Telegram Web Link
#like#share
ወደደንም ጠላንም እኝህ አባት የብዙ ኦሮቶዶክሳዊያን ስማእታት ደም በእጃቸው አለ ። ammatanis Amanuu baataniAbbaan keenyi kun Dhigga wareggamtoottaa Harka isaani irra jira.
ዲ/ን ዶር ቴዎድሮስ በለጠ ከአንድ ዓመት የጽሙና ጊዜ በኋላ ቀሪ ጊዜያቸውን በምንኩስና ሕይወት ለመኖር ጉዞውን ጀምረዋል። አባ ክፍለ ሥላሴም እንደ ተባሉ ምንጮች ገልጠዋል። የአበውን ጸጋ ሰጥቶ ያጽናልን
“ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤” 1ኛ ቆሮ 7፥32

ምንጭ፦ማ/ሚድያ

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የብርሃን እናት ነሽና /፪/
ለምኝልን ድንግል /፪

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
ዲ/ን ፈለገ አትናቴዎስ

ብርቱ አርቶዶክሳዊ ወጣት ቤተ ክርስትያን ብዙ ፈለገዎች ያስፈልጓታል በርታልን ወንድማችን ።

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
‘‘እኔና ልጄ ሰግደን እንመለሳለን‘‘ ...
EOTC Germany Archdiocese የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት
እኔና ልጄ ሰግደን እንመለሳለን
  
           
Size:-54.4MB
Length:-58:44

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ


#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
የቅዱስ ሲኖዶስ  መግለጫ

ግንቦት ፳/፳፻፲፯ ዓ.ም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ አካሂዷል፡፡
የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነትና እድገት፣ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋትና ለመንፈሳዊ ልዕልና ልዩ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ለሰላምና ለአንድነት ቅድሚያ መስጠት፣ምትክ ለሌለው የሰው ልጅ ሕይወት ባለአደራ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ሰላም ያለማቋረጥ መጸለይ፣ ጸሎተ ምሕላ ማወጅ፣ የሰላምና የአንድነት ጥሪ ማስተላለፉ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሰላምና ለአንድነት ልዩ ትኩረት ሰጥተው ሁሉን አቀፍ ሥራ የሚሠሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ኮሚቴ” በማድረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
ኮሚቴውም ዘላቂ ሰላምንና አንድነትን ለማስፈን፣ የዜጎችን ሕይወት እየነጠቀ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥረት እንዲያደርግ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ባካተተ መልኩ በየደረጃው የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና፣ ውይይቶችንና የጥናት መድረኮችን እንዲያዘጋጅ፤ አፈጻጸሙንም በየሦስት ወሩ ለቋሚ ሲኖዶስ ሪፖርት እንዲያደርግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

@ortodoxtewahedoo
2. ለሰዋስው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የትርጓሜ መጻሕፍትና የሴሚናሪ ደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት ዲግሪ እንዲሆን በተወሰነው መሠረት በመማር ላይ ያሉትና በቀድሞው ሥርዓተ ትምህርት ተምረው በመመረቅ ቤተ ክርስቲያናችንን በማገልገል ላይ የሚገኙት ምሩቃን ተጓዳኝ ትምህርቱን ተምረው ዲግሪያቸውን ማግኘት እንዲችሉ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ እንዲደረግ፣በኮሌጁ የተጀመረው ሁለገብ ሕንፃም በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት እንዲጠናቀቅ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3. በገዳማት አስተዳደር መምሪያ አስፈጻሚነት የተደረገው የአንድነት ገዳማት ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ በየዓመቱ እንዲካሄድና የአቋም መግለጫው ላይ የቀረቡት ሐሳቦች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በኩል እየታዩ በቅደም ተከተል እንዲፈጸሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስልፏል፡፡
4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችን እድገትና ሥልጣኔ ፈር ቀዳጅ በመሆን ያበረከተችው አስተዋጽኦ በታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ጉልህነት ያለው ሲሆን፣ አሁንም እየተሠራ ባለው የኮሪደር ልማት መርሐ ግብር ላይ ኃላፊነቷን እየተወጣች ትገኛለች፡፡
ይኽን ቋሚ ታሪክ ያልዘነጋው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ለግንባታ በሚያመች ሁኔታ አሰባስቦ በመስጠት ለፈረሱ ቤቶች ካሣ በመክፈል፣ በጽርሐ ምኒልክ ሕንጻ ምትክ በነባሩ ቦታ ላይ B+G+4+ቴራስ በመንግሥት በጀት መልሶ እንዲገነባ በማድረጋቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

በይዞታዎቻችንም ላይ ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ ለማካሄድ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተሰይሞ ገቢ የማሰባሰብ ሥራው በሕጋዊ መንገድ እንዲከናወን ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም በፈረሱት ቤቶች ምትክ የተረከብናቸውን ክፍት ቦታዎች በአጭር ጊዜ ማልማት ግዴታ ስለሆነ በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እንደ አባቶቻችሁ የታሪክ ባለቤቶች ትሆኑ ዘንድ ልማቱን በገንዘብና በእውቀት እንድታግዙ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
5. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተፈጠረውን የአስተዳደር ችግር አስመልክቶ በብፁዓን አባቶች የሚመራው አጣሪ ልዑክ ባቀረበው ሪፖርት መሠረት ውይይት በማድረግና የሥራ ኃላፊዎቹን በማንሣት ቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
ወደፊትም በየደረጃው ያለውን ችግር ማስተካከል ይቻል ዘንድ ችግሩን እያጠና የሚያቀርብ ኮሚቴ እንዲቋቋም ምልአተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

6. ዝክረ ኒቅያ በሚል መሪ ቃል ከመላው ሀገራችን በተወከሉ የምስክር ጉባኤ ቤቶች መምህራን በተካሄደው ጉባኤና የጥናት ውይይት የቀረበው ምክረ ሐሳብ እጅግ የሚጠቅም የሊቃውንት ድምጽ በመሆኑ፣በነገረ ማርያም፣ በነገረ ክርስቶስና በሌሎችም አስተምህሮዎች ዙሪያ የተሰጡት ሐሳቦች የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜን መሠረት በማድረግ ተብራርቶና ተስተካክሎ፣ የጎደለው ሞልቶ፣ የጠመመው ተቃንቶ በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በመጽሐፍ መልክ እንዲታተም፣በሚዲያ ሊተላለፍ የሚገባው አስተምህሮ ደግሞ በሊቃውንት ጉባኤ ብቻ እንዲተላለፍ፣
የሊቃውንት ጉባኤውም በተሟላ የሰው ኃይልና በጀት ተጠናክሮ እንዲደራጅ፣ሀገር አቀፍ ጉባኤው በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲደረግና የጉባኤው መዋቅር በየአህጉረ ስብከቱ እንዲጠናከር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

7. የመናገሻ አምባ ማርያምና የጋራው ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም ጥንታዊ የሆነ ሰፊ ታሪክ ያለው በመሆኑ ሁለቱ ገዳማት በአንድ አበምኔት በአንድነት ገዳም ሥርዓት በጋራ እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤

8. በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት መነኰሳትን ከመላክ ጀምሮ፣በአስተዳደራዊና ቀኖናዊ አሠራር ክፍተት ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን በማረምና ሊቀ ጳጳሱን በማዛወር ማእከላዊ መዋቅር እንዲጠበቅ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ሲሆን፣ነባሩ መተዳደሪያ ደንብ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ሰይሟል፤

9. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ልቡና፣በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል ያገኘቻቸው ዶግማዊ፣ ቀኖናዊና ትውፊታዊ ሀብቶቿ የሕግ ጥበቃና ከለላ አግኝተው ሃይማኖታዊ፣ታሪካዊና ሁለንተናዊ ይዘታቸውን ሳይለቁ ተከብረውና ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
10.  የ2018 ዓ.ም የመደበኛ እና የካፒታል ዓመታዊ በጀት ብር 5,407,415,607.25/አምስት ቢሊየን አራት መቶ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ዐሥራ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ሰባት ብር ከሃያ አምስት ሣንቲም/እንዲሆንና የበጀት አርዕስቱ ተጠብቆ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11. በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ሕንጻ በተመለከተ የተፈጠረው የአሠራር ግድፈት እንዲታረም፣ዩኒቨርስቲው ከባንክ ጋር የገባው የብድር ውል እንዲቋረጥና የተጀመረውን ሕንፃ በራሱ አቅም እንዲገነባ ሆኖ፤ የቤተ ክርስቲያናችንን አንጡራ ሀብት ማለትም ሕንጻዎችን፣መሬቶችንና ሌሎች ቋሚ ንብረቶችን በማስያዝ የሚደረጉ ብድሮች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ የሚያደርግ መመሪያ ለሁሉም አህጉረ ስብከት እንዲተላለፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
12. የቤቶችና ሕንፃዎች አስተዳደር ልማት ድርጅትን አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት መሠረት የሥራ ክፍተቱን በማረም በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች እንደየጥፋታቸው እንዲጠየቁና እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
13. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምርጫን አስመልክቶ በሥራ ላይ የነበሩት ብፁዓን አባቶች የሥራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ በመሆኑ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚሠሩ ብፁዓን አባቶችን ለመምረጥ ዕጩዎችን የሚያቀርቡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመሰየም ምልዓተ ጉባኤው ተገቢውን ምርጫ አከናውኗል፡፡
በዚሁም መሠረት ፡-
*. ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ በደቡባዊ ዞን ማይጨው፣ የደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን መርጦ ሰይሟል

*. ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪጅነት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣የሸገር ከተማ እና የምስካዬ ኀዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀጳጳስን መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀድያና ስልጤ አህጉረ ሰብከትን እንደያዙ  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መርጦ ሰይሟል፡፡
* ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ
* ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሜኖሶታና የኮሎራዶ አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መድቧል፡፡

@ortodoxtewahedoo
14. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ሰብከት ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች አህጉረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካልፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሚዲያ ያስተላለፏቸው ትምህርቶች ስሕተትና ነቀፋ ያለባቸው  መሆናቸውን አምነው ቅዱስ ሲኖዶስንና መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ይቅርታ በመጠየቅ ሊቃውንት ጉባኤ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቅስ ያቀረበውን አስተምህሮ የተማሩት የሚያምኑትና የሚያስተምሩት መሆኑን በመግለጻቸው ቅዱስ ሲኖዶስ የሦስቱን አባቶች ይቅርታ ተቀብሎ ወደፊት እንዲህ ዐይነት የስሕተት  ትምህርት ውስጥ እንዳይገኙና ነቀፋ ያለበትን ትምህርታቸውን በማረምና በማስተካከል  ርቱዕ የሆነውን የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  መገናኛ ብዙኀን ሥርጭት ድርጅት በመቅረብ ትምህርት እንዲሰጡ በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
15. በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ በግልና በቡድን ተደራጅተው ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመክፈት ከሃይማኖት ሥነ ምግባር በወጣ መልኩ የቤተ ክርስቲያናችንን ልዕልና የቅዱስ ሲኖዶስን ክብር የሚጋፋ ፣የአባቶችንና የአገልጋዮችን ተልእኮ የሚያደናቀፍ ያልተገባና መሠረት የሌለው መግለጫ የሚያሰራጩ አካላት እንዲታረሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

በመጨረሻም በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታየው ግጭትና መፈናቀል ተወግዶ፣የሰው ልጅ የመኖርና የመዘዋወር መብት ተከብሮ፣ ሰብዓዊ ክብሩ ተጠብቆ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በጋራ እንዲኖር፤ አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

ግጭት፣ ጥላቻና ደም መፋሰስ፣ አካል ከማጉደልና ንብረት ከማጥፋት በቀር የሚያመጡት ክብርና ዘላቂ ሰላም ስለሌለ ልጆቻችን ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንድትፈቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ደጋግሞ ጥሪውን በማቅረብ በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላምና ዕርቅ እንዲሰፍን በመጸለይ ቅዱስ ሲኖዶስ ግንቦት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ዓመታዊ ጉባኤውን በጸሎት አጠናቋል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ

                  አባ ማትያስ ቀዳማዊ
      ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@ortodoxtewahedoo
‘‘ትዳር‘‘ በርእሰ ሊቃውንት ቆሞስ አ...
EOTC Germany Archdiocese የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት
ትዳር
  
           
Size:-61.2MB
Length:-1:06:04

    በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
+ ደብረ ምጥማቅ +

ከሠላሳ ሶስት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው ግንቦት_21 ቀን የሚከበረው ይህ የእመቤታችን በዓል ደብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ የወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ሲሆን በዚህ ቀን በግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ተገለጽላቸው ነበር ።

እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር ይኸውም አልቀረም በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል ።

በዚህ ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበር ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሣት ታይታለች

እስከ አምስት ቀንም ምእመናኑን አረማውያኑን አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች ከዚህም በኋላ ምእመናንም አረማውያንም በየዓመቱ እነዚህን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 25 ለአምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል ።

እኛም ለልጆቿ በሕይወታችን እየተገለጠች በረድኤት በበረከት ትባርከን !!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ነው።

ይህም በዓል ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር።

እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየአገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ ፤ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተ...ከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር።

ህዝቡ የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል ግማሹ ነብዩ ዳዊትን ግማሹ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል፤እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር።

አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው።የእመቤታችን ረድአት እና በርከቱ በሁላችን ላይ ይድርብን አሜን 🙏

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የመገለጥ በዓል (ደብረ ምጥማቅ) በሰላም አደረሳችሁ †

†ደብረ ምጥማቅ †

=>የአርያም ንግሥት: የሰማይና የምድር እመቤት: የሰውነታችንም መመኪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በዚሕች ዕለት በምድረ ግብፅ ለተከታታይ ቀናት ተገልጻለች::

+ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:

+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድረ ግብፅና ኢትዮዽያ በተሰደደ ጊዜ ከድንግል እናቱ: ከዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ዛሬ ደብረ ምጥማቅ በሚባለው ቦታ ላይ አርፎ ነበር:: ቦታውን ባርኮ ለዘለዓለም ያንቺ መገለጫ ይሁን ብሎም ቃል ኪዳን ገብቶላት ነበር::

+ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት ቤት ሆነ:: እመቤታችንም በልጇ ፈቃድ ግንቦት 21 ቀን አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላት መጣች::

+በዚያ ሕዝበ ክርስቲያንም: አሕዛብም ተሰብስበው ለ5 ቀናት ከእመ ብርሃን ጋር ይሰነብታሉ:: እንግዲህ ልብ በሉት:-
እንኩዋን የአርያም ንግስት: የአምላክ እናቱ እመቤታችንን ይቅርና በዚሕ ዓለም ሰይጣን ቤቱ ያደረጋቸውን: የመዝናኛው ኢንዳስትሪ ዝነኛ ሰዎችን ለማየት የዘመናችን ሰው እንዴት እንደሚቸኩል::

+እመቤታችንን በአካል መመልከት አይደለም ስሟን መጥራት ነፍስን ከሥጋ መለየት የሚችል ጣዕምና ደስታ አለው:: ባይሆን ይሔ ለሚገባውና ላደለው ብቻ ነው::

+የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች ከእመቤታችን ጋር የሚቆዩባቸው ቀናት የዘለዓለም የሕይወት ስንቅ የሚይዙባቸው ናቸው:: ፈልገው የሚያጡት: ጠይቀው የማይፈጸምላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግል: መነኮሳት: መላዕክትና ሊቃነ መላእክት ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበርና:: እመ ብርሃንም እየመላለሰች ትባርካቸው ነበር::

+እነዚያ እርሷን ያዩ ዐይኖች: በፊቷ የቆሙ እግሮች ክብር ይገባቸዋል:: 5ቱ ዕለታት ሲፈጸሙ ሕዝቡ እመቤታችንን በዕንባ ይሰናበቷታል:: እመ ብርሃንም በብርሃን መስቀል ባርካቸው ከቅዱሳኑ ጋር ታርጋለች::

እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጽልን:: ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን: ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን:: †††

"+ የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ::
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው::
ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው::
በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . .
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ::
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ::
ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ::

+"+ (መዝ. 44:12-17)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
ስርዓተ ኦሪት ስርዓተ ሀዲስ ከተፈጸሙባቸው 5 መቅደሶች መሐከል እንዷ የሆነችው የደቡቧ ኮከብ ብርብር ማርያም ነገ የእናታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ መገለጧን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች።
~~~

የደቡብ ክልል የክርስትና መነሻ እና የጥንታዊ ህገ እግዚአብሔር አምልኮ ማዕከል የሆነችው በጋሞ ጎፋ ሀገረስብከት የምትገኘው ብርብር ማርያም ነገ የእናታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ መገለጧን በደምቀት ታከብራለች።

በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሰዋተ ኦሪት ከተፈጸመባቸው 5ቱ መቅደሶች መሀከል አንዷ የሆነችው ብርብር ማርያም ገዳም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓላትን እንደ ብሔራዊ በዓላት ልክ የአከባቢው ምዕመናንን እንደሚያከብሩ ይታወቃል።

የቴሌግራም ቻናላችን ከታች ያለውን ሊንክን በመስፈንጠር ቤተሰብ ይሁኑን፤

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
❖ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል በሰላም አደረሰን/አደረሳችሁ።

#ዕርገት

ቤተክርስትያናችን ከምታከብራቸው በዓላት ውስጥ አንዱ የጌታችን የመድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ዕርገት ነው።ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከሞት ከተነሳ በ፵ኛው ቀን ማረጉን በማሰብ ቤተክርስትያናችን ዕርገትን ትንሳኤን በተከበረ በ፵ኛው ቀን ዕርገትን ታከብራለች።በዚህ ዓመትም ቤተክርስትያነችን ዕርገትን ግንቦት21 ታከብረዋለች።
ዕርገት ልክ እንደ ትንሳኤ ሁሉ ቀኑ ይለዋወጣል። ነገር ግን ምንጊዜም ዕርገት ሐሙስን አይለቅም።ልክ ትንሳኤ እሁድን ስቅለት አርብን እደማይለቅ ሁሉ እርገትም ሐሙስን አይለቅም።

ዐረገ በስብሐት

ዐረገ በስብሐት ዐረገ በእልልታ
በስብሐት በእልልታ ዐረገ በስብሐት በእልልታ
አዝ
ሞትን ደል አድርጎ የሰራዊት ጌታ
አረገ በስብሐት በእልልታ
አዝ
እየዘመሩለት መልአክት በደስታ
አረገ በስብሐት በእልልታ

❖ መልካም በዓል #ምሽት/ቀን ይሁንልን።


#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
☞ግንቦት 26 እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የልደት በዓላቸው
በሰላም አደረሳችሁ፡፡
☞አባታቸው ፍሬ ቡሩክ እናታቸው ዮስቴና የሚባሉ በሕገ እግዚአብሔር፡
በሃይማኖት በምግባር ጸንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች የገኙ አባት ናቸው፡፡
☞አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፤ ውልደታቸው ግንቦት
26፤ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡
☞አቡነ ተክለሃይማኖት አቡነ ሀብተማርያምን አምስት መቅሰፍታት እንዲጠፋ
በደጄ በደብረ ሊባኖስ ተቀበርልኝ ብለው የለመኗቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ይህ
እንዴት ነው ቢሉ
☞አቡነ ተክለሃይማኖት እኔ ከተቀበርኩበት ቦታ እድትቀበር ቃልኪዳን ግባልኝ
ብለው ጠየቋቸው፡፡
☞አቡነ ሀብተማርያምም አባቴ ሆይ ይህንን አደርግ ዘንድ ሰለምን ትወዳለህ?
አላቸወ፡፡
☞አቡነ ተክለሃይማኖትም በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅስፍቶች አሉና
ሰለዚህ ነው እነዚህም አንዱ መብረቅ ሁለተኛው ቸነፈር ነው ሦስተኛው ረሀብ
ነው፤ አራተኛው ወረርሽኝ ነው አምስተኛው የእሳት ቃጠሎ ነው፡፡ የአንተ አጽም
በውስጡ የተቀበረ እንደሆነ ከነዚህ መቅስፍታት ትድናለች አሏቸው፡፡
☞አቡነ ሀብተ ማርያም ንዑድ ክቡድ የምትሆን አባቴ ሆይ ልዩ ክብር በሚሆን
በአንተ አጽም መቀበር ያልዳነች በእኔ አጽም መቀበር ድኅነትን ታገኛለችን?
ብለው ተከራከሩ በዚህም ጊዜ አቡነ ተክለሃይማኖት መልሰው
☞አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር የተሰጠህ እኔ የማውቀው
ክብር አለህና ሰለዚህ ነው፡፡ ይልቅስ እንዳልኩህ በተቀበርኩበት ቦታ እንድቀበር
ቃልኪን ግባልኝ ብለው ማለዷቸው፡፡
☞ይህንንም ሲባባሉ እንዲህ የሚል ቃል መጣላቸው ከወዳጄ ከሀብተ ማርያም
እንደበት ይህ ቃል አይወጣም፤ ዳግመኛም ወዳጄ ተክለሃይማኖት ሆይ እርሱ
በወደደው የሚቀበር አይደለምንና እኔ ከተቀበሩኩበት እንድትቀበር ብለህ
የምታስገድደው ለምንድ ነው?
☞እኔ በወደድሁት ቦታ ይቀበራል እንጂ የሚል ቃል ተነገረ፡፡
☞አቡነ ተክለሃይማኖትንም እየለመኑና እየሰገዱከሥላሴ ዙፋን ተንበረከኩ፡፡
☞በሦስተኛውም ይሁን እንዳልከው ይቀበርልህ የሚል ቃል ተሰማ፡፡
☞ዳግመኛ በአንተም አጽም በሀብተ ማርያምም አጽም ቦታህ ከመቅሰፍት
ትድናለህ ልጆችህ ግን በቸነፈር ደዌ ቢሞቱ ከሰማዕትነት ተቆጥሮላቸው ወደ
መንግሥት ሰማያት እንዲገቡ በራሴ ምዬ ቃልኪን ገብቼለሃለሁ አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አቡነ ተክለሃይማኖት እጅግ ደስ ተሰኙ፡፡

(ገድለ አቡነ ሀብተማርያም)

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
2025/07/05 15:57:24
Back to Top
HTML Embed Code: