Telegram Web Link
የጣፈጠ #ህይወትን ይፈልጋሉ?

አንተ ልዩ ሆነህ የተፈጠርከው በእግዚአብሔር  ፈቃድ ነውና ምንም ሳታማርር ህይወትህን ኑራት።
#ባለህ_እየታመንኽ ህይወትህን አጣፍጣት። #ሰዎችን_ለመምሰልና_የነሱ_ግልባጭ_ለመሆን_አትጣር
 የአንተ ንጹህና እጹብ ድንቅ ያልታየ ማንነት የሚወጣው በራስህ
#መተማመን፣መኩራትና እራስህን ማክበር ስትጀምር ነውና። በዙሪያህ ምንም አይነት ዝነኞች ትልቅና ልዩ ተሰጦ ያላቸው ሰዎች ቢኖሩም በአንተ ውስጥ ያለው ልዩ ስጦታ ግን ከሁሉም ይለያል! ይልቃል! ይበልጣል! እነዚህ ልዩ ያልካቸው ሰዎች በአፈጣጠራቸው የተለዩ ሆነው ሳይሆን ይህንን ምስጢር ስላወቁትና ስለተገበሩት ብቻ ነው ከሌሎች ተለይተው አሁን ያሉበት የደረሱት። አንተም እንደነሱ የደረሱበት እንደውም ከነሱበላይ መስጠት መስራትና ማበርከት ከፈለክ ወደ እኔ ጠጋ በልና ጆሮህን ስጠኝ እኔም ሚስጢሩን ሹክ ልበልህ።

 ተጠጋኸኝ ልጀምር? "

#እራስህን_ሁን! #እራስህን_አክብር! #እራስህን_ውደድ!" #እራስህን_እንደማትወደው_እንደማታከብረውና_እንደማትሆነው_ስታስብ_ከማይመረመረው_ከእግዚአብሔር _እውቀትጋር_እየተደራደርክ_ነውና_ሁለቴ አስብ። ሰዎች ከሚሉህ በላይም እግዚአብሔር ሲፈጥርህም ምክንያት አለውና የሌለህን ትተህ ያለህን ዋጋ ስጥ። በሌለህ ነገር ስለምታገኘው ሳይሆን ባለህ ነገር ስለምትለውጠው ተመራመር። በሌለህና ባልተጨበጠው ነገር ትልቅ ነገር ለመስጠት ከማሰብ ይልቅ ባለህ ነገር ትንሽ ነገር ለመስጠት ሞክር። ያኔ አንተ ውስጥ የተደበቀው ከሌሎች የተለየው ድንቅ ፍልቃቂ ማበብ ይጀምራል። ብርሃንህ በዓለም ሁሉ ይሰፋል። ስምህም በሰዎች ልብ ውስጥ ይነግሳል። በምድር ላይ በኖርክበት ዘመን ሁሉ ዘመንህ የጣፈጠ ይሆንልሀል።

👉 ለመቀላቀል

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
“ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።”

— ዮሐንስ 8፥12

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#ፍትህ ለሊቁ

ይህ ዘመን የቤተ ክርስትያን የስደት ዘመን ነው ።
ያለ ጥፋት ያሰሩሀል የፈለጉትን የሚደረግበት ሊቁ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከታሰረ 13 ቀን ሆነው ።
ኦርቶዶክስ መሆን ወንጀል ነው ?????

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
መላእክት ምስጋናቸው እረፍታቸው ፣እረፍታቸው ምስጋናቸው ሆኖ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ እግዚአብሔርን ያለማቋረጥ ያመሰግናሉ፡፡

ቤተክርስቲያንም አምሳለ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ናትና ይህን አብነት በማድረግ ልዑል እግዚአብሔር ሃያ አራት ሰዓት የሚመሰገንበትን የምስጋና ሥርዓት ዘርግታለች፡፡

ሕያው እግዚአብሔር የአዳም ልጆች በመላእክት ምስጋና
እንዲያመሰግኑት በመውደዱ ሰማያዊውን ምስጋና ይማር
ዘንድ ቅዱስ ያሬድን መረጠ፡፡

ማህሌታዊው ቅዱስ ያሬድ የመላእክት የምስጋናውን እንጀራ
ያበላን የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ እንቁ ነው።

በረከቱ ይደርብን!

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሰተ ዐፅማቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓለ ንግሥ በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ዋለ።

@ortodoxtewahedo
#ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ መታመሙን ሰማን ለህክምና የሚሆነው ብር ያስፈልገዋል እና የተቻለንን እናድርግ በዝማሬው ብዙ አትርፈናል ፣ተጠቅመናል ጤናው ተመልሶ እንድናየው አባታችንን እንርዳው።
#እግዚአብሔር ይማርህ አባታችን!!!🙏❤️🙏
#አካውንቱን 1000481007287
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ/ወልደመስቀል
አባካችሁ ሼር አድርጉ ለሌሎችም ይድረስ

@ortodoxtewahedo
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
2024/05/22 00:04:22
Back to Top
HTML Embed Code: