Telegram Web Link
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_16

...🖊ኪሩቤልና ቅዱስ በሩን ቢያንኳኩም ሀና ግን ለመክፈት
ፍቃደኛ አልነበረችም እንዲያውም ፖሊስ ሳልጠራ ሂዱ
እያለች መጮህ ጀመረች ይሄኔ ቅዱስ ኪሩቤልን
እንደምንም አሳምኖትና ተመልሰው ስትረጋጋ
እንደሚመጡ ነግሮት ይዞት ሄደ ኪሩቤል በጣም ነበር
ያዘነው ... በ3ኛው ቀን ኪሩቤል ለብቻው መጣና ሀና
ሳታየው ወደ ፀጉር ቤቷ ገባ ይሄኔ ሀና ድንገት ስትዞር
ኪሩቤል ገብቶ በሩን ሲዘጋው ተመለከተች ኪሩቤልም
ስታየው ትጮሃለች ብሎ ስለፈራ "እባክሽ ሀና አንዴ
ስሚኝ ከዛ እሄድልሻለው ግን አዳምጪኝ ወደ ጀርመን
ልመለስ ጥቂት ቀን ነው የቀረኝ ሁለት ወር ሙሉ
ፈልጌሻለሁ ግን አጣሁሽ ስልክሽንም አጥፍተሽዋል ቅዱስ
ነው ንፅህናሽን የነገረኝ በድርጊቱ በጣም ተፀፅቷል..."
ሲል ንግግሩን አቋርጣ...
"የሱ መፀፀት ምን ይጠቅመኛል? የትኛውን የተበላሸ
ማንነቴን ያቃናዋል? የትኛውን ሀጥያትና ጥፋቴን
ያርምልኛል? ንገረኝ ከየትኛው የህሊና ቁስል
ይፈውሰኛል ?..." ሀና እንባ እየተናነቃት ንግግሯን እንኳ
መቋጨት አቅቷት ጭንቅላቷን ይዛ እናቱን እንደቀበረ ሰው
ተንሰቅስቃ አለቀሰች ... ሀና የእውነትም በቫይረሱ
ከመያዝ ጀምሮ ከአባቷ ጋር እስከማደር ያደረሳት በቅዱስ
ጥፋት ተስፋ በመቁረጧ ነው!
ኪሩቤልም እንባውን መንታ መንታ እያዘነበ "እባክሽ ይቅር
በይኝ ያኔ ያየሁትን ማመን አልነበረብኝም ካንደበትሽ
መስማት ነበረብኝ ..." አለ ፀፀትና ቁጭት እየታገለው
ሀናም ለደቂቃዎች ዝምታን ከመረጠች ቡሃላ እራሷን
በራሷ ሁሌም እንደምታረገው እያረጋጋች "ኪሩ ምንም
ጥፋት የለብህም የኔ እድልና እጣ ፈንታ የተፃፈው በዚ
መልኩ ስለሆነ ነው... እናም እስካሁን ከማውቃቸው
ወደፊትም ከምተዋወቃቸው ሁሉ በልቤ ትልቅ ስፍራ
ያለህ ብቸኛ ሰው ነህ! አንተን መጥላትም መቀየምም ለኔ
ሀጥያት ይመስለኛል እና ግን ኪሩ በቃ ሂድ ዳግም እኔጋር
እንዳትመጣ!!..." ይህን ስትናገር ሀዘኗን ለመሸሸግ
እየሞከረች እንደነበር ፊቷ ላይ በደንብ
ይነበባል...ኪርቤልም በአባባሏ ግራ እየተጋባ "የኔ ውድ
በጣም አፈቅርሻለሁኮ ያላንቺ ሁሉም ነገር አስጠልቶኛል
እባክሽ አትግፊኝ" አለ ሀናም አፈቅርሻለሁ የምትለዋን
ቃል ስትሰማ ልቧ ምቱ የጨመረ መሰላት ግን ቀጥ ብላ
ልታየው አልደፈረችም አይኖቹን ስታይ ያኔ ድሮ ልጅ ሆና
ያሳለፈችው የታፈነ ፍቅር ይመጣባታል...
ሀና ኪሩቤልን በቆሸሸው ማንነቷ መቀበል አልፈለገችም
ያሳለፈችውን ታሪክ ደግሞ ብትነግረው እንደሚጠላት
አልፎም እንደሚጎዳ ታውቃለች ለዚም ሀና የሷን ፍቅር
አፍና እሱ ተስፋ ቆርጦ ወደ ጀርመን እንዲሄድ ብዙ
ደከመች ነገር ግን ኪሩቤል ከሷ ውጪ ፈፅሞ ማፍቀርም
ማግባትም እንደማይፈልግ አስረግጦ ነገራት።
ስለዚህ የነበራት አማራጭ ያሳለፈችውን ሳትደብቅ
መንገር ይህን ለማድረግም አቅም እንዲሆናት እቤቷ
እራት ጋብዛው መጠጥ መጠጣት ጀመረች "ሆድ
ያባውን..." አይደል አባባሉ... ያን አስባ ነበር መጠጣቷ
ግን ያሰበችው ሳይሆን እንዲሆን የማትፈልገው ነገር
ተከሰተ ሀናና ኪሩቤል ያለጥንቃቄ አብረው አደሩ...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_አስራ_ሰባትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90

━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_17

...🖊ሀና ከኪሩቤል ጋር ማደሯ እጅግ በጣም ነበር
ያስደነገጣት ፈፅሞ ይህ እንዲፈጠር አልፈለገችም ነበር
በዚም ምክንያት ጧት ላይ ቀድሟት ነቅቶ ቁርስ እየሰራ
ስታየው እራሷን አንቃ ብትገል ደስ ባላት ነበር ኪሩቤልን
እንደገደለችው ተሰማት። አሁን አብረው አድረዋል ይህም
ማለት ወደ ጀርመን የመመለስ እድል አይኖረውም ይህ
ደግሞ በሷ ምክንያት መሆኑ ህሊናዋን እረፍት አሳጣት
"ኪሩ እባክህ ይቅር በለኝ" አለች ከየት መጣ የማይባል
እምባ ጉንጯን አልፎ በቅጡ ያልተሸፈኑ ጡቶቿን
እያራሰ... "ያለፈው አልፏል ውዴ አትጨናነቂ ደግሞ
ሰክረሽ እንደምታፈቅሪኝ ነግረሽኛል ስለዚ ካፈቀርሽኝ ለኔ
በቂዬ ነው!" አለ በደስታ ፈገግ ብሎ ስስ ፀጉሮቿን
እያሻሸ... ሀና እንባዋ እየባሰ መጣ ኪሩቤልን ከማጣቷ
በላይ በሷ ምክንያት የሚጎዳው ጉዳት አሳሰባት...
ኪሩቤል ደረቱ ላይ ልጥፍ አርጓት እረጅም ሰአት
ቢቆይም ሀና ግን ልትናገረው የምትፈልገውን ነገር
ለማውጣት ከራሷ ጋር ሙግት ገጥማ ነበር ይሄኔ "ሀኒ"
አለ ኪሩቤል ፍርሃት ጭንቀትና እንባ በወረሱት አይኖቿ
ተመለከተችው "እባክሽ በመሃላችን ስለነበረው መራራቅና
ክፍተት እርሺ ከዛም ፍቅራችንን ብቻ እናዳምጥ ሀኒዬ
አይናችንን ባይናችን እንይ አሁኑኑ አግቢኝ!! ከዛ ከፈለግሽ
እዛ አወስድሻለው ካልፈለግሽ ደግሞ ሀገርሽ ላይ
እንደንግስት እንከባከብሻለሁ... " አለ በአይኖቹ
እየተማፀናት... ሀናም ይህን ስትሰማ ድሮ ቢሆን ምን
ያህል በደስታ እንደምትሰክር አሰበች አሁን ግን ባዶ ተስፋ
ሆነባት እናም ኪሩቤልን ከላይዋ ላይ ገፋ እያደረገች ...
"በቃህ ይሄ ሁላ ከንቱ ምኞት ነው ስለኔ ብዙ
የማታውቀው ጉድ አለ... አንተጋ ለመምጣት ፕሮሰስ
ጀምሬ ተስፋ በሰነኩበት ሰአት ቅዱስ የሚባል አውሬ
በደካማ ጎኔ ገብቶ ህይወቴን አመሰቃቀለው ከዛም ወደ
ሴተኛ አዳሪነቴ ተመለስኩ... ይህን ያረኩት ከሀገር
ለመውጣት በቂ ገንዘብ ስላልነበረኝ ላጠራቅም ነበር ግን
ፈጣሪ ያኔ ገና ቴዎድሮስ ልጅነቴን ሲነጥቀኝ እረስቶኝ
ነበርና (H I V )ኤች አይ ቪ በደምሽ ውስጥ አለ ተባልኩ
እናም ያንቺ እጣ ሴተኛ አዳሪነት ነው ብለው ፈረዱብኝ...
በቃ ወንዱን ሁሉ በተለይ ሀብታምና ባለስልጣን
እየመረጥኩ ስበቀል ኖርኩ ግን በስተመጨረሻ ወላጅ
አባቴ ፀጋዬ ገ/ማርያም አንሶላ ተጋፈፈኝ... " አለች ይህን
ስትናገር በስሜት ጮክ ብላ ነበር ሀናን ለሚሰማት ልብ
ወለድ ትረካ እንጂ እውነት የሷ ታሪክ አይመስልም ነበር
... ኪሩቤል ይህን ሁሉ ጉድ ሲሰማ እራሱን አለመሳቱ ምን
ያህል ጠንካራ እንደሆነ ያሳያል ... ሀና ንግግሯን ቀጠለች
"እሺ አሁን ይሄን ሁሉ ጉዴን ሰምተሃል በላ ዝም አትበል
እንደመጀመርያህ ያላንቺ አልኖርም... ምናምን በለኝ እ
ዝም አትበለኝ ኪሩ አሁንስ አግብተኸኝ መኖር
ትፈልጋለህ?" ኪሩቤል መቋቋም ተሳነው ምንም
ሳይመልስላት ወጥቶ ሄደ...
ኪሩቤል ከወጣ 2ወር ሆነው ስለሱ ምንም ሰምታ
አታውቅም ስልኩም ዝግ ነበር ሀና ስለኪሩቤል ብዙ
ትጨነቃለች ስለሱ ምንም ባለመስማቷ ደግሞ ጭንትቷን
እጥፍ አርጎባታል ይህ በንዲህ እንዳለ ሀና የወር አበባዋ
ቀረ ለዚህም በመጠራጠር ሆስፒታል ስትሄድ የ2 ወር
ነብሰ ጡር መሆኗን አረጋገጠች ከዚህ የባሰው ለሀና
ያስደነገጣት ነገር ግን ከኤች አይ ቪ ነፃ ነሽ መባሏ
ነበር... ይሄ ለሀና ተአምር ነበር... አላምን ብላ 3 ሀኪም
ቤት ሄደች ግን ለውጥ የለውም ሀና ነፃ ናት... ግን አሁን
እረፍዷል ኪሩቤል ጥሏት ሄዷል ይሄ ደግሞ ልጁን
እንዳትወልደው ያደርጋታል ምክንያቱም ሀና ያለ አባት ልጅ
ላታሳድግ ያለፈ ህይወቷ ያስገድዳታል...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_አስራ_ስምንትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90

━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_18

...🖊ሀና ልጇን ለማሶረድ መወሰን አቃታት ምክንያቱም
ያረገዘችው ከምታፈቅረው ሰው ከኪሩቤል ነው ግን
ኪሩቤል አድራሻውን በማጥፋቱ ልቶልደውም
አልፈለገችም በዚ ተጨንቃ ሳለ አንድ እለተ እሁድ ሀና
ፀጉር ቤቷን ከፍታ እያፀዳዳች ሳለ አንዲት ወጣትነት
ያለፋት እርጅና ግን ገና ያልያዛት በ30ዎቹ መጨረሻ ላይ
የምትገኝ ሴት ገርበብ ያለውን የፀጉር ቤት በር ገፋ
አድርጋ ገባች ሀናም እንደወትሮዋ ሁሉ ምን ልታዘዝ ልትል
ዞር ስትል ሁሌም ስትናፍቀው የኖረችውና ልታየው ግን
ድፍረት ያጣችው ሰው ፊቷ ቆሟል በዛች ቅፅበት
ለተመለከታት ስሜቷ ምን እንደነበር ለመግለፅ ቃል
አይኖረውም ነበር ... የሆነው ሆኖ ሀና ለጥቂት ሰከንድ
ከተመለከተቻት ቡሃላ እማ ብላ በቁሟ ተዘረረች ይሄኔ
የወንበሩ ጠርዝ ግንባሯን አግኝቷት ኖሮ በደም
ተለወሰች...
ሴትየዋ የሀና እናት አፀደ ነበረች በርግጥ የልጇን እዛ
መኖር በጭራሽ አታውቅም ነበር እዛ ቤት በምን አጋጣሚ
እንደገባችም እስካሁን ለእራሷ ለአፀደም እንቆቅልሽ ነው
አንዳንዴ ሰዎች ሲጠይቋት... "እኔ የገባሁት ለምን
እንደሆነ የፈጠረኝ አምላክ ነው የሚያውቀው ግን
ግን"... ትላለች አፀደ የኑሮ ፈተና ያጠወለገው ፊቷን
በእጇ ደገፍ እያረገች "ግን ግን ልጄ በህይወት መኖሯን
እንዳይ የቅዱስ ገብርኤል ፈቃድ ሆኖ ነው እያክለፈለፈ
የወሰደኝ ብዬ አላመሰግነውም ምክንያቱም ልጄን በኔ
ሰበብ ድንጋጤ ገሎብኝ ነበር..." ትልና አቀርቅራ
ታነባለች... ሀና ሳትነቃ 3ሳምንት ሆናት እናቷም
የምታውቃቸውን ታቦቶች ሁሉ እየጠራች በፀሎት ካጠገቧ
ሳትነቃነቅ ሰነበተች አንዳንዴ እዛው የሀና አልጋ አጠገብ
ተንበርክካ... "አምላክ ሆይ ልጄን አሳይተኽ ስታበቃ
አትንሳኝ እባክህ ከፈለክ ትንንሾቹን ውሰድ!!" ትላለች
ይሄኔ ቴድሮስ ከሰማ ታድያ ጦርነት ይከፍታል...
ሀና ነቃች ግን ነገሮችን ለማስታወስ ጊዜ ወስዶባት ቆይታ
ስታስታውስና እናቷን በድጋሚ ከጎኗ ስታይ ትኩስ እንባዋ
በተንጋለለችበት ጆሮዋ ውስጥ ሞላ ሀናም አንደበቷን
መጠቀም ስላቃታት እናቷን ይቅርታ ለመጠየቅ አቅም አታ
በአይኖቿ የእናቷን ልብ ለማኘኝት ተማፀነች እናቷ የሀናን
መንቃት ስታይ እልልታዋ ሀኪም ቤቱን አወከው አምላኳን
ለማመስገን ቃል አጣች ይሄን ያየ ሁሉ በአፀደና ልጇ
ሁኔታ ስሜቱ ያልተነካ የለም እናትና ልጅ ከልብ
ያስለቅሳሉ...
ቀናት አለፉ ሀና ከሀኪም ቤት ወታ እናቷ ቤት ናት እህትና
ወንድሟ አድገዋል ሀና ዳግም የተወለደች እስኪመስላት
ለመጀመርያ ግዜ በሚባል መልኩ ዛሬ የደስታ
ጭላንጭል ይታይባታል እናቷ በመገኘቷ ደስተኛ
ከመሆንዋ የተነሳ የት እንደነበረች ለመጠየቅ
አልፈለገችም!...
ቴድሮስና ሀና ሳይነጋገሩ 4 ወር አለፈ ሀናም ሀኪም ቤት
በነበረችበት ጊዜና በመታመሟ ምክንያት ስለፅንሱ ምንም
ሳትወስን የ6ወር ነብሰ ጡር ሆነች ግን ሀናን እንጂ የሀናን
እናት የልጁ አባት አመምኖር አላሳሰባትም ሀናም ከቀን
ወደቀን የኪሩቤል አለመመለስና የልጇ የወደፊት እጣ
ያስጨንቃት ጀመር በዚም ምክንያት ሀና ብዙ ቀን
ትታመማለች
አንድ ቀን ማለዳ ሀና የሀኪም ቤት ቀጠሮ ኖሯት ሄደች
... ይሄኔ ቤት የነበረው ቴድሮስ ብቻ ነበር ።... ይሄኔ በር
ተንኳኳ ቴወድሮስም በር ከፈተ ኪሩቤል ነበር በርግጥ
በአካል አያውቀውም እረስቶታል ኪሩቤል ግን ቴድሮስን
አረሳውም... ሀናን እንደፈለጋትና የልጇ አባት እንደሆነ
ሲነግረው ቴድሮስ ፊቱን አጨፍግጎ... "እስካሁን የት
ነበርክ ?" ሲል ጠየቀ ኪሩቤልም ነገር ሳያንዛዛ "ሀገር
ውስጥ አልነበርኩም!" አለ ቴድሮስ ግን "እዚ አትኖርም
ዳግም እንዳትመጣ" ሲል አስጠነቀቀው...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_አስራ_ዘጠኝን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90

━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━
💌
… ዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ወደድኩ… " በልብ ያለን ሰው መርሳት አይከብድም? …እንዲሁ መተውስ ቀላል ነው?" …መልሱን ለእኔ አትንገሪኝ… እራስሽን ጠይቂ እና እራስሽ መልሺው…💌

🎈 @monhappy 💌
🎉 @BINCJ90 💫
:)
ከቅርብ ጊዜ በፊት ነው…አዋ እርግጠኛ ነኝ በጣም ከቅርብ ጊዜ በፊት ነገሮች እንዲህ አልነበሩም…እኔም ብሆን እንዲህ አልነበርኩም…አሁን ላይ ከሚቀየሩት ነገሮች ጋር ተቀይራለው…በምትቀያየር ዓለም እየኖሩ ግን አለመቀይር ግን ይቻል ይሆን ?
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_19

...🖊ኪሩቤል አጠያይቆ ሀና መኖሯን እርግጠኛ የነበረ
ቢሆንም ቴድሮስ ግን በውሸት አሳምኖ እንደሌለች
ነግሮታል... ኪሩቤልም በማርፈዱ እያዘነ የሃናን እንጀራ
አባት ተሰናብቶ ሄደ... ከሰአታት ቡሃላ ሀና ተመለሰች
ለመውለድ አንድ ወር ቢቀራትም ሀና ግን ደስተኛ
አይደለችም ልጇን ገና ሳትወልደው ማክቤል ብላ
ትጠራዋለች ማክቤል ማለትም (በማልፈልገው ቦታ
የወለድኩት የምወደው ልጄ) ማለት ነው።
ሀና ቀኗ ደርሷል እናቷም በደስታ ልጇን ለማረስ የገንፎ
እና የአጥሚት እህል ቅቤ ቡላ... የቀራት የለም ሁሉን
አዘጋጅታለች ሀናም ኮንዶምንየም ቤቷን አከራይታ ጥሩ
ገንዘብ ታገኛለች ፀጉር ቤቷንም ቀጥራ ታሰራበታለች
ስለዚህ በገንዘብ ደረጃ ቤተሰብ አታስቸግርም... ይህ
በንዲህ እንዳለ አንድ ሀሙስ ቀን የሀና ታናሽ ወንድም
ወረቀት ይዞ መቶ ለሀና ሰጣት ሀናም በፍጥነት ገልጣ
ማንበብ ጀመረች ኪሩቤል ነው ...
"ሀኒ የእንጀራ አባትሽ ቴድሮስ እንድንገናኝ ስላልፈለገ
እንደሌለሽና ድጋሚ' ሀና አለች ?' ብዬ እንዳልመጣ
አስጠንቅቆኛል ታናሽ ወንድምሽ ነው መኖርሽን የነገረኝ
ሀኒዬ እኔ እንድርቅሽ ብለሽ ነው አይደል (ኤች አይ ቪ)
አለብኝ ብለሽ የዋሸሽኝ ? ግን ተመረመርኩ ውሸትሽን
እንደሆነ አረጋገጥኩ ያን ቀን ስሜታዊ ሆኜ ጥዬሽ
በመሄዴ ግን አፈርኩ እናም ይሄን ሁሉ ግዜ በፍቅርሽ
ስደሰት በመለያየታችን ስከፋና ሳዝን ቆየሁ ሀኒ አሁን ግን
አንድ የሚያረገንና ይቅር የሚያባብለን ልጅ በሆድሽ
ይዘሻል እናም የኔ ውድ ይቅር በይኝና ሽማግሌ ልኬ
ልውሰድሽ እንጋባና አዲስ ህይወት እንኑር ፍቀጂልኝና
ደስተኛ ላርግሽ... ያንቺው ኪሩ" ይላል...
ሀና አንብባ እስክትጨርስ እንባዋ ወረቀቱን ያጥበው ነበር
"ሁሌም ኪሩ ያለጥፋቱ ይቅርታ ይጠይቃል!" አለች
ለመንሳት እየጣረች አንብባ ጨርሳ ወንድሟን ጠርታ
ኪሩቤል ጋር እንዲወስዳት ስትጠይቀው ድንገት ቴድሮስ
መጣ ይሄኔ "የት ልትሄጂ ነው?" አለ ሀናም የውስጥ
ንዴቷ እየተፈታተናት አንተ በውሸት የለችም ብለህ
ያባረርከው የልጄ አባት ጋር አለች ቴድሮስም ዲቃላሽን
አርፈሽ ውለጂና አሳድጊ እንዲ ሆድሽ ተንገፍጥጦም
ወንድ ትመኛለሽ? አላት ፈገግ እንደማለት እያለ...
ሀና ንዴቷን መቆጣጠር አቃታት "ስማኝ ቴድሮስ አንተ
ማለት ልጅነቴን የነጠከኝ ክፉ ሰው ነህ እናቴ የበደልከኝን
በደሎች ብታውቅ ዝም የምትልህ ይመስልሃል ግን ምን
አይነት ክፋ ነህ እስቲ ዛሬንኳ አንደበትህን አርመው የህፃን
ገላ ለወሲብ ጥማትህ የተጠቀምክ አሳፋሪኮ ነህ..."
አለች ሀና ከንዴቷ ብዛት የምትናገረውን መምረጥም ማን
ካጠገቧ እንደነበር ማስተዋልም አልቻለችም ነበር ... ግን
ይሄ ዋጋ አስከፈላት እናቷ የሁለቱን ምልልስ ስሰማ
ስለነበር ደምግፊቷ ጨምሮ እራሷን ሳተች የእናቷን
መውደቅ ያየችው ልጅም እናቷን ለማዳን አምቡላንስ
ጠራች ሆኖም የሀና እናት የልጇን ልጅ ሳታይ ልጇንም
ሳትጠግባት እስከወዲያኛው አሸለበች ... የእናቷን ሞት
መቋቋም ያልቻለችው ሀናም እናቷ ቀብር ላይ እንኳ
ለመገኘት ሳትታደል ቀረች በድንጋጤ በመውደቋም
ያለቀኗ ለመውለድ ተገደደች...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_ሃያን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90

━━━
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_20

...?ሀና በእናቷ ሞት ማዘን ከሚገባት በላይ አዝናለች ልጇን
ያለቀኗ ብትወልደውም ጤነኛ ነበር የተወሰነ ቀን ማሞቅያ
ክፍል አቆይተው ለሀና ጡት እንድታጠባው ከጎኗ
አረጉላት ሀና ግን የማታውቀው ስሜት ልጇን
እንዲያስጠላት አርጓታል... "እውነት ዲቃላ ነህ? ማክቤል
ልጄ እውነት አባትህ አብሮን አይኖርም? ልጄ ይህን
አላደርግም እሺ!!! ያለአባት አታድግም!" ትላለች እንባዋን
መንታ መንታ እያዘነበች ልጇ የሚሰማት ይመስል ልጇ
ከጎኗ ከተኛ 3ቀን ሞላው ሀኪሞቹም መውጣት
እንደምትችል አበሰሯት ለሷ ግን እዛው ይሻላት ነበር ።
ምክንያቱም ስትወጣ የት እንደምትገባ አታውቅም አንድ
የእናቷ ጓደኛ የነበረች ሴት ብቻ ነበረች እየተመላለሰች
የምትጠይቃት ...
ሀና ምግብ አትበላም የእናቷ ጓደኛ ቤቲ ሁሌም ምግብና
አጥሚት ሰርታ ትወስድላታለች ሀና ግን ካጠገቧ ለተኙ
አራሶች ትሰጠው ነበር በዚህም ምክንያት ልጁ ከእናቱ
ጡት ማግኘት የሚገባውን አያገኝም ይሄኔ ልጁ ያለቅሳል
ሀናም አብራው ታለቅሳለች የሀና ሁኔታ ያሳሰባቸው
ዶክተሮች የስነ ልቦና ሀኪም እንደሚያስፈልጋት ያምናሉ
ግን ገና ሀሳቡን ሲያነሱላት ብላቹ ብላቹ እብድ አረጋቹኝ
ትልና ትጮሀለች... ሀና ከእለት ወደ እለት ሰውነቷ
እየከሳና እየተጎሳቆለባት ነው እሷም ስትወጣ ከሀኪም
ቤት እንድትገባበት ኮንዶምንየም ቤቷን የተከራዩትን ሰዎች
እንዲለቁ የእናቷን ጓደኛ ላከቻት ...
ከሀኪም ቤት የመውጫዋ ቀን ሀናና ልጇን እንቅልፍ
ሸለብ አርጓቸው ሳለ በድንገት አንድ ሰው በሩን ከፍቶ ገባ
ከአልጋው ጎንም ተንበርክኮ እናትና ልጁን እያየ ስቅስቅ
ብሎ ያለቅስ ጀመር ይሄኔ ሀና ነቃች ካጠገቧ ያለውን
ሰው ስታይ የሷ እንባ ባሰ አቅፋው... "ኪሩዬ እናቴ
ሞተችብኝ ብቻዬን ትታኝ ሄደች ኪሩዬ ... እኔ ነኝ ጥፋተኛ
እናቴ እንድትሞት መንስኤ እኔ ነኝ የምኖረው ለሷ ነበር
የልፋቷን ውጤት ሳታይ ሄደችብኝ..." ሀና ለቅሶዋንም
የቁጭትና ፀፀት ንግግሯንም ማቆም ተሳናት...
ኪሩቤልም እሷን ቀርቶ እራሱን ማፅናናት አቃተው
በልቡም እድለቢስነቷን አሰበ ተቃቅፈው ተላቀሱ ...
ከነርስ እስከ ታካሚ ያያት ሁሉ ለሀና አለቀሰ ...
ኪሩቤልም እንደምንም እራሱን ተቆጣጥሮ "አይዞሽ ውዴ
ይሄው የእናትሽን ምትክ አግኝተሻል አሁን አንቺ ራስሽ
እናት ነሽ የኔ ውድ ጠንከር በይልኝ።" አለ ትኩስ እንባው
ከሱ አልፎ ሀናን እያራሳት ...ሀናም ማልቀሷን ሳታቆም "
እኔኮ እድለቢስ ነኝ ህይወቴ በስቃይ የተሞላ መኖር
ልጀምር አንድ ስል ልክ እንደልጆች እቃቃ ይፈርስብኛል
እናቴን አግኝቻት ሳልጠግባትና ልጄን በአይኗ ሳታይ
ሞተችብኝ..." አለች ኪሩቤል ማፅናኛ ቃል አጣ በዚ
ቅፅበት ዶክተሩ መቶ ኪሩቤል የልጁ አባት መሆኑን
ካረጋገጠ ቡሃላ ለብቻው ጠርቶት ሀና ምግብ ካልበላች
ልጁ አደጋ ላይ እንዳለ አስጠነቀቀው!
ኪሩቤልም ሀናን ከሆስፒታል ይዟት ወቶ ወደራሱ ቤት
ወሰዳት ኪሩ መኪና ገዛህ? አለች ሀና ኪሩቤልም የሀና
መረጋጋት በደስታ እያቁነጠነጠው አዎ የኔ ፍቅር አለ ትንሽ
ተጉዘውም እጅግ በጣም የሚያምር ቪላ ቤት ደረሱ
ኪሩቤልም መኪናውን ወደግቢ አስገብቶ ሰራተኛዋን
እንድትረዳው በመጠየቅ ሀናን ከመኪናው አስወረዳት
ሰራተኛዋም በጥንቃቄ ልጁን አቅፋ ተያይዘው ገቡ ሀና
የቤቱን ውበት በአይኗ መሰከረች የልጇ ክፍል እጅግ
በጣም ያምር ነበር ቀጣይ የነሱ መኝታ ክፍል ስትገባ ምን
ያህል ተጨንቆ እንዳሰራው ያስታውቃል ሀና ስሜቷ ታወከ
ደስታ ይሁን ሀዘን የማታውቀው ስሜት እረበሻት ... የኔ
ንግስት አፈቅርሻለሁ አለና ተንበርክኮ ቀለበት አሰረላት
ሀና እንባ ባረገዙት አይኖቿ ጎንበስ ብላ ፊትለፊቷ
የተንበረከከውን ሰው አየች ይሄኔ እንባዎቿ ረገፉ
ኪሩቤልም ዳግም እንዳታለቅስና ምግብ
እንደምትበላለት ቃል አስገባት... ከዛ ቀን ጀምሮ ሀና
ሀዘኗን በልጇና በባሏ መርሳት ጀመረች ....
ሀና ወንድምና እህቷን ማየት ብትፈልግም ቴድሮስ ግን
ፍቃደኛ አይደለም ይሄኔ ሀና ቴድሮስ ላይ ዛተች አባቷንና
የእንጀራ አባቷን እንደምትበቀላቸው ለራሷ ቃል ገብታ ነበር
...
ከሁለት አመት ቡሃላ ሀና ፀጉር ቤቷ ስራ ጀምራለች ...
ቴድሮስ ታመመ ይሄንም ታናሽ ወንድሟ መቶ ነገራት
ሀናም የእህትና ወንድሟ አባት ነውና አላስችል ብሏት
ልትጠይቀው ሄደች ቴድሮስ ግን ታሞም መጥፎነቱ
አለቀቀውም ነበርና ልትገይኝ መጣሽ አላት ይህን ሲናገር
ወደኋላ መለሳት ያሁላ በደሉና የእናቷ ሞት ፊቷ ላይ
ተደቀኑ ይሄኔ ማስታገሻ መድሃኒቱን አንስታ ጣለችበት
መነሳት እንደማይችል ስለምታውቅ ሰውም እንዳይረዳው
መድሃኒትም እንዳያገኝ ስልኩን ወስዳበትና በሩን
ዘግታበት እህትና ወንድሟን ይዛ ሄደች ... እሱም በደከመ
ድምፁ ልጆቼን መልሽ መድሃኒቴን ... ይላል ድምፁ ግን
እንኳን ለጎረቤት አጠገቡም ለቆመ በቅጡ አይሰማም...
ቴድሮስ ቢሞት ግን ሀና ወንጀለኛ ትባል ይሆን???...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_ሃያ_አንድን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90

​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_21

...🖊ሀና ቴድሮስን የሞት አፋፍ ላይ ጥላው ያለምንም
ርህራሄ ወደ ቤትዋ ስትሄድ ኪሩቤል ልጇ ማክቤልን
እያጫወተው ደረሰች ሀና ከባልዋ ምንም አትደብቅም
እሱም ደግሞ አይኗን አይቶ አዲስ ነገር ካለ ያውቅባታል
... በዚም ሀና እህቷንና ወንድሟን ይዛ ስትገባ ኪሩቤል
ተነስቶ እየተጠጋት ... "ሀኒ ውዴ ቴዲ ደና ነው?" ብሎ
ጠየቀ ሀናም ባደረገችው ነገር ምንም የጥፋተኝነት
ስሜት ሳይሰማት "ኪሩ ቴድሮስን ወደሚስቱ እንዲሄድ
መንገድ አመቻችቼለት መጣሁ የእናቴ ብቸኝነት ስላሳሰበኝ
ከነክፋቱም ቢሆን ይሂድላት..." አለች ኪሩቤልም
ትከሻዋን በሁለት እጆቹ ይዞ "ይህን አንቺ አታደርጊም
ውዴ ገደልሽው??" ብሎ ጠየቃት የሱን ድንጋጤ ስታይ
ሀና ተርበተበተች ከዛም የሆነውን በቅደም ተከተል
ነገረችው ...
ኪሩቤልም "የኔ ፍቅር ቂምና በቀል እንዲሁም ጥላቻ
የሴጣን ነው! እስቲ አስተውይ ውዴ እህትና ወንድሞችሽን
እያቸው እሱኮ ለነሱ እጅግ በጣም ጥሩ አባታቸው ነው
ሲያድጉ ይህን ማድረግሽ ስህተት በመሆኑ ያዝኑብሻል!
በዛ ላይ አንቺ ከዚም በላይ ጥሩ ቦታ ቆመሽ አላማሽን
አሳክተሽና እንደምኞትሽ ጥሩ ገጣሚ ሆነሽ... በመድረክ
ላይ ትምህርት አዘልና አዝናኝ ግጥሞችሽን ስታቀርቢ
ህዝቡ በአድናቆት ሲያጨበጭብልሽ ሲያይ ያኔ እሱ
እራሱ ይሸነፍልሻል!! ቴድሮስን የሚቀጣው ጥንካሬሽና
ጉብዝናሽ እንጂ ጭካኔሽ አይደለም!"... አላት ሀና
ኪሩቤልን በስስት እያየችው እንባዋ መውረዱን እንኳ
አላስተዋለችም እሱም ቀና አድርጓት "ሂጂ እራስሽ
አድኝው እንዳታረፍጂ የኔ ልእልት" ...አለና እንባዋን ጠርጎ
ግንባሯን ሳም አረጋት አናም ወንድሟን ይዛ በፍጥነት
ወጣች ...
ሀና ስለኪሩቤል ስታስብ ካቅሟ በላይ ይሆንባታል
ኪሩቤል አክብሮቱና ለሷ ያለው ፍቅር ለራሷ ለሀና
ይገርማታል ሴተኛ አዳሪ እንደነበረች ቢያውቅም እንኳን
እሱ እሷን እንድትረሳው አድርጓታል ሀና ካሳለፈቻቸው
ችግሮችና እናቷን ከማጣቷ የተነሳ ነጭናጫና ቶሎ
የምትከፋ በዛ ላይ ቶሎ ተስፋ የምትቆርጥ አይነት ሴት
ናት ሆኖም ግን ይህን አመሏን ችሎ አንድም ቀን
እንዳይከፋት ይጥራል ለዚም ነው ልቧን ማሸነፍ የቻለው
እንኳን ጥሩ ምክሮቹ ቁጣው በራሱ ለሀና ትርጉም አለው
በቃ ታፈቅረዋለች ብል ቃሉ ያንሳል !!.... አንዳንዴ ፍቅር
የለም ሲባል ስሰማና የዘንድሮ ፍቅረኛሞች ሳይ
እውነትም ፍቅር የለም !! እላለው ከዛ ግን ኪሩቤልንና
ሀናን ሳይ ፍቅር ቦታ አጥቶ እንጂ በትክክል አለ ብዬ
እርግጠኛ እሆናለው...
ሀናና ወንድሟ በግዜ ደርሰው ቴድሮስን አዳኑት ኪሩቤል
ለቴድሮስ ማሳከምያ ሳይሰስት ነበር ገንዘቡን ያወጣው...
ቴድሮስ ድኖ ከሆስፒታል ሲወጣ በኪሩቤል ግፊት
ለ1ወር ሀና ቤቷ አስታመመችው ከዛም ሰራተኛ
ቀጥራለት ልጆቹን ይዞ ቤቱ ገባ ሀና ሁሌም ስታየው
ክፋቱን ታስታውሳለች ያሳለፈችው ስቃይ በጠቅላላ በሱ
ጭካኔ የተመሰረተ ነው ልጇን ሲስመው ብትከለክለው ደስ
ይላታል ምክንያቱም ያኔ በሆዷ እያለ ዲቃላ ብሎ
ሰድቦባት ስለነበር...
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሀና ከፀጉር ስራዋ በተጨማሪ
የግጥም ተሰጦዋን ለማዳበር ትምህርት ቤት ገብታ
መማር ጀመረች ...ብዙ ግጥሞችንም መፃፍ ጀመረች
በዚም ሀና የራሷ አስተማሪ የጥበብ ምሽት ላይ ስራዋን
እንድታቀርብ ጋበዛት ይህም የህይወቷ ትልቁ እርምጃ
ነበርና በደስታ እየቦረቀች ላባልዋ ልትነግረው ስትጣደፍ
ከልጇ ትምህርት ቤት ተደወለላት ማክቤል ታሟልና ቶሎ
ድረሽ ተባለች ሀናም የልጇ መታመም ከልክ በላይ
አስደንግጧት ባልዋ ለልደቷ በሰጣት ቪትስ መኪና
ስትበር ደረሰች...
ሀኪም ቤት ገብቶ ወላጅ አባቱ ደም እንዲሰጥ ታዘዘ
ይሄኔ ማመን የሚከብድ ጣጣ ገጠማት ኪሩቤል
የማክቤል ወላጅ አባት አይደለም ኪሩቤል ይህን ሲሰማ
ራሱን ሳተ...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_ሃያ_ሁለትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy || 📩 @BINCJ90

:)
በጣም ብዙ ነገሮች ትላንት የሆኑ ያህል ትዝ ይሉኛል…አንዳንዴ ልክ እንደ ህፃን ልጅ እፈራለው…እማ አንቺን ያስከፉሽን ፈጣሪ ይቅር ይበላቸው እኔ ግን አልችልም…



(ጉንፋን🤒)

🖤 @monhappy 💙
@BINCJ90
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_22

...🖊ሀና ችግሮቿ አሁንም አለመቆማቸው ቢያበሳጫትም
የልጇ አባት ኪሩቤል መሆኑን ግን እርግጠኛ ነች። ነገር
ግን እንዴት ሀኪሞቹ አባቱ አይደለም አሉ? ይሄ
የማይታመን ነው ኩሩቤልም ልጇ ማክቤልም አሁን አልጋ
ላይ ናቸው ታመዋል ሁለቱም ደግሞ ለሀና የመኖሯ
ዋስትና ናቸው! ለዚም ሁለቱም በፍጥነት መዳን
አለባቸው ... ሀና እያለቀሰች "ኪሩ የልጄ አባት ነው
እባካቹ አስተውሉ ልጄን ወይ ባሌን ባጣ ዋጋ
ትከፍላላቹ!!" እያለች የሀኪም ቤቱን ቢሮ ባንድ እግሩ
አቆመችው ዶክተሩም በድጋሚ ለመመርመር ቃል
ገብቶላት ሀናን አረጋጋት እሷም ባልዋን ለማየት
ወደተኛበት ክፍል አመራች...
ኪሩቤል ነቅቷል ስታየው እንባዋን መቆጣጠር አቃታት የኔ
ፍቅር አለችና ከተኛበት አልጋ ስር በጉልበቷ ተንበርክካ
እጆቹን ያዝ አደረገች ኪሩቤል ግን እጁን አስለቅቋት ፊቱን
አዞረባት ይህን ማየት ለሀና ትልቅ ህመም ነው ኪሩቤል
ከነብዙ ጉድለቷ እብዝቶ አፍቅሯት ነበር ዛሬ ግን ኪሩቤል
አዝኖባታል ... ሀናም "የኔ ፍቅር በሞተችው እናቴ ስም
እምልልሃለው ማክቤል ያንተ ልጅ ነው የኔ ውድ እባክህ
እራስህን አረጋጋ !" አለች እሱም አይኑ እምባ አቅርሮ
መናገር ጀመረ "ውዴ አፈቅርሻለው ግን ማክቤልን
ነጠቅሽኝ ያለፈ ማንነትሽን ባውቅም ልጄ የኔ መስሎኝ
ነበር ግን አንቺ ጨካኝ ሴት ነሽና ለኔ ሳልሰስት
ለማፈቅርሽ ሰው እንኳ አራራሽም!" አለ ይህን ሲናገር
ለመጀመርያ ግዜ ተስፋ መቁረጥ ይነበብበታል... ይህን
እይተባባሉ አንዲት ቀጠን ያለች ነርስ በሩን ከፍታ ገባች...
ሁለቱም በእንባ ታጅበው ወደነርሷ ተመለከቱ...
ነርሷም ረጋ ባለ አነጋገር "ይቅርታ የማክቤል ወላጆች
በተሳሳተ መረጃ ነበር የኪሩቤልና የህፃን ማክቤል ደም
ያልተመሳሰለው ለዚም ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን አሁን
ልጃቹ በሙሉ ጤንነት ላይ ስለሚገኝ ወላጆቹ እንዲያዩት
ይፈልጋል!" አለች ኪሩቤል ከተኛበት ተፈናጥሮ ተነሳ ያ
ተስፋ የቆረጠውና መነሳት አቅቶት በሆስፒታል አልጋ
የተኛው ሰው አሁን ሙሉ ጤነኛ ነው እንዳዲስ የተወለደ
መሰለው ሀናን አቀፋት ተቃቅፈው ተላቀሱ .... ኪሩቤል
ለልጁ ደም በመለገሱና ራሱስ ስቶ ስለነበር እንዲያርፍ
ቢነገረውም እሱ ግን ማንንም ሳይሰማ ልጁን ለማየት
ክፍሉን ለቆ ወደ ማክቤል ከሚስቱ ጋር ሄደ ...
ሀናም የግጥም መድብሎቿን ይዛ ልታቀርብ
ወደተጋበዘችበት ሆቴል ስትሄድ ኪሩቤል አብሯት ነበር
ከሰአታት ቡሃላ መድረክ መሪው ሀና ፀጋዬ እባክሽ ወደ
መድረክ አለ ሁሉም ሰው እሷን ለማየት የጓጓ ይመስላል
ሀና በፈገግታ ወደመድረክ ወጣች ሁሉም ሰው
በጭብጨባ ተቀበላት ሀና ልእልት መስላለች ኪሩቤልም
በስስት እያያት ግጥሟን ለማዳመጥ ህሊናውን ሰብሰብ
አደረገ ይሄኔ ሀና ድምፅ ማጉሊያውን ተቀብላ ...
# እማ...
እናቴ የት አለሽ ድምፅሽን አሰሚኝ
እስቲ ቀና ብለሽ ላፍታ ተመልከቺኝ
ያኔ ስትለፊልኝ ስትደክሚ ኖረሻል
እድሜሽን ሰውተሽ ህይወት ሆነሽኛል
ታድያ ቀና በያ ውጤቱ ደርሶልሻል
እማ ተመልከቺ ዘርሽ አፍርቶልሻል
ለከፈልሽው ዋጋ ክፍያ ይሁንሽ ብዬ
አንቺን ለማስደሰት ይሄው ዛሬ ደረስኩ
በሁለት እግሮቼ ተደላድዬ ቆምኩ
ግን አንቺ የለሽም
የዘራሽውን ዘር ቡቃያ አላየሽም
የልጅሽን ስኬት ለማየት አልታደልሽም...
ሀና ግጥሙን ሳትጨርስ እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት
አቆመችው ሁሉም ሰው በሀና ግጥም ስሜቱ ተነካ
ሁሉም ሰው እንባውን አዘነበው ይሄኔ ሀና ለመረጋጋት
ውጪ ወጣች ቴድሮስም ከየት መጣ ሳትለው " ሀና"
አላት ስታየው እንደመደንገጥ አለች "መድረክ ላይ ወጣሽ
ደስ ብሎኛል ግን አንድ ነገር እወቂ እጠላሻለሁ እናም
ስምሽን አጠፋዋለሁ ሴተኛ አዳሪ በነበርሽበት ወቅት
ከአባትሽ ጋር ስላደረግሽው ነገር አሶርቼ በሀፍረት
እራስሽን ታጠፊያለሽ!!!!" አላት ሀና የእንጀራ አባቷን
የእውነቷን ፈራችው "ይህን እንዳታደርግ" አለች ድምፅዋ
እየተቆራረጠ እሱም እሱን "እንዳላደርግ እብረሽኝ እደሪ"
አላት ሀናም በስሜት ንዴቷን መቆጣጠር እያቃታት በጥፊ
መታችው...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_ሃያ_ሶስትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy
📩 @BINCJ90
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_23

...🖊የእንጀራ አባቷ አብሯት ማደር መፈለጉ እንኳን ለሀና
ለሰሚም ይከብዳል ... ሀና በጥፊ ስትመታው ቴድሮስ
ከት ብሎ ሳቀ ይሄኔ ሀና በፍርሃት መንቀጥቀጥ ጀመረች
... ሁለቱ በዚ መልኩ ተፋጠው ሳለ ስታስበው ያብስራ
መጣ ባልጠበቀችው ጊዜና ቦታ መገኘቱ ለሀና ትንሽ ግራ
ቢገባትም ያብስራ ግን በእንባ ተሞልቶ "እህቴ ሀና ታውቂ
ነበር??"... ብሎ እንደ ህፃን ልጅ ጭምቅ አርጎ አቀፋት ...
ሀና ግን ሀሳቦቿ ትርምስምስ ስላሉ ያብስራ ያለውን
በስትክክል አልሰማችም ... ቴድሮስም "ኦ ያባቷ ልጅ
ካካካ..." ብሎ እሷን ለማናደድ የውሸት የሚመስል ሳ
ሳቀ ያብስራ ግን ነገራቸው ስላልገባው ንግግሩን ቀጠለ
"አዎ ሀናን ከልጅነቴ ጀምሮ ከልቤ እመኛት ነበር እውነት
ለመናገር እህቴ መሆኗን ሳላውቅ አፍቅሬአት ብዙ
ተሰቃይቼ ነበር ግን እሷ ምክንያቷን ሳላውቀው ሸሸችኝ
ግን አሁን ገባኝ ሀኒ እህቴ ናት ..." አለ ያብስራ ይህን
ሲናገር ኪሩቤልም ካጠገባቸው ይሰማ ነበር ...
ቴድሮስም ሀናን ቀና ብሎ እያየ "የልጄ ወንድም ስለሀናና
አባቷ ግንኙነት ታውቃለህ? ወይስ ልንገርህ ?" አለ
ኪሩቤል በቴድሮስ ንግግር ግራ ተጋባ እናም ኮስተር ብሎ
"ምን ለማለት ፈልገህ ነው?" አለው ሀና ግን ለማንም
ምንም መልስ አልሰጠችም! ኪሩቤል ሲመለከታት አንድ
ነገር እንዳለ አውቋል ግን ምን እንደሆነ አልገባው አለ ...
ቴድሮስም "ሀና አስቢበት እንገናኛለን!" ብሎ ሄደ
ሁለቱም ሀናን ተመለከቷት ሀና ተረብሻለች "ያብ ግን ማን
ጠራህ እዚ" አለችው እሱም ወደኪሩቤል እየተመለከተ
ጥሩ ባል ነው ያለሽ... እህቴ እንደሆንሽ አባቴ ከነገረኝ
ወዲ ስፈልግሽ ነበር!" ሲል ሀና አቋርጣው አባቴ?
ያውቀኛል እንዴ? አለች አይ ሀኒ አሁን አያውቅሽም
የልጅነትሽን ፎቶ ይዞት ስለነበር አሳየኝ እና እኔ አወኩሽ
አለና.. .ንግግሩን ቀጠለ ከዛ ትላንት ባለቤትሽን
አግኝቼው እዚ ዝግጅት ላይ ጋበዘኝ እናም..." አለና
ንግግሩን ሳይጨርስ እንባው አስቸግሮት ዝም አለ... ከዛ
"እሺ ያብዬ እንገናኛለን " ብላ ወንድሟ ያብስራን
ተሰናብታው ኪሩቤልን እጁን ይዛ ወደመኪናዋ
ተጣደፈች...
ከዛ ቀን ጀምሮ ከያብስራ ጋር ይጠያየቁ ጀመር ከአባቷ
ጋር ሊያስተዋውቃት ቢፈልግም እሷ ግን ብቻዋን
ሰርፕራይዝ ልታረገው እንደምትፈልግ ነገረችው እሱም
በሀሳቧ ተስማማ ... አንድ ቀን ፀጉር ቤቷ ቁጭ ብላ
መፅሃፍ ስታነብ ቴድሮስ መልክት ላከ ስልኳን ከፍታ
ማንበብ ጀመረች ቴድሮስም ሀኒዬ እንዴት ነሽ ዝም ስልሽ
የተውኩት እንዳይመስልሽ ግዜ ልስጥሽ ብዬ ነው
ለማንኛውም የፊታችን እሁድ ጥሩ ሆቴል እራት
እጋብዝሽና አብረን እናድራለን አይ ካልሽ ግን ለወንድምሽ
ከአባትሽ ጋር እንደማገጥሽ እነግረዋለው በዛም
አይበቃኝ..." ይላል ይሄኔ ሀና በውስጧ አምላኳን
አማረረች ውሳኔ ላይ መድረስ እንዳለባት በማመን
"ተስማምቻለው!" ብላ ላከችለት ...
ሀና ለባልዋ ሳትነግረው ከያብስራ የአባቷን ስልክ
በመቀበል አባቷን እራቅ ያለ ቦታ ቀጠረችው አባቷም
በተባለው ሰአት ደረሰ ሀናን ሲያያት ደነገጠ የት
እንደሚያውቃት አያውቅም ግን ይህችን ሴት ያውቃታል
ልጄ ከዚ በፊት አይቼሽ አውቃለሁ አላት ለማቀፍ
እየተጠጋ እሷም እንዳትነካኝ አቶ ፀጋዬ አለች ይቅርታ
ይሄን ያክል አመት ልጄ አለማለቴ ጥፋት ነው እናም...
ሲል ንግግሩን ሳታስጨርስ አይ አይ አሁን ይቅርታ
እንድጠይቀኝ አልመጣሁም ባንተ ሀጥያት ስቀጣ መኖሬ
ሳያንስ ባንተ ልክስክስነት ከገዛ ልጅህ ጋር በማደርህ
ዛሬም ወደፊትም ስቃይ ላይ ነኝ እናም ይህን ለልጆችህ
ተናግሬ በሀፍረት ሳትሞት በፊት እኔን ከዚ ታደገኝ ከስቃይ
አውጣኝ አለች በምሬት አባት ግን ይህን የሚሰማበት
ሞራል አጣ ማንም በሌለበት ጭር ባለው ቦታ እያየችው
መሬት ላይ ተዘረረ...

#ይቀጥላል...

#ክፍል_ሃያ_አራትን_ለማንበብ_የቸኮለ👉♥️

♨️ታሪኩ ከተመቻችሁ ♥️🤏 በመንካት #VOTE ያድርጉልን ለኛም ብርታት መስጠት ነው!!

@monhappy
📩 @BINCJ90
:)
እኔ ከዓለም ምስጋናን ከማይሹት…ከፍታን ከማይመኙት…ከማንም ምንም ከማይሹት…ዝቅታን ከማይፈሩት…የራሳቸውን ህይወት እንደራሳቸው ከሚኖሩት ወገን ነኝ…ዘላዛም ደሞ አመስጋኝ ነኝ🙏🏽
:(
እረፍት የለሽ መንገድ…ማብቂያ የሌለው ሽሽት…ሰላምን ፍለጋ ዛሬም ድረስ ብዙዋች ይሰደዳሉ…ከሚወዱት እና ከሚወዳቸው ተለይተው…እኔ ና አንተን ግን ቀን አስተዛዘበን…ወዳጄ ለካስ እኔ ና አንተ ህመማችን ለየብቻ ነበር…መቻልን የመሰለ ግን ምን አለ? 😔🖤

🖤 @monhappy
​​​​​​. 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

#ክፍል_24

...🖊የሀና አባት እራሱን መሳቱ ለሀና ደስ አላላትም
ምክንያቱም እሷ የፈለገችው ለአባቷ ቴድሮስ "ስምህን
ሊያጠፋው ነው ሀጥያትክን ለልጆችህ ሊናገርብህ ነው!"
ብላ ነግራው አባቷ ደግሞ ቴድሮስን አፉን እንዲያዘጋው
ለማድረግ ነበር ግን አባቷ ቀድሞ ራሱን ሳተ ሀናም
በፍጥነት አምቡላንስ ጠርታ አባቷን ሀኪም ቤት
ካስገባችው ቡሃላ ለኪሩቤል ደወለችለት ኪሩቤልም
ያለችበት ድረስ በፍጥነት ደረሰ...
ሀናም ልክ ኪሩቤልን ስታይ እሩጣ አቅፋው ማልቀስ
ጀመረች ኪሩቤል በሁኔታዋ ግራ ተጋብቶ ምን እንደሆነች
ጠየቃት ከዛ ሀና አንድ ባንድ መናገር ጀመረች ... "
" ... ቴድሮስ በልጅነቴ ያደረገው ሳያንስ አሁንም ገላዬን
ተመኘ እናም የእናቴ ባል እኔ ህሊና ቢስ ስለመሰልኩት
ስሜ እንዳይጠፋ ስል አብሬው እንድጋደም ፈለገ እምቢ
ካልኩ ቅድሚያ ለአባቴ ልጆች ከዛ ደግሞ መነጋገርያ
እንድሆን መፅሄት ላይ ከአባቴ ጋር አብሬ ማደሬን
እንደሚያስወራብኝ አስፈራራኝ እኔም አባቴን አግኝቼው
እንዲያስቆመው ፈልጌ ነበር ግን ለካ ችግረኛ ሴት
በመጨረሻ የምታሸንፈው ፊልም ላይ ብቻ ነው! ለካ
የእውነተኛው አለምላይ ይሄ የለም" ... ይህን ስትናገር
ሀና በንዴትና በቁጭት እየጮኸች ነበር ኪሩቤል
ካወራችው ሁሉ ውስጡ ዘልቆ የገባው ቴድሮስ ሀናን
መመኘቱ ነበር ኪሩቤል ደርቆ ቀረ ሀናም "በቃኝ ከዚ
ቡሃላ መኖር አልፈልግም እራሴን አጥፍቼ እገላገላለው
ተስፋዬ በሙሉ አልቋል ተስፋ ቢስ ሴት ነኝ!!" አለችና
ትታው ልትሄድ ስትል እጇን ይዞ ..."ሁለተኛ ይሄን ቃል
እንዳትደግሚው ለእኔና ለልጄ እጅግ በጣም
ታስፈልጊናለሽ ውዴ እኔ ቅጣት ለሚገባው ቅጣቱን
እሰጥልሻለሁ!" አለ ኪሩቤል እንዲ ለበቀል ጥርሱን
ሲነክስ የመጀመርያው ነበር...
የሀና አባት ተሽሎት እቤቱ ገባ ሀናም ከቤት መውጣት
አትፈልግም የፃፈቻቸውን ግጥሞች በሙሉ ቀዳደቻቸው
ኪሩቤል በሀና ሁኔታ ያዝናል ! እሁድ ደረሰ ቴድሮስ ያን
ቀን ካላገኛት ምን እንደሚፈጠር መገመት ለሀና ቀላል
ነበር ጭንቀቷን ያየው ባልዋ ያን ቀን እሱ እስከሚደውል
ድረስ ከቤት እንዳትወጣ በማስጠንቀቅ ከቤት ወጣ
እህትና ወንድሟ ደግሞ እሷ ቤት ነበሩ ።
ኪሩቤል ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ ምሽት 4:00 ሞላ
ይሄኔ ሀና በጭንቀት ልታብድ ደረሰች ልክ 4፡ 15 ላይ
ስልኳ ጠራ አነሳችው ኪሩቤልም ቴድሮስ ቤት ነኝ ቶሎ
ነይ አላት ሀናም ምን እንደተፈጠረ እንኳ ለመገመት ግዜ
አታ በፍጥነት ደረሰች ኪሩቤል ቴድሮስን በጣም
ቀጥቅጦት ነበር ሀና ይሄን ያደረገው ባሏ ባይሆን
የቴድሮስን ሞት ለማየት ትቀመጥ ነበር ግን ኪሩቤል
ይህን ማድረጉ እጅግ በጣም አስፈራት ቴድሮስም በደም
በተለወሰው አፉ "ይቅርታ አርጊልኝ ሀና ክፉ የሆንኩት
ወድጄ አይደለም እኔንም የእንጀራ እናት ነበረችኝ ክፉ ቃሉ
የማይገልፃት እናም ሁሌም በአባቴ ላይ ትማግጥ ነበር
በዛ ላይ ምግብ አትሰጠኝም ግን ቤታችን ውሃ ባለመኖሩ
ውሃ ከእሩቅ ቦታ እየቀዳው የማመላልሰው እኔ ነበርኩ
ሴት ልጅ እያለቻት እቃ ስታሳጥበኝና ቤት ስታፀዳኝ
የምትውለው እኔን ነው እርሃብና መድሎ ተደማምረው
ጭካኔዋ ውስጤ ጭካኔን ዘራ...በቃ ክፉ ሆንኩ" አለ
ለመጀመርያ ግዜ ቴድሮስ በሀዘን ተውጦ በአይኖቹ እምባ
ሲፈስ ሀና በአይኗ ተመለከተች የሰራው ሀጥያት ቢበዛም
መሰረቱ ሌላ መሆኑን አወቀች ...
በዚ ቅፅበት ከየት መጣ ሳይባል የሀና አባት በሩን በርግዶ
ገባ በያዘው መሳርያም ቴድሮስን እዛው ከተንጋለለበት
መሬት ሳይነሳ በጥይት ግንባሩን አለው ሀናና ኪሩቤል
በድንጋጤ ጮሁ እዛው ባሉበት ደርቀው ቆመው ሳላ
አካባቢው በሰው ተሞላ ከደቂቃዎች በኋላም ፖሊስ
መጥቶ ሶስቱንም ይዟቸው ወደጣብያ ሄደ ሀና በነጋታው
ጠዋት ብትፈታም ባሏና ወላጅ አባቷ ግን እስኪጣራ
በሚል ሳይፈቱ ቀሩ...

#ይቀጥላል...

🕹የመጨረሻው ክፍል ከ200♥️ VOTE ቡኃላ የሚቀርብ ይሆናል፡፡

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡

🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@monhappy // ,,📩 @BINCJ90
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
............♥️💍••●🍃🌹🍃●•..............
@monhappy
@monhappy
​​.​​ 💕✿ተስፋ ያጣች ሴት✿💕

▤▵በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ታሪክ▵▤

🔥#የመጨረሻው_ክፍል🔥

...🖊ሀና ነገሮች እስኪጣሩ ተብሎ የታሰረውን ባሏን ቀን በቀን
ትጠይቃለች በተፈጠረው ነገር በጣም ከመደንገጧም
በላይ የቴድሮስ መሞት ውስጥ የኪሩቤል እጅ አለበት
መባሉ እረፍት ነስቷታል እውነት ለመናገር ኪሩቤል
ሊያስፈራራው እንጂ ሊገለው እንደማይደፍር እርግጠኛ
ነች ... ሀና ልጇን ትምህርት ቤት አድርሳ ባልዋን
ትጠይቅና እቤቷ ተቀምጣ ታስባለች ... ቴድሮስ
ሲደፍራትና ሲያሰቃያት መኖሩ ከሞት በላይ ቢቀጣም
አያሳዝናትም ነገር ግን ቴድሮስ በመጨረሻ ሰአት
የተናገረውን አስታወሰች ለዚ ክፋት ያበቃችው አንዲት ክፉ
ሴት ናት ... ሀና ይህን ካሰበች ቡሃላ "አይ አይ አይሆንም
ምንም ቢሆን ይቅር አልለውም እኔ በእንጀራ አባቴ
ስለተበደልኩ ወደፊት ሌላ ሰው ላይ ክፉ መሆን
የለብኝም!" አለች...
መሽቶ ይነጋል ኪሩቤልና የሀና አባት ሳይፈቱ 35 ቀናትን
አስቆጠሩ ሀና የሷ ሳያንስ በሷ ምክንያት ለፍቅር ሲል
መስዋዕት እየከፈለ ያለው ባልዋ ያሳዝናታል
ያስጨንቃታል ሁሌ ታለቅሳለች በዚ መሀል ያብስራ
ሊያገኛት ቢለፋም ሀና ግን ልታየው አፈረች ሁሌም
ያብስራ ወንድሟ መሆኑን ስታስብ ከአባቷ ጋር የሰራችው
ስህተት እረፍት ይነሳታል... የእናቷን ልጆች እሷ ጋር
አምጥታ ከልጇ ጋር እያኖረቻቸው ነው ...
እለተ ሀሙስ ሀና በጥዋት ተነስታ ሰራተኛዋን ልጆቹን ወደ
ትምህርት ቤት እንድታደርሳቸው ካዘዘቻት ቡሃላ ወደ ቤተ
ክርስትያን ሄደች ዛሬ የፍርድ ቀን በመሆኑ ኪሩቤል ነፃ
ይወጣ ዘንድ እንባዋን አውጥታ ለአምላኳ ፀለየች ...
ከዛም መኪናዋ ውስጥ እረጅም ሰአት ከቆየች ቡሃላ ወደ
ፍርድ ቤት ሄደች ሰአቱ ደርሶ ስለነበር ሁሉም ሰው ገብቷል
እዛ ያብስራም አለ አቃቢው የክስ ይዘቱን ማስታወስ
ጀመረ "... ሟች አቶ ቴድሮስን አቶ ኪሩቤል መስፍንና አቶ
ፀጋዬ ገ/ማርያም በግል ፀብ ተነሳስተው ገለዋቸው
እንደነበር በማስረጃ አሳይተናል ... በመሆኑም ለዛሬ
ፍርድ ሊሰጥ ቀጠሮ በመያዙ ፍርድ ቤቱ ተገቢውን ቅጣት
እንዲሰጥልን እንጠይቃለን...!!" አለ ሀና ኪሩቤልን
እያየች እንባዋ ይወርልዳ በዚ ጥቂት ቀን ውስጥ እንዲ
ከተጎሳቆለ አመታት ቢፈረድበት ምን ሊሆን ነው ትላለች
በውስጧ...
ዳኛው ንግግራቸውን ቀጠሉ "ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት
ተከሳሾች የምትሉት ካለ" አሉ ይሄን ግዜ የሀና አባት
ያለምንም መረበሽ ..."ቴድሮስን የገደልኩት እኔ ነኝ ልጅ
ኪሩቤል ምንም አያውቅም ልጄን ሲያሰቃይ በመኖሩና
ሲዝትባት አናዶኝ ሆን ብዬ እኔ ገደልኩት ስለዚህ ኪሩቤል
ነፃ ነው!!!" አለ ሀና ደንግጣ ፈዛ ቀረች ... የሀና ወላጅ
አባት 15 አመት እስራት ሲፈረድበት ኪሩቤል ግን ነፃ
ወጣ ሀና ፀሎቷ በመስመሩ ፈጣሪዋን አመሰገነች ...
አባቷ ለመጀመርያ ግዜ ጥሩ ስራ በመስራቱ እረፍት
ይሆነው ዘንድ ይቅር አለችው ። ሀና ሁለተኛዋን ልጇን
ነብሰ ጡር እንዳለች ኪሩቤል ፕሮሰስ ጨርሶ እሷንም
እህትና ወንድሟንም ወደ ጀርመን ወሰዳቸው በርግጥ
ለሀና ከሀገር መውጣቷ ልክ ነበር ብዙ ችግሮቿን
ለመርሳት በቅታለች አሁን ጀርመን ላይ ከምታፈቅረው
ባልዋ ጋር በደስታ መኖር ከጀመረች አመት አልፏታል።

ተፈፀመ

🕹ምስጋና
:-ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ!

📬በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት ከታች 📮አስተያየት መስጫ📮 የሚለውን በመንካት ያድርሱን፡፡

🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••
@monhappy // ,,📩 @BINCJ90
“ሁሌም በጣም የሚያስፈራው የሆነ ነገር ለማድረግ ከመጀመራችሁ በፊት ያለው ጊዜ ነው”
.
ስቴፈን ኪንግ (Stephen King) ገና የሁለት አመት ህፃን እያለ ወላጅ አባቱ ቤተሰቡን ጥሏቸው ጠፍቷል። አባቱ ከጠፋ በኋላ እናቱ ቤተሰቡን ለማስተዳደር የምትችለውን ሁሉ ያለመታከት ያደረገች ቢሆንም የእሷ ድካምና ጥረት ቤተሰቡን ከድህነት ህይወት የሚያወጣ አልነበረም። በዚህም እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ ከማደግ ውጭ አማራጭ አልነበረውም።
.
የ1ኛ ደረጃ ተማሪ በነበረበት ወቅት ከቅርብ ጓደኛው ጋር ከቤታቸው ትንሽ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደው በመጫወት ላይ እያሉ ጓደኛው በአሰቃቂ ሁኔታ በባቡር ተገጭቶ ህይወቱ ሲያልፍ በአይኑ ተመልክቷል። ያኔ ለጨዋታ የወጣው ስቴፈን ኪንግ በከፍተኛ ድንጋጤና በዝምታ ወደቤቱ ተምልሷል። ከዚያም ብቸኝነት የሚያጠቃው እና መፃፍ የሚያዘወትር ልጅ ሆኖ ነበር።
.
ስቴፈን ኪንግ በሜይን ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ተከታትሎ ለመመረቅ የሚያስፈልጉትን ክፍዎች ለመፈፀም የፅዳት ሰራተኛ ፣ የጋዝ ፓምፕ አስተናጋጅ እና በኢንዱስትሪ የልብስ ማጠቢያ ተቋም ውስጥ ሰራተኛን ጨምሮ የተለያዩ ያልተለመዱ ሥራዎችን ሰርቷል፡፡ በዚህ ወቅትም በህይወቱ ደስተኛ ባለመሆኑ የአደንዛዥ እፅ ሱሰኛም ሆኖ ነበር።
.
ከዩኒቨርሲቲ ተመረቀም በኋላ አግብቶ አንዲት ሴት ልጅ የወለደ ሲሆን ያኔ ነበር ከአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት ጋር ከአስር ዓመት በላይ የዘለቀ ትግል ያደረገው፡፡ የአልኮል ሱሰኛ እና የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኛ ነበር፤ ኮኬይን ፣ ማሪዋና ፣ ዣንክስ ፣ ቫሊየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን አላግባብ የሚጠቀምና ህይወቱ አደጋ ላይ የወደቀ ሰው ነበር፡፡
.
በቤተሰቦቹ ከፍተኛ ድጋፍ፣ በህክምና እርዳታ፣ እና በራሱ ከፍተኛ ጥረት ከነበረበት የአልኮልና የአደንዛዥ እፅ ሱሰኝነት የተላቀቀ ሲሆን የቤተሰቡን የዕለት ጉርስ እና የቤት ኪራይ ለመሸፈን የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ጎን ለጎን የጽሁፍ ስራውን መስራት ጀመረ፡፡
.
ስቴፈን ኪንግ በሚያሳዝን ድህነት ውስጥ እየኖረ እና የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ የመጀመሪያ ድርሰቱን ማጠናቀቅ ችሏል። ነገር ግን በማይታመን ሁኔታ CARRIE የተሰኘው የመጀመሪያ ልብ ወለድ ስራው በአንድ ኩባንያ ከማታተሙ በፊት በድምሩ ለ30 ጊዜ በተለያዩ ኩባንያዎች ውድቅ ተደርጓል ፡፡
.
በዚህም ተስፋ በመቁረጡ ድርሰቱን ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ወርውሮታል። ሆኖም ባለቤቱ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ያገኘችውን የተቀዳደዱ ፅሁፎች ሰብስባ ትንሽ ማስተካከያ ቢያደርግበት ጥሩ ጽሁፍ እንደሆነ ስላበረታታችው በእሷ አነሳሽነት ለፅሁፉ ማስተካከያ በማድረጉ እና በአንድ ኩባንያ ተቀባይነት በማግኘቱ ለህትመት ሊበቃ ችሏል። መፅሀፉም ህይወቱን የቀየረ እና ተቀባይነቱን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደገ ሆነ።
.
ስቴፈን ኪንግ ኪንግ ወደ 200 የሚጠጉ አጫጭር ታሪኮችን የጻፈ ሲሆን ከ 350 ሚሊዮን በላይ ቅጅዎችን የተሸጡ 54 መጻሕፍትን ጽፎ አሳትሟል ፣ ብዙዎቹም ወደ ፊልሞች እና የቴሌቪዥን ትርዒቶች ተቀይረው ለእይታ በቅተዋል፡፡ የብሔራዊ የመጽሐፍ ሽልማት (National Book Award) እና የሁጎ ሽልማትን (the Hugo Award) ጨምሮ በደርዘን የሚቆጠሩ ሽልማቶችን ለማግኘተም ችሏል ፡፡ እሱ በሥራው የተመሰገነ እና የተተቸ ቢሆንም ያለ ጥርጥር በዓለም ላይ በጣም ዝነኛ እና በጣም ስኬታማ ከሆኑ ጸሐፊዎች መሀከል አንዱ ነው፡፡
.
በውስጣችሁ ያለውን ክፋት በውስጣችሁ ባለው መልካምነት የምታሸንፉበት የተዋበ ቀን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!

@monhppy
@BINCJ90
"በእድሜ ትንሹ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለመሆን ተወዳድሮ የተረታው ሰው ዛሬ በእድሜ ትልቁ ፕ/ ት በመሆን አዲስ ታሪክ ለመፃፍ በቅቷል።"
አይሰበሬው ሰው - ጆ ባይደን !


@monhappy
"በእድሜ ትንሹ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለመሆን ተወዳድሮ የተረታው ሰው ዛሬ በእድሜ ትልቁ ፕ/ ት በመሆን አዲስ ታሪክ ለመፃፍ በቅቷል።"
አይሰበሬው ሰው - ጆ ባይደን !
የመጀመሪያ ልጅ ሆኖ ወደዚች ምድር ሲመጣ አብሮት መጥፎ አድል ወደቤቱ ገባ ። ታላቅ የቢዝነስ ሰው የነበረው አባቱ ወደከባድ ድህነት ተምዘገዘገ ። አባቱ ስራ አጥ እስከመሆን ደርሶ ነበር ። ቤተሰቡ ራሱን መደጎም አቅቶት የእናቱ ቤተሰቦች ጋር ጥገኛ ሆኖ ለመኖር ተገዶ ነበር ። ከሀብታም ቤተሰብ ተወልዶ | የደሀ ቤተሰብ እጅ ላይ የወደቀ መዘዘኛ ልጅ ነበር።
ገና አስራዎቹ ውስጥ ሳይገባ ትምህርትቤት ውስጥ አትክልተኛ በመሆን ቤተሰቡን በገንዘብ የመደጎም ሀላፊነት ተጥሎበት ነበር ። በክፍሉ ውስጥ የሚያስመዘግበው ውጤት እጅግ ዝቅተኛ ስለሆነ ማንም ለፕሬዚደንትነት ይወዳደራል ብሎ ያሰበው አልነበረም።
እድሜው ከፍ ሲል አፉ እንደፈርኦኑ ቤት ሙሴ ተብታባ ስለነበር የመምህራንና የተማሪዎቹ መሳቂያ መሳለቂያ ነበር ። ማንም ይሄ ተብታባ ልጅ ፖለቲከኛ ይሆናል ብሎ አልጠበቀም ። ይሄን አፉን ለማስተካከል ለሰዐታት መስታዎት ፊት ቆሞ ለራሱ መነባንብ በማቅረብ ንግግር ይለማመድ ነበር።
ታሪክ | ፖለቲካል ሳይንስና | ህግ ተምሯል ። የህግ ዲግሪውን ሲይዝ ከ85 ተማሪዎች 76ኛውን ውጤት ነበር ማግኘት የቻለው ። በሃያዎቹ እድሜው ውስጥ ህይወት ለእሱ ያደላች መሰለች ። ትዳር መስርቶ ሁለት ወንድና አንዲት ሴት ልጅ ወለደ ። በጠባብ ውጤት ተቀናቃኙን በመርታት በ29 ዓመቱ የሴኔት አባል ሆኖ በመመረጥ ስድስተኛው በእድሜ ትንሹ ሴናተር በመሆን ተመረጠ።
ህይወቱ የመጥፎ እድልና የሰቀቀን ነበር ። ህይወት መከራውን ስታበዛው ትንሽ ፈገግታ አሳይታ በጥፊ ጆሮግንዱን ትደረግምለታለች ። ገና ለሴናተርነት ተመርጦ ወንበሩን ሳይቀመጥበት ለገና በዐል ገበያ የወጡ ቤተሰቦቹ የመኪና አደጋ ሲሳይ ሆኑ ። የስድስት ዐመት አፍላ ትዳሩ በዚያው ተቋጨ ። ባለቤቱና የአንድ ዐመት ሴት ልጁ እዛው ክልትው አሉ ። የሁለትና ሶስት ዐመት ወንድ ልጆቹ ከብዙ ቁስልና ስብራት ጋር የሆስፒታል አልጋዎች ላይ ተገኙ።
በወቅቱ የመኖር ትርጉም ጠፍቶበት ራሱን ስለማጥፋት ማሰቡን በብዙ ቃለምልልሶቹ ላይ ይገልፃል ። [ለቀሪ ልጆቼ ማን አላቸው] ስል መኖርን መረጥኩ ባይ ነው ። እነሱን ለማስታመም ራሱን ከስልጣን ለማግለል ወስኖ በወዳጆች ጉትጎታ ቃለመሀላውን ከልጆቹ መኝታ ጎን በሆስፒታል ውስጥ ፈፀመ።
የእግዜርን ህልውና መጠራጠር ለጀመረው ጆሴፍ ባይደን ህይወት መልሳ ፈገግታዋን ለገሰችው ። ከ3 የሰቀቀን ዐመታት በኋላ ከዶ|ር ጂል ጄኮብስ ጋር ትዳር መስርቶ ሴት ልጅ ተካ ። በሴኔት ቆይታው እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰው ነበር ። በርካታ ህጎችን በማፀደቅና በማስሻር የባይደን አሳማኝ መከራከሪያዎች ውጤታማ ነበሩ ። ከ13 ዐመታት በኋላ ጆ ባይደን በታሪክ በእድሜ ትንሹ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለመሆን እጩ ሆኖ ቀረበ ። ከነበረው ስምና ስኬት አንፃር ውድድሩን የማሸነፍ ትልቅ ግምት ተሰጥቶት ነበር።
ህይወት ስቃ የማትስቅለት ሰው የምርጫ ዘመቻው ላይ ከባድ እክል ገጠመው ። ለምርጫ ቅስቀሳ የተጠቀማቸው የንግግር መስመሮች ከሌሎች ፖለቲከኞች ንግግሮች ጋር ቃል በቃል በመመሳሰላቸው ከፍተኛ ዘለፋን አስተናገደ ። በመጨረሻም ራሱን ከምርጫው ለማግለል ተገደደ ። በዚያው ሰሞን ጭንቅላት ውስጥና ሳምባ ውስጥ ባሉ የደምስር ችግሮች [intracranial berry aneurysm, pulmonary embolism] ምክኒያት ተደጋጋሚ የጭንቅላት ቀዶ ጥገናዎችን አድርጎ ነበር ። ሞት ደጃፉን እያንኳኳ ጥሎት የሄደ ሰው ነው።
ያሳለፈው የምርጫ ፉክክር ታሪክ እንቅፋት ሆኖበት ከፕሬዚደንታዊ ምርጫ ገለል ያለው ብርቱ ሰው 2008 ላይ ለፕሬዚደንትነት ቢወዳደርም በባራክ ኦባማ ድል ተደረገ ። ነገር ግን ኦባማ የባይደንን ብቃት በማድነቅ ምክትሉ ሆኖ እንዲወዳደር በጠየቀው መሰረት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚደንት ለመሆን በቃ ። እጅግ በጣም ድንቅ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ኤክስፐርትና የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ተደራዳሪ እንደነበር የሚነገርለት ባይደን ከፕሬዚደንት ኦባማ እጅ ከፍተኛውን የሀገሪቱን የክብር ሜዳሊያ ሲሸለም እምባውን መቆጣጠር ተስኖት ታየ።
ፈገግ ያለችለት የመሰለችው ህይወት መልሳ መዳፏን ወልውላ ጥፊ ለመሰንዘር ብዙ አልታገሰችውም ። ከመኪና አደጋ የተረፈው | በወታደርነት ኢራቅ ዘምቶ ሀገሩን ሲያገለግል የኖረው ወንድ ልጁ በጭንቅላት ካንሰር ማቅቆ ከዚህ አለም በሞት ተለየ ። ስምንት አመት ሀገሩን በምክትል ፕሬዚደነት ላገለገለው አይበገሬው | ይሄ በእርጅናው ዘመኑ የገጠመው ከባዱ ፈተና ነበር።
በ2020 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ላይ ሲወዳደር ከፕሬዚደንት ትራምፕ ከባድ ክብረነክ ዘለፋዎችን ለማስተናገድ ተስኖት ስሜታዊ ሲሆን ታይቷል ። እንቅልፋሙ ጆ | Sleepy Joe | እያሉ በሚጠሩት ሰው በወታደር ልጁ ማንነት ላይ | በልጅነት በነበረው ደካማ የትምህርት ብቃት | እንዲሁም በእድሜ በሚመጣ የመርሳት ችግሮች ላይ ያነጣጠረ በርካታ ዘለፋዎችን አስተናግዷል።
ዛሬ ግን ህይወት ከፈገግታም አልፋ ከት ብላ የሳቀችለት ትመስላለች ። በእድሜ ትንሹ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለመሆን ተወዳድሮ የተረታው ሰው ዛሬ በእድሜ ትልቁ ፕሬዚደንት በመሆን አዲስ ታሪክ ለመፃፍ በቅቷል | አይሰበሬው ሰው።
© ዶ/ር ዮሴፍ ወርቅነህ

@monhappy
@BINCJ90
"ጀግናዋ ቤርናዴትና የተከላካዩ አበሳ"

@monhappy
@BINCJ90
2025/07/09 10:55:15
Back to Top
HTML Embed Code: