Telegram Web Link
የ12ኛ ክፍል ፈተናን በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተማሪዎች  የሙከራ ፈተና ተሰጠ፡፡ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም
++++++++++++++++++++++++++++++
የዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ ይታወቃል ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው  በበይነ መረብ እና በተለመደው የወረቀት ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በመሆኑም ፈተናቸውን በበይነ መረብ ለሚወስዱ ተማሪዎች የሙከራ ፈተና ሰኔ 17/2017 ዓ.ም እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ይህም ተፈታኞች በበይነ መረብ መፈተንን እንዲለማመዱ እና  ምንም አይነት ችግር ሳይገጥማቸው ፈተናቸውን በተሳካ ሁኔታ ለመውሰድ የሚያችላቸውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው በበይነ መረብ የመፈተን አቅም ዝግጅት የሚገመገምበት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስለ ዩኒቨርሲቲያችን ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ።
Website: www.aastu.edu.et
Facebook: http://facebook.com/aastu.edu.et
Telegram: www.tg-me.com/pir2011
Email: [email protected] | [email protected]
YouTube: youtube.com/@aastu_official7418
X (formerly Twitter): x.com/aastu_addis
Discussion held at CSSH, AASTU June 24/2025.

The College of Social Sciences and Humanities (CSSH) at Addis Ababa Science and Technology University recently held a productive discussion with its dedicated faculty. As we approach the end of the academic year, it was essential to reflect on our experiences, said Dr. Befekadu Lemma, Dean of the College.
The meeting focused on identifying opportunities, addressing challenges, and directing the way forward. The participants praised the College’s achievements while also giving significant attention to the areas that need improvement. They stated “Together, we are committed to making CSSH even stronger!”

For more information about AASTU, reach us via,
Website: www.aastu.edu.et
Facebook: http://facebook.com/aastu.edu.et
Telegram: www.tg-me.com/pir2011
Email: [email protected] | [email protected]
YouTube: youtube.com/@aastu_official7418
X (formerly Twitter): x.com/aastu_addis
Training Delivered on UNISA Ethiopia Regional Learning Center Library Outreach Program, June 28/2025.
A training session on the UNISA Ethiopia Regional Learning Center Library Outreach Program for Partner Libraries was successfully conducted. This initiative aims to enhance the capacity of partner libraries, particularly the Addis Ababa Science and Technology University (AASTU) Library, to provide responsive, user-centered services in an increasingly dynamic information landscape.
The half-day training offered valuable opportunities for professional development, knowledge exchange, and practical skill-building. Participants focused on improving service delivery and reinforcing the role of libraries as vital hubs of academic excellence.
For more information about AASTU, reach us via,
Website: www.aastu.edu.et
Facebook: http://facebook.com/aastu.edu.et
Telegram: www.tg-me.com/pir2011
Email: [email protected] | [email protected]
YouTube: youtube.com/@aastu_official7418
X (formerly Twitter): x.com/aastu_addis
ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ/ም
ማስታወቂያ
ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ

የ 2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እንዲሁም አገልግሎት ፈላጊ፡- 

1. ከፈተናው እና ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ተቋሙ ባጅ ከተሰጣችው መምህራንና ሰራተኞች በስተቀር ከሰኔ 21/2017 ዓ.ም  ጀምሮ እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው::
  2. ባጅ የተሰጣችሁ መምህራንና ሠራተኞችም ማንኛውንም ዓይነት ተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) ይዞ ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው፤
  3. በግቢ የምትኖሩ የተቋሙ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸሁ በመኖሪያ አቅራቢያ በሚገኙት በሮች ብቻ እንድትጠቀሙ እያሳሰብን ተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) መያዝም ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን፤ ስትወጡ እና ስትገቡም የተዘጋጀላችሁን ባጅ ማንጠልጠል እንደሚኖርባችሁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
  5. ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ ተማሪዎች በሚንቀሳቀሱበት የግቢው ክልል መንቀሳቀስ  ፈፅሞ የተከለከለ  ነው፣
  6. ፈተናው እስኪጠናቀቅ ሁሉም ቤተ-ሙከራዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት የማይሰጡ መሆኑን እገልፃለን፤
  7. ከየኒቨርሲቲው አገልግሎት የምትፈልጉ የውጭ ባለ ጉዳዮች ቅጥር ግቢ መግባት ስለማይፈቀድ ጉዳያችሁን በር ላይ ለሚኖሩ የፀጥታ አካላት መልእክት በመተው እንድተመለሱ እያሳሰብን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለፈተናው መሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት  በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
                 የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናቸውን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለሚወስዱ ተማሪዎች ገለፃ ተደረገ ሰኔ 22/2017 ዓ.ም
++++++++++++++++++++++++++++++++++
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሃገር አቀፍ ደረጃ ከሰኔ 23-ሃምሌ 8/2017 ዓ.ም በተለያዩ ተቋማት ይሰጣል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን በበይነ መረብ እና በወረቀት ለሚወስዱ ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ ተሰጥቷል፡፡
በገለፃው ተፈታኞች በፈተና እና በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት መደረገ የሚገባቸው እና መደረግ የማይገባቸውን ተግባራት ግንዛቤ  ኖሯቸው ፈተናቸውን በተሳካ ሁኔታ እንዲያጠናቅቁ የሚረዳ ነው፡፡
በዚህም የመጀመሪው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሰኔ 23/2017 ዓ.ም ፈተናቸውን የሚጀምሩ ይሆናል፡፡

ለሁሉም ተፈታኞች መልካም ፈተና !

ስለ ዩኒቨርሲቲያችን ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ።
Website: www.aastu.edu.et
Facebook: http://facebook.com/aastu.edu.et
Telegram: www.tg-me.com/pir2011
Email: [email protected] | [email protected]
YouTube: youtube.com/@aastu_official7418
X (formerly Twitter): x.com/aastu_addi
2025/07/14 17:27:42
Back to Top
HTML Embed Code: