Telegram Web Link
የአና ማስታወሻ ክፍል 03
📙 የ መጻሕፍት ትረካ 🎙
●●◦የአና ማስታወሻ ክፍል 03◦●●
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
➲ ተርጓሚ አዶኒስ, ተራኪ ዩሐንስ የዝና

➲ የ15 ዓመት ልጃገረድ የሆነችው የአና ፍራንክ ዳየሪ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @monhappy
@BINCJ90
በመላው አለም ለምትገኙ ወንድም እህቶቼ እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤

ኢድ ሙባረክ!
የቅዳሜ ቀደዳ 24-(፳፬)
እንደምን ነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? እንደተለመደው ቅዳሜያችንን ፈካ፣ ዘና፣ ፀዳ ልናደርጋት እና ልንማማርባት ተከስተናል!
.
.
.
አንድ "James Carse" የሚባል ሼባ "Finite and Infinite games" በሚል ርዕስ የፃፈውን ፀዴ መፅሃፍ ሰሞኑን እያነበብኩ ነው። የሚያነሳቸው ሃሳቦች እና ዓለምን የሚያይበት መነፅር ደስ ይላል!
ገና መፅህፉን ስትጀምረው ምን ይላል መሰለህ?
እዚህች ዓለም ላይ ጦርነትም በለው፣ ስፖርትም በለው፣ ህይወትም በለው፣ የፍቅር ግንኙነትም በለው፣ ቢዝነስም በለው፣ ፖለቲካም በለው፣ ስራም በለው በሁለት ጨዋታዎች ላይ የተመሰረተ ነው።
አንደኛው "Finite games" ወይም "ማብቂያ ያለው ጨዋታ" ሲሆን ሰዎች፣ ቡድኖች ወይም ሃገራት ይሄንን ጨዋታ የሚጫወቱት ለማሸነፍ ነው። በዚህ ጨዋታ፣ ውድድር፣ ፍልሚያ ወይም ጦርነት ውስጥ የተገደበ የመጋጠሚያ ሜዳ እና የተወሰነ ግዜ አለ። ለምሳሌ የእግር ጓስ ጨዋታ ውስጥ አንዱ ቡድን 12 ሆኖ ሌላውን "X" የሚባል ቡድንን ይገጥማል። ጨዋታው የሚታወቁ ህጎች አሉት፣ መደበኛ የመጫወቻ ሰዓታቸው ተወስኖለታል፣ አሸናፊውም መጨረሻ ላይ ይታወቃል።
በዚህ ጨዋታ ውስጥ ለምሳሌ ጦርነት ከሆነ ሁለቱ ተጋጣሚዎች በውስጠ ታዋቂነት የሚያከብሯቸው ህጎች ይኖሯቸዋል። ጦርነቱ ከየት ተጀምሮ የት እንደሚያልቅ ይታወቃል፣ ሁለቱም ተጋጣሚዎች የታወቀ ድንበር/ወሰን አላቸው።
በድሮ ጦርነቶች ወቅት ሁለት ሃገራት/ቡድኖች ሲፋለሙ "...አንተም አለኝ የምትለውን ትጥቅ እና ወታደሮች ይዘህ ና፣ እኔም የራሴን ይዤ እመጣለሁ! ከዛም ሚያዝያ 26 ከሰዓት በኃላ ጦርነቱን እንጀምራለን! ከተሸነፍን እንገዛለን፣ እንገብራለን! ካሸነፍናችሁ ደግሞ እንደዛው! ታድያ በጦርነቱ ወቅት ህፃናትን መግደል ወይም የተማረከን ማሰቃየት የተከለከለ ነው!..." ተባብለው ይስማማሉ! በዚህ ጨዋታ ውስጥ ግዜ፣ ድንበር እና የመጨረሻ ግብ(ዓላማ) አሉ!
ጨዋታውን የሚጫወቱት ወይም የሚዋጉት ሁለቱ ቡድኖች የተፃፈ ባይሆንም የሚስማሙበት እና ሁለቱም የሚያከብሯቸው ህጎች አሏቸው!
ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ "Infinite games" ወይም "ማለቂያ የሌለው ጨዋታ" ይባላል! በዚህ ጨዋታ ውስጥ ሁለቱም ቡድኖች ጦርነቱ/ጨዋታው እንዲያበቃ ወይም እንዲገደብ አይፈልጉም። ልክ ጨዋታው ወደ መገባደድ ሲደርስ ከሁለት አንዱ ግዜ ገዝቶ ጨዋታውን/ጦርነቱን ያራዝመዋል!
ይሄኛው ጨዋታ ውስብስብ ነው፣ አሸናፊ እና ተሸናፊ የለውም፣ መቼ እንደሚያልቅ አይታወቅም፣ ሁለቱም ተፋላሚዎች ወይ ደግሞ ከሁለቱ አንዱ ጦርነቱ/ጨዋታው ማለቂያ እንዲኖረው አይፈልግም። ህግ የሚባል ነገር አይሰራም! በዚህ ጨዋታ ውስጥ ሁለቱ ተፋላሚ ቡድኖች ከራሳቸው በተጨማሪ ሌሎች ሰዎችን/ቡድኖችን ወይም ሃገራትን ስበው ያስገባሉ። አንደኛው ተፋላሚ እንዳበቃለት ወይም ዋጋ እንደሌለው እየተረዳ በመጣ ቁጥር ጦርነቱን/ጨዋታውን ወጥሮ መጫወት ይጀምራል! የሱ ህልውና በጨዋታው መቀጠል ላይ የተመሰረተ ነውና!
ማሳያ አንድ!
በአሜሪካ እና በራሽያ መካከል የነበረው "Cold war" ወይም "ቀዝቃዛው ጦርነት" እንደ "infinite games" ሊወሰድ ይችላል። አሸናፊም ተሸናፊም የለውም! አበቃ ስትል ቀጥሏል! የትኛው ቡድን ምን እንደሚፈልግ በግልፅ አይታወቅም። ጨዋታው በቀጠለ ቁጥር ሁለቱም ተፋላሚዎች ተጠቃሚ እየሆኑ ይመጣሉ፣ የማን ጡንቻ ትልቅ እንደሆነ ለሌሎች ለማሳየት ይጋጋጣሉ። አሁን ላይ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው ፍልሚያ "Cold war" የሚል ስያሜ አይሰጠው እንጂ ሽኩቻው፣ ጡንቻ ማሳየቱ እና እርስ በእርስ ጣልቃ መገባባቱ እንደቀጠለ ነው፣ ለወደፊትም ይቀጥላል! ምክንያቱም "infinite game" ውስጥ ናቸው።
ማሳያ ሁለት!
ብዙ ግዜ ችግር የሚፈጠረው አንዱ ተፋላሚ "Finite games"ን ሲጫወት ሌላኛው ተፋላሚ ደግሞ "infinite games" መጫወት ከመረጠ ነው። ምክንያቱም "finite games"ን የሚጫወተው ተፋላሚ የሚጫወተው ለማሸነፍ (winner) ለመሆን ሲሆን "infinite games" የሚጫወተው ተፋላሚ ደግሞ ለመኖር እና ለህልውናው ሲል ነው። ለሱ ጨዋታው የ "survival" ጉዳይ ነው!
እ.ኤ.አ 1978 ላይ የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት (የአሁኗ ራሽያ) በወቅቱ የሚችላት የለምና አፍጋኒስታን ውስጥ የተጠነሰሰን መፈንቅለ መንግስት "sponsor" አድርጋ የፈቀደችውን መሪ እና መንግስት ታስቀምጣለች። ነገር ግን ህዝቡ የተቀመጠውን መንግስት አልቀበልም ብሎ በከባዱ አመፀ! ግማሹ ይሄንን መንግስት ለመጣል ተደራጅቶ አማፂ በመሆን እራሱን "Mujahideen" ብሎ ሰይሞ ጫካ ገባ! እነዚህ አማፅያን ሃገራቸው ነው! መውጫ መግቢያውን፣ ጋራ ሸንተረሩን... ብቻ ምን አለፋህ ሁሉንም በደንብ አብጠርጥረው ያውቁታል። የአማፅያኑ ፀብ ከራሽያ ጋር ስለሆነ አሜሪካ ሳትቀር አስታጥቃቸዋለች። እነዚህን አማፅያን ለማሸነፍ ቀናት አይፈጅብኝም በማለት ራሽያ ጦሯን ወደ አፍጋኒስታን አዘመተች። ጦርነቱ በ "finite" እና በ "infinite" ተፋላሚዎች መካከል ይደረግ ጀመር! ሶቭየት ህብረት(ራሽያ) ለማሸነፍ፣ አማፅያኖቹ ደግሞ ለህልውናቸው!
ጌታዬ! በቀናት ውስጥ ጦርነቱን አገባድዳለሁ ብላ ያሰበችው ሶቭየት ህብረት ጦርነቱ የተጀመረ ሰሞን ማሸነፍ ብትችልም አማፅያኑ ቀስ በቀስ እየተጠናከሩባት መጡ!
ብታምንም ባታምን እነዚህ አማፅያን 451 የጦር ጀቶቿን ከአየር ላይ ከሰከሱባት ፣147 ታንኮቿን ከጥቅም ውጪ አደረጉባት፣ 15 ሺህ ወታደሮቿም ሞቱ! ይህ ብቻ ሳይሆን ከ 35 ሺህ በላይ ወታደሮቿ ክፉኛ ቆሰሉ!
በዚህ ውጥንቅጡ በወጣ ጦርነት ወቅት በአፍጋኒስታን በኩል ደግሞ 1 ሚልዮን ሰዎች ሞቱ(አብዛኛዎቹ ንፁሃን ናቸው) ፣ 5 ሚልዮን አፍጋኒስታናዊያን ለስደት ተዳረጉ፣ 3 ሚልዮን የሚሆኑ ደግሞ ቆሰሉ! ከአማፅያኑ ወደ 56 ሺህ ሰዎች ረገፉ! ህፃናት ተራቡ፣ ሴቶች ተደፈሩ፣ መሰረተ ልማት ወደመ! በመጨረሻም ከአስር አመታት እልቂት በኃላ ጦርነቱ አሽናፊም ተሸናፊም ሳይኖረው የሶቭየት ጦር ከአቅሙ በላይ ሆኖበት አፍጋኒስታንን ጥሎ ወጣ! ጦርነቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሶቭየት ህብረት መዳከም እና ኃላም ላይ መበተን አስተዋፅኦን አበረከተ! ከዛ በተጨማሪ ደግሞ ለአፍጋኒስታን የእርስ በእርስ ጦርነት ቡርቅቅ ያለ በርን ከፈተ።
የ "Vietnam" ጦርነት ወቅት የተፈጠረውም ተመሳሳይ ታሪክ የ "infinite games" እና የ "finite games" ገፅታ ያለው ነው!
እዚህ መፅሃፍ ላይ ከተቀመጡት ታሪኮች በጣም የመሰጠኝን አንድ ሌላ ነገር ላንሳልህ!
👇👇
ይቀጥላል
በ "finite games" ውስጥ ጦርነት ላይ ሳይቀር ህግ ይሰራል!
ወቅቱ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት የሚካሄድበት ግዜ ነው! አንደኛው ጎራ ጃፓን፣ ጀርመን እና ጣልያንን አሰባጥሯል! ሁለተኛው ጎራ ደግሞ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ራሽያ እና አሜሪካን ይዟል! ጌታዬ! ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማለት ከ 100 ሚልዮን በላይ ወታደሮች የተሳተፉበት፣ የሰው ልጅ ኒዩክለርን የሚያክል ነገር ታጥቆ ወደ ጦርነት የገሰገሰበት፣ በሰው ልጅ ታሪክ እጅግ አደገኛው እና ከፍተኛ እልቂት የደረሰበት ጦርነት ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን ፋሺስት ጣልያን፣ ናዚ ጀርመን እና የጃፓን ዘውዳዊ አገዛዝ የወደቀበት እና ከ 50 ሚልዮን በላይ ንፁሃን ዜጎች ያለቁበት እጅግ ቀፋፊ ጦርነት ነው።
በዚህ መሃል ጀርመን ውስጥ "Heidelberg" በምትባል ከተማ ውስጥ ከ 600 ዓመታት በላይ የቆየ ዩኒቨርሲቲ አለ። "Heidelberg university" ይባላል! ይቺህ ጥንታዊት ከተማ እና ታሪካዊ ዩኒቨርስቲ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በቦንብ እንዳትደበደብ ተፋላሚዎቹ ተስማምተው እውነትም ሳትደበደብ መትረፍ ችላለች! አሁን ላይ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ቦንብ ያልነካት ከተማ በመባል እንደጉድ ቱሪስቶች እየጎረፉ ይጎበኟታል።
እንግሊዝ የሚገኘው "Oxford" ከተማ እና ከ 900 ዓመታይ በላይ ያስቆጠረው "Oxford University"ም እንደዚሁ ከ "Hitler" ቦንብ ድብደባ በስምምነት መትረፍ ችሏል!
በተመሳሳይ የፈረንሳይዋ ጥንታዊት ከተማ "Paris" በውስጧ ብዙ ታሪኮችን እና የሚደንቁ ሙዝየሞች ያሉባት በመሆኗ እና በወቅቱ ጦርነቱን ሸሽተው ብዙ ስደተኞች የተጠለሉባት ከተማ ስለነበረች "Hitler" እንደሌሎቹ ከተሞች የቦንብ ናዳን ሳያወርድባት አልፏል!
ምክንያት?
"The game was finite! It had certain rules! It was time bound! It had goals!"
ማጠቃለያ!
በነገራችን ላይ "James Carse" ይህንን መፅሃፍ የፃፈው የዛሬ 35 ዓመት ነው! በወቅቱ መፅሃፉን እምብዛም ትኩረት የሚሰጠው ጠፍቶ በደንብ አልተነበበለትም ነበር! ነገር ግን ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች እንደ አዲስ እየተነበበ ነው።
ጌታዬ! ፀሃፊው "Finite" እና "infinite" ጨዋታዎችን ከህይወት፣ ስራ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ሌሎች ጉዳዮች ጋር እያዛመደ አሪፍ እይታን ይሰጥሃልና ብታነበው አትጎዳም! እረፍትህን በሱ አሳልፍ!
መልካም ምሽት! ፅድት ያለች ቅዳሜ ትሁንላችሁ!
፡ እኔ ማለት ያ ነኝ ⛅️

የሆነ ቀን መንገድ ዳር ያየሺው…አይተሺም የሸሸሺው…ጫማ ያላረገ…ልብሱ የተቀዳደደ…አዋ እሱ ሰውዬ እኔ ነኝ…

🌸 እግዛብሔር ግን መልካም ነው 🌸

🥀 @monhappy 🥀
@monhappy
የአና ማስታወሻ ክፍል 04
📙 የ መጻሕፍት ትረካ 🎙
●●◦የአና ማስታወሻ ክፍል 04◦●●
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
➲ ተርጓሚ አዶኒስ, ተራኪ ዩሐንስ የዝና

➲ የ15 ዓመት ልጃገረድ የሆነችው የአና ፍራንክ ዳየሪ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @monhappy
@BINCJ90
የቅዳሜ ቀደዳ 25-(፳፭)
እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት አመሸሽ እናቴ? ወደ ቅዳሜያችን መጥተናል! የዛሬው የፀዳ ነው!
.
.
".....ወቅቱ እ.ኤ.አ 1986 ላይ ነው! የአሜሪካ ደህንነት ተቋም የሆነው "CIA" ከሰሜን አፍሪካዋ ሃገር ሊብያ ከሳተላይት እና ኤሌክትሮኒክ ሰርቪላንስ የሚሰበሰቡ የተለያዩ ሚስጥራዊ መልእክቶችን እየቃረመ ነው። ከነዚህ ሚስጥራዊ መልእክቶች ውስጥ ለአሜሪካ የደህንነት ስጋት የሚሆን ነገር ከተገኘ ይመረመራል። የዛን ቀን "CIA" 397 የተለያዩ ሚስጥራዊ መልእክቶችን አዳምጦ ምንም የደህንነት ስጋት የሚሆን ነገር አላገኘም! ነገር ግን ጠልፈው ከሚሰሟቸው መልእክቶች ውስጥ 398ኛው መልእክት ለአሜሪካ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ሆኖ ተገኘ። መልእክቱ "...stand by and be ready to attack American targets and Execute the plan..." የሚል ነበር! ይህ መልዕክት የደህንነት ተቋሙ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ። ከሊቢያ ተጠልፎ የተሰማው መልእክት "Muammar Gaddafi" ከሚመራው መንግስት እንደሆነ ማወቅ ቢችሉም ጥቃት እንዲደርስባቸው የተባሉት አሜሪካውያን የት እና መቼ እንደሆነ ግን ማወቅ አልተቻለም። ማጣራታቸውን ቀጠሉ! የዛኑ ቀን የሊብያ የደህንነት ተቋም ጀርመን ከሚገኘው የሊብያ ኤምባሲን ጋር መልእክት እንደተለዋወጠ እና ጀርመን የሚገኘው የሊብያ ኤምባሲ ለሊብያ የደህንነት ተቋም "Tripoli will be happy when you see the headlines tomorrow!" የሚል መልእክት እንደላከ ደረሱበት! በመጨረሻም ጥቃቱ ጀርመን ውስጥ የሚገኙ አሜሪካውያን ላይ ሊፈፀም እንደታሰበ አረጋገጡ። ጥቃቱን ግን ለማስቆም በቂ ግዜ አልነበራቸውም! የዛን ቀን ምሽት አንዲት የጀርመን ከተማ ውስጥ አሜሪካውያን የሚያዘወትሩት መሸታ ቤት አንዲት ሴት በሻንጣዋ ውስጥ ቦንቦች ይዛ የመሸታ ቤቱ ሶፋ ላይ አስቀምጣው ሄደች! ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ቦንቡ ፈንድቶ 230 ሰዎች ሲቆስሉ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች ደግሞ ህይወታቸው አለፈ! "CIA" እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት "Ronald Reagan" ከዛን ግዜ በኃላ ጋዳፊ መወገድ እንዳለበት ወሰኑ! የወቅቱ የ "CIA" ዳይሬክተር የነበረው "William Casey" ጋዳፊን በምን አይነት መንገድ ማስወገድ እንደሚቻል ሃሳብ አቀረበ! ጋዳፊን መግደል ቀላል አይደለም! ብዙ ሺህ በተጠንቀቅ የሚጠብቁት ጥበቃዎች አሉት! ከዚህ በተጨማሪ 40 እጅግ የሰለጠኑ ድንግል ሴት የግል ጥበቃዎቹ አሉ! ሊቢያ ሙሉ በሙሉ በእርሱ ቁጥጥር ስር ናት! "CIA" በወቅቱ ሊብያ ውስጥ ጋዳፊን ለማስገደል ሊጠቀምባቸው የሚችላቸው ኤጀንቶች የሉትም! "CIA" ጋዳፊን በቀጥታ መግደል ቢፈልግም በአሜሪካ ህግ ፖለቲካዊ ግድያ(political assassination) መፈፀም ተከልክሏል። የነበረው አማራጭ የአየር ጥቃት በአሳቻ ሰአት መፈፀም ነበር! የሊብያ መንግስት የሽብር ጥቃቶች እንዲፈፀሙ ትዕዛዝ የሚሰጥበትን ቦታ ለማጥቃት አሜሪካ ወሰነች! ነገር ግን "...የሽብር ጥቃት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ይሰጥበታል..." የተባለው ቦታ የጋዳፊ መኖርያ ቤት ነው! የአሜሪካ ግብ በቀጥታ ጋዳፊን ከመግደል ይልቅ የጋዳፊን ቤት "የሽብር ጥቃት የሚቀነባበርበት ቦታ" የሚል ስያሜ በመስጠት የአየር ላይ ድብደባ አድርጎ በሂደቱ ጋዳፊን መግደል ነው!
ከዛስ?
"CIA" በዚህ ቀመር ውስጥ አንድ ፈተና ገጠመው! በጥቃቱ ጋዳፊን ለመግደል ጋዳፊ በመኖርያ ቤቱ ውስጥ የሚኖርበትን ሰዓት ማወቅ አስፈላጊ ነበር።ይህንን ማወቅ ግን አስቸጋሪ ነው! ከዛም "CIA" ወደ እስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ሄደ! የሞሳድ ሰላዮች ጋዳፊ በመኖርያ ቤቱ የሚገኝበትን ትክክለኛ ሰዓት ሰላዮቻቸውን በአካል በመላክ አጣሩላቸው! ከዛም አሜሪካ በተባለችው ሰዓት ሁለት የጦር ጀቶችን ልካ ጋዳፊ ይገኝበታል በተባለው ሰዓት መኖርያ ቤቱ ላይ ቦንቦችን አዝንባ ተሰወረች! አሜሪካ በጥቃቱ ጋዳፊ እንደሚሞት እርግጠኛ ሆና ሰበር ዜናን ትጠባበቃለች! ከቀናት በኃላ ግን ኮሎኔል ጋዳፊ አንዲት ቦታ ሳይጫር በሃገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ በቦንብ ጥቃቱ የተጎዱ ሊብያውያንን ሆስፒታል ሄዶ ሲጎበኝ ታየ!
ያኔ የ "CIA" ጋዳፊን በቀላሉ ማስወገድ እንደማይቻል ተረዳ! ሁለተኛውን አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አመነ! ሁለተኛው አማራጭ "...ጋዳፊን የሚቃወሙ ሊብያ ውስጥ የሚገኙ አማፅያንን ወይም ተቃዋሚዎችን በሁሉም ዘርፍ መርዳት ወይ ደግሞ ህዝቡ የሃገሪቱ መንግስት ላይ ከዳር እስከ ዳር እንዲያምፅ ማድረግ..." የሚል ነበር! አሜሪካ የተለያዩ አማፅያንን ማሰልጠን እና ማስታጠቅ ጀመረች! ነገር ግን እነዚህን የተለያዩ አማፅያን አንድ ላይ አቀናጅቶ የጋዳፊን መንግስት የሚጥል መሪ እንደሚያስፈልግ "CIA" ተረዳ! ከብዙ ጥናት በኃላ አንድ ሰው ተገኘ! የተገኘው ሰው ኮሎኔን "Khalifa Haftar" ይባላል! ይህ ሰው በአንድ ወቅት ጋዳፊ ወደ ስልጣን ሲመጣ አብሮት የነበረ ታማኝ የጦር መሪ እና አገልጋዩ ነበር! ጋዳፊ ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ሊብያ ከጎረቤት ሃገር "Chad" ጋር ጦርነት ውስጥ ስትገባ የሊብያን ጦር የመራውም ይህ ሰው ነበር! እንደ አጋጣሚ ታድያ ይህ ኮሎኔል በጦርነቱ ወቅት በ "Chad" ወታደሮች ተማርኮ ይታሰራል! ጋዳፊ የጦር መሪው "Khalifa Haftar" እንዲፈታ ጥረት ከማድረግ ይልቅ እስከመፈጠሩ ጭራሽ ረሳው! "Khalifa Haftar"ም ለ 7 ዓመታት በ " Chad" መንግስት ታሰረ! ይህ መረጃ ያለው "CIA" የ "Chad" ፕሬዝዳንት ጋር ደውሎ "Khalifa Haftar"ን እስር ቤት ሄዶ ሁለት አማራጮችን እንዲሰጡት አደረገ!
አማራጭ አንድ፡ እዚሁ እስር ቤት በስብሰህ እና የጦር ምርኮኛ ሆነህ ትሞታለህ? ወይስ
አማራጭ ሁለት፡ እንደዛ በታማኝነት ያገለገልከው የሃገርህ መሪ ጋዳፊ ከድቶኻል! እስከ መፈጠርህም አላስታወሰህም! እንደውም በመማረክህ በሽቋል! ስለዚህ ከእስር እንፍታህ! አሜሪካዊ ዜግነት እንስጥህ! ከ "CIA" ጋር አብረህ ስራ! የተበታተኑትን አማፅያን አድራጅተህ "Libyan National Army" የሚባል ጦር እዚሁ "Chad" ውስጥ አቋቁም! "CIA" በጦርም፣ በመሳርያም፣ በታክቲክም፣ በሃሳብም.. በሁሉም ነገር ይረዳኻል!
Guess what?
ኮሎኔል "Khalifa Haftar" ሁለተኛውም አማራጭ ተቀበለ! "CIA" "Khalifa Haftar"ን እና አማፅያኑን ጎረቤት ሃገር "Chad" ውስጥ አየረዳ እና እያሰለጠነ አቆያቸው!
ነገር ግን ያልታሰበ ነገር በመሃል ተፈጠረ!
በአሜሪካ መንግስት ይደገፍ የነበረው የ "Chad" መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት ተደረገ! መፈንቅለ መንግስት መደረጉ ችግር አልነበረውም! ነገር ግን በመፈንቅለ መንግስቱ ስልጣን የያዘው አካል የአሜሪካ አጋር ስላልነበረ "CIA" ጋዳፊን ለመጣል "Chad" ውስጥ የሚደግፋቸው እና የሚያሰለጥናቸው አማፅያን (Khalifa Haftar)ን ጨምሮ ከ "Chad" እንዲወጡ አዲሱ የ "chad" መንግስት አዘዘ!
ጌታዬ! "CIA" ምን እንዳደረገ ታውቃለህ?
"Khalifa Haftar"ን ጨምሮ አብረውት የነበሩ 300 አማፅያንን በናይጄሪያ፣ ዛየር እና ኬንያ በኩል አድርጎ ወደ አሜሪካ ወሰዳቸው! ከዛም ኮሎኔሉን ጨምሮ እነዚህን 300 የሚደርሱ ሊብያዊ አማፅያኖች የ "CIA" ዋና መቀመጫ የሆነችው "Virginia" ውስጥ መኖርያ ቤት ተሰጥቷቸው ለግዜው እንዲቆዩ አደረጉ!
ከአመታቶች በኃላ!
እ.ኤ.አ 2011 ላይ የአረቡ ዓለም ተቃውሞ(Arab spring) ተቀሰቀሰ! ቱኒዝያ፣ ግብፅ እና ሊብያ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ተነሳ! ይህንን አጋጣሚ ለ 30 ዓመታት ጓጉታ ስትጠብቅ የነበረችው አሜሪካ "Khalifa Haftar" እና አማፅያኑን ወደ ሊብያ በማስገባት አመፅ እና ጦርነቱ እንዲፋፋም አደረገች! ጋዳፊም በአማፅያዩ የተከፈተበትን ጦርነት ለማክሸፍ ከልክ በላይ እርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ። በዚህ መሃል የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት "Barack Obama" ከ "NATO" ጋር በመቀናጀት የአየር ላይ ጥቃቶችን ሊብያ ላይ ይፈፅም ጀመር! አማፅያኖቹ ከአሜሪካ በሚያገኙት ድጋፍ ምስራቅ ሊብያን መቆጣጠር ቻሉ! አባዬ! "Khalifa Haftar" በመሬት ይዋጋል፣ አሜሪካ በሰማይ ታግዘዋለች! ከስድስት ወራት ጦርነት በኃላ የሊብያ ዋና ከተማ በአማፅያኑ ቁጥጥር ስር ወደቀች! ጋዳፊ እና ልጆቹ ተደበቁ! አማፅያኑ እና "CIA" ተቀናጅተው ጋዳፊን ከተደበቀበት ለማግኘት አሰሳቸውን ቀጠሉ! በመጨረሻም "NATO" ጋዳፊ የሳተላይት ስልክ ተጠቅሞ የደወለበትን የስልክ መስመር መጥለፍ ቻለ! ከዛም ለማምለጥ ጋዳፊ ሲጓዝበት የነበረውን የጭነት መኪና በድሮን አሜሪካ "Las vegas" ላይ ቁጭ ብለው አጋዩት!
እ.ኤ.አ October, 20,2011 ላይ "sirte" በምትባል ከተማ አማፅያኑ ለ 42 ዓመታት ሊብያን የመራውን መሪያቸውን መሬት ለመሬት እየጎተቱ፣ እየተሳለቁ፣ ፎቶ እየተነሱ፣ ፀጉሩን እየነጩ እና እያሰቃዩ ገደሉት!
አለቀ!
ምዕራባዊያኑ እንዲህ ይሉታል!
"Muammar Gaddafi" አንባገነን ነው፣ ጨቋኝ ነው፣ ሌባ ነው፣ ገዳይ ነው፣ አፋኝ ነው፣ ደፋሪ ነው፣ ሽብርተኛ ነው፣ ሽብርተኞችን ደጋፊ ነው ፣ ጠላቶቹን ይገድላል፣ ተቃዋሚዎች ያስራል፣ ሲፈልግ እንዲሰወሩ ያደርጋል፣ የሱ ቢጤ ጨፍላቂዎቹን የአፍሪካ መሪዎች (ኤዲያሚን ዳዳን፣ ኢሳያስን፣ ሙጋቤን እና መንግስቱን) ይደግፋል!
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት "Ronald Reagan" ጋዳፊን "The mad dog of the middle east(የመካከለኛው ምስራቅ እብድ ውሻ)" እያለ ይጠራዋል!
ግን...ግን
"Muammar Gaddafi" በምዕራባዊያኑ እና በሃገሪቱ ጥቂት ሃብታሞች ተይዘው የነበሩ የእርሻ መሬቶችን ለደሃው የሰጠ፣ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት 10% የነበረውን የሃገሪቱን የተማረ ህዝብ ወደ 88% ያሳደገ፣ "United States of Africa" የምትባል ጠንካራ እና የራሷ መከላከያ ሰራዊት ያላት አፍሪካን መፍጠር የሚፈልግ፣ አፍሪካውያን አንድ ወጥ ፓስፖርት እንዲኖራቸው የሚሻ እና አህጉሪቱ አንድ የጋራ የመገበያያ ገንዘብ እንዲኖራት የሚፈልግ ሰው ነበር!
"Muammar Gaddafi" ሃገሩ ሊብያ ያላትን የነዳጅ ሃብት በአግባቡ እንድትጠቀም ያደረገ፣ በዚህም ስልጣን ሲይዝ እ.ኤ.አ 1969 ላይ ደሃ የነበረው የሊብያ ህዝብ በአፍሪካ ቁጥር አንድ ሃብታም ህዝብ እንዲሆን ያደረገ እና የሃገሪቱ "GDP" ከ 42 ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በ 600% እንዲያድግ ያደረገ መሪ ነበር!
እሱ ብቻ አይደለም!
ሊብያውያን በአፍሪካ ትልቁ የነብስ ወከፍ ገቢ የነበራቸው በእርሱ የስልጣን ግዜ ነበር! ጌታዬ! ሊቢያ በእርሱ የስልጣን ግዜ 0% እዳ ያለባት ሃገር ነበረች!
ሰውየው "Regional African satellite communication organization" ለሚባል ተቋም 300 ሚልዮን ዶላር በመስጠት ከአውሮፓ የሳተላይት ጥገኝነት አፍሪካ እንድትላቀቅ የሚያልም ሰው ነበር! አንዳንድ ደሃ የአፍሪካ ሃገራት የአፍሪካ ህብረት አባልነት መዋጮን መሸፈን ሲያቅታቸው ጋዳፊ መዋጮአቸውን ሳይቀር ይሸፍን ነበር!
"Muammar Gaddafi" አፍሪካ የራሷ "African Monetary Fund" የሚባል ተቋም እንዲኖራትም ይፈልግ ነበር!
"Gaddafi" የዶላር እና የይሮን የበላይነት ለማስቀረት የወርቅ ዲናሮችን አትሞ አፍሪካ እና የዓረቡ ዓለም በነዚህ የወርቅ ዲናሮች እንዲገበያይ ሳይቀር ይወጥን ነበር!
"Gaddafi" የሃገሪቱ የነዳጅ ሃብት "privatize" ተደርጎ እያንዳንዱ የሃገሪቱ ዜጋ የዚህ ነዳጅ ሃብት ባለቤት እንዲሆን የማድረግ ስራን ይሰራም ነበር! ለአዳዲስ ሙሽሮች 50 ሺህ ዶላር ቤት ለመግዣ እና መቋቋሚያ እንዲሆን በስጦታ መልክ ይሰጥ ነበር የሚባለው ጋዳፊ ምዕራባዊያኑ ሳይቀር በማይክዱት መልኩ ሃገሩን ድብን አድርጎ አሳድጓል!
ምን ዋጋ አለው ጌታዬ?
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት "Donald J. Trump" እንዲህ ይላል!
"...ዓለማችን ጋዳፊ እና ሳዳም ስልጣን ላይ ቢቆዩ ኖሮ ይሄንን ያህል ውጥንቅጥ ውስጥ አትገባም ነበር! ይህ ሁሉ ውጥንቅጥ እንዲፈጠር ያደረጉት ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ እና ሴጣኗ ሂላሪ ክሊንተን ናቸው! ጋዳፊ እና ሳዳም ጥሩ ሰዎች ናቸው እያልኩ አይደለም! ነገር ግን ስልጣን ላይ እንዲቆዩ ብናደርግ ኖሮ አሁን ላይ ለዚህ ሁሉ ጣጣ አንዳረግም ነበር!..."
እ.ኤ.አ 2016 ላይ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት "Barack Obama" አሜሪካ ጋዳፊን ከስልጣን ለማንሳት የከፈተችው ጦርነት በፕሬዝዳንትነት ግዜው ከሚፀፀትባቸው ውሳኔዎቹ ውስጥ አንደኛው እንደሆነ ተናግሮ አምኗል!
"Muammar Gaddafi" የገዛ ዜጎቹ መሬት ለመሬት እየጎተቱ ሲደበድቡት እና ሲሳለቁበት የጠየቃቸው እንዲህ ብሎ ነበር!
"What did i do to you?"(ምን አደረኳችሁ?)
መልካም ቅዳሜ! መልካም ምሽት!የቅዳሜ ቀደዳ 25-(፳፭)
እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት አመሸሽ እናቴ? ወደ ቅዳሜያችን መጥተናል! የዛሬው የፀዳ ነው!
.
.
".....ወቅቱ እ.ኤ.አ 1986 ላይ ነው! የአሜሪካ ደህንነት ተቋም የሆነው "CIA" ከሰሜን አፍሪካዋ ሃገር ሊብያ ከሳተላይት እና ኤሌክትሮኒክ ሰርቪላንስ የሚሰበሰቡ የተለያዩ ሚስጥራዊ መልእክቶችን እየቃረመ ነው። ከነዚህ ሚስጥራዊ መልእክቶች ውስጥ ለአሜሪካ የደህንነት ስጋት የሚሆን ነገር ከተገኘ ይመረመራል። የዛን ቀን "CIA" 397 የተለያዩ ሚስጥራዊ መልእክቶችን አዳምጦ ምንም የደህንነት ስጋት የሚሆን ነገር አላገኘም! ነገር ግን ጠልፈው ከሚሰሟቸው መልእክቶች ውስጥ 398ኛው መልእክት ለአሜሪካ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ሆኖ ተገኘ። መልእክቱ "...stand by and be ready to attack American targets and Execute the plan..." የሚል ነበር! ይህ መልዕክት የደህንነት ተቋሙ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ። ከሊቢያ ተጠልፎ የተሰማው መልእክት "Muammar Gaddafi" ከሚመራው መንግስት እንደሆነ ማወቅ ቢችሉም ጥቃት እንዲደርስባቸው የተባሉት አሜሪካውያን የት እና መቼ እንደሆነ ግን ማወቅ አልተቻለም። ማጣራታቸውን ቀጠሉ! የዛኑ ቀን የሊብያ የደህንነት ተቋም ጀርመን ከሚገኘው የሊብያ ኤምባሲን ጋር መልእክት እንደተለዋወጠ እና ጀርመን የሚገኘው የሊብያ ኤምባሲ ለሊብያ የደህንነት ተቋም "Tripoli will be happy when you see the headlines tomorrow!" የሚል መልእክት እንደላከ
ደረሱበት! በመጨረሻም ጥቃቱ ጀርመን ውስጥ የሚገኙ አሜሪካውያን ላይ ሊፈፀም እንደታሰበ አረጋገጡ። ጥቃቱን ግን ለማስቆም በቂ ግዜ አልነበራቸውም! የዛን ቀን ምሽት አንዲት የጀርመን ከተማ ውስጥ አሜሪካውያን የሚያዘወትሩት መሸታ ቤት አንዲት ሴት በሻንጣዋ ውስጥ ቦንቦች ይዛ የመሸታ ቤቱ ሶፋ ላይ አስቀምጣው ሄደች! ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ቦንቡ ፈንድቶ 230 ሰዎች ሲቆስሉ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች ደግሞ ህይወታቸው አለፈ! "CIA" እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት "Ronald Reagan" ከዛን ግዜ በኃላ ጋዳፊ መወገድ እንዳለበት ወሰኑ! የወቅቱ የ "CIA" ዳይሬክተር የነበረው "William Casey" ጋዳፊን በምን አይነት መንገድ ማስወገድ እንደሚቻል ሃሳብ አቀረበ! ጋዳፊን መግደል ቀላል አይደለም! ብዙ ሺህ በተጠንቀቅ የሚጠብቁት ጥበቃዎች አሉት! ከዚህ በተጨማሪ 40 እጅግ የሰለጠኑ ድንግል ሴት የግል ጥበቃዎቹ አሉ! ሊቢያ ሙሉ በሙሉ በእርሱ ቁጥጥር ስር ናት! "CIA" በወቅቱ ሊብያ ውስጥ ጋዳፊን ለማስገደል ሊጠቀምባቸው የሚችላቸው ኤጀንቶች የሉትም! "CIA" ጋዳፊን በቀጥታ መግደል ቢፈልግም በአሜሪካ ህግ ፖለቲካዊ ግድያ(political assassination) መፈፀም ተከልክሏል። የነበረው አማራጭ የአየር ጥቃት በአሳቻ ሰአት መፈፀም ነበር! የሊብያ መንግስት የሽብር ጥቃቶች እንዲፈፀሙ ትዕዛዝ የሚሰጥበትን ቦታ ለማጥቃት አሜሪካ ወሰነች! ነገር ግን "...የሽብር ጥቃት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ይሰጥበታል..." የተባለው ቦታ የጋዳፊ መኖርያ ቤት ነው! የአሜሪካ ግብ በቀጥታ ጋዳፊን ከመግደል ይልቅ የጋዳፊን ቤት "የሽብር ጥቃት የሚቀነባበርበት ቦታ" የሚል ስያሜ በመስጠት የአየር ላይ ድብደባ አድርጎ በሂደቱ ጋዳፊን መግደል ነው!
ከዛስ?
"CIA" በዚህ ቀመር ውስጥ አንድ ፈተና ገጠመው! በጥቃቱ ጋዳፊን ለመግደል ጋዳፊ በመኖርያ ቤቱ ውስጥ የሚኖርበትን ሰዓት ማወቅ አስፈላጊ ነበር።ይህንን ማወቅ ግን አስቸጋሪ ነው! ከዛም "CIA" ወደ እስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ ሄደ! የሞሳድ ሰላዮች ጋዳፊ በመኖርያ ቤቱ የሚገኝበትን ትክክለኛ ሰዓት ሰላዮቻቸውን በአካል በመላክ አጣሩላቸው! ከዛም አሜሪካ በተባለችው ሰዓት ሁለት የጦር ጀቶችን ልካ ጋዳፊ ይገኝበታል በተባለው ሰዓት መኖርያ ቤቱ ላይ ቦንቦችን አዝንባ ተሰወረች! አሜሪካ በጥቃቱ ጋዳፊ እንደሚሞት እርግጠኛ ሆና ሰበር ዜናን ትጠባበቃለች! ከቀናት በኃላ ግን ኮሎኔል ጋዳፊ አንዲት ቦታ ሳይጫር በሃገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣብያ በቦንብ ጥቃቱ የተጎዱ ሊብያውያንን ሆስፒታል ሄዶ ሲጎበኝ ታየ!
ያኔ የ "CIA" ጋዳፊን በቀላሉ ማስወገድ እንደማይቻል ተረዳ! ሁለተኛውን አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አመነ! ሁለተኛው አማራጭ "...ጋዳፊን የሚቃወሙ ሊብያ ውስጥ የሚገኙ አማፅያንን ወይም ተቃዋሚዎችን በሁሉም ዘርፍ መርዳት ወይ ደግሞ ህዝቡ የሃገሪቱ መንግስት ላይ ከዳር እስከ ዳር እንዲያምፅ ማድረግ..." የሚል ነበር! አሜሪካ የተለያዩ አማፅያንን ማሰልጠን እና ማስታጠቅ ጀመረች! ነገር ግን እነዚህን የተለያዩ አማፅያን አንድ ላይ አቀናጅቶ የጋዳፊን መንግስት የሚጥል መሪ እንደሚያስፈልግ "CIA" ተረዳ! ከብዙ ጥናት በኃላ አንድ ሰው ተገኘ! የተገኘው ሰው ኮሎኔን "Khalifa Haftar" ይባላል! ይህ ሰው በአንድ ወቅት ጋዳፊ ወደ ስልጣን ሲመጣ አብሮት የነበረ ታማኝ የጦር መሪ እና አገልጋዩ ነበር! ጋዳፊ ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ሊብያ ከጎረቤት ሃገር "Chad" ጋር ጦርነት ውስጥ ስትገባ የሊብያን ጦር የመራውም ይህ ሰው ነበር! እንደ አጋጣሚ ታድያ ይህ ኮሎኔል በጦርነቱ ወቅት በ "Chad" ወታደሮች ተማርኮ ይታሰራል! ጋዳፊ የጦር መሪው "Khalifa Haftar" እንዲፈታ ጥረት ከማድረግ ይልቅ እስከመፈጠሩ ጭራሽ ረሳው! "Khalifa Haftar"ም ለ 7 ዓመታት በ " Chad" መንግስት ታሰረ! ይህ መረጃ ያለው "CIA" የ "Chad" ፕሬዝዳንት ጋር ደውሎ "Khalifa Haftar"ን እስር ቤት ሄዶ ሁለት አማራጮችን እንዲሰጡት አደረገ!
አማራጭ አንድ፡ እዚሁ እስር ቤት በስብሰህ እና የጦር ምርኮኛ ሆነህ ትሞታለህ? ወይስ
አማራጭ ሁለት፡ እንደዛ በታማኝነት ያገለገልከው የሃገርህ መሪ ጋዳፊ ከድቶኻል! እስከ መፈጠርህም አላስታወሰህም! እንደውም በመማረክህ በሽቋል! ስለዚህ ከእስር እንፍታህ! አሜሪካዊ ዜግነት እንስጥህ! ከ "CIA" ጋር አብረህ ስራ! የተበታተኑትን አማፅያን አድራጅተህ "Libyan National Army" የሚባል ጦር እዚሁ "Chad" ውስጥ አቋቁም! "CIA" በጦርም፣ በመሳርያም፣ በታክቲክም፣ በሃሳብም.. በሁሉም ነገር ይረዳኻል!
Guess what?
ኮሎኔል "Khalifa Haftar" ሁለተኛውም አማራጭ ተቀበለ! "CIA" "Khalifa Haftar"ን እና አማፅያኑን ጎረቤት ሃገር "Chad" ውስጥ አየረዳ እና እያሰለጠነ አቆያቸው!
ነገር ግን ያልታሰበ ነገር በመሃል ተፈጠረ!
በአሜሪካ መንግስት ይደገፍ የነበረው የ "Chad" መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት ተደረገ! መፈንቅለ መንግስት መደረጉ ችግር አልነበረውም! ነገር ግን በመፈንቅለ መንግስቱ ስልጣን የያዘው አካል የአሜሪካ አጋር ስላልነበረ "CIA" ጋዳፊን ለመጣል "Chad" ውስጥ የሚደግፋቸው እና የሚያሰለጥናቸው አማፅያን (Khalifa Haftar)ን ጨምሮ ከ "Chad" እንዲወጡ አዲሱ የ "chad" መንግስት አዘዘ!
ጌታዬ! "CIA" ምን እንዳደረገ ታውቃለህ?
"Khalifa Haftar"ን ጨምሮ አብረውት የነበሩ 300 አማፅያንን በናይጄሪያ፣ ዛየር እና ኬንያ በኩል አድርጎ ወደ አሜሪካ ወሰዳቸው! ከዛም ኮሎኔሉን ጨምሮ እነዚህን 300 የሚደርሱ ሊብያዊ አማፅያኖች የ "CIA" ዋና መቀመጫ የሆነችው "Virginia" ውስጥ መኖርያ ቤት ተሰጥቷቸው ለግዜው እንዲቆዩ አደረጉ!
ከአመታቶች በኃላ!
እ.ኤ.አ 2011 ላይ የአረቡ ዓለም ተቃውሞ(Arab spring) ተቀሰቀሰ! ቱኒዝያ፣ ግብፅ እና ሊብያ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ተነሳ! ይህንን አጋጣሚ ለ 30 ዓመታት ጓጉታ ስትጠብቅ የነበረችው አሜሪካ "Khalifa Haftar" እና አማፅያኑን ወደ ሊብያ በማስገባት አመፅ እና ጦርነቱ እንዲፋፋም አደረገች! ጋዳፊም በአማፅያዩ የተከፈተበትን ጦርነት ለማክሸፍ ከልክ በላይ እርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ። በዚህ መሃል የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት "Barack Obama" ከ "NATO" ጋር በመቀናጀት የአየር ላይ ጥቃቶችን ሊብያ ላይ ይፈፅም ጀመር! አማፅያኖቹ ከአሜሪካ በሚያገኙት ድጋፍ ምስራቅ ሊብያን መቆጣጠር ቻሉ! አባዬ! "Khalifa Haftar" በመሬት ይዋጋል፣ አሜሪካ በሰማይ ታግዘዋለች! ከስድስት ወራት ጦርነት በኃላ የሊብያ ዋና ከተማ በአማፅያኑ ቁጥጥር ስር ወደቀች! ጋዳፊ እና ልጆቹ ተደበቁ! አማፅያኑ እና "CIA" ተቀናጅተው ጋዳፊን ከተደበቀበት ለማግኘት አሰሳቸውን ቀጠሉ! በመጨረሻም "NATO" ጋዳፊ የሳተላይት ስልክ ተጠቅሞ የደወለበትን የስልክ መስመር መጥለፍ ቻለ! ከዛም ለማምለጥ ጋዳፊ ሲጓዝበት የነበረውን የጭነት መኪና በድሮን አሜሪካ "Las vegas" ላይ ቁጭ ብለው አጋዩት!
እ.ኤ.አ October, 20,2011 ላይ "sirte" በምትባል ከተማ አማፅያኑ ለ 42 ዓመታት ሊብያን የመራውን መሪያቸውን መሬት ለመሬት እየጎተቱ፣ እየተሳለቁ፣ ፎቶ እየተነሱ፣ ፀጉሩን እየነጩ እና እያሰቃዩ ገደሉት!
አለቀ!
ምዕራባዊያኑ እንዲህ ይሉታል!
"Muammar Gaddafi" አንባገነን ነው፣ ጨቋኝ ነው፣ ሌባ ነው፣ ገዳይ ነው፣ አፋኝ ነው፣ ደፋሪ ነው፣ ሽብርተኛ ነው፣ ሽብርተኞችን ደጋፊ ነው ፣ ጠላቶቹን ይገድላል፣ ተቃዋሚዎች ያስራል፣ ሲፈልግ እንዲሰወሩ ያደርጋል፣ የሱ ቢጤ ጨፍላቂዎቹን የአፍሪካ መሪዎች (ኤዲያሚን ዳዳን፣ ኢሳያስን፣ ሙጋቤን እና መንግስቱን) ይደግፋል!
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት "Ronald Reagan" ጋዳፊን "The mad dog of the middle east(የመካከለኛው ምስራቅ እብድ ውሻ)" እያለ ይጠራዋል!
ግን...ግን
"Muammar Gaddafi" በምዕራባዊያኑ እና በሃገሪቱ ጥቂት ሃብታሞች ተይዘው የነበሩ የእርሻ መሬቶችን ለደሃው የሰጠ፣ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት 10% የነበረውን የሃገሪቱን የተማረ ህዝብ ወደ 88% ያሳደገ፣ "United States of Africa" የምትባል ጠንካራ እና የራሷ መከላከያ ሰራዊት ያላት አፍሪካን መፍጠር የሚፈልግ፣ አፍሪካውያን አንድ ወጥ ፓስፖርት እንዲኖራቸው የሚሻ እና አህጉሪቱ አንድ የጋራ የመገበያያ ገንዘብ እንዲኖራት የሚፈልግ ሰው ነበር!
"Muammar Gaddafi" ሃገሩ ሊብያ ያላትን የነዳጅ ሃብት በአግባቡ እንድትጠቀም ያደረገ፣ በዚህም ስልጣን ሲይዝ እ.ኤ.አ 1969 ላይ ደሃ የነበረው የሊብያ ህዝብ በአፍሪካ ቁጥር አንድ ሃብታም ህዝብ እንዲሆን ያደረገ እና የሃገሪቱ "GDP" ከ 42 ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በ 600% እንዲያድግ ያደረገ መሪ ነበር!
እሱ ብቻ አይደለም!
ሊብያውያን በአፍሪካ ትልቁ የነብስ ወከፍ ገቢ የነበራቸው በእርሱ የስልጣን ግዜ ነበር! ጌታዬ! ሊቢያ በእርሱ የስልጣን ግዜ 0% እዳ ያለባት ሃገር ነበረች!
ሰውየው "Regional African satellite communication organization" ለሚባል ተቋም 300 ሚልዮን ዶላር በመስጠት ከአውሮፓ የሳተላይት ጥገኝነት አፍሪካ እንድትላቀቅ የሚያልም ሰው ነበር! አንዳንድ ደሃ የአፍሪካ ሃገራት የአፍሪካ ህብረት አባልነት መዋጮን መሸፈን ሲያቅታቸው ጋዳፊ መዋጮአቸውን ሳይቀር ይሸፍን ነበር!
"Muammar Gaddafi" አፍሪካ የራሷ "African Monetary Fund" የሚባል ተቋም እንዲኖራትም ይፈልግ ነበር!
"Gaddafi" የዶላር እና የይሮን የበላይነት ለማስቀረት የወርቅ ዲናሮችን አትሞ አፍሪካ እና የዓረቡ ዓለም በነዚህ የወርቅ ዲናሮች እንዲገበያይ ሳይቀር ይወጥን ነበር!
"Gaddafi" የሃገሪቱ የነዳጅ ሃብት "privatize" ተደርጎ እያንዳንዱ የሃገሪቱ ዜጋ የዚህ ነዳጅ ሃብት ባለቤት እንዲሆን የማድረግ ስራን ይሰራም ነበር! ለአዳዲስ ሙሽሮች 50 ሺህ ዶላር ቤት ለመግዣ እና መቋቋሚያ እንዲሆን በስጦታ መልክ ይሰጥ ነበር የሚባለው ጋዳፊ ምዕራባዊያኑ ሳይቀር በማይክዱት መልኩ ሃገሩን ድብን አድርጎ አሳድጓል!
ምን ዋጋ አለው ጌታዬ?
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት "Donald J. Trump" እንዲህ ይላል!
"...ዓለማችን ጋዳፊ እና ሳዳም ስልጣን ላይ ቢቆዩ ኖሮ ይሄንን ያህል ውጥንቅጥ ውስጥ አትገባም ነበር! ይህ ሁሉ ውጥንቅጥ እንዲፈጠር ያደረጉት ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ እና ሴጣኗ ሂላሪ ክሊንተን ናቸው! ጋዳፊ እና ሳዳም ጥሩ ሰዎች ናቸው እያልኩ አይደለም! ነገር ግን ስልጣን ላይ እንዲቆዩ ብናደርግ ኖሮ አሁን ላይ ለዚህ ሁሉ ጣጣ አንዳረግም ነበር!..."
እ.ኤ.አ 2016 ላይ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት "Barack Obama" አሜሪካ ጋዳፊን ከስልጣን ለማንሳት የከፈተችው ጦርነት በፕሬዝዳንትነት ግዜው ከሚፀፀትባቸው ውሳኔዎቹ ውስጥ አንደኛው እንደሆነ ተናግሮ አምኗል!
"Muammar Gaddafi" የገዛ ዜጎቹ መሬት ለመሬት እየጎተቱ ሲደበድቡት እና ሲሳለቁበት የጠየቃቸው እንዲህ ብሎ ነበር!
"What did i do to you?"(ምን አደረኳችሁ?)
መልካም ቅዳሜ! መልካም ምሽት
የቅዳሜ ቀደዳ 26-(፳፮)
እንደምነህ ጌታዬ? ቅዳሜሽ እንዴት ነው እናቴ?
ፈካ፣ ፀዳ፣ ዘና ወዳለው ቋሚው ቅዳሜያችን ተመልሰናል!
ምን መሰለህ?
.
.
.
እንደ "Belgium" አፍሪካ ላይ የተጫወተ አንድም ሃገር የለም! የቤልጂየሙ ንጉስ "Leopold II" እ.ኤ.አ 1884 ላይ አውሮፓ አፍሪካን ለመቀራመት ስትወስን "Congo" የእርሱ እጣ ሆነች!
ተዝቆ በማያልቅ የተፈጥሮ ሃብቷ የምትታወቀው "Congo" ወርቅ፣ አልማዝ፣ የዝሆን ጥርስ፣ መዳብ፣ ዩራንየም፣ ኮልታን እና ኮባልት ምናምን የሚባሉ ሃብቶቿ እና መዓድኖቿ ለዘረፋ ተመቻቹ!
"Leopold II" አውሮፓውያኖችን እንዲህ አላቸው!
"....ያለኝን የግል ሃብት "Congo" የምትባል አንዲት የአፍሪካ ሃገር ውስጥ ማፍሰስ እፈልጋለሁ! እዛች ሃገር ውስጥ ያለውን ምስኪን፣ ደሃ እና አሳዛኝ ህዝብ የተሻለ ህይወት እንዲኖ ማድረግ እሻለሁ! ሃይማኖት የላቸውም! ስለዚህ ሚሽነሪዎችን ከዚህ ልኬ ክርስትናን እንዲቀበሉ አደርጋለሁ፣ አሰለጥናቸዋለሁ፣ ከአውሬነትም እታደጋቸዋለሁ! ስለዚህ እቺን ሃገር እንደ "personal Properly" (የግል ንብረቴ) አድርጌ ወስጃታለሁ!...." ብሎ ተረከበ!
በሃገሪቷ የሚገኙ የሃገር ሽማግሌዎች እና የጎሳ መሪዎችን ሰብስቦ "Congo" የግል ግዛቱ(ንብረቱ) እንደሆነች የሚደነግግ ስምምነት አስፈረማቸው! ሃገሪቷንም "Congo Free State" ብሎ ሰየማት!
በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ አረመኔ ንጉስ የህዝቡን እጅ እና እግር እየቆረጡ አስገድዶ ያሰራው ጀመር! የሃገሪቱን የተፈጥሮ ሃብትም እያጋዘ ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ እንደጉድ ነገደው!
ይህ ሰው "Congo"ን የግል ንብረቱ አድርጎ ሲሸምታት የህዝብ ቁጥሯ ወደ 20 ሚልዮን ይጠጋ ነበር! ጌታዬ! ብታምንም ባታምንም ከዚህ ውስጥ 10 ሚልዮን የሚሆነውን ህዝብ ቅርጥፍ አድርጎ ገድሏል!
"...እንዴት አልተወራለትም? እንዴት ሳላውቀው?" ካልከኝ ደግሞ፣ መልሱ! "...ሟቾቹ አውሮፓውያን፣ አይሁዳውያን ወይንም አሜሪካውያን ሳይሆኑ እንደ አውሬ የሚታዩት "አፍሪካውያን" ስለሆኑ ነው!
ይህ ንጉስ ወደ 200 የሚጠጉ ኮንጎዋዊያንን ወደ ሃገሩ ቤልጄየም በመውሰድ "የሰው ልጅ Zoo" ከፍቶ አፍሪካውያን እንደ እንስሳ እንዲጎበኙ ያደረገ ሰው ነው! አባዬ! ጥቁሮች በሽቦ የታጠረ "Zoo" ውስጥ ሆነው አውሮፓውያን እንደ ብርቅዬ እንስሳ እየጎበኟቸው ከውጪ ሙዝ ሲወረውሩላቸው ዝም ብለህ አስበው!
ከግዜያት በኃላ!
ይህ ንጉስ ሞተ! አፍሪካውያንም እ.ኤ.አ ከ 1950ዎቹ በኃላ ነፃነታቸውን ማግኘት ጀመሩ! ከፍተኛ ውስጣዊ ጫና እና የህዝብ ተቃውሞ የቤልጄየም መንግስት ላይ እየደረሰ ሲመጣ ተተኪው ንጉስ ኮንጎዋዊያን የራሳቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች መመስረት እንዲችሉ እና ምርጫ እንዲያደርጉ ፈቀደች! ከምርጫው በኃላም ኮንጎ ነፃነቷን እንደምታገኝ ቃል ገባች!
በዚህ መሃል ኮንጎ ተዝቆ የማያልቅ የተፈጥሮ ሃብት እንዳላት፣ ህዝቦቿ የተሻለ ኑሮ እንደሚገባቸው የሚያስብ፣ አፍሪካን የሚወድ፣ ስለ አፍሪካ አንድነት የሚጨነቅ፣ የተሻለች አፍሪካን ማየት የሚያልም፣ የተማረ፣ የሰለጠነ፣ ስርዓት ያለው፣ ግርማ ሞገሱ የሚያምር፣ መልከ መልካም ጎልማሳ "Congolese National Movement (የኮንጎ ብሄራዊ ንቅናቄ)" የሚባል የፖለቲካ ፓርቲን መስርቶ ምርጫ ተወዳደረ! አብላጫ ድምፅ አግኝቶም አሸነፈ! እ.ኤ.አ 1960 ላይ የመጀመርያው ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የተመረጠ የኮንጎ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነ!
ሰውየው "Patrice Lumumba" ይባላል! ከነፃነት በኃላ የኮንጎ የመጀመርያው ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ ሲመረጥ ገና 34 ዓመቱ ነበር!
ከዛስ?
እ.ኤ.አ ሰኔ, 30,1960 ላይ ቀኝ ገዢዎቹ በተገኙበት መድረክ ይህንን ንግግር አደረገ!
"....የዛሬዋ ቀን በልባችሁ ፀንታ ትቆይ! ሃገራችን ነፃ ወጥታለች! ስለዚች ቀን ለልጆቻችሁ እና ለልጅ ልጆቻችሁ በኩራት ወደፊት ታወራላችሁ! ሃገራችን አሁን ላይ በገዛ በራሷ ልጆች እጅ ትገኛለች! ወንድሞቼ እና እህቶቼ! ከዚህ በኃላ አዲስ ትግል ይጠብቀናል! ይህ ትግላችን ሃገራችንን ወደ ሰላም፣ እድገት እና ታላቅነት መውሰድ ነው! በጋራ ሆነን ማህበራዊ ፍትህን እናሰፍራለን! እስከዛሬ ጥቁር በመሆናችን ተዋርደናል፣ ተሰድበናልን፣ ተንቀን ኖረናል! የገዛ መሬታችንን ተዘርፈናል! የሃገራችን ህግ ለነጮች ያደላ ነው! ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው እና በእምነታቸው ብቻ ታስረዋል፣ ተገድለዋል! ከተማዎቻችን በቅንጡ የነጮች ቤትና በጥቁሮች የዳስ መኖርያ ቤትተወሯል! ጥቁሮች በገዛ ሃገራቸው የተለያዩ ሬስቶራንቶች እና ሲኒማ ቤቶች እንዳይገቡ ተከልክለዋል። ይህንን ድል ያገኘነው በከባድ ትግል ነው። በግኝ ግዛት ወቅት በነበርንባቸው 80 ዓመታት የደረሰብን ቁስል አሁንም እንዳመረቀዘ ነው! አሁንም ያመናል! በቂ ምግብ ሳይሰጡን ጉልበታችን በዝብዘዋል! እንደ ሰው ልጅ እንኳ የምንለብሰውን አሳጥተውናል! ልጆቻችንን በቅጡ ማሳደግ እንኳን አልቻልንም!
ረጅም እድሜ ለነፃነት ላበቁን የነፃነት ታጋዮቻችን! ረጅም እድሜ ለነፃነት እና ለአፍሪካ አንድነት! ረጅም እድሜ ለነፃ እና ሉዓላዊት ሃገር ኮንጎ! ..."
ከምዕራቡ ዓለም የተቀዳ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለምን ፍፁም የማይደግፈው እና "Positive neutralism" በሚባል መርህ የሚመራው "Lumumba" ከነጮቹ ተፅእኖ ነፃ የሆነች ኮንጎን ለመገንባህ "ሀ" ብሎ ጀመረ!
ነገር ግን ከገዛ የሃገሩ ህዝቦች እና የሃገሪቱ ጦር ከባድ ፈተና ገጠመው!
ዋናው ፈተና!
"Katanga" የሚባል የሃገሪቷ ክፍል ከፍተኛ የመዓድን ክምችት አለ! ዓለም አቀፍ መዓድን አውጪ ተቋማት ያሉትም እዚህ ነው! ምዕራባውያኑ ሃብት የሚያግዙት ከዚህኛው የሃገሪቱ ክፍል ነው! "Patrice Lumumba" ደግሞ ይህንን የሚያስቆም አይነት መሪ ሆነ!
ታክስ ሊጨምርባቸው ወይ ደግሞ ጭራሹኑ ሊያባርራቸው እንደሚችል የገመቱት ቤልጄየሞች እዚሁ የሃገሪቱ ክፍል ውስጥ የሚገኙ አማፅያንን ረድተው የመገንጠል ጥያቄ እንዲያቀርቡ አደረጉ! በአሜሪካ እና ቤልጄየም የሚረዱት እነዚህ አማፅያን ሰውየውን አላስቀምጥ አሉት!
ወደ ስልጣን ከመጣ ወራት እንኳን ያላስቆጠረው "Lumumba" ፊቱን ወደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) አዙሮ የቤልጄም ወታደሮች አማፅያኑን እየረዱ እንደሆነ ፣ የአማፅያኑን የመገንጠል እና ሃገር የመበታተን ፍላጎትም ቤልጄየም እየደገፈች እንደሆነ እና የቤልጄም ወታደሮች ከዚህ ክልል እንዲወጡ፣ በምትኩም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ሃይል ገብቶ ሃገሪቷን የማረጋጋት ስራ ይስራልኝ ብሎ ለመነ!
ጌታዬ! የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩን ከምንም ሳይቆጥረው ዝምታን መረጠ!
ያኔ "Lumumba" ራሽያ ጋር ሄዶ በር አንኳኳ! በወቅቱም ራሽያ አፍሪካ ላይ ያላትን ተፅህኖ ማጠናከር አጥብቃ ትፈልግ ስለነበር ጥያቄውን ሳታቅማማ ተቀብላ "Lumumba"ን መርዳት ጀመረች!
አንደምታውቀው ወቅቱ አሜሪካ እና ራሽያ ቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ውስጥ የነበሩበት ግዜ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ራሽያ ፊቷን ወደ ኮንጎ ማዞሯ አሜሪካ እጅግ እንድትሰጋ አደረጋት!
አሜሪካ እና ቤልጄየም ለዘመናት ተባብረው ሲበዘብዟት እና እንደ ልባቸው ጠፍጥፈው የሰሯት ኮንጎ ከእጃቸው ልትወጣ እንደሆነ ገባቸው! የሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለምን የሚያቀነቅኑ መንግስታት አፍሪካ ውስጥ መመስረት መጀመራቸው እና በራሽያ መንግሥት ድጋፍ ማግኘታቸው ያሳሰባት አሜሪካ "Patrice Lumumba" መወገድ እንዳለበት ወሰነች!
ሰውየውን አሜሪካ፣ "CIA"፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ቤልጄየም፣ በሃገሪቷ ውስጥ ያሉ አማፅያን እና የገዛ ከስሩ ያፈነገጡ ባለስልጣናት ወጥረው ያዙት!
የሃገሪቱ መከላከያ ውስጥ ያሉ ጥቁሮች የእርከን እድገት በፍጥነት እንደሚያገኙ፣ ደሞዝ እንደሚጨመርላቸው፣ ከነጮቹ ሃብት ንብረት ተቀምቶ ለነሱ እንደሚሰጣቸው እና ሃገሪቱ በአንዴ እንደምትለወጥ ጠብቀው ነበርና እነርሱም ፊታቸውን ያዞሩበት ጀመር!
እንዴት ገደሉት?
አሜሪካ እና ቤልጄየም "Katanga" ያሉትን አማፅያን በጦር መሳርያ ረድተው ለራሳቸው እንዲመች አድርገው የሰሩትን መንግስት ስልጣን እንዲቆናጠጥ አደረጉ! "Mabutu Sese seko" የሚባል ቀውስ አምባገነንን ስልጣን ላይ አስቀመጡ! "Lumumba" ሃገሪቷን ሰባት ወር እንኳን በቅጡ ሳይመራ በቁጥጥር ስር አውለው አሰሩት! የገዛ ሚስቱ እና ልጁ እያዩ የሃገሪቱ ወታደሮቹ የፊጥኝ በገመድ አደባባይ ላይ ጠፍረው ፀጉሩን እየጎተቱ ወሰዱት! በመጨረሻም በቤልጄየም መንግስት ትዕዛዝ ብዙ ተስፋ ሰንቆ ወደ ስልጣን የመጣው "Lumumba" እንደ ወንጀለኛ ዛፍ ላይ ታስሮ እንዲረሸን ተደረገ!
አሳዛኝ ነገር!
"Lumumba"ን ከገደሉት በኃላ ሬሳው ላይ "ሰልፈሪክ አሲድ" በማፍሰስ ሰውነቱ እንዲበጣጠስ እና ፈፅሞ እንዳይገኝ አድርገዋል! በዚህ ግዜ አንድ ቤልጄማዊ ወታደር ሁለት ጥርሶቹን ነቅሎ ወደ ሃገሩ ቤልጄም ወስዷል!
አሁን ላይ!
የ "Lumumba" ግድያ ተፈፃሚ እንዲሆን የአሜሪካ መንግስት ሃላፊነት ሰጥቶት የነበረው የ "CIA" ኤጀንት "Larry Devlin" ቃል በቃል እንዲህ ይላል!
"....."Lumumba" ለኮንጎ ብቻ ሳይሆን ለዓለማችንም አደጋ ነበር! አደጋ እንዲሆን ያደረገው ራሽያን ወደ ኮንጎ እንድትገባ ማድረጉ እና የነርሱን ወዳጅነት መምረጡ ነው! ይህ ለኛ ትልቅ ስጋት ነበር! ቀስ በቀስ ራሽያ ኮንጎን ከኛ ቁጥጥር ውጪ ታደርግብን ነበር!..."
በነገራችን ላይ "CIA" የመረጠው ሰውየውን ማስወገጃ መንገድ መርዞ መግደል ነበር! በወቅቱ "CIA" ውስጥ ኬሚስት እና የ"poison Expert" የነበረ "Sidney Gottlieb" የሚባል ሰው የጥርስ ሳሙና ውስጥ መርዝ ቀምሞ በመክተት "Lumumba"ን መርዞ ለመግደል ወደ ኮንጎ አቅንቶ የነበረ ቢሆንም አልተሳካም! ጌታዬ! ካላመንከኝ "Sidney Gottlieb" ብለህ ብትፈልግ እውነታውን ትረዳለህ!
ይፋዊ (declassified) የ "CIA" ዶክመንቶችን ብትመለከት ደግሞ "Lumumba"ን አስገድሎ ስልጣን ላይ የወጣው "Mobutu Sese Seko" ከአሜሪካ የገንዘብ ስጦታ እና የጦር መሳርያ ድጋፍ እንደተደረገለት በግልፅ ያትታል!
በአንድ ወቅት "Malcolm X" እንዲህ ብሎ ነበር!
"...."Lumumba" አፍሪካ በታሪኳ አይታው የማታውቀው ድንቅ መሪ ነው! እርሱ ማንንም አይፈራም! ነጮቹ እጅግ በጣም ይፈሩት ስለነበር ነው ያስገደሉት! ሊገዙት እና ሊደልሉት ሞክረው አልቻሉም! ሊያስፈራሩት ሞክረው ሊፈራቸው አልቻለም!....."
እናም!....ብዙዎች አሁን ኮንጎ ያለችበት የላሸቀ ሁኔታ ካዩ በኃላ... "Lumumba's assassination was Congo's original sin" ብለው ይደመድማሉ!
መልካም ምሽት! መልካም ቅዳሜ!
የቅዳሜ ቀደዳ 27-(፳፯)
እንዴት ነህ ጌታዬ? እንደምን ነሽ እናቴ?
እንደተለመደው መጥተናል!
ምን መሰለህ?
ታላቅነት ደስ ይላል! ታላቅነት ያኮራል! ታላቅ ህዝቦች ነበሩ! የጥንት ፐርሽያዎች(Persians) እነርሱ ናቸው!
"አረቦች ናችሁ ወይ?" የሚለውን ጥያቄ አይወዱትም! ይበሳጫሉ! "...እኛ አረቦች ሳንሆን ፐርሺያኖች ነን!..." ብለው ይመልሳሉ። ጥንታዊ ታሪክ ካለ እነርሱ ባዶ ነው! የብዙ ሺህ አመታት ታሪክ ያላቸው ጥንታዊ ህዝቦች ናቸው! ሂሳብ ከነሱ እንደፈለቀ ይነገራል፣ መድሃኒት ቅመማ ተሰጥቷቸዋል፣ የአስትሮኖሚ እና ፊዚክስ ሊቅ ናቸው፣ ኬሚስትሪ በእጃቸው ነበር፣ የግንባታ እና አርክቴክቸር ፈር ቀዳጆች ናቸው። ሃይማኖት፣ ፍልስፍና፣ ሳይንስ ከነርሱ ፈልቋል! ጥንታዊው "Zoroastrianism" የነርሱ ነው!
እነዚህ ህዝቦች ከዛሬ 2500 አመት በፊት አንድ "Cyrus the great(ታላቁ ቂሮስ)" የሚባል ንጉስ ነበራቸው!ኤስያ፣ ከፊል አውሮፓ እና ሰሜን አፍሪካ የእርሱ ግዛት ነበር። ንጉሱ የ "ምህረት ንጉስ" በሚባል ቅፅል ስም ይታወቃል። በግዛት ማስፋፋት ወቅት የተያዙ ምርኮኖችን አይበድልም! የአሜሪካው ፕሬዝዳንት "Abreham Lincoln" የዛሬ 158 አመት ባርነትን ከማስወገዱ በፊት "Cyrus" ከ 2500 አመት በፊት ባርነትን ያስወገድ ስልጡን ንጉስ ነበር! ግዛት ሲያስፋፋ የወረራቸው ማህበረሰቦች ባህል፣ ቋንቋ እና እሴት ተጠብቆ እንዲቆይ ጭምር ያደርግ ነበር!
ይህ ንጉስ በትንቢተ ኢሳያስ፣ እዝራ እና ዳንኤል ውስጥ በስፋት ተቀምጧል! በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ አይሁዳዊ ሳይሆን "በእግዜር የተቀባ(anointed)" የተባለለት ብቸኛ "non-Jew" ነው። "Cyrus the great" በወቅቱ አይሁዳውያንን ከባቢሎኖች ቀንበር ነፃ እንዳወጣቸውም ይነገራል! ጌታዬ! እነዚህ የጥንት "Persians(ፐርሺያኖች)" እነማን መሰሉህ?
የአሁኖቹ "ኢራናዊያን!" ናቸው!
ብዙዎች ኢራን አረብ ትመስላቸዋለች! ኢራኖች አረቦች ሳይሆኑ ከአረቦች በብዙ የሚለዩ የራሳቸው ቋንቋ እና ባህል ያላቸው ህዝቦች ናቸው! ቋንቋቸው "Farsi" ይባላል! 99% ህዝባቸው ሙስሊም ነው! ከዚህ ውስጥ አብዛኛው "Shia Muslim" ነው!
"ኢራን" ሲባል ብዙዎቻችን ስለ ኒዩክለር፣ ማዕቀብ ወይም አሸባሪነት እናስብ ይሆናል! የህዝቦቿ ታሪክ እና ማንነት ግን ከዚህ ይዘላል! ኢራናዊያን(ፐርሺያኖች) እጅግ የተማሩ ህዝቦች ናቸው። አሁን ላይ 4.5 ሚልዮን ኢራናዊያን በየአመቱ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ! 90% የሚሆነው ጎልማሳ በሚገባ ማንበብ እና መፃፍ ይችላል!
ዘመናዊ ታሪካቸው!
እ.ኤ.አ 1940ዎቹ ላይ እንግሊዝ ኢራን ያላትን የነዳጅ ሃብት ለማውጣት ተከሰተች! ነገር ግን ኢራን በገዛ ሃገሯ ከነዳጅ ሃብቱ 16% እንድታገኝ ተደርጎ አብዛኛውም የነዳጅ ሃብት እንግሊዝ እንድትዘርፈው ተደረገ! በእንግሊዝ ቁጥጥር ስር ሆኖ እንደ ልብ ሲዘረፍ የኖረው የሃገሪቱ የነዳጅ ሃብት ለኢራናውያን ጥቅም እንዲውል በማሰብ እና ደሃው የሃገሩቱ ህዝብ ከዚህ ሃብት ተጠቃሚ እንዲሆን እ.ኤ.አ 1951 ላይ "Mohammad Mosaddegh" የሚባል የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ዘርፉን "nationalize" አድርጎ እንግሊዞችን አባረረ! እንግሊዝ "....ነዳጅ ማጣርያዎችን ገንብቼ ፣ እንዴት ነዳጅ እንደሚወጣ አስተምሬ ተባረርኩ?..." ብላ ቀወጠችው! ጠቅላይ ሚንስትሩንም ነከሰችበት! መጀመርያ ጉዳዩ በንግግር እንዲፈታ ሞከረች! ሰውየው አሻፈረኝ እለ! ያኔ እንግሊዝ ከአሜሪካ ጋር ተመሳጥራ ሰውየው ላይ መፈንቅለ መንግስት አስደርጋ እስር ቤት አስወረወረችው!
ከዛስ?
እንግሊዝ እና አሜሪካ ለራሳቸው የሚመች እና የሃገሪቷን የነዳጅ ሃብት እንዲዘርፉ ፍቃድ የሚሰጣቸው ንጉስን አስቀመጡ! ሰውየው ንጉስ "Mohammad Reza Shah" ይባላል! ንጉሱ ከአሜሪካ እና የአውሮፓ መንግስታት ጋር ሸሪክ ስለሆነ ባልተለመደ መልኩ ኢራን ውስጥ ስር ነቀል ለውጦችን ማምጣት ጀመረ! ሃገሪቷ አደገች፣ መሰርተ ልማት ተስፋፋ፣ የሃገሪቷ የነዳጅ ሃብት በቢልዮን ዶላሮች ማምጣት ጀመረ!(በርግጥ ንጉሱ ከዚህ ውስጥ አብዛኛውን ዘርፎታል!)
ለማንኛውም ለውጡ ሃገሪቷን የምዕራቡ ዓለም ገፅታ እንዲኖራት አደረገ! ትምህርት ተስፋፋ! ሴቶች የመምረጥ መብት እንዲኖራቸው ተደረገ! ብዙ ገደቦች ተነሱ! ኢራን "Middle East" ውስጥ የምትገኝ ሌላ "አሜሪካን" ሆነች! የአሜሪካ ባህል፣ ቋንቋ እና የአኗኗር ዘይቤ የኢራን ህዝቦች ላይ መስረፅ ጀመረ! ብዙዎች ይህንን ለውጥ "Americanism"ን የማጥመቅ አካሄድ አሉት! ብዙ ኢራናዊያንንም አስቆጣ! በተለይ ደግሞ የሃገሩቱ የእስልምና መሪዎችን!
"...ንጉሱ ሃገሩን ሸጧል፣ የአሜሪካ "puppet" ነው፣ ሙሰኛ ነው! የኢራናዊያን ታሪክ እና ባህል እንዲጠፍ እና አሜሪካዊነት እንዲስፋፋ በር ከፍቷል! ከዛም አልፎ የሃገሪቷን የነዳጅ ሃብት አዘርፎ ይበልጥ ህዝቡን አደህይቷል!..." በማለት ታመፀበት! እ.ኤ.አ 1979 ላይ ንጉሱ ሸሽቶ ወደ አሜሪካ ሄደ! የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት "Jimmy Crater"ም ጥገኝነት ሰጡት!
በዚህ መሃል ይህንን የህዝብ አመፅ ሲመራ የነበረው "Ayatollah Ruhollah Khomeini" ከፈረንሳይ ወደ ሃገሩ ኢራን ተመለሰ! ከዛም በዛው አመት እ.ኤ.አ 1979 ጀምሮ ኢራን "Islamic Republic of Iran" ተባለች!
ከዛስ?
ሃገር በድሏል የተባለው ንጉስ ፍትህ ሳያገኝ ወደ አሜሪካ መሽሹ እና ለንጉሱ የአሜሪካ መንግስት ጥገኝነት/ከለላ መስጠቱ ያበሳጫቸው ወጣት ኢራናዊያን የሃገሪቱ ዋና ከተማ የሆነችው "ቴህራን" ውስጥ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በመሄድ 52 አሜሪካውያንን አገቱ! የታገቱትን አሜሪካውያንም ወጣቶቹ አይናቸውን በጨርቅ አስረው ሲያንገላቷቸው በቴሌቪዥን መስኮት ታየ!
ያኔ አሜሪካ እና ኢራን የለየላቸው ጠላቶች ሆኑ!
ከ 1979ኙ "Islamic revolution" በኃላ የሃይማኖት መሪው የኢራን "Supreme leader" እንዲሆኑ ተደረገ! አሁን ላይ የኢራን "Supreme leader" "Ali Hosseini Khamenei" ይባላሉ! የሃገሪቱ የመጨረሻው ውሳኔ የእርሳቸው ነው! የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት የእርሳቸውን ያህል ስልጣን የለውም!
አሜሪካ ሰውየውን እንደዚህ ትገልፀዋለች!
"....ገንዘብ አለው፣ ጥይት አለው፣ መረጃ አለው፣ የሃገሪቷ እስር ቤቶች ቁልፍ በእጁ ነው፣ ሚድያው በእርሱ ቁጥጥር ስር ነው! ህግ አውጪው፣ ህግ ተርጓሚው እና ፖሊሱ በእርሱ ስር ነው! የራሱን የኢኮኖሚ ኢምፓየር ገንብቷል! የሃገሪቷ ጦር አዛዥ ሳይቀር እርሱ ነው! ኢራናውያን ታፍነው ይገኛሉ! ሰውየው የምዕራቡን ዓለም አይወድም! አሜሪካን አንደ ጭራቅ ያያል! ሽብርትኞችን ይደግፋል! "Hezbollah" እና "Hamas"ን ያስታጥቃል! ኑውክለር ያበለፅጋል! ለዓለም ስጋት ነው!..." ወ.ዘ.ተ...
አሜሪካ ኢራን ላይ ማዕቀብ መጣል የጀመረችው ከኢምባሲ ሰራተኞቹ እገታ በኃላ የዛሬ 42 አመት ነው!
አሜሪካ ኩባ፣ቬንዝዌላ፣ ሰሜን ኮርያ እና ሊብያ ላይ የጣለችው ማእቀብ ቢደመር ኢራን ላይ የጣለችውን ያህል አይደርስም!
ምንም አይነት የንግድ ግንኙነት ከኢራን ጋር እንዳይደረግ፣ ነዳጇን ማንም እንዳይገዛት፣ ከኢራን ባንኮች እና የፋይናን ተቋማት ጋር ምንም አይነት "transaction" እንዳይኖር እና የኢራን ባለስልጣናንት ወደ አሜሪካ ድርሽ እንዳይሉ አድርጋለች። የኢራን ምንጣፍ እንኳን ሳይቀር ወደ አሜሪካ መግባት አይችሉም!
በእነዚህ ማዕቀቦች ሳብያ ኢራናዊያን ያላቸው ብቸኛ አማራጭ በራሳቸው መንገድ የሃገሪቷ ኢኮኖሚ እየተንገዳገደም ቢሆን እንዲቆም ማድረግ ነበር! በፊት ከአሜሪካ እና አውሮፓ ይገዙ የነበሩ ምርቶችን እራሳቸው ማምረት እንዲጀምሩም አድርጓቸዋል! ችግሩ በዚህ ጫና ውስጥ የሃገሪቷ ገንዘብ የመግዛት አቅም አጥቶ ብዙ ዜሮዎች ከኃላው እየተጨመሩበት ነው! መድሃኒቶችን ላይ ማዕቀብ መጣል ባይቻልም አብዛኛዎቹ ዓለም አቀፍ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች ከአሜሪካ ጋር ላለመጎራበጥ በሚል ለኢራን መድሃኒቶችን ከመሸጥ ተቆጥበዋል። በዚህ ምክንያት ብዙዎች ይሰቃያሉ! ጌታዬ! ጋዜጣ ለማተም ወረቀት ማስገባት ሳይቀር መከራ ነው! የስጋ፣ ወተት እና ዳቦ ዋጋ ከ 20% በላይ ጨምሯል!
በዚህ ሁሉ ጫና ውስጥ ኢራን 865 ሺህ ወታደሮችን ይዛ ራሽያ እና ቻይናን የአደጋ ግዜ ተጠሪ በማድረግ እራሷን ከአሜሪካ በመጠበቅ ላይ ትገኛለች!
".....እስራኤል ከምድረ ገፅ መጥፋት አለባት ብለው የሚያስቡ እና አሜሪካ ሼጣን ናት ብለው ለሚናገሩ ኢራናውያን እንዴት ኒዩክለር ይሰጣል?...." ብላ የምትከራከረው አሜሪካም ኢራንን ለማንበርከክ መታተሯን ቀጥላለች!
ማጠቃለያ!
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር "Benjamin Natanyahu" በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ "....የእስራኤል ሶስቱ አደጋዎች ማን ማን ናቸው?..." ተብሎ ሲጠየቅ
.
.
.
Iran
Iran
Iran
ብሎ መልሷል! ዓለምን ጠፍጥፋ የመስራት አጋጣሚ የነበራት ታላቋ ኢራን ዛሬ ላይ ተዳክማ በዚህ ሁሉ ጫና ውስጥ ትገኛለች! በታሪክ አጋጣሚ ታላቅ መሆን ቀላል ነው! ከባዱ ታላቅነት አስጠብቆ መቆየት ነው!
መልካም ምሽት! ፍክት ያለ ቅዳሜ!

(በወንድዬ እንግዳ)
፡ ብቻ ምን አለፋሽ 😕

ይሄ ልቤ ደሞ ሰውን ይወዳል…የመቀየምን ጥግ አያውቅበትም…እስዋ መስታዋቴ ናት ያደፈውን ማትነቴን እማይባት…

እስዋ ሰላሜ ናት 💖

🪴 @monhappy 🌼
@BINCJ90 🌴
:)
ከእለታት የሆነን ቀን 🥀

የሆነ ቀን…እራስህን ብቻህን በህይወት ውስጥ ታገኘዋለህ…እኔ ሰው የለኝም እንዴ ብለህ እስከምትገርም እራስህን ብቻህን ታገኘዋለህ…

🌷 @monhappy🌷
🌺 @itsmefilimon 🌺
2025/06/29 18:03:58
Back to Top
HTML Embed Code: