Telegram Web Link
በዚህ መርጫ ቢያንስ ፓርላማ ውስጥ ለኛ ድምፅ መሆን የሚችል ጥቂት ተወካይ ካገኘን ትልቅ ድል ነው።
ሰለዚህ በድምፃችን እንጠቀምበት
@nidatube @nidatubebot
አስቸኳይ መረጃ !

"ምርጫው እስከ ምሽቱ 3:00 ሰአት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ይቀጥላል ።"
ስብራቶች ሁሉ የነገር መጨረሻዎች አይደሉም፤ እንዲያውም አንዳንድ ስብራቶች የመልካም ጅማሬ ብስራቶች ይሆናሉና ተስፋ አትቁረጥ!
©abu kudama

@nidatube @nidatubebot
🐺 ቀበሮው ዶሮውን «የአባትህ ድምፅ በጣም ደስ ይለኝ ነበር» አለው።
🐓 ዶሮውም « ታዲያ የኔም ድምፅ እኮ እንደ አባቴ ነው» በማለት መለሰ።
🐺 ቀበሮውም «እንደዛ ከሆነ እባክህ ልታሰማኝ ትችላለህ ??» በማለት ተማጸነው።
🐓 ዶሮው «ምን ችግር አለው !» በማለት ጩኸቱን ለማሰማት ዓይኑን ሲጨፍን ቀበሮው ይዞት ተፈተለከ።

ውሾች ሁሉ ዶሮውን ከቀበሮው አፍ ለማስጣል እየጮኹ እግር በእግር ተከታተሉት።

🐓 ዶሮው ለቀበሮው «ከውሾቹ ለመዳን ከፈለግክ ዶሮው የእናንተ ሰፈር አይደለም !!» በላቸው አለው። ቀበሮውም የተባለውን ለመናገር ሲሞክር ዶሮው ከአፉ አመለጠው።
🐺 ቀበሮውም በፀፀት ተውጦ «ዝም ማለት ሲገባው የተናገረ አፉ ይረገም ፤ ይኮነን» አለ።
🐓 ዶሮም በበኩሉ «መንቃት ሲገባው የተጨፈነ አይን ይረገም፤ ይኮነን» አለ።

( ط أ /Aumar Alaa)

® Awwal Hamza Hamza

@nidatube @nidatubebot
የኡዱሒያ ቅድመ መስፈርቶች የትኞቹ ናቸው?

ሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል‐ዑስይሚን አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ብለዋል:‐

1⃣ የሚታረደው እንስሳ "በሂመት አል‐አንዓም" በመባል ከሚታወቁት ግመል፣ ላም ወይም በሬ እና በግ አልያም ፍየል መሆን አለበት።

2⃣ በሸሪዓ የተገደበለት የእድሜ ወሰን ላይ የደረሰ መሆን አለበት። ማለትም:‐

📌 በግ ከሆነ፥ ስድስት ወር የሞላው መሆን አለበት።

📌 ፍየል ከሆነ፥ አንድ አመት የሞላው መሆን አለበት።

📌 ላም ወይም በሬ ከሆነ፥ ሁለት አመት የሞላው መሆን አለበት።

📌 ግመል ከሆነ፥ አምስት አመት የሞላው መሆን አለበት።

3⃣ የሚታረደው እንስሳ በሸሪዓ የኡዱሒያን ብቁነት ለማረጋገጥ ከተጠቀሱት ጉድለቶች እና እንከኖች ነፃ መሆን አለበት። እነሱም:‐

📌 ግልፅ ከሆነ ሸውራራነት ነፃ መሆን አለበት።

📌 በግልፅ ከሚታወቅ በሽታ ነፃ መሆን አለበት።

📌 በጉልህ ከሚታይ አንካሳነት ነፃ መሆን አለበት።

📌 በከፍተኛ ሁኔታ ከመክሳት እና ከመድከሙ የተነሳ መቅኒ የሌለው ከመሆን ነፃ መሆን አለበት።

🔖የኡድሒያን ቆዳ መሸጥ ይቻላልን?

ኡድሒያ የሚታረደው ወደ አላህ ለመቃረብ ነው!
ስጋውን ለሶስት ከፍሎ፥ አንድ ሶስተኛውን ለቤት፣ አንድ ሶስተኛውን በስጦታ መልኩ ለዘመድ፤ለጎረቤትና ለጓደኛ፣ አንድ ሶስተኛውን ሳይበስል ለአቅመ-ደካሞች መስጠቱ የጠበቀ ሱና ነው

የኡድሒያውን ቆዳም ይሁን ሌላ ነገር ሽጦ ገንዘቡን መጠቀም ወይም በገንዘቡ ፋንታ ለሰራተኛ መስጠት አይቻልም!

ቆዳውን ሳይሸጡ ለራስ መጠቀም ወይም ለአቅመ ደካማ በነጻ-ሰደቃ- መስጠት ግን ይቻላል

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

ኡስታዝ ጣሀ አህመድ

@nidatube @nidatubebot
👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ግብዣ ወደ ቱርክ ሊጓዙ ነው

ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ቱርክ የሚጓዙት በአገሪቱ ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ግብዣ መሆኑን የቱርክ ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬትን ጠቅሶ አናዱሉ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት ፕሬዝደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ቱርክ ለኢትዮጵያ የትኛውንም አይነት ድጋፍ ታደርጋለች በማለት ወዳጅነታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

ፕሬዝደንቱ ይህን ማለታቸው የተሰማው ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ በተወያዩበት ወቅት እንደነበር ተገልጾ ነበር።

ሁለቱ መሪዎች ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም በስልክ በተወያዩበት ወቅት ቱርክ ለኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ ፕሬዝደንት ኤዶጋን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ቱርክ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ካደረጉ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን የጨርቃ ጨርቅ እና የኤሌክትሪክ ማስተላላፊያ ገመዶች ማምረቻዎችን ጨምሮ የቱርክ ኩባንያዎች 2.5 ቢሊዮን ዶላር በኢትዮጵያ ፈሰስ ማድረጋቸውን ከዚህ ቀደም የቱርኩ ዜና ወኪል አናዱሉ ዘግቧል።

ቱርክ በመካከለኛው ምሥራቅ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ ነች።

Bbc

@nidatube @nidatubebot
ስድስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል።
የወንድማችን ሙሐመድ ሳልህ ልጆች ልጆቻችን ናቸው።
ቤተሰቦቹ ቤተሰቦቻችን ናቸው። እርሱን ማጣት ሃዘኑ ከባድ ነው። ከወንድማችን ቤተሰቦች ጎን በመቆም የአላህን ውዴታ እንፈልግ።

በቤተሰቦቹ ፈቃድ የቤተሰብ እድር አባላት በሆኑ ሶስት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000427892232
ይማም አህመድ
ኢስማዒል ይስማው
ሙሐመድ ተስፋዬ

@nidatube
የሴቶች፣ህጻናት እና ወጣቶች ሚኒስትሯ ፊልሰን አብዱላሂ የስራ መልቀቂያ አስገቡ።

በዕድሜ ትንሿ የካቢኔ አባል ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልቀቂያ ማስገባታቸውን በተለያዩ የማህበረሰብ ገጾቻቸው አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ በሰው ሃይል እና በጀት እጦት እምብዛም ይሰራ ያልነበረውን መስሪያ ቤት የመምራቱን ሃላፊነት መረከቡ ለውድቀት እንደመመቻቸት ሆኖ ነው የተሰማኝ ሲሉ በገለጹበትና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጻፍኩ ባሉት ደብዳቤያቸው በችግሮች መካከልም ቢሆን የተቋሙን የ10 ዓመታት እቅድ ከማዘጋጀት ጀምሮ ባለፈው አንድ ዓመት ትልቅ ጥረትን ስናደርግ እንደነበር በኩራት ለመናገር እችላለሁ ብለዋል፡፡

በማንኛውም የስራ ጫና እና ውጥረት ውስጥ ሆነን መቼ እንስራ እና መቼ እንልቀቅ በሚል የሚያጋጥሙ ልዩነቶችን እንደሚቀበሉ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉም ነው ፊልሰን በደብዳቤያቸው ያሰፈሩት፡፡

ስነ ምግባሬን የተመለከተ ማንኛውም ሁኔታ ከእምነት እና እሴቶቼ የተቃረነ ነው ያሉም ሲሆን ይህን አሳልፎ መስጠት ለራሴ እና ለዜጎች ያለኝን እምነት መጣስ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ለህሊናዬ በሚከብዱ ባሏቸው ግላዊ ምክንያቶች ምክንያት የመልቀቂያ ደብዳቤውን መጻፋቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቋሙን እንዲመሩ ለሰጧቸው እድልም አመስግነዋል፡፡

ወ/ሮ ፊልሰን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አቅራቢነት መጋቢት 3/2012 ዓ.ም የሴቶች፣ህጻናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ሆነው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሾማቸው የሚታወስ ነው፡፡
Via al ain
@nidatube
👍2
ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም በአለም ዙርያ ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸውን ተራኪንግ ድረ ገጾች አስታውቀዋል።

ችግሩ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።
Via al ain

@nidatube @nidatubebot
1
የፓኪስታን የኒኩሌር አባት አብዱልቃድር ከሃን ህወታቸው አለፈ

አብዱልቀድር ከሃን ፓኪስታን የኒኩሌር የጦር መሳሪያን የታጠቀች የመጀመሪያዋ እስላማዊ ሀገር ማድረግ የቻሉ ናቸው

አብዱልቀድር ከሃን በህመም ምክንያት በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የፓኪስታን ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሆነው ቢቲቪ ዘግቧል።

ፓኪስታናዊው የኒኩሌር ተመራማሪ አብዱልቀድር ከሃን የሀገሪቱ ብሄራዊ ጀግና ተደርገው ነው በበርካቶች የሀገሪቱ ዜጎች ዘንድ የሚታዩት።

ምንያቱ ደግሞ አብዱልቀድር ከሃን ፓኪስታን የኒኩሌር የጦር መሳሪያን የታጠቀች የመጀመሪያዋ እስላማዊ ሀገር እንድትሆን ማድረግ በመቻላቸው ነው ተብሏል።

አብዱልቀድር ከሃን የፓኪስታን የመጀመሪያው የኒኩሌር ማብላያ ጣቢያ በኢስላማባድ አቅራቢያ እንዲተከል ማድረግ የቻሉ ሲሆን፤ እንደ አውሮፓውያኑ በ1998 ሀገሪቱ የመጀመሪያውን የኒኩሌር የጦር መሳሪያ ሙከራ እንድታደርግም አስችለዋል።

Via alain
የጁምአ ቀን
~~~~

ነብዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ)እንዲህ ብለዋል ፡ አርብ(ጁመዓ) ቀን፡ ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ፡ቅባትና ሽቶ ከተቀባ በሗላ ጁመአ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ ፡በመሔድ ሌሎች ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሺ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ ፡ከዚያም የቻለውን ያህል (ነፍል) ከሰገደ በሗላ በፀጥታ ኹጥባን(የኢማሙን ንግግር )ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመዓ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሐጢያቱን አላህ ይተውለታል፡፡ ነብዩ{ሰ,ዐ,ወ} ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ኑጉስ ነው እነዚህ አምስት ነገሮች በጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል። እነሱም
1, አላህ አደምን የፈጠረው በጁመአ ቀን ነው፣
2, አደም ከጀነት የወጡት በጁምአ ቀን ነው፣
3, አደም የሞተውም በጁመአ ቀን ነው፣ 4, ቂያማ የምትቆመውም በጁመአ ቀን ነው፣
5, በጁምአ ቀን የሆነች ሠአት አለች።አንድ የአላህ ባሪያ የጠየቀውን ነገር ይሠጠዋል፣ያቺን ሠአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልሆነ ድረስ አላህ ይቀበለዋል። በሌላ የሀድስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሠማ ጁማአውን ከሰገደ አላህ ካለፈው ጁምአ እሥከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል። በሌላ የሀድስ ዘገባ የጁምአ እለት በመጀመሪያ ሠአት ወደ መስጅድ የገባ ግመል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታላ። ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘግቡት መላኢኮች የኢማሙን ኹጥባ ለመስማት መስጂድ ይገባሉ። የአላህ መላእክተኛ(ሰ,ዐ,ወ) እንድህ ብለዋል፦

የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላወትን ማውረድ አብዙ፣ማንኛውም ሠው የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላዋት አያወርድም ሠላዋቱ ቢቀርብልኝ እንጅ።

{አልባኒ ሶሂህ ብለውታል} ‌"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ።" ‌ "ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ። ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡" ((62:9_10)

የጁመአ ቀን ሱናወች ~~~~~~~~~
~ገላን መታጠብ
~ ጥሩ ልብስ መልበስ
~ሽቶ መቀባት ለወንዶች
~ ሲዋክ
~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ
~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰ፣ዐ፣ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ።

‌ اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد ال

لَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ

https://www.tg-me.com/joinchat-QoR5qFfHQ7j_IRrI
አሜሪካ፤ ህወሓት ወደ ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች መቃረቡን እንዲገታ ጥሪ አቀረበች

ተኩስ ለማቆም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድርድር ይጀመርም ነው ዋሽንግተን ያለችው

የጦርነቱ መዛመት እጅግ አሳስቦኛል ያለችው አሜሪካ ህወሓት፤ ከአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲወጣ በድጋሚ ጥሪ አቀረበች።

ህወሓት ወደ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መቃረቡን እንዲገታም ጥሪ ያቀረበችው አሜሪካ ከባድ መሳሪያዎችን ወደ ከተሞች እንዳይተኩስ አሳስባለች።
መንግስት በመቀሌና በሌሎች የትግራይ አካባቢዎች የፈፀማቸውን የአየር ድብደባዎች በጽኑ መቃወሜ ይታወስልኝ ያለችው ዋሽንግተን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ድርድር መጀመር አለባቸው ብላለች።
Vi al ain

@nidatube
👍1
የህወሓት ታጣቂዎች በንፋስ መውጫ ከተማ በ9 ቀናት ውስጥ 71 ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል - አምነስቲ

ወንጀሎቹ የተፈጸሙት በህጻናት ፊት መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል

ሴቶቹ የተደረፈሩት የህወሓት ታጣቂዎች በከተማዋ በቆዩባቸው ዘጠኝ ቀናት ውስጥ ነው

የህወሓት ታጣቂዎች በንፋስ መውጫ ከተማ 71 ሴቶችን አስገድደው መድፈራቸው ተገለጸ፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቋም አምኒስቲ ኢንተርናሽናል የህወሓት ታጣቂዎች በወረራ በያዟቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ያደረሱትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አስመልክቶ ያጠናቀረውን ሪፖርት አውጥቷል፡፡

ተቋሙ በሪፖርቱ እንደገለጸው የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ንፋስ መውጫ ከተማ ከነሀሴ 6 ቀን እስከ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በከተማዋ በቆዩባቸው ዘጠኝ ቀናት ውስጥ የተለያ ጥቃቶችን ፈጽሟል፡፡

ታጣቂዎቹ ከፈጸሟቸው ወንጀሎች መካከል በቡድን ሴቶችን መድፈር፣ ንብረት ማውደም፣ መዝረፍ እና አጸያፊ ስድቦችን በንጹሃን ላይ መፈጸማቸውን ድርጅቱ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

ስለተፈጸመባቸው የቡድን አስገድዶ መደፈር አስመልክቶ በአምኒስቲ ኢንተርናሽናል ቃለመጠይቅ ከተደረገላቸው ሴቶች መካከል አንዷ ገበያነሽ የተባለች የከተማው ነዋሪ ናት፡፡

ምግብ በመሸጥ እንደምትተዳደር የገለጸችው የ30 ዓመቷ ገበያነሽ "የሆነብኝን መናገር ቀላል አይደለም። ለሶስት ሆነው ደፈሩኝ። የደፈሩኝ ልጆቼ እያለቀሱ ነው። ትልቁ ልጄ 10 ታናሹ ደሞ 9 ዓመቱ ነው። ሁለቱም ወታደሮቹ ሲደፍሩኝ እያዩ ያለቅሱ ነበር። ከደፈሩኝ በኃላ እየሰደቡኝ ሽሮና በርበሬ ወሰዱ። በጥፊ መቱኝ። በፊቴ መሳሪያቸውን እያቀባበሉ እንደሚገድሉኝ አስፈራሩኝ" ስትል ተናግራለች፡፡

ሌላኛዋ በህወሓት ታጣቂዎች በቡድን የተደፈረችው የ28 ዓመቷ ሀመልማል ስትሆን እንጀራ በመሸጥ ሕይወቷን የምትመራ የከተማው ነዋሪ ናት።

"የ10 ዓመትና የ2 ዓመት ልጆች አሉኝ። ወታደሮቹ ልጆቼን እንዳይገድሉብኝ ፈርቼ ነበር። ልጆቼን አትግደሉብኝ እኔን እንደፈለጋችሁ አድርጉ አልኳቸው። ትንሿ ተኝታ ነበር። ትልቋ ግን እያየች ደፈሩኝ። ምን እንዳየች ለመናገር አቅሙ የለኝም" ስትል በህወሃት ታጣቂዎቹ የደረሰባትን ተናግራለች፡፡

ታጣቂዎቹ የህክምና ተቋማትን ማውደማቸውን የገለጸው ይህ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋም በተለይም ተገደው የተደፈሩ ሴቶች ህክምና እንዳያገኙ መደረጉንም አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ቃለመጠይቅ ካደረጋቸው 16 ሴቶች መካከል 14ቱ በህወሓት ታጣቂዎች በቡድን መደፈራቸውን ተናግረዋል፡፡

አምነስቲ አክሎም በንፋስ መውጫ ከተማ በአጠቃላይ 70 ሴቶች በታጣቂዎቹ መደፈራቸውን ከከተማው ሴቶች እና ህጻናት ጽህፈት ቤት መስማቱንም በሪፖርቱ አካቷል፡፡

የተቋሙ ዋና ጸሃፊ አግኔስ ካላማርድ በማጠቃለያ ሪፖርቱ ላይ በሰጡት አስተያየት “የህወሓት ታጣቂዎች በንፋስ መውጫ ከተማ የጦር ወንጀል መፈጸሙን ከተጎጂዎች ያገኘነው መረጃ ያስረዳል” ብለዋል፡፡

የቡድኑ ታጣቂዎች አሁንም በአማራ እና አፋር ክልሎች ጥቃቱን ቀጥለዋል ያሉት ዋና ጸሃፊው እየፈጸሟቸው ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡

Via al ain

@nidatube
የጋዳፊ ልጅ በሊቢያ ለፕሬዚዳንትነት ሊወዳደር ነው ተባለ
ጋዳፊ በኔቶ መራሹ ጦር በ2011 ከስልጣን መወገዳቸውና መገደላቸው ይታወሳል

የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙዓማር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል እስላም ጋዳፊ በቀጣይ ወር በሀገሪቱ በሚካሄደው ምርጫ እንደሚሳተፍ ተገለጸ፡፡

የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽኑ ባለስልጣን እንደገለጹት ታህሳስ 24 ቀን በሊቢያ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ በመሆን ከተመዘገቡት መካከል የቀድሞ የሊቢያ መሪ ሙአማር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል እስላም ጋዳፊ አንዱ ነው፡፡
ሰይፍ አል እስላም ጋዳፊ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ሆኖ መመዝገቡ አሁን ላይ መረጋገጡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የ 49 ዓመቱ የጋዳፊ ልጅ ዛሬ በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በምትገኘው ሴብሃ ከተማ ለፕሬዝዳንትንት ለመወዳደር ዕጩ ሆኖ ሲፈርም ታይቷል ነው የተባለው፡፡
የሊቢያው የቀድሞ መሪ ሙአመር አል ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል እስላም ጋዳፊ እ.ኤ.አ በ 2011 አባቱ በኔቶ መራሹ ተልዕኮ ከመገደላቸው በፊት ሁነኛ የሀገሪቱ ሰው እንደነበር ይገለጻል፡፡

አል ዐይን

@nidatube
የጦርነቱ መዘዝና ቀጣይ እጣ ፈንታችን

ጦርነቱን የፈለጉት፣ በውጤቱም አትራፊ የሚሆኑ አካላት መኖራቸው የማያጠራጥር ሀቅ ነው። በሌላ በኩል የጦርነቱ ውጤት ምንም ይሁን ምን የሚከስሩ ህዝቦች አሉ። ከነዚህ ቀዳሚው የወሎ ህዝብ ነው። የጦርነቱ አብዘሀኛው የወጪ ደረሰኝ የተቆረጠው ምንም ትርፍ በማያገኘው የወሎ ህዝብ ሰም ነው። በዚህም የህይወት፣ የንብረትና የሰነ ልቦና ኪሳራ ከፍሏል፣ እየከፈለ ይገኛል።

ጦርነቱ በወሎ ህዝብ ላይ ያደረሰውን ኪሳራ ለመረዳት አራት የሚሆኑ ጥናቶችን መመለከት አጋዥ ይሆናል: —

1) የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ጦርነቱ በመሰረተ ልማት ላይ ያደረሰውን ጉዳት በጥናት አቅርቧል። በጥቅሉ ከ300 ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያለው መሰረተ ልማት ወድሟል። ት/ቤቶች፣ ጤና ተቋማት፣ መንገዶች፣ የህዝብ መገልገያዎች ወድመዋል። ይህ ወጪ የህዝቡን የንብረት ኪሳራ ሳይጨምር ነው። የወሎ ህዝብ ወታደሩን ሲቀልብ፣ ነጋዴ ለህልውና ዘመቻ አዋጣ እየተባለ ከየትኛውም አካባቢ በላይ አዋጥቷል። እነዚህ ወጪዎች ሲደመሩ ኪሳራው የከፋ ነው።

2) ሌላኛው ጥናት በሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን የተዘጋጀው ሲሆን ከንፁሀን ሞት፣ መደፈርና መፈናቀል ጋር የተያያዘ ነው። ባለው ምቹ ያልሆነ ተጨባጭ ውስጥ በተደረገው ጥናት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ህይወታቸውን ተነጥቀዋል፣ በሚሊየኖች ተፈናቅለዋል፣ በመቶ ሺዎች ረሀብ አፋፍ ላይ ናቸው። ገና ካሁኑ በመድሀኒት እጦት ሰለሚሞቱ ወገኖቻችን እየሰማን ነው። የሰነ ልቦና ጉዳቱ በጥናቶች መዳሰስ የሚችልና የሚለካ አይደለም። ምናልባትም ትውልድ ተሻጋሪ ሊሆን ይችላል። የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመላው ሀገሪቱ ሲከናወን የወሎ ተማሪዎች ጢሻ ለጢሻ እየተንከራተቱ ነበር። የሌሎች አካባቢ ተማሪዎች ወደ ት/ቤት የወሎ ተማሪዎች ወደ ሰደተኛ ካምፖች ተመዋል። የዚህ ሂደት ውጤት ዘመን ተሻጋሪ ነው። ሁኔታዎች በዚሁ ከቀጠሉ ደግሞ ሞት፣ መፈናቀሉና የሰነ ልቦና ጉዳቱ ይከፋል።

3) የፎርቹን ጋዜጣ ለንባብ ያበቃው ሪፖርት በአካባቢው የደረሰውን የእህልና ሰብል ውድመት ይገልፃል። በሪፖርቱ መሰረት 8 ሚሊየን ኩንታል ገደማ እህል በጦርነቱ ምክኒያት በወሎ ብቻ ተከስሯል። ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ የሰብል ኪሳራው ከዚህ ሊከፋ እንደሚችል ሪፖርቱ ይጠቅሳል። በአካባቢው ከባድ ርሀብ ሊከሰት እየተቃረበ ለመሆኑ ከዚህ በላይ አመላካች የለም።

4) የክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ያወጣው አጠቃላይ ክልላዊ ሪፖርት የሰብዐዊና ቁሳዊ ውድመቱ እጅግ የከፋ መሆኑን የሚያመላክት ነው። The reporter በእንግሊዝኛ ዘገባው የክልሉን ፕላን ኮሚሽን ዘገባ ጠቅሶ ባወጣው ሀተታ "ክልሉን ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት ለመመለስ ከሰላሳ እሰከ አርባ" አመት ይፈጃል ሲል አሰነብቧል። በዚሁ ዘገባ ላይ የግብርና ምርት ኪሳራው ብቻ ከ260 ቢሊየን ብር በላይ እንደሆነ የክልሉ ፕላን ኮሚሽን ገልፀዋል።

ለህዝባችን የተሻለው ቢሆናል የቱ ነው?

ጦርነቱን በተመለከት አራት ቢሆናሎች (scenarios) ፊት ለፊታችን ተደቅኗል።

→ አንደኛው ቢሆናል መንግሰት መልሶ ማጥቃት በማድረግ ጦርነቱን ያሸንፋል የሚል ነው። ይህ የቢሆናል ግምት እውን ቢሆን እንኳ በወሎ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው ሰብዐዊና ቁሳዊ ቀውስ የትየለሌ ነው። ጦርነቱ ወደ ሙሉ ወሎ በመሰፋፋቱ ህዝቡ hostage የሆነበት ተጨባጭ ተፈጥሯል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የሚደረግ መልሶ ማጥቃት የሚኖረው Collateral damage ለማሰብ የሚከብድ ነው። በተጨማሪ በአጭር ጊዜ የመሳካት እድሉ አነሰተኛ መሆኑ ከጦርነት የተረፈውን ህዝብ ርሀብ የሚጨርስበት እድል ይፈጥራል።

→ ሁለተኛው የቢሆናል ግምት የህወሀት ሀይሎችና ሌሎች አጋሮቻቸው ጦርነቱ ያሸንፋሉ የሚል ነው። ይህ ቢሆናልም በአጭር ጊዜ የሚሆን ባለመሆኑ ከላይ የተጠቀሰው የህዝቡ መራብን ቀጣይና የተባበሰ ያደርገዋል።

→ ሶስተኛው የቢሆናል መላምት ጦርነቱ የተራዘመና አሸናፊ የሌለው ይሆናል የሚል ነው። ይህ ቢሆናል ዋነኛ የጦርነት ቀጠና ለሆነው ወሎ ተጨማሪ ሞት፣ መፈናቀልና የንብረት መወደም የሚያሰከትል ብሎም እየተባባሰ የመጣውን የረሀብ አደጋን የሚያፋጥን ነው።

→ አራተኛው የቢሆናል መላምት ጦርነቱ ቁሞ ድርድር ይደረጋል የሚል ነው። ይህ የመሆን እድሉ እጅግ አነሰተኛው መላምት ነው። ሁለቱም አካል ለድርድር የሚያሰቀምጧቸው መሰፈርትና አጀንዳ የተራራቀ ነው። ቢሆንም ግን በአንድም ይሁን በሌላ ምክኒያት ወደ ድርድር ከመጡ ቢያንሰ በጊዜያዊነት የረሀብ አደጋ የተደቀነባቸውን ወገኖች መታደገ የሚያስችል አማራጭ ነው። ድርድሩ ይሳካም አይሳካም ጅምሩ ብቻ የሰብዐዊ እርዳታ የሚደርሰበትን ኮሪደር (Humanitarian Coridor) ሰለሚያሰገኝ በምግብና መድሀኒት እጦት ወደ ሞት እየቀረቡ ያሉ ዜጎችን ህይወት ይታደጋል።

ከነዚህ አራት ቢሆናሎች የመጀመሪያዎቹ ሶስቱ ለወርና ሁለት ወር እንኳ ከቀጠሉ ከጥይት የተረፉ ብዙ ወዳጆቻችንን በምግብና መድሀኒት እጦት ያሳጡናል። በርግጥ ለወሎ ህዝብ በዚ ሰዐት ማን መጣ ማን ሄደ ከሚለው በላይ ህልውናውን የሚያቆይበት ዳቦ ማግኘት ያሳሰበዋል። ይህ በአሰቸኳይ ሊሳካ የሚችለው አንድም የሰብዐዊ እርዳታ ኮሪደር ሲመቻች {መንግሰት ወደ ኮምቦልቻ የሰብዐዊ እርዳታ በረራዎችን እፈቅዳለው ቢልም ያሰቀመጠው ግልፅ ጊዜ የለም} አልያም ጦርነቱ በድርድር የሚያልቅበት መንገድ ሲኖር ብቻ ነው።

በርግጥ ይህ ሀሳብ ለብዙዎች ሊጎረብጥ ይችላል። ይህን እረዳዋለሁ። ከስሜታዊነት ወጥተን፣ ከራሳችን ቁጭትና የበቀል ስሜት ይልቅ የህዝባችንን ህልውና ስናሰቀድም ግን ለወሎ ህዝብ ካሉት መጥፎ አማራጮች አነሰተኛው መጥፎ የጦርነቱ በድርድር መጠናቀቅ ነው። ለወራት ጦርነት ጎስመን ለህዝባችን መከራ፣ መንከራተትና ውርደትን እንጂ የፈጠርንለት አንዳች ነገር የለም።

Ye Emmu Lij - የእሙ ልጅ
@nidatube @nidatubebot
👍1
ምዝገባ ተጀመረ!
~~~~~~~~~~
ወዶ ዘማች የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተምሳሌታዊ ወጣትን የማፍራት ተልእኮውን ለማሳካት ለአንድ አመት የተለያዩ ወጣት ተኮር ዝግጅቶችን ለማህበረሰባችን አድርሷል፡፡ በአዲሱም ምእራፍ የፕሮግራሙን ማእቀፍ በማስፋት በርካታ ዘርፎች ላይ የሚሰራ የወጣት ፕሮጀክት እንዲሆን ታሳቢ በማድረግ ቋሚ አባላት የሚፈሩበት አንደኛ ዙር ምዝገባ ጀምሯል፡፡ በመሆኑም የእንቅስቃሴው አካል መሆን የሚፈልጉና የፕሮጀክቱን እሴቶች የሚጠብቁ ሁሉ ከታች ባለው ሊንክ መመዝገብ የሚችሉበት ልዩ እድል ተመቻችቷል፡፡ ምዝገባውን በአግባቡ ያካሄዱና (ኢንተርቪውን ጨምሮ) የተለያዩ የማጣሪያ እርከኖችን ያለፉ ውስን ወጣቶች የፕሮጀክቱ ሙሉ አባል ይሆናሉ፡፡

ከታች ያሉትን ሊንኮችን በመጫን መመዝገብ ይቻላል!

ሙሉ ስም
እድሜ
የትምህርት ደረጃ
አባል ለመሆን የፈለጉበት ምክንያት
ልዩ ተሰጥኦ
የአባልነት ግዴታ ለመወጣት ያለዎት ዝግጁነት
አድራሻ (ስልክ ቁጥርና የመኖሪያ አድራሻ)

በቴሌግራም www.tg-me.com/Temsaletawi_Wetat ላይ በውስጥ መስመር መረጃዎችን መላክ፤ አልያም በጉግል ፎርም መሙላት ይቻላል፡፡

https://forms.gle/q2xAXxKWSasjnpiE7
ቻይና በ2030 አሜሪካን በመብለጥ የዓለም ቁጥር አንድ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት እንደምትሆን ተተነበየ።
በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት የዓለም ቁጥር አንድ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ቻይና እንደምትሆን የምጣኔ ሀብት አማካሪ ድርጅቶች አስታወቁ።

አሁን ላይ የዓለም ሁለተኛዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ቻይና በአውሮፓውያኑ 2030 ቁጥር አንድ በመሆን አሜሪካን ልትበልጥ እንደምትችልም ነው የተተነበየው።

የቻይና ኢኮኖሚ በመንግስት ኢንቨስትመንት ላይ ፣በትላልቅ የቴክኖሎጂ ላማትና በሀገር ውስጥ ፍጆታ ላይ ትኩረት በማድረግ የአሜሪካን ቦታ እንደሚረከብም ነው በስፋት እየተገመተ ያለው።

ከብሪታኒያው የኢኮኖሚና ቢዝነስ ምርምር ማዕከል ትንቢያ በተጨማሪም የብድር ኢንሹራንስ ኩባንያ የሆነው ኢዩለር ሄርሜስም ተመሳሳይ ትንቢያ ሰርቷል ተብሏል።

የቤጅንግ እና የዋሸንግተን የንግድ እሰጥ አገባ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ ተገልጿል።

በአውሮፓውያኑ 2020 የቻይና ጠቅላላ ኢኮኖሚ 15 ነጥብ 92 ትሪሊየን ዶላር እንደሆነ አይ ኤችኤስ የተባለ ኩባንያ ጠቅሷል። በቀጣዩ ዓመት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ18 ቢሊዮን እንደደረሰም ነው የተነገረው።የአሜሪካ ጠቅላላ ኢኮኖሚ ደግሞ 23 ትሪሊዮን ዶላር መሆኑም ተገልጿል።

የቤጅንግ እና የዋሸንግተን ፉክክር ኢኮኖሚያዊ ቢመስልም አሁን አሁን ግን ወታደራዊ መልክ እየያዘ መምጣቱም እየተነገረ ነው። ሀገራቱ አሁን ላይ በምጣኔ ሀብት ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው በስፋት እየተወራ ሲሆን መሪዎቹ በጉዳዩ ላይ መወያየታቸው ይታወሳል።

አል ዐይን
👍21
ራፍያ አርሻድ
ሙስሊም ሴቶች በቤተሰብ ተፅዕኖ እንጂ በፍላጎታቸው አይደለም ሂጃብ የሚያደርጉት የሚለው የአንዳንድ ማህበረሰብ ህሳቤ የተሳሳተ ነው

እኔ እስኮላር ሺፕ ተመዝግቤ ቃለ መጠይቅ በማደርግበት ቀን ቤተሰቦቼ እንዲህ ነበር ያሉኝ

" በእንግሊዝ የተማሪዎች ምልማላ ቦርድ ለመመረጥ ሂጃብሽ ተፅዕኖ ይፈጥርብሻል በመሆኑም ሂጃብሽን አስቀምጠሽ ምዕራባውያን ሴት መስለሽ ለኢንተርቪው ቅረቢ በአስገዳጅ ሁኔታ ሂጃብሽን በማውለቅሽ ፈጣሪ አያዝንብሽም ነበር ያሉኝ

በሂጃቤ ምክንያት ዕድሉን የማጣው ከሆነ አላዝንም
አለማዊ ምቾቴን ለማስተካከል አኼራዬን አላበላሽም በማለት ሂጃቤን እንዳጠለቅኩ ነበር ወደ ቃለ ምልልስ የሄድኩት

ኢንተርቪውን አለፍኩ ይኸው ከ17 አመታት በኃላ በእንግሊዝ ብቸኛዋ ሂጃብ ለባሽ ሙስሊም የፌደራል ዳኛ በመሆን ተመረጥኩ " ነበር ያለችው

Via bilal zeyad

@nidatube
👍4
2025/07/13 21:07:20
Back to Top
HTML Embed Code: