Telegram Web Link
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶት የነበረው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው መታገዱ ተገለጸ።

ሚያዝያ ፲፮/፳፻፲፯ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሰሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማዕከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርትን ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።
              
ምንጭ:-   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ


@ortodoxtewahedo
👍14🔥71
'' ነይ ነይ እምዬ ማርያም ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም ''

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
35👏3👍2
‘’ክብር በምግብ ቢሆን ጅብ ይበልጠን ...
ሀገሬ ቴሌቪዥን Hagerie TV
ክብር በምግብ ቢሆን ጅብ ይበልጠን ነበር
            ቆይታ ከሀገሬ ቴሌቪዥን ጋር
Size:-83.4MB
Length:-1:30:06

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍6😍1🤝1
+++ ይህ የአባቶቻችን የሐዋርያት ትዕዛዝ ነው፡፡
ሰው በልቦናው ቂምንና በቀልን ቅንዓትንና ጠብን
በባልንጀራው ላይ በማንም ላይ ቢሆን አይያዝ፡፡
+++
~~~~ ቅዳሴ ~~~

@ortodoxtewahedo
18👍7🥰3👏1
"ድንግል ሆይ አንቺን የሰደበ ሰው እንዴት ይኖራል " አይኖርም እንጂ ምክንያቱም በልጅሽ የፍርድ መፅሐፍ ላይ እናት አባቱን የሰደበ ሰው ይሙት ይላል የጌታን እናት ሰድቦ እንዴት ይኖራል።

#አባ ፅጌ ድንግል

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
🔥14👍63👏3
#ምክረ አበው!

"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው"

#ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ

"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል"

#ቅዱስ ቆጵሮሳዊ

"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"

#ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ

"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም"

#ቅዱስ ባስልዮስ

"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር"

#ሊቁ ጠርጡለስ

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍174👏2
🌿 🌿 🌿 🌿 🌿 🌿 🌿 🌿 🌿

#እንኳን_ለዳግመ_ትንሣኤ_አደረሳችሁ_በአሉ_የሰላም_የፍቅር_የደስታ_በአል_ይሁንላችሁ!!!

#ዳግመ_ትንሳኤ!!!

ዳግመ ትንሳኤ የተባለበት ምክንያት፦ዳግም ትንሳኤ ሲባል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ ተቀብሮ ዳግም ተነሳ ሳይሆን በድጋሜ ቅዱስ ቶማስ ባለበት ልክ በመጀመሪያ እንደተገለጠላቸው ሆኖ ስለታያቸው ነው።

  #ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በአስሩ ሀዋርያት ሲገለጥላቸው ሀዋርያው ቶማስ አልነበረም መጥቶ በተገናኛቸው ጊዜ እሱም ጌታችን እንደተነሳ መጥቶ ሰላምታ እንደሰጣቸው እንዳዩት ሲነግሩት ግን"የተቸነከረውን እጅና እግሩን በጦር የተወጋውን ጎኑን ካላየሁ አላምንም አለ።"ዮሐ 20:25 ይሄን ሊል የቻለው ሀዋርያው ቶማስ የተጠራው ትንሳኤ ሙታን የለም ከሚሉት ከሰዱቃውያን ወገን ነበርና አንድም ሌሎች ሐዋርያት ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ አየነው እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብዬ ላስተምር ነው።ጌታም የቶማስን ጥርጣሬ ያስወግድለት ዘንድ በተነሳ በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ቶማስ ከሌሎች ሐዋር ጋር ሳለ እንደገና በትንሳኤ እንዲታያቸው ሆኖ በዝግ ቤት ገብቶ ሰላምታ ከሰጣቸው በኋላ ሀዋርያው ቶማስን ለይቶ"ቶማስ ቶማስ ና በችንካር የተቸኘከሩ እጆቼን እይ እንዲሁም እጅህን አምጥተህ በጦር ወደተወጋው ጎኔ አግብተህ ዳሰኝ ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን ባለው ጊዜ ቶማስ እጁን በጦር የተወጋ ጎኑን በእጆቹ በዳሰሰ ጊዜ ከእሳት እንደገባ ጅማት ኩምትርትር ሲል ጌታዬ አምላኬ ብሎ ተጣራ አምላክነቱንም መሰከረ።አንተ አይተሃል አምነሃል ነገር ግን"ሳያዩ የሚያምኑ ብፁአን ናቸው"ብሎ ፈውሶታል።ዮሐ 20:29 በአከባበር ስርአት የመጀመሪያውን ትንሳኤ ስለሚመስል ነው።ትንሳኤ እለቱ የሚባለው እግዚአብሔር ሳይለወጥ በሙሉ በዚህ ቀን ይደገማል።ከዚህም ሌላ፦

#ሁለት_መጠሪያ_ስሞች_አሉት
እነዚህም"ፈጸምነ አግብአተ ግብር"ይባላሉ።

1.ፈጸምነ የተባለበትም፣የሰሞነ ትንሳኤ በአል አክብረን ፈጸምን ማለት ነው።

2.አግብአተ ግብር የተባለበትም፤ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ"አባ ወአቡየ ግብር ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ....እኔ ልሰራው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር ላይ አከበርኩህ"ያለውን ከቅዳሴ በኋላ ሊቃውንት በዚህ ቀን ስለሚዘምሩት ነው።ዮሐ 17:4

🌿ወስብሐት ለእግዚአብሔር🌿

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍11👏91🥰1🙏1
ተገናኝቶ ሻይ ቡና ብሎ መለያየት
ተገናኝቶ አንድ ሁለት ብሎ መለያየት
ተገናኝቶ ስለ ኳስ ስለ ፊልም አውርቶ መለያየት
ተገናኝቶ ስለ ሰው አውርቶ መለያየት
ተገናኝቶ ሃጢአት ሰርቶ መለያየት

#ተገናኝቶ_አብሮ_ንስሐ_ገብቶ_አብሮ_መቁረብ🙏🙏🙏

(አንዳንድ እህቶች እና ወንድሞች ቅዱስ ቁርባን እንደሚፈሩት እግዚአብሔርን ቢፈሩት መልካም ነበር። ቅዱስ ቁርባን ፈርተው ይቀርቡታል እንጂ ፈርተው አይርቁትም፥ የቅዱስ ቁርባን ክብሩ እኛ ስንቀበለው ነው። ከቆረብኩ በኋላ ሀጢአት ብሰራ ባል ባላገኝ ወዘተ የሚሉ ሰይጣናዊ ህሳቤዎችን ወደጎን በመተው ጉዞ ወደ ቅዱስ ቁርባን።)

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
46👍16🙏5
ቋሚ ሲኖዶስ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።
***
ሚያዚ
ያ ፳፪ ቀን ፳፻ ፲ዘ፯ ዓ.ም
+++++++++++++++++++
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
"""""""""""""""""""""""""""
ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከቤተክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አዳራሽ የሰጡትን ትምህርትና በማኅበሩ ሚዲያ የተላለፈበትን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬው መደበኛ ጉባኤው በሰፊው ተወያይቶ ለመወሰን በያዘው ቀጠሮ መሰረት በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ካደረገ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

1. ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር በተለያዩ ጊዜያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ውጪ በሚዲያው ያስተላለፈው የስሕተት ትምህርት የቤተክርስቲያናችንን አባቶች፣ሊቃውንቱንና መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘነ በመሆኑ በማህበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ በኩል ጊዜያዊ የእገዳ ደብዳቤ እንዲደርሰው እና በመምሪያው በኩል አስፈላጊው ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዲቋቋም አድርጓል።
በዚህም መሰረት ቋማ ሲኖዶስ ያቋቋማቸው አጣሪ ልዑካን አጠቃላይ የማህበሩን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እና በሚዲያው ያስተላለፋቸውን የስህተት ትምህርቶች በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከማህበራት ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ጋር በመነጋገር በሚገባ መርምርውና አጣርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ፣

2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “ማርያም ቤዛዊተ ዓለም” አትባልም በማለት ከቤተ ክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ የሰጡት ሕጸጽ ያለበት ትምህርት በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚገባ ተመርምሮና ተጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ብፁዕነታቸውም ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተአቅቦ እንዲቆዩ፣

3. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፏቸው የስሕተት ትምህርቶችና በሌሎችም መምህራን የተላለፉ ነቀፋ ያለባቸው ትምህርቶች ካሉ የሊቃውንት ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንጻር በሚገባ መርምሮና አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብ፣

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኝ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር ሚዲያ የአየር ሰዓት የሰጠበትን ዝርዝር ሁኔታና ከማኅበሩ ጋር በተያያዘ አየር ላይ ያዋላቸውን ትምህርቶች የሚያሳይ ሪፖርት እንዲያቀርብ ይደረግ በማለት ቋሚ ሲኖዶስ ወስኖ የዕለቱን ጉባኤ በቅዱስነታቸው ጸሎተ ቡራኬ አጠናቋል።

መረጃው የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation ,EOTC ነው።

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍17👏72
#ሊቀ ሰማዕታት ፀሐይ ዘልዳ

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ፡-

ጊዮርጊስ ማለት ‹‹ኮከብ ብሩህ፣ ፀሐይ›› ማለት ነው፡፡ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀገሩ ፍልስጤም ልዩ ስሟ ልዳ ሲሆን የተወለደው በ277 ዓ.ም ጥር 20 ቀን ነው፡፡ አባቱ ዞሮንቶስ ወይም አንስጣስዮስ የ...ልዳ መኳንንት ሆኖ ተሹሞ ይኖር ነበር፤ እናቱ ቴዎብስታ ወይም አቅሌስያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሌላ ማርታና እስያ የሚባሉ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዳለች፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ዐሥር ዓመት በሆመው ጊዜ አባቱ ስለሞተ ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ አሳደገው፡፡ መድፍኑም በጦር ኃይል አሰለጠነው፡፡ ሃያ ዓመትም በሞላው ጊዜ መስፍኑ የ15 ዓመት ቆንጆ ልጅ ነበረችውና እርሷን አግብቶ ሀብቴን ወርሶ ይኑር ብሎ ድግስ ሲያስደግስ ጌታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ሀገር ሄደ፡፡ በቤሩት ደራጎንን ያመልኩና ሴት ልጆቻቸውን ይገብሩለት ስለነበር ሰማዕቱ ደራጎኑን በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል፡፡
ወደፋርስ ቢመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት አቁሞ ሲሰግድ ሲያሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖቱ ቀናዒ ነውና ከቤተመንግስቱ ገብቶ በከሃዲያኑ ሰባው ነገሥታት ፊት ክርስቲያን መሆኑን በመመስከር የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ ዱድያኖስም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ ‹‹አንተማ የኛ ነህ በዐሥር አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ›› አለው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ‹‹ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም›› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ዱድያኖስ እጅግ ተናዶ ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰበት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ጌታችንን ‹‹ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት›› በማለት መከራውን ይታገስ ዘንድ ለመነው፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ፈቃዱን ይፈጽምለት ብዙ በመከራው ሁሉ ጽናትን ሰጥቶታል፡፡ ሦስት ጊዜም ከሞት አስነሥቶታል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም የደረሱበት እጅግ አሠቃቂ መከራዎች የሰው ኅሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው፡፡
በመጀመሪያም ዱድያኖስ በእንጨት ላይ ካሰቀለው በኋላ ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምቶት ሂድ አለው፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል፡፡ ዳግመኛም በሰባ ችንካሮች አስቸንክሮ በእሳት አስተኩሶ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ፡፡ ሥጋውንም በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ነሰነሰበት፡፡ ሥጋውም ተቆራርጦ መሬት ላይ ወደቀ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ ከፈወሰውና ‹‹ገና ስድስት ዓመት ለስሜ ትጋደላለህ፣ 3 ጊዜ ትሞታለህ፣ በ4ኛውም ታርፋለህ›› ካለው በኋላ በመከራውም ሁሉ እርሱ እንደማይለየው ነገረው፡፡
ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከዚያ ካደረሰበት አሠቃቂ መከራዎች ሁሉ ድኑ ፍጹም ጤነኛ መሆኑን በተመለከተ ጊዜ እጅግ ደንግጦ ‹‹የሚያሸንፍልኝ ቢኖር ብዙ ወርቅ እሰጠዋለሁ›› ብሎ ተናገረ፡፡ አትናስዮስ የተባለ መሰርይ አንዲትን ላም በጆሮዋ ሲያንሾካሹክባት ለሁለት ተሰንጥቃ ስትሞት ለንጉሡ አሳየውና ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲሚያሸንፍ ምልክት አሳየ፡፡ ንጉሡም ያሸንፍልኛል ብሎ ደስ አለው፡፡ መሰርይውም ሆድ በጥብጦ አንጀት ቆራርጦ የሚገድል መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞበት እንዲጠጣው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኝቷል፡፡ በዚህም ጊዜ ጠንቋዩ ማረኝ ብሎ ከእግሩ ሥር ወደቀ፡፡
+
ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በመንኰራኩር አስፈጭቶ ከትልቅ ጉድጓድ ጥሎት ደንጊያ ዘግቶበት አትሞበት ሄደ፡፡ ጌታችንም የተፈጨውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋ በእጁ ዳስሶ ፈውሶታል፡፡ ወደ ከሃዲውም ንጉሥ ተመልሶ ‹‹አምላኬ ከሞት አዳነኝ›› በማለት መሰከረ፡፡ ንጉሡም ዳግመኛ በብረት አልጋ አስቸንክሮ ከበታቹ እሳት አነደደበት ነገር ግን እሳቱ ደሙ ሲንጠባጠብበት ጠፍቷል፡፡ ጌታችንም ፈወሰው፡፡ ከዚህም በኋላ ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን ‹‹ኢየሱስ አምላክ መሆኑን አሳየኝ›› ቢለው የለመለሙትን ዕፅ አድርቆ፣ የደረቁትን ደግሞ አለምልሞ፣ ከሞቱ 430 ዓመት የሆናቸውን ሙታንን አስነሥሰቶ አሳይቶታል፡፡ ነገር ግን ንጉሡ ልቡ ክፉ ነውና በርኃብና በጽም ይሙት ብሎ ምንም ከሌላት መበለት ቤት አሳስሮታል። እርሷም የሚቀመስ ስትፈልግ ቤቷን በእህል አትረፍርፎ የታሰረበትን ግንድ ማለትም የቤቱን ምሰሶ አለምልሞታል፡፡ ልጇም ጆሮው የማይሰማ ነበርና ፈወሰላት፡፡ መበለቲቷንም ከነልጆቿ አጥምቆአቸው መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ከእስራቱ ፈትቶት ተመልሷል፡፡
ዳግመኛም ንጉሡ ዱድያኖስ ጭፍሮቹን ‹‹በመንኰራኩር ፈጭታችሁ አጥንቱን ደብረ ይድራስ ተራራ ላይ ወስዳችሁ ዝሩት›› ብሎ አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋ በመንኰራኩር ፈጭተው ወስደው በተራራው ላይ ቢረጩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ ‹‹ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፣ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር›› እያሉ አመስግነዋል፡፡ አሁንም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነሣውና ሥጋውን ፈጭተው በተራራም ላይ ሥጋውን በትነውት ወደ ንጉሡ የሚመለሱትን ወታደሮች በመንገድ ከኋላቸው ሄዶ ደረሰባቸውና ‹‹ቆዩኝ ጠብቁኝ›› አላቸው፡፡ እነርሱም እጅግ ደንግጠው ይህ እንዴት እንደሆነ ሲጠይቁት ‹‹አምላኬ ከሞት አዳነኝ›› አላቸው፡፡ ጭፍሮቹም እጅግ ደንግጠው ከእግሩ ስር ወድቀው ይቅር በለን ብለው በአምላኩ እንደሚያምኑ መሰከሩለት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ከመሬት ላይ ውሃ አመንጭቶ በጸሎት ጌታችንን ቢጠይቅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ አጥምቋቸዋል፡፡ እነርሱም በንጉሣቸው ፊት ሄደው ስለጌታችን በመመስከር በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዐፅሙ ተቃጥሎ አጥንቱ ተፈጭቶ በደብረ ይድራስ ተራራ ላይ የተበተነው በዛሬዋ ዕለት ነው፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን፤ የዓሥራት አገሩን ቅድስት ኢትዮጵያን ይጠብቅልን፡፡
#ምንጭ፡ ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ
፠፠፠
+ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለምን አሳልፈህ የምትኖር የወለድ የመንፈስ ቅዱስ ልባቸው አብ ሆይ ላንተ ሰላምታ ይገባሃል፡፡
+ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለምን አሳልፈህ የምትኖር የአብ ፤ የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ወልድ ሆይ ላንተ ምስጋና ይገባሃል፡፡
+ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለምን አሳልፈህ የምትኖር የአብና የወልድ ሕይወታቸው እስትንፋሳቸው መንፈስ ቅዱስ ሆይ ላንተ ሰላምታ ይገባሃል፡፡
+ የፀጋው ብዛት የማይታወቅ: ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው: ጌታችን አምላካችና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምሥጢሩን ይግለጽልን: ክብር ምስጋና ይግባው።
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክ ቡ ር
†† † † ††

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍17🔥1
ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍81
#ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ

እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ የዕረፍቱ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን !!!

" እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው።"
                 መዝ.፷፯፥፴፭ /67፥35/

✝️ ገና በሃያ ዓመት ዕድሜው የአባቱን መዓረግ ለመቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘንድ በሄደ ጊዜ ንጉሡ ሕዝቡ ጣኦት ያመልክ ዘንድ ያስገድድ ስለነበረ በንጉሡ ሥራ አዘነ

✝️ በንጉሡ ሥራ የተናደደው ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለውን ንብረት ሸጦ ለድሆች ሰጠ፣ ከባርነትም አወጣቸው

✝️ በኢየሱስ ክርስቶስ ታምኖ ክርስትናውን ጠብቆ ለጣኦት መሰግድን አሻፈረኝ አለ

✝️ በዚህም ብዙ መከራና ስቃይ ደረሰበት፤ በብዙ ሕማምና ስቃይ አለፈ፤ በተደጋጋሚም ስጋውን ገደሉ

✝️ የክብር ጌታ፣ የታመነለት አምላክም ደጋግሞ አስነሳው

✝️ ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለው ታላቅና ክቡር የሆነ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዕረፍቱ ሚያዚያ ፳፫ ቀን ሆነ

የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በረከትና ምልጃ ይደርብን። አሜን።

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
26🙏14👍10👏5
🔴 እንደ አባቶቼ አምናለሁ || እመቤታ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
እንደ አባቶቼ አምናለሁ
            ድንግል ማርያም ቤዛዊት ናት
Size:-67.5MB
Length:-1:12:55

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo
👍14🤣21
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
" የአባቶቻችን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን ፤ የተማርናት ፤ ተስፋ የምናደርጋት ሃይማኖት ይህች ናት:: እንኖርባታለን ፤ እንሞትባታለን ፤ በእግዚአብሔር ፍቃድ እንነሣባታለን "

ሃይማኖተ አበው
እንቁ መምህራችን የሆኑት እዮብ ይመኑ ትምህርቶች ለማግኘት ከታች ናለድ ሊንክ ይግቡ❤️


የይቱብ ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ
      👇👇👇
https://youtu.be/yI-3Sl9NB5c?si=1fCKjnh4FjRC2OJ9
https://youtu.be/yI-3Sl9NB5c?si=1fCKjnh4FjRC2OJ9
11👍5
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
💚💛❤️💚💛❤️💚💛💚

"ወሀቢተ ፀጋ በከንቱ "
ስጦታን እንዲሁ
የምትሰጪ አንቺ ነሽ

ለመቀላቀል 👉 @ortodoxtewahedo

💚💛❤️💚💛❤️💚💛❤️
10👍6👏1
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ታሪክ

#ታቦተ መድኃኔ ዓለም

የመድኃኔ ዓለም ጽላት በ፲፰፻፺፭ዓ.ም. በግርማዊ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክና በእቴጌ ጣይቱ ትእዛዝ በመምህር ፈቀደ እግዚእ አማካኝነት ወደ ኢየሩሳሌም ተወስዶ በዴር ሡልጣን (የንጉሥ ገዳም) ውስጥ ለ፴፬ ዓመታት ሲጸለይበት ቆይቷል፡፡ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ በስደት እንዳሉ ልመናቸውን እና ጸሎታቸውን የሚያቀርቡበት አንድ ጽላት የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ስለአመኑበት ወደ ኢየሩሳሌም ለዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ (በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ) በጥር ፲፫/፲፱፻፳፱ ዓ.ም. “…አንድ ጽላትና አምስት መነኵሳት የሚያስፈልገውን ይዞ እንዲመጣ አባ ሐናን ልኬዋለሁና ከመምህር ገሪማ ጋር ተማክራችሁ ዐቢይ ጾም ሳይገባ እንዲደርስ አድርጋችሁ እንድትልኩልን ይሁን” ብለው በላኩላቸው በስደት በሀገረ እንግሊዝ የሚገኙ ንጉሣውያን ቤተሰቦች እና ለሌሎች ምእመናን ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ከአምስት ልዑካን ጋር ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ለንደን ሄዶ እስከ ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. በእንግሊዝ ሀገር ቆይቷል፡፡

የመድኀኔ ዓለም ታቦት በነሐሴ ፳፫ ቀን ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ግርማዊት እቴጌ መነን ዐዲስ አበባ በገቡበት ቀን አባ ኃይሌ ቡሩክ የተባሉት መነኵሴ ይዘውት ገብተዋል፡፡ ታቦቱም በቤተ መንግሥት የተለየ ቦታ ተደርጎለት በአባ ኃይሌ ቡሩክ ጠባቂነትና አጣኝነት ከቆየ በኋላ ሚያዚያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፴፭ ዓ.ም. ደግሞ ቀድሞ ቤተ ሳይዳ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሆስፒታል በዛሬው የካቲት ፲፪ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ምስካየ ኅዙናን በመባል ተሰይሞ ተተክሎ ነበር፡፡

የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም ገዳም መነኵሳት በኅብረት /የአንድነት ኑሮ/ ለመኖር በመስማማታቸው በግንቦት ፲፮ ቀን በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. በዕጨጌ ገብረ ጊዮርጊስ /በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ/ እና መምህራን ሊቃውንት በተገኙበት በቀድሞው ሥፍራ በቅዳሴ ተከብሯል፡፡

ታቦቱ ዐዲስ አበባ ከገባ ከሰባት ዓመታት በኋላ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ዐዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት በሚያዚያ ፳፯ ቀን ፲፱፻፵ ዓ.ም. በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የመሠረት ድንጋዩ ተጣለ፡፡ የተጣለውም በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ክበብ ውስጥ ነው:: በዚህ ሥፍራም እንዲሠራ የሆነበት ምክንያት ለተፈሪ መኮንን (ወንድ ተማሪዎች) እና ለእቴጌ መነን(ሴት ተማሪዎች) ተማሪዎች ሲባል እንደሆነ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የመሠረት ድንጋይ ሲያኖሩ " ... ይህን መሠረት ስንመሠርት በዚህ ... ወጣቶች የኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖታቸውን ሥርዓት እንዲጠብቁበት ሥርዓተ ጸሎትና ሥርዓተ ቁርባን በመፈጸም እንዲጠቀሙበት አስበን ነው። ... ፍሬውንም ለማየት ተስፋችን እርሱ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ነው።" ብለው ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል፡፡

የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተጠናቅቆ በ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ሚያዚያ ፳፯ ቀን ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀ.ኃ.ሥ. ግርማዊት እቴጌ መነን እና ሌሎቹም በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል፡፡

በዚህ ወቅት ሥርዐተ ቅዳሴውን ያካሄዱት ልዑካን፤ ሠራኤ ካህን፡- ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ የሸዋ ጳጳስ፣ ተራዳኢ ካህን፡- ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የሲዳሞ ጳጳስ፣ ሠራኢ ዲያቆን፡- አባ ተክለ ማርያም (ኹለተኛ አስተዳዳሪ የነበሩት)፣ ተራዳኢ ዲያቆን፡- አባ ሐና ጅማ (የመጀመሪያ አስተዳዳሪ)፣ አባ ኃ/ኢየሱስ፣ አባ ገ/ሚካኤል ነበሩ፡፡

የገዳሙ ልዩ አስተዳደራዊ መዋቅር፡-
ገዳሙ የሚተዳደረው ቀጥታ በቅዱስነታቸው ትእዛዝ ነው፡፡ በሊቀ ጳጳስ የሚመራ አስተዳዳር ቦርድ አለው፡፡ የገዳሙ መምህር (አስተዳዳሪ) የሚመሩት የአስተዳደር ጉባኤ አለው፡፡ ከዚሁም ጋር መጋቢ፣ ቄሰ ገበዝ እና ሊቀ ዲያቆናት የየራሳቸው ሐላፊነት አላቸው፡፡

የመጀመሪያውም አስተዳዳሪ አባ ሐና ጅማ ሆነው በ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. ግርግር እስከ ተገደሉበት ቀን ድረስ እንደሚገባ አገልግለዋል፡፡

ስያሜው እና ልዩ ሥርዐቱ
ከቤተ ሳይዳ ጀምሮ የገዳሙ ስያሜ ምስካየ ኅዙናን ማለት ያዘኑ መጠጊያ ማለት ነው፡፡ ይኽም ከላይ እንዳየነው የኢትዮጵያን እንባ አብሶሷልና ያዘኑ ምእመናን እየመጡ እንባቸው እንዲታበስ በማመን የተሰየመ ስም ነው፡፡

ልዩ ሥርዓቱ በስሙ ትርጓሜ መሠረት ቤተ ክርስቲያኑ ከበሮ የማይመታበት ጸናጽልም የማይሰማበት ነገር ግን ሥርዓተ ቅዳሴ የሚቀደስበት፣
የሰዓታት ጸሎት፣ የኪዳን ጸሎት፣ የሠርክ ጸሎት የንስሐ መዝሙር የሚቀርብበት የኅዙናን መጠጊያ ነው፡፡

የገዳሙ መምህራን
ከክቡር አባ ሐና ጅማ እስከ አሁኑ መምህር ክቡር መልአከ ገነት አባ ገ/ሥላሴ ይርሳው /ቆሞስ/ ድረስ ሃያ ሁለት አበው ገዳሙን አስተዳድረውታል፡፡
ያዘኑ ሁሉ መጠጊያ እና መጽናኛቸው የሆነ መድኃኔ ዓለም ከሀዘን ከመከራ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ይጠብቅ።ለዓለሙም ሁሉ መዳኛውን ይስጥ።

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!


#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
7👍7
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#አባ አጋቶንና አታላይ አጥማቂዎች

" በዘመኑም ሰይጣን ያደረበት ሰው ተገለጠ። ብዙ ወገኖችንም አሳታቸው። እርሱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚቀመጥ ሆኖ ትምህርቱን የሚሰሙ ሕዝቦች የእንጨት ቅርንጫፎችን በመያዝ በዙሪያው ይቀመጣሉ። አባ አጋቶንም ልኮ ወደ እርሱ አስመጣው። በላዩም ጸለየና በሰውየው ላይ አድሮ ለሰዎች በመናገር የሚያስተውን ሰይጣን ከእርሱ አስወጣው።

እንዲሁም ሰማዕት ሚናስ ያነጋግረኛል የምትል ሴት ተነሥታ በቅዱስ ሚናስ ስም የውኃ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ በጠበሉ ውኃ ተጠምቀው ከደዌያቸው እንዲፈወሱ የአገርዋን ሰዎች አዘዘቻቸው። ያቺንም ሴት ወደ እርሱ አስመጥቶ በላይዋ ጸለየ፤ ርኩስ መንፈስንም ከእርሷ አስወጣው። የዚያችንም ሀገር ሰዎች ለጠበል ብላ ያስቆፈረችውን ጉድጓድ እንዲደፍኑት አዘዛቸው።

ዳግመኛም ሌላ ሰው ተነሣ። እርሱም ጋኔን ይዞ ያሳበዳቸውን ሰበሰባቸው። ሲደበድባቸውም ለጥቂት ጊዜ ጋኔኑን ያስተዋቸዋል። ብዙዎችም ጋኔን የያዛቸው ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። ቅዱስ አባ አጋቶንም ወደ እርሱ እንዲመጣ ወደ ሰውየው ላከ። ሰውየውም ትእዛዙን ሰምቶ አልመጣም። የስሕተት ሥራውንም አልተወም። የዚያችም አገር ገዢ ሲያልፍ የሰበሰባቸው እብዶች ሰደቡት፣ ረገሙትም። ስለዚህ ያን ሰው መኮንኑ ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሰቃየውና በሥቃዩ ውስጥ ሞተ።"
/ስንክሳር ፣ መስከረም ፲፬/

ዛሬም በእኛ ዘመን የምናያቸው ከላይ ከተገለጹት ከሦስቱ ታሪኮች በምንም አይለዩም። ዛሬ ማርያም ፣ አርሴማ አዛኛለች ፣ ጽላት አስቆፍሬ አወጣለሁ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ያን ጊዜም ሚናስ ሰማዕት አናግሮኛል የምትል ጠበል ያስቆፈረች ነበረች።
በኃይል እፈውሳለሁ እያለ ለጊዜው የሚያስታግስ አጋንንትን የሚያስለፈልፍ ሰውን የሚያሰድብ የሚያጣላ ዛሬ እንዳለው ሁሉ ያኔም ነበረ። ገዳም ቤተ ክርስቲያን ሆኖ የሚናገርና እንደ በቃ ቅዱስ የሚታይ ሰው ድሮም ነበረ፣ ዛሬም አለም።

አሁን ልዩነቱ እንደ አባ አጋቶን ያለ ጻድቅ ተገልጦ በአሳቾቹ ላይ ያደረውን ሰይጣን አስወጥቶ አጥማቂ ነን ቅዱሳን ያናግሩናል የሚሉትን ስሑታን እስከ ተከታዮቻቸው የሚያድን ስውር ቅዱስ ብቻ ነው።

የአባ አጋቶን በረከት ይደርብን፣ እርሱን የመሰሉትን አስነሥቶም ስተው የሚያስቱትን ይፈውስልን።

ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!


#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
👍63
2025/07/12 16:12:20
Back to Top
HTML Embed Code: