Telegram Web Link
​​​​​​. 😘 ♥️✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

😘 ♥️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘●▬ተከታታይ ልቦለድ▬

#ክፍል\_7

...🖍ከማክሰኞ እስከ አርብ አስራሁለተኛ ክፍሎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ስለሚፈተኑ ትምህርት አልነበረንም። ለሙድ ብለን እሮብ ተገናኝተን ቃምን። ለነገሩ ትንሽ ቅጠል ስለነበር የጎረስኩት አልመረቀንኩም። ከሪሜ ግን አይኑ ቦግ ብሏል። ጥርሴን እየፋቅኩኝ ቅዳሜ እና እሁድን ሶደሬ ስለማሳልፍ ሚኪ ቅዳሜ በጠዋት እኛ ቤት ሄዶ ለእማዬ እንጀራዉን ወደ ምግብ ቤት እንዲያደርስላት አደራ አልኩት። አርብን እዚሁ የተከራየነዉ ቤት አድሬ በለሊት ለመሄድ ነዉ ያሰብኩት።
የጎፈረ ፀጉሩን እየፈተለ "ስታይል ሀቢቤ ደሞ ለዚህ አንሳለሁ እንዴ?" አለኝ። እንዳያረፍድባት ደጋግሜ አደራ አልኩት።
አብነት የመጨረሻዋን ቅጠል እየጎረሰ "ስማ ሀቢቤ ያቺ የጎረቤታችሁ ልጅ አስራሁለተኛ ክፍል ናት ምናምን ያልከዉ ፈተና እንዴት ነዉ አለችህ? ሰርተዉታል?" አለኝ። እዉነት ለመናገር አምሪያ ተፈታኝ መሆኗን በራሱ ረስቼዉ ነበር።
.
ማታ ከእማዬ ጋር ወደ ቤት ስንገባ አምሪያ በራቸዉ ላይ እንጨት አጋድማ ለመፍለጥ ስትሞክር ደረስን። ሲጀመር መፍለጥ አይደለም መጥረቢያ መያዝ ራሱ አትችልም። እናቴ ሂድ አግዛት ማለቷ አይቀርም ብዬ ቀድሜ "እንኪ ሰፌዱን ላግዛት!" አልኳት።
እማዬ ፈገግ ብላ "ተወዉ ደክሞሀል!" አለችኝ። በጣም ደስ አለኝ! ግልግል አልኩ በልቤ። ወዲያዉ እናቴ ሳቀችና "አመዳም ሂድና ፍለጥላት! ሴት ልጅ የጉልበት ስራ ስትሰራ ይሰማህ!" አለችኝ። እየተበሳጨሁ ወደነአምሪያ ቤት በር ሄድኩና መጥረቢያዉን እየተቀበልኳት "አምሪ ግቢያችሁ ዉስጥ አትፈልጪም ነበር? ዉስጥ አይሻልም?" አልኳት። እዉነት ለመናገር ምርር ብሎኛል።
አምሪ ጥርሷን ያጠረዉ ሽቦ እስኪታይ ድረስ ፈገግ እያለች "ቴራዞ ነዉ ሙሉ ግቢዉ! እንጨት ቢፈለጥበት ይሰበራል።" አለችኝ። ቴራዞዉ አየር ላይ አልቆመ የሚሰበረዉ! የሆነች ብሽቅ።
በመጥረቢያዉ የሰነጠቅኩትን እንጨት በእጆቼ ለመለያየት እየሞከርኩ "ፈተና እንዴት ይዞሻል?" አልኳት።
"ምንም አይልም! ያዉ ዉጤት ሲመጣ ነዉ እንዴት እንደነበረ የሚታወቀዉ።" አለችኝ። እኔ እየፈለጥኩ አምሪያ ቆማ እያወራችኝ አባቷ ከቤት ወጡ። እንጨቱን እያዩ "ይሄ ደግሞ ለምንድነዉ?" አሉ።
አምሪያ እየተሽቆጠቆጠች "ለማንደጃ ፈልገነዉ ነዉ።" አለች። አባቷ ለቤቱ እንጨት ሲያስፈልግ አለማወቃቸዉ ገረመኝ። ለነገሩ እሳቸዉ ኩሽና አይገቡ! አባቷ መኪናቸዉ ዉስጥ ገብተዉ እንደሄዱ "ቆይ አባትሽ ወዴት ነዉ ሁሌ በዚህ ሰዓት የሚሄዱት?" አልኳት።
"ትልቅ የሀይማኖት ትምህርት ቤት አለዉ። ቀን ንግድ ላይ ስለሚዉል አይመቸዉም ፤ አሁን ነዉ ሄዶ ያለዉን ነገር የሚያየዉና ለአስተማሪዎቹ የሚያስፈልገዉን ነገር የሚያሟላላቸዉ።" አለችኝ።
ፈልጬላት ስጨርስ ወደ ግቢያቸዉ እንጨቱን እያስገባሁላት "መልካም ፈተና!" አልኳት።
እሷም መልሳ "መልካም ፈተና!" አለችኝ። እኔ ተፈታኝ አልነበርኩም። የሆነች ቀዉስ ነገር።
.
ቅዳሜ አይደርስ የለ ደረሰ። እነፌቪ ቀደም ብለዉ ሚኒባስ ኮንትራት አናግረዉ ስለነበር ከያለንበት ለቃቀመን። እማዬ የምታዉቀዉ ከሪሜ ቤተሰቦቹ ለቅሶ ለመድረስ ክፍለሀገር ስለሚሄዱ ከሱ ጋር ለመሆን መሄዴን ነዉ። በነገራችን ላይ ከፌቪ ዉጪ ሌሎች አራት ልጆች አብረዉን አሉ። አንዷ ፍቅር ናት የፌቪ ጓደኛ! ባለፈዉ ካፌ ያገኘኋት! ስገምት እሷም ከፍቅረኛዋ ጋር ናት። አብሯት የተቀመጠ ቀላ ያለ ልጅ አለ። ሁለቱ የቀሩትም ፍቅረኞች ናቸዉ። ሶስት ወንድ ሶስት ሴት ነን። ደብረዘይትን እንዳለፍን እማዬ ጋር ደዉዬ ሚኪ መጥቶ እንጀራዉን እንዳደረሰላት አረጋገጥኩ። ሶደሬ እንደደረስን ፌቨን እና አንድ ፍራኦል ነኝ ብሎ የተዋወቀኝ ልጅ አልጋ ለመያዝ ተሯሯጡ። ሶስት አልጋ ያዝን። እቃችንን አስተካክለን ፈታ ማለት ጀመርን። ቅዳሜ መሽቶ የቁርጡ ሰዓት ደረሰና ከፌቪ ጋር ከአዲስ አበባ አዳማ ድረስ ያስመጣንን ጉዳይ ተገበርነዉ። ማንም ያልነካት ልጃገረድ ነበረች። እኔ የመጀመሪያዋ ሆንኩኝ። አብረን አደርን።
.
እሁድ ጠዋቱን እኔ እየዋኘሁ ፌቪ ገንዳዉ አጠገብ ተቀምጣ እያየችኝ እያለ ትልቁ መዋኛ ፊትለፊት በፍፁም ያልጠበቅኩትን ሰዉ አየሁ። አምሪያ ነበረች። ረዥም ቀሚሷን እንደለበሰች ከዋና ገንዳዉ ፊት ለፊት ቆማለች። ምን ልትሰራ መጣች? ደሞ አይታኛለች። ፌቪን ትቼ ወደ ትልቁ መዋኛ ብረቱን ዘልዬ ገባሁ። እየዋኘሁ አምሪያ ወደ ቆመችበት ጥግ ሄድኩ። ዉሀዉ ዉስጥ እንደሆንኩ ቀና ብዬ እያየኋት "እንዴት መጣሽ?" አልኳት።
ትልቁ ገንዳ ዉስጥ የሚዋኙትን ልጆች እያሳየችኝ "ፈተና ስለጨረስን ዘና ለማለት ከጓደኞቼ ጋር መጥተን ነዉ። አንተ እዚህ ምን ትሰራለህ?" አለችኝ።
እነፍራኦልን እያሳየኋት "አንዳንዴ ዋና ጥሩ ነዉ ብዬ ከጓደኞቼ ጋር መጥቼ ነዉ።" አልኳት።
በሽቦ የታጠረዉ ጥርሷ እስኪታይ ሳቀችና በከንፈሮቿ ሽቦዉን ለመሸፈን እየሞከረች "ደስ ይላል! በርታበት። ለማንኛዉም ቤት ሌላ ቦታ እንጂ እዚህ እንደምዝናና ስለማያዉቁ እዚህ እንደተገናኘን እንዳታወራ!" አለችኝ።
እየሳቅኩ "አላወራም! ባይሆን ክፍያዉን አስቢበት!" አልኳትና ወደነፌቪ ተመለስኩ። ለፌቪ ማንነቷን በደንብ አስረዳኋት...

😘#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃..................❥

😘🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳,
​​​​​​😘♥️✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

😘♥️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘 ●▬ተከታታይ ልቦለድ▬

#ክፍል\_8

...🖍ከሴቶች እየዋኘች የነበረችዉ ፍቅር ብቻ ነበረች። ሌሎቹ የማታዉ የሞት ሽረት ትግል አልፈስፍሷቸዋል። ከመዋኛ ገንዳዉ ወጥቼ ከፌቪ ጋር ወደ መኝታ ክፍላችን ሄድን። ስልኬን ስመለከተዉ ሶስት ሚስኮል አለ። ከፍቼ አየሁት። ሁለቱ ከሚኪያስ ነዉ። አንዱን አብነት ነዉ። ሚኪ ጋር ደወልኩኝ። እየተበሳጨ "እሷ ልጃገረድ ለሆነችዉ አንተን ምን ያሽኮረምምሀል!? ስልክ አታነሳም!?" አለ።
"ባክህ እየዋኘን ነበር አትጩህ!" አልኩት። ሚኪ ስለነበረዉ ነገር ጠይቆኝ ፌቪ አጠገቤ ስለነበረች በማያስባንን ቋንቋ አዳራችንን ነካካሁለት። የሚኪን እንደዘጋሁት አብነት ደወለና "ሀቢቤ ነዳጅ እንደፈለቀልን ቁጠረዉ ሜሮን ማለቴ ራቁቷን ፎቶ የላከችልኝ ልጅ ስምንት ሺህ ብር ላከችልኝ።" አለኝ። ፌቨን አጠገቤ ስለነበረች ማታ ስመለስ እንደምደዉል ነግሬዉ ዘጋሁት። እንዴት ብታብድለት ይሄን ሁሉ ብር እንደላከችለት ገርሞኛል።
.
ከሶደሬ እንደተመለስን ከፌቪ ጋር ልንለያይ ስንል ፌቪ አይን አይኔን እያየች "አትራቀኝ እንጂ ገና ነብሴንም እሰጥሀለሁ!" አለችኝ። ቻዉ ተባብለን መንገድ ስጀምር መልሳ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ። ሁሉነገሯ እኔ ጋር ያለ ይመስላል። አይኗ ዉስጥ ፍርሀት እና አክብሮት በደንብ ይታያል። በደንብ አቅፌ ተሰናበትኳትና ወደ ቤት ሄድኩ። መንገድ ላይ እያለሁ ፌቪ ደወለችልኝ። ሁኔታዋ ሁሉ ገርሞኛል። አዳሩ ሁሉ ነገሯን ቀያይሮታል። ፍቅሯ በዝቶባት ወደ አምልኮት እንዳያድግ ፈራሁ። በቃ የሷን ስሜት የሚገልፅላት ሙዚቃ ነዉ። ዘፈነችልኝ። አዳመጥኳት። ልብ ትበላለች።
.
ቤት ስገባ እማዬ፣የአምሪያ እናትና አምሪያ ተቀምጠዉ ይጨዋወታሉ። አምሪያ ቡና እየቀዳች ነዉ። ከመቼዉ ደርሳ እንደሆነ ፈጣሪ ነዉ የሚያዉቀዉ። ምናልባት ቀደም ብላ መጥታ ይሆናል። ሰላም ብያቸዉ ተቀመጥኩ።
"ሽኩሪያዬ አምሪያ ጓደኞቿ ጋር ሄዳ አረፈደችብኝ እንጂ ቶሎ ነበር ለመምጣት ያሰብኩት!" አሉ። ሽኩሪያ የእናቴ ስም ነዉ። ሁሌም እማ ስለምላት ሽኩሪያ ሲባል ሌላ ሰዉ የተጠራ ነዉ የሚመስለኝ። አምሪያ በአይኗ "አፍህን ዝጋ!" የሚል ቆንጆ ማስጠንቀቂያ ሰጠችኝ።
እናቴ አምሪያን እያየች "ቆይ አምሪያዬ ብዙ ጊዜ እሁድ እሁድ አላይሽም የት ነዉ የምትዉይዉ?" አለች።
አምሪያ "ጠዋት ጠዋት መስጂድ ትምህርት አለኝ። ከዛ
በኋላ ደግሞ ወንድሞቼ ቤት ስለምሄድ ይሆናል።" አለች። እንግዲህ አሁን ስለመስጂድ ከተነሳ የአምሪያ እናት ወይዘሮ ለይላ መስጂድ ለምን አትሄድም ብለዉ ስለሚነዘንዙኝ ቀድሜ ብወጣ ይሻላል ብዬ ወደ መኝታ ክፍሌ ሄድኩ።
ወዲያዉ አብነት ጋር ደዉዬ እንዴት ስምንት ሺህ ብር ሁሉ ልትልክለት እንደቻለች ጠየቅኩት።
"እናቴ ታመዋል ለኦፕራሲዮን ብር አጣሁ ስላት ከእናትህ ምንም አይበልጥብኝም ብላ ላከችልኝ።" አለኝ። ብሽቅ አልኩ። የሆነ ለማኝ ነገር ነዉ። እናቴ ታመዋል ብሎ ብር ከሚያስልክ ብሩ ጥንቅር ብሎ ቢቀርብን ይሻል ነበር።
የኔዎቹ ለልብስህ መግዣ ፣ ስጦታ ይሁንህ ምናምን እያሉ ነዉ የሚልኩት። እኔ ሲጀመር ማለቃቀስ አይመቸኝም። ጠብረር ስልባቸዉ ወደነሱ ለመሳብ ሲሉ የሆነ ነገር ይልካሉ። አለቀ!
.
እኔ መኝታ ክፍል ተቀምጬ ፌስቡክ ላይ እጀናጀናለሁ። እነእማዬ ደግሞ ሳሎን ቡናቸዉን እየጠጡ ይጨዋወታሉ። መጀናጀን ከጀመርኩ ትንሽ እንደቆየሁ ሁሉም በአንዴ ፀጥ አሉ። ጫጫታቸዉ ጠፋ። እማዬ ስታቃስት ሰማሁ። አምሪያ "ሀቢብ!" ብላ ጮኸች። ከአልጋዉ ላይ ተስፈንጥሬ ተነስቼ ወደ ሳሎን ተንደረደርኩ። እማዬ ፍራሹ ላይ ተዘርራ በእጆቿ ሆዷን ጨምድዳ ይዛ እግሮቿን እያፋተገች ታቃስታለች። ወይዘሮ ለይላ ተደናግጠዉ አንገቷን ደግፈዉ ይዘዉ ያዩኛል። የማደርገዉን ነገር ነዉ ያጣሁት። አጠገቧ ተቀምጬ አያታለሁ። ወይዘሮ ለይላ "አምሪ አባትሽ ጋር ደዉይለት!" አሉ። አምሪያ ወዲያዉ አባቷ ጋር ደወለች። አላማዉ መኪና ይዞ እንዲመጣ እና ሀኪም ቤት እንድንወስዳት ነዉ። ድንዝዝ ብያለሁ! እማዬ እንደዚህ ስትታመም አይቼ አላዉቅም። አንዳንዴ ያማት ነበር። ታይታዉ ጉበትሽ ላይ ነዉ ችግሩ ብለዋት ነበር። ከዛ በኋላ ህክምናዉን የወሰደችም አይመስለኝም። ግን አልፎ አልፎ ቢያማትም እንዲህ እንደዛሬዉ አሰቃይቷት አያዉቅም። ፊቷ ሙሉ ለሙሉ ነዉ ቅይር ያለዉ።
ከአምስት ደቂቃ በኋላ የአምሪያ አባት ሀጂ ራህመቶ ደረሱ። እማዬን መኪናዉ ዉስጥ አስገብተን ወደ ሆስፒታል ሄድን። ለሚኪ የተፈጠረዉን ነገር ደዉዬ ነገርኩት። ሰፈራችን ያለ አንድ የግል ሆስፒታል ነበር የሄድነዉ። ሀኪሞቹ እማዬን አስገብተዉ ማከም ጀመሩ። እኛ ዉጪ ሆነን እንጠብቃለን። ጭንቅ ብሎኛል። ሚኪ ሲከንፍ ደረሰ፤ የአምሪያ አባት ሀጂ ራህመቶ አብረዉኝ አሉ። የሆነ የማላስበዉ ስሜት ዉርር አደረገኝ። ተጨንቄ አላዉቅም! በጣም ጨነቀኝ...

😘 #ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃..................❥

😘 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳
😘 ከ15❤️ በኋላ ይቀጥላል
😘✿የማይፋቅ ስህተት✿

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ💢

😘●▬ተከታታይ ልቦለድ▬

😘 ክፍል_9

...🖍እማዬን ያስገባንበት የግል ሆስፒታል ዶክተሮች ይሯሯጣሉ። ዶክተሯ አስጠርታ አየችኝና "ምኗ ነህ?" አለችኝ። ይሀ ስንት ሴት እንደ ቅቤ የሚያቀልጠዉ ምላሴ እየከዳኝ "ልጇ!" አልኳት። ፈገግ አለችና "ከቤተሰብ አባላችሁ ዉስጥ ካንተ ከፍ ያለ ሰዉ አለ?" አለችኝ።
"ቤተሰብ እንኳ የለም ጎረቤት ግን አሉ።" አልኳት።
የተቀመጠችበትን ወንበር ወደ ጠረዼዛዋ እያስጠጋች "ስምህ ማነዉ?" አለችኝ።
"ሀቢብ ከማል" አልኳት።
ዶክተሯ በረዥሙ ከተነፈሰች በኋላ እንግሊዘኛ የቀላቀለ የረዥም ሰዓት ማብራሪያ መስጠት ጀመረች። እኔ ሀሳቤ ብትንትን ብሏል። የምትለዉን ሁላ ማዳመጥ አልቻልኩም።
መጨረሻ ላይ "...ስለዚህ ሀቢቤ የእናትህ ጉበት አሁን ባልኩህ መልኩ ለረዥም ጊዜ የቆየ ጉዳት ስላስተናገደ አሁን ሙሉ ለሙሉ ፌል ወደማድረጉ ተቃርቧል። በቀዶ ጥገና የቻልነዉን ለማድረግ እንሞክራለን። ሌላ ሰዉ ከሌለ አንተ ትፈርምልናለህ።" አለችኝ። የሆነ ድንዝዝ ስል ይታወቀኛል። ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ ወደ ዉጪ ወጣሁ። ኮሪደሩ ላይ ሀጂ ራህመቶና ሚኪ ተቀምጠዋል። ከዶክተሯ ቢሮ ስወጣ ሁለቱም ከመቀመጫቸዉ ብድግ ብለዉ ተጠጉኝ።
ሀጂ ራህመቶ "ምን አሉ?" አሉኝ። ዝም ብዬ መተላለፊያዉ ላይ ያለዉ ወንበር ላይ ዘፍ አልኩኝ።
.
ሀጂ ራህመቶ ፈጠን ብለዉ እየተራመዱ ወደ ዶክተሯ ቢሮ ገቡ። ሚኪ ከአጠገቤ እየተቀመጠ "ሀቢቤ ጠንከር በል እንጂ ያንተ መፍዘዝ ችግር ሊፈጥር ይችላል።" አለኝ። እንባዬን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ "እንደመምከር ቀላል ቢሆን ጥሩ ነበር።" አልኩት።
ሀጂ ራህመቶ ከዶክተሯ ጋር አንድ ላይ ሆነዉ ከቢሮ ወጡ። ዶክተሯ እጇ ላይ ወረቀት ይዛለች። ከአጠገቤ ተቀመጠችና "ዶ/ር ቀመሪያ እባላለሁ።" አለችኝ። ስገምት ሀጂ ራህመቶ ብቸኛ መሆኔን ምናምን ነግረዋት መሆን አለበት።
ወረቀቱን እያስጠጋችልኝ "እኛ እናትህን ለማዳን የምንችለዉን እናደርጋለን። አንተ ግን ፍቃድህን ልትሰጠን ይገባል።" አለችኝ።
ሀጂ ራህመቶ "ሀቢቤ መቆየታችን ችግር ይፈጥራል። ቶሎ ወረቀቱ ላይ ፈርምላት።" አሉኝ። እጄ እየተንቀጠቀጠ ወረቀቱ ላይ ፈረምኩ። ወዲያዉ ሀጂ እና ዶክተሯ እየተጣደፉ ወደ ፎቅ ወጡ። እኔና ሚኪ ተክዘን ተቀምጠናል። ክፍያዉን ሁሉ የከፈሉት ሀጂ ራህመቶ ናቸዉ።

😘ሚኪ ስልኩ በተደጋጋሚ ይጠራል። ዞር ብዬ ሳየዉ በአንድ እጁ የኔን ስልክ በሌላኛዉ እጁ የራሱን ይዟል። መች ስልኬን እንደሰጠሁት ፈጣሪ ነዉ የሚያዉቀዉ። ትንሽ ቆይቶ የኔም ስልክ ሲጠራ ሰማሁ። ሚኪ ወዲያዉ ዘጋዉ። ያዉ ፌቨን ናት የምትሆነዉ። ምሽቱን ቻት ላይ ስጠፋ ጨንቋት መሆን አለበት። አንገቴን እንዳቀረቀርኩ "ሚኪ ስንት ሰዓት ሆነ?" አልኩት። "ዘጠኝ ከሩብ" አለኝ። የፈጣሪ ያለህ ፌቪ እስከአሁን አልተኛችም።
"ከዚህ በኋላ ከደወለች አንሳና አናግራት።" አልኩት። ብዙም ሳይቆይ ደወለች ሚኪ ከመቀመጫዉ ተነስቶ ወደ ታች ደረጃዉን እየወረደ ማናገር ጀመረ።
.
ለሊቱን ይሀ የፈረደበት ወንበር ላይ እንደተቀመጥኩ አነጋሁት። ሀጂ ራህመቶ ለሊቱን ሙሉ ሲሯሯጡ ቆዩ። እኔ እንደሆነ ከመንቀሳቀሴ በቀር በድን ሆኛለሁ ብል ይቀላል። ሚኪ ባይኖር ሀጂ በጣም የሚቸገሩ ይመስለኛል።
ጎህ እንደመቅደድ ሲል ሚኪ እና ሀጂ ራህመቶ ከላይኛዉ ፎቅ ወረዱ። ሚኪ ከአጠገቤ እየተቀመጠ "ቀዶ ጥገናዉን ጨርሰዋል።" አለኝ። ልቤ ትንሽ ሲረጋጋ ይሰማኛል። "እና እማዬ ደህና ናት?" አልኩ። በስንት መከራ ከአፌ የወጣች ቃል ነበረች። "ገና አልነቁም ግን ደህና ናቸዉ።" አለኝ።
ሀጂ ራህመቶ ለሊቱን ሙሉ ሲንቀጠቀጥ ያደረዉን ወገባቸዉን ለማሳረፍ ቀስ ብለዉ ወንበሩ ላይ ተቀመጡ።
ሀጂ ፈገግ ካሉ በኋላ "ሀቢቤ አንተ ደክሞሀል አረፍ በል እኛ እንቆያለን።" አሉኝ። የሚገርሙ ሰዉ ናቸዉ። ይሄን ያህል ለሰዉ መኖር ማን ይሆን ያስተማራቸዉ? ምንም ቢደክመኝም እናቴ ሆስፒታል ተኝታ እኔ ወደ ቤት መሄድ አልፈለግኩም። ባይሆን እሳቸዉ አረፍ እንዲሉ ጠየቅኳቸዉ ግን አሻፈረኝ አሉ። ወዲያዉ ዶክተሯ ቦርሳዋን ይዛ እየወጣች "እዚህ ተቀምጣችሁ ምንም አትሰሩም። ከነቁ ነርሶቹ ስላሉ ችግር የለም። እስከ አራት ሰዓት አረፍ ብላችሁ ተመለሱ።" አለችን።
ወዲያዉ ሀጂ ራህመቶ ሰዓታቸዉን ተመለከቱና "ዉይ አስራ ሁለት ተኩል ሆኗል። እስከዛ አፋችን ላይ ምግብ ጣል አድርገን እንመለስ።" አሉ። በሀጂ መኪና ሶስታችንም ወደነ ሀጂ ቤት ሄድን።
.
እነሀጂ ቤት ስንደርስ ሁሉም ከእንቅልፋቸዉ ተነስተዋል። ቤቱ ተሰነዳድቷል። በልቤ "ለሊቱን አይተኙም እንዴ?" አልኩ። ማታ አምሪያና ወ/ሮ ለይላ አብረዉን ሊመጡ ሲሉ ሀጂ እኛ እንበቃለን ብለዉ እንደመለሷቸዉ ትዝ አለኝ። ሀጂ መንገድ ላይ ሆነን ደዉለዉ ስለነበር ይመስለኛል ገና እንደገባን አምሪያ መጥታ ምንጣፉ ላይ የሚያምር ላስቲክ አነጠፈች። ሚኪ በአይኑ "ምንድነዉ?" ብሎ ጠየቀኝ። ያዉ ምግብ ሲቀርብበት ይገባዋል ብዬ ዝም አልኩት። ወዲያዉ አምሪያና ወ/ሮ ለይላ ምግቡን አቀራረቡና መብላት ጀመርን። ወ/ሮ ለይላ ስለ እናቴ ሁኔታ ጠየቁ። ሀጂ ሁሉንም በዝርዝር አስረዷቸዉ። የአምሪያ ፊት ላይ የሀዘን ድባብ ይታያል። ምግቡን በልተን እንደጨረስን እኔና ሚኪ እኛ ቤት ገብተን አረፍ አልን። ወገብ ለማሳረፍ ያክል ነዉ እንጂ በወጉም እንቅልፍ አልወሰደኝም ነበር። ትንሽ ካንገላታኝ በኋላ ግን እንቅልፍ ይዞኝ እብስ አለ።
.
ከእንቅልፌ ስነቃ ሚኪያስ አጠገቤ የለም። ከአጠገቤ ስልኬ ተቀምጧል። አነሳሁና ሰዓቱን ተመለከትኩት። ስድስት ሰዓት ሆኗል። ደንግጬ ከአልጋዉ ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ። የአልጋዉ ጫፍ ላይ ወረቀት ተቀምጧል። አንስቼ አነበብኩት። የሚኪ ፅሁፍ ነዉ። "ሀቢቤ አረፍ ብለህ ና እኔናሀጂ እዛዉ ስለሄድን አትጨነቅ።" ይላል። ወዲያዉ ተነስቼ ተጣጠብኩና ወደ ሆስፒታሉ ለመሄድ ከቤት ወጣሁ። ወዲያዉ ፌቨን ደወለችልኝ።
አነሳሁትና "ወዬ ፌቪ" አልኳት።
ፌቪ እያለቀሰች "ሀቢቤ በጌታ የት ሆስፒታል ነዉ ያላችሁት ጓደኛህ አልነግርም አለኝ። ፕሊስ መረጋጋት አልቻልኩም ልምጣና ልያቸዉ።" አለችኝ። ለቅሶዋ ልብ ይነካል። ልነግራት አሰብኩና ሀጂ ራህመቶ መኖራቸዉን ሳስብ መምጣቷ አግባብ እንዳልሆነ ተሰማኝ።
"ፌቪ አንቺ መምጣትሽ ለኔ ጥሩ አይደለም። ባይሆን ሰዓት ካገኘዉ እኔ ወጥቼ አገኝሻለሁ።" አልኳት። ምንም መምጣት ብትፈልግም ለኔ ጥሩ አይደለም ስላልኳት ተስማማች።...

😘 ይቀጥላል...

😘❥..........

😘🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳
😘,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,

ክፍል አስር ከ15 ❤️ ቡኋላ ይቀጥላል
ፍቅር እና ሳቅ😂 pinned «😘✿የማይፋቅ ስህተት✿ 😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ💢 😘●▬ተከታታይ ልቦለድ▬ 😘 ክፍል_9 ...🖍እማዬን ያስገባንበት የግል ሆስፒታል ዶክተሮች ይሯሯጣሉ። ዶክተሯ አስጠርታ አየችኝና "ምኗ ነህ?" አለችኝ። ይሀ ስንት ሴት እንደ ቅቤ የሚያቀልጠዉ ምላሴ እየከዳኝ "ልጇ!" አልኳት። ፈገግ አለችና "ከቤተሰብ አባላችሁ ዉስጥ ካንተ ከፍ…»
😘💏 ለጥሩ የፍቅር ግንኙነት የሚረዱ መንገዶች
♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡
1- እርስ በእርስ መዋደድ
2- አለመዋሸት
3- ሁሌም ጥሩ ለመሆን መሞከር
4- ስትጎዳም ሆነ ስትጎዳ ይቅርታ በማድረግ ላይ አተኩር
5- ቀና ማሰብ
6- ስለ መነጣጠል ምን ጊዜም አታስብ
7- ምንጊዜም ውስጥህ ላይ የሆነ ችግር እያለ ምንም ችግር የለም አትበል
8- ያለፈውን ጊዜ ከ አሁኑ ሂውት አታነፃፅር
9- መስጠትም መቀበልም ልመድ
10- ሀሳብን ሙሉ ለሙሉ በነጻነት መግለፅ አለመፍራት
♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡♡

💞 በመጨረሻም እዚህ ምድር ፍፁም ሰው የለምና ለሚገጥምህ ችግር በሙሉ ነገር ከአምላክ ነው የመጣው ብለህ ትግስት አድርግ::

👫 የምን አይቶ ዝም ማለት ነው ለወዳጅ ዘመድዎ ለጓደኛዎ ማጋራትን አይዘንጉ
👫 #Share
👫 #Share
@pclovee
@pclovee
😘✿የማይፋቅ ስህተት✿

😘♥️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘●▬ተከታታይ ልቦለድ▬

😘ክፍል_10

...🖍ግን ሀቢቤ ስደዉል ስልክ አንሳልኝ እሺ!" አለችኝ።
እሺ ብያት ተሰነባበትን።
.
ሆስፒታል ስደርስ ሀጂ እና ሚኪ እማዬ የተኛችበት ክፍል ዉስጥ ተቀምጠዋል። እማዬ ነቅታለች። የሆነ የሆነ ነገር ተሰካክቶላት ተጋድማለች። መናገር ምናምን ግን አልጀመረችም። ሳያት የማላዉቀዉ ስሜት ዉርር አደረገኝ። ወዲያዉ ግንባሯን ሳምኩና ከነሚኪ ጋር ተቀመጥኩ። ወዲያዉ ሀጂ ፈገግ ብለዉ "ዶክተሯ ነገ ይወጣሉ ብላለች።" አሉኝ። በጣም ደስ አለኝ። እማዬ እንደዚህ በአጭር ቀን ከሆስፒታል ትወጣለች ብዬ አልገመትኩም ነበር።
"እና ዉጤቷን ነገሯችሁ?" አልኩ በጉጉት የሚሉትን ለመስማት እየጠበቅኩ።
ሚኪ ወዲያዉ ፈጠን ብሎ "አዎ ነገሩን ደህና ናት ነገ በጣም ከበዛ ከነገ ወዲያ ወደ ቤት እንወስዳቸዋለን።" አለኝ። ሚኪ ደግሞ ሌላ አንድ ቀን ልትቆይ እንደምትችል አረዳኝ። ቢሆንም ጠብቄዉ ከነበረዉ የተሻለ ነገር ነበር።
.
ከከሰዓቱን አብነት እና ከሪም ወደ ሆስፒታል መጡ። ስገምት ሚኪ ነግሯቸዉ መሆን አለበት። አብነት እያቀፈኝ "አብሽር ሀቢባችን ይሻላቸዋል እሺ!" አለኝ። ከሪሜ አይኔን ማየት እየከበደ
ዉ ሰላም አለኝ። እናቴን አይተዋት ካለችበት ክፍል እየወጣን አብነት "ሀቢቤ መላ ከየት አግኝተህ ነዉ እዚህ ያስተኛሀቸዉ?" አለኝ።
ሚኪ ፀጉሩን እየጠቀለለ "ባክህ አንድ መልዓክ የሆኑ ሰዉዬ ናቸዉ የተሯሯጡለት አሁን ስራ ቦታቸዉ ላይ አንድ አንድ ነገሮችን ለማስተካከል ሄደዉ ነዉ።" አለ።
አይን አይኔን እያየ "እግዚአብሔር ይጠብቃቸዉ። የእዉነት በጣም ጥሩ ሰዉ ናቸዉ። ግን ማናቸዉ?" አለኝ።
ከሪሜ ዝም ማለቱ ገርሞኝ እያየሁት "የአምሪያ ፋዘር ናቸዉ። ያቺ ጎረቤታችን" አልኩ።
ሚኪ ከሪምን እያየዉ "አንተ ደሞ ምናባህ ነዉ የምትቆዝመዉ?" አለዉ።
ከሪሜ ፈገግ ለማለት እየሞከረ "ኧረ አልቆዘምኩም!" አለ። የሆነ ጭንቀታም ነገር ነዉ። በኔ ቦታ ቢሆን ምን ሊሆን እንደሚችል አስቤ ገረመኝ።
ወዲያዉ አብነት ከኪሱ ዉስጥ መቶ መቶ ብሮችን አዉጥቶ እየሰጠኝ "ይኸዉ ሀቢቤ ሰዉየዉን ብዙ ብር ከምናስወጣቸዉ ቢያንስ ልጅቷ የላከችልኝን ስምንት ሺህ ብር እናግዛቸዉ።" አለኝ።
ወዲያዉ ምን ብሎ ልጅቷን ብር እንዳስላካት ትዝ ብሎኝ እየበሸቅኩ "ስማ አንተ ጀዝባ ያንተ ሟርት ነዉ ይኸዉ እናቴን ቀዶ ጥገና ላሰራበት ብለህ ብር አስልከህ እናቴን ቀዶ ጥገና አስገባሀት። ወደዛ ዉሰድልኝ አልፈልገዉም!" አልኩት።
አብነት እንደመለማመጥ እያደረገዉ "ሀቢቤ ታዉቃለህ እኔ ጋር ከሆነ ለረባ ነገር አንጠቀምበትም ስለዚህ ልጅቷም ትፅደቅበት ደሞ ጓደኝነታችን ለመቼ ነዉ?" አለ።
ሚኪ ብሩን እየተቀበለዉ "ዝም በለዉ ባክህ!" አለና ወደኔ እየዞረ "ሰዉየዉ አባትህ መሰለህ እንዴ? ቢያንስ ይህቺን ብር ሰጥተን ልናግዛቸዉ ይገባል።" አለ። በርግጥ ሚኪ ልክ ነዉ። ሀጂ ብዙ ብር ነበር ያወጡት።
ወዲያዉ ከሪሜ "በነገራችን ላይ ፋይናል እሮብ ይጀመራል። ማስታወቂያ ተለጥፏል።" አለን።
"ዛሬ ቀኑ ምንድነዉ?" አልኩ ወደ ከሪሜ እየዞርኩ።
ከሪሜ "ዛሬ ሰኞ ነዉ ፈተናዉ ከነገ ወዲያ ነዉ።" አለ።
ሚኪ "ባክህ አሽቅ የለዉም እኛ እንደሆነ አናጠናም ያዉ ከሪሜ ቸክይና ከቀለሞቹ ጋር እያዋዛን እንሰራዋለን።" አለ።
.
ትንሽ እንደቆየን አምሪያ እና ወ/ሮ ለይላ መጡ። አምሪያ በእጇ ዘንቢል ይዛለች። አጠገባችን ሲደርሱ ወ/ሮ ለይላ ፈገግ ብለዉ "ሀቢቤ ሽኩሪያዬ የት ናት?" አሉኝ። ፈገግ ብዬ ወደ ዉስጥ ይዣቸዉ ገባሁ። አምሪያ ዘንቢሉን ለሚኪ ሰጠችዉ። ወ/ሮ ለይላ ቁጭ ብለዉ ትንሽ ካወሩን በኋላ ከመቀመጫቸዉ እየተነሱ "ምሳችሁን አምጥቼላችኋለሁ። አደራ በደንብ ብሉ። ወደ ማታ ብቅ እላለሁ።" አሉን።
ወዲያዉ አምሪያን እያየሁ "አምሪ ግን ወደ ማታ መምጣት ትችይ ነበር ትምህርት ለምን ቀረሽ?" አልኳት።
አምሪ ሳቀችና በከንፈሯ ጥርሷን ያጠረዉን ሽቦ ለመከለል እየሞከረች "ሀቢቤ ባለፈዉ አርብ እኮ ኢንትራንስ ወሰድን ረሳኸዉ እንዴ አስራሁለት ነኝ እኮ ጨርሰናል።" አለችኝ። ዉይ ሶደሬ ፈተና ጨርሳ ዘና ልትል እንደተገናኘን ትዝ አለኝና "እንዴ ለካ ..." ብዬ ልቀጥል ስል አምሪያ አቋርጣኝ "ለካ አስራሁለተኛ ክፍል ነኝ።" አለች። እኔ ሶደሬ ተገናኝተን ነበር ልል ነበር። እንዴት እንዳወቀች እኔንጃ! ደሞ ለማንም እንዳልናገር አስጠንቅቃኝ ነበር። ወዲያዉ አምሪ እና ወ/ሮ ለይላ ተነስተዉ ወጡ። እነሱ እንደሄዱ ሚኪ ምግቡን አዘገጃጀና ለአራት አጣደፍነዉ።
.
ወደ አመሻሹ አስራ አንድ ሰዓት ሲሆን ፌቪ ደወለችልኝ። ስልኩን አንስቼ ሆስፒታሉ የት እንደሆነ ነገርኳት። ስትደርስ ምልክት አደረገችልኝና ወጥቼ አገኘኋት። ከትምህርት ቤት በቀጥታ ነበር የመጣችዉ ዩኒፎርሟን እንደለበሰች ናት።
ገና አጠገቧ ስደርስ "የኔ ጌታ!" ብላ ተጠመጠመችብኝ።
የሸሚዜን ኮሌታ ይዛ "ሀቢቤ አሁን ማማ እንዴት ናቸዉ?" አለችኝ።
"ደህና ናት ማታ ኦፕራሲዮን ተደርጋ ነበር። አሁን እንደ መንቃት ብላለች።" አልኳት።
ፈገግ ለማለት ሞከረችና ከቦርሳዋ ዉስጥ አንድ እሽግ ብር እያወጣች "ይኸዉ ሀቢቤ ለአንዳንድ ነገር ይሆናቸዋል። ብራዘር ለአንዳንድ ነገር የላከልኝ ነዉ እትጨነቅ።" አለችኝ።
ፈገግ ብዬ ስለ ሀጂ ራህመቶ ተረኩላት። ገንዘቡ ለጊዜዉ ስለማያስፈልገኝ እንደማልቀበላት ነገርኳት። ሲያስፈልገኝ ልቀበላት ቃል አስገብታኝ ተለያየን። ሌላ ጊዜ ቢሆን እንዴት ሰፍ ብዬ ብሩን እንደምቀበላት አስቤ ገረመኝ። ሀዘን ትንሽ ስርዓት ያስይዛል።
.
ማታዉን ሀጂ ራህመቶ መጡ። ትናንት ማታ ስላልተኙ ዛሬ ቤት ሄደዉ እንዲተኙ አስገደድናቸዉ። አብነት እና እኔ አደርን። ሚኪ እና ከሪሜ ወደ ቤት ሄዱ። ትናንት ያሻትን በማድረግ ስትደሰት የነበረችዉ ነብሳችን በሀዘን ተሸምቅቃ አደብ ገዝታለች።...

😘#ይቀጥላል...

😘❥..................🍃🍃...................❥

😘🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳,
😘ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ላይክ አድርጉ
😘♥️የማይፋቅ ስህተት♥️



😘🌹ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌹

😘▬ተከታታይ ልቦለድ▬💢

😘ክፍል አስራ አንድ 1⃣1⃣

...🖍በህይወት ዉስጥ ምንም አይነት መደነቃቀፍ ባይኖር ኖሮ የሰዉ ልጅ አምላክ መሆኑን የሚጠረጥር ይመስለኛል። አንድም ቀን እንደዚህ ይጨንቀኛል ብዬ ገምቼ አላዉቅም። እናቴ ሁሉንም ቀዳዳዎቼን ሸፍና አንደላቃኝ ነበር። ዛሬ ግን እናቴ መተማመኛ እንደማትሆነኝ ሊያሳየኝ ሲፈልግ ንቁዋ እናቴን ድንዝዝ አድርጎ ከአልጋ አጋደማት። አሁን ከእናቴ ዉጪ ዞር ብዬ አይቼዉ የማላዉቀዉን ጌታ እየተማፀንኩት ነዉ። ችግር ሲጨመድደን ትናንት ዞር ብለን ያላየነዉን አምላክ ከመማፀን በቀር ምን አማራጭ አለ? ምንም!
.
ማክሰኞ ጠዋቱን እማዬን ከተኛችበት የሆስፒታል አልጋ ላይ እንደተጋደመች ክፍሉ ዉስጥ ካለዉ የኦክስጅን ሳጥን ጎን ተቀምጬ አያታለሁ። እማዬ ፊቷ ሙሉ ለሙሉ ወደ ቢጫነት ተቀይሯል። ፈጣሪ ግን ምነዉ አለ? ያለአባት በመከራ ያሳደገችኝን እናቴን ለምን ያሰቃይብኛል? ለነገሩ ጉልበተኛ ነኝ አይደል የሚለዉ እንዳሻዉ! ብቻ ዝም ብዬ እናቴን አያታለሁ። ያላደላት ሚስኪን ፍጡር!
አብነት እንቅልፍ በዘጋዉ ጎርናና ድምፅ "ስማ ቁርስ አያመጡልንም እንዴ?" አለ። ማታ አብረን ያደርነዉ እኔናአብነት ነበርን።
ቀና ብዬ የተቀመጠበትን ነጭ ባለስፖንጅ ወንበር የእጅ መደገፊያ እያየሁ "አንተ አስታዉሰኸዉ እነሱ የሚረሱት ይመስልሀል?" አልኩት። አብነት ሳቁን ለቀቀዉና "ኧረ ባክህ? ፈጣሪህን ይህን ያህል ብታምነዉ ወርቅ ከሰማይ ያዘንብልህ ነበር።" አለኝ።
ዉስጤ ላይ ብሶቴ እየተቀጣጠለ "ባክህ እሱ መከራ ያዝንብ ተወዉ!" አልኩ።
እኔና አብነት እየተጨዋወትን ብዙም ሳንቆይ አምሪያ የክፍሉን በር ከፍታ ገባች። በእጇ ሰማያዊ ዘንቢል አንጠልጥላለች። አብነትን ዞር ብዬ አየሁትና ሳቅኩ።
አምሪያ በሩን ዘግታ ወደኛ እየዞረች "ምን ያስቅሀል? ለነገሩ ሲጀማምር እንደዚህ እኮ ነዉ።" አለች።
አብነት ወዲያዉ ዘንቢሉን ተቀብሎ ምግቡን ማቀራረብ ጀመረ። እንደሆዱ የሚያፈቅረዉ ነገር ያለ አይመስለኝም።
አምሪያ ከእማዬ አጠገብ ያለዉ ወንበር ላይ እየተቀመጠች "ሀቢቤ አሁንም ምግብ መዉሰድ አልጀመሩም?" አለችኝ። "አዎ ባክሽ ግልኮስ ነዉ የያዛት! ምንም አላማረኝም።" አልኳት። እማዬ በሲቃ በታጀበ ድምፅ "ተዉ ሀቢቤ እንደሱ አይባልም። ፈጣሪ አለ።" አለችኝ። እማዬ መናገር ተራራ ከመግፋት እየከበዳት መጥቷል። እንደዉም ዛሬ ትንሽ አነጋገሯም ተስተካክሏል። አይ እማዬ ፈጣሪ አለ ነዉ ያለችዉ? ፈጣሪማ ለማሰቃየት ሲሆን መች ይጠፋል!? አብነት ምግቡን አቀራርቦ ሲጨርስ አምሪያን "ባለአጥሯ ነይ እንብላ!" አላት። ሳቅኩኝና ወደ አብነት ተጠጋሁ። አምሪን በአንገቴ ነይ ስላት ወንበሯን ይዛ ከኛ ጋር ተቀመጠች። አብነት ገና እጁን ወደ ምግቡ ሲሰነዝር አምሪያ "ወይኔ ስጋ ነዉ እንደዛኛዉ ልጅ ነህ አይደብርህም አይደል?" አለች። እንደዛኛዉ ልጅ ያለችዉ ሚኪያስን ነዉ። አብነት የጠቀለለዉን እየጎረሰ "በፈጣሪ ስም ነዉ የታረደዉ አይደል እንዴ? በእግዚአብሔር ይሁን በአላህ እነሱ ይስማሙበት። የኔ ሀላፊነት መብላት ነዉ።" አለ። እኛ አንድም ቀን የሙስሊም የክርስቲያን ስጋ ብለን ለይተን በልተን አናዉቅም። ያገኘነዉን ማተራመስ ነዉ።
አምሪያ የአብነት ንግግር ስቅጥጥ እያላት "አይ እምነት እንኳ እንዲህ ድንበር የሚታለፍበት ጉዳይ አይደለም። ማንነትህን በደንብ የምትረዳዉ ስታከብረዉ ነዉ።" አለች።
አየር ስለያዙብኝ እየበሸቅኩ "ይቅርታ እንብላበት!" አልኩ።
"እሺ እጃችሁን አትታጠቡም? ከመድሀኒት ጋር አድራችሁ?" አለች።
"አምሪ ኧረ ምንም አንሆንም ይኸዉ ሀያ አመት ሊሞላኝ ነዉ አንድም ቀን ታጥቤ አላዉቅም። ምን ሆንኩ?" አልኳት።
ካልታጠባችሁ አልበላም ብላ ስታሸማቀን ተነስተን ታጠብንና መብላት ጀመርን።
አብነት የአምሪያን ፊት የሚያክል ጉርሻ ጠቅልሎ ላጉርስሽ ሲላት ከአይኗ እንባ እስከሚፈስ ድረስ ሳቀች። በመሀል እማዬ እያየችን ፈገግ ስትል አየኋት። ወደሷ ስዞር "ሀቢቤ ለሴት ልጅ የሚሆን ጉርሻ በመጠኑ አጉርሳት!" አለችኝ።
እማዬ ብላኝ እንቢ ብዬ አላዉቅም። አጎረስኳት። አምሪ መጉረስ አልፈለገችም ነበር ግን እማዬን ላለማስከፋት ብላ ጎርሳልኝ ፈገግ አለች።
.
አምሪያ ከሄደች በኋላ የክፍል ተማሪዎች እየተንጋጉ ሆስፒታሉን ወረሩት። የኢምባሲ በር ጋር ተቃዉሞ የወጡ እንጂ በሽተኛ ሊጠይቁ የመጡ አይመስሉም። እየመሯቸዉ የመጡት ሚኪያስናከሪሜ ናቸዉ። አምስት አምስት እየሆኑ እየገቡ እናቴን አይተዋት ወጡ። እኔም እናቴም በጣም ደስ ብሎናል። ሆስፒታሉ ዉስጥ ግርግር ላለመፍጠር ብለን ግቢዉ ዉስጥ ወርደን ማዉራት ጀመርን። ሀብታሙ እንባ እየተናነቀዉ "ሀቢቤ አብሽር እሺ ለፈተና እንዳታስብ እኔ አለሁልህ።" አለኝ። ሀብታሙ እና እኔ እኮ በወጉ እንኳ ክፍል ወስጥ አዉርተን አናዉቅም። ብቻ ሀበሻ በችግር ሰዓት መልዓክ ካልሆንኩ የሚል ሚስኪን ፍጡር ይመስለኛል። ፈገግ ብዬ አየሁት። ሴቶቹ በየተራ ምግብ ካላመላለስን አሉ። እኔ ግን ምንም የምግብ ችግር ስለሌለ እንዳይለፉ ነገርኳቸዉ። ብቻ ብቅ እያሉ እንደሚጠይቁ ነግረዉን ነገ ለፈተና እንዳላረፍድ አስጠንቅቀዉኝ ሄዱ። ሰብስበዉ የሰጡኝን ብር ደስ እንዲላቸዉ ብዬ ተቀብያቸዋለሁ።
.
ማታዉን ወ/ሮ ለይላ መጥተዉ እማዬን በደንብ ፈታ አደረጓት። ሀጂ ቀጣዩን ሶስት ቀን ፈተና መሆኔን ስለተረዱ ለሊት ስድስት ሰዓት ድረስ እየተኙ የቀረዉን ለሊት አምሪያን ሆስፒታል አድርሰዉ እኛን ወደቤት መልሰዉን ከአምሪያ ጋር እማዬን ሲጠብቁ ለማደር አሰቡና አማከሩን። ምንም ቢከብደንም አማራጭ ስላልነበረን ተቀበልነዉ። ፈተናዉ ተጀመረ። የረቡዕ እለትን ሙሉ ፈተና የሰራልኝ ሀብታሙ ነበር። ትምህርት ብቻ ሳይሆን ማስኮረጅም አንደኛ ነዉ። ሀሙስ ጠዋት ወደ ፈተና ልገባ ስል ሁለት ሀይማኖተኛ ሀይማኖተኛ የሚሰራራቸዉ የግቢያችን ልጆች አገኙኝና "ሀቢብ አሁንስ የትም ብትዘል የማታመልጠዉ አምላክ መኖሩ ገባህ?" አሉኝ። ሸምድደዉት የመጡ እስከሚመስለኝ ድረስ ሁለቱም ደጋገሙልኝ። ዉስጤ በጣም ቆስሏል። ሌላ ጊዜ ቢሆን አንስቼ አፈርጣቸዉ ነበር። አሁን ግን ቅስሜ ስብር ስላለ ትቻቸዉ ሄድኩ። ምን ራሳቸዉን የፈጣሪ መልአክተኛ ያስመስላሉ? የሆኑ አመዳሞች።...

😘#ይቀጥላል...

😘❥..................🍃🍃...................❥

😘🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ
😘ክፍል አስራ ሁለት ከ15❤️ ቡኋላ ይቀጥላል
ጁንታ ማለት ምን ማለት ነው🤔 ‼️

ብዙ ሠዎች ለመሆኑ ጁንታ ምን ማለት ነው? የሚል ጥያቄ ሲጠይቁ አስተውያለሁ። የዚህ ቃል ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል።

ጁንታ ቀጥታ ከእንግሊዘኛ የተወሰደ ቃል 'Junta' ሲሆን፤ ያለ ሰፊ ሕዝባዊ ድጋፍ ጥቂት ግለሰቦች የሥልጣን ጥማቸውን ለማርካት ሲሉ ነባሩን ሕገመንግስት በመጣስ፣ በወታደራዊ ኃይል መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሲንቀሳቀስ ያ ቡድን ጁንታ ይባላል።

ቃሉ በተለይም በአብዮት ዘመን በስፋት ጥቅም ላይ ሲውል ነበር።

#SHARE #FORWARD

♻️ ሀሳብ እና ጥያቄ ካላችሁ 👇 ከታች Comment ላይ አስቀምጡልኝ 😁

@jaden_36
በድጋሚ የቀረበ


​​​😍😍የምፈልጋትን ሴት እንዴት በ telgram ወይም በ facebook chat በማረግ የራሴ ማረግ እችላለሁ???😍😍
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹 ❤️🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄

የመጀመሪያ ቀን Chat ላይ ሴቶች እየቆዩ ይመልሳሉ አደል? በተጨማሪም አጫጭር መልሶች ነው የሚመልሱት ዎናው ነገር ያንተ ትግስት ነው የምትፈልጋትን ሴት በ chat ብቻ ትኩረትዎን መሳብ ቀላል ነው፡፡
4ነገሮችን ሁን መጀመሪያ::
1,አትቸኩል
2,እንደ ጉዎደኛ እንጂ ምንም አይነት ጅንጀና አትጠቀም
3,ለሴት ልጅ ያለህን ክብር አሳይ
4,አስተሳሰብህ የረቀቀ ይሁን
ለምሳሌ ከላይ ያሉትን በዝርዝር እንመልከት
♨️ አትቸኩል ይላል የመጀመሪያው ይሄም ማለት ወደድኩሽ የኔ ማር የኔ ፍቅር ከማለት ተቆጠብ ለሁሉም ጊዜ እና ሰአት አለው፡፡
2ተኛው ምንም አይነት ጅንጀና አትጠቀም የሚለው በጣም አሪፍ ነው Hey ብለህ ጀመርክ hey አለችህ አንተም selam nw በል hi fkr hey mar እያልክ አጀምር ምክንያቱም ኩራት + ይሰማታል እና፡፡ በመቀጠልም alen ወይም fine ስትልህ እኔም አለሁ አግዚያብሄር ይመስገን ወይም አላሀምዱ ሊሊህ በላት ይህም ማለት የመጀመሪያ አንድ ወሳኝ ነገር አሳየሀት ማለት ነው እሱም ጀንጃኝ እንዳልሆንክና በፈጣሪህ እንደምትገዛ አስብ እ/ይመስገን እኔም አለሁ ነው ያልካተት ስለዚህ አሁን ካልተመቸሀት እርግጠኛ ነኝ አይታ ዝም ነው ምትለው ነገር ግን amen ወይም እና ምን አዲስ ወይም nurilgn ካለች 2ኛ ያልኩህ አለቀ ማለት ነው፡፡
♨️3ተኛ ላይ ለሴት ልጅ ያለህን ክብር አሳይ ስል ምን ማለቴ መሠለህ ሁሌም አንድ አይነት ንግግር አስለምዳት በተጨማሪም ስለ ሴት ልዮ ስለመሆንዎ ንገራት ሴት ልጅ ከምንም በላይ መሆንዎን ንገራት ለምሳሌ mar enay eko betam nw makbrsh berget set selhonsh becha adelm makbrsh weym ente miste eht hunsh y medr hiwoten selmumoye sayhon set kemhonsh befit sew selhonsh nw በላት አየህ እዚጋ ደግሞ ባስተሳሰብህ ትማረካለች ለሰው ያለው ክብር ኡፋፋፋፋ ደስ ሲል እኮ እያለች ታወራልሀለች ስለዚህ ቀጣዮ ስራህ ምክሮችን መለገስ ነው ለምሳሌ ከተሳደበች ወይም ስድብ ያለበት ወሬ ካወራች ማር መሳደብ እኮ ትንሽነት ነው ቢሰድቡሽም አትስደቢያቸው የሰው ልጅ እንስሳ ብትይው ይናደዳል ይበሳጫል አንበሳ ብትይው ግን ደስ ይለዎል አየሽ ሁለቱም አንድ መሆናቸውን አልተረዳም ማለት ስለዚህ ከማይረዱት ወገን አትሁኚ ስድብ ለሰው መጥፎ ማሠብ ትንሽነት ነው plz ለኔ ስትይ አቁሚ አንቺ ላይ አያምርም አንቺ ልዮ ሴት ነሽ በላት፡፡ ስለዚህ አስተሳሰብህ የረቀቀ ይሁን ያልኩህንም ያጠቃልላል፡፡ በፍፁም ስልክ ቁጥር እንዳጠይቅ እንገናኝም እንዳትል እሷ ወዳንተ ለማጥመድ ሞክር እንጂ አንተ እንዳትጠመድ፡፡ አንዳንድ አገረጣሚወችንም ተጠቀም ለምሳሌ ጨረቃ ሙሉ በምትሆን ሰአት semima eski wede wech wechi kechalsh ena chrkwan temlkchat atamrm? ስለማላቅሽ ልሰጥሽ የምችለው ስጦታ እሷ ናት ፍፁም አትበላሽብሽም ወድቃም አትሰበርም ደግሞ ልክ እንዳንቺ ውብ ሁናለች በላት ከዛ ደግሞ የሙገሳ ቃላት መጠቀም አቁም እና ቁም ነገረኛ ሁን ያኔ ባህሪህ ሲቀያየር አንተን ማሠብ ትጀምራለች ባቶድህ ለራሱ፡፡ ቀልድ አታብዛ መናገር ብቻ ሳይሆንም ማዳመጥ እንደምችል አሳያት፡፡ ባጭሩ ያልሆንከውን ሁነህ ቅረባት መፅሀፍ ማንበብ እንደምቶድ ንገራት፡፡ እንደ ጉዎደኛ 3ወር ከቆየህ በየቀኑ እየተፃፃፍክ የምቶዳት ከሆነ በ 3ተኛ ወር ንገራት እርግጠኛን ከተገበርካቸው ይሳካልሀል፡፡ ከ 100% 92% ይሳካለታል፡፡ እንደምቶዳት ንገራት ስል ታዲያ ግልፅ በሆነ መልኩ አይደለም ልክ ካንጂ ጋ ሳወራ ደስታ ይሰማኛል የማለውቀው ስሜት ይሰማኛል ምናምን ተትላለህ ከዛ የሱዎን መልሶች እያመዛዘንክ መቀጠል ነው፡፡



🌝አንብቦ ማለፍ ትንሽነት ነው #SHARE ይደረግ።

••●◉Join us share

T.me/pclovee
😘​​♥️የማይፋቅ ስህተት♥️


😘💢ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ💢

😘🔰ተከታታይ ልቦለድ🔰

ክፍል_12

...🖍እማዬ ከሆስፒታል መዉጣት የነበረባት እነሚኪ በነገሩኝ መሰረት ከሆነ ማክሰኞ ወይም ረቡዕ ነበር። ግን ምግብ ስለማትወስድ ትንሽ ትቆይ ብለዉ እስከአሁን አልወጣችም። ፌቪዬ በቀን ከአስሬ በላይ የምትደዉልበት ጊዜ ሁሉ አለ። እማዬን ለማሳየት ምቹ ጊዜ አላገኘሁላትም እንጂ አስጎበኛት ነበር። ወይ እንደክፍል ልጆች ሰብሰብ ብለዉ ቢመጡ ያመች ነበር። ለነገሩ ነግሬያት ቅዳሜ ትምህርት ቀርተዉ ከጓደኞቿ ጋር እንደሚመጡ ነግራኛለች። የግል ስለምትማር ቅዳሜም ቀኑን ሙሉ ትምህርት አላቸዉ።
ቀኑ እየቆጠረ ሄዶ አርብ ደረሰና ፈተና ጨረስን። እኔ እኮ ባልማርም ግድ የለኝም። የምማረዉ እማዬን ደስ እንዲላት ብዬ ነዉ።
.
አርብ ከፈተና መልስ አራታችንም ተሰብስበን ወደ ሆስፒታል ሄድን። ልክ ስንደርስ እናቴ የተኛችበት አልጋ አጠገብ ዶክተሯ እና አምሪያ አብረዉ ቆመዋል። ነርሷ በተቃራኒ አቅጣጫ በኩል ቆማ ዶክተሯ የምትነግራትን ትመዘግባለች። እንደገባን ዶ/ር ቀመሪያ ፈገግ እያለች "ሄይ ሀቢብ" አለች። እየሳቅኩ "እሺ ዶ/ር አለሽ ግን?" አልኳት።
"አለሁ ባክህ አንተ መች ትገኝና ነዉ ሰሞኑን ኤግዛም ቢዚ አድርጎሀል አሉ።" አለችኝ። ስታወራኝ የታካሚዋ ልጅ ሳልሆን ጓደኛዋ ነዉ የምመስለዉ።
እማዬን አይታ ስትጨርስ "ሀጂ መች ነዉ ሚመጡት?" አለችኝ።
አምሪያ "ከፈለግሽዉ አ
ሁን እደዉልለታለሁ።" አለቻት። ሀጂን አንተ ስትላቸዉ ልደነግጥ አልኩና ትዝ ሲለኝ ለካ አባቷ ናቸዉ።
ዶ/ር ቀመሪያ ስልኳን አየችና "አሁን ኦሬዲ ኢትስ ኤይት በቃ ቴን ሰርቲ ላይ ቢሮ ይምጡ!" አለች።
ምናልባት ከክፍያ ጋር የተያያዘ ከሆነ ስምንትሺህ ብሩን ሀጂ አልቀበልም ስላሉን እግረመንገዴን ለመክፈል በማሰብ "ምነዉ ግዴታ እሳቸዉ የሚያስፈልጉበት ነዉ? እኔ መምጣት አልችልም?" አልኳት።
ከነርሷ ጋር ሆነዉ ከክፍሉ እየወጡ "ኖ እሳቸዉን ፐርፐዝሊ ስለፈለግኳቸዉ ነዉ።" አለች።
አምሪ ለሀጂ ደዉላ ነገረቻቸዉ። አስር ከሩብ አካባቢ መጡ።
ከሪሜ ዛሬ አብሮኝ ስለሚያድር ቤት ልብስ ቀይሮ ሊመጣ ሄደ።
ሀጂ ዶክተሯ ቢሮ ቆይተዉ ከመጡ በኋላ ፈገግ ብለዉ "ኢንሻአላህ ነገ ወደ ቤት እንወስዳቸዋለን።" አሉኝ። ደስ አለኝ። ቢያንስ የእነ ሀጂ እንግልት ይቀንሳል። ለእማዬም ቤት መሆኗ ይሻላታል። ቢያንስ እንደተሻላት ይሰማታል።
.
በነጋታዉ ጠዋቱን ከከሪሜና አብነት ጋር ተቀምጠን እያወራን ፌቪ ሶደሬ አብረን ከሄድናቸዉ ጓደኞቿ ጋር ሆና መጣች። ገብተዉ እናቴን ጠይቀዋት እንደወጣን ጓደኞቿ ቀደም ብለዉን ሲሄዱ ፌቪ ጥምጥም አለችብኝና ከንፈሬን ሳመችኝ። እኔ እንኳ ለእንደዚህ አይነት ነገር ያለኝ ስሜት ወርዷል። ግን እንዳይደብራት በሚል በወጉ አስተናገድኳት። ሆስፒታል ዉስጥ የተሳሳሙ ብቸኛ እብዶች ሳንሆን አንቀርም።
አይን አይኔን እያየች "ሀቢቤ ሁሉም ይስተካከላል አይዞን እሺ!" አለችኝ።
.
እነፌቪ ሄደዉ ትንሽ እንደቆየን ሀጂ እና ወ/ሮ ለይላ መጡ። ዶ/ር እስከምትገባ ትንሽ ጠበቅንና ያለዉን ነገር ጨራርሰን እማዬን ወደቤት ይዘናት ሄድን። እማዬ ዉሀ ነገር ካለዉ ከረጢት በመርፌ ወደ ሰዉነቷ እንደተሰካላት ነዉ። ዶ/ር ቀመሪያ አየችኝና "ሀቢቤ ችግር ካለ ደዉልልኝ" ብላ ስልኳን ሰጠችኝ።
እማዬን ወደቤት እየወሰድናት ሚኪ ደወለልኝ። "ሀቢቤ እናትህ ይሻላቸዉ እንጂ ሀብታም ሆነናል።" አለኝ። ያዉ የፈረደበት ከአረብ ሀገር ሴቶች የተነጨ ብር ተገኝቶ ነዉ። በልቤ "እማ ይሻላት እንጂማ የኔዎቹንም አልባቸዋለሁ" አልኩ።
እነሀጂ እንዳይገባቸዉ እየተጠነቀቅኩ "ቆይ ስንት ታዝኖ ነዉ?" አልኩት።
"በኔ በኩል አምስት ሺ በከሪሜ ደሞ ሰባት ሺህ!" አለኝ። ተሰናብቼዉ ስልኩን ዘጋሁት።
ይሄ ቢዝነስ እያጓጓኝ ነዉ። ቆይ ብቻ እማዬ ይሻላት። ቤት ስንደርስ አምሪ ቤታችንን ፏ አድርጋዉ እየጠበቀችን ነበር። ፈጣሪ መልዓክ ማዉረድ አይጠበቅበትም እኮ! የሰዉ መልአክ ምድር ላይ አለ። ደስ ሲሉ የሚያስቀና ቤተሰብ!...

#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃😘...................❥

😘🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳


ከ15❤️ ቡኋላ ክፍል አስራ ሶስት ይለቀቃል
😘💢የማይፋቅ ስህተት💢


😘💯ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ💯

😘🔰▬ተከታታይ ልቦለድ▬🔰

😘ክፍል_13

...🖍እማዬን ከሆስፒታል አዉጥተን ቤት እንዳስተኛናት ሌሎች ጎረቤቶቻችንም እየተመላለሱ መጠየቅ ጀመሩ። ሆስፒታልም መጥተዉ ጠይቀዋል። እኔ ግን ሲጠይቋት አልነበርኩም። ሲጀመርም አባቴ ከሞተ በኋላ ብዙም ከጎረቤቶቻችን ጋር አንቀራረብም። አጥራቸዉን አስረዝመዉ ከመኖር በዘለለ ጉርብትናን በቅጡ የሚረዱ አይደሉም። እድሜ ለነሀጂ እማዬም ቆንጆ ዘመድ አገኘች። እማዬ ቅዳሜ ከሆስፒታል ከወጣች ይኸዉ ዛሬ ማክሰኞ አራተኛዋ ቀን ሆነ።
.
አምሪያ ሰሞኑን ከኛ ቤት አትጠፋም። ቤቱን ማፅዳት እና ለእማዬ የሚያስፈልጋትን ነገር ማቀራረብ የዘወትር ስራዋ ሆኗል። ዛሬ እንዲህ መድሀኒቴ ልትሆን ነገር ትናንት ለአምሪያ እንጨት እየተማረርኩ የፈለጥኩበት ጊዜ አበሳጨኝ።
ዛሬም መኝታ ክፍል እማዬ ከተኛችበት አልጋ ጎን ተቀምጣለች። ሰማያዊ ሂጃብ ጠምጥማለች። ፈገግታዋ ደስ ይላል። ቀኝ እግሯን ግራ እግሯ ላይ ሰቅላዋለች።
"ሀቢቤ!" አለችኝ። ድምጿ ደስ ይላል።
"ወዬ?" አልኳት። እማዬ እስከአሁን ምግብ በደንብ መብላት ስላልቻለች ከጭንቀቴ የተነሳ ድምፄ ርቆኛል።
አምሪያ ትክ ብላ እያየችኝ "ልብስህን ከቀየርከዉ ቆየህ እንዴ? ቆሽሿል እኮ!" አለችኝ።
"አዎ ባክሽ ደሞ ሸሚዞቼ እንዳለ ቆሽሸዋል።" አልኳት።
ከመቀመጫዋ ብድግ እያለች "በቃ ስጠኝ ልጠባቸዉ!" አለችኝ። "ኧረ አምሪ አይነፋም! ሹራብ ነገር እለብሳለሁ ተይዉ።" አልኳት። ዉለታዋ ሲበዛ ከብዶኛል። ልታዳምጠኝ ፈቃደኛ አልሆነችም። "ባክህ አታካብድ ብዙ አይደለም እኮ!" አለችና ቆሻሻ ልብሶቼን አልጋዉ አጠገብ ያለዉን ቁምሳጥን እየከፈተች መፈለግ ጀመረች።
"በቃ እሺ እዛ ዉስጥ ነዉ።" አልኳት የኔ ልብስ ወዳለበት እጄን እየጠቆምኳት።
ልብሶቹን እያወጣች ቁምሳጥኑ ጥግ ላይ የተቀመጡትን ፎቶዎች አነሳችና "እነዚህ ደሞ እነማን ናቸዉ?" አለችኝ። ቀና ብዬ ሳይ ፎቶዎቹ የሰላም፣ የሜሮን ፣ የሰሚራ እና የፌቨን ነበሩ። ምላሴ እየተሳሰረ "የትምሮ ቤት ልጆች ናቸዉ።" አልኳት። ቆይ ምን አስደነገጠኝ? አምሪን ለምን ፈራኋት?
የሰላምን ፎቶ እያሳየችኝ "ስንት ትምህርት ቤት ነዉ የተማርከዉ? ማለቴ የዚች ልጅ ዩኒፎርምና ያንተ ዩኒፎርም ይለያያል።" አለችኝ።
የፈጣሪ ያለህ በጣም አስጨነቀችኝ። ዝም ስላት ልብሶቹን ይዛ ለማጠብ ወጣች። አምሪ እንደወጣች እማዬ በደከመ ድምፅ "ሌላ እናት አገኘህ አይደል?" አለችኝ። አምሪያን ማለቷ ነዉ። ፈገግ ብዬ ዝም አልኳት።
.
እማዬ አምሪያ ወጥታ ትንሽ እንደቆየች በደከመ ድምፅ ሀጂን እንድጠራላት ጠየቀችኝ። ስራ ስለሆኑ ማታ ቢመጡ እንደሚሻል ብነግራትም አሁን ካልሆነ ብላ ተቆጣች። ከመኝታ ክፍል ወጥቼ ለአምሪያ ነገርኳት። ግቢ ዉስጥ ልብሶቼን እያለቀለቀች ነበር። በረንዳዉ ላይ የተቀመጠዉን ስልኳን እያሳየችኝ "አቢ የሚል ፈልግና ደዉለህ አገናኘኝ።" አለችኝ። አባቷን አቢ ነዉ የምትላቸዉ። ደወልኩና ሲጠራ ጆሮዋ ጋር አስጠግቼ ያዝኩላት። እጇ አረፋ ስለነበር ስልኩን እንዳይነካዉ መሆኑ ነዉ። ስልኩን ይዤላት ስታወራ በትኩረት አያታለሁ። ደስ ስትል። አለ አይደል የሆነ እርጋታዋ፣ የአይኖቿ እንቅስቃሴ ፣ ፈገግታዋ የሆነ ያዝ ሲያደርገኝ ተሰማኝ። ምን እየሆንኩ ነዉ? አምሪያ "አንተ እብድ ልጠብበት አታዝገኝ።" አለችኝ። ለካ እሷ አዉርታ ጨርሳለች። እኔ ስልኩን ጆሮዋ ላይ ለጥፌ ይዤ ፈዝዣለሁ። ደነገጥኩና ስልኩን ከጆሮዋ ላይ እያነሳሁ "እና ምን አሉ?" አልኳት።
"አሁን ይመጣል። የሚገርምህ ደሞ ለምሳ እየመጣ ነበር።" አለችኝ።
ላግዛት መዘፍዘፊያዉን ወደራሴ ስስበዉ "በአላህ አታዝግ ሂድና ማዘርን አጫዉታቸዉ።" አለችኝ። ለምን እንደሆነ ባላዉቅም አጠገቧ መቀመጥ ፈልጌያለሁ። "ስማ ሂድ! ማዘርን አታስደብራቸዉ!" ብላ ስትኮሳተር ተነስቼ ወደ እማዬ ክፍል ሄድኩ።
ወደ እማዬ ክፍል ስገባ በር ተንኳኳ። አምሪ እጇ ላይ ዉሀ አፍስሳ ልትከፍት ስትሄድ የመስኮቱን መጋረጃ ገልጬ አያታለሁ። ከፈተችዉ። እነሚኪ ነበሩ። ሶስቱም እንደሀብታም ልጅ የመዓት ኮተት ምናምን በፌስታል ይዘዉ ገቡ። አብነት አምሪያ ላይ ዉሀ ረጭቶባት አለፈ። አናደደኝ። ለምን ተናደድኩ? "ኧረ ሀቢቤ ተረጋጋ ሲቀልድ እኮ ነዉ!" አልኩት ለራሴ...

#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃😘...................❥

😘🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳


😘••●◉Join us share◉●••
ክፍል 14 ከ15❤️ ቡኋላ ይለቀቃል
😘የሠርግ ማታ ባል ለሚስቱ የሰጠው ምክር💜

የኔ ፍቅር ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለኔ የመኖር ትርጉሜ ነሽ
በእኔ እና ባንቺ መሃል ከእንግዲህ ምንም አይነት ድብብቆሽ ሊኖር አይገባም።

የኔ ውድ በፊት እኔ ትልቅ ልጅ ነበርኩ አሁን ግን በድጋሚ ህፃን እሆናለሁ፣
ትዝ ይለኛል ህፃን እያለሁ ምግብ ባልቼ እንደሆነ ወይንም እርቦኝ እንደሆነ የምታውቃኝ እናቴ ነበራች
ጥዋት ከእንቅልፍ የምትቀሰቅሰኝ እናቴ ነበራች
ከቤት ከመውጣቴ በፊት መስተካከል ያለበትን ነገሮች አስተከክለ የምትሸናኝ እናቴ ነበራች

ከእንግዲህ ግን እናቴ አንቺ ነሽ
ከእንግዲህ የኔን ደካመ ጎን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም
ከእንግዲህ ጥማቴን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም
አየሽ ፍቅር ልጅ እያለሁ የሆንኩትን ነገር ሁሉ ለእናቴ ነበረ መጥቼ የምናግራት እሷም ምስጢሬን ለማንም ነግረ አታውቅም
አሁን ግን እናቴ አንቺ ነሽ ምስጢሬን የምናግርሽ ላንቺ ብቻ ነው
ለማንም ምስጢሬን አሰልፈሽ አትስጪ

ልጅ እያለሁ ብዙ ጥፍቶችን አጠፍ ነበረ እናቴም ለጊዜው በጣም ትቆጠኝ ነበረ ግን ቁጣወ ብዙም አይቆይም ወዲያውኑ ተመልሳ መሳቅ ትጀምራለች
የኔ ፍቅር ምናልባት አንቺንም ሊያስከፍሽ እችላለሁ እባክሽን ግን ቅም አትያዥብኝ ጥፍቴን ግን አይታሽ ዝም አትበይ ምክር ስጪኝ እቀበላለሁ

የኔ ማር ወደ ጣፋጭ የአልጋ ጨዋታ ከመሄደችን በፊት ደግሜ የምናግርሽ ነገር ለሰዎች ወሬ በፍጹም ጆሮ አትስጪ
ከእንግዲህ ወዲህ ላንቺ ከእኔ የሚቀርብ ማንም ሊኖር አይችልም መኖር የለበትም።

የኔ ፍቅር የብዙ ሰዎች ትዳር መፍረስ ምክንያት ጎሮቤት አልያም የጓደኛ ብዛት ነው ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ከልክ በላይ አታቅርብ

በፈጣሪ ፊት ቃል እገባለሁ እኔም ምርጡ አባትሽ ሁለም ከጎንሽ መቆም የምችል ከማንም አስቀድሜ ለልጄ ለሚስቴ የሚል መልካም ባል እሆንልሻለሁ!!

የባል ምክር የተመቸው ሼር ያድርግ😂🙈

ፍክት ያለ ምርጥ ቀን ተመኘውላቹ😘🙏
@pclovee
@pclovee
😘✿የማይፋቅ ስህተት✿

😘♥️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘🔰▬ተከታታይ ልቦለድ▬🔰

😘ክፍል_14

...🖍ቤት እንደገቡ የያዙትን ኮተት ሳሎን አስገብተዉ ቤቱን ፏ ማድረግ ጀመሩ። ሀቢብ ብለዉ እንኳ አልተጣሩም። ድፍረታቸዉ አንደኛ ደረጃ ነዉ። ከመኝታ ቤት ወጥቼ ወደ ሳሎን ገባሁ። የጁስ መዓት ብስኩቶች ቸኮሌት እና ምግብ ለመስራት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ሳይቀር ይዘዉ መጥተዋል።
"አራስ ምትጠይቁ መሰላችሁ እንዴ ብስኩት፣ ቸኮሌት ምናምን? ላደጉት ልጆች ነዉ?" አልኳቸዉ።
ሚኪ ፈገግ ብሎ እያቀፈኝ "የሸመጠጥካቸዉ ልጆችህ አያታቸዉን ሊጠይቁ ከመጡ ብለን እኮ ነዉ።" አለኝ። እኔ እኮ የሚገርመኝ የሚኪ መልስ ነዉ። ምላሱ ጫፍ ላይ ተቀባብላ የተቀመጠች ነዉ የሚመስለዉ።
ትንሽ እንደቆየን አምሪ ልብሶቹን አጥባ ጨርሳ ወደ ቤት መጣች። ካመጡት ቸኮሌት ትልቁን አንስቼ ሰጠኋት። ተቀብላኝ ወደ መኝታ ክፍል ሄደች። ከኔ ጋር ሲሆን ነዉ እንጂ ወንድ ሲበዛ አብራ መቀመጥ አትወድም።
የቤቱ በር ሲንኳኳ ልከፍት ወጣሁ። ሀጂ ነበሩ። ሰላም ብለዉኝ ወደቤት ገባን። ሀጂ እነሚኪ እንዲህ ተሰብስበዉ ቤቱን ሲያደምቁት ሲያዩ ደስ አላቸዉ። አብረን ወደ መኝታ ክፍል ገባን። እማዬ ሀጂን ስታያቸዉ ፈገግ እንደማለት አለችና "አምሪ እና ሀቢቤ አንዴ ዉጪ ቆዩ!" አለችን። እኔና አምሪ ተያይተን ፈገግ አልንና ወደ ሳሎን ሄድን። እነሚኪ ያመጡትን ኩኪስ ብስኩት ምናምን ፈትተዉ እያመቻቹ ነዉ። አምሪ ወከባ መፍጠራቸዉ ገርሟት "ማን ሊመጣ ነዉ?" አለችኝ።
አብነት ከሪምን እያየ "ዛሬ ልደቱ ነዉ።" ብሎ ሳቀና "ስቀልድ ነዉ የትምሮ ቤት ልጆች ሊጠይቁ ሊመጡ ነዉ። ለዛ ነዉ የምንሯሯጠዉ!" አላት። አምሪ ፈገግ አለችና "ኦኬ ፎቶዉ ላይ ያሉት ልጆች?" አለች። ነገር ትበላለች። ሳቅኩና ፈገግ ብዬ "ኧረ በቃ አምሪ ፍቺ!" አልኳት።
.
ሀጂ ራህመቶ ከእማዬ ጋር አዉርተዉ ጨረሱ መሰለኝ ጠሩኝ። እኔን መኝታ ክፍል አስገብተዉ በሩን ዘጉት። እማዬ አየችኝና እያቃሰተች "ሀቢቤ ዛሬ በደንብ አዳምጠኝ!" አለችኝ። ዝም ብዬ አያታለሁ። ቀጠለች "ሀቢቤ እኔ አዝዤህ አንድም ቀን እንቢ ብለኸኝ አታዉቅም። እንዳከበርከኝ አላህ ክብር ያድርግህ። አሁን ግን እኔ ባልኖር ሀጂ እንደ አባትህ ናቸዉ። እኔን እንደምትታዘዘዉ ታዘዛቸዉ። ገደል ግባ ቢሉህ እንኳ እሺ በል። ያኔ እኔ እደሰታለሁ።" አለችኝ። ንግግሯ የስንብት ይመስላል። እንባ ከአይኖቼ ያለማቋረጥ ፈሰሰ። መንሰቅሰቅ ጀመርኩ። ሀጂ አቅፈዉ አባበሉኝ። ስረጋጋ የእማዬን እጅ ጭምቅ አድርጌ ይዤ "እማዬ አንቺ አዘሽኝ የማልቀበለዉ የለም።" አልኳት። እማዬ ፈገግ አለች። ፈገግታ ደስታ ነዉ? ፈገግታ ምንድነዉ? ፈገግታ ስንብት ይሆን እንዴ? ጨነቀኝ። ከመኝታ ቤት እንደወጣን ሀጂ ፈገግ ብለዉ ከቀረበዉ ላይ አንድ ብስኩት አንስተዉ እየበሉ ከቤት ወጡ። ልክ ሀጂ እንደወጡ አብነት እየተገረመ "ባለአጥሯ ግን አባትሽ ሙድ አላቸዉ።" አለ። ባለአጥሯ የሚላት አምሪያ ጥርሷ በሽቦ ስለታጠረ ነዉ።
ሀጂ ወጥተዉ ትንሽ እንደቆየን ፌቪ ከጓደኞቿ ጋር ሆና መጣች። መኝታ ቤት ገብተዉ እማዬን ጠይቀዋት ሳሎን ተቀመጡ። ለካ ሚኪ የትምሮ ቤት ልጆች ያለዉ ላለማስጠቆር ብሎ ነዉ። አምሪ ፌቨንን አየቻትና "ፎቶ ላይ ያየኋት ናት አይደል?" አለችኝ። ፈገግ ብዬ "አዎ" አልኳት። እኛን ሳሎን ትታን ወደ መኝታ ክፍል ገባች። ፌቪ ልክ አምሪያ ስትወጣ
መጥታ አቀፈችኝና ተቀመጠች። ተርባኝ የነበር ይመስላል። እኔ ግን ብዙም ትዝ አላለችኝም።
.
በነጋታዉ እሮብ እማዬ ድክም አለች። አስሬ መጣራት ጀመረች። መጨረሻ ላይ ድምጿም እየጠፋ መጣ። እኔናአምሪ ከአጠገቧ አንጠፋም። ዛሬ ወ/ሮ ለይላም አብረዉን ናቸዉ። እማዬ ደክማለች። ሀሙስ ጠዋቱን ወደ ሁለት ሰዓት ገደማ እማዬ ፊቷ በላብ ጥምቅ ማለት ጀመረ። እግሮቿ ይፋተጋሉ። ወ/ሮ ለይላና አምሪ ቁርስ አምጥተዉልኝ ከአጠገቧ ተቀምጠዋል። አይናችን እያየ ሰዉነቷ ቀዘቀዘ። አይኖቿ ፈጠጡ። ወ/ሮ ለይላ በእጆቿ የእማዬን አይኖች ከደነቻቸዉ። እንባዬ ልብሴን አጠበዉ። ፈጣሪ ጨካኝ እንደሆነ ተሰማኝ። እንዴት ምድር ላይ ያለ አንዳች ዘመድ ብቻዬን ያስቀረኛል? እንዴት? አምሪያ ወንበሩ ላይ ተቀምጣ ታነባለች። ሀጂ ተደዉሎላቸዉ መጡ። እናቴ ታጥባ በከፈን ተጠቀለለች። ወደ ሰባት ሰዓት ገደማ ተሰግዶባት ተቀበረች።
እማዬን ቀብረን ስንመለስ በጣሙን ተስፋ ቆረጥኩ። ፈጣሪን የከለከላቸዉን ነገሮች ሁሉ በመዳፈር ልበቀለዉ ወሰንኩ። እነሚኪ ቤት ተቀምጠዉ ጠበቁኝ። ትንሽ ደስታ የሚሰማኝ እነሱን ሳይ ነዉ። ገና እንዳየኋቸዉ እንባዬ ይባሱን መዉረድ ጀመረ። ወይኔ ሀቢብ!...

😘ይቀጥላል...

ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ ።
😘❥..................🍃🍃..............😘.....❥

😘🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

ከ15❤️ ቡኋላ ክፍል አስራ አምስት ይቀጥላል
😘✿የማይፋቅ ስህተት✿

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

😘ክፍል_15

...🖍ዝም ብዬ እስቃለሁ። ከዛም አለቅሳለሁ። ቆይ ለምን? ፈጣሪን ምን አደረግኩት? ለሌላዉ ሀብትም ጤናም ሰጥቶ ቤተሰቦቹንም ይጠብቅለታል። እኔን ምነዉ ድሀ መሆኔ ሳያንስ ቤተሰብ አልባ አደረገኝ? ይሁና! መች ሀይ ባይ አለዉ!? እንደልቡ ይሁን!! ቆይ ለኔ ምን ሰጠኝ? ጠይም መልክ? ረዥም ቁመት? ሉጫ ፀጉር? ጉልበት? ምላስ? ይሄ ኮተት ለኔ ምን ያደርግልኛል? ሰዉ ከጎኔ ሳይኖር መልክ ፣ ቁመት ወላ ጉልበት ለኔ ምኔ ነዉ? ለነገሩ መች ከሳሽ አለዉና! እንዳሻዉ ይሁን!
.
እማዬ ከተቀበረች ሳምንት ሞላት። ሚኪ ሁሌም አብሮኝ ያድራል። ፌቪ ሰሞኑን ከጓደኞቿ ጋር አብራ እየመጣች ታዳብረኛለች። አምሪ ለቅሶ ለመድረስ የሚመጣዉን ሰዉ በማስተናገድ ተጠምዳለች። ዘመድ ባይኖረኝም ጎረቤትና ጓደኛ ሞልቷል። ለአምሪያ ለየት ያለ ስሜት ዉስጤ ላይ እየተፈጠረ ነዉ። ማታ ላይ ሁሉም ሰዉ ወደቤቱ እንደተበተነ አምሪ እኔና ሚኪ ወዳለንበት ክፍል መጣችና "ሀቢቤ በቃ ቤት ልገባ ነዉ። ደህና እደሩ!" አለችኝ። ልትወጣ ስትል ተከተልኳት። የዉጪዉ በር ጋር ስትደርስ "አምሪ ለምን እዚህ አታድሪም?" አልኳት። አምሪ ቀልዴን መስሏት "አዝግ!" ብላኝ ልትወጣ ስትል እጇን ያዝኳት። እንደመቆጣት እያለች "ሀቢብ!" አለችኝ። ለምን እንደያዝኳት እኔ ራሱ አላዉቅም። ቀስ ብዬ እጇን ለቀቅኳት። በቃ የሆነ ለማንም ሴት ተሰምቶኝ የማያዉቅ አይነት ስሜት ለሷ ልቤ ዉስጥ እየተቀጣጠለ ነዉ። አምሪ ፈገግ እንደማለት አለችና "ደህና እደር ሀቢቤ!" ብላኝ ወጥታ በሩን ዘጋችዉ። በረዥሙ ተነፈስኩና እዛዉ ቁጢጥ አልኩ። ሚኪ ሳሎን ቤት ሆኖ መስታወቱን አንኳኳዉ። ስዞር ሚኪ የሳሎን ቤቱን በር መስታወት መጋረጃ ገልጦ የማደርገዉን እየታዘበ ነበር። ተነስቼ ወደ ቤት ገባሁ። ሚኪ ዝም ብሎ አየኝና "ሀቢቤ ልጅቷ ጎረቤት ነህ ብላ እንዲህ መልፋቷ አይበቃም? አተርፋለሁ ብለህ እንዳትከስራት!" አለኝ።
"ሚኪ እኔ ራሴን ማዘዝ አልቻልኩም። እሷ ስትሄድ በጣም ነዉ የሚጨንቀኝ።" አልኩት።
ሚኪ ሳቀና "እና ፎንቃ አስጨመድዳታለሁ ብለህ ዝተህ የነበርከዉ ልጅ ፎንቃዋ ጨምድዶህ አረፍከዋ!?" አለኝ።
እየሳቅኩ ተቀመጥኩ። ሚኪ እየሳቀ ለአብነት እና ለከሪም ደዉሎ ነገራቸዉ። ምንም አላልኩትም እንደዉም ደስ አለኝ። ከፈለገ ለምን አምሪያን አፈቀረ ብሎ በየፖሉ አይለጥፍም፤ እንኳን በሷ በስንቱ ታምቻለሁ።
.
በነጋታዉ ሀጂ ደዉለዉ ወደ ቤታቸዉ ጠሩኝ። አምሪ እጇን ስለያዝኳት ተናዳ ነግራቸዉ ከሆነ ብዬ በጣም ፈራሁ። ቤታቸዉ ስሄድ አምሪ ፈገግ ብላ ስትቀበለኝ በሷ ምክንያት እንዳልሆነ ገመትኩና ቀለል አለኝ። ሀጂን ሰላም ብያቸዉ ተቀመጥኩ። ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ "ሀቢቤ ከዚህ በኋላ እንደአባትህ እየኝ! ያዉ እናትህ ባስገባችኝ ቃል መሰረት ላንተ መልካም ያልኩትን አደርጋለሁ። አሁን የናንተ ቤት እየተከራየ ገንዘቡ ባንክ እንዲቀመጥ ብናደርግ፤አንተ ደግሞ እኛ ቤት ብትኖር ምን ይመስልሀል?" አሉኝ። ሳስበዉ ትንሽ ነፃነቴን የሚጋፋኝ መሰለኝ። ደግሞ ከአምሪያ ጋር አብሮ መኖር ልጀምር መሆኑ ጥሩ ነዉ። አይሆንም ለማለት የማቀርበዉ ምንም አይነት ምክንያት ስላልነበረኝ ፈገግ አልኩና "ጥሩ ሀሳብ ነዉ።" አልኳቸዉ።
"በቃ ከተስማማን ጥሩ! አምሪያዬ ክፍልህን ታሳይሀለች። ልብሶችህን ታመጣቸዋለህ። የቤቱን እቃም ተከራይ ሲገኝ የሚሸጠዉ ይሸጣል።" አሉኝ። ተስማማሁ።
.
እነሀጂ ቤት የተሰጠኝ ክፍል ደስ ይላል። ልብሴን አምጥቼ ክፍሌ አስቀመጥኩት። አምሪ ቆንጆ አድርጋ ቁምሳጥኑ ዉስጥ አስተካክላ አስቀመጠችልኝ።
.
ሀዘኑ ቀለል ሲልልኝ ወደ ቀደመዉ ህይወቴ ተመለስኩ። ኦፊሳችን ስሄድ እነ አብነት የሌለ አሳብደዉታል። ትልቅ ፍራሽ፣ ገራሚ ትራሶች ምናምን ቤቱን ሞልተዉታል። የአዲስ ጎጆ ወጪ ቤት ይመስላል። ፌቪን ቀጥሬ ነበር የመጣሁት። እንደተቀመጥኩ ፌቨን መጣች። ሁለታችንም ምን እንደምንፈልግ ተግባብተናል። አብሮ መተኛት! በሩን ዘግተነዉ ሰላም እንኳ ሳንባባል የልባችንን ወደ ማርካቱ ሄድን። የምንግባባበት ዋናዉ ጉዳይ ይሄዉ ነዉ። አላፈቅራትም፤ለሷ ምንም ስሜት የለኝም። አሁን ከዚህ በላይ ከፌቪ ጋር መዛዛግ ስለደበረኝ ላሰናብታት ፈልጌያለሁ። እሷን ከማሰናበቴ በፊት ግን ሌላኛዋን ማዘጋጀት ይኖርብኛል። አምሪያን ማስመጡ እንደዚህ ቀላል አይሆንም። ለምን አምሪያ ጋር ስደርስ አቅም እንደማጣ ፣ ለምን ከሌሎች ሴቶች ተለይታ ክብድ እንደምትለኝ አላዉቅም። አጠገቧ ተቀምጬ ሳያት ብዉል አይቆጨኝም። ከፌቪ ጋር ያነፋፈቀንን የስጋችንን ጥሪ ምላሽ ከሰጠን በኋላ ወደ ቤቷ ሸኘኋት። ልንለያይ ስንል አይኖቿን አይኖቼ ላይ እያቁለጨለጨች "ሀቢቤ ላርግዝልህ?" አለችኝ። የሆነ እብደት የተጠናወታት መስሎኝ በግርምት እያየኋት "ፌቪ ግን ደህና ነሽ?" አልኳት።
ፈገግ ለማለት እየሞከረች "ሀቢቤ የእናትህ ሞት የብቸኝነት ስሜት ከፈጠረብህ የኔ የምትለዉ አንድ የስጋ ዘመድ ይኑርህ ብዬ እኮ ነዉ።" አለችኝ።
ግርም እያለችኝ "ሀሳብሽ ጥሩ ነዉ ግን ያንቺ ህይወት ላይ የሚፈጥረዉ ቀዉስ አልታየሽም?" አልኳት።
ፊቷ ላይ እልኋን እያስነበበችኝ "ዲቃላ ወለደች ይላሉ። አለቀ! አንተን ካስደሰተህ ምንም አደርጋለሁ።" አለችኝ።
ቆይ ምንድነዉ ልቧን እንደዚህ የሰቀለዉ? መተት አሰራሁባት እንዴ? ራሴን መጠርጠር ጀምሬያለሁ።
"ፌቪ ስላሰብሽልኝ አመሰግናለሁ። በዚህ ሰዓት ልጅ መዉለዱ ግን ለኔም ላንቺም ስለማይጠቅም ደግመሽ እንዳትጠይቂኝ!" አልኳት።
ፈገግ አለች! ምንም የተጋነነ ዉበት ባይኖራትም የደስ ደስ አላት። ፈገግ እንዳለች "ካልክ እሺ!" አለችኝ። ተሰናብቼያት ወደ አዲሱ ቤቴ ወደነአምሪያ ቤት ሄድኩ።...

😘 #ይቀጥላል...

❥......

🌳ከወደዱት ላይክ❤️ ያድርጉ
​​😘ሚስት_ለማግባት_መስፈርቱ

💔ቆንጆ ከሆነች አስተሳሰብ ዜሮ ትወርድብካለች
💟አስተዋይ ከሆነች ኮስታራ ትሆንብካለች
🤎ሀብታም ከሆነች አታከብርክም
💘ጠንካራ ሰራተኛ ከሆች ላንተ ጊዜ የላትም
💗ኮስታራ ከሆነች መስፈርቷ ይበዛል
🤍የዋህ ከሆነች ልቧ በሆነ መንገድ ተጎድቷል
💛ሀላፊነት እሚሰማት ከሆነ ለፍቅር ደንታ የላትም
💚በጣም የተማረች ከሆነች ሁሌ ትክክል ነኝ ትላለች
🖤ካልተማረች ስታርማት ታኮርፋለች (ትቆጣለች)
💙ብልጥ ከሆነች በባዶ ሜዳ ሁሉ ትዋሻለች
ጨዋ ከሆነች የጨረሰች ሰነፍ ትሆንብካለች
💞ፉንጋ ከሆነች ምግብ ላይ ቅመም ታበዛለች
🤍ነጋዴ ከሆነች ባል ትሆንብሀለች
💝የቤት ልጅ ከሆነች ከወጣች አትመለስም

#ሼር አድርጉ ይመቻችሁ

T.me/pclovee
❤️❤️❤️

@pclovee
[Forwarded from ትምህርት ሚኒስተር ]
ሰበር ዜና
ከ ትምርህርት ሚኒስትር የተሰጠ መግለጫ
ከዚህ በፊት ባወጣነው ማስታወቂያ ሁሉንም ተማሪዎች ወደ ትምርት ገበታ መጥራታችን ይታወሳል ሆኖም ሀገራችን ላይ በተከሰተው አለመረጋጋት የ ኮሚኒቲ ተማሪዎችን ሆነ ሌሎች ተማሪዎች ከዚህ በኋላ ምንጠራ አይመስለንም ስለዚህ በያላቹህበት አካበቢ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አማራጮችን እንዲመርጡ እናሳስባለን
1, ስራ ካገኛቹህ ፈልጉ..
2,ማግባት ያሰባቹህ አግቡ ።
3, መመንኮስ የምትፈልጉ መንኩሱ።
4, መሰደድ ምትፈልጉ ባስቸኳይ ተሰደዱ።
5, Activist የሆናችሁ ደከመን ሰለቸን ሳትሉ ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎአቹሁን ቀጥሉበት ።
6,ግቢ እንመለሳለን ብላቹህ እንዳትጠረጥሩ
7,እስካሁን ስለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን 🙏🙏

ትምህርት ሚንስተር
😘 ♥️የማይፋቅ ስህተት♥️
......❥
😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ😘
❥...❥
😘▬ተከታታይ ልቦለድ▬
❥...❥
😘 #ክፍል 16

...🖍ዛሬ ወንድሞቿ መጥተዉ ቤቱ ደመቅመቅ ብሏል። ኢስማኢል የሚባለዉ ታላቅ ወንድሟ ገና ስገባ ፈገግ ብሎ ተቀበለኝ። ለቅሶ መጥቶ ጠይቆኝ ነበር። ሁለቱ ሰላሀዲን እና ረመዳን ይባላሉ። ለቅሶ አልመጡም ነበር። ገብቼ ትንሽ እንደቆየሁ ሁለት ሰዓት ሊሆን አካባቢ የ"ኢሻ" ሰላት ለመስገድ ሁሉም ብድግ አሉ። እኔ ብቻ ቁጭ አልኩ። ታላቅ ወንድማቸዉ ኢስማኢል "ሀቢቤ ዉዱዕ የለህም መሰለኝ። እንጠብቅህ ሂደህ አድርገህ ና!!" አለኝ። ዉዱዕ ከስግደት በፊት የሚደረግ ትጥበት ነዉ። ሽክክ አለኝ። አልሰግድም ማለቱ ደግሞ አሳፈረኝ። ተነስቼ ተጣጥቤ ተከተልኳቸዉ። ስግደት ላይ የሚባሉት ዉዳሴዎች ብዙዎቹ ጠፍተዉኛል። ልጅ ሆኜ አባቴ ሳይሞት ከሰገድኩ እስከዛሬ ሰግጄ አላዉቅም። ይኸዉ ነፃነቴን መጋፋት ጀመሩ። የእናቴ ቃል ሆኖብኝ እና የሀጂ ራህመቶ ዉለታ ባይዘኝ አብሬያቸዉ አልኖርም ነበር።
ሰግደን እንደጨረስን አምሪያ ምግብ አቀረበች። ምግቡን እያቀራረበች ፈገግ ብላ ታየኛለች። ስሰግድ ስላየች ሙድ እየያዘች መሆኑ ገባኝ። ቆይ ይሂዱ ብቻ የሆነች ተምች የሆነች ልጅ!
ምግቡን በልተን እንዳበቃን የኢስማኢል ታናሽ ሰላሀዲን "ሀቢቤ ትምህርትህ ላይ እንዴት ነህ?" አለኝ።
ምን ልበለዉ ግራ ገባኝ። ግራ ስጋባ አየኝና "በትምህርትህ የመቀጠል ህልም አለህ ወይስ ሰዉ ስለሚማር ነዉ የምትማረዉ?" አለኝ።
የመጣዉ ይምጣ አልኩና "እስከዛሬ የተማርኩት እናቴን ደስ እንዲላት ነበር። ከዚህ በኋላ ባልማር ደስ ይለኛል።" አልኩት።
ረመዳን የሚባለዉ ታናሽ ወንድማቸዉ ፈገግ አለና "ካልተመቸህ ካሁኑ የሚጠቅምህ ህይወት ላይ ትኩረት አድርግ።" አለኝ። ከረመዳን ጋር ትንሽ ሙዳችን እየገጠመ ሳይመጣ አልቀረም።
ትንሽ ከተጫወቱ በኋላ ሶስቱም ተያይዘዉ ወደየቤታቸዉ ሄዱ። እኔም ከአምሪያ መኝታ ክፍል ጎን ወዳለዉ መኝታ
ክፍሌ ገብቼ ሳዑዲ የምትኖር ብዙ ጊዜ ብር የምትልክልኝን ተሚማ የምትባል ሚስኪን ታላቢዬን መጀንጀን ጀመርኩ። በመሀል ፌቪ እንደለመደችዉ ደዉላ ረዥም ሰዓት አወራችኝ። ክፍሉ አስተማማኝ ስለሆነ እንደልብ ለመጀናጀን ይመቻል።
.
ሊነጋጋ ሲል ሀጂ ራህመቶ የንጋት ስግደት እንድሰግድ በሩን አንኳክተዉ ለመቀስቀስ ሞከሩ። እንቅልፍ ብዙም ባይዘኝም ላለመስገድ ብዬ ባልሰማ ተኛሁ። አስራሁለት ሰዓት ሲል እንደለመድኩት ቻት ላይ ተጥጄ ከፌቪ እና ከተሚማ ጋር መጀናጀን ጀመርኩ። ተሚማ ፎቶዋን ልካልኛለች። አሪፍ ነገር ናት። በድምፅ የምንላላካቸዉ መልዕክቶች ልብስ ያስወልቃሉ። ትንሽ እየተፃፃፍኩ እንደቆየሁ አምሪያ የመኝታ ቤቴን በር አንኳኳችና " ሀቢቤ ተነስ ቁርስ ብላ!" አለችኝ። እዚህ ቤት ከአስራአንድ ሰዓት በኋላ እንቅልፍ የለም። ተነስቼ ልብሴን ቀያየርኩና ተጣጥቤ ወደ ሳሎን ሄድኩ። ቤቱ ፏ ብሏል። ደስ ይላል። ሀጂ ቁርስ እንድንበላ እየጠበቁኝ ነበር። አጠገባቸዉ ስቀመጥ "እንቅልፎ ሰገድክ?" አሉኝ። ፈገግ ብዬ "አዎ!" አልኳቸዉ። አለመስገዴን ማን ያዉቃል? ማንም! ፈጣሪ ነዉ እሱ እንደሆነ ይበለዉ።
በልተን እንደጨረስን "ሀቢቤ ማታ መማር እንደማትፈልግ ተናግረሀል። እኔ ከልጆቼ ጋር መክሬበት መስከረም ሲመጣ የሀይማኖት ትምህርት እንድትጀምር ወስኛለሁ። እኔ ሀይማኖታዊ ትምህርት ቤት ስላለኝ እዛ ትገባለህ።" አሉኝ። በህይወቴ ከዚህ በላይ የምጠላዉ ነገር ያለ አይመስለኝም። ሀጂ ደግሞ እሺ እሺ ስላቸዉ የሌለ አበዙት።
ምርር እያለኝ "ሀጂ ግን ስራ ብጀምር አይሻልም?" አልኳቸዉ።
"ሀቢብ ይሄ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም! ትማራለህ! የእናትህን አደራ አትርሳ!!" አሉኝ። በእናቴ ስም ይነግዳሉ እንዴ ብሽቅ ነገር ናቸዉ።
በልተን ስንጨርስ ሀጂ የወጪ ብለዉ መቶ ብር ሰጡኝ። ባይሆን ይሄ ሙዳቸዉ የሌለ መስጦኛል። ዛሬም ከፌቪ ጋር ተገናኝቼ በእናቴ ህመም ምክንያት ያላገኘኋትን ለማካከስ አሰብኩ። አዲስ ሴት እስከማሰምጥ ከሷዉ ጋር ልዛዛግ!
.
ሀጂ እንደወጡ አምሪ ፈገግ ብላ "ዛሬ ምንጣፍ አጥባለሁ አታግዘኝም?" አለችኝ።
ቀይ ምንጣፍ ላይ ህዝብ ተሰብስቦ እያጨበጨበልህ ትራመዳለህ ያለችኝ ያህል ደስ አለኝ። ፈገግ ብዬ "በጣም ደስ ይለኛል!!" አልኳት።
እነአምሪ ቤት ሰራተኛ አለመኖሩ ግርም ይለኛል። አንዴ አምሪን ጠይቄያት "ሁለት ሴት ያለበት ቤት ለሶስት ሰዉ ተብሎ ሰራተኛ እንዴት ይቀጠራል?" ብላኛለች። እኛ ለስራዉ አናንስም አይነት ነገር!
ምንጣፉን አዉጥቼ ግቢ ዉስጥ ዘረጋሁት። አምሪ ምንጣፉ ላይ ወጥታ በጎማ ዉሀ እያፈሰሰች በብሩሽ ማሸት ጀመረች። ጫማዬን አዉልቄ አምሪ በሰጠችኝ ብሩሽ ልክ እንደሷዉ ማሸት ጀመርኩ። ሁሉ ነገሯ ልቤን ይዞታል። እንደሌላዉ ሴት እንኳ ለማስመጥ ክብድ ብላኛለች።
ምንጣፉን እያየሁ "አምሪ" አልኳት።
ቀና ብላ አይታኝ ፈገግ አለችና በከንፈሮቿ ጥርሷን ያጠረዉን ሽቦ እየሸፈነች "አርፈህ እሽ!" አለችኝ። እየገባት ነዉ ልበል? እኔንጃ!
ፈገግ እያልኩ "ምኑን?" አልኳት።
ሳቋን መቆጣጠር አቅቷት እርጥቡ ምንጣፍ ላይ እየተቀመጠች "አመዳም ምንጣፉን ነዋ!" ብላ ብሩሿን ወረወረችብኝ።
እየሳቅኩ የወረወረችብኝን ብሩሽ መልሼ አቀብያት እሷ እንደምትቦርሸዉ ምንጣፉን መቦረሽ ጀመርኩ።...

😘#ይቀጥላል...

🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

❥..................⚘.................❥
2025/06/28 10:29:47
Back to Top
HTML Embed Code: