Telegram Web Link
😘♥️✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️
😘 ♥️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

😘ክፍል_17

...🖍ከአምሪ ጋር ምንጣፉን አጥበን እንደጨረስን ፀሀይ እንዲያገኘዉ ከግቢ ዉጪ አሰጣነዉ። አምሪ ግቢዉን ጠርጋ ስትጨርስ "ያዉ ዝናብ ከዘነበ ምንጣፉን ብቻዬን ማስገባት ስለማልችል ዛሬ የትም መሄድ አትችልም!" አለችኝ። ማዕቀብ ቢመስልም ደስ በሚል ሰዉ የተጣለ ደስ የሚል ማዕቀብ ስለሆነ ወድጄዋለሁ። አምሪ የግቢዉን በር ዘጋችና በረንዳዉ ላይ ከአጠገቤ እየተቀመጠች "ሀቢቤ ታዉቃለህ አንዳንዴ በህይወትህ ዉስጥ አንዴ ተሳስተህ የምትሰራዉ ስራ ህይወትህን ምስቅልቅል ሊያደርገዉ ይችላል።" አለችኝ።
አንገቴን አቀርቅሬ "ምን ተሳስተሽ ነዉ?" አልኳት። መልስ ሳትሰጠኝ "ከሱ የሚከፋዉ ደግሞ ያንተ መልካም ያልሆነ ምግባር ለሌላዉ ህይወት መበላሸት ምክንያት ሲሆን ነዉ!" አለችኝ። ልትነግረኝ የፈለገችዉን ነገር ከመተንፈስ በዘለለ ለማብራራት እንዳልፈለገች ስለተረዳሁ ላስጨንቃት አልፈለግኩም። ዝም ብዬ "ልክ ነሽ!" አልኳት። ሳቀች። ምን አሳቃት? እኔንጃ አልጠየቅኳትም።
ከአምሪ ጋር እየተጨዋወትን ሚኪያስ ደወለ። እየሳቀ "ሀቢብ ራህመቶ!" አለኝ። ሰሞኑን ሙድ መያዣ አድርገዉኛል። ዛሬ ከሄለን ጋር ኦፊስ ስለሚያሳልፉ ወደ ኦፊስ ድርሽ እንዳልል ሊያስጠነቅቀኝ ነዉ የደወለዉ። እኔ እንኳ ሲጀመርም ቆንጆ እስር ላይ ነኝ።
አምሪ በወሬያችን መሀል "ሀቢቤ ግን እኔና አንተ አብረን እንዲህ ረዥም ሰዓት ስንቀመጥ ቢያዩ ኡሚም አቢም እንደሚቆጡ ታዉቃለህ?" አለችኝ። ዛሬ ወ/ሮ ለይላ ከሀጂ ራህመቶ ጋር በጠዋቱ ወጥተዋል።
ግርም እያለኝ "ለምን?" አልኳት። "ሀይማኖታችን አይፈቅደዉም!" አለችኝ።
"ይገርማል ታዲያ ለምን አብረሽኝ ተቀመጥሽ?" አልኳት።
"እኔ እንኳን..." አለችና በረዥሙ እየተነፈሰች "ይለፈኝ!" አለችኝ። እኔ ሰዉ ማስጨነቅ ብዙም አይመቸኝም። አለፍኳት።
ደስ የሚለዉ ምንም ክረምት ቢሆንም ዛሬ ጠዋት ምንጣፉን ከማጠባችን በፊት የዘነበ ቀኑን ሙሉ አልዘነበም። ከአምሪ ጋር ባዶ ቤት ብቻችንን መሆናችንን ሳስብ ስለሷ የሚሰማኝን ስሜት ልነግራት አሰብኩ። ደሞ ነግሬያት ቢደብራት ወዳጅነታችንም ሊቀር ይችላል ብዬ ስለፈራሁ ተዉኩት።
.
እነአምሪያ ቤት እየኖርኩ ትንሽ እንደቆየሁ የኛ ቤት የቤት እቃዎች በሙሉ ተሸጡ። ትናንሽ የቤት ዉስጥ መገልገያዎችን ሰፈራችን ላለች አንድ ሴትዮ ሰጠናቸዉ። ቤቱም ተከራየ። አዲስ ባለትዳሮች ናቸዉ ቤታችንን የተከራዩት። የአስራሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ዉጤት ወጣ። አምሪ አምስት መቶ ዘጠና ሁለት አመጣች። ወንድሞቿ በሽልማት አንበሸበሿት። እኔም ከአረብ ሀገሯ ታላቢዬ ከተሚማ ባጨድኩት ብር የእንግሊዘኛዉ ኤ መሀሉ ላይ የተንጠለጠለበት የብር የአንገት ሀብል ስጦታ ሰጠኋት። አምሪ ስጦታዬን በጣም ወዳዋለች።
.
ክረምቱ እያለቀ ሲሄድ ከአምሪያ ጋር ያለን ቅርርብ በጣም እየጠበቀ ሄደ። ፈጣሪ ይባርካት በህይወቴ በልቼ የማላዉቀዉን በርገር የሚባል ምግብ ሱስ አስያዘችኝ። ብር እኔም ሀጂ ስለሚሰጡኝ እሷም ከወንድሞቿ እና ከሀጂ ስለሚሰጣት አንዳንዴ ካልሆነ አጥተን አናዉቅም። ወጣ ብላ ስትመለስ ለኔ ገዝታ ይዛልኝ ትመጣለች።
እኔ አስራአንደኛ ክፍልን እንደምንም ባልፍም ላለመማር ወስኛለሁ። ሀጂ ሀይማኖታዊ ትምህርት በግድ ሊያስተምሩኝ ወስነዋል። እኔም የእማዬ አደራ ሆኖብኝ ሳልወድ በግዴ እሺ ብያቸዋለሁ። እነሚኪያስ ትምህርት እንደማልቀጥል ስነግራቸዉ በጣም ተበሳጩ። ሀጂ ነፃነቴን እንደገፈፉኝ ተሰማቸዉ። በርግጥ ሀጂ ሀይማኖታዊ ትምህርት እንድማር እንጂ አለማዊ ትምህርት እንዳቋርጥ አላስገደዱኝም። መማር እንደማልፈልግ ስላወቁ ነዉ ይህን የፈረዱብኝ።
ፌቪ ቢያንስ በሳምንት ሶስት ቀን ኦፊስ ዉስጥ አብራኝ ታሳልፋለች። እነሀጂ ቤት መኖር መጀመሬን አልወደደችዉም። አንዳንዴ ትምህርታችንን ትተን የሆነ ነገር እየሰራን አብረን እንኑር ትለኝ ነበር። በጣም የሚገርመኝ ቀን ከሌት የሚለፉላት እና የሚያንቀባርሯትን ቤተሰቦቿን ከቁብም ሳትቆጥር እነሱን ትታ ከኔ ጋር ለመኖር ማለሟ ነዉ።
ሴት ልጅ ከወደደች፣ ከተያዘ ነፍሷ፣
የቤተሰብ ክብር ፣ ጨዋታ ነዉ ለሷ። አይደል የሚባለዉ። ይሄን ግጥም ፌስቡክ ላይ አንዷ ለጥፋዉ ነዉ ያነበብኩት። የማን እንደሆነ አላዉቅም። ከስሩ ግን ከበደ ሚካኤል የሚል ፅሁፍ ያየሁ መሰለኝ። ግጥሙ ፌቪን በደንብ ይገልፅልኛል።
ክረምቱ ተጠናቆ አዲስ አመት ተበሰረ። የነአምሪ የዩኒቨርሲቲ ምድብ ወጣ። አምሪ ክፍለሀገር ቢደርሳት በጣም ሊደብረኝ እንደሚችል ይሰማኝ ነበር። ግን ቢደርሰኝም እዚሁ የግል ዩኒቨርሲቲ እማራለሁ ስላለችኝ ተረጋጋሁ። ደስ የሚለዉ ምድብ ሲወጣ ህክምና አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ደረሳት። ሁላችንም በጣም ደስ አለን።
.
ዛሬ የአዲስ አመቱ ፀሀይ ፈገግ ያለ ይመስላል። በጠዋቱ ተነስቼ ግቢዉ ዉስጥ ፑሽአፕ እየሰራሁ ነዉ። ሀጂ የንጋት ስግደት እንድሰግድ ሲቀሰቅሱኝ እሺ ብዬ መብራቱን አበራና ሲሄዱ አጠፋዋለሁ። ያዉ ግን ስለለመደብኝ አስራሁለት ሰዓት ላይ ቻት ማድረግ እጀምራለሁ። ሀጂ ለቁርስ ሊጠሩኝ ሲመጡ ነቃ ብዬ ስልክ ስጎረጉር ስለሚያዩኝ የሰገድኩ ይመስላቸዋል። ዛሬ ፑሽአፕ ስሰራ አምሪ መጥታ ሀጂ እየጠሩኝ እንደሆነ ነገረችኝ። ስሄድ ፈገግ ብለዉ ተቀበሉኝና "ሀቢቤ ነገ ወደ መርከዙ ትሄዳለህ። ልብስህን አምሪያ ታዘገጃጅልሀለች።" አሉኝ። መርከዝ ያሉት የሀይማኖት ትምህርት ቤት ማለታቸዉ ይመስለኛል።
"ልብስ ምን ያደርግልኛል?" አልኳቸዉ።
ሀጂ ፈገግ እንዳሉ "አዳሪ ነዉ እኮ ትምህርቱ!" አሉኝ። ዉስጤ ንዴት ቅጥልጥል ሲል ይሰማኛል። እንዴት ነዉ እንደዚህ አይነት ህይወት የማሳልፈዉ? አዳሪ ይላሉ እንዴ?
ምርር እያለኝ "አዳሪ ማለት?" አልኳቸዉ።
"ያዉ አዳሪ ማለት ትምህርቱ እስኪያልቅ አዳርህም እዛዉ ነዉ ማለት ነዋ!" አሉኝ።
የሆነ ስሜት ዉስጤ ላይ ጥፋ ጥፋ ሲለኝ ይሰማኛል። የእናቴን ቃል ከምጥስ ትምህርት ቤቱን ብጥብጥ አድርጌዉ ለመባረር ወሰንኩ። ሀጂ ከሄዱ በኋላ ለአምሪ ያሉኝን ነገርኳት። "ባክህ ልብሱን አስተካክይለት ብሎ ነግሮኛል።" አለችኝ። ሳላስበዉ "አምሪ ትናፍቂኛለሽ እኮ!" አልኳት። ፈገግ ብላ አየችኝና "ሀቢቤ አትጨነቅ መድረሳዉ የአቢ ነዉ። እኔም እሁድ እሁድ ስለምማር እየመጣሁ አገኝሀለሁ።" አለችኝ። የሆነ ትልቅ ሸክም የወረደልኝ ያክል ቅልል አለኝ። አምሪ እንዲህ አቅልላ ያየችዉ እዛ ያለዉን ህይወት ስለምታዉቀዉ ይመስለኛል።
ከልቤ ፈገግ እንዳልኩ "እሺ!" አልኳት።...

😘 #ይቀጥላል...

❥.........

😘🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

••●◉Join us share◉●••

ርቀታችንን እንጠብቅ
ህይወትን እንታደግ
መኖርን ምርጫ እናድርግ

😘🚶‍♀_____2m_____🚶 🙏
😘✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

😘 #ክፍል_18

...🖍ወደ ማታ ከነሚኪያስ ጋር ተገናኝቼ የተፈረደብኝን ነገርኳቸዉ። በጣም አዘኑ። ሚኪ "ያዉ አንተ እንደምንም እያመቻቸህ ትወጣና ኦፊስ ትከሰታለህ። እኛ ፌቪን አመቻችተን እንጠብቅሀለን። አትጨነቅ!" አለኝ። በርግጥ እኔን ያስጨነቀኝ ነፃነቴ እንጂ የፌቪ ጉዳይ አይደለም።
ወደ ቤት ስመለስ አምሪን መኝታ ክፍሌ ዉስጥ ልብሴን በሻንጣ ስታስተካክል አገኘኋት። "ሀቢብ እስከምጨርስ ሳሎን ሁን!" አለችኝ። አሳሳች ቦታዎች ላይ ብቻችንን ስንሆን በጣም ትጠነቀቃለች። ዛሬ እንኳ እናቷም ነበሩ። አስተካክላልኝ ስትጨርስ ዉጪ በረንዳዉ ጋር ሆና ጠራችኝ። ስሄድ "ስማ ሀቢብ እዛ ስልክ መጠቀም አይፈቅዱልህም። ስለዚህ መላ መፈለግ አለብህ። ስትገባ ይፈትሹሀል። እኔ ከፈተሹህ በኋላ ላቀብልህ እሞክራለሁ። በፍፁም ግን እንዳይታወቅብህ!" አለችኝ።
ፀጉሬን እየጠቀለልኩ "ኧረ አምሪ ስራዬ ነዉ አትጨነቂ! ብቻ ስልኩ ይግባ!" አልኳት።
"ደሞ ለካርዱ አታስብ እኔ እልክልሀለሁ። የምመጣ ቀን ደግሞ አስቀድሜ እነግርሀለሁ።" አለችኝ። ይህን ሁሉ ለምን ታደርግልኛለች? እሷም እንደኔ እናፍቃት ይሆን እ
ንዴ? አላዉቅም። ፍዝዝ ስልባት "ሀቢብ ይህን ሁሉ የማደርገዉ አንተ በጣም ጨለማ ዉስጥ ያለህ ሰዉ ስለሆንክ በአንዴ ወደ ብርሀኑ ሲወረዉሩህ ጨረሩ በዝቶ እንዳይጎዳህ ብዬ ነዉ። ህይወትህን እንደልብህ ስትሆን እንዳሳለፍክ አዉቃለሁ። አሁን መታፈኑ እንዳይከብድህ ትንሽ ማስተንፈሻ እያመቻቸሁልህ ነዉ።" አለችኝ።
"ልክ ነሽ!" አልኳት ብስለቷ ግርም እያለኝ። ቆይ ግን ስለኔ ህይወት እንዴት እንደዚህ በድፍረት ልትናገር ቻለች? ዋናዉ ግን ያቀረበችዉ ሀሳብ መልካም መሆኑ ነዉ። .
በነጋታዉ ጠዋት ላይ በሀጂ መኪና ወደ ትምህርት ቤቱ ሄድን። ከአምሪያ እንደተነጠልኩ ሳስብ በጣም ሆድ ባሰኝ። ሀጂን ገፍቼ የራሴን መንገድ ለመከተል አሰብኩ። ደሞ የእናቴ አደራ ትዝ ሲለኝ እንደምንም ለመጋፈጥ ወሰንኩ። ግቢዉ ዉስጥ ገብተን ከመኪናዉ እንደወረድኩ አንድ ሰዉዬ መጥቶ ከሀጂ ጋር ትንሽ አወራና ሀጂን ተሰናብቶ "ኡስታዝ ሰዒድ እባላለሁ ተከተለኝ።" ብሎኝ ከፊት ከፊቴ መራመድ ጀመረ። ሀጂን ተሰናብቼ ሰዉየዉን ተከተልኩት። አምሪያ እንዳለችዉ ግን ፍተሻ አልተደረገብኝም። ስገምት ሀጂ ስላስገቡኝ ነዉ። ስልኬን አምሪ ወደ ማታ ልታቀብለኝ ተቀጣጥረናል።
ኡስታዙ ወደ ቢሮዉ አስገብቶኝ አንዳንድ ጥያቄዎችን ከጠየቀኝ በኋላ የትምህርት ቤቱን ህጎች መናገር ጀመረ። "እዚህ እስካለህ ድረስ የመኝታ እና የትምህርት ሰዓቶችን ማክበር አለብህ።" አለኝ እና ከተማሪዎች ጋር ሊኖረኝ ስለሚገባዉ ግንኙነት አብራራልኝ።
አዉርተን ስንጨርስ የምተኛበትን ክፍል አሳየኝ። ተደራራቢ አልጋዎች ያሉበት ሰፊ ክፍል ነዉ። ሻንጣዬን አልጋዬ ላይ ካስቀመጥኩ በኋላ የአንድ ክፍል በር እያሳየኝ "አሁን አንድ ልጅ ቁርዓን ሸምድዶ ስለጨረሰ የእንኳን ደስ አለህ ዝግጅት ተዘጋጅቶ ሁሉም እዛ ናቸዉ። ሂድ ግባ!" አለኝ። ወደ ክፍሉ ልገባ በሩን በትንሹ ከፍቼ ሳይ ትንሽዬ መድረክ ላይ አንድ ነጭ ጀለቢያ የለበሰ ሰዉ ቆሞ ያወራል። ተማሪዎቹ ሁሉም ነጭ ጀለቢያ ለብሰዉ እግራቸዉን አጠላልፈዉ በሰልፍ ተቀምጠዋል። ጀለቢያ የሚባለዉ ወንድ ሙስሊሞች የሚለብሱት ቀሚስ ነዉ። ተማሪዎቹ እንዳለ ልጆች መሆናቸዉን ሳይ በጣም ተበሳጨሁ። አሁን ከነዚህ ጋር ማነዉ ሚዛዛገዉ? ከከሪሜ የሚበልጥ አንድ ልጅ ብቻ ነዉ ያለዉ። በጣም ተበሳጨሁ። እቅዴ ከቻልኩ ዛሬ ለመባረር ነዉ። በሩን ከፍቼ ስገባ መድረኩ ላይ ያለዉ ሰዉዬ "አላህ ማንንም አይበድልም። በጣም ፍትሀዊ ነዉ። ሁላችንም የተሰጠንን ፀጋ ብንቆጥረዉ የጎደለን የለም!" አለ። ድምፄን ከፍ አድርጌ "አትዋሽ ፍትሀዊ አይደለም! ከፊሉን እያሰቃየ አንተን ስላስደሰተህ ፍትሀዊ ነዉ አትበል!" አልኩ። ተማሪዎቹ ዞር ብለዉ አዩኝና አጎንብሰዉ ሳቁ። ኡስታዙ አየኝና "ስምህ ማነዉ?" አለኝ። በንቀት እያየሁት "ሀቢብ" አልኩት። "አዲስ ተማሪ ነህ መሰለኝ። በኋላ ቢሮ እፈልግሀለሁ።" አለኝ።
ሊያባረኝ ሊሆን ይችላል ብዬ በጣም ደስ አለኝ።
.
ማታዉን አምሪ መጥታ አስጠራችኝ። ኡስታዙ የሀጂ ልጅ ስለሆነች እንደልቧ እንድትገባ ይፈቅድላታል። በእጇ ፌስታል ይዛለች። "ጀለቢያ አቢ ገዝቶልሀል። አድርሺለት ብሎኝ ነዉ።" አለችና ፌስታሉን ሰጥታኝ ሄደች። ኡስታዙ አጠገባችን ቆሞ ስለነበር ምንም ማዉራት አልቻልንም። እንደሄደች ጀለቢያዎቹን እያወጣሁ ስመለከታቸዉ የአንዱ ኪስ ዉስጥ ስልኬን አገኘሁት። የአምሪ ጥበብ ገረመኝ። ከልጆቹ ተደብቄ ለአምሪ እንዳገኘሁት የሚገልፅ መልዕክት በሚሴጅ ላኩላት።
.
ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ሲል አንዱ ኡስታዝ መጥቶ ቀሰቀሰኝ። በጣም ተበሳጭቼ "ምን ፈለግክ?" ስለዉ ዉሀ እየረጨ ከተኛሁበት አስነሳኝ። አሀ ለካ የመኝታ ህግ የተባለዉ ይሄ ነዉ? ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ተነስቶ መማር? ሰዉ አይደሉም እንዴ? በጣም ቀፈፉኝ።...

😘#ይቀጥላል...



😘✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

😘ክፍል_19

...🖍አዳሪ ትምህርት ቤቱ ከገባሁ አስር ቀናት አለፉ። አስር ቀን ሙሉ አንድ ግቢ ዉስጥ ከመምህሮቹ እና ከተማሪዎቹ ጋር እየተዛዛግኩ አሳለፍኩት። አምሪ እና እነሚኪ የሌለ ናፍቀዉኛል። ከግቢ የምንወጣዉ ከትምህርት ቤቱ አቅራቢያ ያለዉ መስጂድ ለመስገድ ብቻ ነዉ። እሱንም ቀን ላይ ብቻ! ስግደት ይከብደኝ የነበርኩት ልጅ ከግቢ የመዉጫ ሰበቤ እሱ ብቻ ሲሆን ይናፍቀኝ ጀምሯል። ከተማሪዎቹ በእድሜ ለኔ ከሚቀርበዉ ነስሩ ከሚባለዉ ልጅ ጋር በጣም ተመቻችተናል። ኡስታዞቹ ያስተማሩኝን ነስሩ መኝታ ክፍል ለብቻችን ሆነን በደንብ ያስረዳኛል። ኡስታዝ ማለት መምህር ማለት ነዉ። ኡስታዞቹ ከሚያስረዱኝ በበለጠ የሱ ይገባኛል። ነስሩ የደሴ ልጅ ነዉ። በትምህርት ቤቱ ዉስጥ ከአመት በላይ ቆይቷል። ባለፉት ቀናት በልጅነቴ አዉቃቸዉ የነበሩ ብዙ ነገሮችን አስታዉሻለሁ። ቁርአንን እያየሁ ማንበብ እየቻልኩ ነዉ። ነስሩ ሁሌም ሲያስረዳኝ "አንተ ስለምትፈራ ነዉ እንጂ ገርቶልሀል!" ይለኛል። በርግጥ በልጅነቴ በደንብ ቁርዓንን ማንበብ እችል ነበር። የገባሁ ቀን ፈጣሪ ፍትሀዊ አይደለም ብዬዉ ቢሮ እፈልግሀለሁ ብሎኝ የነበረዉ መምህር ያባረኛል ስል እንደዉም ከትምህርት ሰዓት ዉጪ ሁሉ ለብቻዬ እየጠራ ያስተምረኝ ጀምሯል። ለመባረር ከሞከርኩ የትምህርት ሰዓቴ እየጨመረ እንደሚመጣ ስለገባኝ መረበሽ አቁሜያለሁ።
ባለፉት ቀናት ከግቢ ለመዉጣት ብፈልግም ከስግደት ሰዓት ዉጪ መዉጣት አልቻልኩም። አስተማሪዎቹ ደግሞ በአይነቁራኛ ይከታተሉ
😘✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘 ●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

😘#ክፍል_20

...🖍ህይወት ቀጥሎ በእስልምና ትምህርት ቤቱ ዉስጥ አምስት ወራትን አስቆጠርኩ። በቃሌ አምስቱን ረዣዥም የቁርዓን ምዕራፎች ሸመደድኩ። ይህ ማለት ከአንድ መቶ ሰላሳ ገፅ በላይ በቃሌ ሸምድጃለሁ ማለት ነዉ። ሀጂ በጣም ከመደሰታቸዉ የተነሳ የሚያምር ካባ ሸለሙኝ። ጥር አልፎ መጋቢት ሊገባ ሲል የሁለት ሳምንት እረፍት ተሰጥቶን ወደ ቤታችን እንድንሄድ ተፈቀደልን። ከነስሩ ጋር መለያየቴ ቢከፋኝም አምሪያን ሁለት ሳምንት ሙሉ ላገኛት መሆኑን ሳስብ ከደስታዬ ብዛት መላ ሰዉነቴ ነዘረኝ።
ጁምዓ(አርብ) ሊመሽ ሲል ሀጂ በመኪናቸዉ ይዘዉኝ ወደ ቤት ሄዱ። ቤት ስደርስ በጣም ድምቅ ብሏል። እንደገባሁ ማየት የፈለግኩት አምሪያን ቢሆንም ሰፈር መስጂድ ለመማር ሄዳ ስለነበር ገላዬን ለመታጠብ ወደ ሻወር ቤት ሄድኩ። ተጣጥቤ እንደጨረስኩ ጀለቢያዬን ለብሼ ሳሎን ከሀጂ ጋር ተቀመጥኩ። ጀለቢያ ቀሚስ ስለሆነ በጣም ቅልል ይላል። ትምህርት ቤት እያለሁ ሁሌም እሱኑ መልበስ ይቀናኛል።
ትንሽ እንደተቀመጥኩ አምሪ መጣች። ጥቁር አባያ በነጭ ሂጃብ ለብሳለች። አባያ ሙስሊም ሴቶች የሚያዘወትሩት ጥቁር ልብስ ነዉ። ሂጃብ ደግሞ ፀጉራቸዉን ላይ የሚጠመጥሙት ሻሽ! እንዳየችኝ ፈገግ አለች። ጥርሷ አሁንም ዙሪያዉን እንደታጠረ ነዉ። ጥርሷን ያጠረዉን ሽቦ በከንፈሯ እየሸፈነች "ሀቢብ ሀፊዙ!" አለች። ሀፊዝ የሚባለዉ ቁርዓንን ሙሉ ለሙሉ የሸመደደ ሰዉ ነዉ። እየሳቅኩ "ኧረ ገና ነኝ።" አልኳት።
ወይዘሮ ለይላ ፈገግ ብለዉ "አብሽር ትጨርሰዋለህ ከባዱን አልፈኸዋል።" አሉ።
ሀጂ የአረቢያን መጅሊሱን መከዳ አስተካክለዉ እየተደገፉ "ሀቢቤ አሁን አምሪያዬም ስለመጣች እስኪ ከሸመደድከዉ ትንሽ አ
ማን" አሉኝ።
ሀጂ አዘዉ እምቢ ማለት ስለደበረኝ ከኢምራን ምዕራፍ ጥቂት አሰማኋቸዉ። አምሪያ ግርም ብሏት ፍዝዝ ብላ አዳመጠችኝ። ስጨርስ "ሀቢብ የእዉነት አንተ ነህ እንደዚህ በሚያምር ድምፅ የቀራኸዉ?" አለችኝ። መቅራት ማለት ማንበብ ነዉ።
እየተሽኮረመምኩ አንገቴን ደፋሁ። ወ/ሮ ለይላም በጣም ተገርመዉ "አጂብ ተምሮ የማይለወጥ የለም ማለት ነዉ?" አሉ።
ሀጂ እጃቸዉን ከፍ አድርገዉ ዱዓ አደረጉ። ዱዓዉ ለኔም ለአምሪያም ነበር። አሚን አልን። ልቤ ዉስጥ የፈጣሪ ፍቅር በትንሹ ጠብ ሲል ተሰማኝ።
.
ብዙ ከተጨዋወትን በኋላ መኝታ ክፍሌ ገብቼ ተኛሁ። ለምዶብኝ ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ላይ ከእንቅልፌ ተነሳሁ። ተጣጥቤ ክፍሌ ዉስጥ ቁርዓን መሸምደድ ጀመርኩ። እስከ አስራ አንድ ሰዓት ከሸመደድኩ በኋላ የሱብሂ ስግደት ስለደረሰ ሀጂን ልቀሰቅሳቸዉ ወደ ክፍላቸዉ ሄድኩ። ከዉጪ ሆኜ አንኳኳሁ። ሀጂ ተነስተዉ ከመኝታ ክፍል ወጥተዉ ሲያዩኝ እኔዉ ነኝ። ገርሟቸዉ "በስንት ጭቅጭቅ ትነሳ የነበርከዉ ልጅ እኔን ለመቀስቀስ በቃህ? እኔ እኮ አምሪያዬ መስላኝ ነበር።" አሉና ፈገግ ብለዉ "ፈጣሪ ቀናትን በሰዎች መካከል ያዘዋዉራል። እናም ዛሬ አንተ ቀስቃሽ እኔ ተቀስቃሽ ሆንን!" አሉ።
ከሀጂ ጋር መስጂድ ሄደን ሰግደን ተመለስን። ስንመጣ እንደተለመደዉ እነአምሪያ ቤቱን ፏ አድርገዉታል።
አምሪ ልክ ስንገባ "ዛሬ ሀቢቤ ትጋበዛለህ!" አለችኝ። ወ/ሮ ለይላም እየሳቁ "ይገባዋል!" አሉ።
እኔ ከአምሪ ጋር ብቻችንን ሆነን የምናወራበትን ሰዓት እየናፈቅኩ ነዉ። የፈለገዉ ይምጣ እንደምወዳት እነግራታለሁ። ቢያንስ ምናልባት የምትወደኝ ከሆነ ሌላ ወንድ እንዳታገባ ያደርጋታል። ቆይ ግን ያልታጨች ልጅ ብታገባስ ብዬ የምጨነቀዉ ምን ያህል ብሳሳላት ነዉ? እኔንጃ!
.
ጠዋቱን ሀጂ ወደ ስራ ሄዱ። ወ/ሮ ለይላም አብረዋቸዉ ሄደዋል። ወደ ማታ መጥተዉ እኔና አምሪን ሊጋብዙን ቃል ገብተዋል። አምሪ ፈተና ጨርሳ ዕረፍት ላይ ነበረች። ግቢዉ ዉስጥ ትንሽዬ የፕላስቲክ ወንበር ላይ ተቀምጬ ፀሀይ እየሞቅኩ እያለ አምሪ ወንበር ይዛ መጥታ ከኔ ትንሽ ራቅ ብላ ተቀመጠች።
"ሀቢቤ የናንተን ቤት የተከራዩት ሰዎች አዲስ ሙሽራዎች እንደሆኑ ታዉቃለህ?" አለችኝ። አንገቴን በአዎንታ ነቀነቅኩት። ባልየዉን የገቡ ሰሞን አይቼዉ አዉቃለሁ። አዲስ ሙሽራ መሆናቸዉን እንኳ ወ/ሮ ለይላ ሲያወሩ ነዉ የሰማሁት።
ስለቤታችን ሲነሳ እማዬ ትዝ ትለኛለች። እንጀራ ተሸክሜላት ወደ ላስቲኩ ምግብ ቤቷ ሳደርስላት ትዝ ይለኝና እንባ አይኔን ይሞላዋል።
አምሪ ስፈዝባት "ሀቢቤ ምነዉ ተከዝክ?" አለችኝ። የመጣዉ ይምጣ ብዬ ላፈርጠዉ ወሰንኩ።
አንገቴን አቀርቅሬ ምራቄን እየዋጥኩ "አምሪ" አልኳት።
ለሆሳስ በሚመስል ድምፅ "ወዬ" አለችኝ።
ልቤን እያደፋፈርኩ "አንድ ነገር ልነግርሽ ነበር ብትወጂዉም ብትጠይዉም ላታኮርፊኝ ቃል ትገቢልኛለሽ?" አልኳት።
"ንገረኝ አብሽር አላኮርፍህም!" አለችኝ።
"እወድሻለሁ!" አልኳት ድምፄ እየተንቀጠቀጠ። መልሷን ለመስማት አንገቴን ቀና አድርጌ አየኋት። በልቤ እንዳትከፋብኝ ፈጣሪዬን ለመንኩት። ለሚወዱት ሰዉ ፍቅርን እንደመግለፅ የሚከብድ ምን አለ? በተለይ ፆታዊ ፍቅር ሲሆነ...

💖#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃.............😘......❥

😘 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳
​​​​. 😘✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

😘●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

😘ክፍል_21

...🖍አምሪን እወድሻለሁ እንዳልኳት ከአይኗ ዉስጥ ምላሿን መፈለግ ጀመርኩ። የተቀመጠችበትን የፕላስቲክ ወንበር አስተካከለችና "ሀቢቤ እኔም እወድሀለሁ።" አለችኝ። እሷ በወንድምነት እንደተረዳችዉ ከሁኔታዋ ገባኝ። እንደምንም ትንፋሼን ሰብስቤ "አምሪ አፈቅርሻለሁ ለማለት ነዉ የፈለግኩት!" አልኳት። አምሪ ፊቷን ቅጭም አደረገችዉ። ደነገጥኩ። በልቤ ፈጣሪዬን እንዳታኮርፈኝ ለመንኩት።
አምሪ ፊቷን ፈታ ለማድረግ በትንሹ ፈገግ አለችና "ሀቢቤ ስለፍቅር ምን ታዉቃለህ? ማለቴ እንዳፈቀርከኝ እንዴት አወቅክ?" አለችኝ። ለሆሳስ በሚመስል ድምፅ "ሁሌም ትናፍቂኛለሽ ደግሞ ብዙ ጊዜ አንቺን ነዉ የማስበዉ። መርከዝ ሆኜ በራሱ ሳላስብሽ ዉዬ አላዉቅም።" አልኳት።
እየሳቀች "በቃ ፍቅር ያልከዉ ይሄን ነዉ?" አለች።
"ልቤ ይፈልግሻል! ታዲያ ከዚህ በላይ ፍቅር ምንድነዉ?" አልኳት።
አምሪ በከንፈሯ ጥርሷን ያጠረዉን ሽቦ እየሸፈነች "ሀቢቤ ያንተ የፍቅር አረዳድ ከዘፈን ግጥም የዘለለ አይደለም። ቆይ እሺ ብልህ ምን ልታደርግ ነዉ? ልትስመኝ? እ? ንገረኛ! ወይስ ከእንስሳ እንደማይሻሉት አልጋ ላይ ልንንፈራገጥ?" አለችኝ። የእዉነት ግን እሺ ብትለኝ ምን እንደምናደርግ አላዉቅም። ከፌቪ ጋር አደርገዉ የነበረዉ በአምሪ አገላለፅ ከእንስሳ አለመሻል ተብሏል። አምሪ ከእንስሳ ያልተሻልኩባቸዉ ቀናት እንዳሉ ብታዉቅ ምን ትለኝ ይሆን? ትንሽ የሀይማኖት ህግጋትን ስላወቅኩ በፍፁም ፌቪ ላይ ያደረግኩትን አምሪ ላይ ለመድገም ልቤ አይፈቅድልኝም። ብፈልግ እንኳ እሷም አትፈቅድልኝም።
ዝም ስል አምሪ "ንገረኛ እሺ ብልህ ምን እናደርጋለን?" አለችኝ።
"አምሪ አላዉቅም በቃ ስሜቴን ነዉ የነገርኩሽ!" አልኳት።
የግርምት ሳቅ ሳቀችና "ሀቢቤ አንተ ቁርዓኑን ከመሸምደድ እና ከመረዳት በዘለለ የሆነ ወደ ህይወትህ ያመጣኸዉ አልመሰለኝም። እዉቀትህ ስነ ምግባርህ ላይ ካልተገለፀ የአህያዋ ታሪክ ይደገማል። አህያዋም የማትበላዉን ምግብ ተሸከመች ፣ አንተም የማትሰራበትን እዉቀት! እዉቀቱ ቆንጆ ነዉ ግን ወደ ህይወትህ አምጣዉ!" አለችኝ።
"አምሪ ለምን ትፈላሰፊያለሽ ፍቅር እኮ በፍላጎት የሚመጣ አይደለም። እዉቀታቸዉን በተግባር የገለፁ ሰዎችም አፍቅረዋል። በስነ ምግባራቸዉ ወደር ያልነበራቸዉ ነብይም ለአንዷ ሚስታቸዉ ልዩ ፍቅር ነበራቸዉ!" አልኳት።
አምሪ ሳቋን መቆጣጠር አቃታት። እንባዋ ከአይኗ ፈሰሰ። ምን ያስቃታል? አልዋሸሁም። ስቃ ስትጨርስ "ሀቢቤ አሁን ምንም የማያዉቅ ሰዉ ይሄን ንግግርህን ቢሰማ የከጀላትን ሁሉ ለፍቅረኛነት የሚጠይቅ አይመስልህም?" አለችኝ።
እልህ እየተናነቀኝ "አምሪ ምንም አልተሳሳትኩም! ልክ ነኝ።" አልኳት።
አምሪ እንደመረጋጋት አለችና "ሀቢቤ ልክ ነህ ግን ነብዩ ያፈቀሩት ሚስታቸዉን ነዉ። ሌላ ሴት ማፍቀር አይቻልም ማለቴ አይደለም። ግን አሁን እንደጠቀስካቸዉ ሰዎች ስታፈቅር ልጅቷ ፍቅርህን ብትቀበልህ ምን እንደምታደርግ ማወቅ አለብህ። እሺ ብልህ ምን እናደርጋለን ብዬ ለጠየቅኩህ ትክክለኛ መልሱ ኒካህ ነበር። አንተ ከተራ ፍቅቅሮሽ ወይም ከዘፈን ግጥም ዘለህ ስለትዳር ማሰብ አልቻልክም። ለትዳር ብቁ አይደለሁም ብለህ ካሰብክ ስሜትህን ማፈን ነዉ ያለብህ። ካስቸገረህ በፆም ግራዉ! ጭንቅላትህ ስለትዳር ማሰብ ሲችልና ብቁ ስትሆን ግን የወደድካትን ጠይቅ! ተጋብታችሁ መልካም ኑሮ ትኖሩ ይሆናል።" አለችኝ።
ከዚህ በኋላ አምሪን ለማሳመን የምሞክርበት አንድም ቃል አልነበረኝም። ግን ትንሽ ክፍተት ታይቶኛል። ምናልባት ማግባት ስችል ብጠይቃት እሺ ልትለኝ ትችላለች። ለማረጋገጥ ብዬ "እና መልስሽ ምን ሆነ?" አልኳት።
አምሪ ፈገግ ብላ "አንተ በትምህርትህ ላይ ጠንክር! በደንብ ሀይማኖትህን አዉቀህ ወደ ህይወትህ መልሰዉ። እዉቀትህ ሲጨምር ሰዎችን ማስተማር ጀምር! ያኔ ልታገባት የፈለግካትን ታገባለህ!" አለች። ልታገባት የፈለግካትን ታገባለህ ያለችዉ ዉስጥ ታገባኛለህ የሚል መልስ ያገኘሁ መሰለኝ። አምሪን ለማግኘት መስፈርቱ ግልፅ ሆኗል። ማወቅ ፣ ያወቁትን ወደ ህይወት ማምጣት ፣ ሰዎችን ማስተማር! ትምህርቴ ላይ ለመጠንከር ወሰንኩ።
ወዳጅነታችን እንዳይበላሽ እየፈራሁ "አምሪ ግን አንኮራረፍም አይደል?" አልኳት።
"ሀቢቤ እንደዉም ስለነገርከኝ ደስ ብሎኛል። አብሽር ምንም አይቀየርም።" አለችኝ።
ትንሽ ዕረፍት ተሰማኝ።
.
ከከሰዓት የናፈቁኝን ጓደኞቼን ለማግኘት ወደ ኦፊስ ሄድኩ። እነሚኪ እመጣለሁ ብያቸዉ ስለነበር ከሰዓት ትምሮ አልሄዱም። ጀለቢያዬን አዉልቄ በሱሪ ነበር የሄድኩት። ገና ስገባ ሚኪ ከመቀመጫዉ ተነስቶ እያቀፈኝ "ሀቢቤ በመላጣዉ!" አለ። እንደዛ ይፈረዝ የነበረዉ ፀጉሬ በየወሩ የጨዋ ቁርጥ መቆረጥ ጀምሯል።
ሰላም ከተባባልን በኋላ አዲስ የገዙት አልጋ ላይ ተቀምጠን ባለፉት አምስት ወራት ያመለጡኝን ጉዶች ማዳመጥ ጀመርኩ። ከሪም ፍቅረኛ ይዟል። አብነት እየሳቀ "ከሪሜም ባቅሙ ኦፊስ ማጣበብ ጀምሯል።" አለኝ።
ኦፊሱ ቀለም ተቀብቶ የሌለ አምሮበታል። እነሚኪ ከአለባበሳቸዉ ጀምሮ ብዙ ለዉጥ ይታይባቸዋል።
"ሚኪዬ መላ ማን አዝንቦባችሁ ነዉ? የሌለ ዲታ መስላችኋል እኮ!" አልኩ።
ሚኪ ጀነን እያለ "ሀቢቤ አንቺ ሀይማኖታዊ ሸቤ እያለሽ እኛ የአረብ ሀገሩን ቢዝነስ የሌለ አሳብደነዋል። ለአብነት ራቁቷን ፎቶ የላከችለትን ልጅ አስታወስካት?" አለኝ። አንገቴን በአዎንታ ነቀነቅኩለት።
"ፎቶዉን ፌስቡክ ላይ እንለቀዋለን ብለን አስፈራርተናት ስንት ጊዜ የሰራችበትን ብር በሙሉ አስላክናት!" አለና ጮክ ብሎ መሳቅ ጀመረ። እነአብነትም አብረዉት ይስቃሉ። ዉስጤ ላይ በጣም ቅፍፍ ሲለኝ ተሰማኝ። አንድ ሰዉ ከሀገሩ ተሰዶ የለፋበትን ገንዘብ መቀማት የለየለት ዉንብድና ነዉ። ትናንት እኔም አደርገዉ ነበር። ዛሬ እንዴት እንደቀፈፈኝ አላዉቅም። በኔናበነሚኪ መካከል የአስተሳሰብ ልዩነት እየተፈጠረ እንደሆነ ገባኝ። ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ "ይገርማል።" አልኳቸዉ። አብነት ትራሱን አስተካክሎ እየተደገፈ "ኧረ አይግረምህ ገና ብዙ ተዓምር ተፈጥሯል።...

😘#ይቀጥላል...

❥............😘......🍃🍃...................❥

😘🌳ከወደዱት ሼር
😂 @ethio_musicc 👇👇
ኮሜድያን ማርቆስ
በሀገር ቀልድ አይነፋም -New Ethiopian Music 2020(@BiraBiroTube)
🎵JOIN US @ETHIO_MUSICC
​​ 😘✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

#ክፍል_22

...🖍ከሪሜ ከአፉ ላይ ነጥቆ "ሚኪያችን ሄለንን አስጭኗት ባለፈዉ ሄዳ አራገፈችዉ። አሁን ጭሯት ሌላ እብድ የሆነች ወፍ ጠብሷል።" አለ። ሄለን አርግዛ አስወረደች? ሚኪ አልፈልግሽም ብሏት ሌላ ሴት ጠበሰ? ይገርማል። ለምን ይገርመኛል? እኔ ራሴ ፌቪን በቃሽኝ ብያታለሁ እኮ! ዛሬ ስሰራ የነበረዉን ወንጀል እያስደመርኩ መሰለኝ። እነሱ ሰራነዉ ሲሉ ቀፈፈኝ። የራሴስ? ይገርማል።
ዝም ስል ሚኪ "ሀቢቤ ከሰዉ ከምትሰማዉ እኔ ልንገርህ ክለብ መዉጣትና መጠጣት ጀምረናል።" አለኝ። በፊት ሱስ ዉስጥ ያለመግባት ቃልኪዳን ነበረን። በርግጥ እማዬ ስለምታስፈራራኝ ብዬ ነበር ቃል ያስገባኋቸዉ። እነሱ ግን በትንሹ የጀመርነዉን የጫት ሱስ ወደ መጠጥ አሳደጉት።
በጣም ቅፍፍ ስላለኝ "በቃ ወሬ እንቀይር!" አልኩ።
ሶስቱም በሀፍረት አጎነበሱ። ከሪሜ ቀና ብሎ እያየኝ "ዛሬ ከኛ ጋር አትወጣም? ፌቪም ትመጣለች።" አለኝ። የፈጣሪ ያለህ ፌቪንም እዚህ መዓት ዉስጥ ጨመሯት? ምርር እያለኝ "ስማ ከሪም ስለዚህ ነገር ደግመህ ብታወራ እንጣላለን እሺ!" አልኩት።
አንገቱን በአዎንታ እየነቀነቀ "እሺ!" አለኝ።
.
ኦፊስ ተቀምጠን እየተጨዋወትን ፌቪ በሩን ከፍታ ገባች። እንደምመጣ አታዉቅም። በስልክ ካወራን አምስት ወር ሆኖታል። ፌስቡክ ላይ መፃፃፍ ካቆምን ደግሞ አራት ወር። እነሚኪ ኦፊስ መጥታ ታለቅስ እንደነበር ነግረዉኝ ነበር። አሁንማ ቋሚ አባል ሆናለች። አብራቸዉ
መጠጥ ቤት መሄድ ሁሉ ጀምራለች። ስታየኝ ህልም ሳይመስላት አይቀርም። ከስር ጥቁር አጭር ቀሚስ ከላይ ደግሞ ነጭ ሸሚዝ ለብሳለች። በእጇ ብርቱካናማ ቦርሳ አንጠልጥላለች። ቦርሳዋን ወርዉራ ከአይኗ እንባ እየፈሰሰ እንደመሮጥ እያለች ልታቅፈኝ አልጋዉ ላይ ወጣች። እንቢ ማለት አልቻልኩም። አቀፈችኝ። አቅፋኝ እየተንሰቀሰቀች "ሀቢቤ እንዴት እኔ ላይ እንደዚህ መጨከን አስቻለህ? ሀቢቤ እንዴት?" አለች። ለቅሶዋ አንጀት ይበላል። ዝም ብዬ አቅፌያታለሁ። ቀጠለች "ሀቢቤ እኔኮ አንተን ካጣሁ በኋላ ሰዉ መሆን ከበደኝ። ትምህርት መማር አቅቶኝ አቋረጥኩ እኮ! አንተ መለየቱ እንዴት አስቻለህ? እንዴት ጨከንክ ሀቢቤ? እንዴት?" አለች። ትምህርት አቋረጠች!? የፈጣሪ ያለህ! ምነዉ ወንጀሌ በዛ!? የስንቱን ህይወት ይሆን ያተራመስኩት? ሰላም ፣ ሰሚራ አሁን ደግሞ ፌቨን!
ሳላስበዉ እንባዬ ከአይኔ ፈሰሰ። አብነት አላስቻለዉም አነባ። ፌቪ አሁንም እየተንሰቀሰቀች ነዉ። "ሀቢብ በጌታ ትተኸኝ አትሂድ በጌታ! የፈለግከዉን እሆንልሀለሁ። በጌታ አትለየኝ!" አለች። ከእቅፌ ቀና እያደረግኳት "አልተዉሽም!" አልኳት። ከፌቪ ጋር በፍቅረኛነት የመቆየት ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም። ግን ደግሞ ያመሰቃቀልኩትን ህይወቷን ማስተካከል ባልችል እንኳ ቢያንስ እንድትስተካከል ልረዳት እና ቀስ በቀስ ልርቃት እችላለሁ። እሷም ጉዳቷ ይቀንስላታል።
ፌቪ አልተዉሽም ስላልኳት በጣም ተደስታለች። ስትረጋጋ እነሚኪ ክፍሉን ሊለቁልን ተነሱ። "የት ልትሄዱ ነዉ? ተቀመጡ!" አልኳቸዉ።
ፌቪ ፈገግ ብላ የሸሚዟን ቁልፍ መፍታት ጀመረች። አሀ ልንተኛ? የሌለ ጭንቅ እያለኝ "ፌቪ ይቅርብን! ሚኪ እንዳትወጡ!" አልኩ።
ፌቪ እያኮረፈች "ሀቢብ ሌላ ሴት ለመድክ እንዴ?" አለችኝ። አልፈርድባትም ገና ስንገናኝ ፍራሽ ላይ ከመንከባለል ቦዝነን አናዉቅም። ዛሬ አልፈልግም ስል ብትጠረጥር እዉነት አላት።
"ኧረ ሚኪ የት እንደነበርኩ አስረዷት!" አልኳቸዉ። አብነት ሁሉንም ነገር ተተረተረላት።
እየከፋት "እሺ!" አለችና ሸሚዟን ቆልፋ ከአጠገቤ ተቀመጠች። ሰዓቱ ወደ አስር ሰዓት ሲጠጋ የስግደት ሰዓት ስለደረሰና የአምሪ እናት ሊጋብዙን ከአምሪ ጋር ቀጠሮ ስላለን ወደ ቤት ለመሄድ ተነሳሁ።
"ወዴት ነዉ?" አለች ፌቪ አብራኝ ብድግ እያለች።
"ቤት መሄድ አለብኝ። ይጠብቁኛል።" አልኳት።
አይኔን እያየች "ከኛ ጋር ክለብ አትወጣም?" አለች።
ፌቨንን ለብቻዋ ወደ ዉጪ ወስጄ "ፌቪ ክለብ መዉጣቱ አይጠቅምሽም። ከዚህ በኋላ እንዳትወጪ! መጠጥም አትጠጪ!" አልኳት።
"እኔ አንተን ያስረሳኛል ብዬ ነበር ምጠጣዉ በቃ ተወዋለሁ።" አለችኝ።
ልሄድ "ቻዉ!" ስላት ከንፈሬን ልትስመኝ ተጠጋችኝ። አንገቴን ዞር አደረግኩባት። "ኧረ ደስ አይልም!" አለችና ሳላስበዉ ዘላ ጉንጬን ሳመችኝ። ሰቀጠጠኝ። ነገ ላገኛት ተቀጣጥረን ወደ ቤት ሄድኩ።...

#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃...................❥



​​​​. 😘✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

😘#ክፍል_23

...🖍ከኦፊስ ቀጥታ ወደ መስጂድ ሄጄ ሰገድኩና ጌታዬን ተንሰቅስቄ ምህረቱን ለመንኩት። አምስቱን ወር በሙሉ የወንጀልን ምንነት ጠንቅቄ ብማርም አንድም ቀን የራሴ ወንጀል ታይቶኝ አያዉቅም ነበር። በህይወቴ ያበላሸኋቸዉ ህይወቶች ሰላም ነሱኝ! ከስንቱ ጋር አንሶላ እንደተጋፈፍኩ ሳስበዉ ሰቀጠጠኝ። ወንጀሌ ምንም ቢገዝፍ የፈጣሪዬን ይቅርታ አይሸፍነዉም ብዬ ተንሰቀሰቅኩ። ከመስጂድ እንደወጣሁ በቀጥታ ወደ ቤት ሄድኩ። ገና ስገባ አምሪ በታብሌት የሆነ ስዕል ያለበት ነገር እያነበበች "እሺ የኔ ማፍያ ትተኸኝ ሄድክ አይደል?" አለች።
ታብሌቱን እየተቀበልኳት "ምን እያነበብሽ ነዉ?" አልኳት።
"ባክህ 'ስላይድ' ነዉ። ግቢ የምንማርበት ነዉ።" አለችኝ።
ዘግቼ መለስኩላትና "ኡሚ አትጋብዘንም እንዴ?" አልኳት።
ከተቀመጠችበት እየተነሳች "አንተ እስከምትመጣ እየጠበቅንህ ነበር። መጥታለች። መኝታ ቤት ናት!" አለችኝና በደንብ እያየችኝ "ደሞ ጀለቢያህን አዉልቀህ በሱሪ የት ሄደህ ነዉ?" አለችኝ።
"እነሚኪ ጋር ሄጄ ነዉ!" አልኳት።
አምሪ እንደመሳቅ እያለች "ሀቢቤ ከዚህ በፊት የሰራኸዉ ወንጀል ከፀፀተህ ወንጀል ወደሰራህበት ቦታ መመላለስ አታብዛ! ድጋሚ ወንጀል ላይ ይጥልሀል!" አለችኝ። አምሪ ትሰልለኝ ይሆን እንዴ ብዬ መጠርጠር ጀምሬያለሁ። ወንጀል ወደሰራሁበት ቦታ እንደሄድኩ እንዴት አወቀች? ከነሚኪ ጋር ስላልኳት ይሆን? እኔንጃ!
.
አምሪ በግድ ሱሪዬን አስወልቃ ጀለቢያ አስለበሰችኝ። ሴት ያዘዘዉ ሆኖብኝ ጀለቢያ ለብሼ ከወ/ሮ ለይላ እና ከአምሪ ጋር ሰፈራችን ወዳለ ታዋቂ ሬስቶራንት ሄድን። አዝዘን እንደተቀመጥን አንድ ወንድና አንድ ሴት ወደ ሬስቶራንቱ ገብተዉ ወደኛ ጠረጴዛ መጡ። ሲቀርቡ ወንዱን አወቅኩት የኛን ቤት የተከራየዉ ሰዉዬ ነዉ። ሴቷ ሚስቱ መሰለችኝ። መጥቶ እኔን ጨበጠኝ። ልጅቷ ደግሞ እነአምሪን እያቀፈች ሰላም አለቻቸዉ። ልጅቷን ትክ ብዬ ሳያት ድንጋጤ መላ ሰዉነቴን ወረረዉ። አቀረቀርኩ። ሰሚራ ነበረች። የድሮ ፍቅረኛዬ! አንሶላ የተጋፈፍኳት! አግብታለች! ሲገርም! እንዴት ባልጠፋ ቤት የኛን ቤት ተከራዩ!? ከአምሪ እና ከወ/ሮ ለይላ ጋር አዉርተዉ እስኪጨርሱ ቀና አላልኩም። ሲሄዱ ቀና ብዬ አም
ሪያን አየኋት! እየሳቀች ነዉ። ከዚህ በፊት "የናንተን ቤት የተከራዩትን ሰዎች ታዉቃቸዋለህ ወይ?" ብላኝ ነበር። እማዬን ስናስታምም አምሪ የሰሚራን ፎቶ ከቁምሳጥኔ ዉስጥ አግኝታ አይታዉ ነበር። የሰሚራ ባል ይገባዉ የነበረዉን የሰሚራን ክብር እኔ እንደገፈፍኩት ቢያዉቅ ምን ይል ይሆን? ድንግል እንዳልሆነች ሲያዉቅ ምን ብሏት ይሆን? በራሴ ተሸማቀቅኩ።
.
በልተን እንደጨረስን ወደ ቤት ተመለስን። አምሪ ወ/ሮ ለይላ ክፍላቸዉ ሲገቡ ጠበቀችና "ሀቢቤ ልጅቷን አስታወስካት?" አለችኝ። በአዎንታ ጭንቅላቴን ነቀነቅኩላት። "እኔ እኮ ያየኀት መስሎኝ ነበር። ዛሬ ገና ነዉ እንዴ ያየኀት?" አለችኝ። ከሰሚራ ጋር ያደረግነዉ ሁሉ አይኔ ላይ ድቅን እያለብኝ "ኧረ ዛሬ ነዉ ያየኋት።" አልኩ።
"ምክንያቱን ባላዉቅም ብዙ ጊዜ ከባሏ ጋር ይጣላሉ።" አለችኝ። እኔ ግን ምክንያቱን መገመት አልከበደኝም።
ምንም በደሌ ጣራ ቢነካም ሰሚራን ይቅርታ ለመጠየቅ አሰብኩ። አምሪ ፍቅረኛዬ እንደነበረች ልትገምት እንደምትችል ግልፅ ነዉ። ከሷ ጋር ከእንስሳ በታች ሆኜ እንደማዉቅ አምሪ ብታዉቅ ምን ትለኝ ይሆን?
.
በነጋታዉ ከፌቪ ጋር ተቀጣጥረን ነበር። ግን አምሪ ወንጀል የሰራሁበት ቦታ መመላለሴ ወንጀል ላይ ሊጥለኝ እንደሚችል የነገረችኝ ሀቅ ስለሆነ ላላገኛት አሰብኩ። ደሞ ያመሰቃቀልኩትን ህይወቷን ለማስተካከል መሞከር አለብኝ። ለጥቂት ደቂቃ አግኝቼያት ለመመለስ አሰብኩና ጠዋት ወደ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ ኦፊስ ሄድኩ። ሀሳቤ ኦፊስ ሆኜ ልደውልላት ነዉ። ስገባ ፌቪ ፣ አብነት ፣ ከሪም ፣ ሚኪና አንድ የማላዉቃት ልጅ ክፍሉ ዉስጥ ተዘርረዋል። ሚኪና ያላወቅኳት ልጅ ተቃቅፈዉ ተኝተዋል። የሚኪም የሷም ሱሪ ወልቋል። ከሪም የአብነት ደረት ላይ ተመቻችቶ ተኝቷል። ፌቪ ሸሚዟ ቁልፉ ተከፋፍቶ ፀጉሯ ተንጨባሮ ተዘርራለች። ክፍሉ ዉስጥ የቢራ ጠርሙሶች ወዳድቀዋል። በፌቪ በኩል ትዉከት ትራሱን አጨማልቆታል። ክፍሉ በጣም በሚቀፍ ጠረን ታምቋል። እኔን ከነሱ ዉስጥ እንደዚህ ከመዝቀጥ ያተረፈኝን ጌታዬን አመሰገንኩት። ከክፍሉ ልወጣ ስል አብነት አይኑን እያሸ "እንዴ ሀቢቤ! ግቢ! ግቢ!" አለና ከሪምን ከደረቱ ገፍትሮ ቀሰቀሰዉ። ሁሉም ተነሱ። ፌቪ ተነስታ ሸሚዟን ቆላልፋ ወደኔ መጣች። ልትስመኝ ስትሞክር ከለከልኳት። "ኤጭ ሙድህ አይነፋም!" ብላ አልጋዉ ላይ ተቀመጠች። ሚኪና ልጅቷ ተነስተዉ ሱሪያቸዉን ለባበሱ። ሚኪ አይኑን እየጠራረገ "ሀቢቤ ተዋወቃት! አዲሷ ህይወቴ ናት!" አለኝ። ህይወቷን ሊቀማት ህይወቴ ሲላት አሳቀኝ።
ልጅቷ ፍልቅልቅ እያለች "ኤልዳና እባላለሁ" አለችና እጇን ዘረጋችልኝ። እጇን እያየሁ "ይቅርታ ይለፈኝ!" አልኳት።
ሚኪ እየሳቀ "ሀቢቤ ግን አክራሪ ሆነሻል!" አለ።
ፌቪ "ዉጡ ዛሬ ኦፊሱ የኔና የሀቢቤ ነዉ!" አለች።
ከሪምና አብነት የፈጣሪ ትዕዛዝ ይመስል ወዲያዉ ብድግ አሉ። ብሽቅ እያልኩ "ተቀመጡ! ምነዉ ለደህና ነገር እንዲህ በሮጣችሁ!" አልኳቸዉና ወደ ፌቨን ዞሬ "ክለብ አትዉጪ! አትጠጪ! አላልኩሽም ለምን ጠጣሽ?" አልኳት።
ፌቪ ፈገግ እንደማለት አለችና "ሀቢቤ ማስተካከል የማበላሸትን ያህል ቀላል አይደለም እኮ! በአንዴ እኔን ሁኑ ትላለህ እንዴ! ዛሬ አብረኸኝ ከተኛህ ልስተካከል! ትተኛለህ?" አለችኝ።
ንዴቴ እየተቀጣጠለ "አልተኛም!" አልኳት።
ፌቪ ከመቀመጫዋ ተፈናጥራ ተነሳችና "ገና ከመጀመሪያዉ ገብቶኛል! አታፈቅረኝም! አታስመስል! ያበላሸኸዉ እኔነቴ አሳዝኖህ ከሆነ ተወኝ! መመለስ የማልችላቸዉ ብዙ ነገሮቼን አሳጥተኸኛል! ሲፈልግህ የፈጣሪ በግ ሲሻህ የሰይጣን ፈረስ አድርገህ የምትጠፈጥፈኝ ጭቃ አይደለሁም!" አለችኝ። "ምናለ የፈጣሪ በግ ሳደርግሽ ከምትነቂ የሰይጣን ፈረስ ሳደርግሽ በነቃሽ" አልኩ በልቤ።
ፌቪ ተነስታ መጥታ "ደስ ሲልህ ልትተወኝ አትችልም!" አለችና ልትስመኝ ታገለች። ገፍትሬ አልጋዉ ላይ ወረወርኳት። እልህ እየተናነቃት ተንደርድራ ልትስመኝ ተመልሳ መጣች። በጥፊ አልጋዉ ላይ ዘረርኳት። እነሚኪ መሀል ገብተዉ ያዙን።
ፌቪ እያለቀሰች "ሀቢቤ አትተወኝ እንደ ድሮዉ ሁንልኝ!" አለች። ላስተካክላት ብል እራሴን ወደ ዝቅጠት ልመልስ ማለቴ እንደሚሆን ስለገባኝ ቤቱን ለቅቄ...?

😘#ይቀጥላል...

❥...........😘.......🍃🍃...................❥

😘🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

😘😘😘

ይ ቀ ጥ ላ ል
​​😘✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

😘#ክፍል_24

...🖍ወደ ቤት እየተመለስኩ በማይመለስ መልኩ ያበላሸኋቸዉን ህይወቶች አሰብኩ። ፌቪ ምንም የማታዉቅ የቤት ልጅ ነበረች። ዛሬ እኔ በለኮስኩት እሳት ክብሯን ተነጥቃ መጠጥ የሚሉት እርኩሰት ላይ ወደቀች። ትምህርቷን አቋረጠች። አሁን እኔ ማነኝ? ብዙዎችን ያቆሸሽኩ ንፁህ? አላዉቅም።
ወደ ሰፈር ስደርስ ሰሚራ ከሱቅ እቃ ገዝታ ስትመለስ ተገጣጠምን። ባላየ ልታልፈኝ ስትል "ሰሙ አንዴ ላናግርሽ!" አልኳት። ቆመች። ተጠጋኋት።
አንገቴን ደፍቼ "ሰሙ ዛሬ እንደትናንት አይደለሁም። ትናንት ባለማወቅ ህይወትሽን አመሰቃቅያለሁ። በአላህ ይሁንብሽ ይቅር በይኝ!" አልኳት።
ሰሚራ ዝም ካለች በኋላ እያለቀሰች "ሀቢብ ትናንት የገፈፍከዉ ክብሬ ሊመለስ የሚችል አይደለም። ባሌ ድንግል አለመሆኔን ካወቀ ጀምሮ በትንሽ ነገር በተጣላን ቁጥር እያነሳ ያሸማቅቀኛል። ሁሌም በሀፍረት ነዉ ኑሮዬ! በሰዉ ዘንድ እንዲህ ካሸማቀቀኝ አላህ ዘንድ እኔንጃ!" አለች። እንባዋ ፊቷን ሸፍኖታል። በራሴ ተሸማቀቅኩ።
ሳግ ድምፄን እያነቀዉ "ሰሚራ ለሁሉም ነገር ጥፋተኛዉ እኔ ነኝ።ህይወትሽን አበላሸሁ። ፀፅቶኛል። ሰላም እያጣሁ ነዉ። ቢያንስ ይቅር በይኝ።" አልኳት።
"አላህ ይቅር ይበለን።" አለችና እንባዋን እየጠረገች "እኔም ከፈጣሪዬ ምህረትን ፈላጊ ነኝ። ይቅር ብዬሀለሁ።" አለችና ባለሁበት ትታኝ ሮጥ እንደማለት እያለች ወደ ቤቷ ሄደች።
ዉስጤ በሰራሁት ወንጀል ሲደማ ተሰማኝ። ምን አይነት ጨለማ ዉስጥ ነበርኩ?
.
የተሰጠን እረፍት ሲያልቅ ወደ መርከዝ ተመለስኩ። መርከዝ ሀይማኖታዊ ትምህርት የምንማርበት ተቋም ነዉ። ወደ መርከዝ ስመለስ ዉስጤ ላይ ትልቅ አላማ ተፈጠረ። በመሀይምነቴ ያበላሸኋቸዉን ህይወቶች መጠገን ባልችልም በደንብ ተምሬ ንፁሀን እንዳይበላሹ መንገዱን ማሳየት! አዎን በጣም ማወቅ አለብኝ ፤ አዉቄም ህዝቡን ማሳወቅ! የኔ አይነቱ እንዳያጠፋቸዉ ሚስጥሩን ማዉጣት! ከተሳካልኝ ደግሞ አምሪን ማግባት!
.
ወደ መርከዝ ከተመለስኩ በኋላ ህይወቴ ሁሉ ትምህርቴ ሆነ። ከትምህርት ሰዓታት ዉጪ ሳይቀር ኡስታዞቹን እያስቸገርኩ ተጨማሪ ሰዓት የተለያዩ ትምህርቶችን እማራለሁ። የሁለተኛዉ መንፈቀ አመት ትምህርት ተጀምሮ ሁለት ወራት አለፉ። እሁድ ነዉ። በጠዋቱ የትምህርት ቤቱ ግቢ ዉስጥ ከተማሪዎች ጋር ሆነን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየሰራን ነዉ። ነስሩ ፑሽአፕ እየሰራ ያስቆጥረኛል። ከኔ እኩል ለመስራት እየተፍጨረጨረ ነዉ። እላዩ ላይ እጄን ጭኜ መሬት ላይ ጣልኩትና እየሳቅኩ ወደ መኝታ ክፍል ሄድኩ። ወደ መኝታ ክፍል እየሄድኩ መተላለፊያ ላይ ስደርስ አዳራሽ ከምንለዉ ክፍል በጣም በሚያምር ድምፅ ቁርዓን ሲነበብ ሰማሁ። አህመድ ነበር። ገና አስራስድስት አመቱ ነዉ። ቁርዓን ሲያነብ በጣም ያለቅሳል። አሁንም እያለቀሰ ነዉ። የአዳራሹን በር ከፍቼ ገባሁ። አህመድ እየተንሰቀሰቀ ነዉ። ጀርባዉን ስለሰጠ አያየኝም። አህመድ "አለም የዕኒለዚነ አመኑ አንተኽሸዓ ቁሉቡሁም ሊዚክሪላህ?" የሚለዉን የቁርዓን አንቀፅ እየደጋገመ እያነበበ ያለቅሳል። ሰዉነቴ ተንዘፈዘፈ ፣ አይኔን እንባ ሸፈነዉ። በእንባዬ ዉስጥ ብዥታ ይታየኛል። አህመድ ያነበበዉ የቁርዓን አንቀፅ ተቀራራቢ ትርጉሙ "እነዚያ በአላህ ያመኑ ሰዎች ለጌታቸዉ ግሳፄ ልባቸዉ የሚፈራበት ጊዜ አልደረሰምን?" የሚል ወቀሳ አዘል ተግሳፅ ነዉ።
ሰዉነቴ እየተንዘፈዘፈ "ደርሷል ጌታዬ!" አልኩ። ትናንት ሳልፈራ የተዳፈርኳቸዉ ወንጀሎች ሁሉ ፊቴ ተደቀኑ። አህመድ መንሰቅሰቁን ትቶ ዞሮ አየኝ። ሰዉነቴ ከብዶኝ እንሰቀሰቃለሁ። ከተቀመጠበት ተነስቶ መጣና አቅፎኝ መንሰቅሰቅ ጀመረ።
ተላቅሰን ስንጨርስ ልብሴን ለመቀየር ወደ መኝታ ክፍል ሄድኩ።
ላይመለሱ ያጠፋኋቸዉ የሰዉ ህይወቶች መረጋጋት ነሱኝ። ሰላም ፣ ሰሚራ እና ፌቨን! ህይወታቸዉን የቀማኋቸዉ ሚስኪን እንስቶች!...h

#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃...................❥

🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us share◉●••


━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━

​​​​. ♥️✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

♥️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

#ክፍል_25

...🖍የሀይማኖት ትምህርት ቤቱ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ህይወቴ ላይ የፈጠረዉ ለዉጥ ለኔ ብቻ ሳይሆን ለሚያስተምሩኝ ኡስታዞችም የሚደንቅ ሆኗል። ዛሬ ዘጠነኛ ወሬን በመርከዙ ዉስጥ አስቆጠርኩ። ከቁርአን ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆነዉን በቃሌ ሸምድጃለሁ። ከሱ በላይ ደግሞ በተለያዩ የሀይማኖቱ የእዉቀት ዘርፎች ላይ ያለኝ እዉቀት ተዓምር በሚመስል መልኩ መጥቋል። ዛሬም ያበላሸኋቸዉ ህይወቶች ያሳዝኑኛል። አምሪ እሁድ እሁድ ለመማር ስትመጣ ሰላም ሳትለኝ አትሄድም። አንዳንዴ ስትማር ግልፅ ያልሆነላትን እንዳብራራላት ትመጣለች። እኔ እሷን ማስተማሬ እያሳፈረኝም ቢሆን ለሷ በሚገባት መልኩ አስረዳታለሁ።
.
ዛሬ መርከዛችን የቤተሰብ ምሽት አዘጋጅቷል። ዝግጅቱ ለወላጆቻችን የምስጋና ደብዳቤ የምንፅፍበትና በተማሪዎች መካከል መፋቀርን የሚያመጡ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት ነዉ። በታዘዝነዉ መሰረት ደብዳቤ ለሀጂ ፃፍኩ። ፅፌ ስጨርስ ከስሩ "መልካሙን መንገድ እንዳሳዩኝ ፤ በመልካሙ ኑረዉ ዉዷን ጀነት ይግቡልኝ!" ብዬ ለኡስታዙ ሰጠሁት።
ደብዳቤ የመፃፍ ስነ ስርዓቱ እንደተጠናቀቀ ኡስታዙ ከመቀመጫዉ ብድግ አለና "እስኪ ይህን መድረሳ(ት/ቤት) ሳትቀላቀሉ ያደረጋችሁት ወይም የምታስቡት ከገባችሁ በኋላ የተዋችሁት ወይም የተቀየረ ሚስጥራችሁ ያልሆነን ነገር አጫዉቱን።" አለ። ወዲያዉ እጄን አነሳሁ። "እሺ ሀቢብ!" አለኝ። ከመቀመጫዬ ብድግ አልኩና "ትናንት ፈጣሪ በጣም ግፈኛ እና ፍትህ የማያዉቅ ይመስለኝ ነበር። እናቴ ስትሞት ከፈጣሪ ጋር መደባደብ ሁሉ አምሮኝ ነበር።" ስል ሁሉም ጮክ ብለዉ ሳቁ። ሳቃቸዉን ሲጨርሱ ቀጠልኩ "ግን ፍትሀዊ አይደለም ያልኩት ፈጣሪዬ መልዓክ የሚመስሉ ሶስት ሰዎችን ልኮ ማንንም እንደማይበድል አሳየኝ። ሀጂን የመርከዛችንን ባለቤት ከአባቴ በኋላ በምድር አባቴ የሆኑ ታላቅ ሰዉ አደረገልኝ። ሚስታቸዉናልጃቸዉም ብቸኝነቴን አስረሱኝ። ይኸዉ ዛሬ ከነበርኩበት የጨለማ ህይወት ተላቀቅኩ። ለከዚህ ቀደሙ ጌታዬ እንዲምረኝ ለምኑልኝ። ፈጣሪ ሁሌም ፍትሀዊ ነዉ። ከወሰደብን ይልቅ የሰጠን የተሻለ ነዉ። ምናልባት ቤተሰቦቼ በህይወት ቢኖሩ ዛሬ የሆንኩትን አልሆን ይሆናል። ለሁሉም አልሀምዱሊላህ!" አልኩና ተቀመጥኩ። ሁሉም ጮክ ብለዉ "አላሁአክበር!" አሉ።
ሁሉም ከተናገረ በኋላ ኡስታዙ የፃፍናቸዉን ደብዳቤዎች ለቤተሰቦቻችን እንደሚያደርስ ነግሮን ዝግጅቱ ተጠናቀቀ።
በነጋታዉ አምሪ ሰላም ልትለኝ ወደ መርከዝ መጣች። በእጇ ለሀጂ የፃፍኩትን ደብዳቤ ይዛለች። እየሳቅኩ "ማን ሰጠሽ?" አልኳት።
ጥርሷን ያጠረዉ ሽቦ እስኪታይ ድረስ ፈገግ አለች። ፈገግ ስትል ሽቦዉ ቀለሙ ተለየብኝ።
እያየኋት "አስቀይረሽ
ዉ ነዉ?" አልኳት። "አዎ" አለችና ደብዳቤዬ ላይ ሳፈጥ "አቢ ደብዳቤህን ስጦታ ሰጠኝ!" አለችኝ።
"ምን ይጠቅምሻል?" አልኳት።
"አላዉቅም!" አለችኝ። ትንሽ ካወራን በኋላ በትምህርቴ በደንብ እንድበረታ አደራ ብላኝ ሄደች።
አምሪ ሁለነገሯ ደስ ይለኛል። እዉቀቷ ፣ ብስለቷ ፣ ፈገግታዋ! ግርም ይለኛል። አንድ ሚስት ሊኖራት የሚገባዉ ሁሉ ያላት ይመስለኛል።
.
እነሚኪያስ እንደድሮዉ መርከዝ ድረስ እየመጡ መጠየቅ ትተዋል። ስለፌቪም የሚነግረኝ አላገኘሁም። አንዴ የመጡ ጊዜ ክለብ መዉጣት እና አብራቸዉ መጠጣት ህይወቷ እንደሆነ እና ከሪም ፣ አብነት እና ሚኪም ትምህርት እንዳቋረጡ ነግረዉኝ ነበር። የአረብ ሀገሩ ገንዘብ ህይወታቸዉን ሙሉ ያኖራቸዉ ይመስል በሱስ ተተብትበዉ ትምህርት ማቋረጣቸዉ አሳዝኖኛል። ሁኔታቸዉ እንዳላማረኝ ገብቷቸዉ ነዉ መሰለኝ እነሱም ወደኔ መምጣት አቆሙ።...

😘#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃...................❥

😘ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
😘 የማይፋቅ ስህት

😘ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

#ክፍል_26

...🖍ሰባተኛዉ ገፅ ላይ ደግሞ የተርጓሚዉ ማስታወሻ አለ። ከሱ ቀጥሎ ደግሞ የደስታ ሚስጥሮች የሚል አርዕስት አለ። ፀሀፊዋ ደግሞ ..." ስል አምሪ እየሳቀች "በቃ በቃ አንብበኸዋል ብቻ ሳይሆን ለምዶብህ ሸምድደኸዋል።" ብላ አቋረጠችኝ።
እየሳቅኩ ወረቀቱን ይዤ ወደ ድንኳኑ ሄድኩ። የአምሪ ስራ የሌለ ደንቆኛል። እሰራላታለሁ ስል ያገኘችዉን አጋጣሚ ተጠቅማ ሰራችልኝ! እብድ የሆነች ልጅ! የኒካህ ዝግጅቱ ተጠናቆ ሙሽራዉ ሙሽሪቷን ይዞ ሄደ። አምሪ ለታሪክ የሚተላለፍ ጉድ ነዉ የሰራችኝ! ወደ ትምህርቴ ተመልሼ ሶስት ቀንም ሳልቆይ የረመዳን ፆም ስለደረሰ ወደ ሰፈራችን መስጂድ ለማሰገድ ተመለስኩ። አሁን ትንሽ ፌስቡክ ላይ በምፅፋቸዉ ትምህርቶች ሰው እያወቀኝ ነዉ። በርግጥ ፎቶዬን ስለማልለጥፍ በአካል አያዉቁኝም። ስሜ ግን እየገነነ መጥቷል። በረመዳኑ ከብዙ የሀይማኖት መምህራን ጋር ያለኝ ትስስር በጣም ጠበቀ። ረመዳን ተጀመሮ በሁለተኛዉ እሁድ መስጂዳችን ዉስጥ የተዘጋጀ የስብከት መድረክ ላይ ስለጓደኝነት ለአስራአምስት ደቂቃ ያህል እንዳስተምር ተጋበዝኩ። ህዝብ በተሰበሰበበት የማስተምርበት የመጀመሪያዉ መድረክ ስለሆነ በደንብ ተዘጋጅቻለሁ። የመስጂዱ ኢማም ለአንድ ሰዓት የጉረቤት መብትን በተመለከተ ካስተማሩ በኋላ መድረክ መሪዉ ስለ ጓደኝነት እንዳስተምር ጠራኝ። መድረኩ ፊት ለፊት ሶስት ካሜራዎች ተጠምደዋል። ዝግጅቱ ላይ ላልተገኙ ሰዎች እና ዉጪ ሀገር ላሉ ኢትዮጵያዉያን ለማስተላለፍ ታስቦ ይመስለኛል። መድረኩ ላይ ወጥቼ በአረብኛ አላህን ካወደስኩና በነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) ላይ ሰላምታ ካወረድኩ በኋላ ንግግሬን ቀጠልኩ። "የተወደዳችሁ አማኞች፣ ከወንድም ከሴትም ያላችሁ የጌታችን ቅን ባሮች ሰላም በናንተ ላይ ይሁን! ነገ በትንሳኤ ቀን ለቅጣት ተዳርገዉ ከሚቆጩት ሰዎች መካከል አንዱ ማን እንደሆነ ታዉቃላችሁ? ጌታችን በተባረከዉ ቃሉ እንዲህ ይላል" አልኩና ድምፄን አሳምሬ የቁርዓኑን አንቀፅ አነበብኩ። ሁሉም አፉን ከፍቶ ያዳምጣል። ያነበብኩትን በአማርኛ መተርጎም ጀመርኩ። "በዚያ አስጨናቂ ቀን ለቅጣት ከሚዳረጉት ዉስጥ 'ወዮልኝ እገሌን ለምን ጓደኛ አድርጌ ያዝኩ? በርግጥ እዉነታዉን ካወቅኩ በኋላ አጠመመኝ።' የሚሉ አሉ። በምድር ላይ ከመልካምነታቸዉ በጓደኛቸዉ ግፊት የወጡ እና ቅጣት የተረጋገጠባቸዉ ሰዎች ናቸዉ። እስኪ ልጠይቃችሁ..." ስል የፌቨን ጓደኛ ፍቅር ትዝ አለችኝ። ፌቨንን አብረን እንድንተኛ ስጠይቃትና ፌቪ ሄዳ ለጓደኛዋ ለፍቅር ስትነግራት ፤ፍቅር ተይ ይቅርብሽ ብላ የፌቪን ክብር ከማትረፍ ይልቅ ክብሯን የምትነጠቅበትን የሶደሬ ጉዞ አመቻቸች። ምናልባት የፌቪ ጓደኛ ፍቅር መልካም ብትሆን ኖሮ ይቅርብሽ ብላ ባስተወቻት እና የፌቪም ህይወት እንዲህ ባልተቃወሰ ነበር።
ስብከቴን ቀጠልኩ "አዎ ልጠይቃችሁ! ጓደኛችሁ ማነዉ? መልካም ለማድረግ ስትሞክሩ የሚያዳክማችሁ ነዉ ወይስ የሚያበረታችሁ ነዉ? ንገሩኝ እስኪ መጥፎ ነገር ለማድረግ ስትሞክሩ መጥፎ ነዉ ብሎ ያስተዋችኋል ወይስ ያበረታታችኋል? ጓደኛችሁ በመልካም የሚያዛችሁና ከመጥፎ የሚከለክላችሁ ከሆነ እናንተ እድለኞች ናችሁ። በተቃራኒዉ በመጥፎ የሚያዛችሁና ከጥሩ የሚከለክላችሁ ከሆነ ግን የትንሳዔ ቀን 'ወዮልኝ ምናለ ጓደኛ አድርጌ ባልያዝኩት!' ብላችሁ ትፀፀታላችሁ። ዛሬ ስለጓደኛችሁ በደንብ አስቡ!" ብዬ ሌሎችንም የቁርዓን አናቅፅን አንብቤ ካስተማርኩ በኋላ ከመድረኩ ወረድኩ። ገና ተስተካክዬ ሳልቀመጥ ከአጠገቤ የተቀመጠዉ ኡስታዝ "ሀቢቤ ያለንበትን ተጨባጭ በደንብ የሚያስረዳ ዳዕዋ ነበር። የሚቀጥለዉ ሳምንት እኛ መስጂድም ዝግጅት ስላለ በፈለግከዉ ርዕስ ላይ ተዘጋጅተህ ብታስተምር ደስ ይለኛል።" አለኝ። ዳዕዋ ማለት ስብከት ማለት ነዉ። አመሰገንኩትና ግብዣዉን ተቀበልኩ።
.
ስድስት ሰዓት ተኩል አካባቢ የሚሰገደዉ የዝሁር ስግደት ተሰግዶ ሲያልቅ ከሀጂ ጋር ከመስጂድ ወጣን። መኪናዉ ዉስጥ እስክንገባ ድረስ ብዙዎች እየመጡ ያቅፉኝ እና ያመሰግኑኝ ጀመር። እንደምንም ሰውን አልፈን መኪናዉ ዉስጥ ገባን! አምሪ እና ወ/ሮ ለይላ ከሴቶች መስጂድ ከመጡ በኋላ ሀጂ መኪናዉን አስነስተዉ ወደ ቤት መሄድ ጀመርን። አምሪ እየሳቀች "ኡስታዝ ዛሬ በጣም ገራሚ ትምህርት ነዉ ያስተማሩን!" አለችኝ። ወ/ሮ ለይላ እየሳቁ "በቃ አምሪ ልጁ አሰግዶም አስተምሮም ሲወጣ በነገር ወጋ ካላደረግሽዉ አትረኪም አይደል?" አሏት።
ሀጂ እየሳቁ "ባይሆን አምሪ ልጠይቅሽ ጓደኛሽ ማነዉ? ከሀቢቤ ንግግር አልተማርሽም?" አሏት።
አምሪ እየሳቀች "እኔ ጓደኛዬ ሀቢብ ነዉ። እሱ ደሞ በመጥፎ አያዘኝም።" አለች። ሀጂና ወ/ሮ ለይላ ጮክ ብለዉ ሳቁ። መኪናዉ በነሚኪ ሰፈር ጋር ሲያልፍ ፌቨንን ከሚኪ ጋር ወደነሚኪ ቤት መግቢያ አካባቢ ቆማ አየኋት። በደንብ ስመለከታት ያየሁትን ማመን ከበደኝ። ፌቪ አርግዛለች! ሆዷ በጣም ገፍቷል። ሚስኪን ፌቨን! ከማን ይሆን? ትናንት ከኔ ጋር በፍቅረኛነት የጀመረችዉ ሴሰኝነት ዛሬ ለዚህ ሁሉ ኪሳራ ይዳርጋታል ብሎ ማን አሰበ? እወድሻለሁ የሚለዉ ቃሌ ከርካሽ እኔነቴ እንደወጣ መች አወቀች!? ወንድ ልጅ ያላገባትን ሴት እወድሻለሁ ካለ ይህ ንግግሩ ከስሜቱ እንጂ ከልቡ እንዳልሆነ መች ነገርኳት!? ከልቡ ከሆነ እንኳ የማህበረሰቡን እሴት ጠብቆ በፍቅር የመዛለቅ አቅም እንደማይኖረዉ መረዳት እንዴት ተሳናት? ዘላቂ ፍቅር እና መተሳሰብ ያለዉ ትዳር ዉስጥ ብቻ መሆኑን ቤተሰቦቿ ምነዉ ሳያስተምሯት? ወይኔ ፌቪ! የህይወቴ የማትፋቂ ስህተት!
.
በቀጣዩ ሳምንት በኡስታዙ ግብዣ መሰረት ዝግጅታቸዉ ላይ "ወጣቶቻችን የት ናቸዉ?" በሚል አርዕስት ተዘጋጅቼ ለመስበክ ሄድኩ። መስጂዱ ትንሽ ራቅ ያለ ነዉ። በሀጂ መኪና ከአምሪ እና ከወ/ሮ ለይላ ጋር ሆነን ሄድን። መስጂዱ ዉስጥ ስንገባ ለማስታወቂያ የሰሩትን ባነር ተመልክቼ ተገረምኩ። የኔም ስም ሰውን ለማጓጓት በሚመስል መልኩ ተፅፏል።
ዝግጅቱ ከተጀመረ በኋላ አንድ ታዋቂ ዳዒ(ሰባኪ) ወደ መድረኩ ወጥቶ ለአንድ ሰዓት ያክል አስተማረ። ከሱ ቀጥዬ እኔ ወደ መድረኩ ወጥቼ ማስተማር ጀመርኩ።...

#ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃...................❥

🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
😘👌ፍቅረኛ በጣም እንድቶደህ ወይም ፈቅሯ እንዲጨምር ለማድረግ መጠቀም ያለብህ ነገሮች💖

ሰሞኑን የፍቅረኛዬ በሃሪ በጣም ተቀይሮብኛል,ምን አድርጌያት ይሆን ለምን ይሆን እያልክ ከመስጋትና ከመጨነቅ እንዴት ፍቅረኛዬ ለእኔ ያላት ፍቅር ከቀን ወደ ቀን እንዲጨምር ማድረግ እችላለው ሚለው ሃሳብ ለይ ትኩረትህን ማድረግና መፍቴህ መፈለግ ብልህ ያሰኛል። እንሆ እኛም የፍቅረኛቹን መወደድ ከቀን ወደ ቀን ይጨምራሉ ብለን ያሰብናቸውን ልናቀርብላቹ ወደድን

💖💖ጥሩ ስሜት(special)እንደሆነችህ እንዲሰማት አድርግ
💖1.አድንቃት

የፍቅረኛ ትኩረት ወደ አንተ እንዲሆን ከፈለክ
ለእሷ እንደምታስብላትና እንደምትጨነቅላት ማሰወቅ ይኖርብካል እንዲሁም ደግሞ ትርጉም ያለው አድናቆትን ስጣት።
ትኩረትህን ወደ እሷ በማድረግ የለበሰችው ልብስ,የፀጉር ስታይሎ ቆንጆ እንደሆነ ንገራት።
ለምሳሌ የለበሽው ቀሚስ በጣም ያምርብሻል በጣም ወድጄዋለው ትላታለክ እሷ በጣም ተግረማልችህ ደስ ይላታል በማሃላቹ አሪፍ ሰሜት ፈጠራክ ማለት ነው።

💖2.ውለታ ዋልላት

ሌላኛው ፍቅር እንዲጨምር የሚያደረገው ነገር ውለታ ነው።
ምሳ መጋበዝ,መዝናኛ ቦታ መውሰድ,ከስራ ደክሞት ከመጣች ቤቱን አስተካክሎ መጠበቅ ብቻ ላይፏ ቀላል እንዲል አድርግህ በቻልከው አቅም እሷን ለመርዳት ወደ ኋላ እንዳትል ግን ይሄን ስል ከልክ እንዳያለፍ መክንያቱም መናናቅ ሊመጣ ስለሚችል just እሷ ከዚህ በፊት ምታደራግልህን አድራግላት።

💖3.ለፍላጎቷና ለዓላማው ደግፋት ከገኗ እንደሆንክ አሳይት

ፍቅረኛክ ጥሩ ስሜት እንዲሰማት ከፈለክ
በደንብ ተንካባከባት የእሷን ጉዳይ እንደራስክ ጉዳይ እየው ስኬታማ ሆና መየት እንደምትፈለግ አሳያት።
ለምሣሌ አዲስ ስራ እየፈለገችህ ከሆን አሪፍ ኢንተረቪውና ስለ ስራው መረጃ ሰብስብለት።
የእሷ ጉዳይ እንሚያስጨንቅህ አሳይት።
ከተናደደችህ ምቾት እንዲሰማት አድራግ እና ለማውራት ዝግጁ ስትሆን ስለ ጉዳዩ አዋራት።
በደስታዋ ቀን አብራሃት ተደሰት መልካም ምኞትህን ንገራት።

💖4.ስለ ላይፏ ጠይቃት

ከልጅነቶ አንስቶ ከአንተ ጋር ግንኙነት እሰከጀመራቹበት ድረስ ያለውን በይህወቶ ያገጠማትን ገጠመኞች ስለምቶደው ነገር መጠይቅ በደንብ ከመተዋወቅ በሻገር ለጥንቃቄም ይጠቅማል ምክንያቱም በደንብ ስትተዋወቁ በመሃላቹ ግጭት የመፈጠር ዕድል በጣም ይቀንሳል።
በማንነቶ በጣም እንደምቶኮራባት ስለእሷ በደንብ ማውቅ እንደምትፈልግ አሳያት።
ስለራሷ ስትነግራህ ትኩረትህን ወደእሷ አረገህ አይን አይኖን እያየህ ስምት።

💖5. ፍቅርህን አሳያት

ብዙ ወንዶችህ የሴትን እጅ መያዝ አይወዱም ወይም አለተለመደም ግን እጆን አልያስካትም ማለት ደግሞ አቶዳትም ማለት አይደለም።
ስታወሩ እጅህን ትከሻዋ ለይ አድርግ ,ፀጉሯን ነካካው ብዙወቹ ይወዱታል።
ደሞ ሁሌም አይደለም አንደንዴ just በወሬ መሃል ነው ነካ ታደርገታለህ
ሰዎች በተሰበሰቡበት እንዳትስምት ይልቅ ልክ ስትገናኙና ስትለያዩ ወይም ባይ ስትባባሉ ሳማት ይሄ አሪፍ ነው ይወዱታል።

💖6.ማዳመጥ

አሪፍ የሚባሉት ውንዶችህ የማድመጥ ክህሎታቸውን ሲያዳብሩ ሌሎችህ ወንዶች ደግሞ ብዙም ቦታ አይሰጡትም ግን ማድመጥ በፍቅር ግኑኝነት በጣም ጠቃሚ ነገር ነው።
ስታወረክ በደንብ አድምጣት ቃላቶቿን ስማ,ሊረብሽ ሚችል ነገር ካለ አስወግድ,አይኖን እይት።
በፋፁም እንዳታቆርጣት ወይም ችግሯን ለመፍታት አትሞክር just ለመረዳትና ለማድመጥ ብቻ ሞክር።
እንዲህ መድረግህ ለአንተ ጥሩ ነጥብ ያስገኝልካል።
አውራታ ስትጨርስ ጥያቄ ጠይቃት ስሜቷን ለመረዳት
ያህል ምክር ከጠየቀችህ መጀመሪያ ያወራችው እውነት መሆኑን አረጋግጥ።
ሰልክህን አስቀምጥ በፍፁም እያወራችህ አትንካ
እያወራችህ ስልክ መትናካካ ከሆን እብድ ነው ሚያደርጋት።

ይቀጥላል


join& share @pclovee

ሀሳብና አስተያየት

Personal question @jaden_36
​​​​. ♥️✿የማይፋቅ ስህተት✿♥️

♥️ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ♥️

●▬ተከታታይ ልቦለድ▬●

#ክፍል_27

...🖍ትንሽ ካስተማርኩ በኋላ "...በእርግጠኝነት ቤት የምታከራዩ ሰዎች በመካከላችን ትኖራላችሁ አይደል? ቤታችሁን ለማን ነዉ ያከራያችሁት? ወጣቱ የሚባልግበት ቤት የናንተ ቤት ላለመሆኑ እርግጠኞች ናችሁ? ወይስ ስለ ገንዘባችሁ እንጂ ስለማህበረሰቡ ጉዳያችሁ አይደለም? በየሰፈሩ ኦፊስ ተብለዉ የሴቶቻችን ክብር የሚገፈፍባቸዉ ቤቶችን ማነዉ ለባለጌዎች የሚያከራየዉ? እናንተ አይደላችሁም? ስለዚህ ልጆቻችን ተበላሹ ከማለታችሁ በፊት ቤታችሁን አፅዱ! ለብልግና ቤታችሁን አከራይታችሁ የናንተ ልጅ ጨዋ ልትሆን አትችልም! ከልጆቻችሁ ጋር በግልፅ ተወያዩ። ልጃችሁ አንድ ሴት አይቶ ከወደደ ወይም አይታ ከወደደች በግልፅ መጥቶ እንዲነግራችሁ የሚያደርግ ማንነት ይኑራችሁ። ልጆቻችሁን ትዳርን አክብዳችሁ እያሳያችሁ ለዝሙት አታመቻቿቸዉ። ሀብታሞች ወጣቱን አጋቡ! በገንዘብ ደግፉ!..." ብዬ የማህበረሰቡ ወቅታዊ ችግር ናቸዉ ብዬ ያሰብኳቸዉን አርዕስቶች ዳሰስኩ። ከመድረኩ እንደወረድኩ ከፊት ለፊት ተቀምጠዉ የነበሩ አንድ ሽማግሌ መጥተዉ ግንባሬን ሳሙኝ። ከመስጂዱ ስንወጣ ሰው ሰላም ለማለት ከበበኝ። ሀጂ በግርምት ቆመዉ ያዩኛል። ሰላም ብዬ ስጨርስ ሌላ ሰዉ ሳይዘኝ ፈጠን እያልኩ ወደ ሀጂ መኪና ገባሁ። አሁን በጉጉት የምጠብቀዉ የአምሪን ነቆራ ነዉ። አምሪናወ/ሮ ለይላ መኪናዉ ዉስጥ እንደገቡ ሶስታችንም አምሪ ምን እንደምትል ለመስማት ወደሷ ዞርን። አምሪ ወዲያዉ "ሳታገባ አግቡ ምናምን ትላለህ አይደል?" አለች። ሁላችንም ሳቅን። ሀጂ ትንሽ እንደማሰብ አሉና "ሀቢቤ ግን ታዋቂነቱ ሲበዛ ፈተናዉ ከባድ ነዉ። ኒካህ ማሰር አለብህ። ቆይ ጥሩ ልጅ እፈልግልሀለሁ።" አሉኝ። ዝም ብዬ ሳቅኩኝ! ልጃቸዉ እያለች የምን ፍለጋ መዉጣት ነዉ!? ሀጂ አምሪን እያዩ "ምነዉ ልክ አይደለሁም እንዴ?" አሏት። አምሪ እያየችኝ ሳ
ቋን ለቀቀችዉ። ስትስቅ አሳቀችኝ። ሀጂ "ምን ያስቃችኋል? እዉነቴን እኮ ነዉ።" አሉ። ወ/ሮ ለይላም ሀሳባቸዉን ደገፉ። እኔና አምሪ ዝምታን መረጥን።
.
ቤት ገብተን ትንሽ እንደቆየን አምሪ "ሀቢቤ ፌመስ ሆነሀል!" አለችና በስልኳ ስለኔ ፌስቡክ ላይ የተፃፉ ነገሮችን አሳየችኝ። ሳያቸዉ ዛሬ ካስተማርኩት ንግግሬን ቆርጠዉ በፎቶ መልክ ሰርተዉ ከስሩ ወጣቱ ዳዒ ሀቢብ ከማል ብለዉ ፅፈዉበታል። ዳዒ ማለት ሰባኪ ማለት ነዉ። የባለፈዉ ትምህርቴንም የለቀቁ ታዋቂ ገፆችን አምሪ አሳየችኝ። በራሴ የፌስቡክ አካዉንት ስገባ 20,000 ተከታይ አፍርቻለሁ። ገረመኝ።
.
ረመዳኑ ሊያልቅ ሲል ሀጂ ማታ ላይ በተሰበሰብንበት በግልፅ የሴት ምርጫዬን ጠየቁኝ። እየተሽኮረመምኩ "እርሶን ደስ እንዳልዎት" አልኳቸዉ። በጣም ጨነቀኝ! ሀጂ ሌላ ሴት አምጥተዉ ልዳርህ ካሉኝ ምን ሊዉጠኝ ነዉ? በነጋታዉ አምሪን "ምን ይሻላል?" አልኳት። ለሀጂ እንድንነግራቸዉ ነገረችኝ። የዛኑ ቀን ማታ ሀጂን ልናናግራቸዉ ወሰንን። ማታዉን ሁላችንም ባለንበት ፍርሀት እየተናነቀኝ "ሀጂ የሚድሩኝን ሴት እኔዉ ብጠቁሞት ምን ይመስልዎታል?" አልኳቸዉ።
ሀጂ ፈገግ ብለዉ "እንደዉም የወደድካት ካለችማ ስራም ይቀልልናል።" አሉኝ።
ልነግራቸዉ ሳመነታ ሀጂ አንዳች ነገር እንዳስታወሱ ነገር ፊታቸዉን ቀያየሩና "ቆይ ከሱ በፊት እጠይቅሀለሁ እያልኩ ረስቼዉ የነበረ አንድ ነገር አለ። ከሁለት አመት በፊት ወደ መርከዝ ስትገባ ስልክ አልያዝክም ነበር። ከዛም ዉስጥ ስልክ ይዘህ ተገኝተህ ተቀምተሀል። ማነዉ ስልክህን የሰጠህ? መችስ አትዋሸኝም።" አሉኝ። ለሀጂ አምሪያ ናት ያመጣችልኝ ማለት ይከብዳል። ለኔዉ ብላ ስልክ ባቀበለችኝ እሷን ማስጠቆር አልፈለግኩም።
"ሀጂ ይሄ ጥያቄ ይቅርብኝ!" አልኳቸዉ።
ሀጂ እንደመቆጣት እያሉ "ማነዉ እኔ እንድትስተካከል ስጥር ስልክ እየሰጠ ከትምህርትህ ያዘናጋህ? ንገረኝ!" አሉ። አምሪ ስልኩን የሰጠችኝ የለመድኩትን በአንዴ መተዉ እንደማልችል ተረድታ እንጂ ልታዘናጋኝ አይደለም።
ዝም ስላቸዉ "ሀቢብ ንገረኝ! አሊያም እንጣላ!" አሉኝ።
አምሪን አየኋት። ከአባቷ ጋር እንድትጣላማ ምክንያት አልሆንም።
የሞት ሞቴን "ሀጂ በቃ ከኔ ጋር ቢጣሉ ይሻላል ልነግርዎት አልችልም።" አልኳቸዉ።
"ከምር? እርግጠኛ ነህ አትነግረኝም?" አሉኝ።
"ሀጂ ይቅርታ! መናገር አልችልም። ለእርስዎም መልካሙ ባልነግርዎት ነዉ።" አልኩ።
ሀጂ ደግመዉ "እርግጠኛ ነህ?" አሉኝ። እራሴን አጠንክሬ "አዎን ይቅርታ ሀጂ!" አልኳቸዉ።
ሀጂ "እንግዲያዉስ ..." አሉና በረዥሙ ተንፍሰዉ በድጋሚ "እንግዲያዉስ" አሉና ዝም አሉ።
አምሪ አላስቻላትም መሰለኝ "አቢ በቃ ከዚህ በላይ አታስጨንቀዉ!" አለች።
ሀጂ ዝም ብለዉ አዩኝ! ምን ይሉኝ ይሆን? እንቆራረጥ ይሆን? በጣም ፈራሁ። ከነሱ በቀር ምድር ላይ ማን አለኝ? አይ ዱኒያ! ሁሉ ነገርሽ ፈተና! አልቅሰን ሳንጨርስ ደስታ! ስቀን ሳንጠግብ ጭንቀት! ግራ የገባሽ አለም!...

😘 ይቀጥላል...

❥..................🍃🍃...................❥

🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳

,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
••●◉Join us @pclovee
😘ሰውን እንደ ሀገር.....
_
((በተመልካች ጥያቄ መሰረት የተደገመ...😂))
.
.
እግሬ ልራመድ ብቻ
እጄም ልዳብስ ብቻ
ጆሮዬም ላድምጥ ብቻ
አፌም ልጎረስ ብቻ
ጥርሴም ልሳቅ ብቻ
ፀጉሬም ልበጠር ብቻ
ኑሮን ካዩት በኀላ ብቻ ለብቻ
እግሬና እጄ በአንድነት ጎዳና ነጎዱ
ጆሮዬና ምላሴ በእርቅ ኮሚቴ ሰላም አወረዱ
አፌ ከጥርሴ ጋር
በፓናል ውይይት ሁለት ቀን መከረ
ፀጉሬ ብቻ
የመዋሃድ ቀመር ሳይገባው አደረ
===========
ከአካሎቹ(ከአጋሮቹ) ጋራ
የአብሮነትን ሀሳብ እያቀነቀነ
ተላጭቶ ሲቀመጥ፣ሀሳብ እያፈነ
የማያልፉት የለም እያለ ዘፈነ
===========
እናም....
ልምከርህ ፀጉሬ አትሁን መደ-ነስ
ዛሬ ተደምረ ነገ አትቀነስ
አካል ክፍል ሆነ
ፀጉር ነፃ አውጪ(ፀ.ነ.አ) የሚል ግንባር ፈጥረ ብታመጣ
ሰውነት ይኖራል..በራስ ቅል መላጣ
==========


መደ-ነስ=(መደ)መር ና መቀ(ነስ)

ሳሙኤል አለሙ


@pclovee
ፍቅር እና ሳቅ😂 via @like
😘👌ፍቅረኛ በጣም እንድቶደህ ወይም ፈቅሯ እንዲጨምር ለማድረግ መጠቀም ያለብህ ነገሮች💖 ሰሞኑን የፍቅረኛዬ በሃሪ በጣም ተቀይሮብኛል,ምን አድርጌያት ይሆን ለምን ይሆን እያልክ ከመስጋትና ከመጨነቅ እንዴት ፍቅረኛዬ ለእኔ ያላት ፍቅር ከቀን ወደ ቀን እንዲጨምር ማድረግ እችላለው ሚለው ሃሳብ ለይ ትኩረትህን ማድረግና መፍቴህ መፈለግ ብልህ ያሰኛል። እንሆ እኛም የፍቅረኛቹን መወደድ ከቀን ወደ ቀን ይጨምራሉ…
😘የተሻለ ፍቅረኛ ሁን💖

💖7.አራዳ ሁን

ፍቅርኛ ለአንተ ያላት ፍቅር እንዲጨምር በጣም አራዳ መሆን ይኖርብካል ወይም አራዳ መሆን ለይ ትኩረትህን ማድረግ አለብህ።
ክብርና ትኩረት ስጣት ለምሣሌ
👌የመኪና በር ክፈትላት የካፌም ሊሆን ይችላል.
👌ከመቀመጧ በፊት ወንበር ሳብላት.
👌ብርድ ከሆነ ኮትህን አልብሳት.
አታስብ እራድን ማለት just ለፍቅረኛ ክብራ መስጠትና በደንብ treat ማድረግ ነው.ይሄን ስታደርግ የእውነት በጣም ትወድሀለች💖💖

💖8.ተግባቢ ሁን

ብዙ አፍቃሪወች መግባባት ለይ ብዙ ችግር አለባቸው
እንም በፍቅረኛ ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን ከፈለክ ሀሳብህን ሰታደብቅ ግልፅ በሆነና በሚያምር አገላላፅ መናገር ይኖርብሃል.
እንዴት ሳትበሳጭ ማግባባት እንዳለብህ ማወቅ ይኖርብሃል.
የፈለከውን ሳታገኝ ስትቀር ከመናደድ ይልቅ እንዴት አባብለክ ማግኘት እንደምትችል አስብ.
timing
ስታወራት timing ግድ ነው በጣም ከደከማት ምንም ባታወራ ይመረጣል ጥሩ ስሜት ለይ ስትሆን አውራት.

የመግባባት አቅም በጣም እየጨመረ ከመጣ የመወደድ ዕድልህም በዛው ልክ ይጨምራል።

💖9.ጊዜህን ስጣት

ግንኙነታቹ እንዲጠነክር በቂ ጊዜ ያስፈልጋቿል
ጊዜ መስጠት ማለት ደግሞ 24/7 ከእሷ ጋር መሆን አይደለም ለእሷም ከጓደኞቿ ከቤተሰቧ ጋር ምትሆንበት በቂ ጊዜ ልሰጣት ይገባል።

💖10.ነፃነት ስጣት
የእሷን ጊዜና ሰዓት እንዳትሻማት ከጓደኞቿ ጋር እንድትዝናና ያለምንም ቅናት ፍቀድላት በየአምስት ደቂቃ እየደወልክ አታስጨንቃት ጊዜ ስጣት እየደወልክ መታስጨንቃት ከሆን ለእሷ እምንት እንደሌለክ ታስባለች ፍቅሯም ሊቀንስ ይችላል።
ግን ደግሞ ማታስጨንቃት ከሆን በራስ መተማማንክን ታደንቃልህለሀለች ሴቶች ደግሞ በራስ መተማማን ያለው ውንድ 99% ይወዳሉ።

💖11.ቤተሰቧቿንና ጓደኞቿን አክብርለት

ቤተሰብና ጓደኞቿ ለእሷ በጣም ጠቃሚ ናቸው ምንለባት ልቧን ለማገኝት ቁልፍ ሊሆኑ ይችላሉ።
ሰለእነሱ ጠይቃት ሰላምት አቅርብላቸው ጥሩ አመለካከት ይኑራክ.
ይሄን ካደረክ ስለአንተ በኩራት ታወራለችህ ምርጫው የአንተ ነው ።
ፍቅረኛክ ከጓደኞቿ ጋር ጌዜ እንድታሳልፉ ከጠየቀችህ እሺ ማለት አለብህ ይሄ ለአንት በጣም ጥሩ ነው ተፅኖ መፍጠር ችለሃል ማለት ነው።





join&share @pclovee
@pclovee


ሀሳብና አስተያት @jade_36

ጥይቄ @jaden_36
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ተመልሰን መተናል ስለተፋንባችሁ ይቅርታ አርጉልን🙏🙏🙏
​​💋💋በቃ እወድሻለሁ💋💋
┉┉✽̶»̶̥🌹🌹»̶̥✽̶┉┉

ለምን አትበይኝ ምክንያት የለኝም
ፍቅር ስሜት እንጂ ሰበብ አይመስለኝም
ብቻ እወድሻለሁ መውደዴ ጥልቅ ነው
ፍቅርሽ ለእኔነቴ የልብ ዙፋን ነው
ህያው የምሆነው አንቺን በማፍቀር ነው
ጅልነት አይደለም ሁሌ አንቺን ማለቴ
ሞኝነት አይሆንም ለፍቅር መክሳቴ
ጅልነት አይደለም እራሴን መስጠቴ
በቃ አንቺን መውደድ ነው ደስታ መደሰቴ
ውለታን ፈልጌ ውደጂኝ አላልኩም
ፍቅር ስጠሁ እንጂ ምላሽ አልፈለኩም
በቃ እወድሻለው ማለቴን አልተውኩም

አዎ አፈቅርሻለው አዎ እወድሻለሁ
ፍቅርቅር አድርጌህ ሁሌም እኖራለሁ
አንቺን በመውደዴ እፎይታ አገኛለሁ
አንቺን እየወደድኩ ሀሴት አደርጋለሁ
በፍቅርሽ ውቅያኖስ ስዋኝ እኖራለሁ
አንቺ ካለሽልኝ ሙሉ ሰው እሆናለዉ
@pclovee
2025/06/28 06:51:56
Back to Top
HTML Embed Code: