Telegram Web Link
የደብረ ታቦር (ቡሄ) ፕሮፋይል ለምትፈልጉ

እባካቹ ሼር🙏
✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
​ነሐሴ 11/12/2013 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ 1 ቆሮ 5÷11-ፍ.ም
ንፍቅ ዲያቆን፦1 ዮሐ 2÷14-20
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 12÷18-ፍ.ም

ምስባክ ፦ መዝ 44፥16-18
ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ
ወትሰይሚዮሙ መላዕክተ ለኩሉ ምድር
ወይዘክሩ ስመኪ በኩሉ ትውልደ ትውልድ

ትርጉም ፦
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ
በምድር ሁሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያስባሉ

ወንጌል ፦ ሉቃ 6÷20-24
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

​✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
እንኳን ለደብረ የታቦር በአል በሰላምአደረሳችሁ

​✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
እንኳን ለደብረ የታቦር በአል በሰላምአደረሳችሁ

​✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚 @nu_enamasgin 💚
💛 @nu_enamasgin 💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
ስለ.ደብረ.ታቦር.አንድ.አንድ.እንበላቹ!!!!!


​​​​#ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡

የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

#ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡

የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

#ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡

አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሲወርድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

መልካም በአል ብለናል

​✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
ነሐሴ 14/12/2013 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ 1 ቆሮ 1÷10-19
ንፍቅ ዲያቆን፦ ያዕ 1÷12-22
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 1÷30-34

#ምስባክ ፦ መዝ 43፥4-6
ዘአዘዝከ መድኀኒቶ ለያዕቆብ
ብከ ንወግኦሙ ለኩሎሙ ፀርነ
ወበስምከ ናኀስሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ

#ትርጉም
ለያዕቆብ መድኀኒትን እዘዝ
ባንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን
በስምክም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን

#ወንጌል ፦ ማቴ 17÷14-24
#ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

​✥◦◦┈┈◦◦●◉ ✞ ◉●◦◦┈┈◦◦✥
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✥➱➱➱➱➱✟➱➱➱➱➱✥
ጽኑ ቃልኪዳን ነው ለሱ የተሰጠው
አባ ሀብተማርያም ለጽድቅ የመነነው
ክብሩ ታላቅ ነውፀጋው ልዩነው

አዝ

የጸሎቱ ዕጣን ድዊውን አድኗል
የታወረው በርቶ ሽባውን ተርትሯል
ዘሬም ለዓለማችን ጽኑ መዳኛነው/2/
አባ ሀብተማርያም ኪዳኑ ልዩነው/2/

አዝ

እረሀብ ቸነፈር ምድርላይ ቢበዛ
የማዕጠንቱ ፀሎት ፈውሱን አበዛ
በውስጥም በውጪም በጥላው ለሉቱ/2/
ዛሬም መድኃኒትኒ ነው አብትዬማጠንቱ/2/

አዝ

ለሚያምን ይቻላል ታብሎ እንደተፃፈ
በሀብተማርያም ጸሎት ጽኑሞት አለፈ
ከድቅድ ጨለማ መውጣት ከሰኛችው/2/
ሀብተማርያም በሉ ትፈወሳላችው/2/

አዝ

የጻድቅ ሰው ጸሎት ሀይልን ታደርጋለች
በስራዋ ብዙ ፈውስን ትሰጣለች
ይደርብን ለኛም የቅዱሳን ፅጋ/2/
ምልጃ ጥበቃቸው እንዲሆን ከኛጋ/2/
💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
❤️@nu_enamasgin❤️
#ወርኀ_ጳጉሜ "ጳጉሜን"

#ጳጉሜ_ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ በመባል ትታወቃች ፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት / የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡

#ጾመ_ዮዲት

ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙኃኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ፤ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲት 2፥2-7 እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ፤ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ፤ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡

ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች። በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ፤ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ፤ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድንበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲት 8፥2 ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡ ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህም ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡

የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጳጉሜን) ይሁንላችሁ፡፡


💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
ጳጉሜን እኔና ጓደኞቼ
     *~★★~*

… ዘንድሮም እንደተለመደው ፌስቡክ ጳጉሜን መድረሷን ጠብቆ ከገጹ ቢያግደኝም። እኔ በቴሌግራም ቻናሌ እናንተ ደግሞ በፌስቡክ ገጻችሁ ማጥለቅለቃችንን እንቀጥላለን።

•••
እኔ ዘመዴ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ጓደኞቼ በሙሉ አንድ ላይ ሁነን መጪውን የወርሀ ጳጉሜን ፭ቱን ቀናት ልክ እንደ አምናው ካቻምናው ሁሉ ዘንድሮም ዘመነ ማቴዎስን አሳልፈን ዘመነ ማርቆስን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንገኛለን። ዘንድሮ እንዲያውም በቋሚ ሲኖዶሳችን ጭምር ወርሀ ጳጉሜን በጾም፣ በጸሎትና በምህላ እንድናሳልፍ ሁሉ ዐዋጅ ታውጇል። አዲሱን ዓመትም በዚህ መልኩ እንቀበላለን ማለት ነው። እናም እኛም ከጾም ጸሎት ምህላው ጎን ለጎን አምስቷን ቀናት እንደልማዳችን በዚህ መልኩ እናሳልፍ ዘንድ አስበናል። ወስነንም ተዘጋጅተናል።
                     
፩፥ ጳጉሜ ፩  የማዕተብ ቀን።
፪፥ ጳጉሜ ፪  የክብረ ክህነት ቀን።
፫፥ ጳጉሜ ፫  የፊደል ገበታ ቀን።
፬፦ ጳጉሜ ፬ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተክርስቲያን ቀን።
፭፦ ጳጉሜ ፭  ከሱስ ሁሉ የመላቀቂያና ለአቅመ ደካሞች የሥጦታ ቀን።

•••
ጳጉሜ ፩ ፥ የማዕተብ ቀን ነው።

… የተዋሕዶ ልጆች አንገት በሙሉ በአንገት ማዕተብ ክር ያሸበርቃል። የመስቀል ዓይነት የፌስቡክና የቴሌግራም ቻናሎቻችንንም ያጥለቀልቃል። በዕለቱ ፌስቡክ ሌላ ወሬም የለም፣ ሌላ ፎቶም አይለጠፍበትም። ተዘጋጁ፣ ጳጉሜ ፩ እየጾምን፣ እየጸለይንም፣ ማዕተባችንንም አጥብቀን እናስራለን። የአንገት ማዕተብ የሌላችሁ ከወዲሁ ግዙ፣ አስባርካችሁም እሰሩም። አንገታችሁ ባዶ አይሁን።

•••
ጳጉሜ ፪ ፥ የክብረ ክህነት ቀን ነው።

… ለንስሐ አባቶቻችን፣ ለካህናት አባቶቻችን፣ ፍቅራችንን፣ አክብሮታችንን የምንገልጽበት ዕለት ነው። እንኳን አደረሳችሁ የምንልበት፣ ቡራኬ የምንቀበልበት፣ ለበዓሉም ለአባቶቻችን ስጦታ የምንሰጥበት፣ ዕለትም ነው። እኔም አደርገዋለሁ። እናንተም አድርጉት። ተዘጋጁ።

•••
ጳጉሜ ፫፥ የፊደል ገበታ ቀን።

… አከተመ የዚያለት ፌስቡክ በኢትዮጵያ ፊደላት ሲያሸበርቅ ይውላል። የዚያን ዕለት ልብሱ ሁሉ የፊደል ገበታ ነው የሚሆነው። በዓለሙ ሁሉ ስንነበብ እንውላለን። ፊደላችን የፌስቡክን ግድግዳ  አጥለቅልቆት ይውላል።

•••
ጳጉሜን ፬ ፥ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀን።

… ይሄ ምንም ማብራሪያም ዝርዝርም አያስፈልገውም። በዚህ ዕለት ፌስቡክ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ የነፃነት ሰንደቅ ዓላማና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፎቶ አሸብርቆ የሚውልበት ቀን ነው ማለት ነው።

•••
ጳጉሜ ፭ ፥ ከሱሶች ሁሉ የመላቀቂያና፣ የመገላገያ ለአቅመ ደካሞችም የሥጦታ መስጫ ቀን እናደርገዋለን። እነ ሲጋራ በአደባባይ ይረገጣሉ። አልኮል፣ ጫት፣ ሺሻና ሀሺሽም ይወገዳሉ፣ ይረገማሉ። ከዝሙት እንሸሻለን። በአዲስ መንፈስ አዲሱን ዘመን ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ሰማዕታትን፣ እንቀበለዋለን፣ እንቀላቀለዋለንም። ታዲያ እኛ ደስስ ሲለን ሌላ የሚከፋው እንዳይኖር ጉረቤቶቻችንን በዓሉን አዲሱንም ዓመት በደስታ ይቀበሉ ዘንድ ያለንን የምናካፍልበት ዕለትም ነው። ቢያንስ ቅቤ፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ ዶሮና እንቁላል እናበረክትላቸዋለን።

•••
ሰምታችኋል ጓደኞቼ ተዘጋጁ። ደግሞም እናደርገዋለን። አባቴ ይሙት እናደርገዋለን። ይሄን መልእክት የጻፍኩት ለጓደኞቼ መሆኑ ይሰመርበት። መንገደኞችን አይመለከትም። አከተመ።

💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
✞ ጎሳዐ ልብየ

ጎሳዐ ልብየ ቃለ ሰናየ/2/


እንደ ዳዊት ኧኸ
በማህሌቱ ኧኸ
በታቦቱ ኧኸ
በፅዩን ፊት ኧኸ
በጎ አወጣ ኧኸ
ልቦናዬ ኧኸ
ክብር ውዳሴ ኧኸ
ለጌታዬ ኧኸ

/አዝ =====

የተሰዋ ኧኸ
በመስቀል ኧኸ
ንፁሁ ሆነ ኧኸ
አማኑኤል ኧኸ
በቋንቋና ኧኸ
በወገን ኧኸ
የማረከ ኧኸ
አለሙን ኧኸ

/አዝ =====

ቅዳሴ ሀ ኧኸ
ለማርያም ኧኸ
ዋዬድን ኧኸ
ዋይምንግን ኧኸ
እመ ንጉስ ኧኸ
ከድንግል ክብር ኧኸ
ሳላስረዝም ኧኸ
በማሳጠር ኧኸ

/አዝ =====

ንሴብህ ፀጋኪ አምላክን ዘወለድኪ/2/


ንጉስን ኧኸ
ዘወለድኪ ኧኸ
አምላክን ኧኸ
ዘወለድኪ ኧኸ
መድሃኒን ኧኸ
ዘወለድኪ ኧኸ

/አዝ =====

ድንግልና ኧኸ
እናትነት ኧኸ
አስተባብለሽ ኧኸ
ይዘሽ በእውነት ኧኸ
ወለድሽው ኧኸ
በግርግሙ ኧኸ
ቤዛ ሊሆን ኧኸ
ለአለሙ ኧኸ

/አዝ =====

እንዲሁ እንዳለን እንዳለን አምላክ ይባርከን/2/

ይባርከን ኧኸ/2/
ለአለም ሰላም ኧኸ
የሚሰጠው ኧኸ
ሞትን በህይወት ኧኸ
የቀየረው ኧኸ
ደጉን ዘመን ኧኸ
ያሳየን ኧኸ
ከአመት አመት ኧኸ
አይለየን ኧኸ

እንዲሁ እንዳለን እንዳለን ድንግል ትባርከን/2/

ትባርከን ኧኸ/2/
የሊባኖስ ኧኸ
ውብ ሙሽራ ኧኸ
አትለይን ኧኸ
ከኛ ጋራ ኧኸ
ተመላለሽ ኧኸ
በጓዳችን ኧኸ
እንዲሞላ ኧኸ
ማድጋችን ኧኸ

እንዲሁ እንዳለን እንዳለን ያሬድ ይባርከን/2/

ይባርከን ኧኸ/2/
መዙመረኛው ኧኸ
ቅዱሱ ሰው ኧኸ
መርድ ቅኔ ኧኸ
የሚያርሰው ኧኸ
ደጉ ካህን ኧኸ
ይሙላን ዝና ኧኸ
ውዳሴአችን ኧኸ
እንዲሰማ አኸ
ይባርከን ኧኸ/4/

#ጷግሜ_
#ከኑ_እናመስግን

💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
የተወደደ ቀን

የተወደደ ቀን የተወደደ አመት
ወደ አባቴ መቅደስ የተመለስኩበት
አንባር ቀለበትን የተሸለምኩበት
የተወደደ አመት

አምሽቶ የመጣ አይገባም አትበሉ 2
አባክኖ የመጣ አይገባም አትበሉ 2
ፍቅር ስለሆነ እግዚአብሔር ለሁሉ 2
ልጅ ቤቱን ይወርሳል እንደተስፋ ቃሉ 2

ከናዝሬት መልካም ሰው አይወጣም እያሉ 2
ፊሊጶስ ናትናኤል ይነጋገራሉ 2
አድጎታልና ውሀውን ወይን 2
እኔን ለውጦኛል ወስዶታል ልቤን 2

እኔነኝ አላማው እኔ ነኝ ሀሳቡ 2
አባቴ ደግነው የሚራራ ልቡ 2
ዘጠና ዘጠኙ ታምነውት እያለ 2
አንዱን ይፈልጋል ወዴት ነው እያለ 2

ሁሉን አይቻለው ሁሉን መርምሬአለው 2
አለም ካንተ ሌላ እንደሌለ አውቃለው 2
እንደማይለወጥ አባትነትህ ወዳጅነትህ 2
ጠፍቼ ስመጣ አየሁት ልጅህን 2

#ጷግሜ_
#ከኑ_እናመስግን


💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
ለአዲስ አመት አዲስ ለchannel ና group አርማ ወይም logo
ማሰራት የምትፈልጉ ቻናላችንን ብቻ ጆይን በማድረግ በነፃለማሰራት

channel፦ @nu_enamasgin
inbox፦ @logaw94
2024/05/16 09:02:59
Back to Top
HTML Embed Code: