አስደሳች ዜና ከሳውዲ አረቢያ
ከዛሬ እሁድ ማርች 14/2021 ጀምሮ በሳውዲ አረቢያ ከ70 አመታት በላይ ሲሰራበት የቆየው የካፋላ ህግ አገልግሎት በስራ ላይ እንዳይውል በሳውዲ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚንስትር በህግ ተደንግጎ ስራ ላይ ውሏል
በተባበሩት መንግስታት እንዲሁም በአለም የሰራተኞች መብት ተሟጋች የመሳሰሉ ድርጅቶች ለአመታት ሲተች እና ተቃውሞ ሲነሳበት የኖረው የከፋላ ህግ ባልተጠበቀ ሁኔታ ተነስቶ ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ መዋሉ ብዙዎችን አስደስቷል
" ባርነት " ብለው ሲጠራ የነበረው የከፋላ ህግ ከውጭ ሀገር ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚገቡ ሰራተኞችን የመንቀሳቀስ መብት ገድቦ ሰራተኞችን በአሰሪዎች ተፅዕኖ ስር ሙሉ በሙሉ በማዋል እንዳሻቸው ሊገለገሉባቸው ሲያደርግ የቆየ ህግ ነው ።
ከዛሬ ጀምሮ የፀናው ህግ ሰራተኞች ያለ ከፋላ በግላቸው ቀጥታ ከመንግስት መስሪያ ቤት የስራ ፍቃድ ማውጣት እንዲሁም ስራ መልቀቅም ሆነ መቀየር የሚያስችል ሲሆን ወደ ሀገራቸው መመለስ በፈለጉ ጊዜም የአሰሪዎች ፈቃድ ሳያስፈልጋቸው ባሻቸው ጊዜ መውጣት እና ተመልሶ መግባት የሚያስችል ህግ ነው ።
በሳውዲ አረቢያ ከ10 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ሰራተኞች የሚኖሩ ሲሆን በአዲሱ ህግ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል ።
Via.bilal zayid
@nidatube @nidatubebot

የመጅሊስን ችግር የተቋሙ ባለቤት የሆነውን ሕዝበ ሙስሊሙን እንደማያከብሩ የተቋሙን የመጨረሻ የስልጣን ባለቤት የሆነውን የመጅሊስን ጠቅላላ ጉባኤን በማዋከብ ፣በማዋረድና መሰብሰብ እንዳይችሉ በተራ ፖሊሶች እያደናቀፉ በጓሮ በር በሚደረግ የደህንነት ቢሮ ስብሰባ አይፈታም።
ከ42 ቀናት በፊት በሰላም ሚኒስተር ስብሰባ ላይ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በ10 ቀናት ዉስጥ እንዲደረግና ችግሩ በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እንዲፈታ የተደረሰውን ስምምነትን ሙፍቲ ራሳቸው ለዑለሞች «የደህንነት ሀላፊው አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተነጋግረን ነው » እንዳሉት ያስቀረው የደህንነት ቢሮው ነው። የዛሬውን የኢሊሌ ሆቴል ስብሰባንም ያሳገደው የአቶ ተመስገን ጥሩነህ መስሪያ ቤት የሆነው የደህንነት ተቋሙ ነው።ይኸው ተቋም ዛሬ በ12:00 በጓሮ በር እነሙፍቲን ጠርቶ «ኑ እንነጋገር» ብሎ ጠርቷል።የጠቅላላ ጉባኤን እያደናቀፉ የጓሮ ስብሰባ ችግሩን እያስታመሙ ጊዜ ለመግዛት ሌላ ጫወታ በመሆኑ አያዋጣም። «እውነትን ይዣለሁ» ብሎ የሚያምን ዑለማም ሆነ ቦርድ «አለኝ» የሚለውን እውነት ይዞ በጠቅላላ ጉባኤ ፊት ቀርቦ ፊት ለፊት ሞግቶ ይረታል እንጂ ከዑለሞች ሸሽቶ በጓሮ በር ከደህንነት ጋር ችግሮችን ልፈታ ነው ብሎ ማሰበብ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም። የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ እንዳይደረግ እያደናቀፉና ዑለሞችን እያዋከቡ በጓሮ በር ከጥቂቶች ጋር በህዝበ ሙስሊሙ መብትና ተቋም ላይ የሚደረግ ጫወታ ይቁም!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ አለፈ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ አለፈ፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ የኒጀርና የማዳጋስካር አቻ መውጣት ተከትሎ ነው 9 ነጥብ በመያዝ የአፍሪካ ዋንጫን የተቀላለቀለው፡፡
እንኳን ደሰ አለን
@nidatube

የሽግግር ጊዜ የኢ/ እ/ ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) የ2ኛ መደበኛ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ የአቋም መግለጫ
የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለዘመናት ታሪካችንን፣ አሃዛችንን፣ ስነ-ልቦናችንን የሚመጥን በአደረጃጀትና በአሰራሩ የዘመነ ለምእምኑ ወገንተኛ የሆነ፣ ጠንካራና የሀገሪቱ ሙስሊሞች ሁሉ መጠለያና አለኝታ የሆነ፣ ሁለንተናዊ ልማታችንን በበላይ የሚያስተባብርልንና የሚመራን፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና፣ ዴሞግራፊያዊ ውክልና መውሰድ የሚችል፣ ጠንካራ ተቋም ሳይኖረን እዚህ ደርሰናል፡፡ ከዚህ ቀደም ሀገሪቱን ሲያስተዳድሩ የነበሩ መንግሥታትና ሥርዓቶቻቸው እንዲሁም ከውስጥና ከውጭ በተደራጁብን ጣልቃ ገብ ኃይሎች ምክንያት አቃፊና ጠንካራ የሆነ ተቋም እንዳይኖረንም ተደርገን፣ ለዘመናት በመጅሊስ አጀንዳ ላይ ተጠምደን ከብሔራዊ አጀንዳዎች እንድንደናቀፍ፣ የህዝበ ሙስሊሙ ሐገራዊ ሁለንተናዊ ሱታፌም የተገደበ እንዲሆን፣ ህዝበ ሙስሊሙም ለሀገሩ የሚገባውንና የሚጠበቅበትን እንዳያበረክት፣ ከታሪኩና ከአሃዙ አንጻር የሚገባውን ምክንያታዊ ድርሻውን እንዳያገኝ ወይም እንዳያስከብር በመጅሊስ አጀንዳ ተጠምዶ፣ ይህን ተቋም ለማስተካከልም ተገቢ ያልሆነና የተጋነነ ዋጋም ሲከፍል ኖሯል፡፡ ጠንካራ ተቋም በማጣቱም ህዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን አጥቶ ዘልቋል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ የጠንካራ ተቋማት ባለቤት እንዳይሆን ርብርብ ያደረጉ የውስጥና የውጭ ኃይሎችን በመታገልም ሆነ የህዝበ ሙስሊሙ ጭቆናና በደል የሀገር ጭቆናና በደል አካል ነው በሚል ጠንካራና የተራዘመ ትግል በማድረግ በኢትዮጵያም የመንግሥት ሥርዓት ለውጥ እንዲመጣ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ ወኪል ተቋም የሆነውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የኢትዮጵያ ህዝበ ሙስሊሙን ታሪካዊ፣ ዴሞግራፊና አሀዝ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ተክለቁመናውን በሚመጥን መልኩ በሀገሪቱ አዋጅ ተደንግጎ በነጋሪት ጋዜጣ ደረጃ ይፋ የሆነ፣ በመዋቅሩና በአሠራሩ ሕግና ሥርዓትን የተከተለ፣ ሃላፊነትና ተጠያቂነት ያለው፣ በህዝበ ሙስሊሙ እውቅናና ይሁንታ በተመረጡ የዑላማዕና የስራ አመራር ቦርድ የሚመሩት፣ተጠሪነቱ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሆነ፣ የሁሉም እና በሁሉም ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች ባለቤትነት የሚመራ ተቋም ለማድረግ በኢፌዴሪ መንግሥት እውቅናና ድጋፍ፣ በህዝበ ሙስሊሙ ከፍተኛ ጥያቄና ክትትል መሠረት ሠፊ እንቅስቃሴ መደረጉ ይታወሳል፡፡ በሚያዚያ 23/2011 ዓ.ል የሀገሪቱን ጠቅላላ ሙስሊም በሁሉም ዘርፍ ያካትቱታል፣ ይወክሉታል የተባሉ ሙስሊም ምሁራን፣ ታዋቂ ሰዎች፣ መሻኢኾችና ዑለማዖች፣ ባለድርሻ አካላት ባሉበት በህዝበ ሙስሊሙ ትግልና በመንግሥት ትብብር የምክር ቤቱ የበላይ የሆኑ ሃያ ስድስት (26) ዑላማዖችና ሰባት (7) የቦርድ አባላት በጊዜያዊነት ተመርጠው የሽግግር የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱን (መጅሊሱን) እንዲመሩ መደረጉ ይታወሳል፡፡
የሽግግር የኢ/እ/ጉ/ጠ/ ም/ቤት (ጊዜያዊ መጅሊሱን) እንዲያደራጁት እነዚህ በጊዜያዊ አመራርነት የተመረጡት ሃያ ስድስቱ (26ቱ) የዑለማዕ ምክር ቤት አባላትና ሰባቱ (7) የሥራ አመራር ቦርድ አባላት በዋናነት የሚከተሉትን አምድ ሥራዎች እንዲሰሩ የተመረጡ ናቸው፡፡
1. የሙስሊሙን አንድነት ለማረጋገጥ የዑላማዕ አንድነት ሰነድ ረቂቅ ለመተግበር
2. የመጅሊሱን ተቋማዊ ለውጥ ለማረጋገጥ ረቂቅ መዋቅሩን መተግበር
3. የመጅሊሱን በአዋጅ እንዲቋቋም ተገቢውን ክትትል ማድረግ
ከነዚህ ውሥጥ መጅሊሱን በነጋሪት ጋዜጣ በአዋጅ እንዲቋቋም መንግሥት ትልቁን አስተዋጽኦና ትጋት በማሳየት የመጅሊሱ ጊዜያዊ አመራሩም ባደረጉት ርብርብ አዋጁ ጸድቆ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሟል፡፡ የመጅሊሱን ተቋማዊ ለውጥ ለማረጋገጥ ረቂቅ መዋቅሩን ከመተግበር እና የመጅሊሱን በአዋጅ እንዲቋቋም ተገቢውን ክትትል ከማድረግ
አኳያ በተለያዩ ምክንያቶች ይህ ነው የሚባል ሥራ አልተሰራም፡፡
የሽግግር መጅሊሱን ጠቅላላ እንቅስቃሴ ለመከታተል፣ ለመገምገም፣ የጊዜያዊ መጅሊሱን የሁለት ዓመት የአፈጻጸም እንቅስቀሴና የሂሳብ ኦዲት ለመስማት፣ለመገምገም፣ ለማጽደቅ እንዲሁም ቀጣይ የእርምት አካሄድን ለመወሰን የሽግግር መጅሊሱ የበላይ አካል የሆነው ጠቅላላ ጉባኤ በሽግግር መጅሊሱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 7(7)መሰረት በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባ እንዲያርግ ቢደነግግም ጠቅላይ ጉባኤው መደበኛ ስብሰባ ሳያደርግና ሳይጠራ ሁለት ዓመታትን አሳልፏል፡፡ በጊዜያዊነት ህዝበ ሙስሊሙ መጅሊሱን እንዲያደራጁ በጊዜያዊነት አደራ ሰጥቶ የወከላቸው የየክልሉና የከተማ አስተዳደር መጅሊስ አመራሮች በተደጋጋሚ አደራቸውን ለመወጣት፣ ሥራዎችን ለመስራት፣ የሚጸድቀውን ለማጽደቅ፣ የሚታረመውን ለማረም፣ በፌደራሉ መጅሊስ፣ በከተማ አስተዳደር መጅሊሶቹና በየክልሉ መጅሊሶችን አደረጃጀትና አሰራርን ከማጠናከር አኳያ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች፣ የተከናወኑ ሥራዎችን ለመገምገምና ለማስተካከል የጠቅላላ ጉባኤው መደበኛ ስብሰባ እንዲደረግ የየክልሉ መጅሊስ አመራረሮች፣ የከተማ አስተዳደር መጅሊሶች፣ የፌደራል መጅሊሱ የሥራ አመራር ቦርዱና አብዛኛው የዑለማዕ ምክር ቤት በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ያለ አንዳች ህጋዊ አሰራርና መመሪያ ስብሰባው እንዳይደረግ ተደርጎ ዘልቋል፡፡
በመሆኑ በሽግግር መጅሊሱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 15 መሰረት በየካቲት 2005 ዓ.ል በጸደቀው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 26 በስብሰባና የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት ንዑስ አንቀጽ 26.1 እና 26.2 ላይ በተጠቀሰው መሰረት የጠቅላላ ጉባኤው አባላት 1/4ኛ መደበኛ ስብሰባ እንዲደረግ የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ ማድረግ እንደሚችሉ የሚደነግግ በመሆኑ የጠቅላላ ጉባኤው አብላጫ አባላት (23 አባላት ከጠቅላላው 33 አባላት) የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ ያደረጉ በመሆኑ ከ ቀን 20/07/2013 ዓ.ል እስከ 21/07/2013 ዓ.ል በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ በኤሊሌ ሆቴል መደበኛ ስብሰባ ለማድረግ እጅግ በትዕግስት የተሞላ ጥረትና ትግል ጠይቋል፡፡ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላም የጠቅላላ ጉባኤ አባላትና የክልል እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት አመራሮች፣ የከተማ መስተዳድር መጅሊሶቹ አመራሮች፣ ተጋባዥ እንግዶችና ባለድርሻ አካላት ባሉበት የጠቅላላ ጉባኤው አስቸኳይ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ በዚህም የሚከተሉት ባለ አስራ ሦስት (13) ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡
1. እኛ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላላ ጉባኤ አባላት በሸራተኑ ሚያዚያ 23/2011 ዓ.ል የቀረቡትን ረቂቅ ሰነዶች ማለትም የዑለማእ አንድነት ሰነድ ያለ ማሻሻያ እንዳለ እንዲሁም የመጅሊሱ መተዳደሪያ ደንብ (ህገ-መጅሊስ) ሰነድ በማሻሻያ በሙሉ ድምጽ አፅድቀናል። ከዛሬ ጀምሮ ሰነዶቹ ጸድቀው ከፌደራል እስከ ታችኛው የመጅሊሱ እርከን ድረስ ተግባራዊ እንዲሆኑ ወስነናል፤ ለተፈጻሚነታቸውም ታትረን የምንሰራ መሆናችንን እናረጋግጣለን፣
2. ከጠቅላላ ጉባኤው እና ከሥራ አስፈፃሚው ስምምነት ውጪ በግለሰብ ወይም በጥቂት ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ደረጃ የተወሰኑ ማንኛውም ከህግና አሰራር ውጭ የተወሰኑ ውሳኔዎችንና ስራዎችን ውድቅ አድርገናል። ተፈጻሚም አይሆንም፡፡

3. በጠቅላይ ምክር ቤቱ አንዳንድ አመራሮች ከህጋዊነት እና ከኢስላማዊ ሥነ-ምግባር ባፈነገጠ መንገድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን ማገድን እያወገዝን ውሳኔውን የእግድ ውሳኔው የማይጸና መሆኑን ወስነናል።
4. በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትም ሆነ በሌሎች እስላማዊ ተቋማት ውስጥ ለሚነሱ አለመግባባቶች መፍትሄ የሚያፈላልግ የግልግል ሸንጎ መቋቋሙንና ወደ ተግባር እንዲገባ ሁሉም ወገኖች ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን::
5. በጠቅላላ ጉባኤው የሚወሰኑ ውሳኔዎች በሁሉም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ተቋማትና መስጂዶች ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል። ውሳኔዎቹን በማያከብሩ፣ በማይፈፅሙና በማያስፈፅሙ አካላትም ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።
6. በሸራተኑ ጉባኤ ተወስኖ እንዲተገበሩ ከተወሰኑ ወሳኝ የምክር ቤቱ ሥራዎች መካከል የክልል መጅሊሶች መዋቅር ማደራጀት እና እስከ መስጂዶች ማውረድ መሆኑ ይታወሳል። ሆኖም በአንዳንድ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የበላይ አመራሮች ሸፍጥና አሻጥር ምክንያት አንዳንድ ክልሎች እስከዛሬ ድረስ ግዜያዊ አዲስ የመጅሊስ አመራሮችን ሳይመርጡ እንዲሁም አንዳንድ ክልላዊ መጅሊሶች መዋቅራቸው እስከ መስጅድ ድረስ እንዳይወርድ መደረጉ ያደባባይ ሚስጥር ነው። በመሆኑም እኛ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አዲሱ ጊዜያዊ መጅሊስ ያልተቋቋመባቸው ክልሎች ሦስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውሥጥ እንዲቋቋምባቸው እና መዋቅራቸው እስከ መስጂድ ያልደረሰባቸው ደግሞ እንዲደርስ ወስነናል። ይህን ውሳኔ ለማስፈፀምም ባለ ድርሻ አካላት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።
7. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የመተዳደሪያ አዋጅን ለመተግበር የሚያስችሉ ደንቦችና መመሪያዎች ከህግ ባለሞያዎችና ሌሎች ምሁራን ጋር በመተባበር እንዲዘጋጅ ወስነናል።
8. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጊዜያዊ መጅሊስ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ሲሰሩ ለነበሩት ጥፉቶች ተጠያቂ በሆኑት አንዳንድ አመራሮች ላይ በህግ አግባብ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ መውሰዳችንን እናረጋግጣለን።
9. የሙስሊሙን ማሕበረሰብ በብሄር፣ በመዝሀብና በጥቃቅን ልዩነቶች ከፋፍሎ ለማዳከም ከውስጥና ከውጪ የሚደረጉትን አሻጥሮች እያወገዝን ሙስሊሙ ማህበረሰብ አንድነቱን እንዲያጠናክር በማሳሰብ ለተግባራዊነቱ ጠንክረን እንሰራለን።
10. ሙስሊሙ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) የጥቂት እናውቅልሀለን ባዮች ንብረትና ርስት ያለመሆኑን አውቆ ከሩቅ ተመልካችነቱን ትቶ በባለቤትነት ስሜት ተቋሙን እንዲያስከብር ጥሪያችንን እናቀርባለን::
11. በውጭ ኦዲተር የተመረመረውን የኦዲት ምርመራና የተዘጋጀውን የኦዲት ሪፖርት አጽድቀናል፤ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም እንደገና በተመሰከረላቸው ኦዲተሮች እንዲመረመር እንፈቅዳለን
12. አሁን ያለው የእስልምና ጉ/ጠ/ም/ቤት የሽግግር እንደመሆኑና አመራሩም ለስድስት ወር በጊዜያዊነት የተመረጠ ወይም የተሾመ በመሆኑ የሀገሪቱ የመንግሥት ምርጫ በተደረገ ከሶስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውሥጥ ጠቅላላ ሀገራዊ የመጅሊስ አመራር ምርጫ እንዲደረግ ወስነናል፡፡
13. በሚያዚያ 23 ቀን 2011 በሸራተን አዲስ በተደረገው ጉባኤ ላይ የፌደራሉን የሽግግር መጅሊስ እንዲመሩ ከተሰየሙት ሀያ ስድስቱ ዑለማዓዎች መካከል አብዛኞቹ በተለያየ ህጋዊ ባልሆነ አሰራርና ውሳኔ ምክንያት በአዲስ አበባ የስራ ቦታቸው እንዳይገኙ ወደ ተለያዩ ክልሎች መላካቸው ፍፁም አግባብ አለከመሆኑን ጠቅላላ ጉባኤው ወስኗል፡፡ ከዚህ በኃላም በአዲስ አበባ የሥራ ገበታቸው ተገኝተው ሥራቸውን እንዲሰሩና የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነትና የህዝብ አደራ እንዲወጡ ጠቅላላ ጉባኤው በአንድ ድምፅ ወስኗል፡፡
አሏሁ አክበር ወሊላህ አል ሐምድ!!
የሽግግር ጊዜ የኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት
መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ል
አዲስ አበባ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አትክልት ተራ በሁለት ግለሰቦች መካካል በተፈጠረ ፀብ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ፡፡
መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ በግምት 2፡00 ሰዓት አካባቢ በሁለት የጉልበት ሰራተኞች መካከል በስራ አለመግባባት ምክንያት በተፈጠረ ፀብ የአንደኛው ሕይወት ማለፉን እና ገዳዩ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የተወሰኑ ግለሰቦች የግድያ ወንጀል በፈፀመው ተጠርጣሪ ላይ ጉዳት ለማድረስ በፈጠሩት ፀብ ምክንያት በፖሊስ አባላትና በአካባቢ ጥበቃ ስራ በተሰማሩ አጋዥ ሀይሎች ላይ ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
ግርግሩን ለማብረድ ፖሊስ ባደረገው ጥረት አካባቢው ተረጋግቶ መደበኛ ሰራ መጀመሩን እና ግርግር በማስነሳት ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽኑ አሰታውቋል፡፡
በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሁለት ብሔሮች መካከል ፀብ እንደተነሳ ተደርጎ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኮቪድ 19 ክትባትን ለማግኘት ምንም ዓይነት የኮቪድ 19 ቅድመ ላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ አያስፈልግም!
___________
መጋቢት ፣ 4/2013 ዓ.ም በአገራችን በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች የተጀመረው የኮቪድ 19 የክትባት መርሃ ግብር በታቀደው መሰረት በመላው ሀገራችን መሰጠቱን ቀጥሏል፡፡
እስካሁን ባለው ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የጤና ባለሙያዎች እየተከተቡ ሲሆን እድሚያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ከ55-64 ዓመት ሆነው የሚታወቅ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችም ከመጪው ሰኞ ጀምሮ (መጋቢት 27/2013 ዓ.ም) የኮቪድ 19 ክትባትን ማግኘት ይጀምራሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ክትባቱን ለመውሰድ የኮቪድ 19 የቅድመ ላብራቶሪ ምርመራ ያስፈልጋል እና ሌሎች ክትባቱን በተመለከተ የሚነገሩት ነገሮች ማህበረሰባችን ትክክል እንዳልሆኑ በመገንዘብ የክትባት አገልግሎቱን እንዲወስድ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ከአላስፈላጊ ወጪ አልፎም ከሚፈጠረው ትርምስና አካላዊ ንክኪ እንዲቆጠብ ሚኒስቴር መስርያቤቱ መልዕክቱን ያስተላለፋል፡፡
አሁን ላይ ማህበረሰባችን ሊገነዘበው የሚገባው ክትባቱ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ብሎም በወረርሽኙ ሊከሰት የሚችለውን ሞት እና ፀኑ ህመምን ለመቀነስ የሚያግዝ ቢሆንም ሁላችንም የመከላከያ ዘዴዎችን ማስክ መጠቀም፣ ርቀትን መጠበቅ እና የእጅ ንጽህናን መጠበቅ የየዕለት ተግበራችን ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
ዳግም ትኩረት ለኮቪድ 19 ምላሽ በመስጠት ህዝባችንን ከከፋ ጉዳት እናድን!

ሳዳም ሁሴን በስቅላት እንዲገደሉ የፈረዱት ዳኛ ህይወት አለፈ
በቀድሞው የኢራቅ ፕሬዝዳንት ሳዳም ሁሴን ላይ የሞት ፍርድ ያስተላለፉት ዳኛ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አለፈ።
የኢራቅ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ዳኛ መሀመድ አሪቢ መጂድ በኮሮና ቫይረስ ምከንያት ህይወታቸው አልፏል።
የቀድሞው ኢራቅ ፕሬዝዳንት ሳዳም ሁሴን የኒውክሌር ጦር አላቸው በሚል በአሜሪካ እና እንግሊዝ ጥምር ጦር አማካኝነት በተደረገ ዘመቻ መንግስታቸው መፍረሱ ይታወሳል።
በመጨረሻም ሳዳም ሁሴን ታህሳስ 1998 ዓ/ም ከተደበቁበት ዋሻ ተይዘው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው በባግዳድ በስቅላት መገደላቸው አይዘነጋም።
ሳዳም ሁሴን በተከሰሱበት የዘር ማጥፋት ወንጀል እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥፋተኛ ናቸው በሚል የሞት ፍርድ ያስተላለፉት ዳኛ መሀመድ አሪቢ በተወለዱ በ52 ዓመታቸው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
Via .. al ain

ሽሹት እንዳሉት ሸሽተናል!
የዛሬ ሻዕባን 27 ድንቅ የጁምዐ መልዕክት በሸይኽ ሰኢድ ሁሴን (ሱመያ)
«እኛ ሙስሊም ብቻ ነን።ሙስሊም የሚለውን ስም ተቶ ሌላ ቅጥያ ይዞ ከመጣ ሽሹት!!»
•
•
ዛሬ ዕለተ ጁምዐ ሻዕባን 27/1442 የሱመያ መስጅድ ኢማም ሸይኽ ሰኢድ ሁሴን ጠቃሚ የሆነና ሁሉም ሙስሊም ሊሰማው የሚገባ ከወቅታዊ ፖለቲካ ጡዘት የሚያወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሸይኻችን በጁምዐው ኹጥባ ላይ ስላለንበት ሁኔታና ከፊታችን እየመጣ ስላለው ታላቁ ወር በደንብ አድርገው ካስተማሩ በሗላ ኹጥባው አልቆ የጁምዐ ሶላት ተሰገደ። የጁምዐ ሶላት ተሰግዶ ካለቀ በሗላ ብዙወች የሚናፍቁትና የሚፈልጉት የሸይኻችን ሙሀደራ ቀጠለ።
ሸይኻችንም እንድህ አሉ፦
«እኛ ሱፍያም አይደለንም፣ውሀብያም አይደለንም፣ሻፍዕያም አይደለንም፣ሀኒፍያም አይደለንም፣ማሊክያም አይደለንም፣ሀንበልያም አይደለንም። እኛ ሙስሊም ሙስሊማት ብቻ ነን። ሙስሊም የሚለውን ስም ተቶብሌላ ቅጥያ ይዞ ከመጣ ሽሹት።
እባካችሁ ሙስሊም ከሚለው ውጭ ሌላ ክፍፍል ውስጥ አትግቡ። ሱፍያም የሚለው ውሀብያም የሚለው አንድም ቦታ ላይ አልተጠቀሰም። አሏህ የጠቀሰው ሙስሊም የሚለውን ብቻ ነው። ክርስቲያኖችም ሆነ ሌሎች አካላት የሚያውቁን ሙስሊም በሚለው ነው።
ውሃብያ ሱፍያ ብለው የሚከፋፍሉንም ሙስሊም መሆናችንን ነው የሚያውቁት!!» በሚጣፍጠው አንደበታቸው ይህን መልዕክት አስተላልፈዋል።ሀቂቃ ሲናገሩ ስሜታቸው ልዩ ነበር።በጣም ኮስተር ብለው ነበር ይህን መልዕክት ያስተላለፉት።እንደሳቸው አይነት አባትን ያብዛልን።
እሳቸው በተናገሩት የምንጠቀም ያድርገን!!

ሼይኽ ዶ/ር መሐመድ ሐሚዲን አብዱሰመድ እንኳን ደስ አሎት!
የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በብቃት አጠናቀው ለምርቃት በቅተዋል!
መብሩክ ብለናል
ይበልጥ ኡማውን የምትጠቅሙበት፣እንደ ሁልጊዜው ኡማውን በሃቅ ላይ ወደ አንድነት እንዲሰባሰብ ጥሪ የሚያደርጉበት እውቀት አላህ ያድርግሎት
ረጅም እድሜ ከአፊያ ጋር አላህ ይወፍቆት
@nidatube @nidatubebot
የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በብቃት አጠናቀው ለምርቃት በቅተዋል!
መብሩክ ብለናል
ይበልጥ ኡማውን የምትጠቅሙበት፣እንደ ሁልጊዜው ኡማውን በሃቅ ላይ ወደ አንድነት እንዲሰባሰብ ጥሪ የሚያደርጉበት እውቀት አላህ ያድርግሎት
ረጅም እድሜ ከአፊያ ጋር አላህ ይወፍቆት
@nidatube @nidatubebot
ኢናሊላሂ ወኢናኢለይሂ ራጂኡን
✳✳✳✳✳✳✳✳✳✳
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ምክር ቤትና የጠቅለላ ጉባኤ አባል የነበሩት ሼህ ሂዝቡላ ሙሐመድ ዓሚን አረፉ። ሼህ ሒዝቡላህ እስከ እለተ ህልፈታቸው ድረስ ህዝበ ሙስሊሙ ሃይማኖቱን እንዲገነዘብ በማስተማር፣መብቶቹ እንዲከበሩ ከሌሎች ዓሊሞች ጋር ሆነው በተለያዩ ሚናዎችን ለመወጣት ሲታገሉ ነበሩ።ሼህ ሂዝቡላህበህዝበ ሙስሊሙ ችግሮች እንዲቀረፉ እና መጅሊስ እንዲስተካከል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ሲሆኑ በሚያዚያ 23 ቀን በሸራተን ጉባኤ ላይ ተመርጠው ከነበሩ 26 ዑለሞች አንዱ ነበሩ።
ሼህ ሒዝቡላህ ሙሐመድ አሚን ከሰሜን ወሎና ትግራይ ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጉዳዮች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ተሳታፊ የነበሩና የተለያዩ ሚናዎችን ሲወጡ የነበሩ ናቸው። ከነዚህም መካከል: -
1) ሼህ ሒዝቡላህ በሰሜን ወሎና ትግራይ ኪታብ በማቅራት በርካታ ደረሶችን ያፈሩ፣በአከባቢዎቹም በዳዕዋና ኢስላማዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ የታወቁ ዐሊም ነበሩ።
2) በ1984 ሰሜን ወሎን በመወከል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በጊዜው እየተረቀቀ በነበረው የመተዳደሪያ ደንብና የምርጫ ሂደት ላይ ለህዝቡ ግንዛቤ እንዲያስጨብጡና እንዲያወያዩ ተመርጠው ከነበሩት 11 የኮሚቴ አባላት አንዱ ነበሩ።
3) በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጥቅምት 1985 በተደረገው ምርጫ ተመራጭና የመጅሊስ የዕርዳታና በጎ አድራጎት ኮሚቴ ምክትል ዋና ጸሐፊ ነበሩ።
4) የኢትዮጵያ ዑለሞች ማህበር ምክትል ዋና ጸሐፊና የአልሂጅራ መጽሔት የአረብኛው ክፍል ዋና አዘጋጅም ነበሩ።
5) ከ2004 ጀምሮ ሲደረግ በነበረው ህዝበ ሙስሊሙ የመብት ትግል ላይ «መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ»፣ «አህባሽ በግዳጅ በህዝቡ ላይ አይጫን» እና ለየመጅሊስ መሪዎችን መምረጥ ያለበት ህዝቡ እንጂ መንግስት አይደለም» ብለው በመቃወማቸው በተደጋጋሚ ጊዜ ሲታሰሩ ነበሩ።
6) ሼህ ሒዝቡላህ ሙሐመድ አሚን በሚያዚያ 23 ቀን 2011 በሸራተን ሆቴል ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤትን በጊዜያዊነት እንዲመሩ ተመርጠው ከነበሩት 26 ዑለሞች እና 7 የቦርድ አባላት መካከል አንዱ ነበሩ።
7) ሼህ ሒዝቡላህ የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበበ ሲመጡ በመንገድ ላይ ታስረው የተለቀቁ ሲሆን በአዲስ አበባ ከደረሱ በኋላም በኢሊሌ ሆቴል ተጠርቶ የነበረው የጠቅላላ ጉባኤ እንዳይካሄድ በፖሊስና በደህንነት አካላት ወከባ ሲደረግባቸው ከነበሩ ዑለሞች መካከልም አንዱ ነበሩ።
8) ሼህ ሒዝቡላህ የመጅሊሰ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ከፈረሙ ዑለሞች መካከል የነበሩና የመጅሊስ ፕሬዝዳንት ሀጅ ዑመር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በ2 ሦስተኛ የጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፕሬዝዳንቱ አልገኝም በማለታቸው «በመጅሊስ ጉዳይ እኛ የማናውቀው ችግር ካለ ንገሩንና እንወያይ» በሚል ከተለየዩ ክልሎች ተውጣጥተው ወደ ሀጂ ዑመር እድሪስ መኖሪያ ቤት በማቅናት በጥበቃ እንዳይገቡ ከተደረጉት ዑለሞችም አንዱ ነበሩ።
9) ሼህ ሂዝቡላህ ሰሞኑን የተካሄደው የመጅሊስ ጠቅላላ ጉባኤውን ዉሳኔ ሳይፈጸም ወደ ትውልድ ቀያቸው አልመለስም በሚል ከሌሎች ዑለሞች ጋር በአዲስ አበባ ሆነው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የአቤቶታ ደብዳቤ አቅርበው ምላሽ እየጠበቁ እያሉ ትናንት በድንገት ታመው ሕይወታቸው አልፏል።
አላህ ለእርሳቸው መልካም ስራቸውን ተቀብሎ በእዝነቱ ጀነትን እንዲለግሳቸው ፣ለቤተሰብ፣ ለወዳጅና ዘመድ መጽናናት እንዲሁም ለህዝበ ሙስሊሙ ደግሞ ሼህ ሂዝቡላህ እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ድረስ ሳይታክቱ የታገሉለት የመጅሊስ መስተካካልን እንዲያጎናጽፍፈው አላህን እጠይቃለሁ። «ኢንና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!»

እየተካሄደ ያለው የ20/80 እና የ40/60 አማራጭ የማህበር መኖሪያ ቤት ምዝገባ ተራዘመ
ሚያዚያ 6/2013 (ኢዜአ) እየተካሄደ ያለው የ20/80 እና የ40/60 አማራጭ የማህበር የመኖሪያ ቤት ምዝገባ ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው እንዳስታወቀው፤ ምዝገባው እንዲራዘም የተደረገው ከህብረተሰቡ በቀረበ ጥያቄ መሰረት ነው።
በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 አማራጮች ከተመዘገቡት ቤት ፈላጊዎች ውስጥ አቅምና ፍላጎት ያላቸው በጋራ ሕንፃ መኖሪያ ቤት በህብረት ሥራ ማህበር ተደራጅተው የቤት ባለቤት እንዲሆኑ አዲስ አሰራር ተዘርግቷል።
በመንግስት ተዘጋጅቶ በሚቀርብ መሬት የቁጠባ ሂሳባቸውን ያልዘጉ ተመዝጋቢዎች 70 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ በመፈጸም በማህበር ተደራጅተው የመኖሪያ ህንጻዎችን መገንባት እንደሚችሉም አሰራር መዘርጋቱ ይታወሳል።
ምዝገባውም ከመጋቢት 21 እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።
በምዝገባውም እስካሁን ከ8 ሺህ 500 በላይ የማህበር ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውን አስታውቋል።
በተለየ ምክንያት ምዝገባውን ያልሰሙ የአማራጭ ቤት ልማት ፕሮግራሙ ፈላጊዎች በመኖራቸው ተጨማሪ እድል ለመስጠት ሲባል የምዝገባ ጊዜውን ማራዘም አስፈላጊ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።
በመሆኑም ተመዝጋቢዎች ከሚያዚያ 6 እስከ 15 ቀን 2013 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን አውቀው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዲመዘገቡ ጠይቀዋል።
ለመመዝገብ እየፈለጉ በሲስተም መጨናነቅ ምክንያት ላልተመዘገቡና ከመረጃው ማዳረስ አንጻር ተጠቃሚው በቂ ግንዛቤ ባለመያዙ ቀኑ ተራዝሟል።
ተመዝጋቢዎች በማህበራዊ ትስስር ገጽ በቢሮው አድራሻ WWW.aahdab.gov.et ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የሙስሊም AlD አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅትን በማስተባበር ለሀላባ ዞን ከ25 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ
የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጌታቸው እንደገለጹት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ አማካኝነት ከ25 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል።
በኡስታዝ አቡበክር አህመድ አማካኝነት የተገኘው የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ እና በሀላባ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ሀቢብ ዳቆሮ ርክክብ ተደርጓል፡፡
በርክክብ ስነ-ስረዓቱ ላይ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የኡስታዝ አቡበከር አህመድ ተወካይ የሆኑት አቶ ሱልጣን ናስር ተገኝተዋል።
በዚህም የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የAID አሜሪካን ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅትን በማስተባበር ለሀላባ ዞን ላደረጉት የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ በሀላባ ህዝብ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው አያይዘውም በኡስታዝ አቡበክር አህመድ አማካኝንነት የተደረገውን ድጋፍ በማስተባበር ወደ ሀላባ ዞን በአፋጣኝ እንዲደርስ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ለነበሩት ለዞኑ ጤና መምሪያና ለዞኑ ፋይንናስ መምሪያ እንዲሁም ለአቶ ሱልጣን ናስር ምስጋና ችረዋል፡፡
የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጀማል ኑርዬ በበኩላቸው በኡስታዝ አቡበከር አህመድ አማካኝነት የተደረገው ድጋፍ በአፋጣኝ ወደ ዞን እንዲደርስ ለማስቻል በተቀናጀ መልኩ ተሰርቷል፡፡
በዚህም ለሙስሊም AlD አሜሪካ ሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅትን ኣንዲሁም ለኡስታዝ አቡበክር አህመድ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቅርቡም ለአፋር እና ለወሎ ኮምቦልቻ 25ሚሊዬን ብር የሚያወጡ ድጋፎችን ለማድረስ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ኡስታዝ አቡበክር አህመድ አስታውቀዋል!
የዚህ መስሉ ድጋፍንም ለሌሎች ቦታዎች ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ጨምረው ገልፀዋል::
በዚህ የተከበረ ወር የዚህ መሰሉን ድጋፍ በማስተባበር ድጋፍ ላደረጉት ኡስታዝ አቡበክር አህመድ አላህ መልካም ስራቸውን ይቀበላቸው!
አሚን

የረመዳን ስጦታ ዳዕዋ ቲቪ!
ለኢትዮጵዬያ ሙስሊሞች ዲናዊ ጣብያዎች እየተበረከቱለት ይገኛሉ! አልሃምዱሊላህ
በታላቁ አሊማችን በዶ/ር ሼይኽ መሐመድ ሐሚዲን የተቋቋመው ዳዕዋ ቲቪም የሙከራ ቅርጭቱን ጀምሯል!
ይህን አስመልክቶም ሼይኽ መሐመድ ሐሚዲን ይህን መልዕክት አስተላፈዋል:-
"እነሆ ቃል በገባነው መሠረት፣ የሕዝባችንን የዒልም ጥማት ለመቁረጥ በማለም፣ ዳዕዋ ቲቪን ኢትዮ ሳት ላይ ይዘንላችሁ መጥተናል። በአሁኑ ወቅትም የሙከራ ሥርጭታችንን እያስተላለፍን ሲሆን፣ አላህ ከፈቀደ በቅርብ ጊዜ ውስጥ መደበኛ ሥርጭታችንን የምንጀምር ይሆናል። እስከዚያው መልዕክቱን ላልደረሳቸው በማዳረስ ከጎናችን እንድትሆኑ በአክብርዎት እጠይቃለሁ።
#ዳዕዋ_ቲቪ
«ጉዞ ስንቅን ይዞ!»