Telegram Web Link
➥ እጂግ ጥሩ ጂምር ነው በርቱ እንበርታ

አል-ሒዳያ ኢስላሚክ የዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት

ጆሃንስበርጎች ዝግጁ‼️
==============

....ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ እና አካባቢው የምትገኙ ወንድም እህቶች በሙሉ

በጉራጌ ዞን ጉመር በታሪካዊ ቦታ እየተገነባ የሚገኘው #አል-ሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ እነሆ ነገ እሮብ October 15 ከመግሪብ በኋላ በጆሃንስበርግ ከተማ #በኢሜጅ_ላይፍ_ስታይል አዳራሽ

ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ስላለ በጆበርግ እና አካባቢው ነዋሪ የሆናችሁ ወንድም እህቶች በሰዓቱ ተገኝታችሁ  ኩ'ፍርን በዒልም ለመታገል እና ኢስላምን የሚኖር ትውልድ ለመፍጠር በተቋቋመው በዚህ ታላቅ #ኢስላማዊ_ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት አሻራችሁን እንድታኖሩ ተጋብዛችኋል

በደሉንም ግፉንም ጭቆናውንም ችለን እየጠነከርን መጓዝ በአሏህ እገዛ #አይበገሬነትና አሸናፊነት መለያችን ሆኖ ይቀጥል ዘንድ ሁላችንም በጋራ እንትጋ እላለሁ።
👍34
شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
በ➌ቀን ውስጥ ይፍረስ የተባለው መስጂድ ይህ ነው እስኪ ምን ተሰማችሁ እስከመቼስ ነው በዚህ መልኩ የምንቀጥለው⁉️
«ለጊዜው አናፈርስባችሁም ብለዋል‼️

በሶስት ቀናት እናፈርሳለን ካሉ በኋላ
ህዝቡ ቁጣውን ሲገልፅ ለጊዜው ባለበት ይቆይ ማለት አዘናግቶ ለማፍረስ ታቅዷል ማለት ነው ልብ በሉ ⁉️

እንደዚህ አይነት የንቀትና የፌዝ የስላቅና የኩራት ውሳኔስ #ከመንግስት አካል ይጠበቃል ወይ⁉️

«የአመራር እቅዳችሁና የአፈፃፀም ታክቲካችሁ እንደት ነው..እ!?

ግራ ግብት የሚለኝ ነገር «ለጊዜው አናፈርሰውም። ማለት⁉️»
እና ቀን ጠብቃችሁ ማታ በጨለማ ተደብቃችሁ ልታፈርሱት ነው⁉️

የህዝቡ ቁጣና ዝምታ የስሜት ከፍታና ዝቅታ እየተለካ እነርሱ እንዳሻቸው ON/OFF የሚያደርጉን መሆን የለብንም።

አያችሁ ጊዜያዊ ጫጫታ እንደሆነ ተረድተዋል‼️
አስተውሉ ለተወሰነ ቀን ጩኸን ፀጥ እንደምንል ገምተዋል‼️

በመሆኑም እኛ ሙስሊሞች ቋሚና ዘላቂ መፍትሄ እንሻለን ብለን ወጥ አቋም መያዝ አለብን።

እስከ መቼ ድረስ ስለ መስጅድ ፈረሳ፣ ሒጃብና ሶላት እያወራን እንኖራለን⁉️ እስከዛሬ ያፈረሱትንም ይገንቡ፣
ወደፊትም ማፍረሳቸውን ያቁሙ የሚል መርህ ያለውና የፀና አቋም አስቀምጠን እንታገላቸው

«ለጊዜው አናፈርሰውም»
ማለትስ ምን ይሆን በመንግስተኛ ቋንቋ..እንዴ..‼️


ቀልዱን ተውትና ካሁን በኋላ የማይፈርስ መሆኑን ህጋዊ ማረጋገጫ ማግኘት ያስፈልጋል !

ለመሆኑ እስከ ዛሬ ያፈረሳችሁትንስ ምን ሰራችሁበት⁉️

ሸገር በሚባል ከተማ ውስጥ ስንት መስጂድ ነው የፈረሰው ቦታውን ምን ሰራችሁበት⁉️
አልበዛም ወይ⁉️
ለልማት ብላችሁ አፍርሳችሁ ባዶ ሜዳ ያደረጋችሁት እንዲሁም ሌላም ነገር የገነባችሁበት ብዙ ነገሮች አሉ።
ትክክል አይደለም ‼️

ይህ አይነቱ ነገር ሀገር ያፈርሳልና እባካችሁ‼️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍37
የሸገር ሲቲ

ያለምንም ማሽሞንሞንና ማንቆለጳጰስ እየተፈፀመ ያለው ግፍና መከራ የሙስሊሙን አቅም መፈታተንና ተከታታይ ትንኮሳ ጊዜ እየጠበቀ መስጂድ የማፍረስ ዘመቻ እዚህ ላይ በቃህ ተብሎ ሊያከትም ይገባል።

ከዚህም ባሻገር በምትኩ እስካሁን በማናለብኝነትና በዘግናኝ ሁኔታ ያፈረሳቸውን መስጂዶች በጥራት እንዲገነባ መገደድ አለበት።

ለዚህ ደግሙ ከመጂሊስ አመራሮች የጠነከረ አቋም ከመያዝ ባሻገር የህዝበ-ሙስሊሙ ያላሰለሰ ጥረት ሊኖር ይገባል ባይ ነኝ ።

በታቀደና በተጠና ሴራ ነው መከራ እያየን ያለነው ወገን እንንቃ እሽ⁉️

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍61
🔻ምዝገባ ላይ ነን🔺

መርከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዓሪ የቁርኣን ሒፍዝ ማዕከል ለ2018 ዓ.ል  የትምህርት ዘመን በ አዳሪና  በተመላላሽ መርኃግብር  ተማሪዎችን ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ  በምዝገባ ላይ ይገኛል።

የአዳሪ መርኃግብር
ጾታ፡  ለሁለቱም (ለወንድም ለሴትም)
እድሜ: ለወንድ ከ10 - 25 ዓመት
              ለሴት  ከ 10 አመት በላይ

የሚሰጥበት አድራሻ: አንፎ ድልድይ በሚገኘው ዋናው ማዕከል።

የተመላላሽ መርኃግብር፡
ፆታ: ለሁለቱም
እድሜ: ከ 4 አመት በላይ ለሁሉም የእድሜ ክልል 
የሚሰጥበት አድራሻም: በሁሉም ቅርንጫፎች

ለመመዝገብና ለበለጠ መረጃ፡

➡️አንፎ ቅርጫፍ፡
+251913939993 /+251928844757
➡️ቦሌ ቅርንጫፍ፡
+251911119260 /+251930547776

✈️የቴሌግራም አድራሻ
https://www.tg-me.com/merkezabumussa1
https://www.tg-me.com/merkezabumussa1
👍10
«➏»هدية المسلم الجديد"
🎙አቡ-ፋሩቅ حفظه الله
هدية المسلم الجديد

👉ክፍል=➏

«የመጨረሻው ደርስ ነው።»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍19
ከውስጤ አውጥቼ ልናገር የምፈልገው ብዙ ነገር አለኝ ግን .....I choose to remain silent in my pain so as not to cause more suffering to my humble people.

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍63
ናፍቀኸኝ ነበር⁉️

አባቴን
ምን ላድርግልህ አልኩት⁉️
ልጄ
ድምፅህ አይራቀኝ
እየጠፋህ አታስጨንቀኝ
......አለኝ...አባትነት ...ከባድ ሚዛን ነው።

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍199
«ለአባቴ»

ልጅ የመሆን የክብር ማማ አባ የምልህ ኩራቴ፡
በድቅድቅ ጨለማ መሐል የምትፈነጥቅ መብራቴ፡
በጥም በረሃብ ስቀጣ የምታጠግበኝ ራቴ፡
በቃላት የማትገለፅ ሰንደቄ ውብ ቁጥራቴ፡

አንተ ነህ የኔ ማንነት፤
ድምፅህ ነው ደካማ ጎኔ፡
ልጄ ብለህ ስትጠራኝ፤
እንባ ያቀራል አይኔ፡
አባቴ አንተኮ ማለት፤
ውብ አርማዬ ነህ ለኔ፡

በእልፍ ቦታ ተከፍለህ
በእኔ ሐሣብ የጭንቀት ግዞት፡
ነገዬን ልቦናህ አስልቶ፤
መንፈስህ ኒሻኔን ይዞት፡
መቀመቅ ወርደህ በእሳት፤
ነፍስህን ጠባሳ ወርሶት
አሁንም እንባህ ለእኔ ነው ፥
ችግሬ ሆድክን አብሶት፡

ጋሬጣ አሜኬላዬ፤
በእግሮችህ ተሰንቅረዋል፡
ጫንቃና ብርቱ ክንዶችህ፤
በሸክሜ እጅግ ዝለዋል፡
ዋጋህን በስሌት ተመን፤
አስቤ አልደርስበትም፡
አንድ ነብስ በቂው አይደለም፤
ሦስት አራት አያንስበትም፡

አባቴ....

ለካስ አባት
በእናት አንጀት ላይ
ኮስታራ ገፅ አሣይቶ፡
የጋተውን መራራ ሐሞት፤
በሳቅ ግርዶሹ አቆይቶ፡
በሰው ፊት ጀነን ብሎ፤
ተቆጥቶ ገልምጦ ዝቶ፡
የብቻውን የዕንባ ያፈሳል፤
ለቤተሰብ ለልጅ አብዝቶ፡

አባቴ

ኑሮን በሀይሉ እየገፋ መከራን በክንዱ ትግል፡
ልጅ ለማሳደግ ሲታትር ስቃይን ያለ ግልግል፡
ብቻውን በፅናት ቆሞ የገነባውን ብተሰብ፡
ምን ካሣ ይመጥነዋል ምን ይበቃዋል ቢታሰብ፡

....አባቴ....

አውላላ በረሃ መሐል፤
ለምለም መስክ የምታሳየኝ፡
ጢንጫ ካልኩት ህይወቴ ላይ፡
ወዛም ምንጭ የምታቆየኝ።

የፈገግታ የደስታ ሱሴ፤
የእዳ መዝገቤ ሽረት፡
ድክመቴን የምረሳብህ፤
የህይወት ዘመኔ ጂረት፡
አይኖችህ ሳይከደኑ፤
ትንፋሽህ በርዶ ሳይጠፋ፡
ለልጅህ ዋጋ የከፈልክ፤
በፍፁም እንዳልከፋ፡

አባቴ መርሀባ በለኝ፤
ጉልበትህ ሳይከዳህ በፊት፡
በአስታጠቀከኝ የወኔ ዝናር፤
ሽንፈትን ላድርገው ወንፊት፡
መልካም ያልሁትን ሁሉ፤
ላቅርበው አባቴ አንተ ፊት።

አንተን አዝየህ ልዙር
በየትም እንዳታመልጠኝ፡
አውቃለሁ አይንህን ሳየው
ጀግንነት እንደሚሰጠኝ
የኔ አባት አብሬህ ልሁን፤
በአንድ ቃል ፈቃድክን ስጠኝ⁉️

አሁን ላይ የመድረሴ ምንጭ ፤
ከዚያ ከዚህ መውጣት መግባቴ፡
የውበት የግርማዬ አክሊል፤
መልኬ ነህ ውብ ደም ግባቴ፡
የሁሉን ቦታ የሸፈንክ፤
አንተ ነህ ንጉሴ አባቴ.....፡

ከልጅህ ኑረዲን አል-ዓረብ
እናትም አባትም ለሆንከኝ አሏህ ይጠብቅህ ጋሻዬ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍98
➥እስኪ በትዝታ በሀር እንዋኝ...!?

ልጅነቴ ትዝ ..ሲለኝ..ትውስታዬ

እዚህ ጋር ደግሞ አማዬ ወጣ ስትል
ደረቅ እንጀራ ወይም ዳቦ ነገር
ቆርሰን የምናጣጥማት ነገርስ...እ...

........የሚገርመኝ ደግሞ ጥፍጥናው በወጥ ስንበላ እንኳን እንደዛ አይጣፍጥም።

«በዛው ልክ እንዳታየን ፍጥነታችን»

እስኪ እንደዚህ ያደገ እጁን ያውጣ‼️

መዋሸት አይቻልም ...እያንዳንድሽን አውቃችኋለሁ...ሁልሽም ሰርቀሻል።

ያኔ በልጅነት ውብ ነበረ ሞሰብ
ሁሉም ቤት የሚገኝ ሁሉም ጋ እሚታሰብ፡
መለያችን ነበር እንደ ህብረተሰብ፡

....ኑር..በትዝታ አለም...
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍220
يا من أفزعكم غلاء الذهب ، هل أفزعكم قرب الأجل؟ الدنيا ممرّ، والآخرة مقرّ ، فاعقلوا قبل أن يُغلق الباب!"
👍22
(⓯)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎

     👉ክፍል =⓯

«የነብዩን ቤተሰቦች መውደድ»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍22
🔔 ታላቅ የደዕዋ ጥሪ!

🗓የፊታችን ቅዳሜ ይጠብቁን!
ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ (በኢትዮጵያ ሰዓት) ታላቅ እና ልዩ የደዕዋ ፕሮግራም ይኖራል ኢንሻ-አላህ።

🎙ተጋባዥ እንግዳ፡-የተከበሩ ሸይኽ አኒስ ኢብኑ ሷሊሕ አል-ያፊዒይ (አላህ ይጠብቃቸው)

📚በየመን መርከዝ አል-ፊዩሽ አስተማሪ―

💰ዐረብኛ ቋንቋ ለማይችሉ ወንድም እህቶች በሙሉ፣ ፕሮግራሙ ከሙሉ አማርኛ ትርጉም ጋር አብሮ ይቀርባል።

 😂ፕሮግራሙ በቀጥታ የሚተላለፍበት በኡስታዝ ኢብኑ ሙነዎር የቴሌግራም ቻናል ነው፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor

     🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩
🎤 بِشَارَة لِلمُسْلِمِينَ جَمِيعًا!
نُبشِّركم بموعد برنامجٍ دعوي سيُقام – بإذن الله تعالى –
📆 يوم السبت القادم
الساعة الثالثة (3:00) مساءً بتوقيت إثيوبيا

🎙 يُقدِّمه: فضيلة الشيخ أنيس المهندس اليافعي – حفظه الله –
المدرّس في دار الحديث السلفية بالفيوش – اليمن.

🌍 ملاحظة:
سيكون البرنامج مصحوبًا بالترجمة إلى اللغة الأمهرية تسهيلًا للفهم لجميع الإخوة والأخوات

▶️وذلك عبر قناة الأستاذ الفاضل محمد أحمد منور
رابط القناة:
🔗 https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
🔗 https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
📣 ساهم بنشر هذا الإعلان، تكن شريكًا في الأجر
👍17
(⓰)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎

     👉ክፍል =⓰

«በወልዮች ከራማ እናምናለን።»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍18
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰለፍዩ

ምናልባትም በመካከላችን በትንሹም ቢሆን ልንቃረንና ልንነጋገር እንችላለን።

ግን መሀላን በፈቀደው ጌታ እምላለሁ እኔ ህይወትን ካንተ ተለይቸ በፍፁም መኖር አልፈልግም።

በመካከላችን ያሉት ሁሉም ነገሮች በእንቅፋቶች የተሞሉ ቢሆኑም እንኳን እኔነቴ ካንተ እንድነጠል አልሻም።

በድካሜም በብሶቴም በደስታየም በስኬቴም ጊዜ እፈልግሀለሁ።

ከአንተ የሚመጣን ምንም ነገር መቀበልና በአንተ ላይ የሚመጣን ሁሉ መጋፈጥ እፈልጋለሁ።

«በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ሁን ሰለፍይ ከሆንክ #እወድሀለሁ ይህ የማይናወጥ አቋሜ ነው።»

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍62
«በነፈሰበት አትንፈስ»

.......ሐጂ ዑመር ገነቴ...✍️

በመርህህ ላይ ፅና ሲጮሁ አትጩህ የሰወች ጫጫታ ጎርፍ ሆኖ አይውሰድህ«አይደለም ውስን የሚዲያ ሰው የአለም ህዝብ ከሐቅ ቢቃረን ብቻህን ሆነህ በሐቅ ላይ ፅና የሚል የፀና ህግ እንዳለህ አትርሳ እንጂ»ታመዋል!? እና ምን ይጠበስ⁉️

ሀጅ ኡመር ገነቴ በጠና ታመዋል የሚል ዜና በማህበራዊ ሚድያ ሲዘዋወር ተመለልክቻለሁ። ወደ ቱርክ ሀገርም ለከፍተኛ ህክምና እንደሄዱም ሰማሁ ልበል⁉️

➥ሀጅ ኡመር ገነቴን እኔ በግሌ እርሳቸው በሚያራምዱት አቋም ላይ ተመርኩዠ ለአሏህ ብየ እንደምጠላቸው በግልፅ መናገር እፈልጋለሁ። ሰውየው አሏህ ይምራቸውና ከሙስሊም ይልቅ ለማን እንደሚቀርቡ ግልፅ ነው...ይልቅ ከቀረባችኋቸው መሞታቸው ስለማይቀር ወደ አሏህ እንድመለሱ ምከሯቸው።
የሐቅ ሰወችን ለማጥፋት #ካ*ፊሮች ናቸው ከማለት አልፈው #ለነአባይ_ፀሀዬ እየተላላኩ ምን ሲያደርጉ እንደነበር ነግረውናል።

ከዚህ የከፋው ደግሞ ቁቡርይና የሽርክ ተግባርን የሚያስፋፉ ግዙፍ ሽማግሌ ናቸውና #ማሽቃበጡን ትታችሁ በተውሒድ ላይ ሆነው እንድሞቱ ንገሯቸው ለማለት እወዳለሁ።

«እኔ በበኩሌ ከእርሳቸው የግል እይታ እና ስህተት አልፎ ህዝበ ሙስሊሙን ወደ ሽርክ ጨለማ ለመመለስ የሚያደርጉት ድርጊት ለአሏህ ብየ እንድጠላቸው አድርጎኛል።»

ነገር ግን ሀጅ ሙፍቲ ኡመር ገነቴን አሏህ ከነበሩበት የሽርክ፣የቢድዓ፣የተሶዉፍ መንገድ አውጥቶ ትክክለኛ የነብያቶችን መንገድ ተከትለው ሱናን ጨብጠው ሙሉ ጤናቸው ተመልሶ የአለማት ጌታ የሆነውን ብቸኛ በሀቅ ተመላኪ የሆነውን አሏህ ሱብሀነሁ ወተዐላን እንድገናኙ እመኝላቸዋለሁ ኸላስ‼️

➥ከአካላዊ ጤንነት በላይ የአቂዳህ ጤንነት ሊያሳስብህ የግድ ይላል ሀጅዋ ‼️

....ኑር
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍160
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«ይህ ነው የኛ ዑመር »



«ፋሩቅ»

የመካን ሙሽሪኮች እያንሸረደደ፡
አመፀኛን በሰይፍ እየቀረደደ፡
ጀግንነቱ እንደ ጎርፍ ቦይ እየቀደደ፡
በአሏህ ተመክቶ ድልን የለመደ፡
የጦር ሜዳ ጀግና ወታደር አርበኛ፡
ወድህ የህግ ሰው ፍትሀዊ ዳኛ፡
እንኳንስ ተግሳፁ ፈውስ ነው ብትሩ፡
መመጠን ይችላል ቁርዓን ነው ሜትሩ፡

ሐሳቡን ጌታችን የተቀበለለት፡
አነጣጥሮ ተኳሽ ይህ ነው ዑመር ማለት፡
የጠላትን ምሽግ ተራራ እየናደ፡
የገነቡትን ፅንፍ እየገረመደ፡
ከመካ ፍልስጤን የተረማመደ፡
ድል እያደረገ የተንጎራደደ፡

የጀግንነት አርማ የነፃነት ሰንደቅ፡
በየደረሰበት ለሐቅ የሚዋደቅ፡
ጌታውን በመፍራት አይኑ የሚያለቅሰው፡
የፍትህ አርበኛ ንፁህ የሰላም ሰው፡
ታሪኩ በሙሉ ሆድ የሚያላውሰው፡

የተራመደበት ምድሩ ቢመረመር፡
አይጠፋም አሻራው ተባዝቶ ቢደመር፡
ያልሰራው የለውም ሁሉም ይላል ዑመር፡
ጠላት ስሙን ጠርቶ የሚይዘው ቁንጣን፡
እሱን እየፈራ የሚሸሸው ሰይጣን፡
ምነው የሱ ልጆች ዛሬ ሞራል አጣን⁉️

ዛሬም ስሙን ይዘን እጂግ እንኮራለን፡
ዑመር ባልን ጊዜ እንከበራለን፡
እጂግ ጠቢብ ነበር አስተዋይ ነው በሩቅ፡
ጀግና ነው አባቴ ያ ዑመሩል ፋሩቅ፡
....ኑረዲን አል-አረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍85
እኔ እምላችሁ እነዚህ የሚያምሩ #ወፎች የት ገቡ⁉️

እስኪ የምታውቋቸው ስማቸውን ንገሩኝ
.....እኛ «#ድንቢጥ»እንላቸው ነበር!!

አሁን ላይ አይቻቸው አላውቅም
ጥሩ ጥሩው ነገር እየጠፋ ነው ልበል⁉️



በብዛት ጧት በራችን ላይ እና ወፍጮ ቤት አካባቢ ይታዩ ነበር ...የምር ግን የት ገቡ⁉️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍184
2025/10/18 01:35:19
Back to Top
HTML Embed Code: