ወር በገባ በ27 የሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር ወርኃዊ በዓሉ ይከበራል ።
ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ በራእይ ተገልጦ
❤ በ8ኛው ሺህ በሀገራችን ኢትዮጵያ ስለሚመጣው ደገኛ ንጉሥ
❤ ስለ ሀገራችን የኢትዮጵያ ትንሣኤና ደጉ ዘመን
❤ በስምንተኛው ሺህ ዘመን በዓለም ስለሚሆነው
❤ ስለመጨረሻው ዘመን ምልክቶች ሌሎችንም .....
በመናገር የሚታወቀው ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር ነው።
በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ በራእይ ተገልጦ ‹‹ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ፤
በ8ኛው ሺህ ዘመን በሀገራችን በኢትዮጵያና
በግብፅ እንዲሁም
በቁስጥንጥንያና
በሮም ወደፊት የሚሆነውን ነገር ሁሉ
ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር
❤በግልጽ የተናገረው "ትንቢቱና ሙሉው ገድለ ቅዱስ ፊቅጦር"
❤"ከታላቁና ከሙሉው
1ኛ የ12 ወር ፤
2ኛ ጌታ የሰጠው አስደናቂ ቃልኪዳን፤
3ኛ ሰማዕቱ ሚናስ ያደረገው ተአምር ፤
4ኛ ሁለቱ መልክዐ ቅዱስ ሚናስ ከተካተቱበት "
ከገድለ ቅዱስ ሚናስ"ጋር ታትሞ›› ይገኛል ፡፡
ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር ሚያዝያ 27 ቀን በሰማዕትነት ካረፈ ከብዙ ዘመን በኋላ በራእይ ተገልጦ ከጥቂት ዘመናት በኋላ እግዚአብሔር
❤በኢትዮጵያ ሀገር ክርስቶስን የሚወድ ቅዱስ ሰው ያነግሣል፡፡አረማውያንም በእርሱ እጅ ይደመሰሳሉ፡፡
ከዚህ በኋላ ወደ ግብፅ ሀገር ሄዶ አረማውያንና መንግሥታቸውን ሁሉ ያጠፋል፡፡ እግዚአብሔር በቍስጥንጥንያ እርሱን የሚወድ ስሙ
❤" ትውልደ አንበሳ"የተባለ ሰው ያነግሳል፡፡
❤ከኢትዮጵያ ንጉሥ ጋር ይገናኝ ዘንድ ይመጣል፡፡ በግብፅ መሀል ቦታ ላይ ይገናኛሉ፡፡ ከእርሱ ጋርም የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳትና የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ይገናኛሉ፡፡
❤የኢትዮጵያ ንጉሥ ሠራዊቱን በደቡብ በኩል ትቶ የቍስጥንጥንያም ንጉሥ ሠራዊቱን በሰሜን በኩል ትቶ ሁለቱ ነገሥታትና ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት ተገናኝተው እርስ በእርሳቸው ሰላምታ ይሰጣጣሉ፤
❤ሊቃነ ጳጳሳቶቹ በመንበራቸው ላይ ተቀምጠው ነገሥታቱን ‹በየመንበራችሁ ላይ ተቀመጡ› ይሏቸዋል፡፡
የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ‹የእኛ ሃይማኖት ትበልጣለች› ይላል፡፡
የእስክንድሪያውም ሊቀ ጳጳሳት ‹እግዚአብሔር የሰጠኝን ቃል እኔ እነግራችኋለሁ› ይላል፡፡
❤ ሁለቱ ነገሥታትም ‹አባታችን በል ንገረን› ይሉታል፡፡ ‹የአባ ሲኖዳ ወደምትሆን ወደዚህች ታላቅ ቤተክርስቲያን ገብተን በአንዲት ታቦት ላይ እኔ እቀድሳለሁ፣
ይህ ባልደረባዬ ሊቀ ጳጳሳት በአንዲቷ ታቦት ላይ ይቀድስ፤ ሁሉም ሕዝብ ሠራዊቶቻችሁም መጥተው ይመልከቱ› ይላል፡፡ ‹መንፈስ ቅዱስ እያያችሁት ከሁለታችን በአንዱ ቁርባን ላይ ከወረደ በዚያ ሃይማኖት ሁላችን እንሂድ፣ ሃይማኖቷም ትታወቃለች ቀንታለችና› ይላቸዋል፡፡
ሁለቱ ነገሥታት ‹እሺ በዚህ ቃል ተስማምተናል፣ የእግዚአብሔር ምክር ናትና› ይሉታል፡፡ ያን ጊዜ ሁለቱ ነገሥታትና ሊቃነ ጳጳሳት ሠራዊቶቻቸውም ሁሉ ካህናቶቻቸውም፣ ሕዝቡም ወደዚህች ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ይገባሉ፡፡
ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳትም በሁለቱ ታቦታት ላይ ይቀድሳሉ፡፡ በዚያ ያሉ ሁሉ እያዩ መንፈስ ቅዱስ በነጭ ርግብ አምሳል ከብርሃን ጋር የእስክንድሪያው ሊቀ ጳጳሳት በቀደሰው ቍርባን ላይ ይወርዳል፡፡
❤ያን ጊዜ የኢትዮጵያ ንጉሥ ይደሰታል፣ የእርሱም ሊቀ ጳጳሳት ነውና፡፡ በእግዚአብሔር ፊትም የእርሱ የሃይማኖት ሕግ የተወደደ ይሆናል፡፡ 👑የሮም ንጉሥ ግን ........(የበለጠ ከገድለ ሚናስ ጋር የታተመውን ገድለ ፊቅጦርን ያንብቡት)
የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ ፊቅጦር ረድኤት በረከቱ ይዋልብን ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
ምንጭ ከገድለ ሚናስ ጋር የታተመው
❤1ኛ የ12 ወር ፤
❤2ኛ ጌታ የሰጠው አስደናቂ ቃልኪዳን፤
❤3ኛ ሰማዕቱ ያደረገው ተአምር ፤
❤4ኛ ሁለቱ መልክዐ ቅዱስ ሚናስ የተካተቱበት "
❤ሙሉውና ታላቁ ገድለ ቅዱስ ፊቅጦር "

👍22❤4
ቤዛ ኵሉ አለም ዮም ተወልደ
የአለም ሁሉ መድሀኒት ዛሬ ተወለደ
እንኳን ለብርሀነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ መልካም የልደት በዐል

❤43👍11
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - 🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽 🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴:
የመገለጥ ሃይማኖት በአስተርእዮ
~~~> በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
+++ ሃይማኖት የምንቀበለውና የምንጠብቀው እንጂየምንሠራውና የምናሻሽለው አይደለም +++
ከታኅሣሥ 29 ቀን ጀምሮ እስከ ዐቢይ ጾም መግቢያ ድረስ ያለው ወቅት /ጊዜ/ ዘመነ አስተርእዮ /የመገለጥ ወራት/ እየተባለ ይጠራል፡፡ በታኅሣሥ 29 ቀን የጌታችን ልደት ስለሆነ በዚህ አምላክ በሥጋ የተገለጠበት በዓል ይከበራል፡፡ ጥር 11 ቀን ደግሞ በጌታችን ጥምቀት የሥላሴ አንድነት ሦስትነት በይፋ የተገለጠበት ነው፡፡ ጥር 12 ቀን ደግሞ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ማስተማር በጀመረበት ጊዜ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን በመለወጥ አምላክነቱን በይፋ የገለጠበት በዓል ነው፡፡ እነዚህ ሦስት ዓበይት መገለጦች ወቅቱን በአጠቃላይ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የተገለጠበትን መታሰቢያ አደረጉት፡፡
አምልኮተ እግዚአብሔርን ትክክለኛ ሃይማኖት ከሚያሰኙት መሠረታዊ ነጥቦች ዋነኛውና ቀዳሚው የመገለጥ ሃይማኖት /Revealed Religion/ መሆኑ ነው፡፡
የአምላክን ማንነት በእምነት ለሚመረምር ሰው አምላክ ያልተፈጠረና ሁሉን የፈጠረ፣ የማይወሰን፣ በጊዜም የማይለካ ማለት ከጊዜና ቦታ ውጭ /Out of space www.tg-me.com/ መሆኑ ሊጠረጠር አይችልም፡፡ስለዚህ አምላክ ከቦታና ጊዜ ውጭ ከሆነና በሁሉም ቦታ ደግሞ የመላ ወይም ምሉዕ ከሆነ /Omni present/ በቦታ ጊዜ ውስጥ ያሉ ፍጥረታት አምላክን ሊያዩት አይቻላቸውም ማለት ነው፡፡ ይህን ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረትነት እናብራራው፡፡ «ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም «ዘመናትን» በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን» /ዕብ 1፥1/ በሚለው የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ውስጥ «ዘመን» ወይም ጊዜ ፍጥረት መሆኑን በግልጽ እንረዳለን፡፡
መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞንም «ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ ሰባት ምሰሶዎችንም አቆመች» /ምሳ 9፥1/ በማለት በምሳሌው ተጨማሪ ምስክርነት ሰጥቷል፡፡ሊቃውንት በትርጓሜ እንዳብራሩት «ጥበብ» የተባለ ጌታ «ቤት» የተባለ ዓለምን ፈጥሮአል፡፡ ዓለሙ የጸናባቸው «ሰባት ምሰሶዎች» ደግሞ ዓለምን እስከ ዕለተ ምጽአት የሚያጸኑት አዕዋዳት ሰባቱ ዕለታት ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ዓለምን የአጸናው ጊዜ ነው ማለት ነው፡፡ሙሴ «በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ» ዘፍ 1፥1 ባለበት የሥነ ፍጥረት መጽሐፍም ጨለማ የነበረ መሆኑን ከተረከልን በኋላ « ብርሃን ይሁን አለ» ይልና ጠዋትም ሆነ ማታም ሆነ አንድ ቀን በማለት ዓለምና ጊዜ አንድ ላይ መፈጠራቸውን ይነግረናል፡፡ ከዚያም አስከትሎ የቀሪዎቹን የአምስት ቀን ፍጥረታትና የመጨረሻዋን /የሰባተኛውን/ ዕለት ዕረፍትነት ነግሮን ያጠቃልላል፡፡ ከዚያ በኋላ ዓለም ይቀጥላል፤ የዕለታቱ ዑደትም ይቀጥላል፡፡ በሰባት ዕለት አጸናው ማለት ይህ ነው፡፡
ሁሉንም እርሱ እንደፈጠረ ደግሞ « ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳች እንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለም፤» ዮሐ 1፥3 «የሚታዩትና የማይታዩት ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በእርሱ ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል» /ቆላ.1፥15-17/ ተብሎ ስለተጻፈ አምላክ በቅዱሳት መጻሕፍትም ከቦታ ጊዜ ውጭ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡
ፈጣሪ ከቦታ ጊዜ ውጭ ከሆነ ሊያየው የሚቻለው ፍጥረት የለም ማለት ነው፡፡ ወንጌላዊ ዮሐንስ «መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም» /ዮሐ 1፥18/ እንዳለ፡፡ በመቃብያንም «አንተን ሁሉን ታያለህ እንጂ አንተን ማየት የሚችል የለም» ተብሎ ተጽፎአል፡፡ 3ኛ መቃ.9፥26 ቅዱስ ጳውሎስም «ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያየውም አይቻለውም» /1ኛ ጢሞ.6፥16/ ሲል እንዳጸናው ለፍጥረት እግዚአብሔርን ማየት አይቻልም፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ እርሱን በምርምር ማወቅም አይቻልም፡፡ አካሉ ረቂቅና ምሉዕ፣ በቦታ ጊዜ የማይወሰን ከሆነ ማን በምን ሊመረምረው ይችላል፡፡ በግብሩ በባሕርዩ እንመርምረው እንዳንል በእኛ ኅሊናችን ኅሊናን የፈጠረውን መመርመር ሸክላ ሠሪውን ለማወቅ ከመጣር የበለጠ የማይቻል ነው፡፡ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት «ወረሰየ ጽልመተ ምስዋሮ፤ ጨለማን መሰወሪያው አደረገ» እንዳለው ሊመረመር አይችልም፡፡ በጨለማ ማየት እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔር ባሕርይ ሊመረመር የማይቻል ነውና፡፡
ታዲያ ፈጣሪን እንዴት ማወቅ ይቻላል? የሚለው ጥያቄ በዚህ ጊዜ ሊነሳ የሚገባ ነው፡፡ መልሱም ቀላል ነው፡፡ የምናውቀው እርሱ ራሱ ሲገለጥልንና ሲገልጥልን ብቻ ነው፡፡ ከተገለጠበትና ከገለጠውም መጠን በላይ ማወቅ አይቻልም፡፡
ስለዚህ የእውነተኛ ሃይማኖትነት መሠረታዊ ማረጋገጫዎች መካከል አንዱና ዋናው መገለጥ ነው ያልነው ለዚህ ነው፡፡
እርሱ ራሱን ባይገልጥ ማን በምን መንገድ ሊያውቀው ይችላል፡፡ አምልኮተ እግዚአብሔርን በሦስቱም ሕግጋት /በሕገ ልቡና፣ በሕገ ኦሪት፣ በሕገ ወንጌል/ ብንመረምረው መንገዱ ሁሉ መገለጥ ብቻ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እግዚአብሔር ራሱን ለመላእክት በመፍጠር ገለጠላቸው፡፡ ለአዳም ተገለጠለት፣ አነጋገረው፣ ትእዛዝም ሰጠው፡፡ ከበደለውም በኋላ ፈለገው፤ አነጋገረው፤... የሚሉት በሙሉ መገለጥን የሚያመላክቱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እግዚአብሔር አዳምን «አዳም አዳም ወዴት ነህ?» አለው የሚለው ያለበትን ያለማወቅ ሳይሆን አዳም ከበደለም በኋላ ለኃጢአተኛ ባሕርዩ በሚስማማ ሁኔታ መገለጡን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ከዚህም በኋላ በሕገ ልቡና ለአባቶች ሁሉ በየዘመናቸው እንደ ሃይማኖታቸው ጽናት እንደ አእምሮአቸው ስፋት ሲገለጥላቸው ኖርአል፡፡ «በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት» ተብሎ ስለ አብርሃም የተጻፈው ነው፤ /ዘፍ. 18፥1/ የሚለው የዚህ ማረጋገጫ ነው፡፡ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በየዘመኑ ለነበሩ ሰዎች የተገለጠበት መንገድ የተለያየ ከጥንት ወደ አሁን ጊዜ ስንመለከተውም የበለጠ እየተገለጠ እንደመጣ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ ለምሳሌ የሕገ ኦሪት መሥራች ለምንለው ለሙሴ ሲገለጥለት ለአብርሃም ከገለጠለት በላይ ለእርሱ እንደገለጸለት ነግሮታል።
«እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፣ አለውም እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአብርሃምም፣ ለይስሐቅም፣ ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፣ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር» /ዘጸ. 6፥2-3/ ተብሎ የተጻፈው ሌላው ቀርቶ « እግዚአብሔር» የሚለው ስም እንኳ ከዚያ በፊት ላሉት እንዳልታወቀ ያረጋግጥልናል፡፡ ስለዚህ «እግዚአብሔር» የሚለውና ሌሎች ብዙ ነገሮች ከሕገ ኦሪት በኋላ እንደተገለጡ መጽሐፍ ቅዱስ ሰፊ ምስክርነት ይሰጠናል፡፡ ይልቁንም ደግሞ ምሳሌያዊ /Allegorical/ በሆነ መንገድ የተገለጡትን ስንመለከት እጅግ እንደነቃለን፡፡

👍11
እግዚአብሔር ለነቢያቱም በተለያየ መንገድ ተገልጦላቸዋል፡፡ ለሙሴ በሐመልማል ወነበልባል /ዘጸ.3፥1/ ለኢሳይያስ በአምሳለ አረጋዊ ነዋሕ፤ /ኢሳ. 6፥1/ ለዳንኤል በአምሳለ ዕብን ቅውም ከረጂም ተራራ ላይ በተፈነቀለ ትልቅ ድንጋይ / ዳን 9፥ /... ለሌሎቹም በብዙ ኅብርና አምሳል ተገልጦላቸዋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ « በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና» ያለው ይህንኑ ነው፡፡ /ዕብ.1፥1/ በብሉይ ኪዳን የተጻፉ መጻሕፍትን በሙሉ ስንመለከታቸው «እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤...» በሚል መግቢያ የሚጀምሩ ናቸው፡፡ ይህም ቃልና ትምህርቱ በሙሉ ከእግዚአብሔር የተሰጠ እንጂ የእነርሱ ላለመሆኑ በሌላ አነጋገር የመገለጥ ሃይማኖት፤ ትምህርት መሆኑን እየደጋገመ ያረጋግጥልናል፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ በብሉይ ኪዳን ብዙ ነቢያት ተነሥተው ቢያስተምሩም ብዙ መጻሕፍት ቢጽፉም የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት ግን እጅግ ምስጢራዊና ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ እንጂ በግልጽ አልታወቀም ነበር፡፡ ምክንያቱም በሚገባው መንገድ ራሱን ገና አልገለጠም ነበርና፡፡ ለአብርሃም የተገለጡት ሦስት ሰዎች፤ «ኑ እንውረድ፣» የሚሉት ዓይነት ቃላትና ይህንኑ ከሚመስሉት ጥቅሶች በቀር በጊዜው /ብሉይ ዘመን/ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ስለ እግዚአብሔር የአንድነትና የሦስት ምስጢር በበቂው አልተገለጠላቸውም፡፡ በመጽሐፈ ኢያሱ የተጻፈውንና ስለ እሥራኤል የዮርዳኖስ ወንዝ ተሻግሮ ከምድረ ርስትን መርገጥን በተመለከተ «ሙሴም እንዳዘዛቸው የሮቤል ልጆች፣ የጋድም ልጆች፣ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ተሰልፈው በእሥራኤል ልጆች ፊት ተሻገሩ፡፡» የሚል ተጽፎአል /ኢያ.4፥17/፡፡ አንድ የጥንት የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ይህን ሲተረጉመው እነዚህ ቀድመው የተሻገሩት ከአሥራ ሁለቱ ነገድ ሁለቱ ነገድ በሙሉና ሦስተኛው ከፊሉ መሆኑ በብሉይ ኪዳን ዘመን ስለነበረው የሥላሴ ዕውቀት ምሳሌ ነው፡፡ በዚያ ዘመን ስለ አብና ስለወልድ በመጠኑ ስለመንፈስ ቅዱስ ደግሞ እጅግ በብዥታ ያውቁ ነበር፡፡ ሦስተኛው ነገድ በከፊል የተሻገረው ለዚህ ነው፡፡ ሦስቱ ነገድ እንኳን አለመሟላቱም በዘመኑ ምስጢረ ሥላሴ በከፊል በምሳሌና በጥላ ብቻ ይታወቅ የነበረ ስለመሆኑ አሰረጂ ነው በማለት ይተረጉማል፡፡በርግጥም ቀደም ብለን እንዳየነውም የእግዚአብሔር መገለጥ እየጨመረ እየጨመረ እንደመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር ነው፡፡
የብሉይ ኪዳን ዘመን መገለጥ እየጨመረ እየጨመረ ከመጣ በኋላ ፍጹም መገለጥ ሲመጣ ያኛው የጥላውና የምሳሌው መገለጥ ይደመደማል፡፡ ፍጹሙ መገለጥም የአምላክ ሰው ሆኖ መገለጥ ነው፡፡ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ «መጀመሪያ ቃል ነበረ፣...» ካለ በኋላ «ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር፡፡ በዓለም ነበረ ዓለሙም በእርሱ ሆነ ዓለሙም አላወቀውም» ዳግመኛም ከዚያው አስከትሎ «ቃልም ሥጋ ሆነ፣ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነውን ክብሩን አየን» ሲል መገለጡን አበሠረ፤ /ዮሐ 1፥1-18/፡፡ይህን መገለጥ ደግሞ እንኳን ሰዎች መላእክትም ተግተው ይሹት ነበረ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ፤ «ለእናንተ ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤ ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ» /1ኛ ጴጥ. 1፥1-12/ ሲል እንደገለጸው፤ መላእክቱ የአምላክን መገለጥ ለማየት እጅግ ጓጉተው ነበር፡፡ ምክንያቱም እነርሱም ቢሆኑ አምላክን ለማየት ዕድል የሚያገኙት ሰው ሆኖ ሲገለጥ ብቻ ነውና፡፡ቅዱስ ጳውሎስ፤ «እግዚአብሔርንም የመምስል ምስጢር ያለጥርጥር ታላቅ ነው፡፡ በሥጋ የተገለጠ፣ በመንፈስ የጸደቀ፣ ለመላእክት የታየ፣ በአሕዛብ የተሰበከ፣ በዓለም የታመነ፣ በክብር ያረገ» /1ኛጢሞ.3፥16/ በማለት ለመላእክት የታየው በሥጋ በመገለጡ እንደሆነ አረጋግጦልናል፡፡
እነርሱም ምስጢረ ሥጋዌን ከሰው በላይ አጣጥመው ተጠቅመውበታል፡፡ በብሥራቱ ቅዱስ ገብርኤል ብቻ ቢሣተፍም በልደቱ ጊዜ ግን ብዙዎች መላአክት በአንድነት ለእረኞች ለማብሠር ታድለዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በመዋዕለ ሥጋዌው ሁሉ እየተላላኩ አምላክን ማየት ጠገቡ፡፡ ሲሰቀልና ሲሞትም በአርምሞ በመደነቅ ተመለከቱ፡፡ ትንሣኤውን አበሠሩ፡፡ የቀሩትም በዕርገቱ ዕለት ሐዋርያትን አረጋግተው ዳግም ምጽአቱን አውጀው ተሰወሩ፡፡ ዳግመኛ ሲመጣ መለከት እየነፉ ከፊት ከፊት እየቀደሙ ከኋላም እየተከተሉ እንደሚመጡም ተጽፎላቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የአምላክ መገለጥ የመላእክት ደስታ ሆነ፡፡ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ፤ እያሉ የዘመሩት ወድደው አይደለም፡፡ ተገልጦ ባዩት ጊዜ ለመደመማቸው ወሰን ቢያጡ ለሰው ያለውንም ፍቅር ይገልጡት ዘንድ ቢሳናቸው፤ ይህን ምስጋና እያጣጣሙ ክብርና ቅድስናቸውን ለራሳቸው አስጨመሩ፡፡
ይሁን እንጂ አምላክ ሰው በመሆኑ ከረቂቃኑ መላእክት ይልቅ የበለጠ የቀረቡት ሰዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ በዘመነ ብሉይ እንደ ነበረው እንደ ሄኖክ፣ እንደ መልከጼዴቅ፣ አብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ፣ ዳዊትና ሰሎሞን፣ ሙሴና ነቢያት ራሳቸውን የቀደሱና ያነጹ ብቻ ሳይሆኑ በኃጢአት የረከሱት እነ ዘኬዎስ፣ ማርያም እንተ ዕፍረት፣ መጻጉዕ፣ በዝሙት የተያዘችው ሴትና ሌሎቹም ሰውነቱን ዳሰሱት፤ አብረውት በሉ ጠጡ፤ . . .፡፡
ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን መገለጡን በሰፊው አሰበችው፤ በተድላ በደስታ፤ በመብልና በመጠጥም ጭምር የምታከብረውም ለዚህ ነው፡፡ ከዚህ መገለጥ በኋላ የተላኩ ሐዋርያትም የትምህርታቸው አቀራረብ ተለወጠ፡፡ እንደ ነቢያት በዚህ መንገድ አየነው፣ እንዲህ ሆኖ ተገለጠልን የሚለው ቀረና ቅዱስ ዮሐንስ እንዳለው፤ «ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም፣ እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ፤ አይተንማል እንመሰክርማለን፤ ከአብ ዘንድ የነበረንም ለእኛም የተገለጠውን፤ የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን» /1ኛዮሐ. 1፥1-3/ እያሉ ለማስተማር ቻሉ፡፡ ከዕርገቱም በኋላ ቢሆን እርሱ ከቅዱሳኑ ተሰውሮ አያውቅም፡፡ ይልቁንም ከተዋሕዶ በኋላ ምንታዌ የለምና /ሰው ከሆነ በኋላ መታየቱ፣ መወሰኑ፣ መጨበጡ፣ መዳሰሱ አልቀረምና/ በየዘመኑ ይገለጣል፡፡
በየቅዱሳኑ ሕይወት እንደተጻፈው እነ አባ ብሾ/ሶ/ይ እግሩን አጠቡት፣ አዘሉት፡፡ በየዕለቱ ለሰማዕታቱ እየተገለጠ አጸናቸው፤ ጻድቃኑንም ምስጢሩን አብዝቶ ገለጠላቸው፡፡ በየገድላቱም ላይ ቅዱሳኑ ሲያርፉ «ይህን ያህል ቅዱሳኑን አስከትሎ መጣ፤ ነፍሱንም ተቀበለ፣. . .» የመሳሰሉት አገላለጾች ምንኛ ግሩም ናቸው፡፡
አንድ ጊዜ ሰው ሆኖአልና እንደቀድሞው ለነቢያቱ እንዳደረገው ሳይሆን አሁን በሥጋ ተገልጦአልና በየጊዜው ይመጣል፣ ይታያል፣ ይጨበጣል፤ ይዳስሳቸዋል፤ ይስማቸዋል፤ ያወጋቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስን በሮማ አደባባይ «ወዴት ትሔዳለህ?» ብሎ እንደመለሰው፤ በየዘመኑ እየተገለጸ ይመራቸዋል፤ ያነጋግራቸዋልም፡፡ መገለጥ፤ ግሩምና ድንቅ መገለጥ፤ ሃይማኖቱም የመገለጥ፡፡ እርሱ ራሱ «ይህ ዛሬ እናንተ የምታዩትን ብዙ ነቢያት ሊያዩ ወደው አላዩም፤ እናንተ የምትሰሙትን ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም፤ የእናንተ ግን ያዩ ዓይኖቻችሁ፤ የሰሙ ጆሮቻችሁ የተመሰገኑ ናቸው» እንዳለ ፤ የሐዲስ ኪዳን፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ባሕታውያን ስውራን ሁሉ ምን ያህል የተመሰገኑ

👍9❤1
ናቸው፡፡ በየዕለቱ ጌታቸውን ያዩታልና፤ ለዚህም ተጠርተዋልና፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ልዩ የሚያደርጋት ብቻ ሳይሆን ከትክክለኛነቷ ማረጋገጫዎች አሁንም ዋነኛዋ መገለጡ ነው፡፡
የሌሎቹ በተለይም ከኢንዱስትሪው አብዮት በኋላ የተነሡ የክርስትና ክፍልፋዮች /Denominations/ ሁሉ መሠረተ እምነታቸው የሚዋቀረው በዩኒቨርስቲዎችና በየተቋማቱ ባሉ ምሁራኖቻቸው አስተምህሮ በጠረጴዛ ዙሪያ ነው፡፡ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚመሠረተው ግን በገዳማውያን ቅዱሳን መገለጥ ላይ ነው፡፡ ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ሊቃውንቱ ሁሉ በመማር ብቻ ሳይሆን በገዳም ተወስነው፣ ሱባኤ ገብተው፣ በእርሱ መገለጥ የተሰወረ ምስጢር ይገለጥላቸዋል፤ የረቀቀው ይጎላላቸዋል፡፡ ያንን ብቻ ያስተምራሉ፤ እርሱንም ብቻ ይዘን እናስተምራለን፤ በተገለጠውም መሠረት እንኖራለን፡፡
በእኛ ሀገር እንኳን እነ ቅዱስ ያሬድ፤ አባ ጊዮርጊስ፣ አባ ዜና ማርቆስ፤ አባ ተክለሃይማኖት፣. . . ሁሉም በሱባኤ፣ በገዳም፣ በምናኔ፣ በተጋድሎ ተወስነው፤ በተገለጠውና በሚገልጥላቸው መንገድ ብቻ ተጓዙ፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትም የሚያረጋግጡልን ይህንኑ ብቻ ነው፡፡ ሃይማኖትን እንቀበለዋለን ከዚያም እንጠብቀዋለን እንጂ ልንሠራው አንችልም፡፡ የያዕቆብ ወንድም ቅዱስ ይሁዳ «ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችኋለሁ» /ይሁ.1፥3/ ሲል እንደገለጸልን፤ ሃይማኖት ለቅዱሳን በመገለጥ የተሰጠች እንጂ የተሠራች አይደለችም፡፡
ጌታችንም በወንጌል «ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው፡፡ የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ ቃልህንም ጠብቀዋል፡፡ የሰጠኸኝን ሁሉ ከአንተ እንደሆነ ያውቃሉ፤ የሰጠኸኝ ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት. . .» /ዮሐ.17፥22/ ሲል እንዳስተማረው፤ ክርስትና የተቀበልነውና የምንጠብቀው እንጂ የሠራነውና የምናሻሽለው አይደለም፡፡ በዚያ ጊዜ ያልገለጸልንንም «የምነግራችሁ ብዙ ነገር አለ፤ አሁን ግን ልትሸከሙት አትችሉም፤ መንፈስ ቅዱስ በመጣ ጊዜ ግን እርሱ ሁሉንም ያሳውቃችኋል» የሚል ተስፋን ሰጠን፡፡ መንፈስ ቅዱስም ከእኛ ጋር የሚኖረውም እስከ ዕለተ ምጽአት መሆኑን አረጋገጠልን፡፡ ስለዚህም እስከ ዛሬ ድረስ መንፈሳቸውን ላላረከሱት በየጊዜው ይገለጣል፡፡
ለሐዋርያት ገለጠላቸው፤ ለሊቃውንት ገለጠላቸው፤ ለጻድቃን በየገዳሙ ገለጠላቸው፤ ለየመምህራኑም በየሱባኤያቸው በተቀደሱ ጉባኤዎቻቸው ገለጠላቸው፤ እኛም የተገለጠውን ይዘን እርሱንም እየጠበቅን እንጓዛለን፡፡ ከተገለጠው ውጭ መጓዝም የተወገዘ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ፤ «ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን» /ገላ.1፥8/ በማለት አረጋገጡልን፡፡
ስለዚህም በዘመነ አስተርእዮ ይህን የአምላክን መገለጥ እና የመገለጥን ሃይማኖት የምንዘክርበት ምክንያት፤ ሃይማኖት ሰዎች ያልፈጠሩት ነገር ግን በአምላክ መገለጥና እርሱ በገለጠው ሃይማኖታዊ ዕውቀት ብቻ መጓዝን ማዘከር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡
በተገለጠልን ጸንተን ለቅዱሳን የተሰጠችውን ሃይማኖት ተጉዘንባት ለልጆቻችንም አውርሰናትና ጠብቀናት እንድናልፍ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፤ አሜን፡፡

👍10
ቤተልሔም፣ ዮርዳኖስና ቀራንዮ
ዕርቃኑን የተገኘ!
━━━✦༒⛪༒✦━━━
መኑ የሀበኒ ሥጋሁ ለኢየሱስ
ከመ እክድን ዕቃርኖ በልብስ
ለዘከደነ ዕርቃንየ በዮርዳኖስ
[ በዮርዳኖስ እርቃኔን የሸፈነውን እርቃኑን በልብስ እሸፍን ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ማን በስጠኝ]
የዘፍጥረት መጽሐፍ ቀዳሚ መልእክት እንዲህ የሚል ነው «ወምድርሰ ሀለወት እምትካት ዕራቃ (ምድር ግን ከቀድሞው ራቁትዋን ነበረች) ከአዝርዕት ከአትክል ከሰው የተራቆተች ሆና ባዶ ፣ ከንቱ ሆና ምድረ በዳ ነበረች። [ዘፍ ፩፥፪]
የፍጥረቱ አክሊልና የምድራችን ጌጥ የነበረው ራቁትነቱም በብርሃን መጋረጃ የተሸፈነ የከበረው የሰው ልጅም በበደሉ ምክንያት ከጸጋ ልጅነት ከአምላክ ባለሟልነት ሲርቅ እንደተራቆተ እናያለን "አእመሩ ከመ ዕራቃኒሆሙ እሙንቱ … ዕራቁታቸውን እንደሆኑ አወቁ" [ዘፍ ፫፥፮]
እግዚአብሔርን ለመምሰል ብርሃን ተጎናጽፎ ይኖር የነበረው የሰው ልጅ በበደሉ ምክንያት ዕርቃናቸውን የሚኖሩ እንሰሳትን መሰለ።
“ምንት ውእቱ ተመስሎ እንስሳ ዘእንበለ ተከሥቶ ዕርቃኑ ማእከለ ዕፀዊሃ ለገነት ሶበ ነፍጸ አጽፈ ብርሃን ዘላዕሌሁ ኀደጎ አጽፈ ብርሃን ⇨ በገነት ዛፎች መካከል ዕርቃኑን ሆኖ ከመተየት በስተቀር እንስሳን መምሰል ምንድ ነው? የብርሃን ልብስ ከበላዩ ላይ በተገፈፈ ጊዜ የብርሃን መጐናጸፊየው ተለየው” (መጽሐፈ ምሥጢር)
በሠርክ በድምጸ ሰኮና ብእሲ ‘እንደምን ባለ አነዋዋር አላችሁ ይሆን ? በክብር ወይስ በኃሣር ? ’ እያለ ፈልጎ አገኛቸውና ስለመተላለፋቸው ፈርዶ ከቀደመ ክብራቸው አውርዶ ከገነት አስወጣቸው፤ ያን ጊዜ በጊዜአዊነት "ወገብረ እግዚአብሔር ለአዳም ወለብእሲቱ አእዳለ ዘማእስ ወአልበሶሙ … እግዚአብሔር አምላክም ለአዳምና ለሚስቱ የቁርበትን ልብስ አደረገላቸው፥ አለበሳቸውም።” [ዘፍ ፫፥፳፩]
ኋላ በምስጋና መብረቅ የተጋረደና በእሳት ደመና የተሸፈነ አምላክ ወልደ አምላክ የተስፋውን ቃል ለመፈጸም ከውድቀቱም ሊያነሳው ያን የተራቆተ ሥጋ ለበሰለት። የሚካኤል ሠራዊት በፍርኃት የገብርኤል ሠራዊት በመንቀጥቀጥ የሚያመሰግኑት እርሱ ዕርቃኑን በመካከላችን ተገኘ።
🍁 ወበቤተልሔም ወጽአ እምከርሰ እሙ ዕራቁ (በቤተልሔም ከእናቱ ማሕፀን ዕርቃኑን ተወለደ)
መጽሐፍ "ዕራቅየ ወፃእኩ እምከርሠ እምየ" እንዳለ ከእናቱ ማሕፀን ዕርቃኑን ተወለደ፤ ከመለኮቱ ሳይራቆት (ዕሩቅ ብእሲ ሳይሰኝ) ከሥጋ ልብስ ባዶ ሆኖ ወደምድራችን መጣ። ሥጋችንን ለብሲ የሰው ልጅ መባሉ እርሱን ለብሰን በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች ሊያሰኘን ነውና።
የመጽሐፉም ምስክርነት እንዲህ የሚል ነው "አሰረቶ መንኮብያቲሁ ወአስከበቶ ውስተ ጎል ወጠብለለቶ በጽርቅት ⇨ አውራ ጣቱን አሰረችው ፣ በግርግም አስተኛችው፣ በመጠቅለያም ጠቀለለችው” [ሉቃ ፪፥፯]
የ፲፭ ዓመቷ ገሊላዊት ብላቴና እናቱ ድንግል ማርያም በከብቶቹ ማደርያ ስትወልደው ለብኩርናው አውራ ጣቱን አሥራ፣ የተራቆተ ሰውነቱን በጨርቅ ጠቅላላ ፣ ለመኝታው ግርግም አሰናድታ ባላትና ባገኘችው ተቀበለችው። ይህም ለእኛ የተከፈለው ካሣ እረኞችም ምልክት እንዲሆናቸው በመልአኩ በኩል ‘እሱረ መንኮብያት ፣ ስኩብ ውስተ ጎል ፣ ጥብሉል በአጽርቅት (አውራ ጣቱ የታሠረ ፣ ከግርግም የተኛ ፣ በጨርቅ የተጠቀለለ) ሕፃን በበረቱ ታገኛላችሁ’ ተባሉ። [ሉቃ ፪፥፲፪]
ኋላም ሰብአ ሰገል ያመጡለትን ተአምራዊ ቀሚስ ለብሦ በእርሷው ውኃ እያቆረ ፣ ለ፴፫ ዓመት በምድር ላይ ኖረ
(ሰላም ለቀሚስከ ምስሌከ ዘልህቀ… ዘትሰፍር በሕንፍከ ማየ ባህር እሙቀ) እንዲል
🍁 ወበዮርዳኖስ ተጠምቀ በማይ ዕራቁ (በዮርዳኖስ ዕርቃኑን በውኃ ተጠመቀ)
ለኃጢዓታችን ሥርየት የሚሆን በግዕ ዘመስዋዕት፣ ለነፍሳችን ጠባቂዋ እረኛ ሊቀ ኖሎት፤ ወልዱ ለቡሩክ: ከሣቴ ብርሃን የዓለም መድኃኒት በባርያው በዮሐንስ እጅ እንዲጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ከልብሱ መራቆቱን የአበው መጽሐፍ እንዲህ ይገልጣል
"አስተርአየ በውስተ ዮርዳኖስ እንዘ ክሡት ዕርቃኑ ለተጠምቆ ⇨ ለመጠመቅ ራቁቱን በዮርዳኖስ ባሕር ውስጥ ታየ" (መጽሐፈ ምሥጢር)
የዮርዳኖስ ጥምቀት የሁላችን ዕርቃን የተከደነበት ነው።
🍁 ወበቀራንዮ ሰቀልዎ ዲበ ዕፅ ዕራቆ (በቀራንዮ በእንጨት ላይ ዕርቃኑን ሰቀሉት)
አባ ጊዮርጊስ ስለዚህም እንዲህ ብሏል “ወበከመ ተከሥተ ዕርቃነ አዳም ማእከለ ዕፀዊሃ ለገነት ከማሁ ተከሥተ ዕርቃነ ትስብእቱ ለመድኃኒነ ማዕከለ ጉባኤሆሙ ለማኅበረ እስራኤል ⇨ አዳም በገነት ዛፎች መካከል ርቃኑን እንደታየ እንደሁም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በሰውነቱ በአይሁድ ጉባኤ መካከል ዕርቃኑን ሆኖ ታየ” (መጽሐፈ ምሥጢር)
ቅዱስ ያሬድም በፋሲካው ድጓ እንዲህ ይላል
“ሰአሎ ዮሴፍ ለጲላጦስ ወይቤሎ ሀበኒ በድኖ ለኢየሱስ ከመ እክድን ዕቃርኖ በልብስ ለዘከደነ ዕርቃንየ በዮርዳኖስ - ዮሴፍ ለጲላጦስ እንዲህ አለው፡- በዮርዳኖስ እርቃኔን የሸፈነውን እርቃኑን በልብስ እሸፍን ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ስጠኝ”
ዮሴፍና ኒቆዲሞስ እንደ ሰብአ ሰገል ምንኛ እድለኞች ናቸው? የአምላኩን እርቃን የሚሸፍን የራሱን ዕርቃን የሚከድን ነው።
እነርሱስ ከመስቀል ለማውረድ በአዲስ መቃብር ለማኖር ዕርቃኑን ለመክደን ሰውነቱን ለመሸፈን ጠይቀው ተፈቀደላቸው!
ታዲያ እኛስ …
☞ መቼ ይሆን በቤተልሔም ተሰናድቶ በመቅደስ ቀራንዮ ተሰውቶ የምናየውን የዓለም መድኃኒት በንሰሐ በታደሰ ሰውነታችን ተቀብለን በክብር የምናኖረው? መቼ ይሆን ከመንፈሳዊው መአድ ተሳትፈን የእርሱን ሥጋ በልተን የእርሱን ደም ጠጥተን እርሱኑ ለብሰን እርቃናችንን የምንሰውረው?
☞ መቼ ይሆን «ታርዤኮ አላለበሳችሁኝም» ከሚል ወቀሳና ከሰሳ ለመዳን በደጃችን የወደቁትን ዕሩቃን ነዳያን አልብሰን እርሱን ነው ያለበስነው ብለን ለብሰነው የምንከብረው?
☞ መቼ ይሆን … እንዲህ የምንለው

በልደቱ እናቱ ዕርቃኑን በጨርቅ የጠቀለለችው ሰብአ ሰገልም ቀሚስ ሰጥተው ያለበሱት ወልደ እግዚአብሔር አማኑኤል ፣ በጥምቀቱ መላእክት በክብር የጋረዱት መሲህ ክርስቶስ፣ በስቅለቱ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በአዲስ በፍታ የሸፈኑት መድኅን ኢየሱስ ራቁቱን ተወልዶ ተጠምቆና ተሰቅሎ የካሰን ከመራቆት የሸፈነን ዳግመኛ ከእርሱ ተለይተን እንዳንራቆት እርቃኑን አይተነው እንዳንርቀው በቸርነቱ ይጠብቀን!
🌴በቴዎድሮስ በለጠ ጥር ከተራ ፳፻፲፫ ዓም ተፃፈ ✍
. አዲስ አበባ

👍5
Drshaye Akele:
👉 በዓለ ጥምቀት👈
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
👉ጥምቀት_ምንድን_ነው?
ተወዳጆች የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ነገረ ጥምቀቱን እንዲህ መናገር እንጀምራለን
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
✅ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒያ በግእዝ አስተርዮ በአማርኛ መገለጥ ይባላል።
✅ጥምቀት “አጥመቀ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ፍቺውም በገቢር መንከር፣ መድፈቅ፣ መዘፈቅ፣ በተገብሮ መነከር፣ መደፈቅ፣ መዘፈቅ፣ መላ አካልን በውኃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው።
✅በሌላ አገላለጽ ጥምቀት ማለት በተጸለየበት ወይም በተለየና በከበረ ውኃ (ማየ ገቦ ወይም ማየ ሕይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር መጥለቅ፣ መዘፈቅ፣ መነከር ማለት ነው። በመሆኑም የምንጠመቅበት ውኃ ተራ ውኃ አይደለም።
✅ጥምቀት ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው።
💎የጥምቀት በዓል ከዘጠኙ የጌታ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው
💎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓተ አክብሮት መሠረት በየዓመቱ ከጥር አሥር እስከ አሥራ አንድ ቀን በደማቅ ሥነ ሥርዓት በካህናት፣ በምዕመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች አገልግሎት ይከበራል።
💎በዓሉ የሚከበረው ጌታ በዕደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ የተጠመቀበት ምሥጢረ ጥምቀትና ሥርዓተ ጥምቀትን የመሠረተበት ዕለት በመሆኑ ነው። ጌታ የተጠመቀው በተወለደ በሠላሳኛው ዓመት ሲሆን ያ ወራት ዮሐንስ መጥምቁ ሕዝቡን እየሰበሰበ የንስሐ ጥምቀት የሚያጠምቅበት ጊዜ ነበር:: 📗ማቴ. 3:1📗
ታሪካዊ የጥምቀት በዓል አከባበር በኢትዮጲያ
💧ታላቁ የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሲነሳ ኢትዮጵያውያን ሩቅ ዘመንን ተሻግረን የቅዱሳን ሰማዕት አባቶችን፣ የሊቃውንት አባቶችን አስተምሮት እናዘክራለን።
💧በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል።
💧በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
💧ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና እንክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል።
💧የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ።
💧ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ።
💧ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት timqet celebration በዐዋጅ አስነግረው ነበር።
💧ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ካወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ።
💧ኢትዮጵያ ዜና ጥምቀተ ክርስቶስን ከሰማችበት ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በተለይም ከአጤ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (6ኛው መ/ክ/ዘ) ወዲህ የጥምቀትን በዓል ዛሬ በሚታየው አኳኋን ስታከበር እንደ ቆየች ይታመናል።
💧በክብረ በዓሉ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱት ታቦታት በካህናቱ ሃሌታ፣ በምእመናኑ እልልታ እና በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ በተቋቋሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መዝሙሮች ታጅበው በተመሳሳይ አኳኋን እንደሚመለሱ ይታወቃል።
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።
መዝሙረ ዳዊት ፻፶፥፮
💎ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል። የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል። የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።
💎ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው።
✅ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው።
✅እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው።
✅ኢያሱ የጌታ፣
✅እስራኤል የምእመናን፣
✅ዮርዳኖስ የጥምቀት፣
✅ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው።
✅ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣
✅ታቦቱ የጌታችን፣
✅ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣
✅ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው።
✅ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል።
✅‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው።
👉ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ እግር ተጠመቀ።››።
💎ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው። ከወንዝ ዳር ያለ መጠለ
ያ መዋልና ማደር አይቻልም። በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር። በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ።
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር የዐፄ ፋሲል መዋኛን፣ በላስታ የላሊበላ መዋኛን፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። እኒህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ።
💎እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ፈጣሪያችን በዓሉን የበረክት የረድኤት ያድርግልን፡፡
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
ምንጭ ፦ ሥርዓተ ተዋህዶ ርትዕት

👍30❤4🙏1
#ሰበር_ዜና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ
መግለጫውን የሰጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት: ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አሥኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።
ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገ ወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :-
1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።
Via: EOTCTV

👍64👏7
📍📍 ሰበር📍📍
ከደቂቃዎች በፊት የተሰበሰበው አስተዳደራዊ ጉባኤ ከዚህ በታች ያሉት ውሳኔ አስቀምጧል።
ኤጲስ ቆጶሳት ነን ብለው በተገኙ ፳፮ መኖከሳት ላይ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ጉባኤ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላለፈ
***
የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት የአስተዳደር ጉባኤ ዛሬ ማለዳ ላይ በዋለው ስብስባ ትላንት ጥር 14 በወሊሶ ከተማ በተደረገው ህገ ወጥ ሲመት
እራሳቸውን ኤጴስ ቆጶሳት ብለው የገለጡ ከተለያዩ አድባራት እና ገዳማት የተውጣጡ ፳፮ መኖኮሳት ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላልፏል።
በእዚህ መሰረት
፩ኛ .ሁሉም መኖከሳት ከደምወዝ ታግደው እንዲቆዩ
**
፪ኛ. የሚያንቀሳቅሱት የገዳማት እና አድባራት ሂሳብ ካለ እንዲታገዱ
**
፫ኛ. ከእዚህ በፊት ወደሚያገለግሉት የአገልግሎት መዋቅር እንዳይመለሱ
**
፬ኛ.በየትኛው የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አድባራት እና ገዳማት እንዳይገኙ ውሳኔ አስተላልፏል።
ፍትሕ መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀጣይ በሚያደርገው ስብሰባ ይወስናል ተብሎ ይጠብቃል።

👍61
«ነፍሴን አስይዤ እፋለማለሁ፣ የአባቶች አደራ አለብኝና'»
እኔ መጀመሪያ ስሾም የቀደስኩት በኦሮሚኛ ቋንቋ ነበር ብዙ አገልግሎቶችን በኦሮምኛ ቋንቋ ነው የምናከናውነው። የነዚህ ሰዎች አላማ ምንድነው? ቅዱስ ሲኖዶስን ማክበር ያስፈልጋል።
ከዛ ያፈነገጠ አካሄድ ከባድ መለኮታዊ ቅጣት አለው። እኔ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን፥ በአንድ ቤተክህነት አምናለው ከዚህ ውጭ የሚደረግን እንቅስቃሴ ነፍሴን አስይዤ እፋለመዋለው የአባቶቼ አደራ አለብኝና።
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት ።
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋና የምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ አባታችን በረከታቸው ይደርብን
## ከዚህ በፊት የዘመን መለወጫ በዓል ላይ ከተናገሩት።
ይህ በሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለው ቀደም ሲል የተናገሩት ነዉ ፡፡

👍28❤15
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - 🇴🇷🇹🇭🇴🇩🇴🇽 🇹🇪🇼🇦🇭🇩🇴
Photo
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ውጪ የሚደረግን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደማይቀበል የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአቋም መግለጫው አስታውቋል።
ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ
ልዩ ጽሕፈት ቤት፣
ካይሮ፡ 24 ጃንዋሪ 2023 ዓ/ም (ጥር 16 ቀን 2015 ዓ/ም)
የአቋም መግለጫ
የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አቡነ ሳዊሮስ በተባሉ ጳጳስ የተፈጠረውን ቤተ ክርስቲያንን የመክፈልና ራሳቸውን በኢትዮጵያ የኦሮሞ ክልል ፓትርያርክ አድርገው የመሠየም ተግባር ሙሉ ለሙሉ የማይቀበለው ፍጹም ሕግን የጣሰ መሆኑና እና በእሳቸው መሪነት ተሾሙ የተባሉ 26 ጳጳሳት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሕግ የጣሱ እንዲሁም መሠረት ያለውን እና ቋሚ የሆነን ከጥንት ጀምሮ በትውልዱ ሁሉ ሲተላለፍ ከመጣውን ከኦርቶደክስ ቀኖና እና መመሪያ ሕገ ወጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ዕውቅና ውጭ የሚደረግን ሢመት ዕውቅና አትሰጥም አትቀበልም።
ከዚህ በተጨማሪ ኮሚቴው (የውጭ ጉዳይ) ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ወዳጅነት እና አጋርነት እየገለጽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት፤ ሜትሮፖሊታን የሆናቸሁ ሁላችሁ ጥንታዊነት እና በታሪክ የበለጸገች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ትሥሥር በፍቅርና በሰላም ሁናችሁ እንድትጠብቁ በጥብቅ አደራ እንላለን፡፡
የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ
አባ ቶማስ የቂሊያ ሜትፖሊታን እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ።
Via: EOTC TV

👍26❤14
"አቤቱ አምላካችን የከበደውን አቅልልልን። ሀገራችንን ሃይማኖታችንን ጠብቅልን።"
ቅዱስነታቸው በጉባኤ ሲኖዶስ መክፈቻ ሲያሳርጉ የጸለዩት
ከዛሬ ጀምሮ ለ፫ ቀናት ጸሎተ ምሕላ ታውጇል። ጸልዩ!
ቅዱስነታቸው በጉባኤ ሲኖዶስ መክፈቻ ሲያሳርጉ የጸለዩት
ከዛሬ ጀምሮ ለ፫ ቀናት ጸሎተ ምሕላ ታውጇል። ጸልዩ!
👍25❤6👏4