.ሰሞነ ሕማማትን እንዴት ባለ ጾምና አመጋገብ እንድናሳልፍ ነው ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን የምታዘን?


ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ

ተወዳጆች ሆይ በዚህ በሰሞነ ሕማማት የቤተ-ክርስትያናችን የሥርዓት መጽሐፍ የሆነው ፍትሐ ነገሥት የካህኑንም የምዕመናኑንም የሰሞነ ሕማማትን የጾም እና የአመጋገብ አክራሞት እንጠቀምበት ዘንድ፣ጸጋና በረከት እናገኝበት ዘንድ ይደነግግልናል፡፡

ወዳጆቼ ለጊዜው የካህናቱን ትተን/ምክንያቱም በአገልግሎት ስለሚያሳልፉ/ የምዕመናኑን እንመለከታለን፡፡ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ፍትሐ ነገሥት በአንቀጽ 15 በቁጥር 578 ላይ ጨው ያለው ቂጣ እንድንበላና የእግዚአብሔር ውኃ እንድንጠጣ ያዘናል፡፡ እንዲሁም ፉቱ የማለት ልምድ ያለንን ሰዎችንም ‹‹በሊህ ቀኖች ከወይን ከሥጋ ተለዩ›› በማለት በጸሎት እንድንመሰጥ እንጂ መጠጥ እንዳንጨልጥ ያዘናል፡፡

እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ሰሞነ ሕማማትን በቂጣና በውኃ የመጾም ጸጋና ልምድ ያለን ሰዎች ብንተገብረው ብዙ በረከት እናገኝበታለን፡፡ ልምዱና ጸጋው የሌለን ከሆነ ግን ጽኑ ግዴታ ውስጥ አንገባም፡፡ ቂም ቋጥረን፣ነገር ሸርበን፣ከወዳጃችን ተናቁረን፣በሐሜት ተጨማልቀን፣ስድብን በምላሳችን ተሸክመን እንኳን ቂጣ እየቆረጠምን ለምለም እንጀራ በጥሩ ወጥ እየበላን ባንጾም ይሻላል፡፡ ምክንያቱም አፋችንና ልባችን የማይገናኙበት፣ቃሉና ተግባሩ የተራራቁበት ጾማችን ጾም ሳይሆን በረከት አልባ ልምድ ነው የሚሆነን፡፡

በሰሞነ ሕማማው ውስጥ ባለው የአክፍሎት ቀኖች እንደ መንፈሳዊ ልምዳችንና ብርታታችን በሁለት መልኩ በአማራጭ ያስቀምጥልናል፡፡ ይህንንም ‹‹ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፡፡ የሚችል እስከ ሌሊት ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ/እስከ ቅዳሴ ማብቅያ ድረስ/ ምንም ምንም አይቅመስባቸው፡፡ ሰውዬውም ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻል ግን የቅዳሜን ጾም ይጹም›› በማለት አስቀምጦልናል፡፡ ይህንን ዘርዘር አድርገን ስናየው ‹‹ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱን በአንድነት ጹሟቸው›› ያለው የሁለቱን ቀን አክፍሎትን ነው፡፡ ሐሙስ በልተን ዓርብን ስግደት ውለን፣ዓርብን እህል ውኃ ሳንቀምስ ቅዳሜንም ውለን ከትንሣኤ ቅዳሴ በኃላ እንድንገድፍ ያዘዘበት ነው፡፡ ‹‹ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻል ግን የቅዳሜን ጾም ይጹም›› ማለቱ ዓርብን በጾም እና በስግደት ውለው የማክፈል ልምድ የሌላቸው፣የጾም ልምድ የሌላቸው ግን መጾም የተቻላቸው ወጣንያን፣ጎልማሶች አዛውንቶች የስቅለት እለትን ማክፈል ቢያቅታቸው ዓርብን በልተው ቅዳሜን ግን ያክፍሉ ማለቱ ነው፡፡ /ይህ ትዕዛዝ በደዌና ለመጾም የማያበቃ ልዩ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ያገናዘበ ነው/

በሰሞነ ሕማማት ፍትሐ ነገሥት በአንቀጽ 15 በቁጥር 593 ላይ ሴቶች ጌጣቸውን እንዲተዉ ያዛል፡፡ ይህም የሆነው ማንም ሰው ዘመድ ሞቶበት አልያም ለቅሶ ቤት ሲሄድ ለሐዘን የሚመች ልብስ እንጂ ዓይን የሚገባ ጌጣ ጌጥ አድርጎ አይሄድም፡፡ ይህ ሰሞነ ሕማማት የጌታችንን ስቅለት እና ሞት እያሰብን የምናዝንበት እንጂ የምንጋጌጥበት ስላልሆነ ነው ሴቶች ጌጣቸውን አውልቀው ከመጋጌጥ የሚከለከሉት፡፡ እንዲሁም በዚህ በሰሞነ ሕማማት ባል እና ሚስት ሩካቤ ሥጋ እንዳይፈጽሙ ‹‹ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን ኃጢአት ለሚሠራት ሰው ወዮለት›› በማለት ያስጠነቅቃል፡፡ /ቁጥር 597/

በአጠቃላይ በቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሥርዓት መሠረት በዚህ ሰሞነ ሕማማት የተከለከሉት ነገሮች እጅ ተጨባብጦ ሰላምታ መሰጣጣት እና መሳሳም/ይሄ መናጢው ሳንባ ቆልፍን/ኮሮናን/ እጅጉን ለሚፈሩት ሳይጠቅማቸውና እፎይታ ሳይሰጣቸው አይቀርም/፣መስቀል መሳለም እና ማሳለም፣ክርስትና ማንሳት፣ክህነት መስጠት፣ፍትሐት ማድረግ፣መስከር፣አብዝቶ እስከ ቆፈት መብላት፣በተለይም የላመ የጣመ መብላት፣ወዛ ፈዛዛ፣ሳቅ ጨዋታ ጭፈራ የተከለከሉ ናቸው፡፡

ወዳጆቼ ሳንባ ቆልፍ/ኮሮና/ ከቤተ-ክርስትያን ደጃፍ አባሮ፣በቤታችን አጉሮ ሁላችንንም የቁም እስረኛ አድርጎናል፡፡ ይህንን እንደ መቅሰፍት ሳይሆን እንደ ሱባኤ አጋጣሚ በመቁጠር ቤታችን እየሰገድን፣እየጸለይን እየጾምን የባሳ አታምጣ፣ብሩህና ደግ ጊዜ አምጣ እያልን በጌታ ስቃይ ስቃያችን እንዲያልፍልን፣በጌታ መከራ መከራችን እንዲርቅልን እንጠቀምበት።

#ፈጣሪያችን ደጉን ጊዜ ያምጣልን
.#የሕማማት_ጥያቄዎችና_መልሶቻቸው

1. በሕማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይም አናማትብም?
👉🏾የመስቀል ክብር እና ኃይል የታወቀው ጌታ በመስቀለ ከተሰቀለ በኋላ ነው
በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የዓመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው።
በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልገሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት
በሰሞነ
ሕማማት በቤተክርስተያን ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ የማማተብ ስርዓት የለም።

2. በሰሞነ ሕማማት ለምን አንሳሳምም?
👉🏾ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቶአል እኛም እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችንን ለማሰረዳት።
ከዚሀ በተጨማሪም ፍፁም ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት
በሰሞነ ሕማማት እሰከ መሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም።
3. በሰሞነ ሕማማት የማይፈቀዱ ሌሎቸ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
👉🏾ማንኛውም ለስጋ የሚያደሉ ተግባሮችን መቀነስ እና ቢቻለን አብዛኛውን ጊዜአችንን በቤተ እግዚአብሔር የጌታን መከራ ሕማም በማሰብ በፆም በስግደት
በጸሎት ማሳለፍ
በትዳር ያሉ በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ
ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ።
4. ስለ ሰሞነ ሕማማት በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈ አለን?
👉🏾ነብዩ ኢሳይያስ "በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ ሕማማችንንም ተሸክሞአል "
ኢሳ.53፤4 ይላል።
ሕማማት የሚለው ቃለ በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወሰደ ሲሆን የጌታን
መከራ የምናስብበት ሳምንት ነው።
የጌታችንን ሞቱን ሕማሙን ማሰብ መዘከር እንደሚገባ ቅዱስ ጳውሎስ እነዲህ ይላል፦
" ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና" 1ቆሮ.11፤26።
ይህ ሳምንት ለአይሁድና ለመሰሎቻቸው የደስታ ወቅት ቢሆንም
ለክረስትያኖች በጥልቅ ኅዘን ውስጥ የሚገቡበት ሳምንት ነው
እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ''እናንተ ታለቅሳላችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ
ዓለም ግን ደስ ይለዋል እናንተም ታዝናላችሁ ነገር ግን ኃዘናችሁ ወደ ደስታ
ይለወጣል'' ዮሐ16፤20
በእርግጥ ኃዘናችን ትንሳኤውን እሰክናይ ለጥቂት ጊዜ ቢሆንም ግን እናዝናለን
በትነሳኤው ደግሞ ደስታውን እንካፈላለን።
👉🏾ሰኞ አይሁድ እንዴት እንደሚይዙት ለመማከር ክፉ ጉባኤያቸውን ጀመሩ።
''በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው
በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ ጌታ ኢየሱስንም በተንኮል ሊያስይዙት ሊገሉትም ተማከሩ" ማቴ26፡3_4።
ይህንን ጉባዔ ቅዱሰ ዳዊት የከፉዎቸ ጉባዔ እያለ ይጠራዋል።
"ብዙ ውሾች ከበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ" መዝ21፤16 አይሁድ ሰኞ የጀመሩትን ዕረቡ ውሳኔአቸውን አጠናቀው በምሴተ ሐሙስ ከዕራትና ከቁርባን በኋላ ሰይፍ ጎመድ ይዘው መጡ።

በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ሰጣቸው ያዙትም እስከ አርብ ስድስት ሰአት
ሲያንገላቱት ቆይተው ከብዙ መከራ በኋላ ሰቀሉት ዘጠኝ ሰአት ላይ ቅድስት ነፍሱን በፈቃዱ ከቅዱስ ስጋው ለየ። ከአሰራ አንድ ሰአት በፊት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ በምስጋና ገንዘው ቀበሩት።

ከሕማሙ ከመከራው በረከት ያሳትፈን ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን።

👉🏽ትምህርቱ ለሌሎችም ይጠቅማልና ሼር ያድርጉ!
#ዕለተ_ዓርብ#ዕለተ_መድኃኒ

#በዲ/ን_በረከት_አዝመራ

"#ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፤ ጌታችን (መምህራችን) ሆይ! ለመስቀልህ እንሰግዳለን፡፡"
***
"ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም፤ ኃይል ክብር ምስጋና እና ብርታት ለአንተ ይገባል"
በሰሙነ ሕማማት #በስግደት ወቅት ደጋግመን የምንለው #ምስጋና ነው:: ጌታችን ለሰው ልጆች #ድኅነት መከራ ተቀብላሏል: በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ስለእኛ ሞትን በፈቃዱ ቀምሷል:: ይህ ድካም የመሳላቸው ብዙዎች ናቸው:: (አጋንንት፣ ብዙኃኑ አይሁድ፣ መናፍቃን)
ቤተ ክርስቲያን መከራውና ሞቱ የድካም ሳይሆን የካሳ መሆኑን እና ብርቱ የሰው ልጆች ጠላቶች (ኃጢአት፣ ሞት፣ ዲያብሎስ) የተሸነፉበት መሆኑን በማወቅ 'ኃይል ክብር ምስጋና እና ብርታት የአንተ ነው' በማለት ታመሠግነዋለች:: ይህን ምሥጋና ቀድሞ መላእክት #በመስቀሉ ሥር #እየሠገዱ ተናግረውታል::ኪርያላይሶን (ጌታ ሆይ ማረን)
ክርስቶስን ለመከራ ያደረሰው የሰው ኃጢአት ነው:: መከራና ሞቱም #የምሕረት ምንጭ ነው:: በዚህም ምክንያት ኃጢአታችንን እያሰብን እና በመስቀል የተገለጠውን #ምሕረት እና #ፍቅር እያመንን 'ኪርያላይሶን ጌታ ሆይ ማረን' እያልን እንሰግዳለን:: 'እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ' በማለትም ደጋግመን

#እንማጸናለን::
ምስባካት እና ምንባባት
ዲያቆናት ከዳዊት መዝሙር ስለ መከራው እና ሞቱ የተነገሩ ትንቢቶችን በሚያሳዝን ዜማ ይሰብካሉ፤ ሕዝቡም በስግደት ይቀበላል:: ካህናትም በየሰዓታቱ የተደረጉ ድርጊቶችን የሚገልጹ #የወንጌል ምንባባትን ያነባሉ:: ሁሉም በስግደት ይታጀባሉ፤ በየመካከሉ ካህናት የእጣን ማእጠንት እየወዘወዙ ያጥናሉ:: ይህም #ክርስቶስ መልካም መዓዛ ያለው ንጹሕ #መሥዋዕት ሆኖ መቅረቡን ያዘክራል:: የሕዝበ ክርስቲያኑ #ጸሎትና ተዘክሮም ከዕጣኑ ጋር አብሮ ያርጋል::

"አምነስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ..."

ካህናቱ እየመሩ ሕዝቡ እየተከተሉ 'አምንስቲቲ ' እያሉ በሚያሳዝን ዜማ ይጸልያሉ:: 'አቤቱ በመንግስትህ አስበን' ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቁጭ ተብሎ ራስ በነጠላ ውስጥ ይሸፈናል:: ጸሐይ ስትጨልም እና የክርስቶስ #ዘላለማዊ ንጉሥነት ሲገለጥ በቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ (ፈያታዊ ዘየማን) #የጸለየው ጸሎት ነው:: ከሁሉ ቀድሞ #ገነት ያስገባውን ጸሎቱን ጸሎታችን አድርገን እንጸልያለን::
የድል ቀን
ቤተ ክርስቲያን ሕማሙን ትካፈላለች እንጂ ጌታ በግድ የተሰቀለ ይመስል የሽንፈት #ኃዘን አታዝንም:: ይልቁንም በድካም: በሞት የተገለጠ ፍቅሩን እያሰብን ትእዛዙን እየጠበቅን ከእርሱ ጋር ለመኖር ቃል ኪዳናችን እናድሳለን:: የሚታዘነው ፍቅሩ ሊታየው ላልቻለ እና አሁንም ወደ #መድኃኒት ክርስቶስ መቅረብ ላልቻለ ነው::

በዕለቱ የሚነበቡ የነቢያት መጻሕፍት የድል ቀን መሆኑን ነው የሚነግሩን:: ዓርብ በስድስት ሰዓት የሚነበበው የኢሳይያስ ትንቢት "በዚያም ቀን፡— አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ አጽናንተኸኛልምና አመሰግንሃለሁ። እነሆ፥ አምላክ መድኃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፥ መድኃኒቴም ሆኗልና በእርሱ ታምኜ አልፈራም ትላለህ። ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ። በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፡— እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ ተናገሩ። ታላቅ ሥራ ሠርቷልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ። አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፥ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሏልና ደስ ይበልሽ ፤እልልም በዪ" ይላል:: (ኢሳ. 12:1-6)

በዐሥራ አንድ ሰዓትም "ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ: የተመሰገነ እግዚአብሔርን እናመስግነው" የሚለው የእሥራኤላውያንን መዝሙር እንዘምራለን:: እሥራኤል ይህን #ምሥጋና ያመሰገኑት ባህር ከፍሎ እና ፈርኦንን አስጥሞ ወደ #ተስፋዋ ምድር ስላሻገራቸው ነው:: ቤተ ክርስቲያን የምትዘምረው ሞትን አጥፍቶ፣ ዲያብሎስን አሸንፎ፣ ሲኦልን በርብሮ ወደ #ገነት መንግሥተ ሰማያት ስላሻገረን ነው::

https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
✞ ተፈጸመ✞

"ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ" (ዮሐ 19: 30)

ተፈፀመ የሚለው ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ነፍሱን ለወዳጆቹ ሲሰጥ ከመሞቱ በፊት የተናገረው የመጨረሻ ቃል ነው። " ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ" (ዮሐ 19: 30)። ተፈፀመ በግሪክ "ቴትለስታ'ይ" (τελείωσε /Tetelestai) ማለት ሲሆን ትርጉሙም ወደ ፍፃሜ ማምጣት፣ መጨረሻ መድረሱን፣ ማከናወንን ፣ ማለቅን የሚያሳይ ነው። በእርግጥ አማኑኤል TETELESTAI/ ተፈፀመ ሲል ምኑ ይሆን የተፈፀመው? ብሎ የሚጠይቅ ህሊና ያስፈልገናል።

አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ አባቱ የሰጠውን ስራ ለመስራትና ለመፈፀም አምላክነቱን እንደመቀማት ሳይቆጥር በአባቱ በራሱና በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ወደ ዓለም እንደመጣ አስታውቆናል። ከመጣም በሇላ አባቱን የሚያከብር ስራን ሰርቷል "እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ" (ዮሐ 17: 4) እንዲል። ሊሰራ የመጣው የጠፋነውን የሰው ልጆች ሊፈልግና ሊያድን ዘንድ ነው ። በምድር ሲመላለስ የስራው ፍፃሜ የነበረውንም ነፍሱን ስለወዳጆቹ በመስጠት ፈፀመው ። ክርስቶስ ተፈፀመ ሲል የሽንፈት ቃል አይደለም የድልና የአሸናፊነት እንጂ ወደ ዓለም የመጣሁበትን ስራ በሞት ጨረስኩ፣ ህዝቦቼን በሞት አዳንኩ ፣ የኃጢአትን ኃይል ድል ነሳሁ ፣ በሞቴ ሞትን ገደልኩ ፣ በመከራዬ ለመንግስቴ ህዝብን ማረኩኝ ሲል ተፈፀመ አለ እንጂ!

የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ተፈፀመ ብሎ ስለሞቱ ሲናገር "በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፡፡ ሲኦልንም የበዘበዘው እርሱ ነው" አለ።

የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስና ሐዋርያው የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ ስለዚህ ድንቅ ነገር በድርሳኑ ‹‹ነፍሱን ከሥጋው በለየ ጊዜ ያን ጊዜ በሲኦል ፈጥኖ ብርሃን ታየ፡፡ ጌታችን በአካለ ሥጋ ያይደለ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ሔደ፡፡ ሲኦል ተነዋወጠች፤ መሠረቶቿም እፈርስ እፈርስ አሉ፡፡ ምድርን ያለ ጊዜዋ እንዳታልፍ ክብርት ደሙን በምድር ላይ አፈሰሰ፡፡ ከኅልፈት ጠበቃት በእርሷ ያለውንም ዂሉ ጠበቀ፡፡ ስለ ፍጥረት ዂሉ ሥጋውን በመስቀል እንደ ተሰቀለ ተወው፡፡ ነፍሱ ግን ወደ ሲኦል ወረደች ከዚያ ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን አዳነች፤ ሲኦልንም በዘበዘች፡፡ ፍጥረትንም ዂሉ ገንዘብ አደረገች፡፡ ሥጋውም በመቃብር ያሉ ሙታንን አስነሣ፤ ነፍሱም በሲኦል ተግዘው የነበሩ ነፍሳትን ፈታች፤›› እያለ ያወሳል።

በአማን ኢየሱስ ክርስቶስ ተፈፀመ ሲል አስቀድሞ የገባው የአድናችኋለሁ ተስፋ አርብ ተፈጸመ ፣ የሴቲቱ ዘር የእባቡን ራስ እንደሚቀጠቅጥ የተነገረው ተስፋ ተፈጸመ ፣ የኩነኔና የእርግማን ዘመን በሞቱ ተፈጸመ (ገላ 4፥4) ፣ የእግዚአብሔፍ ፍቅር በመስቀል ሞት ፍጹም ሆኖ በመገለጥ ተፈጸመ/ ተከናወነ/ ፣ እኛ እንጸድቅ ዘንድ የኃጢአት ቅጣት በመስቀል ላይ ተፈጸመ ፣ ወደ ሰማይ እየወጣ በአምላካችን ፊት ይከሰን የነበረው የዲያቢሎስ የክስ መብት በክርስቶስ ሞት ተፈጸመ። ዛሬ ይከሰን ዘንድ ወደ ሰማይ ቢወጣ በጌታ በኢየሱስ እጆች ላይ የሚታዩ ችንካሮችና በልብሱ ላይ የሚታየው የደም ነጠብጣብ አፉን ይዘጋዋል። በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ገብቶ የነበረው ጥል በራሱ በጌታችን አስታራቂነት ለአንዴ ተፈጸመ። የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ማለቱ ለእንዴና ለዘላለም የእግዚአብሔርን ምህረት የምናስታውስበት ድምጽ ሆነ ። የበረታ ጌታ ሁላችንንም በቸርነቱ አዳነን እርሱ ተፈፀመ ሲል የኛ ደስታ ፣ የኛ መዳን ፣ የኛ ተስፋ ፣ የኛ መቤዠት በእግዚአብሔር ወልድ በተፈፀመልን የዘላለም ኪዳን ደም መፍሰስ በእውነት ተፈጸመ!!!

ለታረደው በግ ለእርሱ መጀመሪያ ከሌለው አባቱ ጋርና ቅዱስ፣ መልካምና ህይወት ሰጪ ከሆነው መንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ሁሉ ይገባዋል። አሁንና ለዘላለም ለትውልደ ትውልድ አሜን!

https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#ጌታችን በመስቀሉ ከ6-10 ሰዓት በመስቀልላይ ሳለ የተፈጸሙ 7ቱ
ተአምራቶች፤

1ኛ. ፀሐይ ጨለመች
2ኛ. ጨረቃ ደም ሆነች
3ኛ. ከዋክብት ብርሃናቸውን ነሱ
4ኛ. የቤተመቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፈለ
5ኛ. ዐለቶች ተሰነጣጠቁ
6ኛ. መቃብራት ተከፈቱ
7ኛ. የሞቱት ተነሡ፤ ማቴ.27፤45-46

ጌታችን ከ6-9 ሰዓት በመስቀል ላይ ሳለ የተናገራቸው 7ቱ የፍቅር
ቃላት

1ኛ.ኤሎሄኤሎሄ ኤልማስላማሰበቅታኒ ማቴ.27፤46
2ኛ. እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ፡፡
ሉቃ.23፤43
3ኛ.አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራእሰጣለሁ፡፡ ሉቃ.23፤46
4ኛ.አባት ሆይየሚያደርጉትን አየውቁምናይቅር በላቸው፤ሉቃ.2334
5ኛ. እናትህ እነኋት፤ እነሆ ልጅሽ፤ዮሐ.19፤26-27
6ኛ. ተጠማሁ፤ ዮሐ.19፤30
7ኛ. ተፈጸመ፤ ዮሐ.19፤30

13ቱ ሕማማተ መስቀል

1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይመውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድመረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋርመላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀሰፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)
ስብሐትለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱድንግል
ወለመስቀሉክቡር


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
👆👆👆👆👆👆👆👇👇👇
#ሕማሙን ልናገር

#ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ

ሕማሙን ልናገር *አንደበት ቢያጥሩኝም*/2/
መቼም ምንም ቋንቋ *ለዚህ አይገኝም*/2/
ከረጂሙ በጭር *ከሰፊው በጠባብ*/2/
ስለከፈለልኝ *ስለጌታ ላስብ*/2/
አዝ . . . . . . . . . . . //
በጌቴሴማኒ *በአታክልቱ ቦታ*/2/
ምድሪቷ ተሞልታ *በታላቅ ጸጥታ*/2/
የአዳምን ልጅ ስቃይ *በደሉን ሊሸከም*/2/
ጌታችን አዘነ *ተጨለቀ በጣም*/2/
ሐዋርያት ደክመው *ተኝተው ነበረ*/2/
ይሁዳ ከአይሁድ *እንደተማከረ*/2/
ጭፍሮች እየመራ *ጌታውን ሊያስገድል*/2/
የተሠራለትን *ቸርነት ሳይቆጥር*/2/
ፋና እያበሩ *ጭፍሮቹ ሲመጡ*/2/
ጌታን ሊያንገላቱት *እንደዚያ ሲቆጡ*/2/
የአምላኩን ጠላቶች *መንገድ እመራ* /2/
ይሁዳ ብቅ አለ *ከቀያፋ ጋራ* /2/
አዝ . . . . . . . . . . . //
ላቡ ከግንባሩ *እንደ ውኃ ሲወርድ*/2/
በታላቅ ይቅርታ *ጌታችን ሲራመድ*/2/
ምስኪኖችን ሊያጠግብ *ድሆችን ሊታደግ*/2/
ኢየሱስ ቀረበ *እንደሚታረድ በግ*/2/
ይሁዳ ጉንጮቹን *ሳመው በክህደት*/2/
የተማከረውን *የማያውቅ መስሎት*/2/
የአይሁድም ጭፍሮችም *ያዙት ተናጠቁት*/2/
በታላቅ ጭካኔ *በሰንሰለት መቱት*/2/
አዝ . . . . . . . . . . . //
በጲላጦስ ችሎት *አቁመው ከሰሱት*/2/
ንጹሑ እየሱስ *ይሙት በቃ አሉት*/2/
እጆቹን ቸንክረው *በጠንካራ ብረት*/2/
በእፀመስቀሉ *ቀራንዮ ዋለ*/2/
ወልደ እጓለዕመኅያው *ተጠማሁ እያለ*/2/
ሐሞት እና ከርቤ *ቀላቅለው አጠጡት*/2/
እረ እንዴት ጨከኑ *በምሬት ላይ ምሬት*/2/
------------------------------------------
ሕማሙን ልናገር አንደበት ቢያጥሩኝም
መቼም ምንም ቋንቋ ለዚህ አይገኝም
ከረጂሙ በጭር ከሰፊው በጠባብ
ስለከፈለልኝ ስለጌታ ላስብ
አዝ . . . . . . . . . . . //
ፍጥረታት ተጨንቀው በአይሁድ ክፋት
በየተፈጠሯቸው እርቃሉን ሸፈኑት
ጨረቃ ደም ሆነች ፀሐይም ጨለመች
አልፋና ኦሜጋ ተሰቅሎ ስላየች
ከዋክብት እረግፈው ምድር ተናወጠች
መባርቅትም ታዩ ተቆጣ ባሕሩ
መለሳቸው እንጂ ስለፈጹም ፍቅሩ/2/
ከወንበዴ ጋራ ከመሀል አድርገው
ጌታን አንገላቱት በመስቀል ላይ ሰቅለው
በቀኝ የነበረ ወንበዴው ለመነው
በመንግሥትህ ጌታ አስበኝ እያለው
አዝ . . . . . . . . . . . //
ከመስቀሉ በታች ዮሐንስን አየው
እስከመስቀል ድረስ ስለተከተለው
ታላቋን ስጦታ እናቱንም ሰጠው
ተፈፀመ አለ ጌታ ህይወቱን ሰጠ
ሞትንም ከሕዝቡ በፍጹም ቆረጠ/2/
አዝ . . . . . . . . . . . //
እንደተለመደው ዲያቢሎስ ቀረበ
ነፍሳትን ለመብላት እርሱ እንደተራበ
ፍጡር መስሎት ነበር በመስቀል ላይ ያለው
በአራቱም ማዕዝን በንፋስ ወጠረው
በሲኦል ወረደ በኃይሉ ብርሃን
ማረከ ጌታችን የአዳም ልጆችን
በሦስተኛውም ቀን ጌታችን ተነሳ
ሞትን ድል ያረገው የይሁዳ አንበሳ
በቃ ተወገደ የሰው ልጅ አበሳ /2/


#ሼር_share በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓት የጠበቁ ፅውፎች ለማንበብ ሆነ ለመማር፡፡

ለመቀላቀል

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

💠 http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo 💠
💠 http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo 💠
💠 http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo 💠


እግዚአብሔር ሃገራችንን እና ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን የእመቤታችን ምልጃና ጸሎት አይለየን ።
#ጌታ ሆይ

#ሊቀ መ ዘምራን ኪነጥበብ
......
ጌታ ሆይ
አይሁድ አማፅያን ሰቀሉህ ሆይ
የአለም መድሐኒት የአለም ሲሳይ ሰቀሉህ ሆይ
የአለም መድሐኒት የአለም ሲሳይ ሰቀሉህ ሆይl
የአዳም በደል
አደረሰህ አንተን ለመገደል
የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት
የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት ቸሩ አባት
......
ንፁህ ክርስቶስ
ሆንክ ወንጀለኛ ብለህ ስለኛ
መስቀል አሸክመው አስረው ገረፉህ እያዳፉህ
መስቀል አሸክመው አስረው ገረፉህ እያዳፉህ
ግብዞች
እንደራሳቸው መስሏቸው
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ አንተን ሊጎዱ
......
እጅህና እግርህ
በችንካር ተመታ የአለም ጌታ
የሾህ አክሊል ደፋህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ
የሾህ አክሊል ደፋህ ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ
በመስቀል ላይ
ተጠማሁ ስትል ታላቅ በደል
ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው
ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው ጠጣ ብለው
......
ይቅር ባይ
ግልፅ በደላችን ሁሉን ሳታይ
አንተው ይቅር በለን በእኛው ሳትከፋ እንዳንጠፋ
አንተው ይቅር በለን በእኛው ሳትከፋ እንዳንጠፋ


👇👇👇👇👇
👉 https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo 👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
#እውነት_ስለሆነ

#ሊቀ መ ዘምራን ይልማ ሀይሉ

እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ 
ዋለ ባደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ 
የሀሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው 
ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድነው/2/ 

ከቃሉ እብለትን ባያገኙበትም 
ዝምታውን አይተው አላዘኑለትም 
ባላወቁት መጠን ጠሉት ካለበደል 
ጥፋቱ ምን ይሆን የሚያደርስ ከመስቀል/2/ 

የልቡን ትህትና ፍቅሩን ሳያስተውሉ 
ቸሩ ጌታችንን አቻኩለው ሰቀሉ 
እሩህሩሁን ጌታ ቸንክረው ሰቀሉት 
ሞትን አስውግዶ ቢሰጣቸው ህይወት/2/ 

ስለ ቸርነቱ ስድብን ከፈሉት 
ስለ ርህራሄው የሾህ አክሊል ሰጡት 
ሀሞትና ከርቤ ሆምጣጤ ደባልቀው 
መራራ አስጎነጩት ጨክኖልባቸው/2/ 

ፈውስን ለሰጣቸው ልባቸውን ሞልተው 
አሉት ወንበዴ ነው ስቀለው ስቀለው 
ከጁ በረከትን የተሻሙ ሁሉ 
ይጮሁ ነበረ ይገደል እያሉ/2/

💚 https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo 💚
💛 https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo 💛
❤️ https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo ❤️
#አልፋና ኦሜጋ

አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በካሃዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ

ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉሀ
ጽድቅን ስለ ሠራህ በወንጌል ከሰሱህ
ለአዳም ልጅ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
………አዝ…………..
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስረው
እንደ በግ ተጎተትክ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ
………አዝ…………..
በዓውደ ምኲናን ከጲላጦስ ፊት
አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከሄሮድስም ዘንድ አቀረቡህ በዋጅ
………አዝ…………..
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
………አዝ…………..
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አሁዶች በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ፤

👇👇. 👇👇👇
👉 https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo👈
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ኦ አርምሞ ዘመጠነ ዝ አርምሞ ?
ኦ ትዕግስት ዘመጠነ ዝ ትዕግስት?
ኦ ሂሩት ዘመጠነ ዝ ሂሩት ?
ኦ ፍቅር ዘመጠነ ፍቅረ ሠብ ?
( ይህን ያህል ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው ? ይህን ያህል ዝመታ እንደምን ያለ ዝመታ ነው ? ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው ?

ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
"አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ"

2ኛ ቆሮ 5 : 4

@ortodoxtewahedo
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ በትናንትናው ዕለት ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ አሳውቀን ነበር።

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን እየገለጽን፣ ይህነ ላደረገ ሁሌም ለማይተወን ቸር አምላካችን ምስጋና እናቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ በሂደቱ በቀና መንፈስ ለተባበሩን የተለያዩ አካላት እንዲሁም አጣዳፊ ምላሽ ለሰጡን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን።

በተጨማሪም በትዕግሥት ስትከታተሉና በጸሎት ስታስቡ ለነበራችሁ አባቶች፣ ምእመናን እና የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እያመሰገንን፣ በዓሉ የሰላምና የበረከት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

ማኅበረ ቅዱሳን!

@ortodoxtewahedo
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት (የድኅነት ቀን) በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩ እና አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከናወነ ።

@ortodoxtewahedo
2024/05/04 02:37:19
Back to Top
HTML Embed Code: