Telegram Web Link
🔴 መድኃኔአለም 🔴
✍️✍️✍️
መድኃኔአለም ማለት አለምን ያዳነ የአለም መድኃኒት ማለት ነው። ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀድሞ ክብሩ መለሰው። ምን አይነት ፍቅርነው?????
ወንድሜ /እህቴ አስባችሁታል ግን እኛን ለማዳን ብሎእኮ ነው

የተሰቀለው፡ራቁቱን በመስቀል ምን ያህል
አሳፋሪ እንደሆነ እናውቀዋለን
ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ መስቀሉን ናቀው።
በፈጠራቸው ፍጥረት ተተፋበት።
እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት
እየቻለ እርሱ ግን

💖በፍቅር እያዩ የማያውቁትን አያውቁምና
አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር።
ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድበት
አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም
ሲታበዩበት ሁሉ እርስ ግን በትህትና ያያቸው ነበር።

💖ታዲያ እኛ ደግሞ እራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።
ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንባላለን።
በ 5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።

በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያም ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ። አንተም በመስቀሉ ስር
ለመገኘት ከፈለግህ ትእግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።

መድኃኔአለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።

#27 ❤️

"ወዳጄ ሆይ ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው በጌታችን እራስ ላይ እሾህ እዳቀዳጁት ባሰብህ ጊዜ እጅግ ማዘንህ አይቀርም ። ሆኖም አንተም እሾህ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሰራህ ቁጥር በጌታችን ላይ የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ ።በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን ወታደሮች ከጎነጎኑት እሾኽ በላይ የጌታችንን እራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው ደሙን አፍስሶ ያዳነን እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን የምንጎነጉነው የእሾኽ አክሊል ነው ።{ስለመተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል ።!}

{በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ከሚለው ርዕስ የተወሰደ )

[ ሕማማት]
{በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ}

መድኃኔዓለም ሆይ አባት ሆይ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ፥ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህን በጦር በወጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ ።
መድኃኔዓለም ሆይ ጻድቃንን ያይደለ ኃጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ስነ መልክህ ሰላም እላለሁ !

( መልክአ - መድኃኔአለም )27

@ortodoxtewahedo
መ/ር ልደተቃል

ብርቱ አርቶዶክሳዊ ወጣት ቤተ ክርስትያን ብዙ ልደተዎች ያስፈልጓታል በርታልን ወንድማችን ።

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
#በዓለ ጰራቅሊጦስ

የቤ/ክ የልደት ቀን

‹‹ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም›› /ዮሐ. 14፥18/

ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ ግሪክ ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት መጽንኢ በእምነት የሚያጸና፣ መንጽሒ ከኃጢአት የሚያነጻ፣ ናዛዚ ያዘኑትን የሚያረጋጋ፣ መስተፍስሒ፣ የተጨነቁትን የሚያስደስት፣ ከሣቲ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው፡፡

ጰራቅሊጦስ፡- መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ የጰራቅሊጦስ በዓል ታሪክ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም የሚሠራውን ሥራ ከጨረሰ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያትን ወደ አባቴ እሄዳለሁ (አርጋለሁ) ሲላቸው ደነገጡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም መደንገጣቸውን አይቶ ‹‹ኢይደንግድክሙ ልብክሙ እመኑ በእግዚአብሔር ወእመኑ ብየ እስመ ውስተ ቤተ አቡየ ብዙኅ ማኅደር ወምዕራፍ ቦቱ›› (ልባችሁ አይደንግጥባችሁ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም እመኑ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ማለት ባባቴ ቤት በመንግሥተ ሰማያት ብዙ ማዕርገ ሀብታት አለ) /ዮሐ. 14፥1)

እንዲሁም /በዚሁ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14፥18/ ላይ እንደተጻፈው ‹‹ኢየጎድገክሙ ዕጓለ ማውታ ትኩኑ›› (ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም) ሲል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያትን አጽናንቷቸዋል፡፡

/በሉቃስ ወንጌል 24 ቁጥር 49/ ላይ እንደተጻፈው የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያርግ ሲል ቅዱሳን ሐዋርያትን ‹‹አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኃይለ እምአርያም›› (እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ) አላቸውና ዐረገ፡፡ እነርሱም ይህን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ በኢየሩሳሌም በጽርሐ ጽዮን በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው ተሰብስበው ሳሉ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአረገ በአሥረኛው ቀን በተነሣ በሃምሳኛው ቀን የጰራቅሊጦስ እለት ጧት በሦስት ሰዓት ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወረደላቸው ከዚህ በኋላ ፍርሃት ከውስጣቸው ወጣ መንፈሳዊ ድፍረት አገኙ፡፡

አንድ የዕብራይስጥ ቋንቋ ብቻ ነበር የሚያውቁት ሰባ አንድ ዓይነት ቋንቋ (የአገሩ ሁሉ ቋንቋ) ተገለጸላቸው፡፡ ከእነርሱ ጋር በሰባ ሁለት ዓይነት ቋንቋ ተናገሩ፡፡ የአገሩ ሁሉ ቋንቋ የተገለጸላቸውም ሁሉንም በአገሩ ቋንቋ እንዲያስተምሩ ነው፡፡ ከተለያየ ክፍለ ዓለም የመጡ ነበሩ፡፡ እነዚህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? እንዴት የእኛን አገር ቋንቋ ሊናገሩ ቻሉ? በማለት ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው እንጃ ይህ ምን ይሆን? አሉ፡፡ ሌሎች ግን ጉሽ የወይን ጠጅ ጠጥተው ሰክረው ነው አሉ ነገር ግን ቅዱስ ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፡- የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፡- ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ፡፡ ለእናንተ እንደመሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ ገና ሦስተኛ ሰዓት ነውና ነገር ግን ይህ በነቢዩ ኢዩኤል የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፡- ይህም ‹‹እግዚአብሔር ይላል በኋለኛይቱ ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ ደግሞም በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮች ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ትንቢትም ይናገራሉ፡፡ ድንቆችንም በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር ደምም፣ እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል የታወቀችዋም ታላቅዋ የእግዚአብሔር ቀን ሳትመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል›› /ኢዩ. 2፥28-32/ ይህን መሠረት በማድረግ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ልብን የሚነካ ትምህርት ሰጠ፡፡

ሕዝቡም ቅዱስ ጴጥሮስ በሰጠው ትምህርት ልባቸው ተነካ ቅዱስ ጴጥሮስንና ሌሎቹንም ሐዋርያት ወንድሞች ሆይ ምን እናድርግ? አሉአቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ ተጠመቁ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡ የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነው
ስለዚህ ራሳችሁን ከዚህ ክፉ ዓለም አድኑ ብሎ መከራቸው፡፡ በዚህ ቀን ሦስት ሺህ ሰዎች አምነው ተጠመቁ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው የሞቱና የትንሣኤው ምስክሮች ሆኑ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በነሱ ላይ ሲያድር ለቤተክርስቲያን ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ፡፡

ይህ የጰራቅሊጦስ በዓል በግሪኮች ቋንቋ ጰንጠቆስጤ ይባላል፡፡ ጰንጠቆስጤ ማለት ሃምሳኛ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ከተነሣ በኋላ ሃምሳኛው ቀን ነው፡፡ ይህም ዕለት በዓለ ሃምሳ፣ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡

እንዲሁም ታላቁ ሊቅ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን በዓል በሚገባ አነጋገር ‹‹የቤተክርስቲያን የልደት ቀን›› ብሎታል፡፡ ይህ በዓል በብሉይ ኪዳን የእሸት በዓል (በዓለ ሰዊት) ይባላል፡፡ እስራኤል የነጻነት በዓላቸውን ከሚያከብሩበት ከበዓለ ፋሲካ ጀምረው ሃምሳውን ቀን በዓል አድርገው ይሰነብታሉ፡፡ በሃምሳኛው ቀን በዓለ ሰዊትን (የእሸት በዓላቸውን) ያከብራሉ፡፡ በሀገራቸው ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለው ወቅት በሀገራችን ከመስከረም እስከ ኅዳር እንዳለው የእሸት ወራት (የጸደይ ወራት) ነውና የእሸት በዓላቸውን የሚያከብሩት በኦሪት ዘሌዋውያን /ምዕራፍ 23፥10-17/ በታዘዘው መሠረት ማንኛውም እሥራኤላዊ ገበሬ ከዘራው ሁሉ በያይነቱ እሸቱን ቆርጦ ተሸክሞ ወደ ምኩራቡ ይመጣል፡፡ በቤተ መቅደስ የሚያገለግለው ካህን ተቀብሎ ባርኮ ጸልዮ የሚጠበሰው እየተጠበሰ የሚታሸው እየታሸ በማኅበር አንድነት ይበላል፡፡ ይህም ‹‹ቀዳምያት›› ይባላል፡፡ የመጀመሪያው ማለት ነው፡፡ ከማንኛውም በረከት የመጀመሪያው እግዚአብሔር ፊት መቅረብ፣ ለእግዚአብሔር መሰጠት እንዳለበት ታዟልና፡፡

በዚህ መሠረት ከበዓለ ጰራቅሊጦስ የምንማረው፡-ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያትን ‹‹እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ›› ባላቸው መሠረት በኢየሩሳሌም ተቀምጠው ተስፋውን ሲጠባበቁ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል፡፡ ዛሬ መንፈስ ቅዱስ የሚወርድባት ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ናት ‹‹ ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት ወዕፅብት ዛቲ ሰዓት እንተ ባቲ ይወርድ መንፈስ ቅዱስ እመልዕልተ ሰማያት›› (ይህች ቀን ምን ያህል የምታስፈራ ናት? ይህች ሰዓት ምን ያህል የምታስጨንቅ ናት? መንፈስ ቅዱስ ከሰማየ ሰማያት የሚወርድባት) /ሥርዓተ ቅዳሴ/ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ እንደ ወረደላቸው ለእኛም እንዲወርድልን ሁልጊዜ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ይገባል፡፡ ከቤተክርስቲያን ተለይቶ ጽድቅ የለም።

ቤተ ክርስቲያን፡- የመንግሥተ ሰማያት በር ናት ‹‹ዛቲ ይእቲ ኆኅታ ለሰማይ›› (ይህች የሰማይ ደጅ ናት) /ዘፍ 28፥17/
በዚህ መሠረት ለእኛም በ40 ቀንና በሰማንያ ቀን የተሰጠን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እንዳይለየን ሕጉን ትእዛዙን መጠበቅና ጧት ማታ ወደ ቤተ ክርስቲያን መገስገስ ይገባል፡፡
ለዚህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ቅዱሳን በአማላጅነታቸው ይርዱን፡፡ አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡
***

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
ብዙ ስለበደልኩ በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ የሚቻለኝ አይደለሁም አትበል፡፡ ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ተስፋ በመቁረጥ ምክንያት ኃጢአትህን አትጨምር፡፡

መሓሪ በሆነው _ አምላክ ርዳታ ወደ ቀደመ ማንነትህ መመለስ ይቻልሃል፡፡ እርሱ እንዲህ ብሏልና፡- ወደእኔ የመጣውን ወደውጪ _ አላወጣውም፡፡/ዮሐ 6፡37/

እርሱ ንጽሐ ባሕርይ ስለሆነ ወደ እርሱ የሚቀርቡ ወገኖችን እንደሚያነጻቸው እንደሚቀድሳቸውም እውነተኛ የሆነ ንስሐን እመን፡፡

እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡-

« ከክፋት ተመልሰህ መልካም ነገርን አድርግ፡፡/1ኛ ጴጥ 3፡11/

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
"ጾመ ሀዋርያት(የሰኔ ጾም)"

ይህ ፆም ሐዋርያት ለማገልገል ከመሰማራታቸው በፊት አገልግሎታቸው የቀና እንዲሆን ለመንፈስ ቅዱስ ስራ መለየትን እግዚአብሔር እንዲሰጣቸው በመለመን የፆሙት ፆም ነው ::

ሐዋ 13:1-3

መሰረታችን ሐዋርያት ናቸውና የዋኖቻችንን ሥራ እኛም መፈጸም ስላለብን እንጾመዋለን፡፡
ሐዋርያትን እንዳፀናቸው በአገልግሎቱም እንዳበረታቸውና እንደለያቸው ሁሉ እኛም እንዲያፀናን እንዲያበረታን በመማፀን ለመልካሙ ሥራ እንተጋ ዘንድ በመለመን እፆመዋለን ከጵራቅሊጦስ ማግስት ጀምሮ ሐምሌ 5 በመፆም ይፈጸማል።

እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን የበረከት ጾም ይሁንልን

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
“ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።”

  — 1ኛ ቆሮንቶስ 10፥13


#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
Audio
ያሉበትን ቤት ሁሉ ሞላው
         በዓለ መንፈስ ቅዱስ
Size:-28MB
Length:-1:20:27

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
  
           
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር


🕹 #ጊዜ_አጠቃቀም

👍 #የጊዜ_አጠቃቀም_ጥቅሞች

🔸የጊዜ አጠቃቀም ጥቅሞች እንደየሰው ቁጥራቸው ሊጨምርና ሊያንስ ይችላል፡፡ እዚህም ጋር የሚከተሉት ሦስት ዋና ዋና ጥቅሞች ቀርበዋል፡፡

1⃣ በሌሎች ዘንድ የሚኖረን ተቀባይነት ከፍ ይላል


🔹አገልጋዮች ከፍተኛ የሆነ ማኅበራዊ ቁርኝት የሚጠበቅብን በመሆኑ የጊዜ አጠቃቀሙን መጀመርና መልመድ በምናደርገው ግንኙነት የሚጠበቅብንን በጊዜው እንድናከናውን ይረዳናል፡፡

🔸በዚህም በሰዎች ዘንድ የተግባር ሰው፣ ቃል አክባሪ፣ ትጉህ፣ ወዘተ የእኛ መገለጫዎች ይሆናሉ፡፡

🔹እነዚህ እሴቶች ደግሞ በመንፈሳዊውም ሆና ዓለማዊው እንቅስቃሴያችን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጉልናል፡፡

2⃣ የተመጣጠነ ሕይወት እንድንመራ ያስችለናል

🔸የጊዜ አጠቃቀምም በመንፈሳዊ፣ አእምሮአዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ጤናዊ አቋማችን የተመጣጠነ እንዲሆን ይረዳናል፡፡

3⃣ ውጤታማነታችን ያሳድጋል

🔹ውጤታማነት ሲለካ ሥራው መሠራቱ ብቻ ሳይሆን የሚታየው ሥራው የፈጀውም ጊዜ አንዱ መለኪያ በመሆኑ ግንዛቤ ውስጥ ይገባል፡፡

🔸ጊዜያችን በአግባቡ የምንጠቀም ከሆነ በሁሉም ረገድ በትንሽ ጊዜ ብዙ ሥራዎችን በማከናወን ውጤታማ መሆን እንችላለን፡፡

#ማጠቃለያ

❇️ጊዜ ሀብት ነው፤ እንዲሁም ጊዜ ለእያንዳንዳችን እኩል የተሰጠን ሀብት ነው፤ በመሆኑም እያንዳንዳችን አጠቃቀሙን ተረድተን ይህን ሀብታችንን ለውጤታማነት ልናውለው ይገባል፡፡

❇️ምንም እንኳ ጊዜ ሀብት ቢሆንም አጠቃቀሙን ካላወቅንበት፣ ሀብትነቱን ካልተረዳን ምንም ዋጋ አይኖረውም፡፡

👌ይህም ማለት ጊዜ ካወቅንበት እና ከሠራንበት የሚጠቅመን ሲሆን ካላወቅንበት ግን ምንም ጥቅም የለውም፡፡

❇️ጊዜ ለሁላችን እኩል የታደለ ሀብት ቢሆንም ጠቀሜታው ግን ለሁላችን እኩል አይደለም፡፡

👌ምክንያቱም የጊዜን ሀብትነት ተረድተው በአግባቡ የተጠቀሙበት ውጤት ሲያገኙበት ይህንን ያልተረዱ ግን ተጠቃሚ አይሆኑም፡፡

❇️ጊዜ ለእያንዳንዷ እንቅስቃሴአችን አስፈላጊ እና ጠቃሚ ሀብት በመሆኑ ትኩረትን ይሻል፡፡

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

📌ምንጭ
↪️ @Tewahedo12 Channel




🙏 ሼር ማድረግ አይርሱ 🙏

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን

📩Coment- @YeBiruk
- @Samiabush

@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
@ortodoxtewahedo
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ የማታረጅ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ የማትታደስ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ የማትጠፋ
#ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ የማትለወጥ
#ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ የማትሻሻል


📖በክርስቶስ ደም የተመሰረተች እውነተኛ ዘላለማዊ ሕይወት ናት ከድንግል ማርያም ፍቅር ከተዋህዶ ማዕድ አይለየን

📖አሜን ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር
በዚህ ወቡ በሆነች ሐይማኖት እስከዘላለም ያፅናን።

#አሜን
#አሜን
#አሜን

#share #share #share

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

📖ቅጠል ረግፎ ቅጠል እንደሚተካው ሁሉ ሰው ወድቆ ሰውን ያኖራል።

📖እኛም ይሄው ነን ይህ ነው ታሪክና ሂደታችን ኑሮና ይህ ህይወታችንን እየወደቁ ያኖሩን እየሞቱ ያተረፉን ኗሪዎች ነን

📖ያንዳችን ሞት ላንዳችን ህይወት ነው በዚህ መንገድ ነው እየተተካካን የተጓዝነው

📖በዚህ ሂደት ነው ሰው ለመሆን የተንገዳገድነው እየሞቱ ያኖሩን እየወደቁ ያተረፉን የህይወት ቀብድ የተከፈለብን ኗሪዎች ነን

📖ያንዳችን ሞት የሌላችን ህይወት ነውና የተከፈለልንን ዋጋ ላለማባከን

📖 በእምነት በእውነትና በፅናት በመኖር ህሊናችንን እናሳርፈው።

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👉 ትዝታው ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ እና ከቤተክርስቲያን ጋር ባለው ግንኙነት ዙሪያ የተነሱት ስጋቶች፣ በተለይም የሕግ ክፍል ሚና ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው።

የቤተክርስቲያን የሕግ ክፍል ሚና እና ተጠያቂነት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕግ ክፍል፣ ልክ እንደማንኛውም ተቋም የሕግ ክፍል፣ የቤተክርስቲያኗን ሕጋዊ መብቶችና ጥቅሞች የማስጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ይህ የሚያጠቃልለው፡-
የቤተክርስቲያኗን ስም መጠበቅ: ማንኛውም የቤተክርስቲያኗን መልካም ስም የሚጎዳ፣ የሚያጠለሽ ወይም ውሸት የሚያሰራጭ አካል ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ።
ንብረት ጥበቃ: የቤተክርስቲያኗን ንብረቶች (ሕንፃዎች፣ መሬቶች፣ ቅርሶች፣ ገንዘብ ወዘተ) ከሕገ-ወጥ ወረራ፣ ብዝበዛ ወይም ጉዳት መጠበቅ።
የአስተምህሮ ጥበቃ: የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ የሚጻረሩ ወይም ምእመናንን የሚያደናግሩ ድርጊቶችን ሕጋዊ በሆነ መንገድ መከላከል (ይህ ግን የሃይማኖት ነጻነትን የማያደናቅፍ መሆን አለበት)።
ውሎች እና ስምምነቶች: ቤተክርስቲያን የምትገባባቸውን ማንኛውንም ውሎች እና ስምምነቶች ሕጋዊ ገጽታ ማረጋገጥ።
የውስጥ ክርክሮች: በቤተክርስቲያኗ አባላት ወይም አካላት መካከል የሚፈጠሩ የሕግ ጉዳዮችን መፍታት።
"ቤተክህነቱ የሕግ ክፍል ነፍስ አለው?" የሚለው ጥያቄ
ይህ ጥያቄ ቤተክርስቲያን እንደ ተቋም ለሚያጋጥሟት ችግሮች ምላሽ የመስጠት ፍጥነት እና ብቃት ላይ ያነጣጠረ ነው። "ነፍስ አለው?" ሲባል፣ የቤተክርስቲያኗ የሕግ ክፍል ንቁ፣ ብቁ እና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅም አለው ወይ? የሚል ጥያቄን ይዞ ይመጣል።
ተቋማዊ ሕይወት: ማንኛውም ተቋም (እንደ ቤተክርስቲያን) የራሱ ሕግና ሥርዓት ያለው አካል ሲሆን፣ የሕግ ክፍሉም ይህንን ሥርዓት በሕይወት ለማቆየትና ለማንቀሳቀስ ቁልፍ ሚና አለው። ስለዚህ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ "ነፍስ" ወይም "ሕይወት" አለው ሊባል ይችላል።
ተግባራዊ ችግሮች: ሆኖም በተግባር ግን እንደ ማንኛውም ትልቅ ድርጅት፣ የቤተክርስቲያኗ የሕግ ክፍልም ቢሮክራሲ፣ የሀብት እጥረት፣ የሰው ኃይል ውስንነት ወይም የውሳኔ አሰጣጥ መዘግየቶች ሊያጋጥሙት ይችላሉ። እነዚህ ችግሮች "ነፍስ የለሽ ሬሳ" አስመስለው ሊያቀርቡት ይችላሉ።
ትዝታው እና የቤተክርስቲያን መልካም ስም ጉዳይ
ትዝታው በኢትዮጵያ ውስጥ በቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ሲያቀርባቸው የነበሩ አስተያየቶች በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ እንደሆኑ ይታወቃል። የቤተክርስቲያኗን መልካም ስም አጠፋተዋል የሚል ቅሬታ ካለ፣ የቤተክርስቲያኗ የሕግ ክፍል ይህንን ቅሬታ መርምሮ በሕግ አግባብ ክስ መመስረት የሚችልበትን ሁኔታ ማየት አለበት።
ማስረጃ ማሰባሰብ: "ብዙ ማስረጃ አለ" ተብሎ እንደተጠቀሰው፣ የሕግ ክፍሉ መጀመሪያ እነዚህን ማስረጃዎች በጥንቃቄ ማሰባሰብ፣ ማደራጀት እና ሕጋዊ ክብደት እንዳላቸው ማረጋገጥ አለበት።
የክሱ ዓይነት: ክሱ የስም ማጥፋት (defamation)፣ የሐሰት ወሬ ማሰራጨት ወይም ቤተክርስቲያኗን የሚያጎድፍ ሌላ ሕገ-ወጥ ድርጊት ሊሆን ይችላል።
የፍጻሜ አደራረስ: "ሬሳ የሕግ ክፍል ክስ ቢከስም ለፍጻሜ አያደርስም!" የሚለው አስተያየት የሕግ ክፍሉን አቅም መፈተሽ ነው። ክሱ ለፍጻሜ ለመድረስ ጠንካራ የሕግ መሠረት፣ በቂ ማስረጃ፣ ብቁ የሕግ ባለሙያዎች እና የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ አመራሮች የፖለቲካ ፍቃደኝነትና ድጋፍ ያስፈልገዋል። ያለዚህ ድጋፍ፣ ሕጋዊ ሂደቶች ቀርፋፋ ሊሆኑ ወይም ሙሉ በሙሉ ሊዳክሙ ይችላሉ።

የቤተክርስቲያኗ የሕግ ክፍል በሕግ ፊት ስልጣን ያለው አካል ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኗን መብቶች ማስጠበቅ የሕግ ግዴታው ነው። ትዝታው በቤተክርስቲያኗ ላይ ጉዳት አድርሷል ተብሎ ከታመነ፣ የሕግ ክፍሉ ያሉትን ማስረጃዎች ተመልክቶ ሕጋዊ እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን አለው። ሆኖም የሕግ ሂደቶች ውስብስብ እና ጊዜ የሚጠይቁ በመሆናቸው፣ ውጤታማ ለመሆን ጠንካራ የሕግ አቅም እና ተቋማዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያኗ ምን አይነት እርምጃ ትወስዳለች ብለው ያስባሉ?
  
           
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
መ/ር አክሊል

ብርቱ አርቶዶክሳዊ ወጣት ቤተ ክርስትያን ብዙ አክሊልዎች ያስፈልጓታል በርታልን ወንድማችን ።

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo
ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ በቤተ ክርስቲያን ደን ልማት ላደረጉት አስተዋጽኦ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሽልማት ተበረከተላቸው።

Mk tv ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም

ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር በደን ልማት ላደረጉት አስተዋጽኦ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሽልማት ተበረከተላቸው።

ሰኔ 4/2017 ዓ/ም በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በተከናወነው የዕውቅናው መርሐ ግብር ላይ የምስጋና ወረቀትም ዶክተሩ የሚመሩት አመልድ ኢትዮጵያ ለአበረከተው አስተጽኦ ከቤተ-ክርስቲያን ደን ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ተበርክቶለታል።

ሽልማቱ የሰጡት በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በደራ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኙ የስድስት አብያተ ክርስቲያናት እና የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ተወካዮች ናቸው።

የአብያተ ክርስቲያናቱ ተወካዮች እንደገለጹት በዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ የሚመራው አመልድ ኢትዮጵያ በአካባቢያችን ለሚገኙ ጥንታዊ ገዳማት እና አድባራት ተፈጥሮአዊ ደኖቻቸው እና ይዞታቸወ እንዲጠበቅ፣ ኅብረተሰቡን በማስተባበር አጥራቸው እንዲታጠር እና በአካባቢው ለሚገኙ ድሃ ማኅበረሰቦች የኑሮ ማሻሻያ ድጎማ በማድረግ ያደረገውን ተግባራት አውስተው ተወካዮቹ ምሥጋና አቀርበዋል፡፡

የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ዓለማየሁ ዋሴ (ፒ.ኤች.ዲ) እንደተናገሩት ለመጀመሪያ ጊዜ ከፕሮጀክት ተጠቃሚዎች መካከል ምስጋና ያቀረቡ መሆናቸውን አውስተው፣ በቀጣይ የቤተ-ክርስቲያን ደንን መሠረት ያደረገ የመልክዐ- ምድር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ሥራ በሌሎች ቦታዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በአካባቢው የተሠራው ሥራ ዉጤታማ መሆኑን አድንቀዋል፡፡

ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በቤተክርስቲያን የደንና ብዝኃ ሕይወት ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶችን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በማካሄድ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ግንዛቤ መፍጠር የቻሉ ሲሆን እመጓ፣ መርበብት እና ዝጎራ በተባሉት መጽሐፎቻቸውም አንቱታን ያተረፉ መሆናቸው ይነገርላቸዋል።

©የዘገባው ምንጭ አመልድ ኢትዮጵያ ነው።

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
2025/07/05 07:18:27
Back to Top
HTML Embed Code: