Telegram Web Link

ህያብ
ክፍል 40

ፀሃፊ ረምሃይ

ቀናት ቀናትን እየቆጠሩ አለፉ... ህያብ ወደ ትምህርት ገበታዋ ተመልሳለች።

ከጓደኞቿ ዶርም ወጥታ እነ ርሻን ዶርም ገብታለች ሜሮንም ዶርም አስቀይራ ወደ ርሻን መጥታለች የድሮው ወዳጅነታቸው እንዳዲስ ከአመታት ኩርፊያ በኃላ ተመለሰ። ነገሮች ወደቀድሞው መመለስ ጀመሩ ነገር ግን የህየብ ጥፋቶች እየተከተሉ ያድኗት ጀምረዋል። ከነረቂቅ ጋር የነበራትን ጓደኝነት አቁማ ወደነ ርሻን ስትመለስ በጣም.ተበሳጭተውባት ነበር መንገድ ላይ ባይዋት ቁጥር ፊታቸውን ያጠቁሩባታል፤ ከዚህ በፊት ይዛቸው የነበሩት የወንድ ጓደኞች ሲያገኟት ይፈትኗታል፤ ያስቀየመቻቸው በክፉ ቃል የተናገረቻቸው ስታገኛቸው ይገላምጧታል.... አልቻለችም እንደድሮዋ ትህትናን መላብስ አቃታት።

ህያብ ግቢ ውስጥ መቀመጥ ሲጨንቃት ወደ ማታ ላይ አሃዱ ጋር ደወለችለትና እራት ሊበሉ ወደከተማ ወጡ። በብዙ የጊቢ ተማሪዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ልደታ ምግብ ቤት ገብተው ተቀመጡ ምግብ አዘዙ። ምን ሆነሻል ፊትሽ ልክ አይደለም አላት አሃዱ። ከበደይ አሃድዬ በፊት የሰራኃቸው ጥፋቶች ግዜ ጠብቀው እላዬ ላይ እየፈነዱብይ ነው ወደ ቀድሞ ማንነቴ ልመለስ ስል ብዙ ነገሮች ይፈታተኑያል ምን እንደማደርግ አላውቅም ግራ ገብቶያል አለችው። ለውጥ እኮ ቀላል አደለም ሲጋራ ለአመታት ሲያጨስ የኖረን ሰው ድንገት በአንድ ቀን አቁም ብትይው ይከብደዋል ላንቺም እንደዛ ነው ሁሉንም ነገር በአንዴ ለማድረግ አትሞክሪ ማንነት ቀስ በቀስ የሚገነባ ነገር ነው። የሰውን እምነት ለመስበር ሽርፍራፊ ደቂቃዎች በቂ ናቸው ግን ያንን እምነት መልሶ ለማግኘት አመታት ሊፈጅ ይችላል ስለዚህ ትእግስት ይኑርሽ ሁሉም ቀስ በቀስ የሚመለስ ነው አላት። ህያን ደስ አላት

ለተወሰነ ደቂቃ በአርምሞ ተውጣ ስለአሃዱ ታስብ ጀመር አንድ ነገር አስተዋለች ስለአሃዱ የግል ህይወት ምንም የምታውቀው ነገር የለም። ስለእሱ የምታውቀው የባህርዳር ልጅ እንደሆነና ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ወደመቀሌ አስቀይሮ እንደመጣ ብቻ ነው ለምን አስቀይሮ እንደመጣ አታውቅም ሌላው ቀርቶ የአባቱ ስም ማን እንደሆነ እንኳን አታውቅም ገረማት! ታዲያ አሃዱን ሳላውቀው ለምንድነው የወደድኩት ብላ ይበልጥ ተገረመች። አሃዱን ቀና ብላ እያየችው አሃድዬ የአባትህ ስም ግን ማነው አለችው። ፈገግ እያለ አታውቂውም አላትና መልሷን ሳይጠብቅ ቅዱስ ... ቅዱስ ነው የአባቴ ስም አላት። ኦውውውው... ደስ ይላል አሃዱ ቅዱስ! አለችው። ኣ..ኣ... አይደለም አሃዱአብ ቅዱስ ነው አለት ። ህያብ ፈገግ አለች ይህንን ሰው ምንም አላውቀውም ማለት ነው አለች በልቧ።

ስለአሃዱ የግል ህይወቱ ትጠይቀው ጀመር ግን የሚመልስላት መልስ በጣም ውስንና ቁጥብ ነበሩ ምንም እንደፈለገችው ሊሆንላት አልቻለችው እርጋታውን ብትወድለትም ግዜና ቦታ ሊኖረው እንደሚገባ አሰበች። እሱ እንደለመደቻቸው ወንዶች ቀልደኛ ተጫዋች አይነት እንዳልሆነ ብታውቅም ለሷ ሲል ቢሞክር ምን ነበረበት አይወደኝም ማለት ነው ብላ አሰብች። እንዲህ ስታወጣና ስታወርድ ምግባቸው ከረጅም ሰአታት ጥበቃ በኃላ መጣ። በልተው ከጨረሱ በኃላ ከልደታ ወጥተው ቀስ እያሉ ወክ እያደረጉ ወደ አሪድ ግቢ የሚወስዳቸው ታክሲ መያዣ ቦታ አመሩ። ህያብ የደበራት ነገር ቢኖርም መናገር አልፈለገችም ዝም ተባብለው ወደ ግቢ ሄዱ። ግቢ ሲደርሱ ወደበግተራ ሸኝቷት ሊሄድ ሲል ወክ እናድርግ አለችው። እሺ አላትና ወደ ሉሲ መንደር የሚወስደውን አቅጣጫ ይዞ ሊሄድ ሲል እጁን ጎተት እያደረገችው በዚህ በህዳሴ በኩል እንሂድ አለችው። አይ በዚህ እንሂድ በዚህ ይሻላል አላት ህያብም ላለመሸነፍ በህዳሴ በኩል እንሁድ ስንመለስ በሉሲ መንደር እንመለሳለን አለችው። አሃዱ እልህ እንደያዛት ስለገባው እሺ አላትና ፊታቸውን ወደ ህዳሴ ካፌ አቅጣጫ አዙረው ወክ ማድረግ ቀጠሉ።
ይቀጥላል 500👍 ሲገባ

@BINCJ90
@monhappy
የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ በኢትዮጵያ‼️⬇️

- አጠቃላይ በኢትዮጵያ የተደረገ ምርመራ (794,686)
- አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ (43,688)
- ከበሽታው ያገገሙ (15,796)
- ህይዎታቸው ያለፈ (709)

ይህንን መዘናጋታችንን መቼ ነው ግን የምንተወው?? ሁላችንም በቫይረሱ እስክንያዝ ድረስ?? ነው ወይስ ምንድን ነው ነገሩ??😳 ኧረ ወገን እንንቃ አናንቀላፋ! ገዳይ ነውኮ ቫይረሱ... #ገዳይ!!
ሼር
#መልካም_ምሽት

ህያብ
ክፍል 41

ፀሃፊ ረምሃይ

ህያብ እና አሃዱ እግራቸው እንደመራችው እየተጓዙ ነው። የህዳሴን ካፌ አልፈው ወደታይታኒክ በሚወስደው በፅድ ዛፎች እና ብርትኳንማ የመንገድ መብራቶች በተሰለፉበት ጥንዶች በሚያዘወትሩት መንገድ ወክ እያደረጉ ነው። ከሩቅ ሁለት ጥንዶች በነሱ አቅጣጫ ሲመጡ ይታያቸዋል ግድ አልሰጣቸውም ወሬያቸውን እያወሩ መምገዳቸውን ቀጠለ እየተቀራረቡ ሲመጡ ህያብ ከፊትለፊታቸው የሚመጡት ጥንዶች ወንዱ ሃበን እንደሆነ አወቀች እንደመደምገጥ አለች የሆነ የቅናት መንፈስ ያዛት ከማን ጋር ነው ወክ የሚያደርገው ብላ አሃዱን ኮስተር ብላ ጠየቀችው። አላውቅም አላት ሃቡን ሁለቱንም አያቸው ምንም ሳይመስለው ካቀፋት ልጅ ጋር እያወራ አልፏቸው ሄደ። ህያብ ያቀፋት ልጅ ላይ አፈጠጠች ሜላት ናት! ሁለቱን ያጣላቻቸው ሜላት! የድሮ ጓደኛዋ አብራት ዶርም የነበረችው ሜላት! ተናደደች!። ወዲያው ከአሃዱ እቅፍ ወጣችና ወደኃላ ዞራ ፈጠን ፈጠን እያለች ወደ ሃበን ሄደች። ከኃላ ትከሻውንን ነካ ነካ አደረገችውና አንዴ ላናግርህ አለችው። ሃበን ዞሮ አያት ሜላትም ዞራ አየቻት። ዝም ከምል ብላ ሰላም ነው ህያብ አለቻት። ህያብ ምንም መልስ ሳትሰጣት አይኗን ገልመጥ አድርጋ ወደ ሃበን መለሰቻቸው።

ሃበን እንደበፊቱ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ያናግረኛል ብላ ስትጠብቅ። ሃበን በሚገርም እርጋታ ውስጥ ሆኖ ሰላም ነው ህያብ እንዴት አመሸሽ አላት። ህያብ ተበሳጨች ምንድነው ችግርህ ብላ ጮኀችበት። ሃበን ወደ ሜላት እያየ ሜሊ አንዴ ላናግራት እሺ ብላት ህያብን ወደ አንዱ ጥግ ፈቀቅ አደረጋትና ምን ሁነሻል ምንድነው ችግርሽ ብሎ ጥየቃት። ምንም አልሆንኩይም... ከሜላት ጋር ቺት ያደረክብይ ሳያንስ ብለህ ብለህ አቅፈሃት ግቢው ውስጥ ትዞራለህ አለችው። ሃበን ሳቀ... ሃ..ሃ...ሃ... እንቺ እንኳን ከአዲሱ ባልሽ ጋር ወክ እያደረግሽ አይደል እንዴ አላት።

አሃዱ ግራ ገባው ሃበንና ህያብ ባህሪ የተቀያየሩ መስሎ ታየው። ሜላት ወደሱ ሄደች ሰላም አለችው። ሰላም ነው አሃዱ እንዴት አመሸህ ረጅም ግዜ ተጠፋፋም አይደል ደግሞ ወደዚህ ግቢ ማስቀየርክን ሰማው አለችው። አሃዱ ሰላምታዋን እንኳን ሳይመልስ ኮስተር ብሎ... ለመጨረሻ ግዜ ሳገኝሽ ይህ ሰው እንደማይጠቅምሽ ነግሬሽ ነበር መስመርሽን ለማስተካከል አሁንም ጊዜ አለሽ በኃላ እንዳይፀፅትሽ እኔ የበኩሌን ነግሬሻለ አላት።

ህያብ ከሃበን ጋር እየተጨቃጨቀች እንዳለ በመሃል አይኗን መለስ ስታደርግ ሜላት አሃዱ ጋር ሄዳ ስታወራው አየች። ከሃበን ጋር መጨቃጨቋን ትታ በፍጥነት ወደነአሃዱ ሄደች። ደርሳ ሜላትን ገፈተረቻትና ቆይ ምንድነው ችግርሽ እኔ የያዝኩት ነገር ሁሉ የሚያምርሽ እሱንም ልትስሚው ነው አለቻት። ሜላት ስለገፈተረቻት እየተናደደች ያምሻል አንዴ አቺ አሃዱ ድሮ ሃይስኩል እማቀው ልጅ ነው ሰላም ነው ያልኩት ሌላ ነገር ምንም የለም አለቻት። ህያብ አንቧረቀች ዝምምም በይ ውሸታም ብላ ልትደባደሃባት ተጠጋች። ሃበን መሃል ላይ ገብቶ ያገላግላቸው ጀመር። አንድ ሁለት ከተባባሉ በኃላ ሃበን ህያብንን እያያት ስቆ ቅናት እንዲ ነው ገባሽ ብሏት ሜላትን ይዟት ሄደ። ህያብ በበለጠ በሸቀች መናደዷ ይበልጥ እናደዳት። መሬት ላይ ቁጢጥ ብላ ተቀመጠች ትንሽ ራሷን ካረጋጋች በኃላ ድጋሚ ተነሳችና አሃዱ ወዳለበት አቅጣጭ ስትዞር አሃዱ በአከባቢው የለም!። ስላዘነባት ጥሏት እንደሄደ ገባት።

ንዴቷ ስላለቀቃት የራሱ ጉዳይ ጥርግ ይበል አለችና ራሷን ለማረጋጋት ብቻዋን ወክ ማድረጉን ቀጠለች። ቀስ እያለች በአርክ ህንፃ ጀርባ አድርጋ በሞሞና ፓርክ በኩል በሚወስደው ቀጭም መንገድ ብቻዋን እየሄደች ወደ ገዳም ዶርሞች የሚያስወጣው አስፓልት ላይ ደረሰች። ትንሽ ሰከም ስትል እንባዋ መጣ ለማንና ለምን እንደምታለቅስ አታውቅም ግን ማልቀስ ጀመረች እንባዋን ቶሎ ቶሎ እየጠረገች በገዳም ዶርሞች ወደ እንዳየሱስ ቤተክርስቲያን በሚወስደው አስያፓልት ላይ እየሄደች ወደ ቢዝነስ ላውንች አከባቢ ስትደርስ አስፓልቱ ጥግ ላይ ቁጭ አለች። ለቅሶዋን አቀለጠችው።
..........................................
እንዳጋጣሚ የዛን ለሊት እኔም ብቻዬን ወክ እያደረግኩ ብርዱን የምከላከልበት ወፍራም ጃኬቴን ለ ብሼ ኢርፎኖን ሰክቼ እጓዛለው

በከነአን መንደር አልፌ ወደ እንዳኢየሱስ ቤተክርስቲያን የሚወስደውን ወደ ቀኝ ትቼ ወደ ገዳም ሰፈር የሚወስደውን አስፓልት ይዤ ስሄድ በቅርብ ርቀት አንዲት ሴት ስታለቅስ ሰማው... እኔ በዚህ ግዜ ለሌላ ሰው ግዜዬን እማካፍልበት ሰአት አለበረም ከባድ ግዜ እያሳለፍኩ ነበር አልፊያት ሄድኩ። ልክ ሳልፋት ግን ልጅቷ ሳግ ባነቀው ድምፅ ረ..ም..ሃይ ብላ ጠራችኝ። ዞሬ አየኃት ህያብ ናት! ምነው ህያብ ምን ሆነሽ ነው በዚህ ሰአት እዚህ ብቻሽን ተቀምጠሽ የምታለቅሺው ብዬ ጠየቅኳት ህያብ ስታየኝ ለቅሶዋ ባሰባት.... ምንም ሳልላት ሄጄ አጠገቧ ተቀመጥኩ።

ውድ ታሪክ ቻናል ቤተሰቦች ህያብ ምዕራፍ 1 በዚሁ ተጠናቀቀ ምዕራፍ 2 ተዘጋጅቶ እስኪያልቅ በትግዕስት እንድጠብቁንና እስከዛ ድረስ ሌሉች ታሪኮችን የምናደርሱት ይሆናል እስካሆን በህያብ አቀራረብ ላይ ያላችሁን አስተያየት
@BINCJ90 ላይ ያድርሱን ስንት 👍 ይገባናል
🇪🇹 TiK ToK 🇪🇹
ባጭር ጊዜ ተከፍቶ ብዙ ሰዎች የተቀላቀሉት የታዋቂ አርቲስቶች አዝናኝ የTiktok ቪዲዮችን በቴሌግራም በየቀኑ የሚለቀቅበት ቻናል ይቀላቀሉት እመኑኝ ይወዱታል።👍 ቴሌግራም ተጠቃሚዎች ከስር ባለው ሊንክ ይቀላቀሉ👇👇👇
@monhappy
@monhappy
@monhappy
" ኤሴቅ "
ክፍል ~፩~(1)


በራስ አምባ ከተማ ወጣ ባለ የገጠር ክፍል
ቀይ አፈር የገጠር ቀበሌ
ከተራራው ግርጌ ካለች ዛፍ ስር ተቀምጦ ያንጎራጉራል። ፊት ለፊቱ ዝምተኛ ጫካ ከወፍ ጎጆዎቹ ጋር በፀጥታ ተውጧል። ዛፎቹ ድምፅ ሳያሰሙ ከወደ ምዕራብ በሚነፍሰው ነፈስ ይወዛወዛሉ። ተከዜ የውሃ መጠኑን ከክረምቱ እጥፉን ቀንሶ ቁልቁል ይጥመለመላል። ይሄን ትዕይንት በቀራርቶ መልክ እያዋዛ ይለዋል ተፈጥሮ የሆዱን ትነገረዋለች። ተከዜ የብሶቱ መውጫ መሸሸጊያው ናት።ዛሬም እንደ ወጣትነቱ ዛሬም እንደያኔው ራቁቱን ለዘመን መለወጫ የተከዜ ሙሉ ወንዝ ላይ እንደሚዋኘው። ዛሬም የከፋውን ሆድ ያባሰውን ችግር ለማንፃት መታጠብ ይዳዳዋል። በዘመናት ሂደት በአመታት ሩጫ የማያረጅ የማይለወጥ ወንዝ ቢኖር ለእርሱ ተከዜ ነው። ተከዜ ከኢትዮጵያ ገባር ወንዞች አንደኛው ነው ከ12ኛው መቶ ክፍለዘመን በፊት እንደነበር የሚነገርለት ይህ ወንዝ ልክ እንደ አባይ መዳረሻውን ወደ ገሸብፅ ያደርጋል። ስለ ተከዜ ሲነሳ ሲወራ የሰፈሩ ሰው የሚጠይቀው አቶ ታረቀኝ ነው። ልጅነቱን ወጣትነቱን አሁን ደግሞ የእርጅና ዘመኑን የሚያሳልፈው በዚህ የወንዝ ህዳግ ነው። ተከዜ ወንዝ ዳር ከምትገኘው የዋርካ ዛፍ ቁጭ ብሎ ያፏጨ እንደሁ ዛሬም በፉጭቱ የሚማረኩ ልጃገረዶች ጆሯቸውን ቀጥ ያደርጋሉ። እሱ ስለመሆኑ ለአፍታ አይጠራጠሩም። አቶ ታረቀኝ ሲከፋው እዚች ዛፍ ስር መጥቶ ወንዙን በማየት ያሳልፋል። ስለ ወንዙም አብዝቶ በመጨነቅ ከአንድ ጊዜም ሁለት ጊዜ ለመገደብ ሞክሯል የወንዙ የውሃ ሙላት በጭቃ የለሰነውን ግድብ ይዞበት ሄደ እንጅ። አቶ ታረቀኝ በአንድ ነገር አብዝቶ ይጨነቃል ። ወንድ ልጅ እስካሁን አልወለደም እሱ የሱ ትልቅ ድክመት ነበር።ለሰዎች አብዝቶ የሚጨነቀውና ደጉ ታረቀኝ የብዙዎችን ጓዶችን ልጆች ክርስትና ቢያነሳም ወንድ ልጅ ግን አልታደለም። በዚህም የደስታ ማጣቱ ትልቅ ምክንያት ይሄ ነበር።
አቶ ታረቀኝ የሚሰማውን የባለቤቱን ጥሪ ችላ ብሎ አይኑን አሁንም ማዶ ላይ ተክሎ አንዳች ነገር የሚጠብቅ ይመስላል። ትከሻው ላይ ወዝ የጠገበችውን ብትሩን በቀኝ እጁ እያገላበጠ ከቆየ በኋላ መሬት ላይ እየቆረቆረ። " ምን አለ አሁን ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ እድሜየም እየጨመረ ነው። ምን አለ ደርሶ እንደሌላው ወጣት ሆኖ ባላየው እንኳ መልኩን አይቼ ብሞት። ኧረ ተው አምላኬ የወንድ መካን አታርገኝ። እንደው የስንቱን ቤት በወንድ ስትሞላው ምነው? የኔን ሴት ብቻ አድርገህ ወንድ ነሳኸው?" እያለ ፈጣሪን እየጠየቀም እየወቀሰም ተቀምጧል። ባለቤቱ ወይዘሮ አትጠገብ " ኧረ አንቱ ታረቀኝ!" በድጋሚ ተጣራች። እየሰማ ዝም ካላት በኋላ " ጀመራት ደግሞ ይቺ ጨቅጫቃ " አለ። " እንደው እኒህ ሰውየማ ችግር አለባቸው። እንደ ህፃን ልጅ ሰምተው እንዳልሰሙ ዝም ማለት ይወዳሉ።" አለችና " ሂጅና አባትሽን ጥሪውማ ማለፊያዬ ብላ የ10 አመት ልጇን አዘዘቻት። ማለፊያ እየበረረች ሄደችና " አባባ እታተይ እየጠራችህ ነው!" አለች። " ኤጭ ሂጅ ልቀመጥበት ምን ይቺ ተንከሲስ። ምን ቁምነገር ኑሯት ነው አሁን ና የምትለኝ። ብቻየን ተይኝ። ደስ ሲለኝ እመጣለሁ። ብሎሻል በያት።" አለና ማለፊያን ፊት ነስቶ ላካት። ማለፊያም ከወደ አባቷ የተሰጣትን መልዕክት ሳትጨምር ሳትቀንስ ለእናቷ ነገረቻት። " እህህ እንደዛ አሉሽ? እኒህ ሰውዬ ዘንድሮ የሚያደርጉት ጠፍቶባቸዋል። ቆይ ምን አድርጊ ነው የሚሉኝ? እሳቸው የማይፈልጉትን እኔ ሳልፈልግ ቀርቼ ነው? ጉድ እኮ ነው! " አለችና አልጋዋ ላይ ቀስ ብላ ጋደም አለች። አቶ ታረቀኝ ብዙ ከቆየ በኋላ ወደ ቤት መጣ። " እንደው ምን ሁነው ነው እየጠራዎት እንደ ልጅ ዝም የምትሉት?" አለች ወይዘሮ አትጠገብ በድርጊታቸው ተናዳ። " እንግዲህ አትጨቅጭቂኝ ለምን እንደፈለግሽኝ አሁን መናገር ትችያለሽ መጥቼልሻለሁ።አንቺ ደግሞ ጡል ጡል እያልሽ እናትሽ በላከችሽ ቁጥር ወደ እኔ አትምጭ።" አለ አቶ ታረቀኝ በመናደድ ወደ ማለፊያ ዞሮ። ይሄኔ ማለፊያ አለቀሰች። " ኧረ የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል።" አሉ ደግሞ ምን ሆንሽ? ገና ለምን ተናገረኝ ብለሽ ነው? ቆይ " አለና የእጁን ጣት ወደ ማለፊያ ቀሰረ። " ኧረ ምን ሁነው ነው እንደው እንዲህ ፀባዬዎ በየጊዜው የሚለወጠው? ወይ ችግር ካለ ያውጉንና እልባት እንስጠው!" አለች ወይዘሮ አትጠገብ በሰከነ መንፈስ። "ምንም አንቺ ጋር የምንነጋገረው ነገር የለም። በምንስ ጉዳይ ልናወራ እንችላለን ?? እ አንቺ ዝም ብለሽ ሴትሽን ሴት ሴት ልጅሽን ፈልፍይ። አራስሽን አብዢ!"አለ አቶ ታረቀኝ ወይዘሮ አትጠገብ እንደመደንገጥ አለችና " ኧረ እንደዚህ አይባልም። የእርሰዎም ልጆች እኮ ናቸው። ደግሞ ልጄ ሴትም ሆነ ወንድ የተባረከ ልጅ ይሁን ነው እንጅ የሚባለው ልጅ ከልጅ አይመረጥም። " " ኤጭ ይሄ ማስተባበያሽን ወደዛ በይልኝ! በይ አሁን የሚበላ ስጭኝና ወደ ዱሩ ልሂድበት።" " እሽ እንግዲህ ፈጣሪ ነው እንጅ የሚሰጠው እኔ መርጨ አልወልድ!" አለችና ወይዘሮ አትጠገብ በይ ማለፊያዬ በሌማቱ የሚበላ አቅርቢለት። ብላ ማለፊያን ስትመለከታት እያለቀሰች አየቻትና ደግሞ የምን ማልቀስ ነው?አባትሽ አይደል እንዴ የፈለገውን ቢልሽስ" ብላ ኮስተር አለችባት። አቶ ታረቀኝ የቀረበለትን ምግብ በልቶ ምንም ሳይል ወጥቶ ሄደ። " እታተይ ግን እስከመቼ ነው እንዲህ ለአንቺ መጥፎ አይን እና እኛን በጥላቻ አይን የሚያየን?" አለች ማለፊያ " ወንድ ልጅ እስክወልድለት ነዋ! " እንዴ እኔ እሱን ባገኘሁ ቁጥር እየፈራሁ አሁን ምን ሊለኝ ነው እያልኹ ተሳቀኩ እኮ እታተይ" አለች ማለፊያ " አዬ ማለፊያዬ አንቺስ ግማሹን ጊዜ ተማሪ ቤት ትውያለሽ። እህቶችሽና እኔ መከራችንን አይደል የምንበላ። " አለች ወይዘሮ አትጠገብ እንባዋ በአይኗ እየሞላ " እኮ እስከመቼ?" ማለፊያ ጠየቀች። ወንድ ልጅ እስክወልድ ነዋ! እንደው እሱ አንድየ ለዚህ ሰውዬ ሲል አንድ ወንድ ቢሰጠኝ ይሄን የያስኩትን ፅንስ ወንድ ያደረገልኝ እንደሁ ለሚካኤል ስለቴን አስገባለሁ። እንደው አንተ ቅዱስ ሚካኤል እባክህ ተራዳኝ። ያኔ የኒህ ሰውየ ፊት ይገለጣል።" አለችና " በእርግጥ እሳቸውም አበዙት እንጅ አይፈረድባቸውም። ከ አስራሁለት ልጅ አንድ ወንድ እንኳ አለመኖሩ ትንሽ ያስከፋል ። " አለች " እንዴ እና ታዲያ ለምን 22 አንሆንም አንቺ ፈልገሽ አላደረግሽው።" አለች ማለፊያ " እሱማ ልክ ነሽ ግን አባትሽ ይሄን አይረዱም። ለማንኛውም ይሄ የተረገዘ ልጅ ወንድ ሆኖ የቤታችን ሰላም እንዲመለስ ፀልይ።" አለች ወይዘሮ አትጠገብ። " አዬ እናቴ ልጁ ቤቱን ሰላም የሚያደርገው ይመስልሻል?" አለች " እህ አዎና እንዴት አይሆንም ብዬ ላስብ? " አለች " እሽ ይሁና እስኪ ሰንት ወርሽ ነው አሁን ታዲያ?" " አሁንማ እየተዳረስኩ ነው። በዚህ ወር መጨረሻ እወልዳለሁ! " አለች። ማለፊያ ፊቷ ላይ አምባ አልጠፋም አይኖቿ ቀልተዋል። በአባቷ በጣም የተናደደች ትመስላለች!!.......

ሼር
@monhappy
@monhappy

ለአስተያየት
@BINCJ90
:)
ትዝታ (ለፍቅር የተፅፈ ደብዳቤ)

በጉብዝናዬ ጊዜ ብዙ ደብዳቤ እንደፃፍኩልሽ አልዘነጋም… አሁን ቢሆን መች ተወኩት… በርግጥ እንደድሮ አደለህም ካልሺኝ እውነት ነው…

🌷 @monhappy 💐
💐 @BINCJ90 🌷
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፪~ (2)

አመሻሽ ላይ ሁሉም የቤተሰቡ አባል ባለበት የእሳት ዳር ጨዋታውና ተረቱ ለጉድ ነው። ወይዘሮ አትጠገብ በልጆቿ ፊት ላይ የምትመለከተውን ደስታ እያየች ትስቃለች። አቶ ታረቀኝ በሀዘን የቤቱ ታዛ ስር ተቀምጦ መሬቱን በያዘው በትር መታ መታ እያደረገ ሰማዩ መሀል ክፍል ላይ የወጣችውን ግማሽ ጨረቃ ይመለከታታል። ጨለማ ለአይን እየነሳ ነው ሁሉም አባወራ በየ ቤቱ ገብቶ ወሎውን ለልጆቹና ለባለቤቱ በመተረክ ላይ ነው። ከተቀመጠበት ድንጋይ ብድግ ብሎ በትሩን የቤቱ ደጃፍ ላይ አስቀምጦ ወደ ውስጥ ገብቶ የመደብ አልገው ላይ ተቀመጠ። የሚሰማውን የልጆቹን ጨዋታ ና ሳቅ " እስኪ ቀስ ብላችሁ ተጫወቱ ምን የሴት ቤት ልታስብሉት ነው? ድምጣችሁ እኮ ማዶም ይሰማል። ደግሞ ለሰው አፍም ጥሩ አይደለም። የሴት መንጋ ትባላላችሁ። በልኩ አርጉት " አለና ጨዋታቸው ላይ ውሃ ቸልሶበት አልጋው ላይ ጋደም አለ። ሁሉም እርስ በርስ ተያዩ በጣም ተናደዋል። በአባታቸው የእለት ተዕለት ጠባይ ሲበዛ እየተበሳጩና እየጠሉት ነው። ሁሉም ወደየ ማደሪያቸው ተበታተኑ። ማለፊያ ከአድና ጋር ሌሎቹም ሁለት ሁለት ሁነው ተኙ። " አሁንስ ይሄ ሰውየ እንደው ምን መሆን እንደፈለገ አልገባኝም። በየቀኑ እያስጠላኝ ነው። ልጆቹ እኮ አንመስለውም። በእርግጥ የክርስትናችንም አልተገኘም። እኛ እኮ አባታችን የሞተው ያኔ ነው። በየቀኑ ጥላቻየ እየጨመረ ነው የሚሄደው መቼም ይሄን ሰውየ ልወደው አልችልም " አለች። " እኔም እንደ አንቺ ነኝ እኮ እኛ ያለውን ጥላቻና ንቀት ሳይ ግደይው ግደይው ይለኛል።" አለች አድና ሁሉም እህታማቾች የተለያየ ባህሪ ቢኖራቸውም በአባታቸው በአቶ ታረቀኝ በኩል አንድ አይነት የጥላቻ ባህሪ አላቸው። " ለምን ግን እንደልጅ አያየንም? እየተባባሉ ሁሉም ልጆች እርስበርስ ያወሩ ጀመር። የመንደሩ ሰዎች ስለ አቶ ታረቀኝና ልጆቹ በሰፊው ያወራል። የቡና መጠጫ አድርገውታል። አቶ ታረቀኝም ባለፈ ባገደመ ቁጥር አሽሙሩ ለጉድ ነው። " ከሴት በቀር ሌላ መውለድ አይችልም። ዘሩ አንድ ብቻ ነው "እያሉ ያሙታል። አቶ ታረቀኝም ይሄ ሽሙጥና አሽሙር መከራውን አብልቶታል። ለዚህም እሷ መርጣ የምትወልድ ይመስል ሰርክ ወይዘሮ አትጠገብ ላይ እልሁን የሚወጣው። ወይዘሮ አትጠገብም ሁሉን ነገር ችላ የተቀመጠችው ለነገ ነው። ነገ የተሻለ ይሆናል ሁሉም ነገር ይስተካከላል። ይሄ ለሁለት የተከፈለው ቤተሰብም አንድ ይሆናል። የሚያጣላን ወንድ ልጅም ተወልዶ ያስታርቀናል በሚል የተስፋ ጭላንጭል ነው። ወይዘሮ አትጠገብ ልትወልድ ተቃርባለች። ልጆቿ በቂ የሆነ ዝግጅት እያደረጉላትም ነው። አቶ ታረቀኝም በዝግጅቱ ላይ ለሌላዋ ሴት ልጅ ዝግጅታችሁ አሪፍ ነው። መብዛታችሁ ጥሩ ነው ለሁሉም ነገር ለሰሚውም ለምኑም" በማለት ተሳለቆባቸው። ትቷቸው ወጣ። " ቆይ የሚወለደው ልጅ ወንድ ቢሆንስ ምን ሊሆን ነው ይሄ ሽማግሌ?" አለች አድና " እህ ምን ይሆናል? ያው በልጁ ምክንያት የኛንም ልጅነት ያምንና ጥሩ ቤተሰብ እንሆናለን!" አለች ማለፊያ እየሳቀች። አመሻሽ ጀንበር ወደ ታች ስታዘቀዝቅ ወይዘሮ አትጠገብ ምጥ ተያዘች። ይሄኔ አረኛውም ገበሬውም ወደ ቤት በመክተት ላይ ነበር። ሁሉም ጎረቤት የወይዘሮ አትጠገብን ምጥ መያዝ ሰምቶ ወደ ቤታቸው ተመመ።ገሚሱ ምን እሷ ሴት ነው የምትወልድ ባሏ ራሱ በሌለበት ምን አካሄደን እያሉ ይቀሩ ነበር። ግማሾቹ ደግሞ" ኧረ ነግ በኔ " ይደርሳል እያሉ ሄዱ። የነ አቶ ታረቀኝ ጎጆ በሰው ተሞላ ደጁ ሁሉ ሰው ነበር። ሁሉም በአንድ ላይ " ማርያም በሽልም ታውጣት " እያሉ ይፀልዩላት ጀመር። ምጡ እየጠናባት ሄደ። ከተለመደው የአወላለድ ምጥ የተለየ ሆነ ። የጎረቤት ሰዎችም ሁኔታው ለየት ሲልባቸው " ወንድ ነው ማለት ነው?" እያሉ እርስበእርስ መተያየት ጀመሩ። " ኧረ በጭራሽ እሷማ ወንድ አትወልድም በታዕምር እስካሁን ያልወለደችውን ከየት ታመጣዋለች?" ትላለች አንዷ ጎረቤት " ኧረ ባካችሁ እንዲህ አይባልም የፈለገው ቢወለድስ ምን እሷ መርጣ አችወልድ የማሰጣቴ እሱ እእግዚአብሔር ነው። ሆሆሆሆ ተው እንዲህ አይባልም ሰዎች " አለች አንደኛዋ " ወይዘሮ አትጠገብ ለምጥ እንደተንበረከከች አዋላጇም እኩል ከአትጠገብ ጋር ከላይ ከታች እንዳለች እኩለሌሊት ተጋመሰ አቶ ታረቀኝ የቤቱ ታዛ ደጅ ላይ ሆኖ ሁኔታውን ዝም ብሎ ይከታተላል። ሰው እየቆየ እየጨመረ ሄደ ቀዬው ደጁ በሰው ተትረፈረፈ። ወይዘሮ አትጠገብ አይኖቿ እየተስለመለሙ ሄዱ ምጡን መቋቋም አልቻለችም። ሰውነቷ እየዛለ ሄደ ደክሟታል። አዋላጇ " አይዞሽ ግፊ አዎ ትንሽ አይዞሽ ጨክኚ አይዞሽ " እያለች ታስምጣታለች። ነገር ግን ወይዘሮ አትጠገብ የቻለች አትመስልም። አንዷ ጎረቤት " ይሄ ፅንስ ያለ ጊዜ መጥቶ ይሆን እንዴ ወይዘሮ አትጠጠብ እኮ እንዲህ ይሄን ያህል ጊዜ አምጣ አታውቅም?" አለች። " ኧረ እንደው እንጃ ባለፈው ገበያ አግኝቻት ግን ቀኗ በዚህ ወር ማብቂያ እንደሆነ ነው የነገረችኝ " አለች ሌላኛዋ። እንዲህ ሰው የየራሱን መላምት እያስቀመጠ ሌሊት እየተገባደደ ሊነጋጋ ወፍ ጭጭ ሲል ወይዘሮ አትጠገብ ፅንሷን ተገላገለች። አድካሚው የምጥ ጊዜዋ ህፃን ጩኸት ተገባደደ ሁሉም በአንድ ላይ እልልል አሉ። አዋላጇም ቶሎ ብላ የህፃን ፆታ ተመለከተች እሷም በሀሴት ዘለለች። "አባ ታረቀኝ እንኳን ደስ አለዎት ባለቤትህ ወንድ ልጅ ተገላግላለች።" አለች መንደርተኛው በአንድ ላይ እልልታውን አቀለጠው። አቶ ታረቀኝም በሀሴት አለቀሰ። " ፈጣሪየ ልመናየን ሰማ ማለት ነው? " አለ። እነ ማለፊያ አድና በለጡ የኋላነሽ ሁሉም ሴት ልጆች ሁኔታውን በየ አልጋቸው ሆነው ይመለከቱ ነበር። በመጨረሻም ህፃኑ ወንድ ነው ሲባል የአባታቸውን አኳኋን ተመልክተው በሸቁ። አንዳቸውም ሲወለዱ ምንም ሳይል አሁን ወኔድ ነው ሲባል የሚሆነውን ተመልክተው በንዴት በእልህ ከንፈራቸውን ነከሱ። በበነጋው ቤቱ በጠያቂ ተሞላ አቶ ታረቀኝንም እንኳን ደስ አለህ የሚለው ሰው ቁጥር በዛ።እሱ ሴት እንጅ ወንድ አይወልድም ያሉ አፈሩ። መጥተውም የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት አስተላለፉለት።

ሼር
@monhappy
@monhappy

ለአስተያየት
@BINCJ90
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፫~ (3)


በአቶ ታረቀኝ ቤት የነበረው የኩርፊያና የዝምታ አሁን በፌሽታና በደስታ ተሞልቷል። ሁሉም ሰው እየመጣ ደስታውን እየገለጠ ይሄዳል። አቶ ታረቀኝም ገና ህፃኑን ልጅ በአራስነቱ ከነ ደሙ እያነሳ ያቅፈዋል። በዚህ ጊዚ እነ ማለፊያ ና አድና እጅግ መናደድ ጀመሩ። አቶ ታረቀኝ ለደስታው ማካሄጃ የሚሆን ሁለት ፍሪዳ በሬ ጥሎ ዘመድ ጎረቤቱን ጠርቶ ደስታውን ማካፈል ጀመረ። ማለፊያ እና እህቶቿ አጉረመረሙ አድና ቀድማ እንዲህ " እኛ ስንወለድ አይደለም በሬ ዶሮ ራሱ አላረደልንም ነበር። ይገርማል ለካ እኛ ትርፍ ልጆች ነን" አለች ። ማለፊያ ቀጠለችና " አዎ አሁን ሁሉም ነገር ተገለጠልኝ " በማለት ከንፈሯን ነክሳ ራሷን አወዛወዘች። ሁሉም ሴቶች አቶ ታረቀኝን በንዴትና በጥላቻ ተመለከቱት። ለአቶ ታረቀኝ የመጨረሻ ማለትም በቅርብ ለተወለደው ህፃን ስም ለማውጣት ሁሉም ከየስራው ሲመለስ ማታ ላይ ከእራት በኋላ ቤተሰቡ ጉባኤ ተቀመጡ። ሁሉም ሴት ልጆች አውጡ ሲባሉ በአንድ ድምፅ " እኛ አናወጣም " አሉ ወይዘሮ አትጠገብ " ምንተስኖት " አለች ። አቶ ታረቀኝ ደግሞ " ቀዳማዊ " አለው በዚህን ጊዜ እነማለፊያ ከእንደገና በ አባታቸው ስም አወጣጥ በሸቁ። " ምን ማለት ነው ቀዳማዊ ? እኔ የበኩሯና የመጀመሪያዋ እያለሁ" አለች ርብቃ ። እህቶቿም በአነጋገሯ ተሳሳቁ።
እንዲህ እንዲህ በማለት ቀናቶች ተቆጠሩ የቀዳማዊ የክርስትና ቀንም የሰርግ ቀን እስኪመስል ድረስ በዳስና በድንኳን በጎረቤትና በዘመድ እንዲሁም በሹማምንቶች ተከበረ። ይህ የክርስትና በዐል ሳይሆን የሰርግ በዐልም ነው ተብሎ በተጠሪዎች አፍ የድግሱና የበዐሉ ስፋት ተሞካሸ። ከክርስትናው ቀን በኋላ ግን የቤቱ ሰላም በታሰበው መልኩ አልሄድ አለ። ወንድ ልጅ ሲወለድ ቤቱ ይስተካከላል ተብሎ ቢታሰብም ከመጀመሪያው በላይ አስቸጋሪ ሆነ። አሁንም በሴት ልጆቹና በሱ መሀል ያለው ፀብና ጥላቻ እየከረረ ሄደ። ወይዘሮ አትጠገብም ከሴት ልጆቿ ጋ ሆና የአቶ ታረቀኝን ልብ ቁም ስቅሉን አበሉት። ምነው ወንድ ልጅ ባልወለድኩ ብሎ እስኪማረር ድረስ አሰቃዩት። እድሜውም እየሄደ ነበርና የነሱን ንዝንዝና ጭቅጭቅ መቋቋም አልቻለም። ህፃኑ ቀዳማዊ ሁለት አመት ሞላው። አንድ ቀን አቶ ታረቀኝ ከወደ ጫካ ቆይቶ ሲመጣ ህፃኑ እያለቀሰ ያገኘዋል። እናቱ ወይዘሮ አትጠገብ አጠገቡ አልነበረችም። ትታው ወደ መንደር ቡና ለመጠጣት ሄዳ ነበር። ቤት ውስጥ ማንም አልነበረም። በዚህን ጊዜ " አይ ፈጣሪዬ ልትቀጣኝ ነው አይደል ወደ ማምሻ እድሜዬ እንዲህ መከራየን የምታበላው " አለ ቀዳማዊውን አቅፎ። ቀዳማዊ ማልቀሱን ቀጠለ። ሊያባብለው ሞከረ አልቻለም ህፃኑን ተመለከተው። እንባዎች ይወርዳሉ ተንሰቅስቆ ያለቅሳል። ምን እንደሚያደርግ ግራ ገባው አነሳውና አዘለው። ነገር ግን አሁንም ማልቀሱን አላቆመም። የላም ወተት ቅሉ ላይ ነበርና እሱን አውርዶ አጠጣው። ለቅሶውን ገታ አድርጎ ወተቱን ማጣጣም ጀመረ። በዚህ ጊዜ የአቶ ታረቀኝ አይኖች እምባ አቀረሩ። አንጀቱ ተላወሰ። " ምን አለ ቀደም ብለህ ብትመጣ በብቸኝነት ስሰቃይ ምን አለ በወጣትነቴ መጥተህ አብረን ብናድግ" በማለት ልፃኑን ያወራዋል። በዚህ ጊዜ ከስንት ስአት በኋላ ወይዘሮ አትጠገብ መጣች። " እንዴት ባዶ ቤት ልጁን ትተሽው ትሄጃለሽ?" አለ አቶ ታረቀኝ " ምን ይሆናል? ምነው ለልጁ እኔ ብቻ ነኝ የማስበው አልክ እኔም እኮ እናቱ ነኝ አስብለታለሁ አታብዛው እንጅ" አለች እንደስከዛሬው አንቱ ሳትል ።ይሄኔ ነበር ያለው ለውጥ በሙሉ የተገለፀለት። ምንም ሳይል ወጥቶ ወደ ተራራው ሄዶ ተቀመጠ። ማታም ምንም እህል ሳይበላ ምን ሳይል አደረና በጠዋት የቀበሌውን ሹማምንቶች ጠርቶ " ሁሉም ንብረቴ መሬቴ ገንዘቦቼ በሙሉ በልጄ በቀዳማዊ ስም ሁሉም በሱ ስም እንዲሆንልኝ እፈልጋለሁ።" አለ አቶ ታረቀኝ " በጭራሽ ሁሉም ልጆቼ አንድ ናቸው አንዳቸውን ከአንዳቸው መለየት አልፈልግም። በሁላቸውም ስም ነው መሆን ያለበት " አለች ወይዘሮ አትጠገብ አቶ ታረቀኝም " በእኔ ስም ያለውን በፈለኩት ስም የማድረግ መብት አለኝ " አለ የቀበሌው ሹምም " አዎ አቶ ታረቀኝ ያለው ልክ ነው። ያው በጋራ ስም ያላችሁን ንብረት በሁሉም ስም እናደርጋለን። ነገር ግን በሱ ስም ያለውን እሱ ለፈለገው ሰው የማድረግ መብት አለው በእሱ መብት እኛ ጣልቃ አንገባም። " አለ የስም ዝውውሩ ተጠናቀቀ። ሁሉም ንብረት ማለት ይቻላል በቀዳማዊ ስም ሆነ። " ከዚህ በኋላ ለእኔ ብለሽ ሳይሆን ለራስሽ ብለሽ እ እነዛ ልጆችሽም ለእኔ ብለው ሳይሆን ለራሳቸው ሲሉ ይህን ህፃን በጋራ ይንከባከባሉ ትንከባከባላችሁ!!" አለ ወይዘሮ አትጠገብ ተናደደች። ሁሉንም ነገር የተፈጠረውን ነገር ለልጆቿ ነገረቻቸው። " እና ሁሉም ሀብት በቀዳማዊ ስም ሆነ እያልሽ ነው?" አለች ማለፊያ " አዎ ልጄ እኔ ማድረግ የምችለውን ሁሉ አድርጊያለሁ። ህጉም እሱን ነው የደገፈው ማለትም ህጉ የሚለውም እንደዛ ነው።ምንም ማድረግ አልችልም " አለች ወይዘሮ አትጠገብ " ህህህህ ኧረ ነው 12 ሴት ባለበት ቤት ሁሉም ንብረት በአኔድ ሰው ሊሆን ?? ሃሃሃ" አለች አድና ሌሎቹም አብረዋት ራሳቸውን ነቀነቁ። " ይህ ሲሆን ቆሜ አላይም ማድረግ ያለብኝን በሙሉ አደርጋለሁ" አለች ርብቃ " ምን ልታደርጊ ነው?" አለች አትጠገብ " ምን እንደማደርግ ለእኔ ተይው ሁሉንም ነገር በእኔ ጣይው የማደርገውን ጠንቅቄ አውቃለሁ አታስቢ እናቴ " አለች ርብቃ
አቶ ታረቀኝ የባለቤቱ እና የልጆቹ ነገር ካስጠላውና የጎሪጥ መተያየት ከጀመሩም ሰንበትበት ብለዋል። " መቼም እኔ እያለሁ እንዲህ ካደረጋችሁት ስሞትማ አብራችሁ ከእኔ ጋር ወደ መቃብር ነው የሚጥሉት አይ የኔ ልጅ ቀዳማዊ ምን አይነት እጣ ና እድል ይኖርህ? " አለ ና የወንድሙን የአቶ ደሳለኝን ልጅ በቀለን ጠርቶ እንዲህ አለው " ልጄ በቀለ መቼም አንተን ከልጄ እኩል ነው የማይህ በስተመጨረሻም ቢሆን ወንድም ሰጥቼሀለሁ ከእንግዲህ ለእኔ ሳይሆን ለአንተ ነው የሚጠቅምህ ተንከባከበው። አሁን ያለውን የቤት ጉዳይ መቼም አላጣኸውም። ይሄን ልጅ አንድ እንዳያደርጉብኝ ብየ እፈራለሁ። ለትምህርት እንደደረሰ ትምህርት ቤት አስገባልኝ የተማረ የተመራመረ ልጅ እንዲኖረኝ ነው የኔ ህልም እና የዚህን ልጅ አደራ የምሰጠው ለአንተ ነው። አደራየን የበላህ እንደሁ በኋላ በሰማይ እጠይቅሀለሁ! ልጄ እኔ መሄጃየ እየደረሰ ነው። አደራ አደራ አደራ " ብሎ በቀለን ቃል አስገብቶት ተለያዩ። ከእሱ እንደተለየ ተመልሶ ወደቤት መደቡ ላይ አረፍ አለና ወይዘሮ አትጠገብን ጠርቶ " እኔ እንግዲህ መሞቻየ ደርሷል ጥላቻውን ትተሽ ልጆቹን አስማሚያቸው። እንግዲህ ያሻሽን አድርጊ ሁሉም በአንቺ እጅ ናቸው። ይሄን ልጅ ግን አንድ ነገር ቢሆን እኔ ሳልሆን ፈጣሪ በሰማይ ይጠይቅሻል። ልክ ለትምህርት እንደደረሰ 7 አመት ሲሞላው ተማሪ ቤት አስገቢልኝየቄስ ትምህርትም ይማር።" አላትና ጋደም ብሎ ምንም ሳይታመም እስከወዲያኛው አሸለበ። አቶታረቀኝ ላይመለስ ሄደ። ቤቱ በለቅሶና በዋይታ ተሞላ..........

ሼር ላልደረሳቸው ኤሴቅን ለወዳጆ
@monhappy

ለአስተያየት
@BINCJ90
" ኤሴቅ "
ክፍል ~ ፬~ (4)



ሁሉም ዘመድ አዝማዱ ከያለበት የአቶ ታረቀኝ ማረፍ ተነግሯቸው መጡ። ቀብሩም በብዙ ፈረሰኞችና ሙሾ አውራጆች ተካሄደ። የአቶ ደሳለኝ ልጅ በቀለ ለያዥ ለገናዥ አስቸገረ " አጎቴ ምነው? ገና በጠዋት ምነው ልጅህን በውል ሳታየው? አጎቴ " እያለ ስለ ቀዳማዊ እጣ ፈንታ ጮክ ብሎ ያለቅሳል። ሁሉም ሰው በበቀለ አለቃቀስ አንጀቱ ተላወሰ።
ሙሾ አውራጇም እንዲህ ብላ ተቀኘች

"ታረቀኝን ታርቀህ ወንድ ልጅ ሰተኸው፣
ምን አል ወደ ማታ ልጁን ሲቆም ሳያይ በጠዋት የወሰድከው።"

ብላ ስትገጥም ሀዘንተኛው "ዋኣኣኣኣኣ" አለ። በዚህ መልኩ ቀብሩ ተፈፅሞ ሀዘንተኛውና መከረኞቹ ወደየ ቤታቸው ተመለሱ። ሀዘንተኞች ከቀብር ተመልሰው ወደ ቤት ሲሄዱ ህፃኑ ቀዳማዊ የአባቱ ቀብር መፈፀሙንና አባቱ መሞቱን ያወቀ ይመስል ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል። እናቱም ሀዘንተኞቹ እና የሚያዋይዋት ሰዎች ጋር ነበረችና ከቁብ አልቆጠረችው። አንድ ለቀስተኛ የልጁን የመረረ ለቅሶ በደንብ ካዳመጠ በኋላ "ይሄ ልጅ መናጢ ፉግር ልጅ ነው። አባቱን ገደለ አሁን ደግሞ ሌላ መከራ ሊያመጣ ነው? አለቃቀሱ ጥሩ አይደለም " አለ በቀለ ይሄኔ ሰውየውን በደንብ ገላምጦ ተመለከተው።
*
ቤቱ ውጥንቅጡ ወጣ "አባወራ የሌለበት ቤት ወትሮም እንደዚህ ነው። " እስኪባል ድረስ ቤቱን የሚመራ ተለቅ ያለ ወንድ ልጅ እንኳ የሌለበት ቤት አቶ ታረቀኝ በድንገት ሲሄድ ለመውደቅ መንገድ ለመጀመር እየተንገዳገደ ይመስላል። ወይዘሮ አትጠገብ የምታደርገው ምን እንደሆነ ምን ማድረግ እንዳለባት ራሱ አልመጣልሽ አላት። የሚመጣው ወር ደግሞ የእርሻ ወቅት እንደመሆኑ ጠምዶ የሚያርስ ያስፈልጋል። ይሄን ማድረግ የሚችል ወንድ ልጅ ደግሞ የለም። ስለዚህ ያላት አማራጭ ደግሞ ገበሬ መቅጠር ነው። ገበሬ እንዲያፈላልግላት በቀለን ነገረችው። ከብዙ አድካሚ ፍለጋ በኋላ ገበሬ ተገኘ። ለእሱም በሲሶ እህል ክፍያ ተስማምተው መስራት ጀመረ።
እነ ማለፊያና እና አድና ባገኙት ቁጥር ህፃኑን ቀዳማዊን ማስለቀስ የእለት ተእለት ተግባራቸው ከማድረግም ባሻገር ለቅሶውን የደስታቸው ምንጭ ካደረጉት ሰንበትበት ብለዋል። ይሄ ነገር ምንም የማይመስላት ወይዘሮ አትጠገብ ተግባራቸውን እያየች እንኳ " ተው እንዲህ አታድርጉ" በማለት አትገስፃቸውም ነበር። ይልቅስ እነሱን በመቆጣት ፈንታ " ምን ይሄ ገፊ አባቱን ገፋ ደግሞ እኔን ሊገፋ ነው?" በማለት በህፃኑ ቀዳማዊ ትናደድበት ነበር። የልጁ የእለት ተእለት ለቅሶ ያስፈራቸው አንዲት ጎረቤት ወይዘሮ አትጠገብን ጠርታ እንዲህ አለች።" ተይ ልጄ ይሄ ህፃን ልጅ ነው ምነም በማያውቀው አታስለቅሱት አልቅሶ እንዳይሞትብሽና በኋላ የወንድ መካን እንዳትሆኝ " ትላታለች። ወይዘሮ እልፍኝ። ወይዘሮ አትጠገብም የወይዘሮ እልፍኝን ምክር ችላ ብላ በማለፍና በመሳለቅ ተግባሯን በዛው ቀጠለች። ይባስ ብላ ጡት እንኳ ገና በውል ምግብ መብላት ሳይጀምር ነበር ያስቆመችው። ይሄን ድርጊቷን ያዩ ጎረቤቶችም በግርምት ያይዋትና ይታዘቧት ነበር። በእንዲህና በአስቀያሚ ሁናቴ አልፎ ቀዳማዊ የስድስት አመት ልጅ ሆነ።
***
ቀዳማዊ ስድስት አመት እንደሞላው በበቀለ ጎትጓችነት የአስኮላ ትምህርት ቤት ተመዘገበ። ምንም እንኳ ለትምህርት ብቁ የሆነ አእምሮ ላይ ባይገኝም ግን በልጅነቱ መግባት እንዳለበት ስላመነ ና የአቶ ታረቀኝን የሙት ኑዛዜ ለማክበር ሲል ነው በቀለ ወደ ትምህርት ቤት እንዲገባ ያደረገው። የቀዳማዊ የግማሽ ቀን ውሎ ትምህርት ቤት ሆነ። ከትምህርት ቤት ሲመለስ ከብቶቹን ፍየሎቹን እንዲሁም በጎቹን እንዲጠብቅ ወደ በረሃ ይላካል። እድሜው ለከብት ጥበቃ ባይደርስም በእህቶቹ ጫና ይጠብቅና ያግድ ነበር። ማታ ላይ ከብቶቹን ወደ ቤት አስገብቶ ደግሞ ውሃ እንዲቀዳ ይታዘዛል። ውሃውን አልቀዳም ቢል ምን ሊከተልበት እንደሚችል ስለሚያውቅ እሽ ብሎ ሊቀዳ ወደ ወንዝ ይወርዳል። እንዲህ እያለ ቀኑን ሙሉ ሲባክን ውሎ አዳር ደግሞ የአብነት ትምህርት ለመማር ወደ መርጌታ የሸዋ ስላሴ ቤት ይሄዳል። እዛ ውዳሴውን ሲደግም ሲያጠና ያድርና በጠዋት ደግሞ ወደ አስኮላ ትምህርት ቤት ሄዶ የፊደል ገበታ ላይ ይጣዳል። የአብነት ትምህርቱ በቃል ስለሆነ የሚያጠኑት ለመያዝ አልተቸገረም ይሄኛውን ግን ፊደሎቹን ለመያዝ ለትንሽ ጊዜ ተቸገረ። ውጤቱም ዝቅ ያለ ነበር። የአንደኛ ክፍል ውጤቱም ከክፍሉ ተማሪዎች የመጨረሻ ደረጃ ላይ ነበር የተቀመጠው። ታዲያ ይሄን ደረጃ የተመለከተችው ማለፊያ " ደደብ ድሮስ እንደ እኔ ጎበዝ መሆን አምሮህ ነው ትምህርት ቤት የገባኸው? እንደኔ መሆን ያምርሃል እሽ? ጅል አየህ ማንንም አልበለጥክምኮ አንድም ሰው አልበለጥክም።" በማለት ካርዱን ፊቱ ላይ ጣለችበት። እናቱ ወይዘሮ አትጠገብም ደረጃውን በማየት " ይሄኔ በነገር ቢሆን የሚያህልህ አይኖርም ነበር።" በማለት ሰደበችው። ሁሉም ሴቶች እህቶቹ አንድም ሳይቀሩ በስድብ ተረባረቡበት። ህፃኑ ቀዳማዊ ሆድ ባሰው አለቀሰ " ምን ሆንክ ደግሞ የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል አሉ " አለችና ወይዘሮ አትጠገብ እስኪበቃው ገረፈችው። " መጨረሻ ወጥተህ እንኳ አልመታውህም እ ደግሞ በላይ እንደገዳይ ለምን እንዲህ አሉኝ ነው?" አለች በለበቅ እስኪበቃው ገረፈችው " እስኪ የት አባህ? " አሉት እህቶቹ በአንድ ድምፅ!! እንባውን ጠራርጎ የሚለብሳትን የሌት ልብስ ለብሶ ወደ መርጌታ የሸዋ ስላሴ ሄደ። መርጌታ የሸዋ የቀዳማዊን አይን ሲያይ ልክ አይደለም። " ምነው ልጄ ቀዳማዊ ምን ሆነሀል?" አለ ቀዳማዊም እንባወቹ ያለቅጥ እየወረዱ " ምንም መርጌታ " አለ ቢናገር የሚከተለውን ስለሚያውቅ " ተወው ልጄ እሱን እንኳ መች የሆንከው ጠፍቶኝ ከአንተው ልስማው ብየ ነው እንጅ" አለ " ለመሆኑ ምን አድርግ ነው የሚሉህ?" አለ " እንጃ አባ እኔ ምን አውቃለሁ ከሳኩም ካለቀስኩም ዱላ ነው። ስበላም ስጠጣም ግልምጫ ነው። እኔ ወዴት እንደምሄድ ነው ግራ የገባኝ የምሄደው እኮ ዝም ብየ ነው። እንጃ እንዴት እንደማደርግ ከብዶኛል አባ " አለ ቀዳማዊ እምባው ከንግግሩ እየቀደመ። " በል አይዞህ ልጄ ሁሉም ነገር ይስተካከላል። የሚሆን ሁነኛ መፍተሔ እናበጃለን።ለጊዜው ከእኔ ጋር ለትንሽ ጊዜ ትቆያለህ" አለ መርጌታ የሸዋ " ኧረ መርጌታ አይሆንም በኋላ ይገሉኛል።" አለ ቀዳማዊ በፍርሀት የመርጌታን አይኖች እየተመለከተ። "አይዞህ ምንም አይፈጠርም ልጅ ቀዳማዊ " አለና አባበለው የዛኑ ቀን አድሮ ጠዋት ወደ ትምሀርት ቤት ሄዶ ተመልሶ እሱ ጋ ውሎ ማታ ለትምህርት ተቀመጠ። በዚህ ጊዜ ወይዘሮ አትጠገብ መጥታ " መርጌታ ቀዳማዊ እዚህ ነው ያለው?"አለች " እንዴት ውለሽ አደርሽ ወይዘሮ አትጠገብ?" አለ መርጌታ የሸዋ በቅድሚያ ሰላምታ እየሰጣት " ደህና እግዚአብሔር ይመስገን " አለችና ወደመጣችበት ጉዳይ ገባች። " አዎ ትንሽ የምትሰራ ነበረችኝና እሷን እያሰራሁት ነበር "አለና " እንዴት ነው ቃልሽን እየጠበቅሽ ነው? አቶ ታረቀኝ ሲያርፉ እኮ ብዙ ቃል አውግዘዋል ለአንቺ!" አለ ወይዘሮ አትጠገብ ፈጠን ብላ " አዎ መርጌታ! ለዛሬ እኛ ጋ ይደር ልውሰደው አለችና ቀዳማዊን ጠርታ ወሰደችው።
" ደግሞ ስሜን ማብጠልጠል ጀመርክ? እ መቼም ምንም ሳትለው እዛ አያውልህም? " አለችና ጠፈሯን አውረዳ ከላይ የለበሰውን ሹራብ አውልቃ ጀርባውን እስኪበቃው ገረፈችው። ጀርባው ላይ ደም ችፍ አለ። ለሳምንታት በልቡ ተደፍቶ ተኛ። ጎኑም በከፍተኛ ሁኔታ ያመው ስለነበር። በሆዱ ብቻ ለመተኛ
ግን እሱ የተመሰገነ ይሁን…ወድቀን አልቀረንም…ተነስተን መንገዳችንን ቀጥለናል…እኔ እና አንቺ…መውደቅን ስለምናውቅ በመደቁት አንፈርድም…

✍🏾 @monhappy ✍🏾
👫 @BINCJ90 👫
#happy 🤵🏽
" ኤሴቅ "

ክፍል ~ ፭ ~ (5)




ቀዳማዊ በሁለተኛው አመት የትምህረት ዘመን ጅማሮ የተለየ ተማሪ ሆነ። ክፍል ውስጥ በሚገርም ሁኔታ መንቀሳቀስ ጀመረ። በመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ላይ ከክፍሉ አንደኛ በመውጣት ወደ ሁለተኛ ክፍል በሲሚስቴር አለፈ። ሁለተኛ ክፍል ሁለተኛ ሲሚስተር ላይም አንደኛ ወጣ። ሰኔ ሰላሳ ላይ አጠቃላይ ከሁለተኛ ክፍል አማካይ አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነ። ወሬው ሁሉ ቀዳማዊ ብቻ ሆነ። " አቤት ልጅ አቶ ታረቀኝማ ቢሞትም አይቆጨው ነቭር የሆነ ልይ ወልዷል። ስሙን ያስነሳዋል። ኧረ እሱ አልሞተም ። እንግዲህ የተመረቀ ልጅ ከወደ ማታ ነው ሚመጣው።" እያሉ ቀዳማዊይን ያሞካሹታል። በመሸለሙ በመወደሱ እርር ድብን ያሉት እህቶቹ የተሸለመውን ደብተርና እስክርቢቶ ማታ ላይ ተከፋፈሉት ። አምጡ ብሎ ሊቀበላቸው አልቻለም። እናቱን ቢጠይቃት እንኳ " ምን ይሰራልሀል እነሱ ሰባትና ስምንት ናቸው አንተ ገና ሁለተኛ ክፍል ነህ ምን ችግር አለ ቢወስዱት" የሚል መልስ እንጅ ሌላ ምላሽ አልሰጠችውም። ወይም ባመጣው ውጤትና ሽልማት አላበረታታችውም። እነ ማለፊያም ሆነ አድና እንደዚህ እንዳልተሸለሙ ታውቃለች። ያለችውን ተቀብሎ አርፎ ተቀመጠ። ምክንያቱም ከዚህ በላይ ከጠየቀ የሚከተለውን ያውቃልና ትቶ ዝም አለ። ሶስተኛ ክፍል ላይም አንደኛ በመውጣት ደብል ወደ አራት አለፈ። አራተኛ ክፍል ሁለተኛ ሲሚስቴርም የሁተተኛ ክፍል ሁለተኛ ሲምስቴር ታሪኩን በመድገም ተሸላሚ ሆነ ።አገሬው በሙሉ ወሬው ስለ አቶ ታረቀኝ የመጨረሻ ልጅ ቀዳማዊ የትምህርት ጀግንነት ሆነ። " ኤዲያ አየ ልጅ ይህ ነው እንጅ ልጅ ማለት ጀግና ነው። አይ አቶ ታረቀኝ ብታየው ምን አለ አሁን። ፐፐፐ ጥጥት አደረገው እኮ ትምህርቱን። ደግሞ እኮ በሁለት አመት ውስጥ አራተያ ክፍል ደረሰ።" እያሉ ያወሩ ጀመር። ከቤት ሙገሳና አድናቆት የማይሰጠው ቀዳማዊ ክብሮቹን ተጎናፅፎ ወደ ቤት በደስታ ሲመጣ ከእናቱና ከእህቶቹ ጀርባ የሚሰጠው ቀዳማዊ በጎረቤትና በየሄደበት አድናቆት ይቸረዋል። ትልልቅ ሰዎችም ሲያገኙት " አዬ አባትህ ይሄን ጀግንነትህን ቢያይ ኑሮ አየ ጉድ ፐ ምንኛ ደስ ይሰኝ ነበር። እሱም እንዴት ያለ ጎበዝና ጀግና ነበር መሰለህ። ህልሙ ወንድ ልጅ ወልዶ ለቁምነገር ማየት ነበር። ነገር ግን አልታደለም አንተም ዘገየህ። ሲመሽ ወደ ዱሩ እየብቻው ልፋት ሆነ ነገሩ። አይ ጉድ ከአይን ያውጣህ የአባትህ ውቃቢ ይጠብቅህ ልጄ" ይሉና ይስሙታል። ቀዳማዊ በየ ሄደበት ሁሉ ስለ አባቱ ጀግንነት ደግነትና አስታራቂነት እየሰማ ይበልጥ የአባቱን ህልም ለማሳካት ደፋ ቀና ይል ጀመር። ለዚህም አምስተኛ ክፍል ትንሽ ከበድ ስለሚል። ይበልጥ መዘጋጀትና መጎበዝ ነው። ክረምት ላይ ወይዘሮ አትጠገብ ባል አገባች። ባል ያገባችው ገበሬው ትቷቸው ሲሄድና እሷም ገና በመሆኗና በተደጋጋሚ የእናግባሽ ጥያቄ በመብዛቱ ነበር። አዲስ ያገባችው ባል ገና በውል ቤቱን ልጆቹን ሳያውቅ ቀዳማዊን የጎሪጥ ማየት ጀመረ። ቀዳማዊም የእሱን እይታ ትቶ የራሱን ስራ መስራት ጀመረ። አምስተኛ ክፍል ለመግባት ደብተርና እስክርቢቶ ያስፈልግ ስለነበረ። እንደሚያስፈልገው እናቱን ጠየቀ። የተሰጠው ምላሽ ግን የምን አገባኝ አይነት መልስ ነበር። የተሸለመውን ደብተርና እስክርቢቶ እንኳ እህቶቹ እንደለመዱት ተቀራምተውታል። ቢጠይቅ ቢጠይቅ ስላልተገዛለት እስከ አራት የተማረበትን ትምሀርት ቤት ርዕሰ መምህር ያለውን ችግር ነግሮት ለአመት የሚበቃውን እስክርቢቶ ና ደብተር ሰጠው። በዚህ መሠረት የአምስተኛ ክፍል ትምህርትን ጀመረ። አሁንም ታይቶ በማይታወቅ ውጤት አንደኛ በመውጣት ለሶስተኛ ጊዜ አንደኛ በመውጣት ወደ ስድስተኛ ክፍል በሲሚስቴር ተዘዋወረ። ስድስተኛ ክፍል መጨረሻ ላይ ደግሞ ከክፍል አንደኛ ከአጠቃላይ ሁለተኛ በመውጣት ጉብዝናውን አስመሰከረ። እስከ ስድስተኛ ክፍል ድረስ ለመድረስ ሶስት አመት ፈጀበት። በዛን ጊዜ ከአንድ ወደ ሁለት ከሁለት ወደ ሶስት ከሶስት ወደ አራት እንዲሁም ከአምስት ወደ ስድስት በሲሚስተር ማለትም ደብል ማለፍ ይቻል ነበር። ሰባተኛ ክፍል ሲገባ ትምህርቶቹ ሁሉ የተወሰኑት እንደ ሒሳብ፣ ፊዚክስ ፣ባይሎጂ የመሳሰሉት ወደ እንግሊዝኛ ስለተቀየሩ የእንግሊዝኛ እውቀትን ይፈትሹ ነበር። ለዚህም ሜሪት የተሰኘ እንግሊዝኛን ወደ አማርኛ የሚፈታ መዝገበ ቃላት ተሸልሞ ነበርና ሌሊት ማንበብ ፈልጎ ኩራዝ ሲለኩስ። " ጋዝ እኮ ውድ ነው በውሃ የሚሰራ መሰለህ እንዴ " እያለች ወይዘሮ አትጠገብ ታጠፋበት ነበር። ከሚያውቃቸው መምህራን ለምኖ ብር ጋዝ ገዝቶ ቢለኩስ እንኳ " እስኪ እንተኛበት አትረብሸን እያሉ እህቶቹ ያጠፉበት ነበር። በኋላ ደግሞ ጭራሽ " ይሄ ድግምታም ወንድማችሁ ይሄው ተሳካለት" እያሉን ነው በየሄድንበት በማለት ለእናቷ ማለፊያ ተናገረች። " ይሄ ጦሰኛ ደግሞ በተከበርኩበት መንደር ሊያዋርደኝ ነው ቆይ የማደርገውን እኔ አውቃለሁ በማለት ለማለፊያ መለሰችላት። በዚህ ሁኔታ የቀዳማዊ እድሜ 13 ደረሰ። የስምንተኛ ክፍል ተማሪም ሆነ መከራና ስቃዩ እንደ በረዶ እየዘነበበት ገና በለጋ እድሜው ቁጣና ግልምጫን በማስተናገድ ከህልም ጉዞው ከመንገዱ ፍንክች ያላለው ቀዳማዊ አሁን ግን ትልቅ ፈተና ከፊቱ ተጋረጠበት።
*
" ለምን ግን አንገድለውም? እሱን መግደል አለብን!! " አለች ማለፊያ እነ ርብቃ አድና ትብለጥ ሲሳይነሽ ደነገጡ። "እንዴት አድርገን ነው የምንገድለው?" አለች አድና " አፍነን ነዋ" አለች ርብቃ "አይ እሱማ አይሆንም ይታወቅብናል።" አለች ትብለጥ "የምንገድለው አፍነን አሊያም ደብድበን አይደለም " አለች ማለፊያ " እና እንዴት አድርገን ነው የምንገድለው?" አለች ሲሳይነሽ " የምንገድለው በገደል ገፍተረን ነው። ይሄን የምናደርገው ወደ ጫካው ከብቶቹን ለመጠበቅ ሲሄድ ፍየሎቹ በገደሉ ስለሚንጠለጠሉ አንዷን ፍየል ገደሉ ላይ እናስራትና ድንጋይ ቢወረውር እንኳ እንዳትወጣ ትሆናለች። በዚህ ጊዜ ፍየሏን ለማስወጣት ወደ ገደሉ ሲቃረብ እንገፋውና ይወድቃል። አይተርፍም ገደሉ ደግሞ ደም ለምዷል። በዚህ ወድቀው ስንቶቹ ሬሳቸው መጥቷል። እንዲህ አድርገን እስከወዲያኛው መገላገል አለብን። ካልሆነ መሬቱ ምኑ ሁሉም ነገር በእሱ ስም ነው። ያ ማለት እኛ ከእሱ እየለመንን ነው የምንኖረው ማለት ነው። ይሄ ደግሞ ጥሩ አይመጣም ሕይወታችን ምስቅልቅሉ ይወጣል" አለች ማለፊያ ሁላቸውም ዝም አሉ። ከትንሽ ዝምታ በኋላ ትዕግስት እንዲህ አለች " ለምን ከምንገድለው ከአገር እንዲለቅ የትም እንዲሰደድ አናደርገውም?" አለች " ያምሻል?!" ማለፊያ አንባረቀች " እንደዚህ ብናደርገውማ አንድ ቀን ሊበቀለን ይመጣል ።በዛ ላይ መሞቱ ሳይረጋገጥ ንብረቱ ና መሬቱ በእኛ ስም አይዛወርም። ስለዚህ አንድና አንድ መፍትሔው እሱን መግደል ነው።" አለች ማለፊያ ። ሁሉም ተስማሙ "በሉ አሁን ያለውን ነገር እንዳታስታውቁ እንደ በፊቱ መሆን አለባችሁ። ምንም አይነት ነገር እንዳታሳዩ። ይሄ የህይወት ጉዳይ ነው መጠንቀቅ አለባችሁ።" አለች ማለፊያ
**
" ይሄን ሁሉ እርሻ ብቻየን አርሼ አልዘልቀውም በዛ ላይ ብዙ በሬዎች አሉ። ይሄ ልጅ ትምህርቱን ያቋርጥና ሊያርስ ይገባል። ስም ለመፃፍ አክስከዚህ ድረስ ከተማረ ይበቃል። " አለ የቀዳማዊ እንጀራ አባት ከእሱ ቀበል አደረገችና " አዎ ደግሞ ማንም ሰው ወንድ ልጁን ሲያስተምር አላየንም። ቦታ ጠባቂና ገበሬ ነው የሚሆኑት። በዚህም መሰረት አባታችን ደግሞ ይሄን ነው የሚፈልግ የነበረው
Justin Bieber, Chance the Rapper - Holy

Release Date: 18.09.2020
Genre: #Pop
:)
አዋ ይሄ ነው ፍቅር 💖
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሆነ ቀን ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል😇
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
:)
የእናትን ያህል ማንም ውለታን መዋል አይችልም…የእናትን ፍቅር እሚያክል ፍቅርም አይኖርም 👵🏽💖
2025/07/13 18:45:18
Back to Top
HTML Embed Code: