Telegram Web Link
#እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" #ልደታ ለማርያም ድንግል "*+

#ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ:
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ::

" ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) "

=>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን::

+ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል::

+እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9)

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

"ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8)

=>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር::

+ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ::
እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::

+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

+ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::

+እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::

+በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

+እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . .
ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም)

+"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ."
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9)

+እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:-
*አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ=
*በእናቷ:-
-ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና::
*በአባቷ በኩል:-
-ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል::

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::

=>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ልደታ)
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቴክታና በጥሪቃ
4.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ (የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

=>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . .
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::
በውስጧም ሰው ተወለደ::
እርሱም ራሱ ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1-6)

<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.
👍149🔥1👏1
#ልደታ_ለማርያም

“ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ”
"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም ፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ።"

#አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው


ምሥራቀ ምሥራቃት ሙፃአ ፀሐይ እግዝእትነ ዘመና ሙዳይ፤
ተወልደት ዮም ዳግሚት ሰማይ፡፡
#እንኲን አምላክን እናት ለሆነች ለቃልኪዳንዋ እመቤት ለእመቤቴቻን ለቅድስት ድንግል
#ማርያም_ክብረ_በዓልና_አደ ረሳቹ::.

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.
14👍6
በኢያቄም በአባትሽ ወገን የንጉሥ ልጅ ሆይ አመሰግንሻለሁ፡፡ የዳዊት ልጅ ነሽና የሊቀ ካህናት ልጅ ሆይ ውዳሴሽን አቀርባለሁ፡፡ ከእናትሽ ወገን የአሮን ልጅ ነሽና፡፡

ገናንነትሽንም አደንቃለሁ፡፡ የነገድሽን ወገን አመሰግናለሁ ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ተገኝተሻልና፡፡

ስለዚሀም የነጎድጓድ ልጅ ነሽ እልሻለሁ ያዕቆብና ዮሐንስን አኔሬጌስ ብሎ እንደጠራቸው ይኸው የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፡፡ ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ናቸውና፡፡
ስለዚህም የነጎድጓድ ልጆች ተባሉ፡፡

እኔም የነጎድጓድ ልጅ ነሽ አልሁሽ፡፡ የመወለድሽ ድምፅ (ወሬ) እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ይሰማልና፡፡

ከሁለቱ ከተቀቡት ነገድ በነቢያት አለቃ በሙሴ እጅ ለክህነት ከተቀባው ከአሮን ቤት፡፡ በሳሙኤል እጅ ለመንግስት ከተቀባው ከዳዊት ዘር፡፡ (፩ ሳሙ ፲፮፣ ፲፫) (ዘሌዋ ፰፣ ፲፪)

ደግሞም ያንበሶች ልጅ ነሽ እልሻለሁ እንደ አንበሳ ግልገል ጩኸት እንደ ሴትም አንበሳ ድምፅ የልደትሽ ወሬ ይሰማልና፡፡ አባቱ ያዕቆብ ይሁዳን ያንበሳ ግልገል ብሎታልና፡፡ (ዘፍጥ ፵፣ ፱፣ ፱)

ስለዚህም ያንበሶች ልጅ እልሻለሁ፡፡ ሰሎሞን እንደተናገረ እንዲህ ሲል አንቺ ሙሽራ ከሊባኖስ ጋራ ነይ ከሊባኖስ ጋራ ነይ፡፡ ከአንበሶችም ጉድጓድ ወጥተሽ ነይ፡፡ (መሐ፣ ፬፣ ፰)

ከተመረጠ ነገዱ የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ወሬ እጅግ ግሩም ነው፡፡

አርጋኖን ዘሠሉስ

@ortodoxtewahedo
👍2115
ማርያም ...ናቡከደኖፆሮች ጋር የማይስማማ ስም
***

ዘማዊቷ ማርያም የአልባስጥሮስ ሽቱን በክርስቶስ እግር ላይ አፍስሳ ምስጢረ ንሰኅን ስለፈጸመች ብቻ .....

“ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል። ማቴ 26፥13" ....

የተባለው ቃል ላይ አምፆ ዘማዊቷ ሴትን ማክበር ክርስቶስን ይሸፍናል የሚል ኃይል ከዬትም አቅጣጫ አታገኝም።
***

ስለመጥምቁ ዮሐንስ መወለድን በተመለከተ ቅዱሱ መጽሐፍ ...

..."በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል። ሉቃ1፥14" ....ብሎ ሲያውጅ "ደስታችን ክርስቶስ እንጅ ዮሐንስ አይደለም" ብሎ አመጽ የሚወጣ አትመለከትም።

***

አብርሐም ኬጣውያን ሣራን የሚቀበርበትን የቀብር ቦታ መስጠታቸውን እንደውለታ ቆጥሮ ለህዝቡ ሲሰግድላቸው //ዘፍ 23፥7//፤......ያዕቆብ ለታላቁ ኤሳው እየወደቀ እየተነሳ ሰባት ጊዜ እየሰገደ ሲያከብረው //ዘፍ 33፥3//......፤ሙሴ ለአማቱ ሲሰግድ// ዘጸ 18፥7//፤......ናቡከደነጾር ለዳንኤል በግንባሩ ተደፍቶ በፍርሃት ሲሰግድ //ዳን 2፥46//..... ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ብሎ እኝህ ታሪክ የተፃፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ልሰርዝ የሚል አመጸኛም አታገኝም።
***

ጸጋ ሰጭ እና ነሽ ፤ልመናን ከልካይ እና አጽዳቂ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ኤልሳ ኤልያስን .....“ መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ...2ኛ ነገ 2፥9" .....ብሎ ሲማጸነው ..."ቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ለምናለው እንጅ በመሃል ሰው አላስገባም " ብሎ የሚቃወም የለም።

***

ሳሙኤል በዕረፍተ ሥጋ ከተገታ |ሞተ| በኃላ.... “ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል። 1ኛ ሳሙ 28፥17" ....ብሎ በምድር ሳለ ያደርግ የነበረውን የነብይነት አገልግሎት ሞትም እንኳን እንደፈጸመ መጽሐፍ ቅዱስ ምስክር ሆኖ ሲናገር .... "ቅዱሳን ከሞቱ በኃላ ምንም አያውቅም ብሎ" የሚከራከር ሰው አታገኝም።

***

ነገር ግን ስለድንግል ማርያም ስትናገር.....ጩኸት እና እሪታ ይቀልጣል። ስታከብራት ዳስ ጥለው ለቅሶ ይቀመጣሉ። በታወረ ልቦና ጥቅስ ፍለጋ አይን ያባክናሉ።

ስታከብራት ጋረደች፣ስትወዳት አመለካት፣ስትሰግድላት ስግደት ለጌታ ብቻ፣ስትማጸናት ሞታለች አትሰማም ብለው ከላይ የተደረጉ ኩነቶችን ሁሉ ይዘነጋሉ።

እውነት ነው ዘማዊቷ ማርያም በንሰኃ ከዲያቢሎስን ወጥመድ አምልጣለች። አብርሃም ከካራን ነጻ ወጥቷል። ሳሙኤልም በአገልግሎት ድል ነስቷል። ዳዊትም ልባም ሆኖ ሰለሞንም ጥበብ ተጎናጽፎ ከብሯል።
***

ማርያም ግን ....ሲዖል የተበረበረበትን ዲያቢሎስን የሞተበትን የመውጊያ ጦር የሆነ ወንድ ልጅ ተገልጦባታል።

እርሷ መድኃኒት የተጠቀለለበት የሞት ገዳይ ምክንያት ሴት ሆናለች።....

ማርያም....ስሟን ውደዱ እንጅ እየተከተላችሁ አታልቅሱ

Kune Demelash kassaye -Arba Minch
19👍9👏3
38👍3🙏3🕊3👏2
#ርዕሰ ባሕታዊ (ስለ ቅዱስ ገብረ መንፈስ ቅዱስ)

በ ቃልና በኑሮህ ሆነሀል ምስክር
እንደ ፀሐይ አበራህ በእግዚአብሔር አገር
ሰማያዊ ነህ እንጂ አይደለህም ምድራዊ
ገብረመንፈስ ርዕሰ ባሕታዊ

አዝ======

በስምሙ ለሚያምኑት አማላጅ ሆነሀል
በፀሎትህም ኃይል ተማምነንብሃል
የክብር ኮከብ ነህ የገዳም መብራት
አስተምረኸኛል ምግባር ሃይማኖት

አዝ======

የሚያልፈውን አለም የምድሩን ንቀሀል
የታመንከው አምላክ ህያው አድርጎሃል
በሥጋ በነፍስህ እግዚአብሔር ከበረ
የማስታረቅን ቃል በአንተ ላይ አኖረ

አዝ======

በተጋድሎህ ብዛት በፆም በፀሎት
ትተጋ ነበረ በፀናች እምነት
ስለ ቃል ኪዳንህ በረከት ይወርዳል
ያንተ ስም ሲጠራ አጋንንት ይርዳል

አዝ======

ገብረመንፈስ ቅዱስ የእምነት አባት
አናብርት አናብስት የታዘዙለት
ከንሂሳ ተነስቶ ኢትዮጲያ ደረሰ
ፀጋው በረከቱ በእኛ ላይ ፈሰሰ

መዝሙር
በሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
3👍3
#መዝሙረ ዳዊት

#Psalms 102፡(103)።

#የዳዊት፡መዝሙር።

1፤ነፍሴ፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኪ፥ዐጥንቶቼም፡ዅሉ፥የተቀደሰ፡ስሙን።

2፤ነፍሴ፡ሆይ፥እግዚአብሔርን፡ባርኪ፥ምስጋናውንም፡ዅሉ፡አትርሺ፤

3፤ኀጢአትሽን፡ዅሉ፡ይቅር፡የሚል ፥ደዌሽንም፡ዅሉ፡የሚፈውስ፥?

4፤ሕይወትሽን፡ከጥፋት፡የሚያድናት ፥በምሕረቱና፡በቸርነቱ፡የሚከልልሽ፥

5፤ምኞትሽን፡ከበረከቱ፡የሚያጠግባት ፥ጕልማሳነትሽን፡እንደ፡ንስር፡ያድሳል።

6፤እግዚአብሔር፡ይቅርታ፡አድራጊ፡ነው፤ለተበደሉ፡ዅሉ፡ይፈርዳል።

7፤ለሙሴ፡መንገዱን፡አስታወቀ ፥ለእስራኤል፡ልጆችም፡አደራረጉን።

8፤እግዚአብሔር፡መሓሪና፡ይቅር፡ባይ፡ነው፥ከቍጣ፡የራቀ፡ምሕረቱም፡የበዛ።

9፤ዅልጊዜም፡አይቀሥፍም ፥ለዘለዓለምም፡አይቈጣም።

10፤እንደ፡ኀጢአታችን፡አላደረገብንም ፥እንደ፡በደላችንም፡አልከፈለንም።

#ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታል ፡፡ የእናንተ አስተያየት ያበረታናልና አስተያየታችሁ! ይለግሱን ።


📖📖📖📖📖📖📖📖📖

‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3

#Facebook "አርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ" በሚለው search በማድረግ #LIKE or #Follow አድርግው ከ17600 በላይ #like አለው ይቀላቀሉን በተጨማሪ #በቴሌግራም ለመቀላቀል

👇👇👇👇👇👇👇👇

@ortodoxtewahedo

ከ17200 በላይ አባል አለው
#የእናንተ አስተያየት ያበረታናልና አስተያየታችሁን በ @BREAVHEARTT ላይ ይለግሱን !

#ኦርቶዶክሳውያንን #share በማድረግ ይጋብዙ።
7👍6👏4
#ከሽማግሌዎቹም፡አንዱ አታልቅስ እንሆ ከይሁዳ ነገድ የኾነው አንበሳ ርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቷል አለኝ።

ራዕይ 5፥5

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.
6👍1
#አንድ መነኩሴ ወደ ገዳሙ አበ ምኔት ቀርቦ በምሬት እንዲህ አለ :-
"አባቴ በዚህ ገዳም ምንም ጸጋ ምንም ትሩፋት የሌለኝ መነኩሴ እኔ ብቻ ነኝ:: አባ እገሌን እዩት እንደ እርሱ የዋህ የለም! አባ እገሌን እዩአቸው እንደርሳቸው ታጋሽ ማን አለ? አባ እገሌን እዩአቸው ለሁሉ ፍቅር አላቸው!
እኔ ግን ምንም የለኝም አልረባም አባቴ እባክዎ ይጸልዩልኝ የእኔ ጸጋ የእኔ ፍሬ ምንድር ነው?" አለ እያለቀሰ::
አበምኔቱም አይዞህ ጸልይ ብለው አሰናበቱት::
እሱ ከወጣ በኁዋላ ግን አብረዋቸው ላሉት መነኮሳት እንዲህ አሉ :-
"ይህ መነኩሴ በዚህ ገዳም ካሉ ሁሉ የሚበልጥ ጸጋ ተሠጥቶታል:: የወንድሞቹ ኃጢአት አይታየውም
ጽድቃቸውን ግን በትሕትና ሲቆጥር ይውላል:: ከዚህ በላይ ምን ጸጋ አለ? ዝም ያልኩት ይህንን ብነግረው ክብሩን አሳንስበታለሁ ብዬ ነው" አሉ::
"ነፍሳችሁን ተመልከቱ የወንድማችሁንም ኃጢአት አትመልከቱ እግዚአብሔር ያያል"

#ቅዳሴ እግዚእ

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.
23👍12🥰3👏1🙏1
Forwarded from ተ҈ ዋ҈ ህ҈ ዶ҈ (👑 ናኦልዮጵያ ኢዮባዊ 👒)
🔔 ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዘበነ ለማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር እዮብ ይመኑ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
5👍4
#እንዲ እናምናለን አንታመናለን አብ ወልድ መንፋስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብለን

#እንኲን ለወርሐዊው የአብርሀሙ ሥላሴ በዓል አደረሳቹ አደረሰን

📖📖📖📖📖📖📖📖📖.

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.
🙏2
¤የኔታ እንዲህ አሉኝ:-

" የራስህ ልብ ጠላት እንዳይሆንብህ አጥብቀህ
ቆልፈው:: ግን ልብህን በባዶው አትቆልፈው:: ፈጣሪህን
ክርስቶስን : ድንግል እመቤትህን : ቅዱሳን ወዳጆችህን
ካስገባህ በሁዋላ ነው እንጂ . . .

. . . ለምን ትለኝ እንደሁ . . . ዓለም ብትናወጽ : ተራራው
ቢነቀል : ማዕበላት ቢማቱ . . . በሰላም ልብህ ከታተመ
ምንም አይመስልህም::

. . . 3ቱ ሰላሞች ደግሞ የክርስቶስ ሰላም (ዮሐ. ፲፬:፳፯) :
የድንግል ማርያም ሰላም (ሉቃ. ፩:፵፩) የቅዱሳን ሰላም (ማቴ. ፲:፲፫)
ናቸው::

. . . ይህ ካልሆነ ግን . . . ልብህን በባዶው ብትቆልፈው
ከልካይ ያጣ ሰባሪ (ሰይጣን) ገብቶ ይመላብሃል:: ወዲህ
ደግሞ 'የክርስቶስ ሰላም ብቻ ይበቃኛል' ብለህ ብትናገር
የቅዱስ መጽሐፍ ተቃዋሚና ግብዝ መሆንህ ነው::
. . . እና ደግሞ የትኛውንም ጠላት ትሸሸዋለህ:: ግን
ጠላትህ ልብህ ከሆነ (ልብህ ውስጥ ካደረ) የትም
ሸሽተህ አታመልጠውምና ልጄ ሆይ! ልብህን ለሚገባቸው
ከፍተህ : ለማይገባቸው ቆልፍ::"

"' አባቶቻችን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን:: '"

ምንጭ :- Dn Yordanos Abebe

ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.
👍61
"የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።"

#ኤፌ 6፥11

"እርሱስ በአርምሞአችን ካልተጠቀመ በመናገራችን አይጠቀምም"

#አሞ 5፥13

"ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና በዚያ ዘመን አስተዋይ የሚሆን ዝም ይላል።"
#ያዕ.1፥19

"ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን"

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo.
3
"፻፴፪ኛው መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል።

ግንቦት ፭/፳፻፲፯ ዓ/ም  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

፻፴፪ ኛው መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል።

በየዓመቱ ትንሣኤ በዋለ 25ኛ ቀን የሚካሔደው ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  ዛሬ ከሰዓት በኋላ  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  ፓትርያርክ መሪነት የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ  ይካሔዳል።

በየዓመቱ የሚካሔዱት ሁለቱ  ጉባኤያት  አንደኛ  ቋሚ በሆነ ቀን በጥቅምት 12 ሲጀምር ሁለተኛው ግን የአጽዋማቱን አዋጅ ተከትሎ በሚወጣው የባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት በዓለ ትንሣኤ በዋለ 25ኛ ቀን የርክበ ካህናት ጉባኤ ይከናወናል።

በዚህ በ2017 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ነገ ግንቦት 6/2017 ዓ/ም የሚጀምር ሲሆን በዋዜማው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ሥርዓተ ጸሎቱ ይከናወናል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የፕትርክና መንበሩ ከግብፁ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ከሰኔ 21/1951 ዓ/ም ወዲህ  አስቸኳይ ጉባኤያትን ሳይጨምር ከ131 መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት መካሔዳቸውን ታሪክ ያስረዳል።

ከነዚህ መደበኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በቅዱሳን ፓትርያርኮች ጥረት ርእሰ መንበርነት የተመሩ ሲሆን  በሁለት የተለያዩ ዓመታት ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፓትርያርክ ባለመኖሩ ምክንያት በአቃብያነ መንበር በብፁዓን አባቶች ተመርተዋል።

ከእነዚህ አንደኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ በወቅቱ በነበረው አገዛዝ ምክንያት  በግፍ ለግዞት ስለተዳረጉ ግንቦት 11 ቀን 1968 ዓ/ም የዋለውን ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቃቤ መንበር በነበሩት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የመላ ትግራይ  ሊቀ ጳጳስ ርእሰ መንበርነት ተመርቷል።

ሁለተኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 5ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ  ነሐሴ 10/2004 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በማረፋቸው ምክንያት የጥቅምቱ 12/2005 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖደስ ምልዓተ ጉባኤን የወቅቱ አቃቤ መንበር የነበሩት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  በርእሰ መንበርነት መርተዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  በቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ጉዳዮች ውሳኔ የሚሰጥበት ሲሆን እምነት የማጽናት ሥርዓትን  ማስጠበቅ አስፈላጊ ከሆነም መሻሻል ያለባቸውን ጉዳዮች  የማሻሻል ሥልጣን ያለው የቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል ነው።

“በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
  ሐዋርያት ፳፥፳፰

🔵የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ስለ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሓ ወሰላም

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
👍64
" ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ልማትና ዕድገት እናሻግራለን ብላችሁ እየደከማችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን እባካችሁ መለስ ብላችሁ እናታችሁ የተንገላታችበትን እዩና በቃ በሉ፤ሁሉን የሚያግባባ ነገር ፈልጉና ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ፍቱ፤ በዚህ ኣማራጭ እናት ሀገር እፎይታ እንድታገኝ ኣድርጉ፤ ይህንም ለውድ እናት የሚደረግ ካሣ ኣድርጋችሁ ውሰዱት።"
            ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ማትያስ

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ኣሜን!

ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጰጳስ፣
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጰሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!!

እንደዚሁም በዚህ ቀኖናዊና ዓመታዊ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ የተገኛችሁ በሙሉ፤ ጸጋንና ሓዋርያነትን ያጐናጸፈን ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ትንሣኤውን በሰላም ኣክብረን ይህንን ዓመታዊውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለማካሄድ ስለ ሰበሰበን ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን፤ የጉባኤው ኣባላት የሆናችሁ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም እንኳን ለረክበ ካህናት ጉባኤ ኣደረሳችሁ! እንኳንም በሰላም መጣችሁ!
“ረከብነ ጸጋ ወተሰየምነ ሓዋርያተ ከመ ናስምዖሙ ለኣሕዛብ ወይእመኑ በስሙ፡- ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሓዋርያነትን ተቀበልን” (ሮሜ.፩÷፭)፤
ይህ ሐዋርያዊ ኣስተምህሮ የኛን ተእልኮና ተልእኮው ያስፈለገበትን ምክንያት ኣጉልቶ ያሳያል፤ የተቀበልነው ስጦታም ምን ያህል ታላቅ እንደ ሆነ ምንባቡ ያስረዳል፤ ሓዋርያው በዚህ መልእክት የቅዱስ ወንጌል ኣስተምህሮ ዋና ግብ ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ማድረግ ነው በማለት ያስተምረናል፤ እውነት ነው ድሮውኑም ቢሆን ለእግዚኣብሔር መታዘዝ ኣቅቶን ነው የወደቅነው፤ ዛሬም የምንነሣው ከእምነት የተነሣ መታዘዝን ገንዘብ ስናደርግ ነው፤ ከሁሉ በፊት እምነት ይቀድማል፤ ከሱ በኋላ ደግሞ ለእምነቱ በሙሉ ልብ መታዘዝ ይከተላል፤ ይህ ሲሆን መዳንና ትንሣኤ ይገኛል፤ ዓለም በእግዚአብሔር እየተደረገላት ያለ ጥሪ ይኸው የመታዘዝ ጥሪ ነው፤
ይህንን መለኮታዊ ጥሪ ለዓለም የማድረስ ኃላፊነትም ለኛ ለቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት የተሰጠ እንደሆነ ሐዋርያው አስገንዝቦኣል፤ ኃላፊነቱ ሲሰጠን ከነመሳርያው ነው፤ እሱም ጸጋና ሓዋርያነት ነው፤ እኛም እሱን ተቀብለናል፤ እንግዲያውስ የተቀበልነውን ጸጋና ሓዋርያነት በዓለም ውስጥ ላለው ሕዝበ እግዚአብሔር ኣገልግሎት ማዋል ከኛ ይጠበቃል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጰሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣበላት!! 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአሁኑ ጊዜ የሌለበት ክፍለ ዓለም የለም፤ ምክንያቱም የዚህ ሲኖዶስ ወኪሎች ሊቃነ ጳጳሳት በኣፍሪካ፣ በኣውሮፓ፣ በሰሜን ኣሜሪካ፣ በላቲን ኣሜሪካ፣ በካናዳና በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በእስያና በኣውስትራሊያ ወዘተ የሚገኙ ሕዝበ እግዚአብሔር ምእመናንን በማገልገል ላይ ይገኛሉና ነው፤ ይህ ዕድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መለኮታዊ ተልኮውን በአጽናፈ ዓለም ሁሉ ለማድረስ ምቹ መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ከዚህም በመነሣት በየክፍለ ዓለሙ የሚገኙ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃነ ጳጳሳት ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ባሻገር የየአካባቢውን ሕዝብ በማስተማርና በማቀፍ የተጣለባችሁን ሓዋርያዊ ተልእኮ በትጋትና በንቃት መወጣት ይኖርባችኋል፡፡
በማእከል ሆኖ እየመራ የሚገኝ ቅዱስ ሲኖዶስም ለዚህ ተልእኮ ምቹ መደላድል የመፍጠር ኃላፊነቱን በኣግባቡ መወጣት ይገባዋል፡፡ በተለይም ትምህርተ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን  የተማሩና በጥልቀት የተገነዘቡ፣ ብስለትም ያላቸው፤ እንዲሁም በቋንቋና በሥነ ልቦና ዕውቀት የላቀ ሀብተ ጸጋ ያላቸውን በሐዋርያነት እያሠለጠነ በአጽናፈ ዓለም ሁሉ  ሊያሰማራ ይገባል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጰሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣበላት! 
በብሂለ አበው (ፀሐይ ለመስኮቷ ሳታበራ…) እንደሚባለው ለሌላው በብቃት መድረስ እንችል ዘንድ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሲኖዶሱ መንበር በሚገኝባት ምድረ ኢትዮጵያ ከመቸውም የተሻለ ስራ በመስራት ለእግዚአብሔር መታዘዝ ሕዝቡንም ማገልገል ይገባናል፤ ሁላችንም እንደ ምንገነዘበው በሲኖዶሳችን ያልታቀፉ ብዙ ወገኖች በሀገር ውስጥ ኣሉን፤ እነዚህ ወገኖች አንዳንዶቹ በተለያየ ምክንያት ከኛ የወጡ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የሄዱት ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ፣ ሌሎችም ወደ መንጋው እንዲቀላቀሉ በርትቶ መስራት የዚህ ጉባኤ ተቀዳሚ ተልእኮ ነው፤ ምክንያቱም ጸጋንና ሐዋርያነትን የተቀበልንበት ዋናው ምክንያት ይህንን ለማድረግ ነውና፡፡ ከዚህ አኳያ የቤተ ክርስቲያናችን ተደራሽነት በሳሳበት ኣካባቢ ሁሉ የተለየ ትኵረት ሰጥተን መስራትና ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይኖርብናል፤               
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!  
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውሉደ ክህነትና ምእመናን የሆን ሁላችን፣ ከሁሉ በፊት ያለንን ዓቅምና ብቃት በኣግባቡ መገንዘብ ይኖርብናል፤  ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይሁንና ለፈጣሪው በቈራጥነት የሚታዘዝ ምእመን፣ ወጣት፣ ካህን ኣለን፤ ይህ ትልቅ ጸጋ ነው፤ ይህንን ጸጋ እግዚአብሔር፡ ለእግዚአብሔር መንግሥት በሚመች ሁናቴ ዝቅ ብሎ ማገልገል የክብር ክብር ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሓቅ፣ በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ቆመን ካገለገልነውና ኣባትነታችንንና መሪነታችንን በመልካም አሰራር በትክክል በኅሊናው እንዲቀረጽ ካደረግን፣ ይህ ኃይል ከጐናችን እንደማይለይ እርግጠኞች መሆን እንችላለን፤ ይህንን ካሳካን ለኛ የተሰጠ ኃይልና ብቃት በየትም ኣይገኝም፡፡
በዚህም በዚያም ሃይማኖቱ የሚጠይቀውን ሰብእና እና ቁመና ይዘን ከተገኘን፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ ያለውን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን ሳይቀር ለመስጠት ወደ ኋላ የማይል የእግዚአብሔር ሕዝብ ኣለን፤ ስለዚህ ይህንን ማሳካት እንችል ዘንድ ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንድናስገኝ የተቀበልነውን ጸጋና ሐዋርያነት በክብር እንያዝ፤
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!!
ለሕዝበ እግዚአብሔር የምናበረክተው ኣገልግሎት በመንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚውና በማኅበራዊው ኣገልግሎትም ጭምር ነው፤ ከዚህ ኣንጻር ሕዝባችን የተሻለ ማኅበራዊ ኣገልግሎት እንዲያገኝ፣ በኢኮኖሚውም ከድህነት የተላቀቀ እንዲሆን፤ እንደዚሁም ሰላሙና ኣንድነቱ የተጠበቀ እንዲሆን፣ በማስተማርም በተግባር በመሳተፍም የሕዝቡ መሪዎችና ኣርኣያ ሆነን መስራት ይገባናል፤በተለይም ከሰላም እጦት የተነሣ በእጅጉ እየተጎዳ ያለውን ሕዝባችን ሰላምና ፍትሕ እንዲያገኝ በጸሎትም በትምህርትም፣ በምክርም ተግተን መስራት ኣለብን፤


#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
👍61
2025/07/14 11:18:47
Back to Top
HTML Embed Code: