Telegram Web Link
እሁድን በሼይኽ ሆጀሌ ሰፈር መስጂድ ያሳልፉ

ተወዳጁ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ" ይህ ነው እስልምናህ" በሚል ጣፋፅ ዳዕዋ ያቀርባል

ሌሎች ፕሮግራሞችን ይኖራሉ

ከእርሰዎ ብቻ ከነቤተሰብዎ 3:30 ላይ ሼህ ሆጀሌ መስጂድ ይገኙ ።

@nidatube @nidatubebot
ተማሪ ሰአዳ ጀማል የ 12 ክፍል መልቀቂያ ማትሪክ ከ700 ፣ 650 በማምጣት ከመላው ሀገሪቱ ከሴቶች አንደኛ በመሆን አጠናቃለች ።
ማሻአላህ
@nidatube @nidatubebot
አደባባይ "ኬኛ" ለሚሉ

... ሰሞኑን "ራስ ብሩ ከሜዳቸው ቀንሰው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቶስን መስቀል ማክበሪያ አደባባይነት በርስትነት ሰጥተዋታል" የሚል መከራከሪያ ይዘው መጥተዋል። ይህ መከራከሪያ ተቀባይነት የማይኖረው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው:—

1⃣ በፊውዳሊዝምና ኢምፔሪያሊዝም ህግ ልንገዛ አንችልም!

2⃣ ራስ ብሩ ያንን መሬት ገዝተው ወይም አልምተው ያገኙት አይደለም፣ በፊውዳሊዝም የመሬት ወረራ ከኦሮሞ ገበሬ የነጠቁት እንጅ፣ በመሆኑም ከድሃ የተዘረፈ መሬት እንደ ህጋዊ ንብረት አይቆጠርም

3⃣ራስ ብሩ የቦታው ባለቤትነት ማረጋገጫ ህጋዊ ሰነድ የላቸውም ለቤተ—ክርስቲያኒቱም ያስተላለፉበት ህጋዊ ሰነድ የለም

4⃣ ቤተ–ክርስቲያኒቱ የባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ የላትም መስቀል ይከበርበት ነበር ማለት የይዞታ ማረጋገጫ ማስረጃ አይሆንም!

5⃣ የቦታው ስያሜ በደርግ ጊዜ ከመስቀል አደባባይ ወደ አቢዮት አደባባይ ዞሯል። በኢህአዴግ ወደ መስቀል አደባባይነት በይፋ ስለመቀየሩም ማረጋገጫ የለም

6⃣ ቤተ–ክርስቲያኒቱ በስዩመ–እግዜሩ መንግስት ከሌሎቹ ኃይማኖቶች በላይ ተጠቃሚ እንድትሆንና የፊውዳሊስት ዝርፊያው ተጠቃሚ መሆኗ ይታወቃል። ባላት ሲሶ መንግሥትነትም ከግብር ነፃ የሆኑ በርካታ መሬቶችን እንድትሰበስብ እድሉን ፈጥሮላታል። ለዓይኗ ያማራትን መሬት ያለ ህጋዊ ማስረጃ እንድትይዝም ይሁንታው ስለነበራት የመሬት ወረራ ፈፅማለች። በዚህም ሳቢያ ያለ ህጋዊ አሰራር እንደ አቢዮት/መስቀል አደባባይን እንዲሁም ለህዝብ የሥፖርትና መንግሥታዊ ስርዓቶች የተመሰረተውን ጃን ሜዳን ይዛለች። በተቃራኒው የሀገሪቱ እኩሌታ ህዝበ ሙስሊም በአገሪቱ ዋና መዲና ላይ ይህ ነው የሚባል የበዓላትና ፀሎት ማክበሪያ ቦታ የለውም። ይህ አሰራር በ1966ቱ አቢዮት አራግፈነው የመጣነው በመሆኑ ይህ ህገ—ወጥ ተስፋፊነት በሴኪዩላሩ ህገ–መንግስትና መንግሥት ሊዳኝ ይገበዋል።

7⃣ የዶ/ር ዐብይ መንግሥት በአዲስ አበባ መስተዳድር ከህዝቡ በተገኘ ግብር፣ በሙስሊሙ ግብር ጭምር 2.5 ቢሊዮን ብር በጅቶ የመስቀል አደባባይ ፓርኪንግ ሜጋ ፕሮጀክትን እያሰራ ይገኛል። የዚህ ፕሮጀክት መርህ "አደባባዩ የሁሉም የአዲስ አበባ ህዝቦች ንብረት ነው!" የሚል ስለሆነም ነው መንግስት የህዝብን ሀብት ተጠቅሞ እየሰራ ያለው። የቤተ ክርስቲያኒቱ ይዞታ ከሆነማ መንግሥት ምን አግብቶት ለቤተ–ክርስቲያንን ይሰራል? ምንስ ጥልቅ አድርጎት የህዝብን ከፍተኛ ሀብት ለቤተ–ክርስቲያኒቱ ማጠናከሪያ ያውላል?

8⃣ በአደባባዩ ለባለፉት ዘመናት በተደረጉ የግል/ የቡድን የዘፈን ኮንሰርቶች፣ የብሄር ብሄረሰብ በዓላትና ክብረ በዓላት፣ የሃይማኖቶች የፀሎት ፕሮግራምና ስግደቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳዎች፣ የገዥቅ ፓርቲ ድስኩሮች፣ የብሄራዊ አጀንዳችን ልዩ ዝግጅቶች፣ የታዋቂ ሰዎች የቀብር ሽኝት ፕሮግራሞች ሲደረጉ ቤተ–ክርስቲያኒቱን ፈቃድ መጠየቅ ስለላስፈለገና ስለማያገባት የትኛውም አካል ጠይቆም አስፈቅዶም አያውቅም! ይህም ቤተ–ክርስቲያኗ ታሪካዊም ሆነ ሰነዳዊ ማስረጃ ስላልነበራት ነው።

8⃣ከታች የተያያዘው ፕላንም አንደኛ ማረጋገጫ ካርታ አይደለም፣ ሁለተኛ "ጉዳዩ ከቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ወደ መስቀል አደባባይ የሚያገናኝ የመንገድ ጥናት" እንጅ የአደባባዩ ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ አይደለም

9⃣ የጋሽ ብርሃኑ ከማል ማስረጃ

እውነት መስቀል አደባባይ የማን ነው?

ስለጥንቱ መስቀል አደባባይ የማውቀው ባይኖርም ከ1978 ጀምሮ አብዮት አደባባይ ይባል የነበረና ከ1983 ደግሞ ወደ መስቀል አደባባይነት የተመለሰው አደባባይ የኢትዮጵያ ጊዚያዊ ወታደራዊ መንግሥት ከራሺያ፣ ከኩባና ከሌሎችም ሶሻሊት አገሮች ልምድ በመቅሰም የተወሰነ ቦታ ከቅዱስ ዮሴፍ በመውሰድ፣ የተወሰነ ከ?ኢጣሊያ ወይም ከግሪክ ክለብ በመውሰድ፣ የተወሰነ መሬት ከራስ ወልደገብርሬል መሬት በመውሰድ የተወሰነ ደግሞ ወደራጉኤልና ቦሌ በሚወስደው መንገድ መካከል ያለውን በመውሰድ የተሠራ ነው። አፈሩም (ሙሌቱም) ወሎ ሰፈር ድልድይ ከመደረሱ በፊት በስተቀኝ ትገኝ ከነበረች፣ የልዕልት ተናኘ ወርቅ ኃይለ ሥላሴ ይዞታ የነበረች አንዲት ኮረብታ የተወሰደ ነው። በወቅቱም የኛ አብዮት አደባባይ ኩባ ከነበረውና ብራዚል ከነበረው አንጻር ሲተያይ አነስተኛ እንደነበረ በቴሌቪዥን ሳይቀር ይነገር ነበር።

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከ1930ዎቹ የዒድ ሶላት ይሰገድበት ነበር። መስቀል አደባባይ የተባለው እራሱ በ1960ዎቹ በተለይ የአፍሪካ እንድነት ድርጅት ሲመሠረት ይመስለኛል። አደባባዩ መስቀልም፣ ጥምቀትም፣ መስቀልም፣ ዒድም፣ ሙዚቃም፣ የፖለታካ ስብሰባ ይካሄድበት ነበር

ይሁንና አንዳንድ ሰዎች የራስ ወልደጊዮጊስ ርስት እንደነበርና እርሳቸውም ለመስቀል አደባባይነት እንደሰጡ ይናገራሉ። ይህ በእውነቱ ትንሽ አሻሮ ይዞ ከባለእንቅብ ቆሎ ለመቀላቀል የመፈለግ ያህል ነው። ያም ሆኖ የራስ ወልደገብርኤል መሬትም እንኳን በሆን የከተማ ቦታዎችንና ትርፍ ቤቶችን ለህዝብ በደረገው አዋጅ የመንግሥት ሆኗል።ይህም አዋጅ ዛሬም አልተሻረምና መረትም ትርፍ ቦታም አልተመለሰም። ይቀጥላል።

…………………………

በመሆኑም የመስቀል አደባባይ ስያሜው የተፈለገው ይዞታን ለማረጋገጥ ከሆነ ስያሜው ጭምር ህገወጥና የፊውዶ–ኢምፔርያሊስቶች ውርስ ነውና ከነስሙ ይፋቃል

ስያሜውን በታሪካዊ ፋይዳው ተቀበሉልን! ከሆነ በቅንነት ልንቀበለው ብንችልም የአደባባዩ ታሪካዊ ሚና መስቀል ማክበሪያ ብቻ ሳይሆን ኢሬቻም፣ ኢድም፣ ዘፈንም፣ ለቅሶም፣ ፖለቲካም የናኘበት ቦታ ነው።
……………………

@nidatube @nidatubebot
👍1
የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዝግጅቱ ነገ ግንቦት 03/2013 በዚያው አደባባይ ከቀኑ በ10 ጀምሮ በመንግስት ሙሉ ወጪ በጸጥታ ኃይሉ ጥበቃና አጀብ ይደረጋል።አንድ ሆነን በጋራ ከቆምን ሌሎች ጥያቄዎቻችንንም እንዲሁ እናስመልሳለን።

Sagantaan Ifxaara kaleesaa dhorkamee bakkuma sila karoorfameetti bor caamsaa 03/2013 baasii guutu mootumaadhaan Qaama nageenyyatiin kabajaan eegamaa sa'a 10 irraa kaasee ni godhama. Tokko taanee yoo waliin dhaabbannee gaaffilee keenya kaanis akkasuma ni debisiifna.

@nidatube @nidatubebot
“ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ” አዘጋጆች የተላለፈ መልእክት

የሰላም የአንድነት የፍቅር እና የመተሳሰብ ኢፍጣር!

ነገ ግንቦት 03/2013 ከሜክሲኮ እስከ ባምቢስ ባለው መስመር በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል::

ስለሆነም በምናካሂደው “ኢፍጣሮን ያጋሩ” ልዩ የአብሮነት የኢፍጣር እና የዱዓ ዝግጅት የታሰቡትን አላማዎች በታሰበው ልክ ለማሳካት:-

1.ማንኛውም ፕሮግራሙን ለመታደም የሚመጣ ግለሰብ ለፀጥታ አካላት ለፍተሻ ከመተባበር ባለፈ ለሰላሙ ዘብ እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኮቪድ ጥንቃቄ እንዳይለየን ሳኒታይዘር ማስክ እንዲሁ የያራሳችንን መስጋጃ በመያዝ እንተባበር።

2. ከህጋዊ ሰንደቅ አላማ ውጭ ይዞ መምጣት የማይፈቀድ ሲሆን ተንኳሽና ሌሎች ወገኖቻችንን ሊያስከፋ የሚችል ምንም አይነት ጥቅስ መያዝ ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
@nidatube @nidatubebot
🕋🕋🕋 ኢድ ሙባረክ!!! 🕋🕋🕋

እንኳን ለ1442ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

ተቀበለላሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊኸል አዕማል!

★★★★★★★★★★★★★

🕋🕋🕋 Iid Mubaarak! 🕋🕋🕋

Baga Ayyaana Iid al-fixrii bara 1442 tiin nuun gahe!

Taqabbalallaahu Minnaa Waminkum Saalihal A'amaal

🕋🕋🕋 Eid Mubarek 🕋🕋🕋
👍1
የዒድ ሥነ-ሥርዓቶች

1- ገላን መታጠብ፣
2- አዲስ የሆነ ልብስ (ንፁህ ባይሆን እንኳን) መልበስ፣
3- ሽቶ መቀባት፣
4- ዘካት አልፊጥርን ከሶላት በፊት መስጠት፣
5- የተወሰኑ ተምሮችን በልቶ መውጣት፣
6- ለዒድ ሶላት ማልዶ መውጣት፣
7- ልጆችን ጨምሮ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ወደ ዒድ አደባባይ እንዲወጡ ማድረግ፣
8- ሰብሰብ ብሎ በብዛት መስገድ፣
9- ወደ ዒድ መስገጃ ቦታ በእግር መሄድ፣
10- ከፍ ባለ ድምፅ ተክቢራ እያደረጉ መሄድ፣
11- አላህን አብዝቶ ማመስገን፣
12- በዒድ ሶላት ቦታ ላይ ከዒድ ሶላት በፊት ሱንና ሶላት አለመስገድ፣
13- በዒድ መስገጃ ቦታ ላይ አዛንም ሆነ ኢቃማ አለማድረግ፣
14- ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ፣
15- በዒድ ቀን መደሠት፣ መጫወትና መዝናናት፣
16- የእንኳን አደረሣችሁ መልዕክቶችን ማስተላለፍና መጨባበጥ፣
17- ወደ ዒድ ሜዳ በሄዱበት መንገድ አለመመለስ፣
18- ዚያራ ማድረግ፡፡ ወላጆችን፣ ዘመዶችን፣ ዑለሞችን፣ አቅመ ደካሞችን፣ ድሆችን፣ ወዳጆችን መዘየር፡፡
19- ድሆችን መርዳት፣ የዒድን ቀን በደስታ እንዲያሳልፉ ማገዝ፣
20- ሶደቃ ማብዛት፣
21- በዒድ ቀን ወንጀል አለመሥራት፣
©ነጃሺ ማተሚያ ቤት
@nidatube @nidatubebot
«መጅሊስ ዋጋ የከፈልኩበት ተቋሜ ነው»

ነገ ጠዋት ከ 3 ሰዓት ጀምሮ «መጅሊስ ዋጋ የከፈልኩበት ተቋሜ ነው» በሚል በርካታ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች ከጦርሃይሎች በላይ ሆላንድ ኢንባሲ ጋር በሚገኘው የፌደራል መጅሊስ ቅጥር ጊቢ በመገኘት የመጅሊስ አመራሮች የተሰጣቸውን ህዝባዊ አማና በተመለከተ ጥያቄ ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ታውቋል። ከሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ሀሳቦች መካከል:

1) «አማናችሁን በ6 ወራት እንድትወጡ ተሰጥቷችሁ ከ 2 ዓመታት በላይ ባለመወጣት ህዝበ ሙስሊሙን የበደላችሁበት ምክንያት በግልጽ ንገሩን»፣

2) «የመጅሊስ ምርጫ ቁርጥ ቀኑ ይነገረን»፣

3) «መጅሊስ የህዝበ ሙስሊሙ እንጂ የግለሰቦች አይደለም»

4) ፣«ሕዝበ ሙስሊሙን የበደሉት የመጅሊስ አባላት በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ»፣

5) «የጠቅላላ ጉባኤውን ዉሳኔ ያደናቀፉ አካላት በአስቸኳይ ለህግ ይቅረቡልን»

6) ፣«የፌደራል መጅሊስ የክልል መጅሊሶችን ተወካይ ሆኖ ሳላ ስለምን ከነርሱ ፍላጎት በተቃራኒ ቆመ?»

7) በ2004 ህዝበ ሙስሊሙ ለመብቱ ሲታገል የትግሉ መነሻ የሆነውን የአወሊያ ተቋምን መጅሊስ በማዳከም ለማፈራረስ የጀመረው ተግባር በአስቸኳይ ይቁም»

8) ፣ «እኛ ሙስሊሞች ነን።ሱፊ-ሰለፊ ጫወታ አይመለከተንም። መጫወት የፈለገም አካል ዋጋ በከፈልንበት ተቋማችን ሳይሆን በቤቱ ሄዶ ይጫወት»፣

9)«ህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየደረሰ ላለው ትንኮሳ የፌደራል መጅሊስ ሚናውን ካለመወጣት አልፎ ተባባሪ ነው እስክንል ድረስ እየበደለን በመሆኑ ከተጠያቂነት አያመልጥም»፣

10) «በሀጅና በፋይናንስ ክፍል ሆነው ህዝበ ሙስሊሙን ለዓመታት የዘረፉ የቀድሞ የመጅሊስ አባላትን በህግ ተጠያቂ ማድረግ ሲገባችሁ ከተባረሩበት መልሳችሁ እንዴት ሾማችሁ?»፣

11) «ከህወሃት መራሹ መንግስት ጋር ዉድ ዋጋ ከፍለን የታገልነው መጅሊስ የናንተ መጫወቻ እንዲሆን አይደለም»፣

12) «ዑለማ ሆናችሁ በቃል በመገኘትና አማናን በመጠበቅ ለህዝቡ ምሳሌ መሆን ሲገባችሁ እንዴት የዑለማን ስም የሚያሰድብ ተግባር ትፈጽማላችሁ? »፣

13) አህለል ከይሮች እንስራ በማለት እየለመኑ ጭምር ሲጠይቁ መስጊዱ እንዲሰራ ፈቃደኛ ባለመሆን የነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከልን መሬት ለማስነጠቅ የጀመራችሁት አካሄድን በአስቸኳይ በማቆም እንዲገነባ ይደረግ።

14) የተሰጣችሁን አማናንን ቶሎ እንወጣ በማለታቸው በሌላችሁ ስልጣን ቦርዱን በማገዳችሁ በይፋ ይቅርታ ጠይቁ። ወደ መጅሊስ እንዳይገቡ ያዘዘው አካል ላይ በአስቸኳይ እርምጃ ይወሰድበት።

15) «መጅሊስ በአስቸኳይ ህወሃት ካሰማራቸው ካድሬዎችና ተላላኪዎች ነፃ የሆነ ህዝባዊ ተቋም እንዲሆን እንጠይቃለን»፣«የሚሉ ይገኙበታል።

የዑለማ ምክር ቤት አባላት ነገ ወደ ቢሮ እንደሚገቡ የታወቀ ሲሆን በቢሮዋቸው ሳይገኙ የሚቀሩ ከሆነ ሰኞ እለት ጀምሮ በመጅሊስና በመኖሪያ ቤቶቻቸው በመመላለስ ጥያቄ ለማቅረብ መታሰቡ ታውቋል። የመጅሊስ ጉዳይ ይመለከተኛል፣ «ተቋሜን አሳልፌ አልሰጥም» የሚል የአዲስ አበባ ሙስሊም በስፍራው ሲገኝ ጥያቄዎቹን በኢስላማዊ አደብ በሰላማዊ መንገድ ብቻ ማቅረብ እንደሚገባው አሳስበዋል።
👍1
«የሀገር ጉዳይ ይቀድማል»

T.me/ahmedin99

አንዳንዶች የምታነሳቸውን ጥያቄዎችህን እንድታቆም በመፈለግ፣ሌሎች ደግሞ ጉዳዩ ሳይገባቸውና ለሀገራቸው የእውነት ከማሰብና ከመጨነቅ የተነሳ «የሀገር ጉዳይ ይቀድማል» ሲሉ ይደመጣሉ። እውነት ነው የሀገር ጉዳይ ይቀድማል። ሀገር ሕዝበ ሙስሊሙን አያካትትም ካልተባለ በቀር የሕዝበ ሙስሊሙን ችግርም የሀገር ችግር ነው። የህዝበ ሙስሊሙን ቁልፍ ችግርም መፍታት የሀገርን ችግር መፍታት ነው። ችግሩንም አለመፍታትም የሀገር ችግር እንዲቀጥል መፍቀድና መስማማት ነው።

የመጅሊስን ተቋማዊ ችግሮች በተቋማዊ አሰራር እንዲፈታ የሰባት ክልሎች እስልምና ጉዳዮችና ከሁለት ሦስተኛ በላይ የሆኑ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በፊርማቸው የጠቅላላ ጉባኤ ሲጠሩ ፖሊስ ስራዉን መስራት ትቶ ህጋዊ የሆነና 33 ሰዎች የሚሳተፉበትን የመጅሊስን ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባን ለማደናቀፍ ሲሯሯጥ፥የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በራሳቸው ተሰብስበው? በጉዳዩ ላይ በመነጋገር ችግር እንዳይፈቱ ካደረጉ በኋላ ደግሞ ከመንግስት አካላት ጋር ለስብሰባ ተቀመጡ ተባለ። በተድበሰበሰ መልኩ ችግሩ ሳይፈታ «ተፈታ» ተብሎ የተሸፋፈነ መግለጫ እንዲሰጥ ተደረገ። ወዲያው የክልል መጅሊሶችና ቦርዱ ችግሩ እንዳልተፈታ ይፋ ማድረግ ጀመሩ። ችግሩ ሳይፈታ «ተፈቷል» ያሉት አካላትና ሽማግሌዎችም ጭምር ሳምንት ሳይቆይ እንዳልተፈተ ማሳወቅ ጀመሩ።

የ60 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መሪ ተቋም የሆነው መጅሊሱ ፕሬዝዳንቱ በየመድረኩ እየዞሩ በመናገራቸው ብቻ ምንም አይነት እቅድና ሪፖርት ሳይኖረው ለሁለት ዓመታት ያክል ያለምንም፣ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ፣ ዓመታዊ እቅድ፣ተግባርና ሪፖርት በሴራ እንዲመክን ሲደረግ የሀገር ጉዳይ ካልሆነ የሀገር ጉዳይ የሚሆነው የቱ ነው?

ይህን ሁሉ በቅርበት እያየ ያለ ሕዝብ «ጥያቄዬ አልተመለሰም» ብሎ መንገድ ሳይዘጋ ከፊል የህዝበ ሙስሊሙ አካላት ወደ መጅሊስ ቢሮ በመሄድ ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዳያቀርቡ ፖሊስ ራሱ በድንጋይ ጭምር መንገድ ሲዘጋና ሌሎች እየሆኑ ያሉትን ሁኔታዎችን ስታይ የሀገርን ጉዳይ ያላስቀደመው ማን ነው? ሀገርስ የሚቀድመው ህዝበ ሙስሊሙን ወደ ኋላ በማስቀረት ነውን? መፈታት የሚችልን ጉዳይ «የሀገር ጉዳይ ይቀድማል» ስም እንዲድበሰበስ ተፈለገ? ብለህ ለመጠየቅ ትገደዳለህ።
ለዓመታት በሴራ እንዲቋረጥ የተደረገውን የአፋሩን ፕሮጀክት ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ላይ የየበኩላችንን እንወጣ!


ለዓመታት እንደቆመ እንዲቀር የተደረገው ኢስላማዊ ተቋም
★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★★
ትናንት በአፋር ከጎበኘዃቸው ስፍራዎች አንዱ በአሳይታ አቅራቢያ የሚገኘው የሱልጧን ዓሊ ሚራ መስጊድ፣ ኢሰላማዊ ኮሌጀና ቤተመንግሥት ይገኝበታል። ይህ ተቋም እንደመረጃ ምንጮቻችን ገለፃ ከሆነ ግንባታው የተጀመረው በ1980ዎቹ መጨረሻ ገደማ በቀድሞው የአፋር ሱልጧን በነበሩት ሱልጧን ዓሊ ሚራህ ጠያቂነት እና በሸህ ሙሀመድ አሊ ሁሰይን አልአሙዲ የግንባታ ወጪ ሸፋኝነት ነበር። ግንባታው 70% ከተጠናቀቀ በዃላ ነው በህወሃት መራሹ መንግስት ትዕዛዝና ቀጥተኛ ጫና ግንባታው ሳይጠናቀቅ ባለበት እንዲቀር የተደረገው። መስጂዱ ሰፊና በ2ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን ተጀምሮ የነበረው ኢስላማዊ ኮሌጀ ደግሞ ከ50 በላይ መማሪያ ክፍሎች፣ አደራሾችና ክሊኒኮችና ሌሎች ለተለያዩ ግልጋሎት የሚውሉ ክፍሎች አሉት። በማዕከሉም አጠገብ ያረጀው የቀድሞው የሱልጧን አሊሚራህ ቤተመንግስት ያለ ሲሆን በርሱ አቅራቢያም ሱልጧን አሊሚራህ በህይወት እያሉ ለርሳቸውና ለአፋር ሱልጧኖች ዘመናዊ ቤተመንግስት ግንባታ ተጀምሮ የማጠናቀቂያ(ፊኒሺንግ) ሥራ ሲቀረው እንዲቋረጥ ተደርጓል። ቤተመንግስቱ በምስሉ ላይ እንደሚታየው በርካታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ቤተመንግስቱ ተጠናቆ ሱልጧን አሊ ሚራህ በዉስጡ መኖር ሳይችሉ ሲሞቱ በአቅራቢው ተቀብረው ቀብራቸው ይገኛል።

የአካቢው አዋቂዎች እንደሚሉት ሼህ ሙሀመድ ሁሴን አልአሙዲ ኮንትራት ለተሰጠው ተቋራጭ በተዋዋሉት መሠረት ቀሪ 49 ሚሊየን ብር እንኳ እንዳይከፍሉ ጫና ተደርጎባቸው ኮንትራክተሩ ለዓመታት ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ ቢያቀርብም ምላሽ ሳያገኝ ህይወቱ እንደለፋ(ራሱን አጠፋ የሚሉ አሉ) ይገልፃሉ።

የአከባቢው አዛውንቶች እንደሚሉት የአፋር ህዝብ ይህ ኢስላማዊ ኮሌጅ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በዲኑ ላይ ይጠነክራል በሚል ምክንያት የህወሃት አመራርና የአንድ ምዕራብ ሀገር ኢምባሲ ተማክረው እንዳስቆሙ ይገልፃሉ። ዋቢ የሚያደርጉት ደግሞ የዚያ ሀገር ኢምባሲ ሰራተኞች አጠያይቀው ቦታው ላይ መጥተው በጎበኙ በሳምንቱ ግንባታ እንዲቆም መታዘዙን ይጠቅሳሉ። 100% ሙስሊም የሆነው የአፋር ህዝብ ሃይማኖቱን የሚማርበትን ኢስላማዊ ኮሌጅ እንዳይኖረው ማሰናከል የተፈለገውና መልዕክቱ ግልፅ ነው።

በአሁኑ ጊዜ የዚህ ተቋም ግንባታ ለበርካታ ዓመታት ተቋርጦ ቢቆይም በጥሩ የይዞታ ደረጃ ይገኛል። የሚመለከተው አካል ተረባርቦ ሊጨርሰው ይገባል። አንድ አባት እንደገለፁልኝ ሱልጧን ዐሊ ሚራህ በሽግግር መንግስት ጊዜ የኤርትራን መገንጠልን በዃላ ላይም በክልል የህወሃት ሰዎች ጣልቃ ገብነትናና ጫናን በመቃወማቸው ምክንያት በህወሃት ሰዎች ጥርስ ዉስጥ እንደገቡና ከዚህ ጊዜ በዃላ ማንኛውም ሱልጧኑ የደገፉትን ነገር የህወሃት ሰዎች መቃወምና ማደናቀፍ እንደቀጠሉ ገልፀውልኛል። ይህ መስጊድ፣ቤተመንግስትና ኮሌጅ በጊዜ ብዛት አርጅቶ እንደፈራርስ ቢፈለግም ይዞታው ደህናና በአሁኑ ጊዜ ከተጀመረ 20 ዓመታት የቆ ሳይሆን በቅርቡ የተጀመረ ይመስላል።(በድጋሚ የተለጠፈ)
***************

ዛሬ ሰኔ 6 ለአፋሩ ፕሮጀክት መቀጠል በያሉበት ሆነው በዚህ ውብ ታሪክ ላይ አሻራዎን ያኑሩ።
Via Ahmedin Jebel official - አህመዲን ጀበል
@nidatube @nidatubebot
👍1
ግዙፉን የሱልጣን አሊሚራህ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ለማጠናቀቅ በአፋር ክልል በአሳይታ ከተማ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ በመካሄድ ላይ ይገኛል::

ሁላችንም ባለንበት ሆነንም ያቅማችንን ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል የባንክ አካውንት ይፋ ተደርጓል።

በዚህ ታሪክ ላይ የአቅማችንን ለማበርከት:-

የአካውንት ስም: የስልጣን አሊ ሚራህ መድረሳ
የኢትዪጵያ ንግድ ባንክ 1000380109828
ዳሽን ባንክ 2936722484811
@nidatube ,@nidatubebot
1
« #በሴራ ያቆሙት የታላቁ ሱልጣን አሊሚራህን ማዕከል #በስራ እንጨርሰዋለን!!»
ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
@nidatube @nidatubebot
በሰላሳ አመቴ ወሊድ የተባለ ወጣት የትዳር ጥያቄ አቀረበልኝ።በጣም ውብና አማላይ የሚባል ወጣት ነበር።ሁሉ ነገሩን ወድጄ አንድ ነውር ብቻ ነበር ያገኘሁበት።ወሊድ ከኔ በፊት ሌላ ሰው አግብቶ ነበር።በዚያም ትዳር የወለደው አንድ ልጅ አለው።ሚስቱ ህፃኑን በወለደችበት ሰዓት ነበር ያረፈችው።ከሚስቱ ያላለቀ ፍቅር ያለው ወሊድ በእናቱ ግፊት እኔን ለማግባት ወሰነ።እኔም ከጥቂት አመታት በኃላ ከመንደሩ ሰው የሚወረውርብኝን የ"ለምን አታገባም?" ጥያቄ ለመመለስ አገባሁት።
በሰርጋችን ምሽት መጀመሪያ አደራ ያለኝ:-"አሏህ ላንቺ መልካም እንዲያረግልሽ ከሻሽ ለሁሳም መልካም ሁኚ።"ይህ ነበር አደራው።ሁሳም ካለፈ ትዳሩ ያፈራው ልጁ ነው።
ከተጋባን ከአንድ አመት በኃላ ጨረቃ የመሰለ ልጅን አላህ ሰጠኝ።ነገር ግን ልጄ ከልብ ህመም ጋር ነበር አብሮ የተወለደው።በዚህም የተነሳ ለባለቤቴ እሰጠው የነበረውን ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ለህመምተኛው ልጄ መስጠት ጀመርኩ።ይህም በመካከላችን ክፍተትን ፈጥሮ እኔ ወደእናቴ ቤት ሄድኩ።ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ወሊድ በመኪና አደገ ደረሰበት።
አደጋው ከባደ ስለነበር የመትረፍ አድል እንደሌለው ያወቀው ወሊድ በብዙ ነገራት አደራ አለኝ።የመጨረሻው አደራ ግን "አሏህ መልካም እንዲሰራልሽ ከፈለግሽ ለሂሳም በጎ አድርጊ።እሱ አሁን አባቱንም ማጣቱ ነው።" የሚል ነበር።
ይህን ካለ ብዙም ሳይቆይ ወሊድ ጥሎኝ ሄደ።ፍቅሩን በምላስ ብዙ ጊዜ ባይገልፅም እጅግ አዛኝ፣ምግባረሰናይና ርሁሩህ ነበር።
ከዚህ ወዲህ የባሌን አደራ ለመጠበቅ ነብሴን አሳልፌ ሰጠሁ።ቤተሰቦቼ ሁሳምን ለህፃናት ማሳደጊያ አንድሰጥ ቢወተውቱኝም አሻፈረኝ ብዬ እንደልጄ አድርጌ አሳደግኩት።ችግሩን፣ናፍቆቱን ሃሳቡን ሁሉ በጫንቃዬ ተሸክሜ አሳደግኩት።
በሌላ በኩል የኔው ልጅም ከህመሙ ጋር እየተታገለ አስራ አምስት አመታትን ከቆየ ወዲያ እስከ ወዲያኛው አሸለበ።ከሁሳም ውጭ አጫዋችም ሆነ አፅናኝ የሌለኝ ብቸኛ ሆኜ ቀረሁ።
ታዲያ ሁሳምም አድጎ ተመረቀልኝ።በተመረቀልኝም ቀን በሁሉም ፊት ዝቅ ብሎ እግሬን ስሞ ስጦታን አበረከተልኝ።በህይወቱ አንድም ቀን "ጀነቴ" ብሎኝ አንጂ ጠርቶኝ አያውቅም።የኔን መተኛት ሳያረጋግጥ ወደመተኛ ክፍሉም ገብቶ አይተኛም።
ይህ ልጄ ትናንት የራሱን ሆስፒታል ገምብቶ አስመረቀ።በሁሉም ፊትም አንድ ቃል ገባ።በሳምንት ጁሙዓ እለት ሁሉም ሰው በነፃ ህክምና አንዲያገኝ እንደሚያደርግ ቃል ገባ።ይህም ለወንድሙ ሰደቃ እንዲሆን በመሻት እንደሆነም ገለፀ።

ሳራህ አል-ዓቃሪ
Umer Yasin Yusuf 🙏
@nidatube @ndatubebot
ሰበር ዜና
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ራሳቸውን ከምርጫ አገለሉ።

ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በፌቡክ ገፁ

ለጅማ ከተማ ነዋሪዎች

ዘንድሮ በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጅማ ከተማ እንድወክላችሁ ሽማግሌ ከመላክ አንስቶ በተለያዩ መንገዶች እጩ እንድሆን በመጠየቅና ለእጩነት የሚጠበቀውን ፊርማ በራሳችሁ ተነሳሽነት በመፈረምና በማስፈረም የምርጫ ቅስቀሳ እንድጀምር፣ ለቅስቀሳውም «የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመወጣት ከጎንህ ነን» በማለት ላሳደራችሁብኝ እምነትና አክብሮት ከልብ እያመሰገንኩ፤ በግል እጩነት ተመዘግቤ በነበረው በምርጫው በራሴ የግል ምክንያት
ልቀጥል አለመቻሌን ላላሳወቅኳችሁ የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ሳሳውቃችሁ ከታላቅ አክብሮት እና ይቅርታ ጋር ነው።
@nidatube @nidarubebot
👍2
2025/07/13 14:16:18
Back to Top
HTML Embed Code: