Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድንቄም ሴኩላሪዝም i የትምህርት ስርአቱ ከሃይማኖታዊ መገለጫዎች መነጠል አለበት እያሉ የሙስሊም ተማሪዎችን የሚያንገላቱ፣ በሙስሊሞች የተከፈቱ ትምህርት ቤቶችን "ልጆች ይሰግዳሉ ወይ?" እያሉ የሚያፋጥጡ አካላት እነዚህ ነገሮች አይታየዋቸውም። ሴኩላሪዝም የሙስሊም ተማሪዎችን ለማሸማቀቅ የሚመዘዝ የምቀኞች ዱላ ነው። ሌላው እንዲሁ ማስመሰል ብቻ ነው።

Ministry of Education Ethiopia የት አለህ?
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍69
«ግ» የሚባል «ዕዝ» እንደመስረታችሁ መች አወቅን⁉️
👍65
«ከጉንዳን ታንሳለህ⁉️»
-----------------------

ጉንዳኖች ሲጓዙ መንገድ ብትዘጋባቸው ከጉዟቸው አይገቱም፤ሌላ መንገድ ፈልገው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡
ከተስፋ መቁረጥ ጋር ፈጽሞ አይተዋወቁም፡፡
‎ጉንዳኖች ለመጪው ጊዜ ይዘጋጃሉ፡፡ በበጋ ወቅት ለክረምት ጊዜ የሚሆናቸውን ቀለብ ያከማቻሉ፡፡ በዝናብ ወቅት ወደ ውጭ ሳይወጡ ክረምቱን ለማሳለፍ  የቻሉትን ያህል ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡

በክረምት ወቅት ነገ በጋ እንደሚመጣ ወይም ብራ እንደሚሆን እርግጠኞች ናቸው፡፡ ክረምቱ ለረዥም ጊዜ እንደማይዘልቅ ያውቃሉ፡፡ በጋውን በብሩህ ተስፋ ይጠብቃሉ፡፡ ጸሃይዋ ብልጭ ስትልም ተግተልትለው ይወጣሉ፡፡

‎ጉንዳኖች ከአካላቸው ክብደት 20 እጥፍ የሚልቅ ነገር መሸከም ይችላሉ፡፡ ፈጣንም ናቸው፡፡ ሁልጊዜ በሥራ ተጠምደው ነው የሚታዩት፤ ምንጊዜም በእንቅስቃሴ ላይ ናቸው፡፡ መሰራት ያለበትን ሁሉ በትጋት ይሰራሉ፡፡
ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነጋቸውም ያስባሉ - መኖሪያቸውን ይገነባሉ፤ቀለባቸውን ይሰንቃሉ፡፡
‎የሰው ልጅ ታዲያ ከጉንዳኖች ህይወት ምን ይማራል⁉️

‎በአሜሪካ የሞቲቬሽናል አባት የሚባለው ጂም ሮን፣ ከጉንዳኖች ለህይወት ስኬት የሚጠቅሙ አራት መመሪያዎችን መቅሰም እንችላለን፤ ይላል፡፡ "የጉንዳኖች ፍልስፍና" ሲልም ሰይሞታል፡፡
👉 አራቱ የስኬት መመሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
❶‎•  ምንጊዜም ተስፋ አትቁረጡ
➋‎•  ሁልጊዜም ለነገ ወይም ለወደፊቱ አስቡ
➌‎•  አዎንታዊ ብሩህ ተስፋ ይኑራችሁ
➍‎•  የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ!!

‎ይህ ለአንተ ነው አይዞህ ጀግናየ ምንም የጨለመ መቸም የማይቀየር ሁሌ የማይሳካልህ ከመሰለህ ተሳስተሀል።
እውነታው በተቃራኔው ነው ተስፋ እንዳትቆርጥ!
👉ተነስ ሞክር።

....የፋሩቅ አባት
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍52
(❶➍)الواجبات المتحتمات
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
አል-ዋጂባት

         ክፍል=❶➍

➋➍:00 ደቂቃ

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍22
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጌታዬ

ሐቅ ላይ አቁመህ አንተ ዘንድ አክብደን፡
እንደ ኔታንያሁ የትም አታዋርደን!

...........አሚን በሉ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍144
(➎❶)الواجبات المتحتمات
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
አል-ዋጂባት

         ክፍል=❶➎

➋➋:38 ደቂቃ

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍10
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንበሳዎቹ ሙስሊሞች ናቸው መሰለኝ እያለ ነው። አሳማዎቹ ባጠገባቸው እየተንጎራደዱ እያለፉ ዞረውም አላዩዋቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍111
👉ወደ ደመራ እየተደናበራችሁ የምቴዱ ሙስሊሞች!!

👉አይመለከትም!!

የደነዘዛችሁ በመቻቻል ቁማር፡
እጂግ የራቃችሁ ኢስላምን ከመማር፡
ለፈጂር ለኢሻ ከቤት የምትተኙ፡
ለሊት ተነስታችሁ #ታቦት የምትሸኙ፡
በማይክ ጠላት ፊት ሁሌ እምትሞኙ፡

በህዝብ አደባባይ ስትሆኑ ራቁት፡
ሽርክና ቢዲዓን መች ነው የምትንቁት፡
እስልምናችሁን መች ነው የምታውቁት⁉️
ኸረ ዘንድሮ እንኳን ክህደትን ልቀቁት⁉️

ኢስላምን ያወቀ ሀቁን የተረዳ፡
ተውሒድን ያጠና የተማረ አቂዳ፡
ፈጂር የሚሰግድ ተነስቶ ማለዳ፡
ካልሆነ በስተቀር ቆዳ ቆረቆንዳ፡

ለማስመሰል ብሎ አያከብርም መስቀል፡
ይህ ከባድ ነውና ኩ*ፋር መቀላቀል፡
በጠላት ተወዶ ዝና ለመሸቀል፡
አይበጂም አለቅጥ ወደ እሳት መንቀልቀል፡

ሙስሊሙ ተጠንቀቅ ፅና በድንበርህ፡
እምነትህ ነውና ሁሌ እሚያስከብርህ፡
የትም አትሽለጥለጥ እውነቱን ልንገርህ⁉️

ከእንጨቶች ጫፍ ላይ ምስሉ እሚንጠለጠል፡
እኛ አምላክ የለንም በእሳት የሚቃጠል፡
የማይነጥፍ መርህ ባለ ውብ መመሪያ፡
የሁለቱም ሀገር ስኬት ማስተማሪያ፡
የመፈጠር ሰበብ ሁሉን መጀመሪያ፡

ከአንድ አምላክ የመጣ በመለክ ታጂቦ፡
መርሁ እሚነበብ በነብያት ቀርቦ፡
የእስልምና መንገድ ብርሀን ነው አቦ፡
ማንም የማይቀርበው እየጠጣ ጃንቦ፡

በጠራ ንፁህ ሀቅ ነው እንጂ እሚመራ፡
ሁሉን ያሸነፈ በሁሉም ምርመራ፡
ሙስሊም ከዒድ ውጭ የለውም ደመራ፡

....ኑር...

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍54
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተረጋጋ በሉት!
---------------
በማያውቀው ገብቶ ነገር ከሚነዳ፡
ተረጋጋ በሉት ይህን ቆረቆንዳ፡

  ..አናጋሪ..አሉ!
Seducing women in English and talking about monotheism are very different things.

የአሏህ አደራ ነው ተውሒድን ማስተማር፡
ጥመት ነው ካዝናችሁ የናንተማ ቁማር፡
ስንት ጉድ መከራ አመጣችሁብን!?
ምነው ግን በአሏህ ሸክም ባቶኑብን⁉️

አንተ አርፈህ በቃል ደረጃ ብቻ«ቁርኣን፣ ቁርኣን» እያልክ በአይንህ ሴቶችን እየጠቀስክ ተቀመጥ።

ምነው ደግሞ ዛሬ በድንገት አፈላህ!?
ማን በሴራ ላከህ ማንስ ምን አበላህ!?
ተቅነዘነዝክብን እንደጠራራ እባብ፡
ወላሒ አያዋጣም የሁኔታህ ድባብ፡

በቅርብ የጀመረው አዲስ የነ ኑዕማን ኻን ሌጋሲ አለ። ወጣቱና ፍንዳታ ሴቶች ወደ ሌላ ታሪክ እንዲሄዱ የሚደረጉበትና በቁርኣን ተፍሲር ስም ሎጂክ የሚጠመቅበት ቦታ አለ።

ጥመትን ከመስበክ ሴቶችን ሰብስቦ፡
ፈላስፋ ከማድረግ ወጣቶችን ስቦ፡
ፋሽን ከመከተል ወንጀልን ከስቦ፡
ምናል በራብ ቢሞት በተውሒድ ተርቦ፡
የነብዩን ሱና ግርማውን ደርቦ፡
ግደለቻችሁ ዝም በሉ! ዝም ካላላችሁ ግን… እንጀራችሁ ብቻ ሳይሆን የሚደርቀው የተሸከማችሁትም ተልዕኮ ጭምር ነው። አትነካኩን!
ተረጋጋ አስተውል አንተ የሰው ብኩን፡
ያንተ አይነቱ ብጥርቅ አያውቀውም ልኩን፡
መገመት አይችልም ድሮም ኢኽዋን መልኩን፡
አሏህን ያምፃል ሲያራግፍ እከኩን፡
አሳ ጎርጓሪ…  እንዳይሆንባችሁ ከአፋችሁ ለምትወጣዋ እያንዳንዷ ቃል ዋጋ እንዳትከፍሉ።
የጀግና ስም ይዘህ የባለ ማሪፋ፡
ሰብሮ የሚጠግን ቀዶ የሚሰፋ፡
አንተ ግን በጥመት ጉራህን ስትነፋ፡
ተውበትን ሳታገኝ ቶሎ እንዳትደፋ፡
ከጀመርከው ስሜት በቶሎ ተላቀቅ፡
ከአሏህ ጋር ጦርነት አይበጂም ተጠንቀቅ!!

...ኑር..
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍165
«ተውሒድ»
---------------
ህዝባችን አዝሎ የሽርክ ክምር፡
ከተውሒድ ውጭ ምን እናስተምር!?

-----------------------------------
🔸ለተውሒድ ሲባል ሰውና አጋንንት ተፈጥሯል።
🔹ለተውሒድ ሲባል ሰማይ ጣራ ሆኖ ምድር ተስተካክሏል፡፡
🔹ለተውሒድ ሲባል ጀነትና እሣት ተፈጥሯል፡፡
➢ለተውሒድ ሲባል ቀንና ለሊት ተፈራርቋል፡፡
➢ለተውሒድ ሲባል ነብያቶች ተልከዋል፡፡
➢ለተውሒድ ሲባል መፀሀፎች ከሰማይ ተወደዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል አማኝና ከሀዲያን ተለይቷል፡፡
🔹ለተውሒድ ሲባል ጣዖታት ተሰባብሯል።
🔹ለተውሒድ ሲባል አውስና ኸዝረጆች ታርቀዋል።
🔹ለተውሒድ ሲባል ጠላቶች ወዳጂ ሆነዋል።
🔹ለተውሒድ ሲባል ወዳጆች ጠላት ሆነዋል።
🔹ለተውሒድ ሲባል አባትና ልጂ ተለያይቷል።
🔹ለተውሒድ ሲባል ሰይፍ ተመዟል፡፡
🔹ለተውሒድ ሲባል ስንቶች ተፈትነዋል፡፡
🔸ለተውሒድ ሲባል ተዐምራቶች ታይተዋል።
🔸ለተውሒድ ሲባል ለነብዩ ሷሊህ ከድንጋይ ግመል መጥታለች።
🔸ለተውሒድ ሲባል የነቢ ሙሣ ብትር ዘንዶ ሆኗል።
🔸ለተውሒድ ሲባል ነቢ ዒሣ ሙታን አስነስቷል።
🔸ለተውሒድ ሲባል ለነቢ ሙሀመድ የተምር ግንድ አልቅሷል።
🔸ለተውሒድ ሲባል ነቢ ሙሀመድ እንስሳትን አናግረዋል።
🔸ለተውሒድ ሲባል ነቢ ሙሀመድ ከጣታቸው ስር ውሀ ፈልቋል።
🔸ለተውሒድ ሲባል ለነቢ ሙሀመድ ጨረቃ ለሁለት ተከፍሎላቸዋል።
🔸ለተውሒድ ሲባል መናገር የማይችሉ ህፃኖች ተነጋግረዋል።
[ነቢ ዒሣ እና የፊርዐውን ጋር የተፋለመችው የባለታሪኳ ህፃን ልጂ]]
🔸ለተውሒድ ሲባል ኢሳ ያለ አባት ተወልዷል፡፡
🔸ለተውሒድ ሲባል ዛፎች ይናገራሉ ።
[አንተ ሙስሊም ና ይህን አይሁድ ግደለው]
🔹ለተውሒድ ሲባል ኢብራሒም እሣት ላይ ተወርውሯል፡፡
🔹ለተውሒድ ሲባል እሣት ትኩሣቱን አቁሟል።
🔹ለተውሒድ ሲባል ኢስማዒል ለዕርድ ቀርቧል፡፡
🔹ለተውሒድ ሲባል ኑህ መርከብ አዘጋጂቷል።
🔹ለተውሒድ ሲባል ከሀዲያን በውሀ ተሰጥመዋል።
🔹ለተውሒድ ሲባል ሙሳ ፊርዐውን ጋር ተፋልሟል።

➢ለተውሒድ ሲባል አንባገነኖች ወድመዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል የሀቅ ሰወች ገነዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል ሙሀመድ ተንከራተዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል ሙሀመድ ተሰቃይተዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል 23 አመት ለፍተዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል አቡበክር ተተክተዋል፡፡
➢ለተውሒድ ሲባል ፋሩቅ ጀግንነት አሣይተዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል ዑስማን በመላዒካ ታፋረዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል አልይ ሰይፍ መዘዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል ሰሀቦች አንድ ሆነዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል ታቢዕዮች ፀንተው ቆመዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል ኢማሙ አህመድ ተቀጥቅጠዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል የተይምያ ልጂ ታስረዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል ሙሀመድ አብደል ወሀብ ተሰድበዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል ዑለማወች ተጨቁነዋል።
➢ለተውሒድ ሲባል ብዙወች ዱንያን ረስተዋል፡፡
➢ለተውሒድ ሲባል…………የተከሰተው ተዘርዝሮ አያልቅም።
➢ለተውሒድ ሲባል ብዙ ነገር ተከስቷል እናስተውል ይህ ለጥቆማ ነው።

➢ኢማሙ አሻፍዕይ ረሒመሁሏህ እንደሚሉት ተውሒድን ለማረጋገጥ ለነብዩ ሙሀመድ ሰለሏሁ አለይሒ ወሰለም ብቻ ከ3`000በላይ ተአምራት አሣይተዋል ይላሉ ።
ስለሆነም ወገኔ ሆይ ንቃ
ከመሞታችን በፊት የተውሒድ ባለቤት እንሁን
«ተውሒድ ይህ ከሆነ ከተውሒድ ውጭ ምን እንበል »
👉ልብ ያለው ልብ ይበል____

....በኑረዲን አል-ዓረብ
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍96
ኻሊድ ክብሮም፣ በአንድ ደቂቃ ብዙ ጥፋት!
~
ባያያዝኩት ቪዲዮ ላይ ኻሊድ ክብሮም ብዙ ስህተቶችን ፈፅሟል። ለዚህ ጥፋት እርምት መስጠት የሚጎረብጣቸው አካላት እንዳሉ የሚታወቅ ነው። ነገር ግን ሊዘነጋ የማይገባው ነገር ከግለሰቦች ይልቅ ለሐቅ ነው ቀዳሚ ውግንናችን ሊሆን የሚገባው። ማንም እየተነሳ ዲንን የሚያዛባ፣ ህዝብን የሚያሳስት ስብከት በሰጠ ቁጥር ዝም የምንል ከሆነ መቋጫ የሌለው ውድቀት ላይ ነው የምንደርሰው። "የፈትዋ አምባ ገነንነት" እያሉ አፍ ለማስያዝ ለሚሞክሩ ወላዋዮች እጅ ብንሰጥ አንዱ ዘፈን ሲፈቅድ፣ ሌላው ወለድ ሲፈቅድ፣ ሌላኛው የአስካሪ መጠጥ አይነቶችን ሲፈቅድ፣ ሌላው የሲሪያ ኒካሕ ሲፈቅድ፣ አልፎ የሺርክና የቢድዐ ስብከቶች ሲንሰራፉ ብንተላለፍ ኢስላማችን ስሙ ብቻ ተርፎ የተውለቀለቀ ሌላ እምነት ነው የሚቀረን።

ስለዚህ አደባባይ የወጡ ጥፋቶችን ባደባባይ እርምት መስጠት ይገባል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" مَنْ رَأَى مِنْكُمْ مُنْكَرًا فَلْيُغَيِّرْهُ بِيَدِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِلِسَانِهِ، فَإِنْ لَمْ يَسْتَطِعْ فَبِقَلْبِهِ، وَذَلِكَ أَضْعَفُ الْإِيمَانِ "
"ከናንተ መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው። ካልቻለ በምላሱ፤ ካልቻለ ደግሞ በልቡ። ይሄኛው የመጨረሻ ደካማው እምነት ነው።" [ሙስሊም: 186]

በተጨማሪም ነቢያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
ما مِن نَبِيٍّ بَعَثَهُ اللَّهُ في أُمَّةٍ قَبْلِي إلَّا كانَ له مِن أُمَّتِهِ حَوارِيُّونَ، وأَصْحابٌ يَأْخُذُونَ بسُنَّتِهِ ويَقْتَدُونَ بأَمْرِهِ، ثُمَّ إنَّها تَخْلُفُ مِن بَعْدِهِمْ خُلُوفٌ يقولونَ ما لا يَفْعَلُونَ، ويَفْعَلُونَ ما لا يُؤْمَرُونَ، فمَن جاهَدَهُمْ بيَدِهِ فَهو مُؤْمِنٌ، ومَن جاهَدَهُمْ بلِسانِهِ فَهو مُؤْمِنٌ، ومَن جاهَدَهُمْ بقَلْبِهِ فَهو مُؤْمِنٌ، وليسَ وراءَ ذلكَ مِنَ الإيمانِ حَبَّةُ خَرْدَلٍ.
"አላህ ከእኔ በፊት ወደነበሩ ህዝቦች የላከው አንድም ነብይ የለም፣ የሱን ሱና አጥብቀው የያዙ እና ትእዛዙን የሚከተሉ ከህዝቦቹ ውስጥ ደቀመዛሙርቶችና ባልደረቦቻቸው የኖሩት ቢሆን እንጂ። ከዚያም ከነሱ በኋላ የማይሰሩትን የሚናገሩ እና ያልታዘዙትን የሚሠሩ መጥፎ ተተኪዎች ይመጣሉ። እነዚህን በእጁ የታገላቸውም ሰው አማኝ ነው። በምላሱም የታገላቸው ሙእሚን ነው። በልቡም የታገላቸው ሙእሚን ነው። ከዚያ ውጪ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያክል ኢማን የለም።" [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 50]

ስለዚህ ያዩትን መጥፎ ነገር ማስወገድ ነብያዊ አደራ እንደሆነ እንረዳለን። ቀጥታ ማስወገድ ካልተቻለ በቃል ወይም በፅሁፍ መናገር ይገባል። ይሄ ጉዳይ የሁሉም ሙስሊም የጋራ ግዴታ ቢሆንም የዱዓት ኃላፊነት ግን ከሌሎች የከበደ ነው። ሁሉም በዝምታ የተሰማማ ከሆነ ግን ጥፋቶች 'ኖርማል' እየተደረጉ ይያዛሉ።

ይህንን መነሻ በማድረግ ባያያዝኩት ቪዲዮ ላይ ምላሽ እሰጣለሁ። ተናጋሪው ኻሊድ ክብሮም እንዲህ ይላል፦

1. " ጁሙዐ ሶላት ቁጭ ብለን ሰው በፀሐይ ደጅ እየተንቃቃ ... ተውሒድ ለ3 ይከፈላል ብሎ ለ25 ደቂቃ የሚያብራራ አለ።"

መልስ፦

ኹጥባ ያለ ልክ ለሚያስረዝሙ ሰዎች መምከር ከፈለግክ መንገዱ አጭር ነው፣ አላህን ፍሩ በልክ አድርጉ ማለት። ይህንን አስታኮ ከስንት ርእስ መሀል የተውሒድ ትምህርትን ነው ለመማረሩና ለመሰላቸቱ ምሳሌ የሚያደርገው። እነዚህን ሰዎች ከተውሒድ ትምህርት ጋር በዚህ መጠን ያጠማመዳቸው ምንድነው? ትልቁ የኡማው ነቀ ^ርሳ ለነዚህ አፍራሽ ግብረ ኃይሎች መድረክ የሚሰጣቸው አካል ነው። ለተውሒድ ትኩረት የላቸውም የሚለው አይገልፃቸውም፤ ጥላቻና መሰላቸት ነው ያላቸው። ይቀጥላል :-

2. "መስጂድ ላይ ቆሞ የሚያስተምረው ሸይኽ የሆነ አካል አስተሳሰብ ነው የሚያራምደው። ለምን? ደሞዝ የሚከፍለው የሆነ አካል ነው። ለቁርኣን አይደለም ታማኝነቱ ። ታማኝነቱ ለሆነ አካል ነው። ታማኝነቱ ደሞዙን ስለሚቆርጡለት ሰዎች ነው። ይሄን ባልናገር ደሞዜን ይቆርጡታል ይላል። ግን ትውልድን ከቁርኣን የሚቆርጥ ትምህርት ነው እያስተማረ ያለው።"

መልስ፦

ወላሂ አደገኛ ውንጀላዎች ናቸው በዚህ ንግግር ውስጥ ያሉት።

ሀ - በመስጂድ የሚያስተምሩ መሻይኾችን 0ቂዳቸውን ለገንዘብ የሸጡ ናቸው ማለት ብልግና አይደለም ወይ? እርሱ ለገንዘብ ብሎ ነው ደዕዋ የሚያደርገው? የሰዎችን ልብ ሰንጥቆ አይቶ ነው በድፍረት የተውሒድ ዱዓቶችን በዚህ መልኩ የሚወርፈው?

ለ - ደግሞም ከየትኛውም ጭፍራ በላይ ዝቅተኛ የዱንያ ሁኔታ ያላቸው ወደ ተውሒድ የሚጣሩ ዱዓቶች ናቸው። ወላሂ!! አብዛኞቹ ለእለት ኑሯቸው የተቸገሩ፣ ይሄ ነው የሚባል የገቢ ሰበብ የሌላቸው ናቸው። በዚህ ደረጃ ለመቸገራቸው ቀዳሚው ሰበብ ደግሞ ሺርክና ቢድዐ ላይ ጠንካራ አቋም በመያዛቸው ነው። ህዝብን የሚያስደስቱ ርእሶችን እየመረጡ ቢያግበሰብሱማ እሱ የረባ ዒልም ሳይኖረው ፊጥ የሚልበትን መድረክ መቆጣጠር አያቅታቸውም ነበር።

ተሳክቶላቸው ከጎናቸው ደጋፊ ያገኙ የተውሒድ ዱዓቶች ካሉም አላህ ይጨምራቸው። ምቀኛ አፈር ይቃም። ከሀሳብም፣ ከሰው እጅም የሚያወጣ ሐላል ሪዝቅ ሰጥቷቸው በተሻለ አቅም ለወገን የሚደርሱ፣ ጠላት የሚያርርባቸው ያድርጋቸው።

ሐ - ይልቅ ትውልድን ከቁርኣን የሚቆርጥ ትምህርት እያስተማረ ያለው እሱና እሱን መሰሎች ናቸው። የቁርኣን ትምህርት እንዳለ ስለ ተውሒድ ነው። ለተውሒድ እንቅፋት የሆነ ሰባኪ እሱ በትክክል ትውልድን ከቁርኣን የሚቆርጥ ትምህርት እያስተማረ ነው ያለው። ደግሞም ከብዙ አቅጣጫ ደሞዝ የሚያገኙትም እንዲህ አይነቶቹ አፈ ቅቤዎች ናቸው።

ይቀጥላል፦

3. "ሁልጊዜ የቁርኣን ሀሳቡ ተውሒድን መሰረት አድርገን፣ ሽፋን አድርገን ሰውን ወደራሳችን አስተሳሰብ ጠምዝዞ ለማስገባት የኛ አስተሳሰብ ካልሆነ በስተቀር እውነተኛ እስልምና ላይ የለህም የሚል አባዜ እባካችሁ የሚያደክም ነው።"

መልስ፦

እባክህ በመጀመሪያ አንተ ራስህ ቁጭ ብለህ ተውሒድን ተማር። የተውሒድን ምንነትና ዋጋ አለማወቅህ ነው እንዲህ አይነት ጥፋት ላይ የሚጥልህ። የተውሒድ ጉዳይ ቅንጦት አይደለም። የሞት ሽረት ጉዳይ ነው። አሁንም እወቅ ተውሒድ የሌለበት እምነት እውነተኛ እስልምና አይደለም። በተውሒድ ደዕዋ ላይ ቂም ያረገዘ ስብከት እያደረግክ ያለኸው አንተ ነህ። እስቲ ውንጀላዎችህን ተመልከታቸው! የራስህ መሳት አልበቃ ብሎህ ካንተ የጥፋት አስተሳሰብ ጋር ያልገጠሙ ዱዓቶችን፤ በመጥፎ አባዜ የተለከፉ፣ ሰዎችን ከቁርኣን የሚያቆራርጡ፣ ለቁርኣን ታማኝነት የሌላቸው፣ ይልቁንም ለሚከፍሏቸው አካላት ቅጥረኛ የሆኑ አድርጎ መሳል ስህተት ብቻ'ኮ አይደለም፤ ብልግ ^ናም ጭምር እንጂ። ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ "የፈትዋ አምባ ገነንነት" የሚል ታፔላ እየለጠፉ የማጠልሸት ዘመቻ የከፈቱት አካላት እንዲህ አይነት ፀረ ተውሒድ አላማ ያነገቡ ናቸው።

(ኢብኑ ሙነወር፡ ረቢዑ ሣኒ 3/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍98
«በሉ እስኪ ንገሩን»
--------------------
የኢኽዋንን መንጋ ጠቢብ ቢያስተምረው፡
ምን ክስተት ቢፈጠር መከራ ቢመክረው፡
እውነታውን ልቡ ምን ቢያውቀው ቢወቀር፡
#ኢሱ አቅሙን አያውቅም ካልነገሩት በቀር!?

ጨፍጫፊ ከሆነ መሪ ምን ይሰራል፡
ተግባሩ ከሌለ ስም መች ያስከብራል፡
ሐቅ የመውደድ ጥማት ወኔው ከሌላቸው፡
ምን ይጠቅማቸዋል #ኻሊድ ብንላቸው፡
ካልተስተካከሉ ገብተው በመንገዱ፡
ወዳጅ ከሆናቸው የሚያምነው በገዱ፡
ተውሒድና ሱናን ልባቸው ከጠላ፡
እድገታቸው ቁልቁል ፍጥነት ወደ ኋላ፡

ካላስተማሩበት ተውሒድና ሱና፡
ምን ይሰራል ገንዘብ ምን ይሰራል ዝና፡
አለም ያወቃቸው የስልጣን ሱሰኞች፡
የሱና ጠላቶች ክፉና ሸረኞች፡
ስማቸውን ዳግም ለመከለስ ሲሉ፡
በመድረካቸው ላይ ንፁሀን ያማሉ፡
የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላ እማይደሉ⁉️

ተገላግለን ነበር ስልጣን ተሰጥቷችሁ፡
ወረዳችሁ መሰል ደግሞ ተነሳችሁ!?
ሁሌ መቼም ቅጥፈት ስለማይደክማችሁ፡
አሁን ደግሞ በግልፅ ተውሒድን ጠልታችሁ፡
በአዲስ ግልፅ ማሊያ መውጣት ጀመራችሁ⁉️
እመኑኝ ድጋሜ ትሰበራላችሁ⁉️

ምን ታሪክ ቢገለፅ የትኛውም አለም፡
ሐቅን ትግል ገጥሞ ያሸነፈው የለም፡
እሱ ተግባር እንጂ ቃላት ብቻ አይደለም፡
እና አሁንም ቢሆን ብታጥላሉት የትም!!
ወላሒ ተውሒድን አታሸንፉትም፡

አውቀት አልባ ሙግት ጥላቻ አዘል ጠኔ፡
የስልጣን ሱስና አጉል ስልጣኔ፡
ከአመታት በፊት በዛ ሰፈር ገብቶ፡
መንከባለል ይዟል ብዙ ከብት አርብቶ፡
ግባችሁ ከንቱ ነው ንፋስን መከተል፡
መንጋችሁ ደዩስ ነው በየትም መግተልተል፡
ላይጥሉ መታገል ላይከብሩ መባተል፡

....ታሳዝናላችሁ....!!?

ማነው ሀይማኖቱን ለገንዘብ የሸጠው፡
ማነው ህዝባችንን ከሀቅ ያቋረጠው፡
ማነው ተላላኪው ማን ፉሉስ ተሰጠው፡
ማነው ተውሒድ ፈርቶ የሚደነግጠው!?
ማነው ለዝና ሲል የተሽለጠለጠው!?
ማነው ካሜራ የሚቅለሰለሰው፡
ማነው ሱናን ጠልቶ ቢዲዓ እሚልሰው!?

ማነው የሚጫወት ሴቶችን ሰብስቦ፡
ማነው የሚያታልል ወጣቶችን ስቦ፡
ማነው የሚያምታታ ፖለቲካ አቅርቦ፡
ማንስ ነው በሀቁ የሚኖር ተርቦ.!?

እኮ የተውሒድ ሰው በገንዘብ ይታማል፡
ይህ ነገር ከኢኽዋን መውጣቱ ይገርማል!?
ማነው ባለሀብቱን የሚለማመጠው!?
ማነው ለገንዘብ ሲል ደዕዋ እሚለውጠው!?
እኮ ማን ነበረ ሁሉ እንዳይከፋ፡
ሲበትን የነበር ቅጥፈትን በይፋ!?

ማነው በአንድነት ስም የተሰበሰበው፡
ማነው በስልጣን ሱስ ዋሽቶ የቀረበው፡
ማነው ለጥቅም ሲል የተስገበገበው.!?

ማነው ለገንዘብ ሲል ማሊያ የቀየረው፡
ማነው ከሁሉም ጋር የሚተባበረው!?
ማነው ለእስልምና የሆነው እንቅፋት፡
ማነው የሚታገል ተውሒድን ለማጥፋት፡

ማነው ከኩ*ፋር ጋር ሁሌ እሚተሻሸው፡
ማን ነበር ወጣቱን ልቡን ያሞሸሸው፡
አንድ ነን እያለ ህዝቡን የበተነው፡
ለህሌናህ ፋረድ በል ንገረን ማነው!?

ማነው በደዕዋ ስም ከእምነት የራቀ፡
ተረት እያወራ ማነው የታወቀ፡
ለስም እና ዝና ማንስ ተጨነቀ!?
የተውሒድን ትግል የማነው የሚቀማን፡
ሱንዮች በጥቅም ማንስ ነው የሚያማን!?
ስልጣን የሚያሰክረው ማን ነበረ እኮ ማን!?

እስኪ ከውስጣችሁ አውጡትና አብስሩን፡
እስኪ ጥላቻውን እንድህ አስቆጥሩን፡
እኛም እንቁጠረው በሉ እስኪ ንገሩን!?

....በኑረዲን አል-ዓረብ...

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍86
...ጀግናዬ...

ውሀ ሰው ሰራሽ አበባ ላይ የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለው ሁሉ አንዳንዴ ሀይላችን ማን ላይ እንደሚባክር ማወቅ አለብን እላለሁ።

👉ሰላም እደሩልኝ

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍78
(➏❶)الواجبات المتحتمات
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
አል-ዋጂባት

         👉ክፍል=❶➏

❷❶= ደቂቃ

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍21
شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
Photo
እኛ አይደለንም "አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" ያልነው
~
በጀህ ^ሚያ ተወሳክ የተጠቁ ሰዎች በተደጋጋሚ "እናንተ አላህ ከዐርሽ በላይ ነው ትላላችሁ" እያሉ ይከሱናል። ወላሂ እኛ አይደለም ይህን ያልነው። ከዐርሽ በላይ እንደሆነ የተናገረው እራሱ አላህ ነው። ይሄውና:-
{ ٱلرَّحۡمَـٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰ }
"አረሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ።" [ጧሀ፡ 5]

በሌሎች ስድስት ቦታዎች ላይም "ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ አለ" የሚል አለ። [አዕራፍ፡ 54] [ዩኑስ፡ 3] [ረዕድ፡ 2] [ፉርቃን፡ 59] [ሰጅዳ፡ 4] [ሐዲድ፡ 4]

ስለዚህ አላህ ከርሹ በላይ ነው ያልነው እኛ ሳንሆን እራሱ አላህ ነው። ተቅዩዲን ዐብዱሳቲር አልመቅዲሲይ ረሒመሁላህ በ679 ሂ. የሞቱ ታላቅ ዓሊም ናቸው። አንድ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን የሚያስተባብል የዒልመል ከላም አቀንቃኝ በተቃውሞ መልክ “አንተ አላህ ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ ትላለህ አይደል?” ሲላቸው እንዲህ ብለው አፉን አስያዙት፡-
لا والله ما قلته، لكن الله قاله، والرسول ﷺ بلغ، وأنا صدقت، وأنت كذبت !
“በጭራሽ ወላሂ! እኔ እሱን አላልኩም። ይልቁንም አላህ ነው ያለው። መልእክተኛው ﷺ አደረሱ። እኔ አመንኩኝ። አንተ አስተባበልክ!” [ታሪኹል ኢስላም፣ ዘሀቢይ፡ 15/373]

ይህ ቁርኣናዊ መልእክት የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን በሚገባ የሚያመላክት ከመሆኑም ባሻገር ለአፈን ^ጋጮች የጎን ውጋት ነው።። ለዚህም ነው የጀህ ^ሚያው ፊታውራሪ ጀህም ብኑ ሶፍዋን ይህንን ቁርኣናዊ ጥቅስ “የምፍቅበት መንገድ ባገኝ ከቁርኣን ውስጥ ፍቄ አወጣው ነበር” ያለው። [ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ፣ ቡኻሪይ፡ 38] [አሱናህ፣ ዐብዱላህ ብኑ አሕመድ፡ ቁ. 190]

መልእክቱ ሌላ ነው?
-
ተፃራሪዎች በአንቀፆቹ ውስጥ የተጠቀሰውን የኢስቲዋእን መልእክት ሊቆለምሙ በከባዱ ቢታገሉም ይሄ ግን ፈፅሞ ማስረጃነቱን አያደበዝዘውም። ምክንያቱም “ኢስተዋ” የሚለው ከላይ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነ ገላጋይ የሰለፎች ተፍሲር አለና። ይሄውና፡-

[1ኛ] ሶሐቢዩ ኢብኑ ዐባስ፡- “ወደ ሰማይ ከፍ አለ” ብለው የፈሰሩት ሲሆን ከብዙሃን የሰለፍ ሙፈሲሮችም ተመሳሳይ ትንታኔ እንደተገኘ በገዊይ ገልፀዋል። [ተፍሲሩል በገዊይ፡ 1/78] [ተፍሲሩ ሰምዓኒይ፡ 1/63]
[2ኛ] ሶሐቢዩ ኢብኑ መስዑድ፡- “ኢስተዋ” የሚለውን ቃል ሲፈስሩ “ዐርሹ ከውሃው በላይ ነው። አላህ ደግሞ ከዐርሹ በላይ ነው። ሆኖም ከስራዎቻችሁ ምኑም አይሰወረውም” ብለዋል። [ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ፣ ቡኻሪይ፡ 43]

[3ኛ] ታቢዒዩ ሙጃሂድ፡- “ከላይ ሆነ” ብለው ፈስረውታል። [ሶሒሕ አልቡኻሪይ፡ 9/124]
[4ኛ] ታቢዒዩ አቡል ዓሊያም፡- “ከፍ አለ” የሚል ፍች ሰጥተውታል። [ሶሒሕ ቡኻሪይ፡ 9/124]
[5ኛ] እና [6ኛ] ከታቢዒዮቹ ሐሰኑል በስሪይ እና ረቢዕ ብኑ አነስም ተመሳሳይ ተፍሲር ተዘግቧል። [ተፍሲሩ ብኒ አቢ ሓቲም፡ ቁ. 12093] [ጃሚዑል በያን፡ 1/429]

[7ኛ] ከአትባዑ ታቢዒን ትውልድ የሆኑት አልኢማም ቢሽር ብኑ ዑመር አዘህራኒይ (207 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
سمعتُ غيرَ واحدٍ منَ المفسِّرينَ يقولونَ: {الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى}، على العرشِ ارتفع
“{ ٱلرَّحۡمَـٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰ } የሚለውን በርካታ የቁርኣን ሙፈሲሮች ‘ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ’ ሲሉት ሰምቻለሁ።” [ላለካኢይ፡ ቁ. 662]
[8ኛ] አልኢማም አሕመድ ብኑ ሐንበል (241 ሂ.)፡- የኢስቲዋእ ፍቺው “ከፍ አለ፣ ከላይ ሆነ” ማለት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልዐቂዳህ፣ ሪዋየቱል ኸላል፡ 108]

ይሄው በአንቀፆቹ ውስጥ የተጠቀሰውን የኢስቲዋእ ትርጓሜ ቀደምቶቹ ግልፅ አድርገዋል። አላህ ከዐርሹ በላይ ነው ማለት እንደሆነ የነብዩ ﷺ ተማሪዎች፣ ታቢዒዮችና የቅርብ ተከታዮቻቸው እየመሰከሩ ነው። ጀህ ^ ሚዮች እና በጀህ ^ ሚያ ቫይረስ የተጠቁ አሽዐሪዮች ደግሞ ከሰለፎቹ በላይ እናውቃለን ብለው ቁርኣኑን እያዛቡ “ኢስተዋ” የሚለውን “ኢስተውላ” /ተቆጣጠረ/ እያሉ ተርጉመውታል። አልኢማሙ ዳሪሚ ረሒመሁላህ በጀህሚያዎች ላይ ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል፡-

እኛ ዘንድ ተፍሲሩ ተቆጣጠረው ማለት ነው ይላሉ። ከቦታዎች ሁሉ ያልተቆጣጠረው ቦታ ኖሮ ነው በቁርኣኑ ላይ ደጋግሞ ዐርሽን ተቆጣጠርኩት የሚለው? ዐርሽን እንደተቆጣጠረው ሁሉን ቦታ የተቆጣጠረ ከሆነ ዐርሽን ለይቶ መጥቀሱ ምን ትርጉም አለው?! ይሄ ፈፅሞ የማይመስል ሙግትና ከንቱ ንግግር ነው። እያጭበረበራችሁ እንጂ ከንቱነቱን እናንተም አትጠራጠሩም። [ረድ ዐለል ጀህሚያ፡ 40]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል ኣኺር 5/1447)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍44
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«አየህ ኔታንያሁ»
---------------
ነብይ ቢያመጣ አሏህ አክብሯችሁ፡
እናንተ ግን በጎን ወይፈን ቀርፃችሁ፡
በዚያ በክብር ሰው ስንት ግፍ ሰራችሁ!?
አለቀቃችሁም ዛሬም ክፋታችሁ፡
አዬ ጉድ መከራ ዋ መጨረሻችሁ፡

መቼም ብዙ ክፋት ተቋጥሯል በጓዳህ፡
አለም ፊቱን ሲያዞር አሁን ምን ተረዳህ!?
የንፁሀኖች ደም ቢሰማም በአለም፡
ከወሬ ባሻገር የመልስ ምት የለም፡

ፍትህ እንደሌላት ዱንያን አውቃታለሁ፡
ለዛም ትልቅ ሞደል አንተን አይቻለሁ፡
በዚህች አለም ዑደት ፍትህ ቢኖር ኖሮ፡
ስቃይ ተፈርዶብህ ሞተህ ነበረ ዱሮ፡
ውሻ ትሆን ነበር ጂብና ከርከሮ፡

አወ ፍትህ የለም ይሔም ዛሬም አለህ፡
ግን ዕርግጠኛ ነኝ ዋጋ ትከፍላለህ፡
ባንተ ዘግናኝ ተግባር ነፍሳቸው ረክሶ፡
የጋዛ ህፃናት ንፁህ እንባ ፈሶ፡
አይናቸው እያዬ መስጂዳቸው ፈርሶ፡

የእጂህን ሳታገኝ ታሪክህ አይጠፋም፡
ግን ደግሞ ቀደሩ በእኛ እጅ አይገፋም፡
እንደት እንዳረከው ይታይሀል ጋዛ?
ህፃናቶች ሲያጡ መጠለያ ታዛ፡
በረሀብ ሲሞቱ ያለ አንዳች አስቤዛ!?

ሰው መስለኸኝ እንጂ ሀሳብ ስትከነዳ፡
አውቃለሁ ባለጌ#ሰይጣን ነው አይሁዳ፡
ወይፈንን ያመልካል ሙሳን እየከዳ፡
ከየትስ ይመጣል ከዚህ በላይ ባንዳ፡

«ሰሞኑን እንደት ነህ»

አልጋና ትራስ ላይ ተኝተህ ታድራለህ!?
ጥርስህ ይገለጣል ፈገግ ትላለህ!?
እንደት ነው ስሜቱ የተመድ ፓርላማው፡
ጥለውህ ሲወጡ ገብቶሀል አላማው፡
አብሽር ያለህ ሁሉ ሲሸሽህ ወዳጅህ፡
አንተን ይጠቁማል የቆሸሸው እጅህ፡

....ኑር አል-ዓረብ
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍86
👉ጀግናዬ...!!

     ከምትጠነቀቀው ሰው አትፍራ;
ባይሆን ከምታምነው ሰው ተጠንቀቅ!!
👍52
«....የማበድ ፍላጎት...»
-----------------------
የሰው ልጅ ሲፈጠር ሲሰጠው ህሌና፡
እንድኖር ነበረ በሀቅ እንድፀና፡
ህግም እንዳከብር ተውሒድና ሱና፡
አሁን ግን ተረሳ ህሌና ተሸጠ፡
ለጥቅም ለዝና ሰው ተለወጠ፡

የሰው ልጅ ፍላጎት ጨርሶ ባይሞላም፡
በማንም ቢነገር እውነት አያስጠላም፡
ሽርክ እግር ዘርግቶ ቢዲዓ ሲጣጣም፡
የማበድ ፍላጎት ይጨምራል በጣም፡

አላማውን ሳያውቅ ይነሳሳል ደጋሽ፡
ህሌና ዘቀጠ በዛብን እብድ አንጋሽ፡
ፈሪ ነው ተባለ ዝምተኛም ታጋሽ፡


በሀይማኖት ሽፋን በእስልምና ታዛ፡
ህያዋን ነኝ አለ ሙታንም ጀናዛ፡
በሚገርም መልኩ እብድ መሆን በዛ፡


በህይወት መንገድ ላይ በኑሮ ትሩፋት፡
ማስተዋል ከሌለ በጥልቀት በስፋት፡
ትክክል ያልናቸው ይሆናሉ እንቅፋት፡

እርግጥ በዚህ ዘመን እብዱ በበዛበት፡
ፈተዋ እየሰጠ ሁሉም እንደ ዘበት፡
በማያውቀው አለም ስንቱ ተጓዘበት!?

ሰወች ማስተዋልን ሁሌ ካልታደሉ፡
መቻል ካለመዱ እየተበደሉ፡
በእብዶች መንደር ውስጥ ጤነኞች ከሌሉ፡
ጤነኞች ለእብዶች #እብዶች ይሆናሉ፡

አይፀድቅም ጤነኛ በእብዶች መነፀር፡
ሁሉም በእይታው ልክ ነው የሚነፃፀር፡
አንድ እንኳን ጤነኛ ቢኖርም ከመሀል፡
በእብድቺ እይታ ተብሎ ያምሀል፡
በሰከንድ ቅፅበት ከዛ ይባረራል፡
ወይ ደግሞ እንደነሱ አብዶ ይሰበራል፡

መርህ አልባ ቃሉን እንደ ንቃት ቆጥሮት፡
ኩራትና ትዕቢት መንፈሱን ወጥሮት፡
አጉል ልታይ ልታይ መታወቅ አስክሮት፡
ይህንን አቋሙን የከፍታ አድርጎት፡
ሰሞኑን ጨምሯል የማበድ ፍላጎት፡

....ኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍56
2025/10/31 13:07:25
Back to Top
HTML Embed Code: