Telegram Web Link
شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
Photo
የሙስሊሙ ህመም ያምሀል?
~
እንግዲያው በቁጭት ከምትብሰለሰል የድርሻህን ተወጣ።

1. ቢያንስ ቢያንስ ከራስህ ጀምሮ ቤተሰብህን በዲን፣ በስነ ምግባር ኮትኩት። አላማ እንዲሰንቁ አድርጋቸው። ቢቻል ከቤተሰብ አልፎ ሌሎችንም ለመለወጥ ጥረት እናድርግ።
2. ቅንጦትና ድሎት ቀንስ። አደጋ እንደተጋረጠበት ሰው አስብ። ትንሽም ቢሆን ወገንህን ለማጠንከር፣ ለማንቃት፣ ከመከራው ለማውጣት ትጋት ይኑርህ።
3. ከሱስ ራቅ። ጫትን ተፀየፍ። የእለት ቁጭቱን የሚተርክ እንጂ ለአላማው ቆራጥ የሆነ ሰው ከጫት ጋር አይርመጠመጥም። ሌሎችም ሱሶች ካሉ እንዲሁ።
4. ለዲንህ አስተዋጽኦ ይኑርህ። በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበት፣ ብዙ ማገዝ የምትችላቸው ነገሮች አሉ። ዋናው ቁም ነገር ከእንቅልፋችን ልንነቃ ይገባል።
5. ተማር፣ አስተምር፣ የሚማሩትን አግዝ። ትምህርት ትልቅ ትምህርት አለው።
6. ዘካ ትሰጣለህ? ካልሆነ ይሄ ሞት ነው። ከአምስቱ የኢስላምህምሰሶዎች አንዱን ንደህ፣ በዙሪያህ ያሉ ምስኪኖችን ነፍነህ ፣ ከዚያ ስለ ሙስሊም ወገኖችህ መገፋት ማውራት ሰከን ብሎ ለሚያይ ሰው ብዙም ስሜት አይሰጥም።
7. በኢኮኖሚ ለመጠንከር ታትረህ ስራ። ሌሎችንም ወደ ስራ እንዲገቡ አግዝ። መተዛዘን ይኑር። የመተጋገዝ፣ እጅ ለእጅ ተያይዞ የማደግን ስነ ልቦና እናዳብር። ሃብት በዚህ ዘመን ትልቅ ጉልበት ነው። ጉልበቱ ብዙ ትርጉም ያለው።

ያያዝኩት ምስል እንዲሁ ለቁጭት ያክል ነው፦

ንፅፅሩ በጀርመን እና በሀያ ሁለቱ የዐረብ ሊግ ሃገራት መካከል ነው። በያዝነው የፈረንጆቹ 2025 ዓ. ል
* የጀርመን ህዝብ ብዛት 84.4 ሚሊዮን ሲሆን የዐረብ ሊግ ሃገራት ህዝብ ብዛት ደግሞ 478 ሚሊዮን አካባቢ ነው።
* በቆዳ ስፋት :- ጀርመን 357,582 ኪ.ሜ² ስትሆን የዐረብ ሊግ ሃገራት ድምር ስፋት ደግሞ ~13.1 ሚሊዮን ኪ.ሜ² ነው።
* በኢኮኖሚስ? በ Nominal GDP መለኪያ፣ የጀርመን ~$4.74 ትሪሊዮን ሲሆን የጠቅላላው የዐረብ ሊግ ሃገራት GDP ደግሞ ~$3.55 ትሪሊዮን ነው።
በነዳጅ ዘይት እና በተፈጥሮ ሃብት የታደሉት ሃገራት ድምር GDP ከአንዲት ጀርመን ያነሰ ነው። በዚያ ላይ የጀርመን ኢኮኖሚ ትልልቅ ማሽኖችን፣ ትልልቅ ተሽከርካሪዎችን፣ ኬሚካሎችን፣ ወዘተ. አምራች ነው። የዐረቡስ ዓለም? በአብዛኛው የተፈጥሮ ሃብት ሽያጭ ላይ ጥገኛ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍81
👉በሰሞኑ ጉዳይ የመጨረሻ አቋሜ!!

👉የሶስቱ በሬወች ታሪክ‼️
👉ከዘር ቅራቅንቦ ውጣና ተደራጅ!!
--------------------------------
«ከጀርባ ያለው በደል ከሚሆነውና ከሆነው የከፋ ነው መናበብ ካለብህ ከዘረኝነት ልክፍትህ ንቃና ተደራጅ አልያ መከራህ በቅደም ተከተል እየተነጣጠልክ ትበላለህ እንጂ ምን ጠብ አታደርግም።»

በአንድ ጫካ ውስጥ መልካቸው
ነጭ
ጥቁርና
ቀይ የሆኑ ሶስት በሬዎች ይኖሩ ነበር።

አንበሳን ጨምሮ የትኛውም አውሬ ቢመጣ ክብ በመሥራት እየተዋጉ አላስጠጋ አሉ።

አንድ ቀን ግን አያ ጅቦ መጣና “ይሔ ነጭ በሬ ያስጨርሳችኋል፤ እሱ ባይኖር በጨለማ አትታዩም” የሚል መጥፎ ሀሳብ በውስጣቸው ለቀቀባቸው።

ሁለቱ በሬዎች ተባብረው ነጩን በሬ አባረሩት፡፡
ጅቡም ብቻውን አግኝቶት ነጩን በሬ በላው።

ጅቡ ሌላ ጊዜ ተመለሰና ለጥቁሩ በሬ “ቀዩ በሬ ካለ አሁንም ለአደጋ የተጋለጥህ ነህ” አለው፡፡
በዚህ የተነሳ ሁለቱ በሬዎች ተለያዩ፡፡
ጅቡም ቀዩን በሬ በላው።
በሌላ ቀን ጅቡ ጥቁር በሬው ጋር ሄደ፡፡ በሬውም “ዛሬ ምን ፈልገህ መጣህ? ልትበላኝ ነው?” አለው።

ጅቡም “አንተ እኮ የተበላከው መጀመሪያ ጓደኞችህን አሳልፈህ የሰጠህ ጌዜ ነው” ብሎ ጥቁሩን በሬ በላው ይባላል፡፡

ልብ ብለን ልንረዳው የሚገባው ነገር ሁሌም ልዩነታችን ውበትና ጥንካሬ የሚኖረው ከዘር በላይ የሚወደድ ተውሒድና በሀቅ የተገመደ መርህ ሲኖርና ሀይላችን በአንድነታችን ውስጥ እንደሆነ በተግባር ተረድተን ስንፈፅመው ነው።

ከእምነትህ ይልቅ...
#አማራ
#ኦሮሞ
#ስልጤ እየተባባልክ በዘር ተከፋፍለህ እየተናከስክ እንደ በሬወቹ እየተነጠልክ ትበላለህ እንጂ ለውጥ ይመጣል ብለህ እንዳታስብ።

በእምነታችን አንድ  ሙስሊም ሆነን ስንቆም ያኔ እንከበራለን ከዛ ውጭ የአማራን ሙስሊም ለመብላት ሲታሰብ ስልጤን ከጎንህ ማሸሽ የኦሮሙ ሙስሊም ጠላትህ እንደሆነ የሚሰብክህ ለያይቶ ሊበላህ ያሰበ ጂብ ነው።

ከእምነታችን ይልቅ ጠላት በሰጠንን ስም ተቀብለን ስንከፋፈል እንወድቃለን እየነጣጠሉ ይበሉናል።

የመጣው ዘመን ከእስከአሁኑ በከፋ ሁኔታ ለሙስሊሞች ከባድ ነው።
ክብደቱ የሚታወቀው በቤተ-ክርስቲያን በአንድ እምነት መዋቅር ስር ብቻ ተደራጅቶ እኔን ለትግል  ያወጣኝ ሁለተኛ አማራ አልሆንም ያለችው #አይሻ ናት፣
እኛን ከሞቀ ቤታችን ያስወጣን በወለጋ፣ በአርሲ፣ በጅማ፣ በዲላ፣ በጎንደር፣ በአክሱም፣ በላሊበላ፣ በመተከል ስለተጨፈጨፉት ሙስሊሞች ነው ይልህና ውስጥ ግን መስጊድ ልሂድ ስትል ግን አላስወጣ አላስገባ ይልሀል።

የደበረው ቀን መስጂድ አቃጥሎ ምንም አታመጣም ብሎ ይጨፍርብሀል፣
ሲያሻው ደግሞ ቤተ እምነትህ ውስጥ ገብቶ በኮራት ገድሎህ ይፎክራል።
በሙስሊምነትህ ሀገር ከሀገር መንቀሳቀስ አትችልም፣ ልጅክን፣ ሚስትህን አፍኖ ይህን ያክል ሚሊየን ብር አምጣ ሲል ትሰማዋለህ፣ የሆነ መብት ስትጠይቅ እናንተ ደግሞ ስልጤ፣ አሸባሪ፣ አራጅ፣ መጤ ሂድ መካ ከመጣህበት እያለ ከአማኝ እስከ አዋቂ ነኝ ባይ ሁሉ ሊያሸማቅቅክ ይሞክራል።

ካሻውም ውድ ህይዎትክን ይቀጥፍሀል። በሀገርህ እንደባዳ ቆጥሮህ ሙስሊምማ አይገዛንም እያለ ይሳለቅብሀል ይህን የሚለውን መሪ ያደርገዋል፣
ስልጣንማ አይዝም ይልካል ደረቱን ነፍቶ ይህ እየሆነ በአይንህ እያየህ ከሌላ ክልል ሙስሊም ወገንህ ጋር ሌላ ቁርሾ ጠላት በሰጠህ ተልዕኮ እንደ ጂረት የምትፈስ ከሆነ እመነኝ አንድ ቀን ተደግሶልሀል።

ሙስሊም ወንድሞቸ ሆይ ከአላህ በታች በተናጠል የሚደረግ ትግል፥ ወንድም ሁን ሴት ጫት እየበሉ ፍራሽ ላይ መንከባለል የሙስሊሞችን ስቃይ ያባብስ ይሆናል እንጂ የሚያመጣው አንድም የተቀደሰ ለውጥ የለውም።
ይህም ከመጣብን መከራና ሊቃጣብን ከታሰበው መጥፎ ነገር አያድነነም።
በመሆኑም ይህን አውቀን ልብ እንበልና እንንቃ እላለሁ።

ሌላውን ተውትና ልክ እነሱ በቤተ-ክርስቲያን ቅጥር በእምነታቸው እንደተደራጁት እኛም በመስጂዳችን አጥር ስር እንደራጅ እንሰባሰብ ያኔ ከጎንህ ስታጣኝ ሀሜቱን ትደርስበታለህ አሁን ግን በነገር አትውጋኝ የጠላቶቼ ማስፈራሪያ ይበቃኛል።

የምንደራጀው ከፊት ለፊት የሚመጣው በደልናግፍ ካለፈው ስለሚበረታ ራስህን ለመከላከል እንጂ ሌሎችን ለመጫን እንዳልሆነ በተግባር ተነስተህ አሳያቸው ያኔ ትከበራለህ።

የምንሰባሰበው በእስልምናችን ህዝብንና እምነትን እንዲሁም ሀገርን ለመጠበቅ መብትንም ለማስከበር፣
የታፈኑትን ለማስለቀቅ፣
ነጻነትና ሰላም ያጡትን ሰላም እና ነጻነት እንዲያገኙ ለማድረግ፣
ማንም ይሁን በሃይማኖቱ እንዳይሳቀቅ ፍትህ እንዳይጓደል እንጂ ሌሎችን ለመጫንና ለማሳቀቅ እንዳልሆነ ያኔ ለአለም እናሳያለን።

ነፍጥ አንግቦ በጥይት የሚቆላህን ጠላት ግን በፌስቡክ የቃላት ጦርነትና በቲክቶክ ቃለ መሀላ ልትመክተው እንደማትችል ግን ዛሬም ነገም እነግርሀለሁ።
«ይህ ማለት ግን ሚዲያው ምንም ነው ከተናገርነው ያልተናገሩት ይሻላሉ ማለት አይደለም በዚህ ዘመን የሚዲያን ጥቅም ያላወቀ ከንቱ ነው ግን ተግባራዊ እና ምድራዊ ሀይል ጋር ሲታገዝ ነው።»

ለነገሩ አይደለም ተደራጅታችሁ ገና ሙስሊም ለመደራጀት ምክክር ሲይዝ ያኔ ምን አለ በሉኝ ገለባው ከፍሬው፣
እውነቱ ከሀሰቱ፣
ንጹሁ ከቆሻሻው፣
አስማሳዩ ከእውነተኛው እና ጂቡ ከአንበሳው ይበጠራል ያኔ ግልጽ ብሎ ይታይህ ይሆናል።

እስኪ እንደራጅ፣
እስኪ እንመካከር፣
እስኪ አንድ እንሁን፣
እስኪ የሙስሊሞች ጠበቃ እንሁን፣
እስኪ የመስጂዳችን ዘብ እንሁን፣
በአንድ ላይ በመሆን ግፍን ተቃወሙ፣ ለንጹሀን ደጀን እንሁን፣
ፍትሃዊነትን፣
ሰላምን፣
ነጻነትን እናብስር።
የሙስሊሞችን ሰንደቅ በላኢላሃ ኢለሏህ መንገድ ከፍ እናድርግ‼️
«እስኪ አትሳቀቁ በግልፅ ተነጋግረን እንሞክረው መሞከርኮ ከዝታ በሽ እጥፍ ይሻላል።

ያኔ እንደለመዱት በሚዲያቸው አሻባሪ እያሉ ሲያሸማቅቁን፥
እንደቁራ ሲለፈልፉም እንያቸው

...ኑር...✍️
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍83
ለመስጂድ ኮሚቴዎች
~
መስጂዳችሁ ደርስ እና ደዕዋ ይሰጥበታል ወይ? የሰፈሩ ልጆች በተሻለ መልኩ ቁርኣን ለመቅራት የተመቻቸ ሁኔታ አላቸው ወይ? ወጣቱ አልባሌ ቦታ እንዳይውል ትኩረት አግኝቷል ወይ? ሴቶቻችንን ያማከለ ትምህርት አለ ወይ? በሰፈሩ እርዳታ የሚያሻቸውን አቅመ ደካሞች ተረባርቦ ለማገዝ የሚውልበት ጊዜ አለ ወይ?

መስጂድ ማለት ማህበረሰብን ለመለወጥ እጅግ ወሳኝ ቦታ ነው። ከሶላት ባሻገር እንደ ህዝብ ያሉብንን ፈተናዎች ለመወጣት የምንመካከርበት እጅግ ሁነኛ ቦታ ነው። የምንፈልገውን ግብ ለማሳካት የምንጥርበት ማዕከል ይሆን ዘንድ ግን የኮሚቴዎች ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። በዚህ ኃላፊነት ላይ ያላችሁ አካላት ለወገናችሁ ውለታ የምታውሉበት፣ ለኣኺራችሁ የምትሰሩበት ትልቅ እድል ነው እጃችሁ ላይ ያለው። እንደ ዋዛ አትመልከቱት። በክፋትም ይሁን በእዝህላልነት ኃላፊነታችሁን የማትወጡ ከሆነ ግን ለኣኺራችሁ ስትሉ ኃላፊነቱን ለሌሎች ለሚሰሩ አካላት ብትለቁ ይሻላችኋል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍68
«ሁለቱ ስልጤዎች»

አስገራሚ ውበት የስልጡን ህዝብ ሀገር፡
የሙስሊም መለያ እውነት ለመናገር፡
አለን የምትሉን ሙስሊሙ ሲቸገር፡

ወሎዬው ሲረሸን በእምነቱ ሲገለል፡
አንዳንዱ አስመሳይም በጥቅም ሲደለል፡
ድምፅ ስናሰማ ጠንቶብን መከራ፡
ስልጤ ነው የሚሉን ነጥለው ከአማራ፡

አማራነት ማለት ከሆነ እምነታችሁ፡
ስልጤ ካላችሁት ሙስሊሙን መርጣችሁ፡
አወ እኛ ስልጤ ነን ምንም ሳናቅማማ፡
ስልጤነት ሙስሊም ነው የብርሀን ማማ፡

ምንም ባንገናኝ ከኛ ጋር ባትመጡም፡
ጠላቶች ከአፋቸው ስልጤን አያወጡም፡
የወሎን ሙስሊሞች መረሸን ሲያምራቸው፡
ለግፍ ሲያዘጋጁን ለፖለቲካቸው፡
ሰምታችሁ ከሆነ #ስልጤ ነው ያሏቸው!!

መስጂዱ ተደፍሮ በማንም ወጠጤ፡
በስንቱ ሰካራም መንጋና ሰገጤ፡
መግለጫ ሲሰጡ ሽብሩና ዳምጤ፡
የጥፋት ማርከሻው የአብጤና አናውጤ፡
ስንኖር ሙስሊሞች ስንገደል ስልጤ፡

.....እና ስልጤ ማለት....

የሙስሊም ጠበቃ ስም ነሽ የሁላችን፡
አንች ነሽ ከንግድህ የትግል አርማችን፡
መከራ ሲዋጀን በየ መስጂዳችን፡
እየተመረጥን ስንሞት በዲናችን፡
አማራ ላይ ሆነን ስልጤ ነው ስማችን፡

እና ስልጤ ማለት ሙስሊሞች ነው ፍቹ፡
ይህንን እመኑ ሳታመቻምቹ፡
አሁን ሁላችንም ስልጤ ተብለናል፡
የናንተ ወገኖች ወሎ ተገኝተናል፡
የወሎ ስልጤ ነን ወገሬት ብለናል፡

ምንም ቢቀመጡ እልፍ አዕላፍ ህመሞች፡
ፍቱን መድሀኒት ገራሚ ቅመሞች፡
ፀረ-ተባዮች ነን ለጠሉን አረሞች፡

አዋጅ ተናገሩ ስሙኝማ ሰዎች፡
ቅበትም ወራቤ ብሎም ወሎዬወች፡
ኢስላም ነው አርማችን ሁለቱ ስልጤዎች፡

...ኑር...‌‌

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍100
"መንግስት ድምፅ ያፍናል"፣ "ጋዜጠኞችን ያስራል"፣ "ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት የለም" እያሉ የሚተቹ አካላት፣ የተቃወማቸውን ሁሉ "አራት ኪሎን ስንቆጣጠር እናሳያችኋለን!" እያሉ ግለሰቦች ላይ ብቻ ሳይሆን ድፍን ብሄር ላይ ሲዝቱ ማየት የሚገርም ነው። ከህወሓት ጋር በነበረው ጦርነት ጊዜም በጣም እየተጠጉ ሲመጡ እርምጃ የሚወሰድባቸው ሰዎች ብለው የስም ዝርዝር የሚለቁ ታጋዮች ነበሩ። በ1997 ምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተቃዋሚው ቅንጅት ፓርቲ ተወካይ ብርሃኑ ነጋ ገና ስልጣን ሳይዙ የሙስሊም ሴቶች አለባበስ ላይ ገደብ እንደሚያደርጉ የሰጠው ሃሳብ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ግራ የሆነ 'ሜንታሊቲ!'

እዚች ሃገር ላይ በህዝብ ስም እየማለ መንግስትን የሚታገለው ሁላ ተረኛ ጨቋኝ ለመሆን እንጂ የተሻለ ስርአት ለመዘርጋት፣ ወገንን ከድህነት አረንቋ ለማውጣት፣ ለሃገር ሰላምና እድገት አልሞ አለመሆኑ የሚያሳዝን እውነታ ነው። "የኢትዮጵያ ህዝብ ጨቋኝን እንጅ ጭቆናን አይጠላም" የሚለው አባባል እውነትነት እንዳለው የሚያረጋግጡ ብዙ ምሳሌዎች ታይተዋል። እንዲያውም ዛሬ ላይ ቆመን ስናይ ጣልያንን ራሱ የተቃወሙት ለሃገር አስበው ነው ለማለት ያስጠረጥራል።

* ከስር ያያያዝኩት አይነት ዛቻዎች ከሰሞኑ በሰፊው ሲንሸራሸሩ ነበር። በርግጥ ከብዙ ደጋፊዎች ተመሳሳይ ሐሳብ ሲሰነዘር ስላየሁ እንጂ የቡድኑ እውነተኛ ፔጅ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍52
👉ጥያቄ ለእኔ ወንድሞች⁉️

ከሱናው ሰው የሙስሊሞች ድምፅ የሚሆነው ዑስታዝ ኢብኑ ሙነወር ብቻ ነው⁉️

ማነው የሁሉንም ሙስሊም በደልና ግፍ አንድ ሰው ብቻ ይተንፍስ ብሎ እዳ ያሸከመው ⁉️

ሌሎቻችንስ እ‼️

የሱና ወጣቶች ለምንድነው የሚደርሰውን ግፍና መከራ መናገርና ለህዝቡ በቻላችሁት አቅም ድምፅ የማቶኑት...እ...⁉️

👉ከሸሪዓ ባልተጋጨ መልኩ የህዝብን ብሶት ማሰማት ነውር ነውን⁉️

በደሉ እናንተን አይሰማችሁምን⁉️
ነው ወይስ .......⁉️

ይቅርታ ሁሌ ስለሚገርመኝ ነው ወላሒ

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍169
አልቡኮ ወረዳ ነጢ የፋኖ ግፍ

«የአረብ ሀገር ልጆቻችን ሆይ ለምን⁉️
-----------------------------------
በድጋሜ ላልፅፍ ወስኘ ነበረ፡
በህዝቤ መከራ ልቤ ተሰበረ፡
ለቅሶውን ስሰማ ቃሌን አፈረስኩት፡
ድምፅ ልሁን ብዬ ሁሉን ነገር ተውኩት፡


በአልቡኮ ወረዳ ፋኖ በገባባቸው ቀበሌወች እየተሰራ ያለው ግፍና በደል እጂግ የሚዘገንን ለመናገር የሚያሳዝን ግፍ ነው።

ማንኛውም አባወራ በሬ ያለው
በበሬው ግብር ይከፍላል።
ሶላር ያለው በሶላሩ ይከፍላል።
ይህ ፋኖ የሚባል ቡድን የህዝብ ጠላት ነው ስንል የምትቃወሙ ሙስሊሞች ግን ...በምን ቋንቋ እንንገራችሁ።

እነሆ ደቡብ ወሎ በአልቡኮ ወረዳ #ነጢ በሚባል አካባቢ #ፋኖ ማህበረሰቡን እየዘረፈ እያሰቃዬው ነው።

ገበሬዉን በግዳጅ/ አንድ ቁና ስንደ እና
ባቄላ ብሎም ከእያንዳንዱ ማህበረሰብ
1000 ብር አምጡ እያለ ሚስኪን ገበሬ  መሬቱን መዝራቱን ትቶ የልጆቹን ቂጣ #ለፋኖ ታጣቂ ሀይል አስረክቦ ፆሙን እያደረ የቆየ ቢሆንም አማራጭ ስላጣ ችሎ ነበር።

አሁን ላይ ደግሞ በእያንዳንዳችኔ ➌⓪ ሽ ብር አምጡ
ከፋኖ ጎን ሁኑ እያለ አስቸግሯል ሲሉ የአካባቢው ተወላጆች ነግረውኛል::

ይህ እየሆነ ያለው #ነጢ ከምትባል ቦታ ነዉ::
የሚገርመዉ ነገር 
👉አረብ ሀገር ልጁ ያላቸዉን ሰወች ሰብስቦ ደግሞ
አንድ ልጅ ያለዉ ➌❺ሽ  
ሁለት ልጅ ያለዉ ❼⓪ሽ
አምጡ እያለ ፋኖ እየቀማ ይገኛል።

የክፍያ ማጠናቀቂያዉ ጥቅምት ➍ ነው ከዚያ ቀን ካለፈ ያልከፈለ ሰው ደግሞ ❶⓪⓪ ሽ እስከ ➌⓪⓪⓪ ሽ ቅጣት ይቀጣል እየለ ህዝቡን እየረበሸ እያተራመሰ ይገኛል።

መረጃውን ያደረሱኝ ሰወች እንደነገሩኝ ከሆነ




ነገር እየደረሰብን ያለው አረብ ሀገር ያሉት አንዳንድ ልጆች #ከፋኖ_ጎን_እንቆማለን ብለዉ
የጀመሩት የገንዘብ ድጋፍ ነውና እነዚህ ሰወች የህዝባቸውን ነፍስ ቀብድ አሲዘው #መቆመሩን አሏህን ፈርተው ያቆሙ ዘንድ ንገርልን ብለዋል።

 አስከትለውም እናንተ አዋጥታችሁ መሳሪያ ያስታጠቃችሁት ፋኖ ዛሬ የእናንተን ዘላጆች ሲያስፈራራበትና መስጂድ ውስጥ ሲረሽንበት ምን ተሰማችሁ ሲሉም የሀዘን ግርምታቸውን በብሶት አጋርተውኛል።

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍110
በወረኢሉ እና ካቤ መሰል አካባቢ ያላችሁ ሙስሊሞች ጥንቃቄ አድርጉ‼️
አሏህ ይጠብቃችሁ ወገኖቼ
አብሽሩ ሊነጋ ሲል ይጨልማል በየቦታው መከራችን መብዛቱ የድል ብስራት ጂማሮ ሊሆን ይችላል ኢንሻ አሏህ አብሽሩ በአሏህ ተመኩ አሏህም ህዝባችንን ይጠብቅልን አሚን
👍233
ጀግናዬ

ህይወት ቀልድ ብትሆን ኖሮ ብዙ ከልባቸው የሚስቁ ሰዎች ታይ ነበር።
👍63
አልሀምዱ ሊላህ

የታገተው ተርፏል!!
------------------
የአማራ ነፃ አውጭ ሀይል ነኝ የሚለው ፋኖ የሚያግተው አማራን፣
የሚቆጣጠረው አማራን፣
የሚገድለው ሙስሊምን፣
የሚያፈርሰው መስጂድን ግን ደግሞ የአማራ ነፃ አውጭ ታጋይ...ከማን ነው ነፃ የሚያወጣው⁉️

ለማኔኛውም #በመካነ-ሠላም #መስጅደ-ኑር በነበረው #በፋኖ በተደረገ ጭፍጨፋ ወቅት የሸሂድ ወጣት አብዱሶመድ ሙሐመድ የአጎት ልጅ አስከሬን ለማንሳት ወደ መስጅድ ሲመጣ በፋኖ ሃይሎች ታግቶ ተወስዶ ነበር።

ይህን ወደ ሚዲያ ማውጣት የልጁን ህይዎት አደጋ ላይ መጣል ስለነበር ለሚዲያ ፍጆታ አልቀረበም ከአጋቾቹ ጋር በተደረግ ድርድር #በሶስት_መቶ_ሺህ ክፍያ ማስለቀቅ ተችሏል።

የአማራ ነፃ አውጭ ነኝ የሚል አካል አማራ ነኝ የሚልን ሙስሊም ገድሎ የሟችን ቤተሰብ አግቶ 300ሽ ብር የሚቀበል ነፃ አውጭ ቡድን...አይደል⁉️


ለአማራ ህዝብ ነው የምታገለው የሚል ሃይል መልሶ ያንኑ ህዝብ አግቶ ገንዘብ የሚቀበልበት ትግል መቼም ልዩ ትግል መሆን አለበት የምለውክ በምክንያት ነው⁉️

እንጂማ ህሌና ያለው አካል የአጎትን ልጅ ገድሎ የአጎቱን ልጅ አግቶ ብር የሚቀበል "የአማራ ነፃ አውጪ" ትግል እንደት ሊሆን ይችላል⁉️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍147
ለጦለበተል ዒልም
~
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደምን ተጠቀሙባቸው። የምትችሉ በአካል እየተገኛችሁ፣ ካልቻላችሁ የተቀዱ ትምህርቶቻቸውን ብትከታተሉ ትጠቀማላችሁ ኢንሻአላህ።

ዱሩሶቻቸው የሚቀርቡበት የቴሌግራም ቻናል ይሄ ነው :-

ቴሌግራም - https://www.tg-me.com/Sheikhmuhammedzainadam
https://www.tg-me.com/SheikhMuhammedZainAdam


ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም።
👍32
(❽)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎

     👉ክፍል =❽

«ግዙፍ የሆነው ተዓምር ቁርዓን»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍24
ስልጤነት ይለምልም‼️
🎙ኑረዲን አል-ዓረብ
ስልጤነት ይለምልም

ወሎዬው ሲረሸን በእምነቱ ሲገለል፡
አንዳንዱ አስመሳይም በጥቅም ሲደለል፡
ድምፅ ስናሰማ ጠንቶብን መከራ፡
ስልጤ ነው የሚሉን ነጥለው ከአማራ፡


መስጂዱ ተደፍሮ በማንም ወጠጤ፡
በስንቱ ሰካራም መንጋና ሰገጤ፡
መግለጫ ሲሰጡ ሽብሩና ዳምጤ፡
የጥፋት ማርከሻው የአብጤና አናውጤ፡
ስንኖር ሙስሊሞች ስንገደል ስልጤ፡


የእምነት ጠላት ሆኖ ሁሉም ህልሙን ሲያልም፡
በጥላቻ ሰክሮ ሰው ገዳይ ሲሸልም፡
ሙስሊምነት ይፍካ ስልጤነት ይለምልም፡


🎙በኑረዲ አል_ዓረብ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍97
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«እኔ ምንም አልላችሁም ስሙት‼️»

👉ሙስሊሞቹ የዚህ መንጋ ተከታዮች አሏህ ልባችሁን ይመልሰው ሌላ ምን እላለሁ መቼስ‼️

ልብ ያለው ልብ ይበል

የሚገርመው ይህ ሰውዬ ጎጃም ውስጥ የፋኖ ጦር መሪ መሆኑን ስትሰሙ ነው እና የዚህ ሰውየ ጦርና ይህን አቅፎ የያዘው #ፋኖ ለብሔር ነው የሚታገለው ነው ብላችሁ ነው የምታስቡት⁉️

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍73
«የሴት ልጅ አይን ማረፊያ»

እሷ ተውሒድ እንጂ አትሻም ቤሳቢስት፡
ታጋሽ የመርህ ሴት ጀግና ነች ኒቃቢስት፡
ከባጢል አፅድቶ ሐቅ የሚሞሽርሽ፡
ንግስት ነሽ ለኔ ዘመን የማይሽርሽ፡

قرة عين المرأة ؛

زوجٌ يملك من القوامة ما يكفي ليحميها من الحرج ، ويُعفيها من همٍّ لم تُكلَّف به ، وينهي عنها الصراعات قبل أن تبدأ..

ከሀፍረት የሚጠብቃት ፣
ከጭንቀት የሚገላገልላት እና ግጭቶችን ከመጀመራቸው በፊት ለማስቆም የሚያስችል በቂ አመራራዊ ጥበብ ያለው ባል ነው...።

أبهى الرجال في عين المرأة :
القوي العادل ، لا الغني ولا الوسيم!

በሴት ዓይን ውስጥ በጣም ቆንጆው ወንድ ጠንካራ እና ፍትሃዊ እንጂ ሀብታም ወይም መልከኛው አይደለም። #እንዳትሳሳት!!

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍84
«ኒቃቢስት»

ንፁህ ወንድምሽ ነኝ አልልም ደክሜ፡
ግን አስብሻለሁ ጥፋቴን አክሜ፡
ስላንች እፅፋለሁ መፃፍ እስኪሳነኝ፡
ጠላትሽ ሲበዛ ጠበቃሽ እኔ ነኝ፡

...አይዞሽ...

አሸርጋጁ በዝቶ ቢሆን አመድ-አፋሽ፡
ለጠላቶች ሴራ ፈፅሞ እንዳይከፋሽ፡
ከቶ እንዳያስፈራሽ የሚያደርጉት ነገር፡
አንች መርህ አለሽ በሁለቱም ሀገር፡

....አይዞሽ...

በጠላቶች ሴራ እንዳትሳቀቂ፡
ለነሱ ዘመቻ ኒቃብ አታውልቂ፡
አንች ልዩ ሴት ነሽ ይህንን እወቂ፡

ያንችን ልብ ለብሶ ኬንያ ቢጓዝም፡
ምንም ቢያጭበረብር ደምሳሽ ፍቅሪዝም፡
በዘመናት ጠላት በተንኮል ተልኮ፡
ምን በደል ቢሰራም በኒቃብሽ ሾልኮ፡
ያንችን ግርማ-ሞገስ አያውቀውምኮ፡

...እና አይዞሽ እሽ....!!

ሔለንና ቅድስት ስምሽን ሊያጠፉት፡
ሙስሊም ነን እያሉ ምንም ቢሰለፉት፡
ምን ዘመቻው በዝቶ በስምሽ ቢነገድ፡
አደራ እንዳትለቂ #የኒቃቡን መንገድ፡
የተጋለጡ ቀን እውነታው ይጠራል
ፍሬና ገለባው ያኔ ይበራል፡
የነሱ ሲጨልም ያንች ግን ይበራል፡

ከባጢል አፅድቶ ሐቅ የሚሞሽርሽ፡
ንግስት ነሽ ለኔ ዘመን የማይሽርሽ፡
እሷ ተውሒድ እንጂ አትሻም ቤሳቢስት፡
ታጋሽ የመርህ ሴት ጀግና ነች ኒቃቢስት፡

«የወንድምነት ክብር በኒቃቢስት እህቶች ይደምቃል»
«ባል የመሆን ሞገስ በኒቃቢስት ሚስት ይፀድቃል።»


.....ኑረዲን አል-ዓረብ....

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍111
ወላጆች፣ ት/ቤቶች ጥንቃቄ አድርጉ
~
ሰው እያገቱ፣ ህፃናት እየሰረቁ ከፍተኛ መጠን ያለው ብር መጠየቅ በጣም የተንሰራፋ ባህል እየሆነ ነው። ሰላም ሲጠፋ፣ ጠንካራና አስተማሪ ቅጣት ሳይኖር ሲቀር የሰው ልጅ እንዲህ አይነት የተደበቀ አመሉን ያወጣል።

ብቻ ልጆቻችንን እንጠብቅ። ለራሳችንም ቢሆን አጉል ሰዓት ላይ ወይም ራቅ ያለ አካባቢ ብቻችንን አንጓዝ። እንዲሁ ሰበብ ለማድረስ ያህል እንጂ አንዳንድ አካባቢ ቤት ሰብረው፣ ተሳፋሪ አስወርደው ነው ሰው እያገቱ ያሉት። የሃገራችን ነገር እጅግ አሳዛኝ ደረጃ ደርሷል። አላህ ሰላማችንን ይመልስልን።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍72
2025/10/22 07:30:26
Back to Top
HTML Embed Code: