​​🌼 አበባዮሽ 🌼

እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(2)
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ጌቶች አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(2)
ዘመን መጣ ብለን

አበባዮሽ ለምለም(2)
ባልንጀሮቼ ለምለም
ግቡ በተራ ለምለም
በእግዚአብሔር መቅደስ ለምለም
በዚያች ተራራ ለምለም
እንድታደንቁ ለምለም
የአምላክን ሥራ ለምለም
ህይወት ያገኛል ለምለም
እርሱን የጠራ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም (2)
ክረምት አለፈ ለምለም
ጨለማው ጠፋ ለምለም
የመስቀሉ ቃል ለምለም
ሆነልን ደስታ ለምለም
እናገልግለው ለምለም
ቤቱ ገብተን ለምለም
ትንሽ ትልቁ ለምለም
ተሰልፈን ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ያንን ኩነኔ ለምለም
ዘመነ ፍዳ ለምለም
የሞቱ በራፍ ለምለም
ያ ምድረበዳ ለምለም
ልክ አንደ ክረምት ለምለም
ሄደ ተገፎ ለምለም
ፀሐይ ወጣልን ለምለም
ጨለማው አልፎ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ይኸው መስከረም ለምለም
ይኸው ፀሐይ ለምለም
ንጉሡ ወርዶ ለምለም
ከላይ ሰማይ ለምለም
አውደ ዓመት ሆነ ለምለም
ደስታ ሰላም ለምለም
ፍቅር ሲገለጥ ለምለም
በአርያም ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ይኸው አበባ ለምለም
ለምለም ቄጤማ ለምለም
አዲሱ ዘመን ለምለም
አምጥቷልና ለምለም
በሩን ክፈቱ ለምለም
መኳንንቶቹ ለምለም
የክብር ንጉሥ ለምለም
ይግባ ቤታችሁ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(2)

አበባዮሽ ለምለም(2)
ቤታችሁ ይሙላ ለምለም
ሰላም ደስታ ለምለም
ሰጥቷችሁ እርሱ ለምለም
የሁሉ ጌታ ለምለም
ከዘመን ዘመን ለምለም
ያሸጋግራችሁ ለምለም
የሽበትን ዘር ለምለም
ይሸልማችሁ ለምለም

አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ

ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ

አብዬ ኧኸ ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰዎት ብዬ

ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው

💚@nu_enamasgin 💚
💛@nu_enamasgin 💛
❤️@nu_enamasgin ❤️
ምን ሰማህ ዩሐንስ

ምን ሰማ ዩሀንስ በማጸን ሳለህ/2/
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ/2/
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ/2/
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ/2/
አዝ.........
ከተፈጥሮ በላይ ያስገደህ ክብር
እንዴት ቢገባው ነው የእናታችን ፍቅር/2/
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ/2/
አዝ......
በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት/2/
እንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ/2/
አዝ..........
ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍፁም/2/
ከማህፀን ሳለ ተመርጦ ከጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ/2/

💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
ስምኪ ጥዑም

ስምኪ ጥዑም ስምኪ ጥዑም/2/
የአምላክ እናት ማርያም " " "
ወለተ ሃና ወኢያቄም " " "
በበረሃ የወደቁ " " "
ስምሽንም የሰነቁ " " "
ማርያም ማርያም እያሉሽ " " "
ይጠግባሉ በስምሽ " " "
ተማፅኜ በዕንተ ስሟ " " "
አፌ ቅኔን እያሰማ " " "
ተመርጠሻል በአምላካችን " " "
ኪዳነ ምህረት እናታችን " " "
ቅድስት ሀና ደስ ይበልሽ " " "
ሊባኖስ ላይ ፀሀይ ወለድሽ " " "
ቅዱሳንን ያከበረ " " "
አጋነንትን ያሳፈረ " " "
ስምሽ ጣዕም ወይነ ቃና " " "
ላመስግንሽ በበገና " " "
አዝ-----
ስምከ ልዑል ስምከ ልዑል/2/
የበረንዳው አማኑኤል " "
የላፍቶ ሚካኤል " "
የጎፋው ገብርኤል " "
የመርካቶ ራጉኤል " "
የሸጎሌው ሩፋኤል " "
የካሳንቺስ ዑራኤል " "
አዝ-----
ስምከ ቅዱስ ስምከ ቅዱስ/2/
የአራዳው ጊዩርጊስ " "
የጎፋው መርቆሬዎስ " "
አባታችን ፊሊጶስ " "
አባታችን እስትንፋስ " "
አባታችን አማኑኤል " "
አዝ-----
ስምከ አበባ ስምከ አበባ/2/
ሚካኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ገብርኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ዑራኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ሩፋኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ራጉኤል ሆይ ቤቴ ግባ " "
ዑራኤል ሆይ ቤቴ ግባ "

💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from New string art and gift
ለድርጅቶ ወይም ለሆቴል /ለሬስቶራንት በፈለጉት መጠን የፈለጉትን ሎጎ እንሰራለን
For additional information
0925878995
0993507391
በ inbox እራሱ ትዕዛዝ እንቀበላለን
@Worrylessnes
@Worrylessnes
Please share our channel
@new_string_art10
አማኑኤል አንተ ነህ

አማኑኤል አንተ ነህ ገመናዬን ሸፋኝ
አዶናይ አንተ ነህ ገመናዬን ሸፋኝ
እንዳንተ አላየሁም ክፉ ቀን ያወጣኝ 2
እኔስ አላየሁም እንዳንተ የረዳኝ
ገመናዬን ሸፋኝ


ወገን ዘመድ ጠልቶኝ ወጥቼ ከሀገር
ደም እየፈሰሰኝ በህመም ስቸገር
የአብርሀም አምላክ ክርስቶስ መጣልኝ
ልብሱን ብዳስሰው ደሜን አቆመልኝ
ገመናዬን ሸፋኝ


ዝሙት ስካር ዘፈን ህይወቴን አስሮት
በህጋቸው ያዙኝ እንድቀበል ሞት
የሁሉንም ኃጢአት አንተ ገለጥክና
ልጅህን አዳንከኝ ልቤም በአንተ ፀና
ገመናዬን ሸፋኝ


ጅራፍ የሚገባኝ በርባን እኔ ሳለሁ
የሰው ደም ያፈሰስኩ ባይኖቼ እያይሁ
ጌታ ተሰቃየህ እኔ ተፈትቼ
ላመልክህ መራጥኩኝ ፍቅርህን አይቼ
ገመናዬን ሸፋኝ

@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጽጌ ፆም በሰላም አደረሳቹ አደርሰን!!!
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወርሃ ጽጌ ከመስከርም 26 እስከ ህዳር6
#አዘክሪ_ድንግል

አዘክሪ ድንግል አዘክሪ 
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ 
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን /2/ 

ካንቺ መወለዱን አዘክሪ 
በቤተልሔም አዘክሪ 
በጨርቅ መጠቅለሉን አዘክሪ 
መኝታው ግርግም አዘክሪ 
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን 

በዚያ በብርድ ወራት አዘክሪ 
የገበሩለትን አዘክሪ 
የአድግና የላም አዘክሪ 
እስትንፋሣቸውን አዘክሪ 
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን 

በግብጽ በረሃ አዘክሪ 
መሠደድሽን አዘክሪ 
የአሸዋውን ግለት አዘክሪ 
ርሃቡና ጥሙን አዘክሪ 
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን 

በመቃብሩ ዘንድ አዘክሪ 
ባነባሽው እንባ አዘክሪ 
አሳስቢ ድንግል ሆይ አዘክሪ 
ገነት እንድንገባ አዘክሪ 
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን

መልካም የፅጌ ፆም💚

@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
እመብርሃን መመኪያችን

እመብርሃን መመኪያችን/2/
የአዳም ተስፋ አለኝታችን
እመብርሃን መመኪያችን
አዝ-----
እመብርሃን የአባቶቻችን
እመብርሃን ቃና ለዛቸው
እመብርሀን በችግር ጊዜ
እመብርሀን መንገድ መሪያቸው
እመብርሃን ምን ብዬ ልጥራሽ
እመብርሃን ላወድስሽ
እመብርሃን የምግባር ደሀ
እመብርሃን ባዶ ልጅሽ
አዝ-----
እመብርሃን የቅዱሳኑ
እመብርሃን ጣዕመ ዜማቸው
እመብርሃን አንቺ ነሽና
እመብርሃን ውብ ድርሰታቸው
እመብርሃን የኛ ስጦታ
እመብርሃን የድል አክሊል
እመብርሃን ባማላጅነት
እመብርሃን ለታመነብሽ
አዝ-----
እመብርሀን የይስሀቅ መዓዛ
እመብርሃን በፍኖተ ሎዛ
እመብርሃን የያዕቆብ መሠላል
እመብርሃን የአቤል የዋኅት
እመብርሃን የዕሴ ቸርነት
እመብርሃን የኢያሱ ሐውልት
እመብርሃን የሕይወት ውሃ
እመብርሃን የሳሙኤል ዘይት
እመብርሃን ርግበ ሠናይት
እመብርሃን ንግሥተ ሠማይ
አዝ-----
እመብርሃን መልካሟ ርግብ
እመብርሃን የኖሕ መልክቱ
እመብርሃን የኅጥአን ተስፋ
እመብርሃን የልብ ብርታቱ
እመብርሃን ምስራቻችን
እመብርሃን ውስጣችን ያለሽ
እመብርሃን በምድር በሰማይ
እመብርሃን አምሳያም የለሽ

መልካም የፅጌ ፆም💚

💚@nu_enamasgin💚
💛@nu_enamasgin💛
@nu_enamasgin
እንኳን
አደረሳችሁ
ለእናታችን ለቅድስት ባዓታ
ማርያም
(፫)3

💛መልካም ቀን💛
9⃣2⃣.ደሊላ ለምን ሶምሶንን ለፍልስጤማውያን መኳንንት አሳልፋ ሰጠችው ?
Anonymous Quiz
14%
⚪️.ስለምትጠላው
36%
⚫️.በገንዘብ ተታላ
40%
🔴.በገንዘብ ተደራድራ
10%
🔵.መልስ የለም
Forwarded from EMA FIKER
ይህን ሼር ያላደረገ ሰው እንደ መስቀሉ ጠላቶች ነው ምቆጥረው
ስለ ቤተክርስቲያናችን ስንል ስለ መስቀሉ ስንል እንዋጋለን
👇👇👇👇👇👇👇

ፉክክሩ Digitized ሆኗል
መስቀል አደባባይን ጎግል ማፕ ላይ እየገቡ ኢድ አደባባይ እያሉ ኢዲት እያደረጉት ነው። ይህ ደግሞ የአንድ ሰው ኢዲት ብቻ ሳይሆን ሙስሊሞች እየተረባረቡ ኢዲት እያደረጉ ስለሆነ ጎግል መስቀል አደባባይን ''መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ ብሎ ቀይሮታል።
ኦርቶዶክሳወያን መበሳጨት አያስፈልግም ነገሩ ቀላል ነው ሁላችንም እንረባረብና ኢዲት ያደረጉትን እኛም ኢዲት አድርገን ''ወይም ኢድ አደባባይ'' የሚለውን እናጥፋው። እንዲያውም ''Land mark'' የሚለው ላይ ባለቤቱ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስለሆነች ''Orthodox church'' የሚል እንጨምርበታለን።
በቀላሉ አሻራዎን ያሳርፉ ከቤ/ክ ጎን ይቁሙ ። ይህንን ለማድረግ ስልኮት ላይ ጎግል ማፕ (Google map) ይክፈቱ እና ደረጃ በደረጃ ያዘጋጀሁትን አጭር የ Screen shoot instruction ይመልከቱ።
N.B ይህንን ለማድረግ የGmail account (email) login info ከጠየቀዎ User name እና password ያስገቡ
ከዛም:
1. Google Map Application ይክፈቱ
2. Search Bar ላይ ሄደውMeskel square ብለው ይጻፉ
እና Meskele Square, Addis Ababaን ይምረጡ
3. ቀዩን የ ፒን(📌) ምልክት ይጫኑ
4. ከመጡት አማራጮች ውስጥ Sugest Edit የሚለውን ይምረጡ
5. Change Name or other details ይጫኑ
6. Meskel Square ከሚለው በታች በአማረኛ የተጻፈውን
''መስቀል አደባባይ ወይም ኢድ አደባባይ'' የሚለውን ይንኩ እና ''ወይም ኢድ አደባባይ የሚለውን'' ያጥፉ እና መስቀል አደባባይን የሚለውን ብቻ ያስቀሩ
7. Historical Land mark ላይ የሚለው ላይ ይግቡ (ባለቤቱ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ስለሆነች)
8. ከአማራጮች ውስጥ Religion የሚለውን ይንኩ
9. ''search more category'' የሚለው መፈለጊያ ባር ላይ Orthodox church የሚል ይጻፉ እና Orthodox church የሚለውን አማራጭ ይጫኑ
10. መጨረሻ ላይ ዝርዝሩ ቼክ ያድርጉ
ከላይ በእንግሊዘኛ : Meskel Square
በአማረኛ : መስቀል አደባባይ
Category : Orthodox church
ከዛም ከአናቱ ላይ ያለችውን የቀስት(የ telegram ወይም Send ምልክት) የምትመስለውን ይጫኑ። እርማትዎ ለጎግል ይደርሰዋል።

ጎግል የእርማቱን (Edit) ብዛታ ተመልክቶ ''ወይም ኢድ አደባባይ የሚለውን ከቀናት በኋላ ያጠፋዋል።

እርሶ ወደነበረበት ''መስቀል አደባባይ'' አርመው (Edit) አድረገው መመለስዎ የቤ/ክ ክብርን መመለስዎ እንደሆነ አይርሱ። ሲጨርሱ ይሄንን ፖስት ለኦርቶዶክሳውያን ያጋሩ!

#መስቀል_አደባባይ
ሰላም የኑ እናመስግን ቤተሰቦች እዴት ቆያችሁ ለትንሽ ግዜ መጥፋታችን ይታወቃል

አሁን በአዲስ ፖስቶች ብቅ ብለናል የምንለቃቸውን ነገሮች ሼር
እና ቻናሉን join በማለት ይተባበሩን

መልካም ቀን

@nu_enamasgin
@nu_enamasgin
Channel photo removed
2024/04/29 17:59:37
Back to Top
HTML Embed Code: