮቴዋን ሲሰሙ ሴቶች ካገረቀሩበት ቀና ብለዉ በዉበቷ ሊፈዙ አይኖቻቸዉን ይከፍታሉ። ወንዶቹ ከተቀመጡበት ብድግ ብለዉ አካሄዷን እያስተዋሉ፤ ዉበቷን እያደነቁ አንገታቸዉን ይነቀንቃሉ። እሷ ስትመጣ የ"12ኛ C" ክፍል ተማሪዋ ኢማን ሳትሆን የአንድ ግዛት አስተዳደር ንግስት የመጣች እስኪመስል ድረስ የወንዶች ልብ በፍርሀት ይርዳል። ቀና ብሎ የሚናገራት፤ ደፈር ብሎ የሚለክፋት የለም። በጓደኞቿ፤ በትምህርት ቤት፤ በአከባቢዋ ኢማንን ያከብሯታል። ምክንያቱም ኢማን እንደ ስሟ ኢማን አላት። በዉበቷ ያደንቋታል፤ ሴቶች ይቀኑባታል፤ ወንዶች ይማልሉባታል። ቁጥቧ ኢማን...
ኢማን ትምህርት ቤቱ ግቢ ዉስጥ ስትገባ ሶስቱ የቅርብ ጓደኞቿ ቀድመዋት ስለ ቅዳሜና እሁዱ ዉሏቸዉ ሲያወሩ ደረሰች። ቤዛ፤ ፍጡማና ዘሃሪ በጣም ይቀርቧታል። "አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ" ስትላቸዉ ሁሉም በአንድ ላይ ለሰላምታዋ ምላሽ ሰጡ። "ወአለይኩም ሰላም ጓደኛዬ" ብላ ቤዛ ከኢማን ጋር ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ።
"ወይኔ በአላህ ምን ተቀብተሽ ነዉ ኢሙ ጉንጭሽኮ በጣም ለስላሳ ነዉ" አለቻት። ይሄን ትጠይቃት እንጂ ኢማን ፊት ላይ የዉበት ማሳመሪያ ቀለምና ዱቄት አርፎበት እንደማያዉቅ ቤዛ ታዉቃለች።
"ኢሙ ሒሳብ መምህር የሰጠዉን የቡድን ስራ አረሳሽዉማ?" ብላ ጠየቀቻት ዘሀሪ። ምንም እንኳ ጥያቄዉ በቡድን እንዲሰራ ይሰጣቸዉ እንጂ አንድም አምስትም ሆና ጥያቄዉን ለብቻዋ ነዉ የሰራችዉ። ዘሀሪ ለጠየቀቻት መልስ ሳትሰጥ ለመገሰጽ ያክል ጎንተል አደረገቻቸዉ። "እናንተ ግን ለምን አትሳተፉም፤ ለራሳችሁኮ ነዉ። እዚህ እስካለንስ እሺ እኔ ሰራሁ ቆይ ዩንቨርሲቲ ስትገቡ ማን ሊሰራላችሁ ነዉ?" ብላ ፊቷን ኮስተር አደረገቸዉ። ቤዛ የትምህርት ነገር ስለማይሆንላት ማሾፉን ቀጠለች።
"ቆይ ካንቺ ጋር አንድ ቡድን ሁነን ዝቅ ያለ ዉጤት የምናመጣ ይመስልሻል? መምህሩኮ ያንቺን ስም ሲያይ አይኑን ጨፍኖ ነዉ የሚያርመዉ፤ ብትሳሳችም ለሱ ልክ ነሽ..." ሁሉም ተሳሳቁ። "... እዉነቷንኮ ነዉ..." ብላ ዘሀሪ ቀጠለች። " ጋሽ ከድርኮ አይኑን የሚጠቀምበት ዉበትሽን ለማድነቅ እንጂ ዉጤትሽን ለመቀነስ አይደለም።" ስትላት የተቋጠረዉን ፊቷን ሳትፈታ "የሚጠቅማችሁን ነዉ የነገርኳችሁ" ብላ በቆሙበት ትታቸዉ ወደሚማሩበት ክፍል ሄደች።
.
.
... ጋሽ ከድር ከሆጤ ትምህርት ቤት ወደ መምህር አካለወልድ ትምህርት ቤት ከተዘዋወረ ወራቶች አስቆጥሯል። የ12ኛ C ክፍል ሒሳብ መምህር ሆኖ እንደተመደበ ወደ ክፍሉ አምርቶ ራሱን ሊያስተዋዉቅ ሲዘጋጅ ከፊት ወንበር የተቀመጠችዉን ኢማንን ሲመለከተ ስሙ እስኪጠፋዉ ድረስ ፈዞ ቀረ። በቃላት ድርደራ የማይገለጽ፤ በነገራቶች የማይመሰል እፁብ ድንቅ የሆነ ዉበት ከፊት ለፊቱ ተመለከተ። ለተማሪዎቹ ራሱን ለማስተዋወቅ የመጣዉ መምህር ከድር የማይጋፈጠዉ ቁንጅና የመጣበትን ጉዳይ አስረሳዉ። እንደ ምንም ራሱን አረጋጋና ጉሮሮዉን ጠራረገ።
"እ...." ምን ብሎ እንደሚጀምር ግራ ገባዉ። ".... እ..እ... መምህር ከድር እባላለሁ። አዲሱ የሂሳብ መምህራችሁ ነኝ። ...." አይኑን ከኢማን ላይ መንቀል አልቻለም። ዉበቷ ሙሉ እሱነቱን ተቆጣጥሮታል። ማንነቱን ለክፍሉ ተማሪዎች የሚያስተዋውቅ ሳይሆን ለ'ሷ ብቻ ሚያስተዋዉቅ ነዉ የሚመስለዉ። ሁኔታዉን እያዩ ሙሉ የክፍሉ ተማሪዎች ይጠቃቀሱበታል። ሴቶች በቅናት ሲመለከቱት፤ ወንዶቹ ደግሞ ሌላ ተፎካካሪ እንደመጣባቸዉ ሲያዉቁ ይበልጥ ተበሳጩ። "እ... ከዚህ በኃላ አብረን የምንቀጥል ይሆናል።... ከትምህርት ቤቱ በጸባይ አንደኛ እንደሆናችሁ ተነግሮኛል። ስለዚህ እኔም ጋር ሳንቀያየም አመቱን አብረን እንጨርሳለን።" አላቸዉ። ከአንደበቱ ይህንን ያዉጣዉ እንጂ ዉስጡ የሚነግረዉ ፊት ለፊቱ ከሚመለከታት ልእልት ልጅ ጋር አብሮ እንደሚቀጥል ነዉ። "... ያዉ ዛሬ የመጀመሪያ ቀናችን ስለሆነ እንተዋወቃለን። ከፊት ወንበር እንጀምር..." አለና እጁን ወደ ኢማን ሲያመላክት ሁሉም ተማሪዎች በሳቅ ክፍሉን ሞሉት። መምህር ከድር የሳቃቸዉ ምንጭ ስላልገባዉ በተቆጣ ሁኔታ "ምን ያስቃችኃል?" ብሎ ተማሪዎቹ ላይ አምባረቀባቸዉ። በሳቅ የሞላዉ ክፍል ተመልሶ ጸጥታ ነገሰበት። መምህሩ ራሱን ካረጋጋ በኃላ "ምንድን ነዉ ያሳቃችሁ" በማለት ጥያቄዉን ደገመዉ። "አይይይ..." ብሎ እያቅማማ ከተቀመጠበት ተነስቶ "ሁሉም መምህሮች ከክፍሉ ተማሪዎች ጋር መተዋወቅ ሲጀምሩ ከሷ ነዉ የሚጀምሩት" ብሎ በክፍሉ ዉስጥ በተጫዋችነት የሚታወቀዉ ናሆም መለሰለት። አሁንም በተቆጣ ድምጽ "እና እሷ ከፊት ስለሆነች ነዋ!" ብሎ ያሰበዉ እንዳይታወቀበትና ተማሪዎች በሌላ እንዳይጠረጥሩት በማለት በመጀመሪያዉ አቋሙ ጸንቶ ወደ ዉቧ ልጅ እያመላከተ "ራስሽን አስተዋውቂ" አላት።
"ኢማን ጀማል" እባላለሁ ብላ ራሷን አስተዋወቀች። "ኢማን...." ስሟን ለራሱ ደገመዉ። ድምጿም ስሟም ያምራል። ሌሎቹን ተማሪዎች ሳይተዋወቅ ቢወጣ ደስታዉ ነበር። የሷ ስም ብቻ በቂ ነዉ። አጠገቧ ተቀምጣ ስልኳ ላይ ያፈጠጠችዉን ተማሪ "እሺ አንቺስ" ሲላት በድንጋጤ የምትገባበት አጣች። "ሰሚር እባላለሁ" ክፍሉ በሳቅ ሞላ። ቤዛ በፌስቡክ ሰሚር ከሚባል ልጅ ጋር እያወራች ተመስጣ ነበር ድንገት ስትጠየቅ የመለሰችዉ። መምህር ከድር ፈገግ ካለ በኃላ ሊያስተካክላት ሞከረ።
..."ሰሚራ ነዉ ወይስ ሰሚር?"
..."ይቅርታ መምህር ቤዛ እባላለሁ" ብላ ስሟን አቆላምጣ ራሷን አስተዋወቀች። መምህር ከድር ግን ሙሉ ስሟን እንድታስተዋውቅ አዘዛት። "ጓደኞችሽ በሚጠሩሽ ሳይሆን በትክክለኛ ስምሽ እንተዋወቅ" ሲላት በተማሪዎች ፊት ሙሉ ስሟን መናገሩ ተፋፈራት። ከቅርብ ጓደኞቿ ዉጭ ትክክለኛ ስሟን የሚያዉቅ የለም። ሁሉም የሚጠሯት በማህበራዊ ድህረ ገጽ ስሟ "ቤዛ ዲንፕል" እያሉ ነዉ። ነገር ግን አሁን አማራጭ የላትም ትክክለኛ ስሟን ልትናገር ነዉ።
..."Beza.... Bezabeshe fentaw እባላለሁ" "ካካካካ በዛብሽ ሀሀሀ .... " የሳቅ አይነቶች በክፍሉ ዉስጥ ተሰሙ። ኢማንም ሁኔታዉ ፈገግ አደረጋት። ሳቀች። መምህር ከድር ኢማንን ሲመለከት ፈገግታዋ ልቡን ለሁለት ሰንጥቀዉ ወደ ላይ እንደፈነዳ ርችት ዉስጡ በሷ ፍቅር ተቀጣጠለ።
ቤዛ በመምህር ከድር ተበሳጭታበታለች ..

.. ደብቃ የኖረችዉን ስሟን በተማሪዎች ፊት እንድትናገር አድርጎ አስቆባታል። ይበልጥ ያናደዳት ደግሞ ስሟን የሚያዉቁት የቅርብ ጓደኟቿ ሳይቀሩ መሳቃቸዉ ነዉ። እንደዚያም ሆኖ ግን በፌስቡክ የምታወራዉን ልታቋርጥ አልፈለገችም። ከሰሚር ጋር በፌስቡክ ቻት እያደረገች የጽሁፍ መልእክት እየተለዋወጡ ነዉ።
"ቤዝ ጓደኞችሽን አስተዋዉቂኝ" የሚል መልእክት ደረሳት። ሰሚርና ቤዛ ለረጅም ሰአታት የጽሁፍ መልእክት ስለሚለዋወጡ ተላምደዋል። በተለይ እሱ በሚዲያ ከሚታወቁ ሰዎች፤ ዳኢዎች፤ ሙነሽዶችና ጸሀፊዎች ጋር እየተነሳ በሚለቃቸዉ ፎቶዎች ለሱ ጥሩ የሆነ አመለካከትና ግምት አላት።
"ሶስት ጓደኞች አሉኝ። ከሁሉም ግን አንዷ ይበልጥ ትቀርበኛለች። ኢማን ትባላለች" አለችዉ።
"ስሟ ያምራል። ለምን በፎቶ አታስተዋዉቂንም" ብሎ ጠየቃት። ግኑኝነታቸዉን ይበልጥ ማጠናከር መስሎ ስለተሰማት "እሺ እልክላሀለሁ" በማለት መለሰችለት።
በትምህርት ቤቱ ዉስጥ የእረፍት ሰአት ደዉሉ ተሰማ። አብዛሀኛዉ ተማሪዎች በጉጉት የሚጠብቁት ጊዜ ነዉ። በተለይ ወንድ ተማሪዎች እነ ኢማን የመማሪያ ክፍል ሄደዉ የኢማንን ዉበት ዳግም እስከሚያዩት ድረስ ይቻኮላሉ። የ12ኛ E ክፍል ተማሪ የሆነዉ ሁሴን ለጓደኞቹ ስለ ኢማን ቁንጅና ሲናገር እንዲህ ይላል "ጸሀይን በሙሉ አይን ማየት እንደማይቻለዉ ሁሉ እሷንም ትኩር ብሎ ማየት ይከብዳል። ምክንያቱም ዉበቷ ልብን ያርዳል፤ ሳታስበዉ ትማርካሀለች። የፊቷን ቅርፅ፤ የሰዉነቷን ጥራት፤ የቅንድቧን አቀማመጥ፤ የአይኖቿን ገዳይነት ስታይ በክፈለ ዘመኑ ብቻ ሳይሆን ለዘላለሙ እሷን የሚወዳደር ሴት እንዳልተፈጠረ ትመሰክራለህ!..." እያለ ስለሷ ዉበት አድናቆት ሳይጨርስ ፊደላቶችን አገጣጥሞ እሷን የሚመጥን ቃል መፍጠር ያቅተዋል። አብዛኞቹ ተማሪ እንደ ሁሴን ናቸዉ። የኢሙን ዉበት ለመግለጽ መጀመር እንጂ ለመጨረስ አልታደሉም።
እንደተለመደዉ ክፍሉ በተማሪዎች ተሞልቷል። 12ኛ C ክፍል ለተማሪዎች መዝናኛ ክበባቸዉ ነዉ። ፍቅር የጠማዉ፤ ለአይን ረሀብ የተጋለጠ፤ ልቡ በፍቅር ለተናጠ ሁሉ በተሰጣቸዉ ዉስን ደቂቃ ፈዉስ ያገኙበታል።
"ኢሙ በናትሽ እምቢ እንዳትይኝ..." ብላ በልምና አሰተያየት አንገቷን ወደ ጎን ሰበር አድርጋ ተማጸነቻት።
"ምን ልጠይቂኝ ነዉ ቤዝ..." ብላ ፊቷን ወደ ጓደኛዋ አዞረች። ቤዛ ድጋሜ እንደመቅለስለስ አለችና ... "ፎቶ እንነሳ!" አለቻት። የአብዛኛዉ ተማሪ ትኩረት ከነሱ ጋር ስለነበር የሚያወሩትን እያዳመጡ ነበር።
"... ለፌስ ቡክሽ ነዋ.. አይ አይሆንም!" አለቻት።
"እሺ በያት .. እሺ በያት... እሺ በያት" ክፍሉ ዉስጥ ያሉ ተማሪዎች በጭብጨባና በድምጽ ጠባቧን ክፍል አናወጧት። ኢማን መከልከል አልቻለችም። ምክንያቱም የዚያ ሁሉ ተማሪ ድምጽና ጭብጨባ መቆም ካልቻለ ትምህርት ቤት ግቢ ዉስጥ ያሉ መምህራኖችና ሰራተኞች መሰብሰባቸዉ አይቀርም። በሷ ምክንያት ረብሻ ተነስቶ በማይረባ ነገር መወቀስ ስላልፈለገች ተቻኩላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና "እሺ .. እሺ እነሳለሁ። እናንተ ዝም በሉ!" ብላ ተማሪዎቹን አረጋጋቻቸዉ።
ከኢማን ጋር ፎቶ የተነሳችዉ ቤዛ ብቻ አልነበረችም። የክፍሉ ተማሪና ከሌላ ክፍል ለእረፍት የመጡ ወንዶችም ሳይቀሩ ስልኮቻቸዉን ከኪሶቻቸዉ እያወጡ ከኢማን ጋር ፎቶ ተነሱ። ኢማን በተቀመጠችበት ተማሪዎች እየተቀያየሩ ከጎኗ በመሆን ፎቶ ሲነሱ በክፍሉ ዉስጥ ያለችዉ አመቱን ሙሉ የሚያዉቋት ተማሪ ሳይሆን በሚዲያ የምትታወቅ፤ ድጋሜ በአካል እሷን ለማግኘት እድሉ የሌላቸዉና የማያገኟት ታዋቂ አርቲስት የተከሰተች ይመስላል።
ብዙም ሳትቆይ ቤዛ ከኢማን ጋር የተነሳችዉ ፎቶ ለሰሚር ላከችለት። እሱም ቢሆን የተላከለትን ፎቶ ወዲያዉ ነበር የተመለከተዉ። ባየዉ ዉበት እጅግ በጣም ተደመመ። ተንቀሳቃሽ ስልኩ ላይ ፈዞ ቀረ። የብዙዎችን አይን አፍጥጦ፤ የአያሌዎችን ልብ አስደንግጦ የነበረዉ የኢማን ዉበት የሰሚርም አይኖች ከመማረክ አልቦዘኑም። ቤዛን ቆንጆ ነሽ እያለ ሲያደንቅ የነበረዉ ከኢማን ጋር በአንድ ፎቶ ሲመለከታት አፈር ሆነችበት። እዚህ ግባ የማይባል ዉበት ሲያደንቅ እንደኖረ ገባዉ።
ቤተል ፡ አዲስ አበባ
ከምሽቱ 2:00 ሰአት
... ምሽቱ ነፋሻማ ነዉ። በአንድ ትልቅ ግቢ ዉስጥ ከእህቱ ጋር አብሮ የሚኖረዉ ሰሚር እንደተለመደዉ አይኖቹን ከስልኩ ላይ ጥዷቸዋል። ከጧት በኃላ ፌስ ቡክ ስላልገባ የሚያቸዉ ነገሮች አዲስ ሁነዉበታል። ከዚህ በፊት በማህበራዊ ድህረ ገጽ ላይ ያላየዉ ነገር ግን ጧት ቤዛ በዉስጥ መስመር የላከችለት ፎቶ ሚዲያዉ ላይ ሲቀባበሉት ተመለከተ። የሷ የሆነን ፎቶዎች ከወንዶችና ከሴቶች ጋር ሆና የተነሳቸዉን በሰፊዉ ሲዘዋወር ተመለከተ። በፌስ ቡክ ገጽ ብዙ ተከታይ ያላቸዉና የሚያዉቃቸዉም ሰዎች ዉበትን የሚገልጹበት ፎቶ አግኝተዉ በየገጾቻቸዉ ለጥፈዉታል። ለማመን እስከሚከብድ ድረስ በህይወቱ ዛሬ ጧት በፎቶ ያያት ሴት ምሽት ላይ ግን በብዙዎች ተወዳጅነትን አግኝታ ፌስቡክን ነግሳበታለች። በሚዲያዉ ታዋቂ አክቲቪስት የተባለዉ ግለሰብ የኢማንን ፎቶ ገፁ ላይ ለጥፎ ከስር "ዉበትን የምንገልጽበት ሴት በሌለችበት ምድር ይቺ ቆንጆ ተገኝታ ለሷ ዉበት የሚለዉ ቃል አነሰባት!" ብሎ አስፍሯል።
ሰሚር መረጋጋት እስኪያቅተዉ ድረስ ይችን ዉብ ሴት መተዋወቅ ፈልጓል። ቀኑን ሙሉ ፌስቡክ ባለመግባቱ ብዙ የተከማቹ የድምጽና የጽሁፍ መልእክቶች ቢኖሩትም ለማየት ብዙም አልጓጓም። የዚህችን ልጅ ስልክ ቁጥር ማግኘት አለበት።
.
...
"ሄሎ ቤዝ"
"ወይዬ ሰሙሪ"
"ደህና አመሸሽ" አላት። ድምጾቹ ቀዝቀዝ ብለዉ ነበር። ቤዛ ሰሚርን የምታዉቀዉ በተጨዋችነቱ ነዉ። ነገር ግን በዚህ ምሽት የደወለላት የምታዉቀዉ ሰሚር አልሆንልሽ አላት።
"አልሐምዱሊህ ደህና ነኝ። እንዴት ነክ አንተ?"
"አለዉልሽ። ፌስቡክ ስገባኮ አላየሁሽም በሰላም ነዉ?"
"አዎ ሰሙሪ የቤት ስራ ነበረንና ኢሙ እንድታስረዳኝ ከሷ ጋር ሆኜ ነዉ!" አለችዉ። ሰሚር ሰዉነቱን ሙሉ ነዘረዉ። ኢማን ጋር ነኝ ስትለዉ ለመተዋወቅ ጥሩ አጋጣሚ ስለሆነለት በደስታ ጮቤ ረገጠ።
"ኦዉ ደስ ይላል። ኢማን ማለት ቀን ፎቶዋን የላክሽልኝ ልጅ ናታ?" ብሎ ጠየቃት። ለኢማን የተለየ ስሜት እንደተሰማዉ ቤዛ እንድታዉቅበት አልፈለገም ነበር።
"አዎ ናት!"። አረጋገጠችለት።
"ታዲያ በስልክ አታስተዋዉቂኝም እንዴ? ጓደኝነትኮ ደስ ይላል..." አላት። እስከሚተዋወቃት ቸኩሏል።
ይቀጥላል 200Likes ቡሀላ

ክፍል 2
... ሴትን ልጅ እንዴት ማናገር እንዳለበት ያዉቃል። በጽሁፍም ሆነ በድምጽ ሰሚርን የማዉራት አጋጣሚ የነበራቸዉ አብዛኞቹ ምርኮኛዉ ሁነዋል። ለረጅም አመታት በማህበራዊ ድህረ ገጽ የምታዉቀዉ ሄሌን የማዳሟ ሸቃላ 'ምላስህ እንኳን የሴትን ልጅ ልብ ቅቤ ያቀልጣል' ትለዋለች።
"ሄሎ"
"ሄሎ"
"አሰላሙአለይኩም" ብሎ ሰላምታ አስቀደመ።
"ወአለይኩም ሰላም" አጠር ያለ መልስ። ሰሚርን የምታናገረዉ በሰዉ ግፊት አስገድደዋት እንደሆነ በድምጿ ያሳብቅባታል። "ኧረ ፈገግ ብለሽ አናግሪዉ" የሚለዉ የቤዛ ድምጽ ይሰማል። "ፊቴን እያየዉ አይደለምኮ ሚያወራኝ" ብላ ስትመልስላት ከወዲያኛዉ ማዶ በቀጭኗ መስመር የሚወራዉን ሰምቶ ሰሚር ፈገግ አለ።
..." ሰላም ነዋ?"
..."አልሐምዱሊላህ" ሚቀጥል ነገር የለዉም። 'አንተስ እንዴት ነህ' አላለችዉም።
..."አንተስ አይባልም እንዴ? የሰዉ ደህንነት መጠየቅ ምንድን ነዉ ክፋቱ?" አላት። ኢማን በባህሪዋ ሰዉ እንዲቀየማት አትፈልግም። አሁን ደግሞ ስልኩን ቶሎ ለመዝጋት ካላት ጉጉት የተነሳ ማታዉቀዉን ሰዉ እያስቀየመች እንደሆነ ገባት። ስለዚህ ዛሬን ብቻ በጥሩ ሁኔታ ላናግረዉ ብላ በማሰብ ወደ ትክክለኛ ባህሪዋ ተመለሰች።
"ይቅርታ ወንድሜ...." ብላ የጀመረችዉን ሳትጨርስ በመሀል ገብቶ "ሰሚር እባላለሁ" አላት። "... ምናልባትም ኢስላማዊ መድረኮችን የምትከታተይ ከሆነ ልታዉቂኝ ትችያለሽ። ብዙ ጊዜ አልጠፋም።" ይበልጥ ራሱን ሊያስተዋዉቅ ሞከረ። እሷ ግን ትኩረት ሳትሰጠዉ "ኢማን ... " አለችዉ።
"ዛሬ ምሽት ፌስቡክ ባንቺ ፎቶ አሸብርቋል። ሴት፡ ወንዱ ፎቶሽን እየተቀባበሉት ነዉ። ይሄን ያክል ቆንጆ ነሽ ማለት ነዉ?" ብሎ ጠየቃት። ስለዉበቷ መልሶ እሷኑ ይጠቃት እንጂ ከሚያዉቃቸዉ ሴቶች በላይ ዉብ እንደሆነች ህሊናዉ ያዉቀዋል።
"ይሆናል ዛሬ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ጋር ፎቶ እየተነሳን ነበር" አለችዉ።
"ግቢዉ ዉስጥ ተወዳጅ ነሽ ማለት ነዋ"
"እኔንጃ ምናልባትም ከአስቀያሚ ሴት ጋር ፎቶ ተነስተዉ ስለማያቁ ይሆናል" ስትለዉ ሁለቱም አብረዉ ተሳሳቁ። ኢማን ቆንጆ ብቻ ሳትሆን ተጨዋችና ቀልድ አዋቂም ጭምር ናት።
"ይሄን ጨዋታሽንማ ሌላ ጊዜም መስማት እፈልጋለሁ። ለምን ስልክ ተለዋዉጠን አልፎ አልፎ አናወራም።" አላት።
"ከተዋወቅን አይበቃም። በዚያ ላይ እንደነገርከኝ ከሆነ በጣም ታዋቂ ስለሆንክ ስራ ይበዛብሃል..." ስትለዉ ከሁለቱም በኩል በድጋሜ ሳቅ አስከተሉ።
... ምሽቱ አምሮለታል። ሰሚር በፌስቡክና በቴሌግራም የሚያወራቸዉ ሰዎች እጅግ በጣም የበዙ ቢሆንም ከዚህ በኃላ ግን ቅድሚያ ሊሰጣት የሚገባዉ አይነት ልጅ ተዋዉቋል። ኢማን!።
ደሴ ፡ መናፈሻ አከባቢ
... የወሎዋ ማእከል የሆነችዉ ደሴ ከተማ ቀኑን ሙሉ ከተለያዩ አጎራባች ከተሞችና ክልሎች በሚመጡ እንግዶቿ ስትዋከብ ከዋለች በኃላ ምሽቱን ተረጋግታለች። ሁሌም ቢሆን በማይለመደዉ ብርዷ ከኗሪዎቿ ጋር ግብግብ ፈጥራለች። መምህር ከድር መናፈሻ አከባቢ በተከራያት ጠባብ ክፍል ዉስጥ ብርዱን ለማሸነፍ በሚመስል ሁኔታ ጋቢና ብርድ ልብስ ደራርቦ ከአንድ መጽሀፍ ጋር ተፋጧል። በኡስታዝ በድሩ ሁሴን ተጽፎ ለአንባብያን በደረሰዉ "ለዉጥ" መጽሀፍ ላይ አይኖቹን ተክሏል። የኡስታዝ ሉቅማን ገጸ ባህ አጃኢብ ያሰኘ ቢሆንም መምህር ከድር ግን በአይነ ህሊናዉ የተሳለችዉን ቆንጆ ከማለም አልቦዘነም። የሂሳብ ትምህርትን ተማሪዎቹ እንዲወዱት ብዙ ጥረቶች ያደርጋል። የተለያዩ መጽሀፍቶችን በማገላበጥ እንዲረዱት በማሰብ በደንብ ይዘጋጃል። ነገር ግን 12ኛ C ክፍል ሲገባ፤ የኢማንን ቁንጅና ሲያይ የተዘጋጀበት ነገር ሁሉ ይጠፋበታል፤ እዉቀቱ ይተንበታል። ኢማን ልቡን ብቻ ሳይሆን ማሰቢያዉንም ጭምር ተቆጣጥረዋለች። እሷን እንጂ ሌላን ማለም ተስኖታል።
... የሚያነበዉን መጽሀፍ ያቆመበት ቦታ እንዳይጠፋዉ ምልክት አድርጎ ካስቀመጠ በኃላ ከ12ኛ C ክፍል የሰበሰበዉን የቡድን ስራ ወረቀት አነሳ። ከሁሉም ወረቀቶች መርጠና የኢማን ስም ያለበትን ለየና ስሟን ደጋግሞ ተመለከተ። 1. ኢማን ጀማል ፤ 2. በዛብሽ ፈንታዉ ፣ 3. ዘሀራ አህመድ ፣ 4. ፋጡማ አሊ ፣ 5. ኑረዲን እንድሪስ የቡድን አጋሮቿ ስም ዝርዝር ነበር። ከሁሉም ግን አንድ ቁጥር ላይ ያለዉ ስም ያምራል። ኢማን ጀማል!
መምህር ከድር በቤተሰቦቹና በቅርብ ጓደኞቹ ትዳር እንዲመሰርት ለብዙ ጊዚያት ግፊት ሲደረግበት የነበረ ቢሆንም ለሱ የምትሆንና ለትዳር አጋርነት የሚመርጣት ሴት ባለማግኘቱ ቸል ብሎት ኖሯል። አሁን ግን ግዜዉ የደረሰ ይመስላል። ምክንያቱም በሚያስተምርበት ክፍል ዉስጥ ፊቷ ከጨረቃ የሚያበራ፤ በባህሪዋ አመለ ሸጋ የተሰኘች፤ በትምህርቷ ጎበዝ፤ በሀይማኖቷ ጠንካራ ሴት አለች። "ኢማንን ማግባት አለብኝ!" ብሎ ለራሱ ወሰነ። የቡድን ስራዉን ወረቀቶች አስተካክሎ ጠረንቤዛዉ ላይ ካስቀመጠ በኃላ ፍራሹ ላይ በጀርባዉ ተንጋሎ ተኛ። 'ኢማንን እንዴት ነዉ የማናግራት? ምን ብዬ ነዉ የምጠይቃት?'.....
.... "እንዴት አደራችሁ ተማሪዎች" የመጀመሪያዉን ክፍለ ጊዜ ከአስራ ሁለተኛ C ክፍል ተማሪዎች ጋር ሊያሳልፍ በጧቱ ተከስቷል።
.... "ደህና ቲቸር" ሁሉም ተማሪዎች በህብረት መለሱለት። መምህር ከድር ቀኑ ምርጥ እንደሚሆንለት አሰበ። ምክንያቱም ኢማንን ስላያት። ዛሬ ደግሞ ይበልጥ አምሮባታል። ከራሷ ላይ የጠመጠመችዉ ጥቁር ሻርብ ከቀይ ፊቷ ጋር ተደማምረዉ በድቅድቅ ጨለማ ላይ እንደወጣዉ ሙሉ ጨረቃ ታበራለች። ምሽቱን ሙሉ ሲያስብ ያደረዉ ስለሷ በመሆኑ ደፍሮ ባያናግራት እንኳ ስልክ ቁጥሯን ማግኘት እንዳለበት አምኗል።
..."ቤዛ" አላት። ጥቁሩ ሰሌዳ ላይ የጻፈዉን ወደ መማሪያ ደብተሯ በመገልበጥ ላይ የነበረችዉ ቤዛ ቀና አለችና "የስ ቲቸር" ብላ መልስ ሰጠች።
"አንዴ ዉጭ ላናግርሽ?" ብሏት ከክፍሉ ቀድሞ ወጣ።
"አሰላሙዓለይኩም ኢሙ እንዴት ነሽ? ሚመችሽ ከሆነ ልደዉልልሽ ጨዋታሽ ናፍቆኛል!" ብሎ መልእክት ከላከላት ድፍን አስር ደቂቃ የሞላዉ ቢሆንም እስካሁን ግን መልስ አልተሰጠዉም። ይችን አጭር መልእክት ለመጻፍ ብዙ ጽሆፎችን እየጻፈ እያጠፋ ቢሆንም በስተመጨረሻ ግን ልኮላታል። 'ምን ሆና ነዉ የማትመልስዉ?' እያለ በመጨነቅ ላይ ነዉ። ሰሚር መልእክት ልኮላቸዉ የሚቆዩበት ሴቶች የሉም። ሰልከክ ያለ ፤ የወንድ ሚባል አቋም ያለዉ ሰሚር በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ አዉቀዉት የሚያፈቅሩት ሴቶች በጣም የበዙ ናቸዉ። ከሀገር ዉጭና ከሀገር ዉስጥም አድናቂዎች አሉት። ምክንያቱም ታዋቂ ነዉ። በተለይ ከሰሞኑ አዲስ ነጠላ ነሽዳ ሊለቅ ስለሆነ ይበልጥ ታዋቂነቱ ይጨምራል።
"...ብዙ ጊዜ የተለመደዉ የህይወታችንን ጉዞ የሚቀይሱልን በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ናቸዉ። እነሱ በቀደዱልን ቦይ እንፈሳለን፤ የነሱን ፈለግ ተከትለን እንጓዛለን። የራሳችን አላማ የሌለን እስኪመስለን ድረስ በሌሎች አላማ ዉስጥ ራሳችንን ቀብረን የነሱ ጉዳይ አስፈጻሚ እንሆናለን።..." ወጣቱ ኡስታዝ ለቂርአት የመጡ ሴቶችን ህይወታቸዉ ግብ እንዲኖረዉ እየመከራቸዉ ነዉ። ከሴቶቹ መካከል ኢማን አንዷ ናት። አስተምህሮቱን በተመስጦ እየተከታተለች ነዉ። ኡስታዙ ቀጠለ። "... ህይወታችንን ትርጉመ ቢስ አናድርገዉ። እርግጥ ነዉ ስኬት ያለፈተና አይመጣም። መንገዳችን በመሰናክሎች የታጠረ ነዉ። ጠንካራ ሰዉ ማለት እንቅፋት መታኝ ብሎ ተስፋ ማይቆርጥ ነዉ።...." ኢማን ስልኬ እንዳይረብሸኝ ብላ ንዝረት ላይ አድርገዋለች። ቢሆንም ግን ስልኳ ላይ በተደጋጋሚ የሚደወል ስልክ በመኖሩ ተመለከተችዉ። ሁለት

የጽሁፍ መልእክትና አምስት የደወል ምልክቶች አየች። ሁለቱም የተለያዩ አዲስ ስልክ ቁጥሮች ናቸዉ። ከዚህ በፊት አታዉቃቸዉም። የመጀመሪያዉን መልእክት ከፈተችዉ ""አሰላሙዓለይኩም ኢሙ እንዴት ነሽ? ሚመችሽ ከሆነ ልደዉልልሽ ጨዋታሽ ናፍቆኛል!" ይላል። ማን እንደሆነ ማወቅ አልቻለችም። ሁለተኛዉን መልእክት ስትከፍተዉ "አሰላሙአለይኩም ኢማን እንዴት ነሽ? እንዳረበሽኩሽ ተስፋ አደርጋለሁ። ከተመቸሽና ፍቃደኛ ከሆንሽ የማናግርሽ ነገር አለ። መምህር ከድር ነኝ!"። 'ቲቸር ከድር' ብላ ለራሷ ስሙን ደገመችዉ። መምህሯ ስለሷ የተለየ አመለካከት እንዳለዉ እሷ ብቻ ሳትሆን ሙሉ የክፍሉ ተማሪዎች ያዉቃሉ። አስተያየቱ ከተማሪነት በዘለለ የተለየ ፍላጎት እንዳለዉ ያሳብቅበታል። ቢሆንም ግን ኢማን በዚያ መንገድ ማሰብ አልፈለገችም። ስልኳን ወደ ቦታዉ መልሳ አትኩሮቷን ወደ ወጣቱ ኡስታዝ አደረገች።
"... በ'ርግጥ አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ስለኛ እኛ ከመፈጠራችን በፊት ሁሉንም ቀድሞ ወስኗል። ቢሆንም ግን በዙሪያችሁ ያሉ መልካም የማይባሉ ሰዎች የስኬት ጉዟችሁን እንዲያስተጓጉሉባችሁ አትፍቀዱለቸዉ። መንገዳችሁን በጽናትና በትጋት ወደ ፊት ቀጥሉ። ያኔ ስኬታማ ሰዎች ትሆናላችሁ። ሰዎች እንድትገኙ የሚፈልጉበት ቦታ ሳይሆን እናንተ ምትመኙት የስኬት ማማ ላይ ትፈናጠጣላችሁ።...." የስነ ልቦና ትምህርት ምርቁ ወጣቱ ኡስታዝ ንግግሩን በግሩም ሆኔታ አጠናቀቀ።
... ምሽቱ እየተቃረበ ነዉ። ከቀኑ አስራ አንድ ሰአት አከባቢ መምህር ከድር ቃና ዘገሊላ ካፌ ተቀምጦ ብርዱን እንዲከላከልለት ሻይ እየጠጣ ተቀምጧል። ኢማን ለጽሁፍ መልእክቱ ምላሽ አልሰጠችዉም። ሀሳቡ ሁሉ እሷ ስለሆነች ለአፍታም ቢሆን ሌላ ነገር ማሰብ አይሻም። ደግሞ ደጋግሞ ስልኩን ይመለከታል። ካፌዉ ካለበት ህንጻ ስር የተከፈተዉ ለስለስ ያለ የመልካሙ ተበጀ ሙዚቃ ይሰማል።
'ኧረ መላ 'ምጡ ዘመድ ወዳጆቼ
አይናፋር ሁኛለሁ አይናፋር አይቼ
ሰላምታ አልሰጠኃት አላነጋገርኳት
ባይኔ ብቻ እያየሁ አንድ አመት ወደድኳት" ሙዚቃዉን ከዚህ በፊት ቢያዉቀዉም አሁን ላይ ግን በግድም ቢሆን ከራሱ ጋር ሊያገናኘዉ ሞከረ።
ከድርም ሆነ ኢማን አይናፋር አልነበሩም። ነገር ግን ፍቅር አይናፋር እንዲሆን አስገድዶታል። ቀና ብሎ እሷን ማየት፤ ደፈር ብሎ ማናገር አልቻለም። ሲያት ይደነባበራል፤ ሊያናግራት ሲያስብ ምላሱ ይተሳሰራል። ለዚያም ነዉ ደፈር ብሎ ዉስጡ ያለዉን ስሜት በስልክ ለማናገር በማሰብ መልእክት የጻፈላት። ሻይዉን ፉት እያለ፤ ሙዚቃዉን ግጥሞች በደንብ እያጤነ ሳለ ስልኩ ላይ የጽሁፍ መልእክት ገባለት። ለማየት በጣም ተቻኩሏል። በፍጥነት ስልኩ የጠየቀዉን ሚስጥር ቁጥር አስገብቶ ከኢማን መልእክት ጋር ተፋጠጠ።
ይቀጥላል 250Likes ቡሀላ

የቅዳሜ ቀደዳ 17-(፲፯)
እንዴት ነሽ እናቴ? እንዴት ሰነበትክ ጌታዬ?
እንደተለመደው ቅዳሜያችንን ፈታ፣ ዘና፣ ፀዳ እናድርጋት! የዛሬው ደግሞ ጠብሰቅ ያለ ፀዴ ቀደዳ ነው! እውነት ይጠቅምሃል!
እስቲ ዝም ብለህ አስበው?
አሜሪካ ከ 330 ሚልዮን በላይ የሚሆን ህዝብ አላት። ከዚህ ቁጥር ውስጥ ገበሬው ከ 2 ሚልዮን ወይም ከ 1% ያነሰ ነው። ይህ 2 ሚልዮን ገበሬ 330 ሚልዮን የሚሆነውን የአሜሪካ ህዝብ አትረፍርፎ ይመግባል። ህንድ ከ 1.3 ቢልዮን በላይ ህዝብ አላት። ይህንን በቢልዮን የሚቆጠር ህዝብ አርሶ የሚያበላው 16 ሚልዮን ገበሬ ብቻ ነው። ካናዳ 38 ሚልዮን የሚገመት ህዝብ አላት። ይህንን የካናዳ ህዝብ አንደላቆ የሚመግበው የገበሬ ቁጥር 500 ሺህ አይደርስም። ከ 1.3% በታች የሚሆነው የካናዳ ገበሬ 38 ሚልዮን የሚሆነውን የሃገሩን ህዝብ ከመመገብ አልፎ የተረፈውን ስንዴ ለደሃ ሃገራት በእርዳታ መልክ ይሰጣል!
እዚህ ጋር ደግሞ እናት ሃገር ኢትዮጵያ ውስጥ 85% የሚሆነው ገበሬ 120 ሚልዮን የማይበልጠውን ህዝብ መመገብ አልቻለም! ይህንን አሳፋሪ ሃቅ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት በአደባባይ ተሸክመውት ይዞራሉ!
ወደ ዋናው ጉዳይ ላምጣህ ጌታዬ!
ግብርና የሚያድገው የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣ እርሻን ሜካናይዝድ በማድረግ፣ መስኖን በማስፋፋት እና የውሃ ሃብትን በብልሃት በመጠቀም ነው! ምዕራባዊያኖቹ በተለይ አሜሪካ እና ካናዳ ግን የሚመክሩን ሌላ ነው!
"...ደሃ ናችሁ! ከጠኔ አልተላቀቃችሁም። በምግብ ዋስትና እራሳችሁን አልቻላችሁም። አሁንም ስንዴና በቆሎን ከኛ ትለምናላችሁ። ድርቅ ያጠቃችኃል። ምርታማነታችሁ የላሸቀ ነው። የግብርና ቴክኖሎጂ ብርቃችሁ ነው። ዋናኛ እና ብቸኛ አማራጫችሁ እንደኛ "GMO"ን መጠቀም ነው!..." የሚል ነው!
ነገርየውን እንበታትነው!
"GMO" ሲተነተን "Genetically Modified Organism" ማለት ነው። በአማርኛው "በእንስሳት እና እፅዋት ላይ የሚደረግ የዘረ መል ቅየጣ (ለውጥ)" እንደማለት ነው። በአጭሩ ባእድ የሆነ ዘረ መልን ወይም "gene" ንን የሌላ ሰብል ወይም እንስሳ "DNA" ውስጥ ተፈጥሮአዊ ባልሆነ መንገድ መክተት/መውጋት ወይ መጨመር ማለት ነው። በሌላ መንገድ ኢ- ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ላብራቶሪ ውስጥ የአንዱን ዘረ መል ሌላ ዘረ መል ውስጥ በመጨመር አርቴፊሻል ሰብልን እና እንስሳትን መፍጠር ማለት ነው! አባዬ! ስናወርደው ሰዎች የተለያዩ የሰውነት ክፍላቸውን ለማተለቅ አርቴፊሻል ሆርሞኖችን እንደሚወጉት ብለህ አስበው!
ይህንን መንገድ መጠቀም አለባችሁ የምትለን አሜሪካ "ለምን?" ስትባል ".....ምርታማነታችሁ ያድጋል፣ የምትዘሩት ምርት ተባይን፣ ድርቅን እና አደጋን ይቋቋማል! ይህንን መንገድ ስትጠቀሙ የተትረፈረፈ ምርት ስለምታመርቱ የምግብ ዋጋ ይቀንሳል! ገበሬውም ከራሱ አልፎ ህዝቡን በሚገባ ይመግባል! መራብ ታሪክ ይሆናል! ..." የሚል ነው!
"GMO"ን በመጀመርያ የሞከረችው እና ያፀደቀችው እ.ኤ.አ 1994 ላይ አሜሪካ ናት! 90% የሚሆነው አሜሪካ ውስጥ የሚበቅለው በቆሎ፣ አኩሪአተር እና የጥጥ ምርት "GMO" ነው! አሜሪካ ውስጥ 80% በየሱፐር ማርኬቱ የሚሸጡ ምግብ ነክ ምርቶች "GMO" ናቸው!
በቆሎ፣ ፓፓያ፣ ድንች፣ ቲማቲም፣ አቮካዶ፣ አፕል፣ ብርቱካን፣ ሸንኮራ አገዳ(ስኳር)፣ ስንዴ፣ ሩዝ፣ አናናስ፣ አኩሪ አተር፣ ስጋ፣ የአልኮል መጠጦች፣ ለስላሳ መጠጦች፣ የታሸጉ ጁሶች፣ የታሸጉ ወተቶች፣ ፓስታ፣ ዳቦ....ምን አለፋህ ሁሉም ምርታቸው "GMO" ነው! ላሞች፣ አሳማዎች፣ ፈረሶች እና ውሾች ላይ ሳይቀር እየሞከሩት ነው። አሜሪካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ስንዴ እና በቆሎን ጨምሮ 80% የሚሆነው የካናዳ ምግብ "GMO" ነው።
እና ምን ችግር አለው?
አባዬ! በነዚህ ሃገራት ውስጥ ያለውን ህዝብ አይተህ መገመት ትችላለህ! አብዛኛው ህዝብ የሚበላው ምግብ በዚህ ኢ-ተፈጥሮአዊ መንገድ የሚመረት ስለሆነ ብዙ የጤና እክሎች ያጋጥሙታል!
ጥናቶች እንደሚሉት "GMO" በዋነኝነት ካንሰርን ያመጣል! በነገራችን ላይ ከ 10 ሚልዮን ሰዎች በላይ በካንሰር በየአመቱ ህይወታቸው ያልፋል! ዓለም ላይ ከሚሞተው ስድስት ሰው አንዱ በካንሰር ሳብያ ነው። ሌላው መዘዝ ከልክ ያለፈ ውፍረት(Obesity) ነው! 70% የሚሆኑ አሜሪካዊ ጎልማሳዎች ዝርጥርጥ ናቸው። በአሜሪካ ብቻ እስከ 300 ሺህ ሰዎች በየአመቱ በ "Obesity" ሳብያ ይሞታሉ! 12 ሚልዮን አሜሪካዊ ህፃናት "Obese" ናቸው!
በመጪዎቹ አምስት አመታት ውስጥ ብቻ 2.6 ቢልዮን የዓለማችን ህዝብ "obese" ይሆናል! "GMO" ከካንሰር እና ከልክ ያለፈ ውፍረት በተጨማሪ ስኳር፣ የልብ በሽታ፣ የአዕምሮ ዝግመት፣ ጭንቀት እና "organ failure" ጭምር ያመጣል ይባላል!
በቅርቡ አንድ ተመራማሪ አይጦችን ሰብስቦ የ "GMO" ምርት የሆኑ ምግቦችን ብቻ እንዲበሉ ካተደረገ በኃላ አብዛኛዎቹ አይጦች ለጭንቅላት እጢ(Brain tumour) እንደተዳረጉ እና 70% የሚሆኑት አይጦች አንድ ወር እንኳን ሳይቆዩ ወዲያውኑ እንደሞቱ ተናግሯል!
የሚገርም ሃቅ አንድ!
የ "GMO" ምርቶች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው እንደሚያመዝን የተረዱ እነዚህ ሁሉ የአውሮፓ ሃገራት "GMO"ን አግደዋል! አንብብልኝ አንዴ ጌታዬ!
"....ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ኔዘርላንድ፣ ዴኒማርክ፣ ማልታ፣ ጣልያን፣ ክሮሽያ፣ ቤልጄም፣ ስኮትላንድ፣ ፖላንድ፣ ቡልጋሪያ፣ ኢንግላንድ፣ ራሽያ እያለ ይቀጥላል!....."
የሚገርም ሃቅ ሁለት!
አሜሪካ አሁንም ድረስ ሽንጧን ገትራ "GMO is safe!" ብላ ከመከራከር አልፋ የአፍሪካ ሃገራት "GMO"ን እንዲቀበሉ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጫናን ታደርጋለች። ከአጠቃላይ የአፍሪካ ሃገራት እስካሁን "GMO"ን የተቀበሉት ሱዳን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ ናቸው!
"ለምን ይሄንን ሁሉ ጫና ታደርጋለች?" ካልከኝ!
እነዚህን የ "GMO" ዘሮች የሚያመርቱት "Monsanto", "Dow Agro science", "BASF" እና "DuPont" የሚባሉ ግዙፍ የአሜሪካ "Bio-tech" ኩባንያዎች ናቸው! የሚፈልጉት እያንዳንዱ የአፍሪካ ገበሬ በየግዜው ከነዚህ ኩባንያዎች የ "GMO" ዘሮችን እየገዛ እነሱ ላይ ጥገኛ እንዲሆን ነው። ፈረንጅ ምን ይላል መሰለህ ጌታዬ!
"...If you Control oil, you can control nations, if you control food, you can control people!.."
እነዚህ ኩባንያዎች የምትዘራውን ዘር ሲሸጡልህ ብቻ ትዘራለህ! ካልሸጡልህ ትራባታለህ!
ገራሚ ሃቅ ሶስት!
አሜሪካ "GMO" ምንም ጉዳት እንደሌለው ሃገራትን ለማሳመን በብዙ ሚልዮን ዶላሮች መድባ ትሰራለች! ቅድም የጠቀስናቸው ግዙፎቹ የአሜሪካ "Bio-tech" ኩባንያዎች ብዙ ሚልዮን ዶላሮችን ለተለያዩ ሚድያዎች እና የጥናት ተቋማት በመክፈል "GMO" ጉዳት እንደሌለው አድርገው እንዲያጮሁ ያደርጋሉ! አሜሪካ ውስጥ የ"GMO" ጉዳትን የሚያጠኑ ተመራማሪዎች ከስራ ገበታቸው እንዲባረሩ እና ማስፈራርያ ሳይቀር እንዲደርስባቸው ይደረጋል!

ከጀርባ ማን አለ?
አሜሪካዊው ባለ ፀጋ "Bill Gates" "Bill and Malinda Gates Foundation"ንን በመጠቀም "AGRA" ለሚባል መቀመጫውን ኬንያ አድርጎ ግብርና ላይ ለሚሰራ ዓለም አቀፍ ተቋም በየአመቱ ከግማሽ ቢልዮን ዶላር በላይ በመስጠት 11 የአፍሪካ ሃገራት "GMO"ን እንዲቀበሉ ጫና በማድረግ ላይ ነው! (ከነዚህ ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት!)
የምግብ እጥረትን እና ረሃብን ማጥፊያው ዋነኛ መንገድ "GMO"ን መጠቀም ነው ብሎ የሚያምነው "Bill Gates" ቅድም ከጠቀስናቸው ግዙፎቹ የአሜሪካ "Bio Tech" ኩባንያዎች ዋነኛው የሆነው "Monsanto" ውስጥ ከፍተኛ ሼር አለው!
የእማማ ኢትዮጵያ ሁኔታ!
ከሁሉም የአፍሪካ ሃገራት በበለጠ "GMO"ን እንድትቀበል ከፍተኛ ጫና የሚደርሰው ኢትዮጵያ ላይ ነው!
"...እያንዳንዱን የአፍሪካ ሃገር ለማሳመን ግዜ ከማባከን ኢትዮጲያ እንደ አፍሪካ መግቢያ በር ስለምትቆጠር የሆነ ነገር ይዘህ ስትመጣ መጀመርያ ኢትዮጵያን አሳምን! እምቢ ካለችም ደግሞ ከባድ ጫና አድርስባት!..." የሚል ፍልስፍና ምዕራባዊያኖቹ አላቸው! ኢትዮጵያ ለረጅም ግዜ በአቋማ ፀንታ ብትቆይም መጨረሻ ላይ ግን የ "Bio Safety" ህጓን እ.ኤ.አ 2015 ላይ አሻሽላ ሁለት የጥጥ ዝርያዎች ላይ የህንድ ባለሃብቶች "GMO"ን እንዲተገብሩ ፈቅዳለች። ከጥጥ በተጨማሪ በቆሎ እና እንሰት ላይ ደግሞ ለአምስት አመታት ጥናት እንዲደረግ እና አዋጭ ከሆነ እንዲፈቀድ ወስናለች!
"Guess what? ጌታዬ!" ኢትዮጵያ ይህንን ውሳኔ እንዳስተላለፈች በደስታ መግለጫ ያወጣው "United States Department of Agriculture (USDA)" ነው።
ማጠቃለያ!
ኢትዮጵያ በእርዳታም ሆነ በግዢ የምታስገባቸው ብዙ የምግብ ምርቶች አሉ። ለምሳሌ ለዘይት ምርት ግብአትነት የሚውለው አኩሪአተር በአብዛኛው "GMO" ነው። ስለዚህ በእርዳታም ሆነ በግዢ መልክ የምናስገባቸውን ዘይቶች አስባቸው! እሱን ብቻ ሳይሆን ሩዝ እና ሌሎች የታሸጉ ከውጪ የሚገቡ ምርቶች "GMO" የመሆን እድላቸው ሰፊ ነው! ሌላው ችግር ደግሞ ከውጪ የምናስገባቸው ምግብ ነክ ምርቶች "GMO" ይሁኑ አይሁኑ የሚያጣራ እና የሚቆጣጠር አካል የለንም። ቢኖርም ይህንን የመለየት አቅም ያላቸው ባለሙያዎችም ሆነ አስፈላጊው ቴክኖሎጂ የለንም። ቢኖረንም እነዚህ ምርቶች ላይ በአብዛኛው "GMO" ወይም "Non GMO" የሚል የመለያ ፅሁፍ አይገኝም!
ጌታዬ! አንድ ተመራማሪ ምን ይላል!....".... ስለማይወራ እንጂ የምግብ ኢንደስትሪው ከትንባሆ ኢንደስትሪው በላይ ገዳይ ነው! ጥቂት ባለሃብቶች እና ሃገራት ኪሳቸውን ለመሙላት ሲሉ የምንበላውን ሳይቀር እስከመዘወር ደርሰዋል! ስለምትበላው ምግብ ምንነት የማወቅ መብት እንኳን የለህም! ከጥቂት አመታት በኃላ ተፈጥሮአዊ(Organic) የሆነ ምግብን ማግኘት ብርቅ የሚሆንበት ግዜ ይመጣል! አስከፊው ገፅታ ደግሞ በዚህ አካሄዳቸው በምግብ የሰው ልጅን "Genetics" እስከመቀየር ሊደርሱ ይችላሉ!የምንበላቸው ዶሮዎች፣ በጎች እና ፍየሎች የሚመገቡት በ "GMO" የበቀሉ ሰብሎችን ነው! የምንጠጣው ወተት "GMO" ከሚበሉ ላሞች የሚገኝ ሆኗል! በምንም መልኩ እንዳናመልጥ አድርገውናል!...."
ለማንኛውም ቶሎ "organic" "organic" የሆነውን ነገር ብሉ!
መልካም ምሽት! ፀዴ "Organic" የሆነች ቅዳሜን አሳልፉ!

የቅዳሜ ቀደዳ 18(፲፰)
እንዴት ነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? ቅዳሜን ተከስተናል! እንደተለመደው ዘና፣ ፈካ፣ ፀዳ እናድርጋት!
.
.
.
የአንዲት ሃገር ህልውና ባላት የደህንነት ተቋም ጥንካሬ ይወሰናል ይባላል! የፈለገ ሃብታም ብትሆን፣ እንዳሻህ ብታድግ እና ሰላም ወዳድ ህዝብ ቢኖርህ እንኳን ሌት ተቀን ስላንተ ውድቀት የሚሰሩ፣ ሁሌም ጉድጓድህን የሚቆፍሩልህ እና የተዘናጋህበትን አጋጣሚ ጠብቀው የሚያጠቁህ ብዙ ጠላት ሃገራት ይኖራሉ። አንዳንዴ የተለያዩ ሃገራት ውስጥ ያሉ የደህንነት ተቋማት በቋታቸው የያዙት መረጃ ምን እንደሚመስል ለማየት ጓጉተህ አታውቅም? ለማንበብ አትቋምጥም?
ቆይ አንዴ ከዛ በፊት!
"CIA(Central Intelligence Agency)" የአሜሪካ ወሳኝ የደህንነት ተቋም ነው! የተቋቋመው እ.ኤ.አ 1947 ሲሆን የተቋሙ ዋነኛ አላማ የተለያዩ የዓለም ሃገራት ውስጥ እየተካሄዱ ያሉ ወቅታዊ መረጃዎችን በመሰብሰብ እና በመመርመር ለሃገሪቱ ፕሬዝዳንት እና ለአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ካውንስል ማቅረብ ነው። አሜሪካ ላይ ሊቃጡ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ መመርመር እና መከላከል የ "CIA" ቁልፍ ሃላፊነት ነው! ከዛ በተጨማሪ ተቋሙ የተለያዩ ሃገራት ላይ "Objective Analysis" ይሰራል! የ "CIA" አመታዊ በጀት እስከ 20 ቢልዮን ዶላር ይደርሳል! ይህ ብቻውን ኢትዮጵያ እንደ አጠቃላይ ለሃገሪቷ ከምትመድበው በጀት ይበልጣል አባዬ! "CIA" ምን ያህል ሰራተኞች እንዳሉት በውል ባይታወቅም ከ 22 ሺህ በላይ እንደሆኑ ይነገራል።
ተራ ሰው ዝም ብሎ "CIA"ን መቀላቀል አይችልም! ተቋሙን የሚቀላቀሉት እጅግ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው፣ የሰዎችን የሰውነት ቋንቋ(body language) በሚገባ የሚያውቁ፣ መረጃ የማወጣጣት ከፍተኛ ብቃት ያላቸው፣ በአደገኛ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፍ የሚችሉ፣ አካላዊ ብቃታቸው የተረጋገጠ፣ ከፍተኛ የመግባባት እና የማሳመን ችሎታ ያላቸው፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን መናገር የሚችሉ፣ የዓለማችን እጅግ አደገኛ የሚባሉ ቦታዎች ውስጥ ለመላክ ዝግጁ የሆኑ እና ከፍተኛ የሃገር ፍቅር ያላቸው ግለሰቦች መሆን ይጠበቅባቸዋል! ከምንም በላይ ደግሞ ስለ ስራቸው እና ማንነታቸው ማንም ማወቅ የለበትም!
አንድ "CIA" ውስጥ ይሰራ የነበረ ሰው እንዲህ ይላል!
"...እንደ "CIA" ሰራተኛነትህ ዓለምን የሚያድን ጀብድ ፈፅመህ ሊሆን ይችላል! ነገር ግን የፈፀምከውን ጀብድ ለማንም ትንፍሽ ማለት አትችልም!..."
ለማንኛውም የአሜሪካ ስለላ ፊልሞች ላይ እንደምናየው የ "CIA" ሰላዮች(ኦፊሰፎች) የማይሞቱ እና በየትኛውም ከባድ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ የሚችሉ አይደሉም። እስካሁን ድረስ ከ 200 ያላነሱ የ "CIA" ኤጀንቶች በተለያዩ ሃገራት ተልዕኮ ላይ እያሉ ሞተዋል። አሜሪካ ልዕለ ሃያልነቷን አስጠብቃ እንድትቆይ ካደረጉ ተቋማት መካከል አንደኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጠው ይህ ተቋም ነው! የሃገሪቱ ፕሬዝደንት እያንዳንዱ ውሳኔዎቹን የሚወስነው ከዚህ ተቋም በሚያገኘው መረጃ ነው! "...አሜሪካ የትኛውን ሃገር አጋር ታድርግ? ከየትኛው ሃገር ጋር ግንኙነቷን ታሻክር? ለማን አብዝታ እርዳታ ትስጥ? የትኞቹን የነፃነት ታጋዮች ታስታጥቅ? ..." የሚሉትን ውሳኔዎች ሳይቀር ፕሬዝዳንቱ የሚወስነው ከዚህ ተቋም ከሚያገኘው መረጃ ነው።
የሚገራርሙ ሃቆች አንድ!
እ.ኤ.አ 1960 ላይ "CIA" የራሽያን ሳተላይት ከጠፋር ላይ ሰርቆ በአንድ ለሊት ሳተላይቷን ፈታትቶ ከመረመረ በኃላ ራሽያ ሳታውቅ በንጋታው ሳተላይቷ ወደነበረችበት ቦታ እንድትመለስ ያደረገ ተቋም ነው! ጌታዬ! ሰማይ ላይ ሳተላይት ስትሰራረቅ ማሰብ ነው እንግዲህ!
የሚገራርሙ ሃቆች ሁለት!
"CIA" ድመቶችን በመጠቀም ሳይቀር ለመሰለል የሞከረ ጉደኛ ተቋም ነው። "Acoustic Kitty" የሚል ስያሜ የነበረው ይህ ፕሮጀክት በአንድ ወቅት ከ 20 ሚልዮን ዶላር በላይ ተመድቦለት ድመቶችን በማሰልጠን እና ጆሮዋቸው ውስጥ "Microphone" በመትከል ወደሚፈልጉት ሰው ጋር ድመቶቹን ልከው የተጠርጣሪዎችን ንግግር እንዲቀዱ እስከመወጠን ደርሰዋል። የሚያሳዝነው ገና የመጀመርያዋ ድመት አስፖልት ስታቋርጥ መኪና ገጭቷት ስለሞተች ሙከራው ቀርቷል! ነገር ግን በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት "CIA" ብዙ ሺህ እርግቦች ላይ ካሜራዎችን በመትከል ራሽያን ሲሰልል እንደነበር እራሱ ተቋሙ ያምናል!
የሚገራርሙ ሃቆች ሶስት!
"CIA" የኩባ ፕሬዝደንት የነበሩትን "Fidel Castro"ን ለማስገደል ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም! ከሁሉም የሚያዝናናው ሰውየው ሲጋራ ወዳጅ ስለነበሩ ሲጋራቸው ውስጥ ፈንጂን ከትቶ ለመግደል እስከመሞከር መድረሳቸው ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን እ.ኤ.አ 1962 ላይ የቀድሞው የነፃነት ታጋይ እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት "Nelson Mandela" የሚገኑበትን ቦታ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት ጠቁሞ ያስያዛቸው "CIA" ነው! ከዛም እንደሚታወቀው ለ 27 ዓመታት እስር ማንዴላ ተዳርገዋል!
የሚገራርሙ ሃቆች አራት!
በአንድ ወቅት ራሽያ "Serbia" ውስጥ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ እየገነባች ነበር። የነዳጅ ማስተላለፊያው ግንባታ አልቆ ጥቅም ላይ እንዲውል ራሽያ የሚያስፈልጋት አንድ "Software" ነበር! በወቅቱ ይህ "Software" ያላት ሃገር ደግሞ አሜሪካ ነበረችና የራሽያው ስለላ ተቋም "KGB" አሜሪካ ይህንን "Software" እንድትሸጥላት "CIA"ን ይጠይቃል! አሜሪካ ግን አሻፈረኝ አለች! በመጨረሻም "KGB" የ "CIA" ማህደር ውስጥ ገብቶ ይህንን "Software" ይሰርቃል! ነገር ግን "CIA" ይህንን ቀድሞ ስለገመተ የ "Software"ሩን ኮዶች አሳስቶ ነበር ያስቀመጣቸው! ጌታዬ! "KGB" አገኘሁ ብሎ ኮዶቹን ሲጠቀመ የነዳጅ ማስተላለፊው ቱቦው ሙሉ በሙሉ ፈንድቷል!
የ"CIA" ሰላዮች ለተለያዩ አላማዎች ወደተለያዩ ሃገራት ይላካሉ! ለምሳሌ የተለያዩ የአሜሪካ እርዳታ ድርጅቶች፣ ት/ቤቶች እና ቆንፅላዎች ውስጥ ማንም ሳያውቅ የ "CIA" ሰላዮች ስራቸውን ይሰራሉ! እንዳንዴ ግብዳ የጀርባ ቦርሳ እና ካሜራ ተሸክሞ ተራራ ለተራራ "Camp" እያደረገ ፎቶ የሚነሳው አሜሪካዊ ሁሉ ቱሪስት እንዳይመስልህ ጌታዬ!
አንዳንድ ወቀሳዎች!
CIA" ምርመራ በሚያደርግበት ወቅት ተጠርጣሪዎችን ክፉኛ "torture" ያደርጋል ይባላል! እነሱ ቃሉን ሲያሳምሩት "Enhanced Interrogation technique" ይሉታል! ይህ ድርጊት እየተባባሰ የመጣው አሜሪካ ላይ የ 9/11 ጥቃት ከተፈፀመ በኃላ እና "CIA" መረጃዎችን በሚገባ ሳይሰበስብ ቀርቷል ተብሎ ከተወቀሰ በኃላ ነው! ከ 9/11 ጥቃት ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ግለሰቦችን በመያዝ ወዳጅ ሃገራት ላይ በድብቅ ባስገነቧቸው ጭለማ እስር ቤቶች ውስጥ እነዚህ ግለሰቦች ላይ በዓለማችን የጭካኔ የመጨረሻ ጥግ የሚባለውን ምርመራ(Interrogation) ያደርጉባቸዋል! ይህንን ደግሞ እራሱ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት "George W. Bush" ዳር ዳር እያለ አምኗል!

ወደ ዋናው ጉዳይ ላምጣህ!
የ "CIA" ትክክለኛው ገፅ ላይ ሄደህ ወደ ታች ስትወርድ "Freedom of Information Act(FOIA)" የሚል ነገር ታገኛለህ! ስትጫነው የመፈለጊያ ወይም "Search" ማድረጊያ አማራጭ ይመጣል። እዛ ላይ የፈለከውን ነገር ማግኘት ትችላለህ! "CIA" ወደ 12 ሚልዮን የሚጠጉ ድብቅ(classified) ዶክመንቶችን "Declassify (ይፋ)" አድርጓል! "CIA" እነዚህን ዶክመንቶች የለቀቀው ጊዜያቸው ስላለፈ እና አሁን ላይ እነዚህን መረጃዎች ደብቆ ማቆየቱ እንብዛም ጥቅም የለውም ተብሎ ስለታመነበት ነው!
ድህረ ገፁ ላይ ሄጄ "Ethiopia" ብዬ ስፅፍ ወደ 3500 የሚጠጉ ኢትዮጵያን በተመለከተ "CIA" የሰበሰባቸውን በወቅቱ ድብቅ የነበሩ መረጃዎች አግንቼ ይሄንን ሳምንት ስኮሞኩም ነበር የኔ ጌታ! አብዛኛዎቹ መረጃዎች በሃይለ ስላሴ የመጨረሻ አመታት እና በደርግ የስልጣን ዘመን ወቅት የተሰበሰቡ እና (predictive Analysis) የተሰራባቸው ናቸው!
አባዬ! አብጠርጥረው አይደል እንዴ የሚያውቁን?
"February, 26,1975" ላይ የተፃፈ!
እ.ኤ.አ 1974 ላይ የጀነራል አማን አንዶም ግድያ የፈጠረው ቀውስ ፣ ኤርትራ ከኢትዮጵያ የምትገነጠል ከሆነ ለማደግ የምትቸገር ትንጥዬ የአፍሪካ ሃገር እንደምትሆን፣ ከአጠቅላይ የሃገሪቷ መሬት 3% ብቻ የሚሆነው በግብርና እንደለማ፣ ኤርትራ ኢኮኖሚዋን ሊደግፍ የሚችለው የ"livestock" ሃብት እንደሆነ እና ከዚህ ውጪ በእርዳታ ለረጅም አመታት እንደምትቆይ፤ በተቃራኒው ኤርትራ የምትገነጠል ከሆነ ኢትዮጵያ በይበልጥ ከዓለም የተገለለች ሃገር እንደምትሆን፣ ህዝቦቿ ዘመናዊነት እንደሚጎላቸው፣ እንብዛም የተፈጥሮ ሃብት እንደሌላት፣ ወደብ አልባ ሃገር እንደምትሆን እና ጅቡቲ ላይ ጥገኛ እንደምትሆን ያትታል! ስለ ምፅዋ እና አሰብ የወደፊት እጣ ፈንታ ሳይቀር በሰፊው ይተነትናል!
"የመንግስቱ ሃይለማርያም እና የራሽያ ግንኙነት (August,1984)" እንደፃፉት!
ከ 1974ቱ አብዮት በኃላ መንግስቱ ሃይለማርያም ስልጣንን ጠቅልሎ በእርሱ ስር ማድረጉን እንደቀጠለበት፣ በዚህ ሁኔታ በትንሹ ሃገሪቱን ለቀጣይ ሁለት አስርት አመታት ቢያንስ ሊመራ እንደሚችል ነገር ግን ብዙ የግድያ ሙከራዎች እንደሚያጋጥሙት፣ የስልጣን ማብቂያው ምናልባት በግድያ ወይ በመፈንቅለ መንግስት ሊሆን እንደሚችል፣ የራሽያ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት መንግስቱ በስልጣን እስካለ ድረስ ሊዘልቅ እንደሚችል፣ ኢትዮጵያ ራሽያን የምትፈልጋት በሃገሪቱ በሰሜኑ ክፍል ያሉ ነፃ አውጪ ግንባሮችን ለመዋጋት የሚያስችላትን መሳርያ እንድትረዳት እንደሆነ፣ ራሽያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የምትፈልገው ህንድ ውቅያኖስ ላይ ያላትን የባህር ሃይል ለማጠናከር እና የአፍሪካ ቀንድ ለ "Middle East" ቅርብ በመሆኑ እንደሆነ እና ራሽያ ኢትዮጵያን በመርዳት ደሃ ሃገራት ከራሽያ ጋር ሲወዳጁ የሚያገኙት ጥቅም ብዙ እንደሆነ እንደማሳያነት ልትጠቀምባት እንደምትፈልግ፣ ራሽያ ኢትዮጵያን ጓድ መንግስቱ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ ወደ 3 ቢልዮን ዶላር የሚገመት የጦር መሳርያ እንደረዳቻት፣ 1700 የሚሆኑ ራሽያዊያን የጦር አማካሪዎች አዲስ አበባ እንዳሉ ጭምር ይናገራል! ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ እና የኢትዮጵያን ግንኙነት መንግስቱ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ እንደማይሻሻል እና መንግስቱ አሜሪካ "TPLF"፣ ሱዳን እና ሶማልያን" ትረዳለች ብሎ ስለሚያስብ በአይነ ቁራኛ እንደሚመለከታት ይናገራል! በአጠቃላይ በወቅቱ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንደተዳከመ፣ ሰሜን ላይ ያለው ወደ 100 ሺህ የሚቆጠር የኢትዮጵያ ጦር ነፃ አውጪዎቹ "TPLF" እና "EPLF"ን ለምን ማሸነፍ እንደከበደው በሰፊው ይተነትናል። ራሽያ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ልክ እንደሷ እንዲሆን የተለያዩ አማካሪዎችን በእያንዳንዱ የሃገረቱ ቢሮዎች በማስቀመጥ "Shape" እንደምታደርግ፣ ስለ ኦጋዴን ጦርነት፣ ስለ ደርግ ምስረታ፣ ስለ ደርግ የመሬት ፖሊሲ፣ "ግብፅ፣ ሱዳን እና ሳውዲ አረብያ" ራሽያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት እያደገ የመጣ ግንኙነት እንዳሳሰባቸው፣ ስለ የኢትዮጵያ እና የኩባ ግንኙነት፣ ስለ መንግስቱ እና ካስትሮ ወዳጅነት፣ በወቅቱ ኢትዮጵያ ከሊብያ ጋር ስለነበራት አጋርነት፣ ወደ 13 ሺህ የሚጠጉ የኩባ ወታደሮች ኦጋዴን እና ሶማልያ ድንበር ላይ እንደከተሙ እና ኩባ ኢትዮጵያን በጤና፣ በግብርና፣ በጦር መሳርያ እየረዳቻት እንደሆነ፣ በየአመቱም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ኩባ ለትምህርት እየሄዱ እንደሆነ እና ያኔ አለማያ(አሁን ሃሮማያ)፣ ጅግጅጋ እና ድሬዳዋ የሰፈሩት የኩባ የጦር ካምፖች ምን እንደሚሰሩ በሰፊው ይናገራል!
"እ.ኤ.አ 1986" ላይ የተፃፈ!
"አንድ የ "CIA" ኦፊሰር በኢትዮጵያ መንግስት እንደተያዘ፣ ለሁለት ወራት ያህል "torture" እንደተደረገ፣ ለ 35 ቀናት ገላውን እንኳን መታጠብ እንዳልቻለ እና በደርግ መርማሪዎች ከፍተኛ ስቃይ ሲደርስበት የ "CIA" ኦፊሰር እንደሆነ ማመኑን ይናገራል። በመጨረሻም በወቅቱ የአሜሪካ አምባሳደር መንግስቱ ሃይለማርያምን አግኝተው ካግባቧቸው በኃላ ሰውየው ከ 35 ቀናት እስር በኃላ እንደተፈታ እና በውጪ መንግሥት የ "CIA" ሰራተኛ ላይ ከደረሱ አሰቃቂ ተግባራት መካከል አንዱ ይህ እንደሆነ ያትታል!
እ.ኤ.አ 1971 ላይ "Geographic brief on Ethiopia" በሚል ርዕስ "CIA" ባወጣው ሚስጥራዊ የ 55 ገፅ ፅሁፍ ላይ ስለ ታሪካችን፣ ኢትዮጵያ የ "California"ን ሶስት እጥፍ እንደምታክል፣ የህዝብ ቁጥሯም ወደ 24 ሚልዮን እንደሚገመት ያወራል። ስለ ቋንቋችን፣ ስለ ባህላችን፣ ስለ መልከአ ምድራችን፣ የት የት ቦታ የተፈጥሮ ሃብት እንዳለን፣ የትኛው ቦታ ለግብርና ምቹ እንደሆነ፣ ስለ ሰዓት እና ግዜ አቆጣጠራችን፣ ሚንልክ እንዴት የአሁኒቷን ኢትዮጵያ እንደመሰረተ፣ ስለ እያንዳንዳችን የዘር ግንድ አመጣጥ፣ የብሄር ፖለቲካ፣ የትኛው ብሄር ከየትኛው ብሄር ጋር ከፍተኛ ቁርኝት እንዳለው፣ የሃገሪቱ ስጋት ምን እንደሆነ፣ ምን እንደሚያጋጥመን፣ ለወደፊት ምን ሊፈጠር እንደሚችል... ብቻ ምን አለፋህ በወቅቱ ኢትዮጵያ ምን ትመስል እንደነበር እና ምን አይነት እጣ ፈንታ ሊኖራት እንደሚችል ቁልጭ አድርጎ ያስቀምጥልሃል!
ግዜ ካለህ ገብተህ እየው! ጥሩነቱ እያንዳንዱ ዶክመንት "PDF" ስለሆነ አውርደህ መኮምኮም ትችላለህ! እርግጠኛ ነኝ ብዙ ጉድ ታገኝበታለህ! ከዛ በላይ እያብሰለሰልኩ ያለሁት አሁን ላይ እየሰሩብን ያለውን "predictive Analysis" ማግኘት አለመቻላችን ነው!
ለማንኛውም መልካም ምሽት! ፈታ ብላችሁ አምሹ!
ከወንድዬ እንግዳ
(የቅዳሜ ፅሁፍ ለእሁድስ ምን ይለናል😍)