Telegram Web Link
Forwarded from Ⓢ ⓙⓇ ️ ️️
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን !!!

እንኳን ለቅድስት ሥላሴ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

የአብርሐምን ቤት የባረኩ ሥላሴ እኛንም በህይወታችን በኑሮዋጭን በአገልግሎታችን በትዳርአችን በትምርታችን በሥራችን ይባርኩን ።

ሥሉስ ቅዱስ ለሚታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::

#መልካም እለተ ይሁንልን

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈

ለመቀላቀል ➟ @weludebirhane

ለአስተያየት ➟ @weludebirhane_bot

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼.
የአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ትምህርት ቤት መታሸጉን ተከትሎ አባላቱ ቅሬታቸውን ገለጹ !

ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም [ተሚማ/ አዲስ አበባ]

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአርሲ ሀገረ ስብከት ካሉት ቀደምት እና አንጋፋ ሰንበት ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው የአሰላ ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ወንጌል ሰንበት ትምህርት ቤት በደብሩ ሰበካ ጉባኤ አማካይነት መታሸጉን የሚዲያችን የመረጃ ምንጮች ለሚዲያ ክፍላችን መረጃውን አድርሰውናል። ይህንንም ተከትሎ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

በሚያዝያ 08/2017 ዓ.ም በሰበካ ጉባኤ በቁጥር አካ/ደመ/መዓ/ቤክ/ሰጉ/0320/17 በተጻፈ ደብዳቤ የሰ/ት/ቤቱን ሊቀመንበርና የሕጻናት ክፍል መምህር ዲ/ን አበበ ይልማን ከሥራና ከሰ/ት/ቤቱ ሰብሳቢነት ማገዳቸውን በመግለጹ ሰንበት ት/ቤቱ በቀን ምልዓተ ጉባኤ አድርጎ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሊቀ መንበር የታገደበትን ውሳኔ ጠቅሶ ለሰበካ ጉባኤው በደብዳቤ ለወረዳው ቤተክህነት እና ለወረዳው ሰ/ት/ቤት አንድነት አስገብቶ አፋጣኝ ምላሽ ባለማግኘቱ በድጋሚ ለወረዳ ቤተ ክህነቱ በቀን 16/08/2017 ዓ.ም የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቶ ፤ የወረዳው ቤተክህነት ጉዳዩን ተመልክቶ ሊቀ መንበሩ አለአግባብ መታገዱንና የሰ/ት/ቤቱን መብት የነካ ተግባር መሆኑን ጠቅሶ ለሰበካ ጉባኤው በቁጥር 97/2017 በቀን 17/08/2017 ዓ.ም እገዳው እንዲነሳ ደብዳቤ መጻፉን ለሚዲያችን አስረድተዋል።

ሆኖም ግን ሰበካ ጉባኤው ተፈጻሚ የወረዳ ቤተ ክህነቱን ትዕዛዝ ባለመቀበሉ በ25/09/2017 ለብፁዕ አቡነ ያሬድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል ጠቅሰው ያስገቡት ደብዳቤ ምላሽ ሳይሰጣቸው ሰንበት ትምህርት ቤቱ በግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ታሽጎ አገልግሎት መስጠት ማቆሙን ሚዲያችን ለማወቅ የቻለ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከሀገረ ስብከቱ የተላኩ ልዑካን በተገኙበት የታሸገው የሰንበት ት/ቤት ሂሳብ ነክ እና አባላት ቁጥርን ከያዘው ሳጥን ባሻገር ሌላው የታሸጉት ተከፍተው ሰ/ት/ቤቱ ወደ አገልግሎት እንዲመለስ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ደብዳቤ ጽፎ ቢልክም ሰበካ ጉባኤው የታሸገውን ለመክፈት ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን ለመረዳት ችለናል

ይህንን አስመልክቶ የሚዲያ ተቋማችን የካቴድራሉን አስተዳዳሪ አባ ፍቅረ ሥላሴን በተደጋጋሚ ደውሎ ለማነጋገር ቢሞክርም ሐሳባቸውን በስልክ ለማጋራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሐሳባቸውን ማካተት ያልቻልን ሲሆን ፤ በተጨማሪም የወረዳው ሊቀ ካህናት እና የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴን ለማግኘት ያደግረነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
አቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ ተመሰረተ !

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት
የሕግ አገልግሎት መምሪያው ከሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ
ኮሚቴ ጋር በመሆን አቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መሰረተ።

የቤተክርስቲያናችን ሕግ አገልግሎት መምሪያ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ክስ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የምርመራ መዝገቡ መብቱ ለሚፈቅድለት የዐ/ሕግ ዘርፍ እንዲተላለፍለፍ ጠይቋል።

በወንጀል ተጠርጣሪ /ተከሳሽ - አቶ ትዝታው ሳሙኤል
ተጠርጣሪ /ተከሳሹ ነዋሪነቱን በውጪ ሃገር በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካልን ለማዋረድ፣
ለመስደብ እና የምዕመኑን ስሜት ለመንካት ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እና ከ5000 በላይ ተከታዮች ባሉት የራሱ የዪቲዩብ ቻናል በመጠቀም ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

በማያያዝም ግለሰቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችን፣ በየገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ ገዳማውያን መነኮሳትና አገልጋዮችን <<ግብረ ሰዶማውያን ናቸው>> በማለት፣እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን <<የመተት እና ጠንቋይ ቤት ናት >>በማለት፣ሲቀሰቅስ የቆየ መሆኑን የገለጸው መምሪያው ግለሰቡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትገለገልባቸውን ሃይማኖታዊ የፀሎት፣የታሪክ ፣የገድላትና ድርሳናት መጻሕፍትን <<ድውያን መጽሐፍት ናቸው መጥፋት አለባቸው>>ማለቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቅድስናየምታ
ከብራቸውንና የምትዘክራቸውን ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን << ጣኦታትና ጣኦት አምላኪ>> ናቸው በማለት ግለሰቡ የፈጸመውን የወንጀል አድራጎት በመጥቀስም ክስ መስርቶበታል።
Audio
ያሉበትን ቤት ሁሉ ሞላው
         በዓለ መንፈስ ቅዱስ
Size:-28MB
Length:-1:20:27

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
🔴 እግዚአብሔር በሚያደርገው በጎ ነገር...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
እግዚአብሔር በሚያደርገው በጎ ነገር ሚካኤል ይታዘዛል
                         
Size 51.2MB
Length 55:18

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
#ደጉ እና ሩሩህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በዓል እንኳን አደረሳቹ።

"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ"

እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ

የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"

#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል

" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።"

#መዝሙረ ዳዊት 34:7፤)

"በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል። "

#ትንቢተ ዳንኤል 12:1

" የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት። "

#ትንቢተ ዳንኤል 10:13

" ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።
"
#ትንቢተ ዳንኤል 10:21፤)ዐ

"የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።"

#የይሁዳ መልእክት 1:9፤

"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ
እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ

የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"

#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል.

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ"

እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ

የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"

#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
❖ ሰኔ ፲፪ ❖

✞ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት [በነገዱ ውስጥ፥ በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት..፣ በእስክንድርያ ከተማ ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት..፣ የሞት መልእክት የተጻፈባትን የቅዱስ ባሕራንን ደብዳቤ የለወጠበት..፣ ቅድስት አፎምያን ያዳነበት..፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት..በእለኚህ ምክንያት ነው በዓሉን የምናከብረው] ✞

"ሰላም ለሚካኤል መሐሪ ውእቱ፤ ወተአዛዚ ለሰብእ በዲበ ሠናይቱ፤ ለቀርነ ዝንቱ መልአክ በድምፀ ንፍሐቱ፤ በከመ ኮነ ቀዳሚ ውስተ ሰማያት ዕርገቱ፤ ለእግዚአብሔር ይከውን ዳግመ ምጽአቱ።"

@ortodoxtewahedo
"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ"

እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ

የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"

#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል

             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
በዓለ ቅዱስ ሚካኤል

እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል በዓል አደረሳችሁ!

ሚካኤል ማለት ‹‹መኑ ከመ አምላክ (እግዚአብሔር)፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው›› ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እርሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ፣ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ፣ ርኀሩኅ፣ ኃያልና ረቂቅ ማንም እንደሌለ የሚያመለክት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል ሌሎች መጠሪያዎች አሉት፤ እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ፣…›› ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በእርሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸና ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡

መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡ መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታልና በእርሱ አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ፣ በጸሎቱ ተማጽኖና በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከሠራዊተ አጋንንት ተንኰል የሚያድን መልአክ እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ ሙሴንና እስራኤልን በሲና በረሃ (ዘፀ.፳፫÷፳-፳፪)፤ (ዘፀ.፲፬÷፲፭-፳) ኢያሱን በኢያሪኮ (ኢያ.፭÷፲፫-፲፭)፤ ከአሞራውያንም እጅ ሕዝቅያስን እንደረዳቸው ተጽፏል፡፡ (ኢሳ.፴፯÷፴፮) በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፫ ላይ ‹‹የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› በማለት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ተገልጿል፡፡ በዚሁ የመጽሐፍ ክፍል ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፩ ላይ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል›› በማለት ታላቅነቱን፣ ለሰው ልጆች ሁሉ በአማላጅነቱና በተራዳኢነት የሚቆም እንደሆነ በማያሻማ ቃል ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በኦሪት የእግዚአብሔር መልአክ እየተባለ የሚጠራው አብዛኛውን ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምራሉ፤ በድርሳነ ሚካኤልም ተጽፎ ይገኛል፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያልረዳው ቅዱስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በዘመነ ሰመዕታትም ሰማዕታትን በተጋድሎ ያጸናቸው ይህ ሩኅሩኅ መላክ እንደሆነ በእነ ቅዱስ ፋሲለደስ እንዲሁም በእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገድላት ላይ በሰፊው ተገልጿል፡፡
የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየወሩ በ፲፪ ቀን መታሰቢያውን እንድናደርግ አዘውናል፡፡ ይህንንም ያልቻለ በዓመት አራት ዓበይት በዓላትን ከቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ጀምሮ እንደተቻለ ማዝከር ይገባል፡፡ እነዚህም ኅዳር ፲፪ ቀን ቀጥሎ ሰኔ ፲፪ ቀን ከዚያም ነሐሴ ፲፪ ቀንና ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ናቸው፡፡

ሰኔ ፲፪፡- በቅዳሴያችን ‹‹ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ለሚካኤል ምሕረት (ይቅርታ ርኀራኄ) ተሰጠው እንላለን፤ ነቢዩ ሄኖክም ምሕረት ለሚካኤል መሰጠቱን ገልጿል፤ ትሕትናውን ታዛዥነቱን አስረድቷል፡፡ (ሄኖ.፮÷፭፣፲÷፲፪)

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ፣ ለሰው ሁሉ የሚራራና ስለ ሰው ልጆች ሳያቋርጥ ወደ ፈጣሪው የሚለምን፣ ርኀሩኀና ትሑት የሆነው ኃያሉ ቅዱስ ሚካኤል ባሕራንን ከሞት ያዳነበት፣ የሞቱን ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት የመታሰቢያው ዕለት ነው፡፡


             
#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ለሃሳብ አስተያየት

@ortodoxtewahedoo

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
2025/07/05 03:21:07
Back to Top
HTML Embed Code: