Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍68
(➒)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎

     👉ክፍል =➒

«በመጨረሻ ቀን ማመን»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍30
እህታችን نعيمة جمال أم عيناية በብዙ ፈተና ተፈትናለች። በስደት፣ በትዳር መፍረስ፣ በህመም፣ አግኝቶ በማጣት ይሄው አሁን ደግሞ ብዙ የደከመችበት ልጇን በሞት አጣች። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!

ህመሟን እንድትታከም ለችግሯም በተወሰነ ለመደጎም ከጎና እንቁም። ትንሽ ትልቅ ሳንል በቻልነው እናግዛት። ወገን ለዚህ ካልሆነ ለምን ሊሆን ነው? ለነገ ለኣኺራችን ይሆነናል፣ ኢንሻአላህ። አካውንቷ ይሄውና


1000391550728
ነይማ ጀማል
ንግድ ባንክ

ሌሎችን ያነሳሳል ካላችሁ የላካችሁበትን ላኩልኝ። አላህ ከጭንቅ ከመከራ ያውጣችሁ።
ሼር አድርጉት ባረከላሁ ፊኩም።
👍63
ክንፍ ተሰብሮ ብረር እንጂ አይባልም የምትናገሩትን እያስተዋላችሁ።
👍100
➨ሙሀመድ ይባላል....ﷺ

አሏህ ብሎ ያለው ቀና በል አትዘን፡
የሰላም የፍትህ አርማና ማዕዘን፡
ደግነት ብቻ ነው ሙሀመድ ያዘዘን፡

....የኛ ነብይ..ﷺ

ራሱን ለአሏህ ሽቅብ ቀና አድርጎ፡
ከረሒሙ ጌታ እዝነቱን ፈልጎ፡
በሙሽሪኮች በደል እየደረሰበት፡
ስሙ እየጎደፈ ዋሽተው ቀጥፈውበት፡
ፍፁም በሌለበት እየተወቀሰ፡
ጌታዬ ህዝቦቼን ብሎ ያለቀሰ፡

ሙሀመድ ይባላል።

የስልጣኔ አርማ የእድገት የከፍታ፡
ስሙ እማይረሳ ለሰከንድ ለአፍታ፡
እንኳን ላመነበት በመንገዱ ፀንቶ፡
አያውቅም ጠላቱን በክፋት አንስቶ፡

ከመጥፎ ከልክሎ መልካሙን ያሳያል፡
ከማንም ከምንም ሙሀመድ ይለያል፡
መከራው ሲጠና በአሏህ ይወከላል፡
ችግር ሲደራረብ ሀስቢየሏህ ይላል...
መደምደሚያው ነብይ ይባላል...

«እስኪ ሶለዋት እናውርድ⁉️

....✍️በኑረዲን አቡል-ፋሩቅ

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍123
«ተሰውረህ እደግ»

ከሰወች አይን ተሰውረህ እደግ
እድገትህ ስውር ከሆነ ግልፅ የወጣህ ሰዓት ማንም አይቋቋምህም።
ለጠላቶችህ ዱብዳ ሁንባቸው Background ሳታሳውቅ ድንገት የምትጋፈጥ ክስተት ሁን ያኔ ታሪክህ ሙሉ አሸናፊነት ይሆናል።

.....ኑር

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍129
የሰለምቴወችን ፅናት ያየሁበት ፖስት ነው።

«ለካ ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም»

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍209
👉ታላላቆቻችን ሆይ....‼️

ታላላቅ መሪዎች ምን ማድረግ እንዳለብህ አይነግሩህም እንዴት እንደሚደረግ ነው የሚያሳዩህ ..ይባላልና እኛም አሳዩን እንላለን።

የመከራ መብረቅ በሚንጣት ሀገር፡
ይህን የደም ጂረት እንደት እንሻገር⁉️
ነዓም ታላላቆች ሐቅ ላይ አቁሙን፡
እንደት እንራመድ አቅጣጫ ጠቁሙን⁉️

.....ኑር...✍️
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍153
(⓾)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎

     👉ክፍል =⓾

«በቀደር ማመን»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍28
በዚህ ዘረኝነት በተንሰራፋበት ዘመን የፖለቲከኞችን የጥላቻ ስብከት ረጋግጦ ከየትኛውም ብሄር ቢሆን ወንድሞቹን መውደድ የቻለ ሰው ምንኛ የታደለ ነው?!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
👍64
ዘር⁉️

በሚያሳዝን እና በሚያሳፍር መልኩ ከሙስሊም ወገናቸው ይልቅ በብሔራቸው የተሸጎጠው በአሏህ የካ*ደውን ያስበልጣሉ...

የነሱ ዘር ከሆነ ምንም ሆነ ምን ደንታ የላቸውም ሁሉንም እምነት ይወዳሉ እምነታችው ምንም አይታያቸውም ይህ አይነት #የሰከረ በሞላበት ሀገር ላይ ከዘር ትብታብ ወጥቶ #የተውሒድ_ወገኑን መውደድና ማቀፍ በርግጥም እድለኝነት ነው።

ከኦሮሞ ሙስሊም የአማራ ክርስቲያን ይሻለኛል።
ከአማራ ሙስሊም የኦሮሞ ክርስቲያን ይቀርበኛል።


የሚሉ መፈክሮችን የስልጡንነት መገለጫ ያደረጉ ተማርን ያሉ መሀይማን በበዙበት በዚህ ዘመን እውነትም ከዘረኝነት የወጥመድ ቅርቃር ወጥቶ ለአሏህ እጅ መስጠት ትልቅ ስኬት ነበር ግን አልተረዳንም ።

አሁን ላይ ዘረኝነትን ተው በእምነታችሁ ተሳሰሩ ማለት ተላላኪነት ወይም ሰርጎገብነት ተብሎ በጥርጣሬ አይን እንድትታይ ያደርግሀል።

በእምነትህ ተመርጠህ ተገድለህ ገዳዮችህን ስታወግዝ እሱኮ ዘረኛ ነው የሚል የራሳቸውን የበሽና ስም ጠርተው ላንተ መታወቂያ እንድሆን ይጭኑብሀል።


የሚያሳዝነው ይህን ነገር የሚያራግቡት በድን ውስጥ የተደበቁ የሆነ ማዕረግ ያላቸው ሲሆኑ ደግሞ ነገሩን የከፋ ያደርገዋል።

አሁን በተወገዘው ዘረኝነት ፈንታ እምነትን እያወገዙ ዘረኝነትን መቀደስ እጂግ ተከታይ ያበዛል ያሳዝናል በጣም።

ኦሮሞነት ከእምነት በላይ ነው!!
አማራነት ከእምነት በላይ ነ!!?
ተብሎ በነበር ስንቶች ያጨበጭቡ ነበረ ግን የተባለው በዘር እና በብሔር ሳይገደብ የእምነት ወንድም እህቶቹን የወደደ ነው በርና ምክሩ ብዙም ቫይራል አይወጣም።

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍51
በሀቅ አንድ እንሁን ዘረኝነት ይውደም፡
በዘር አሉባልታ አይፍሰስ የሰው ደም፡
ተውሒድና ሱና ከሁሉም ይቀደም፡

#ኑር__!!
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍133
. ለሰው አድርሱልኝ...

«አንድ አቋም ይኑርህ»
--------------------------
በመኖር ክንውን ሰው በመሆን አለም፡
በአቋም እንደ-መፅናት ትልቅ ፀጋ የለም፡
ሐቅ ነው የሰው ልጅ አንድ መልክ አይደለም፡
በውበት በቁመት በፀባይ ደረጃ፡
ላሳይህ ተከተል ሁሉን በመረጃ፡
ገልጨ ላሳይህ አንድ መጋረጃ፡

.....ብዙ አይነት ሰው አለ...!!

ምንም ሳታደርገው አንስቶ እሚጥልህ፡
ምንም ሳታደርገው የሚያንጠለጥልህ፡
ምንም ሳታደርገው የሚነጣጥልህ፡
ምንም ሳታደርገው ከልብ ወዳጂህ ጋር፡
ምንም ሳታደርገው ከህይወትህ አጋር፡
ምንም ሳታደርገው ስምህን አንስቶ፡
ራሱን ቀድሶ አንተን አስረስቶ፡
በስሜት ተጉዞ ብዙ መስመር ስቶ፡
በግራና በቀኝ ማዕረጉን ቀስቶ፡

ብዙ የሆንክለት ብዙ ያደርግሀል፡
የምነግርህ ነገር አሁን ይገባሀል፡
ያላልከውን ብሎ ቆርጦ እሚቀጥልህ፡
የኔ ነው ያልከው ነው ደፍሮ የሚያቀልህ፡

ሰው ከባድ ሚዛን ነው፤
በምንም ሁኔታ ውሉ አይጨበጥም፡
ወደድኩህ ያለህን፤
ታገኘው ይሆናል ስምክን ሲቆረጥም፡
አመንኩት ያልከው ሰው፤
ድንገት በሆነ ዘውግ ይሆናል እንዳይጥም፡
ይህ አይነቱን አካል፤
ከዝምታ ውጭ አይገልፀውም ግጥም፡

...እና ዝም....

ይህንን አስተውለህ፤
ዝም ስትል ኮራህ ብለው ይወጉሀል፡
እሽ ብለህ ደግሞ
የተናገርክ ቀን ሞኝ ነህ ይሉሀል፡
ለክፋት ነው እንጂ፤
ህልምና ፀባይህ ጠፍቷቸው መስሎሀል⁉️

በፅናት ታግሰህ ከተሰወርካቸው፡
እሽ ይሁን ብለህ ወዳ ስትርቃቸው፡
በዜና ይመጣል የሴራ ሸፍጣቸው፡
ይህም ነገር ሆኖ ምንም ባትላቸው፡
የደበቁት ክፋት ሰላም ሲነሳቸው፡
ስምህን ማጥፋት ነው ደስታ እሚሰጣቸው‼️
በዚህ ልክ ክፋት ግን ምን አረካቸው..⁉️

መቼም ሰው ነህና በልብህ ላይ ፅፈህ፡
መንገድክን ስትቀጥል ብዙ ህመም አልፈህ፡
እሽ ይሁን ብለህ ዝቅ ስትል ደግሞ፡
መጣብን ይሉሀል ከኛ ጋር አዝግሞ፡
ብቻ የሰው ፀባይ አይገባም ፈፅሞ፡

የዚህ አይነት ፀባይ ቤት የሰራባቸው፡
ለቁጥር የበዙ እጂግ እልፎች ናቸው፡
በጂምላ እንዳልፈርጅ አሉ እሚረጋጉ፡
ክፉዎችን እንጂ አይደለም ደጋጉ፡
አለ እሚዝረበረብ የክፋት ልጋጉ፡
አንዳንዱ በበደል ይረካል በጂጉ፡
አሉ በየ ቦታው የሚሰገሰጉ፡
እንዳይታወቁ አይሆኑም በወጉ፡

እናም ከሰማኸኝ ይህን እልሀለሁ፡
በዚህች አጭር እድሜ ብዙ አስተውያለሁ፡
ማንም ምንም ይበል በሰው ወሬ አትደፍርስ፡
ምቀኞችን ሰምተህ ህልምህን አታፍርስ፡
በጌታህ ተመካ ደግነት አትቀንስ፡
በማንም ውድቀት ላይ አትደሳ አትደንስ፡
አንተም ተረኛ ነህ አስተንትን ይልቅስ፡
ዛሬን በእምነትህ ኑር ነገን በተስፋ አልቅስ፡

የሰው ልጅ ምንም ሁን የሚልህ አያጣም፡
ከአንተ አንፃር ጉዳዩ ምንም ባይጣጣም፡
ባልሆንከው ማንነት ጌታችን አይቀጣም፡

......እናም የምመክርህ....

ጠላቶችህ ሁሉ፤
እሾህ ነው እያሉ ሲያደርጉህ አጀንዳ፡
እንደዚህ በላቸው፤
ከነ እሾሁም ቢሆን ውብ ነው ፅጌረዳ፡
በማለት መልሰህ፤
ተራመድ በደስታ አትሁን ምድረ-በዳ፡
እንጂ ለምቀኞች፤
ምንም አሉኝ ብለህ ውስጥህን አትጉዳ፡

በቃ በአቋም ተጓዝ፤
ለመጣ ለሔደው አትሞክር ማስረዳት፡
ሁሉንም አትመን፤
ጋዛም ያስጠጋችው አይሁድ ነው የከዳት፡
በቤቷ ባስጠጋች፤
ያ ሰው ነው ዛሬ ላይ ጨክኖ የሚያርዳት፡

....አገኘኸኝ...አሁን⁉️

ይህን ሁሉ ነገር የምደረድረው፡
ቃላት እየመረጥኩ ቤት የምሰድረው፡
ቢገባህ ብዬ እንጂ ምናልባት ብትነቃ፡
ያለፈው ጊዜማ አልፏልኮ አበቃ፡
መመለስ አትችልም ሰከንድም ደቂቃ፡

......እኔ ግን ልንገርህ.....

አንዳች ትንሽ ፍሬ ምን ቢታጣብኝም፡
ምንም ስነ-መግባር እውቀት ባይኖረኝም፡
ከነ-ወንጀሎቼም አምላኬ አልተወኝም፡
ትናትናም አልሸሸኝም ሳማርረዉ በአንደበቴ፡
ደጋፊ አጥቶ ሲዝለፈለፍ ውብ ጉልበቴ፡
ዛሬም አለ ተነስ ብሎ እያነሳኝ ከዉድቀቴ፡
እዚህ ድረስ ከነገርኩህ ይህ ነውና የኔ እውቀቴ፡

የፈፀምከው ህፀፅ ሆኖ፤
አዕምሮህን ጠይቅና ህሌናህን ይቆርቁርህ፡
እንደ ሰው ሁን በሰውነት፤
በባለፈው ተፀፅተህ የሰራኸው ግፍ ይምረርህ፡
በመርህ ተራመድ፤
በማስተዋል ላይ ቁም አንድ አቋም ይኑርህ፡

....በኑረዲን አል-ዓረብ....
ረቢዑ-ሳኒ 20/1448

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍51
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማለዳ

በማለዳው ንቃ በወፍ ዜማ ታጀብ፡
አንበሳ ሆነህ ኑር የህይወትን ወጀብ፡
ለእውነት ብቻ ታገል በሶብር ተዓጀብ፡
ቅጥረኛ እየሆኑ ዋሽቶ ከመታጀብ፡

ከመኝታው ነቅቶ ሁሉም ሲሰናዳ፡
መመከት እንድትችል የፈተናን ናዳ፡
ጀግና ሁን አንበሳ ተነስ በማለዳ፡

....ኑር....

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍87
(⓫)من أصول عقيدة أهل السنة
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
◎አቂደቱ አህሊ-ሱና◎

     👉ክፍል =⓫

«የኢማን ትርጓሜ በአህለ-ሱና አረዳድ»

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍34
«إنّما الدنيا صَبر ساعة ، والجنّة دَار الأفراحِ»

فَيا ربّ يومًا بلا ذنب،
يا ربّ اجعلنا كما تُحب وترضىٰ

www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍42
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሒ ራጂዑን

...ለዚህች ድንገት ለምንሰናበታት እድሜ ......

«አሏህ ይዘንልህ ወንድሜዋ!!»

«ዛሬ አንድ ወንድሜ መዲና ላይ በመኪና አደጋ እንደሞተ ሰማሁ ወላሒ ማመን አቃተኝ ያ አሏህ»

...ሁላችንም ወደዛው ነን በቀጠሮ ነው የምንለያየው...

...የሚገርመው «ሚስቱን ሊቀበል ደፋ-ቀና እያለ ነበር...ሚስቱ ልትመጣ በረራ ብቻ ነበር የቀራት....አሏህ የሻውን ሰራ ...።

👉ያ አሏህ እሽ ምንድነው የምትባለው⁉️
👍266
መካ እና ጂዳወች ተጠንቀቁ
---------------------------

«አንድ ሀበሻ አረብ ገድሎ ከፍተኛ ተፍቲሽ አለ ተጠንቀቁ‼️»

በመጀመሪያ የመጣነውኮ ዝቅ ብለን ልንሰራ እና አሏህ ከሻልን ተለውጠን ሀገራችን ልንገባ ነው አይደል⁉️

👉ታዲያ ምነው በዚህ ልክ...ወገን⁉️

እረዳለሁ ልንበደል እና የተለያዩ ነገሮች ሊደርሱብን ይችላሉ ግን #አረብ_ሀገር ተቀምጠህ #ስደተኛ ሆነህ #አረብን_መግደል ሰይጣናዊ አባዜ ነው።

«ሲጀመር ሰው መግደልን እንደ መፍትሔና እንደ ቀላል ብሎም እንደ ጀግንነት የሚመለከት ብቸኛ ህዝብ ይህ የኛ ህዝብ ይመስለኛል...ማንስ ቢሆን ለምን ይገደል..እንዴ⁉️»


እንደት አይነት አዕምሮ ነው በዚህ ርቀት #ግድያ_ድረስ የሚወስደን ነገር ምንድነው በአሏህ 👉#ይህንን_ኸረ_ገዳይ የሚባል #ፉከራና_ድንፋታ ብናቆመውና #በሰላማዊ መንገድ ከሁሉ ተግባብተንና ተስማምተን ብንኖር የተሻለ ነው።

አሏህ እንደዚህ ይላል፦

أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ
أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا
وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا


እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ጻፍን፡፡

በአንዳንድ መጥፎ ሰዎች የስንት ሚስኪኖች መከራና ስቃይ ችግርና እንግልት አልፎም እንደ ሀገር በመጥፎ እና በጥርጣሬ አይን እንድንታይ የምታደርጉ ወንድሞች እባካችሁ።

ከተበደላችሁ በመረጃ ክሰሱ በተለይ እዚህ ሀገር መረጃ ካለህ #ፍትህ አለ ብዬ አስባለሁ ...በርግጥ ፕሮሰሱ አድካሚ ሊሆን ይችላል ግን ለፍርድ ከቀረብክ ፍትህ ታገኛለህ ...።

ይህ አማራጭ እያለ ግድያን እንደ አማራጭ መጠቀም ግን እጂግ ዘግናኝና ለአንድ ሰው ብቻ ሳይሆን ለመላሁ ኢትዮጲያዊያን ስደተኛ ሰላም እየነሳችሁ እንደሆነ አውቃችሁ ከዚህ ድርጊት ብትቆጠቡ መጠቆም እፈልጋለሁ።

«ይገባኛል በደል ብዙ ያደርጋል ፣ለመጥፎ ውሳኔ ሰይጣንም ነፍስያም ይጨማመራሉ ግን በዚህ ርቀት መጓዝ በፍፁም ትክክል አይደለምና እባካችሁ.... በስንት መከራ ውስጥ አልፈው እዚህች ሀገር ተደብቀው የቤተሰባቸውን ሪዝቅ የሚያገኟት የሚሰብቡ እልፍ ሰላማዊ ሰወች አሉና ለሌሎቹ ስንል እንረጋጋ እባካችሁ እላለሁ።

👉ለማንኛውም ጥንቃቄ አድርጉ‼️

መካ እና ጂዳ አካባቢ ያላችሁ ወንድሞች በጣም ተጠንቀቁ በሰሞኑን አንድ ሀበሻ አረብ ገድሎ ተፍቲሽ እጂግ ከፍቷል እና እባካችሁ።

http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
http://www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍163
Audio
«የሐራኑ መብረቅ»

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ

👉እስኪ በአንድ ቃል ግለጿቸው⁉️

🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍37
👉የአረብ ሀገር ሴት....!?

«በጂምላ አትፍረዱ»

አውቃለሁ አንዳንዶች ሊኖሩ ይችላል፡
የጂምላ ፍርድ ግን በጣሙን ያስጠላል፡
ሁሉን ስደተኛ መስደብ ምን ይባላል‼️

ቁሞ ቀር ሆነህ ቀርተህ ስታበቃ፡
ታመነዥካለህ የዲኗን ጠበቃ!?
ማን ነህ አንተ ደግሞ የማነህ ቅዠታም፡
የአረብ ሀገር ሴት አታገባም ሽንታም፡
ፅኑ ነች በእምነቷ በአቂዳ ነች ሀብታም፡
በአንተ አይነት ሰው ትችት ፈፅሞ አትረታም፡
የመርህ ጀግና ነች ካገባች አትፈታም፡

.....እናም የስደት ሴት...

አስመሳዮች እንጂ የዋህ የሚያደርጓት፡
ለገንዘቧ ቀርበው በግፍ የሚወጓት፡
ለእምነቷ እምትለፋ ጀግና ነች አይናፋር፡
ፍትህን የማያውቅ አታገባም ደፋር፡
ለቸገረው ሁሉ አዝና ስለረዳች፡
ላለቀሰ ሁሉ እንባ ስለቀዳች፡

ለምን ይሆን ንቀት የሚወጥራችሁ፡
አንዳንድ ወንድሞች ግን ምንድነው ስራችሁ፡
ስደት የቀመሰች እህትም የላችሁ⁉️

እሷን ከማገባ ጭራሽ ቆሜ ልቅር⁉️
ወሬኛ ቀጣፊ የነገር ጥንቅር፡
ሲጀመር ያንተ አይነት አታገባም እሷ፡
በተውሒድ የፀናች የነጋች ነች ነፍሷ፡

.....ቁሜ ልቅር...⁉️

እንደዚህ እያሉ«የአረብ ሀገር እንስቶችን» ለሚዲያ ፍጆታ የሚያቀርቡ #ነፈዝ የሆኑ ወንዶችን ብገርባቸው ነውር ይሆናል⁉️

በአንዳንድ መጥፎወች ሁሉንም መወረፍ፡
የጥላቻ ቃላት ከአዕምሮ ላይ መዝረፍ፡
ከወንዶች አንደበት ይህ አይጠበቅም፡
ካልሆነ በስተቀር መጥፎ ጫት የሚቅም፡
የቢዲዓ ሙሪድ ጥመት የሚለቅም፡
ከወንዶች አንደበት ይሄ ቃል አይወጣም፡
ምንም ቢለባብስ ቀሚስና ጥምጣም፡

የአረብ ሀገርን ሴት ላታሸማቅቋት፡
እሷን ላታስገቡ በክፋታችሁ ቋት፡
ያለችበትን ጉድ ግፏን ሳትረዱ፡
ሁሉን ጠቅልላችሁ በጂምላ አትፍረዱ‼️

...ኑር...✍️
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
www.tg-me.com/nuredinal_arebi
👍153
2025/10/21 21:49:38
Back to Top
HTML Embed Code: