Telegram Web Link
መልካም ዜና!

14ኛ ዙር የስብዕና ግንባታና የሳይኮሎጂ ስልጠና (Life Improvment Training)  ሀምሌ 8 ሊጀምር ነው።

ስልጠናው ላለፉት 6 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙ መቶዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ተግባራዊ ስልጠና ነው።


🔖የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ፈልጎ ማግኘት
🔖ተግባቦትና በራስ መተማመን
🔖ስኬታማ የሕይወት ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
🔖የስሜት ብልህነት
🔖ፍርሀት ማሸነፍና፣ ድብርትንና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
🔖ስራ ፈጠራና የገንዘብ አስተዳደር
📖ሳይኮሎጂ/ሥነልቦናን መረዳት
📖የሥነልቡና ቀውስና መፍትሄዎች መረዳት


ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን በስራ ቀናት (ከሰኞ - አርብ) በጠዋት በከሰአትና በማታ እንዲሁም ቅዳሜና እሑድ ይኖረናል።

በአንድ ፈረቃ ጥቂት ብቻ ቦታ ስለሆነ ያለን ቀድመው ይመዝገቡ።
ለመመዝገብ / መረጃ ለማግኘት 0960865151 ወይንም 0912664084 ይደውሉ።

🏠 አድራሻ :- ቦሌ ብራስ፣ መገናኛ ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት፣ ዛሙ ፈርኒቸር ህንፃ ቁጥር 206


🖼🎁ለመለወጥ መወሰን እንጂ ሰበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!! ሕይወትዎን ለመቀየር አሁኑኑ ይወስኑ!
ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ

@psychoet
7👏1
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷‍♂
Photo
#ይሉኝታ
እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ይነበብ

#ይሉኝታ_ምንድን_ነው?
ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት ነው፡፡

#የይሉኝታ_መንስኤዎች
✿ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት

✿በራስ መተማመን ማነስ

✿ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ

✿የውስጥ መረጋጋት ከሌለን

✿አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ

✿ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡- በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ

#ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች

✿ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት

✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?

✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ

✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ

✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ

✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር

✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር

✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል

©zepsychology

ይሉኝታን ለማስወገድ ስልጠናዎቻችንን ለመውሰድ 0912664084 ይደውሉ
6👏1
💪በራስ መተማመንን ማጎልበት💪
Developing Self Confidence

በራስ መተማመን ማለት ሰው ባለው ችሎታ፣ አካላዊ ውበትና ሁለንተናዊ ማንነት አለመፍራት እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ራስን መቀበል ማለት ነው፡፡ ትእቢት ፣ ትምክህት፣ ያልተገባ አውቃለሁ ባይነት እና ከመጠን ያለፈ ድፍረት በራስ መተማመን አይደለም።

በራስ መተማመንን የሚያጎለብቱ ብልሀቶች

🔥 ራስዎን ከሌሎች ጋር አለማነፃፀር።

🔥 ያለዎትን ክህሎት እና ድክመት መለየት።

🔥 የአካላዊ ገፅታ ውበትን መጠበቅ ደግሞም የሰውን ትኩረት ከልክ ባለፈ ሁኔታ የሚስቡ ጌጣጌጦችንና ሜካፖችን አለመጠቀም።

🔥 ጥሩ እና ምቹ አለባበስ መልበስ።

🔥 ነቃና ቀልጠፍ ብሎ መራመድ ።

🔥 በሰው ፊት ሀሳብዎን መግለፅ ሲኖርብዎ ቀድመው በቂ ዝግጅት ማድረግ።

🔥 መልካም በሆነ የህይወት እንቅስቃሴ የበኩልዎን አስተዋፅዖ ማድርግ።

🔥 ጥሩ የሚሰሩ ሰዎችን ማድነቅ/ ማበረታታት።

🔥 ሰዎች የተቃወሙዎት ወይም የናቁዎት ሲመስልዎ በእርጋታ ምላሽ መስጠት።

🔥 ሰዎች ስህተትዎን ሲነግሩዎ በቀና ማየት(ስለሚጠሉኝ ነው አለማለት)።

🔥 እርዳታ ሲያስፈልግዎ ያለፍርሀት መጠይቅ።

🔥 ሰአት ማክበር።

©በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት
YouTube: Dink Mikir

#Like #Share በማረግ ለሌሎችም እናስተምር

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
www.tg-me.com/psychoet

በቀጣይ ሳምንት የሚጀምረውን ስልጠናችንን ለመካፈል በ 0912664084 ይደውሉ።
👍10
የዘራነውን ነው የምናጭደው

እንደሚታወቀው ግንቦት፣ ሰኔ እና እስከ ሀምሌ አጋማሽ በሀገራችን ገበሬው መሬቱን ለሚዘራበት ሰብል የሚያርስበት ወቅት ነው። እናም ይሄ የሚዘራው ዘር የኩንታል ያህል መጠን ቢሆን ሲታጨድ ግን ብዙ ኩንታል እህል ይሰጣል።

ይሄ የዘር ምሳሌ ለማንሳት የፈለኩበት ምክንያት በህይወታችን ላይ ነገ የምናገኛው ህይወት ዛሬ የምንሰራውን ወይም ደግሞ የምንዘራውን ነው። ጊዜ መሬቱ ሲሆን ስራችን ደግሞ ዘሩ ነው። ስለዚህ ጊዜ ተሰቶሃል በዚያ ጊዜ ላይ የምናደርገውን ነገር ደግሞ ነገ ላይ በብዙ የምናጭደው ነገር ነው።

በህይወታች ላይ ነገ ማየት የምንፈልገው ፍሬያማነት ዛሬ በምናደርገው ታታሪነት እና ጠንካራ ሠራተኝነት ሳቢያ የሚመጣ ነው።

የምታጭደው የምታዝራው ነገር በብዛት መሆኑን አትርሳ። በዕድሜ ላይ ጥቂት አመት ካላገጥክ ለአንተ፣ ለቤተሰብ፣ ለትዳር አጋርህ እና ለጎደኞችህ አልፎ ተርፎ ደግሞ ለሀገር የሚተርፍ ቀውስ ትፈጥራለህ። በተቀራኒው መልኩ ደግሞ ዛሬ መልካም ነገሮች ላይ ጊዜ የምታፈስ ከሆነ ነገ ለብዙዎች የሚተርፍ ነገር በአንተ ውስጥ ይገኛል። ስለዚህ እንጠንቀቅ! አሁን ጊዜ በሚበል መሬት ላይ እየዘራን እንደሆነና የሆነ ሰዓት ማጨዳችን እንደማይቀር ማወቅ አለብን።

የምታጭደው ነገር ለአንተ ብቻ እንዳልሆነ በመገንዘብ ምን አገባኝነትን እና ግድየለሽነትን ከህይወት አጥፋ። ለምናደርገቸው ነገሮች በትኩረት እናደርግ። ምክንያቱም ዛሬ የምትዘራውን ነገር አውቀህም ሆነህ ሳታውቅም ብታደርግ ነገ ላይ ማጨድ አይቀርም። ነገ ላይ ፍሬው ሲመጣ ሳላውቅ ነው ብትል ማምላጫ መንገድ አይሆንህም። ስለዚህ ጊዜህ መሬት ሲሆን ስራክ ደግሞ ዘርህ እንደሆነ ተገንዘብህ እያንዳንዱ እንቅስቃሴህን ቃኝ። ዛሬ መልካም ዝራ፤ ነገ ብዙ መልካምነት ታጭደለህ!
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━

©ህልመኛው

🌟በቅንነት ለሌሎች ያጋሩት

በዚህ ክረምት ጥሩ ዘር የሚሆን የስብዕና ግንባታና የሳይኮሎጂ ስልጠናችን በቀጣይ ሳምንት ስለሚጀምር 0912664084 በመደወል ይመዝገቡ። ስልጠናችን በአካልም በኦንላየንም ይሰጣል።

Join and follow our page
www.tg-me.com/psychoet
4
2025/07/09 22:16:26
Back to Top
HTML Embed Code: