ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝ በሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ የጨዋታ እንግዳ ላይ ከመዓዛ ብሩ ጋር በነበረው ቆይታ ላይ መዓዛ እንዲህ ስትል ጠየቀችው ፦ “ዶ/ር ዳዊት ላንተ የተሠጠህ ትልቁ ሥጦታ የቱ ነው ?" “ዶ/ር ዳዊት፦ ሁሌም ይህን ጥያቄ ስጠየቅ በተደጋጋሚ የምመልሰው መልስ ይሄንን ነው። በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ፕሬዝዳንት ሆኜ ስሠራ አንድ ምስኪን ገበሬ ከአምቦ አካባቢ ልጃቸው በጠና ታሞ ይዘው መጥተው እንከታተልላቸው ጀመር ልጁም ከቀን ወደ ቀን ለውጥና መሻሻል ማሳየት ጀመረ፡ አባትም ቢሮዬ ድረስ መጡ። “ዶክተር እንደው እባክህ ከድፍረት እንዳታይብኝ እባክህ ብለው ተጨናነቁ” ፤ ምንድነው አባቴ? አልኳቸው እሳቸውም ወጣ ብለው ማዳበሪያ ተሸክመው መጡ ። ማዳበሪያ ውስጥም በቆሎ እሸት ነበረ ። “ይሄ ነው የደረሰው ብለው” እሱን ሲሰጡኝ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር፡ ተርፏቸው ሳይሆን ካላቸው ላይ ነበረ ለኔ ሥጦታ ብለው ያመጡልኝ።”
❤40👍10
አልበርት አንስታይን የካቲት 5 1930 ዓ.ም ላይ ለልጁ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ላከለት፦
“ህይወት ብስክሌት እንደመንዳት ናት ሚዛንህን ለመጠበቅ መንቀሳቀስህን መቀጠል አለብህ። የስኬት ሰው ብቻ ለመሆን አትሞክር ይልቅ ዋጋ ያለው ሰው ለመሆን ሞክር። ምክንያቱም ስኬት የሚለካው በምትወስደው ነገር ሲሆን ዋጋ የሚለካው ደግሞ በምትሰጠው ነገር ነው።
ሞኝ ማለት አንድ አይነት ነገርን ደጋግሞ ሰርቶ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ነው። የተለየውን መንገድ ተከተል አዲስ ነገር ታገኛለህ። አትቀመጥ ምክንያቱም ምድራችን አደገኛ የሆነችው በክፉ ሰዎች ስራ ሳይሆን ምንም በማይሰሩ ሰዎች ውጤት ነው።
ትምህርት እውነትን አያስተምርም ይልቅ የአእምሮ አስተሳሰብን ማበልጸጊያ ልምምድ ነው። የሌሎች ጫጫታ የአንተን የውስጥ ድምፅ እንዲውጠው ማድረግ የለብህም። ማንም ሰው ባንተ ላይ ገደቦች እንዲጥል አትፍቀድ፤ ገደብህ በራስህ ያወጣኸው የህይወት መመርያ መሆን አለበት!።”
©ሞገስ ዘአምደ

👍16❤3
ይህ የኢትዮጵያውያን ህክምና ባለሙያወች ታሪክ ነው ::
የአፍሪካ ዝቅተኛዋ ደሞዝ ከፋይ ሀገር
Specialist ሀኪም ወርሀዊ 120ዶላር
አጠቃላይ ሀኪም 84ዶላር
ነርስ 70ዶላር ወርሀዊ ክፍያ ምትከፍል ብቸኛ ሀገር ናት
ራሱን ለtb, hepatitis virus,hiv እና ሌሎች መሰል በሽታወች አጋልጦ ሚሰራው ሀኪም የጤና insurance የለውም።በትንሽ ክፍያ ሚሰራው የጤና ባለሙያ ለዚህ ሁሉ በሽታ ተጋልጦ እየሰራ ያለ insurance እየሰራ የጤና መድህን እንኳን ተጠቃሚ እንዲሆን አይፈቀድለትም?
ህይወት ሲያድኑ ኖረዋል አሁን ግን ህይወታቸውን ልናድን ይገባል!
ከሀኪሞች ጎን እቆማለሁ#
ሼር ይደረግ

👏22👍15❤2
ራስን በመቆጣጠር ድብርትን መከላከልና መጋፈጥ
#Share
የራስ ቁጥጥርና (self-regulation) የድብርት ስሜት ተዛማጅና ግንኙነት ያላቸው የስነ-ልቡና ክስተቶች ናቸው፡፡ ራስን መቆጣጠር ማለት አንድን ነገር ከግብ ለማድረስ ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብንና ጠባይን መግራት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራስን መቆጣጠር ከግብ ወይም አላማችን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ለምሳሌ ግባችን መማር፤ጥሩ ስራ መያዝ፤ የፍቅር ጓደኛ መያዝ፤ትዳር መመስረትና ልጆች ማፍራትና የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል፡፡ እናም አላማችን ከትናንሽ የዕለተለት ግቦች እስከ ላቅ ያሉ ለህይወታችን ከፍተኛ ትርጉም ያላቸው ግቦች ድረስ ሊሆን ይችላል፡፡
ራስን መቆጣጠርና የድብርት ስሜትን ምን አገናኛቸው?
ራስን መቆጣጠር ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብና፣ጠባይንና ከአላማነችን አንጻር መግራት ነው በሚለው ከተስማማን፤ የግባችን የስኬት መጠን ከድርጊታችን በኋላ ለሚሰማን ሰሜት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ያሰብነውና ያቀድነው ነገር በተሰካ ጊዜ ደስታ፣እርካታ፣ተሰፋና ለነገ የተነሳሽነት ስሜት ይፈጥርልናል፡፡ ያሰብነውና ያለምነው ነገር ሳይሳካ ሲቀር በተቃራኒው የድብርተና ተዛማጅ አሉታዊ ስሜቶች ሊፈራረቁ ይችላሉ፡፡ በዚህም ምክኒያት ራስን መቆታጠርና ድብርት የጠለቀ ግንኙነት አላቸው፡፡
የድብርት ስሜት ለራስ ቁጥጥር ያለው እንድምታ
ምንም እንኳን የድበርት ስሜት ምችት የማይሰጥ ቢሆንም ሳይንሳዊ መላምቶችና ምርምሮች እንደሚያመላክቱት ከሆነ እራሳችን ለመቆጣጠር የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ለምሳሌ ለፍቅረኛችን ታማኝ መሆን ሲገባን በስህተት ተማኝነታችንን ብናጎድል ከፈጸምነው በኋላ የድብርት ስሜት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ነገ ተደጋጋሚ ስህተት ላለመፈጸም ለእራሳችን ግበረ-መልስ (feedback loop) ነው:: ስለዚህ አላማችን ያማረ የፍቅር ህይወት መመስረት ከሆነ ለዚህ አላማችን መሳካት የእራሳችንን ጠባይ እንድንቆጣጠር የድብርት ስሜቱ አስተዋጽኦ ያበረክታል ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ሁሌም ታማኝነታችንን እያጎደልን ከፈጸምነው በኋላ ፌሽታና ደስታ የሚሰማን ከሆነ በዛው እምነት አጉዳይነታችን የመቀጠላችን እድል የሰፋ ነው፡፡ በተመሳሳይም በትምህርታችን ጥሩ ውጤት የማስመዝገብ አላማ ቢኖረንና ጊዜያችንን በአግባቡ ሳንጠቀም የፈለግነው ውጤት ባይመጣ አሁንም የድበርት ስሜት ሊከስት ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ለእራሳችን ጠባይ ከሰነቅነው አላማ አንጻር ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ አእምሯችን እራሱን የሚገመግምበት ግብረ-መልስ ሲሆን፤ ለወደፊት ይህ እንዳይከሰት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ በአጭሩ በዚህ የአረዳድ ድባብ መሰረት የድብርት ስሜት መፈጸም በምንፈለግገውና በፈጸምነው መካከል ልዩነት ሲፈጠር የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡
ተደጋጋሚ ውድቀትና ድብርት
በተደጋጋሚ ያሰብነውና ያቀድነው ነግር በማይሳካ ጊዜ የድብርት ስሜቱም እየጠነከረ በተደጋጋሚ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት፣መንስኤና ውጤት አትኩሮት ሰጥተን እንድናሰላስል በር ይከፍታል፡፡ ይህም ክስተት rumination በመባል ይታወቀል፡፡ ይህ አጥብቆ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት ማንሰላሰል ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ አብዛኞቹ በዚህ ዙሪያ የሚያጠኑ የስነ ልቡና ጠበብቶች አጥብቆ ከልክ በላይ ማሰቡ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አጽኖት ሰጥተው ይናገራሉ፡፡
ስለዚህ ከድብርት እራሳችን ለመካከልና ለመቋቋም ምን እናደርግ?
❖ተግባራዊ ግብ
በተደጋጋሚ ነገሮች ሳይሳኩ ሲቀሩ የድበርት ስሜት የሚከሰት ከሆነ፣ በተደጋጋሚ ላለመውደቅ ሊተገበር የሚችል ግብ ማውጣት፡፡ የነገሮች አለመሳክት ሁልጊዜ የችሎታ ማነስ፣እድለቢስነትና የሌሎች ተዛማጅ ነገሮች እጥረት ሳይሆን፤ በህይወታችን የምንሰነቃቸው ግቦች ሊተገበሩ የማይችሉና የራስ ቁጥጥራችን ደካማ ስለሆነ ሊሆን ይችላል፡፡
❖ግባችን ለመምታት አስፈላጊ ግብዓቶቸን ማፈላለግ
ተግባራዊ እቅዶችን ከነደፍን በኋላ ወደዚያ ጎዳና ለመድረስ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ከእራሳችንንና ከአካባቢያችን ማፈላለግ፡፡ ተሰጥኦቻችንን ማበልጸግ፤ ድክመታችንን ማሻሻልና የሚጎድለንን መሙላት፡፡
❖ጽናት
ተግባራዊ ግቦችን ካስቀምጥንና ወደ አላማችን የሚያደርሱንን ግብዓቶችንን ካመቻቸንን፤ ቀጣዩ የአላማ ጽናት (persistence) ነው፡፡ ሁሌም አዲስ ነገር ሲጀመር በወረትና በመነሳሳት መንፈስ ማደርግ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ድርግጊቱ መሃል ሲገባና ጫና ሲበዛ መፍረክረክ ግባችንን እንዳናሳካ ያደርገናል፡፡ ፈተና ሊበዛ ይችናል፡፡ ነገር ግን ካለ ተግዳሮትና ፈተና የሚገኝ የቤተሰብ ውርስ ብቻ ነው፡፡ የራሳችን ነገር፣ በእራሳችን ብርታት የምንፈልግ ከሆነ ፈተናና ተግዳሮት አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም ከፈተናና ተግዳሮት ልምድ መቅሰምና እራሳችንን እንዲጠቅመን መቀየር ነው፡፡ ለዚህም ራስን ማዘጋጀት፡፡ ሁሉም ነገር አልጋባልጋ ይሆናል ብለን ከተነሳን፤ በኋላ ተግዳሮቶች ሲከሰቱ የመንፈስ ስበራቱ ያለምነው ግባችን ላይ እንዳንደርስ መሰናክል ይሆናል፡፡ ስለዚህ ለተግዳሮቶችና ፈታናዎች ራስን በማዘጋጀት የአይበገሬነት መንፈስ መቀናጀት፡፡
❖አንዴ አልተሳካም ማለት ህይወት አከተመላት ማለት አይደለም
ህይወት መስመሯ አባ ጎርባጣ እነደመሆኑ መጠን ዛሬ ያቀድነው ነገር አልተሳካም ማለት አጠቃላይ ህይዎታችን አለቀላት ማለት አይደለም፡፡ እንደዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ለድበርት ስሜትና ለሌች የስነ ልቡና ችገሮች መከሰት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ምክኒያታዊ ያልሆነ አስተሳሰብ (irrational belief) ነው፡፡ ዛሬ ያፈቀርካትን ልጅ ስላላገኘሀት አጠቃላይ የፍቀር ህይዎትህ ዜሮ ሆነ ማለት አይደለም፡፡ ዛሬ የፈለግኸውን ስራ ስላላገኘህ የነገ መንገድህ ተቆረጠ ማለት አይደለም፡፡ ያለተሳካው ከብዙ የህይወት ግብ ውስጥ እንዱ ወይም የተወሰኑት ናቸው፡፡ ህይወት ደግሞ በአንድና ሁለት እቅድ አትመዘነም፡፡ ይህም የህይወትንና የተፈጥሮን ታላቅንት ማሳነስ ነው፡፡
❖ራስን መቆጣጠር ልምምድ ይፈልጋል
እንግዲህ ተግባራዊ ግብ ማስቀመጥና አስተሳሰባችንን፤ውስጠ ስሜታችንንና ጠባይያችንን ከዚህ ግብ አንጻር መግራት የራስ ቁጥጥር አንኳር መገለጫዎች ናቸው፡፡ የማይተገበር ግብ ማስቀመጥም ለውድቀት ይዳርጋል፤ ተግባራዊ ግብ ቢኖረንም በጽናት ጠባይያችንንና nአስተሳሰባችንን ካልገዛነውም ለውድቀት እንዳረገልን፡፡ ስለዘህ እራሳችንን የመቆጣጠር ክህሎት ለመካን ከትናንሽ ነገሮች ጀምረን እንለማመደው፡፡ ያኔ የስብእናችን ዋነኛ ምሰሶ ይሆናል፡፡
(በአሸናፊ ካሳሁን)©Zepsychology
@psychoet

❤16👍15
ማኔጅመንት እወቅ!
ምንም ትምህርት ብትማር ማኔጅመንት/አስተዳደር ልታውቅ ያስፈልግሃል።
ማኔጅመንት፣ አስተዳደር፣ አመራር፣ ቁጥጥር የተባሉት የትምህርት ወይም የእውቀት ዘርፎች አንድነትና ልዩነት አላቸው። መሠረታቸው ግን ማኔጅመንት ነው። ማኔጅመንት ሁሉን-አቀፍ ነው። ማኔጅመንት ውስጥ አመራር አለ፤ ማኔጅመንት ውስጥ አስተዳደር አለ፤ ማኔጅመንት ውስጥ መቆጣጠር አለ።
ማኔጅመንት ገሪነት ነው። ማኔጅመንት ሥራን፣ ሰውን፣ የአሠራር ባህልን ይገራል። ማኔጅመንት የገሪነት ሚናውን የሚጫወትበት ብዙ ሞዴሎች፣ ስልቶች እና ዘዴዎች አሉት።
የብዙ ችግሮች መፍትሔ ማኔጅመንት ውስጥ አለ። ህይወትህን በስርዓት ለመምራት ማኔጅመንት ልታውቅ ግድ ነው። ማኔጅመንት እውቀት ከሌለህ ችግር መዝዘህ እንኳን ሊተገበር ያልታለመ ችግር ውስጥ ትዘፈቃለህ። ግዴለም ማኔጅመንት እወቅ!
መጀመሪያ የተማርከው ምንድን ነው?
የተማርከው ምንም ይሁን ማኔጅመንት ብታውቅ ህይወትህ ለማቃናት ትልቅ እገዛ ያደርግልሃል። ማኔጅመንት ካላወቅህ ግን ሌሎች ይጫወቱብሃል። አንተም ጊዜ ጉልበት እና ገንዘብ ታባክናለህ። ችግርህን ለመፍታት የሚችል ሲስተም ያጥርህና ትግል እና ግጭት ውስጥ ትገባለህ።
ልብ በል! ከዚህ ቀደም እንዳልነው
SYSTEM = Save Your Self Time, Energy Money ማለት ነው።
ለራስህ ይሁን ለሀገርህ ጊዜ፣ ጉልበት እና ገንዘብ የሚቆጥብ ወይም የሚያባዛ ስርዓት ካልፈጠርህ ከንቱ ድካም እና የችግር አዙሪት ቀለበት ውስጥ ነህ።
የተማርከው ህክምና ይሁን ምህንድስና፣ ህግ ይሁን ፍልስፍና ለውጥ የለውም። ማኔጅመንት ልታውቅ ግድ ይልሃል።
ማኔጅመንት ማቀድ፣ ማደራጀት፣ መምራት፣ እና መቆጣጠር የሚሉ ዋና ተግባራት አሉት።
ለማቀድ ግብን እና የትኩረት አቅጣጫን መምረጥ ይጠይቃል። ማኔጅመንት የሚያውቅ ሰው ያገኘው ጦርነት ውስጥ ነጠላዬን አቀብሉኝ ብሎ ዘው ብሎ አይገባም። ማኔጅመንት የሚያውቅ ሰው ጦርና ጋሻ በእጁ ስላለ፣ ስልጣን ወንበር ላይ ስለተቀመጠ፣ ህግ ስለሚደግፈው ያየውን ችግር ሁሉ በህግና በጉልበት ልፍታ አይልም። ይህ የሚገባህ ማኔጅመንት ስታውቅ ነው። ማኔጅመንት በጠርሙስ ታሽጎ ያለን ጂኒ ክዳኑን ከፍቶ ራሱን ችግር ውስጥ አይጥልም።
ማኔጅመንት ስታውቅ ዋናውን እና ቀላሉን፣ ጠቃሚና ገለባውን፣ ግንድ እና ቅርንጫፉን ለይተህ የምታተኩርበትን ትመርጣለህ፤ ብራንድህን በፈለግኸውና ጠቃሚ በሆነ መስመር ትገነባለህ፤ ለሥራና አገልግሎትህ በቂ ክፍያ የሚያስከፍል ስርዓት ትዘረጋለህ፤ የመቆጣጠሪያ ዘዴ ትዘረጋና አካሄድህን እየለካህ በመገምገም ማስተካከያ ታደርጋለህ።
ማኔጅመንት ከታች ጀምሮ በየትምህርት ሳይክሉ በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን ቢሰጥ ጠቃሚ ነው። በኮሌጅ ደረጃ ላሉም የትምህርት መስኩ ቢያንስ 2 የማኔጅመንት ኮርስ ሊሰጥ ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ። ማኔጅመንት የማያውቅ "አዋቂ" ስራው ስርዝ-ድልዝ ዓይነት ነው።
በነገራችን ላይ በደረጃዎች የተከፋፈለ Mini-MBA የሚባል ስልጠና አለን። ይህ ስልጠና ለብዙዎች አስፈላጊ ነው።
የህግ ሰው ብትሆን፣ ሀኪም ብትሆን፣ መሃንዲስ ብትሆን፣ ኢኮኖሚስት ብትሆን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህር ብትሆን፣ ፖለቲከኛ ብትሆን፣ የታክሲ ሾፌር ብትሆን፣ የኳስ አሰልጣኝ ብትሆን፣ ባል ብትሆን፣ ሚስት ብትሆኚ፣ ሚኒስትር ብትሆን፣ ፓስተር ብትሆን፣ ... ማኔጅመንት ካላወቅህ ችግር ውስጥ ነህ። ማኔጅመንት እወቅ!
ችግር የሚፈጠረው ማኔጅመንት ባለማወቅ ነው። ችግር የሚፈታውም የማኔጅመንት ስልት በማወቅ ነው።
የሀገራችን ህዝብ የማኔጅመንት እውቀት ከፍ ሊል የተገባ ነው።
የህዝባችን የማኔጅመንት እውቀትና ልምድ ሲዳብር የመነጋገሪያ አጀንዳችን ይቀየራል፣ የጠራ ግብ ይኖረናል፣ የትኩረታችን አቅጣጫ ይቀየራል፣ ችግርን ለመፍታት ሚና ሚናችንን ለይተን እንደራጃለን፣ አካሄዳችንን ከግባችን አንጻር እየለካን፣ እየገመገምን እና እያስተካከልን ወደ ግባችን እንገሰግሳለን።
ማኔጅመንት የእውቀት ሁሉ መቋጠሪያ ነው።
የማኔጅመንት ትምህርት ስለሲስተም ነው።
ማኔጅመንት ሳይንስም ጥበብም ነው።
እስኪ በዚህ የማኔጅመንት መነጽር ሰሞኑን አየር ላይ የናኙትን የአስጌ ደንዴሾን የመክሰስ ሀሳብ፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሀኪሞችን Enough is Enough የሚል የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ፣ የኢሠማኮ የደሞዝ ወለል ይደንገግልኝ ጥያቄ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ፣ የሰይፉ እና ኩኩ ኢንተርቪው፣ የቴዲ ኮንሰርት እና ሌሎችም ሰፊ ሽፋን ያገኙ የሀገራችን ጉዳዮች ፈትሹት።
የቱ ለዓቅመ-አጀንዳነት ይበቃል? የቱ በየትኛው ስልትና ዘዴ ሊኬድበት ይገባል? የቱ ሰፊ ጊዜ ይፈልጋል? የቱ ሀገራዊ አጀንዳ ነው? የሁሉም ችግር ስረ-መሠረትስ ምንድን ነው?
በጨዋነት እንወያይ።
#Focus!
Get Toughe Zer

👍29❤4👏2
መለወጥ መፈለግ ጥሩ ጅምር ነው። ግን በቂ አይደለም። እውነታው ግን ህልሞች ያለድርጊት ህልም ሆነው ይቀራሉ:: ሁሉንም መጽሃፍቶች ማንበብ፣ ሁሉንም አነቃቂ ቪዲዮዎች መመልከት እና ፍጹም የወደፊት ዕጣህን በጭንቅላትህ ማቀድ ትችላለህ። ነገር ግን አንድ እርምጃ ካልወሰድክ እና ትንሽም እንኳን እንቅስቃሴ ከሌለ ምንም ነገር አይለወጥም::
ዝግጁ አንደሆንክ ስለተሰማህ ብቻ ለውጥ አይመጣም። ለውጥ የሚመጣው ያለሁበት ቦታ መቆየት ሰለቸኝ ብለህ ቆርጠህ የተነሳህ ጊዜ ነው። እንደ መብረቅ የሚያነሳሳህን ነገር መጠበቅ አቁም። ለራስህ 'ነገ' ማለትን አቁም:: የተሳካላቸው ሰዎች ሁልጊዜ የተነሳሱ አይደሉም ነገር ግን ስሜታቸው ባይሆኑም እንኳ የሚንቀሳቀሱ ናቸው:: ስለዚህ ጀምር። የተመሰቃቀለ፣ ዘገምተኛ፣ የማይመች ቢሆንም ለማንኛውም ጀምረዉ። ምክንያቱም ባለህበት ቦታ መቆየትም ይጎዳል ነገር ግን ልዩነቱ - አንዱ ወደ ፀፀት ሌላኛው ደግሞ ወደ እድገት ይመራል::
©Dani

👍10❤8
#ስንፍና_ማሸነፊያ_8ቱ_የጃፓን_ዘዴዎች
1- ኢኪጋይ፦ በጠዋት ከአልጋህ በደስታ የምትነሳበትን የሕይወትህን ዓላማ ፈልግ።
2- ካይዘን፦ ትልቅ ውጤትን ከመጠበቅ በየቀኑ ትንንሽ መሻሻሎች ላይ አተኩር።
3-ሾሺን፦ ሁልጊዜ የትኛውንም ስራ የጀማሪነት አስተሳሰብ ይዘህ ቅረብ።
4-ሃራ ሃቺ ቡ፦ ሆድህ 80% ሲሞላ መብላትህን አቁም።
5-ሽንሪን ዮኩ፦ የተፈጥሮ ሻወር ማለት ነው። ተፈጥሮ ውስጥ ጊዜ ማሳለፍን ልመድ።
6- ዋቢ ሳቢ፦ ሁሉም ነገር ፍጹም አይሆንም። ፍጹም ያልሆነው ነገር ውስጥም
ውበትን እይ።
7-ጋንባሩ፦ በየትኛውም ትግዳሮት ውስጥ የምትችለውን ያህል ጥረት በማድረግ ስራ።
8-ጋማን፦ ነገሮች ሲከብዱና ሲከፉ ትዕግስትና ጽናት ይኑርህ።

❤23👍6
👍16❤7👏1
አንብቡና አትርፉ!!!!
አንድ የሳይኮሎጂ መምህር ተማሪዎቹ የዉሳኔ እና ተግባርን ልዩነት እንዲረዱ በማሰብ አንድ ጥያቄ ይጠይቃል፤ ጥያቄዉም ...... "በአንድ ዛፍ ላይ የተቀመጡ ስምንት ወፎች አሉ ብላችሁ አስቡ፤ከነዚህ ስምንት ወፎች መሃል ስድስቱ ለመብረር ቢወስኑ ስንት ወፎች በዛፉ ላይ ይቀራሉ???" የሚል ነበር።
አብዛኞቹ ተማሪዎች "ሁለት ወፎች ብቻ ናቸዉ የሚቀሩት!!" ሲሉ ይመልሳሉ።
አንድ ተማሪ ግን "በዛፉ ላይ የሚቀሩት ወፎች ስምንት ናቸዉ።" በማለት ይመልሳል።
መምህሩም እንዴት ስምንት ወፎች ሊቀሩ እንደሚችሉ እንዲያብራራ ይጠይቁታል...
ተማሪዉም "ጥያቄዉ ወፎቹ ለመብረር መወሰናቸዉን እንጂ መብረራቸዉን አይገልፅም!!!ዉሳኔ እና ተግባር ፍፁም የተለያዩ ናቸዉ!!!!"ሲል ያብራራል
መምህሩም ትክክለኛው መልስ ልጁ የመለሰዉ እንደሆነ በመግለፅ ....."ብዙዎች ይህን አደርጋለሁ፣ይህን አላደርግም ሲሉ በተዋቡ ቃላት መወሰናቸውን ሲገልፁ ይሰማሉ፤ይሁን እንጂ ኑሯቸዉን ስትመለከቱ ተናገረዋቸዉ የነበሩ ዉቡ ቃላቶችን አታገኟቸዉም።ብዙዎች ያወራሉ ጥቂቶች ብቻ ይተገብራሉ፤ዉሳኔ አንድ ነገር ነዉ ተግባር ግን መገለጫ ነዉ።
ከጠቀማችሁ,ሌሎችም እንዲያነቡ አድርጉ,,,

👏17❤6👍2
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷♂
Photo
የደሀ ወንድ ባህሪያት
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪወች በ2015 ጥናት አድርገው ነበር። ለምንድነው ብዙ ወንዶች በአገራችን በተለይም በከተሞች ደሀ የሆኑት የሚል።
የሚደንቅ ነው እናም ከጠየቋቸው 8000 ያህል ደሀ ወንዶች የ98% ድሀ ያደረጓቸው ባህሪያትን ጠቅሰዋል
1. ሁልጊዜም የማይተገብሩትን ሀሳብ ቁጭ ብለው ያስባሉ ያቅዳሉ
ሆኖም ከማሰብ ይልቅ ተጨባጭ የሆነ ለውጥ ለማምጣት ወደለውጥ መንገዶች አይገቡም ሲበዛ ሰበበኞች ናቸው። ይህም ማቀድ ማለም ብቻውን ያለ ዲሲፕሊን ዋጋ የለውም እናም እነዚህ ወንዶች ይበልጥ ድሀ እየሆኑ ይኖራሉ።
2. በእጣ ፋንታ እና በእድል ያምናሉ
በነገራችን ላይ እጣ ፋንታ እና እድል ብለው የሚያምኑ ሰወች በምድር እጅግ ያልሰለጠነ አስተሳሰብ አራማጆች ናቸው ሲል በአለም የድህነት ሰንጠረዥ ታች የወደቁ አገራትን የአስተሳሰብ ባህሪያትን ያጠናው አለማቀፍ አጥኝ ቡድንም ይፋ ያደረገው እውነት ሲሆን ይህ አስተሳሰብ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድሀ ወንዶች ዋነኛ መገለጫው ነው። እጣፋንታየ ነው እድሌ ነው በሚል የውሸት ማባበያ ህልም አለም ፈጥረው እንዳከኩ ኖረው እንዳከኩ ያልፋሉ። በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በቃ የተፃፈልኝ ነው ይህ ነው እድሌ ወዘተ በሚል ያልሰለጠነ አስተሳሰብ ይዘው የሚጓዙ ብዙወች ናቸው።
3. ብዙ ሰአታቶቻቸውን በቤተእምነቶቻቸው ያባክናሉ
እነኝህ ወንዶች የድህነት ሂወታቸውን መርሳት የሚችሉት በየመስጊዱ በየቤተክርስቲያኑ በፀሎት ተጥዶ በመዋል ይመስላቸዋል። ይህ አይነቱን ክስተት በሜዲቫል ዩሮፕ ዘመን ታሪክ ስታነቡ እጅግ ድሀ የሚባሉ ሰወችን አንቆ የያዘ አስተሳሰብ ነበር ድህነትን በየቤተእምነታቸው እየሄዱ ማምለጫ መስሎዋቸው ብዙ ይበልጥ ደህይተው ያለፉ ሲሆኑ በተለይም ከሁለቱ የአውሮፓ ኢምፓየሮች መውደቅ በሁዋላ ሰው እየሰለጠነ በየቤተእምነቶቻቸው ተዘፍዝፈው የሚውሉትን ገሸሽ አርገው ይበልጥ በስራ በላቡ የሚያምን ትውልድን ፈጠሩ ተሳከላቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰወች ለድህነታቸው መፍትሄ የሚመስላቸው ብዙወች በቤተ እምነቶች እየሄዱ በማልቀስ በመወዘፍ አንድ የሰሙትን ቃል እንደ ጅል ደጋግመው በመስማት እራሳቸውን በድህነት አስረው ያልፋሉ ያለን የቢቢሲ ጥናትም ነበር። በዚህም በኢትዮጵያ ድሀ ወንዶች በሱስ እና በቤተእምነቶች ብዙ ጊዜያቸውን ያጠፋሉ።
4..ጥቅሶች በየቤቶቻቸው ሞልተዋል
ይህም ጥናት አድራጊወቹ 50% ያህሉ የገንዘብ ድሀ ኢትዮጵያውያን ወንዶች ጥቅስ እና ስዕል ያበዛሉ ካሉ በሁዋላ
ጥቅሶቻቸው ይበልጥ ሰርቶ ከመለወጥ ይልቅ የጅል አፅናኝ ጥቅሶች ናቸው ብለዋል።
<ይህም ያልፋል>
<የትዕግስት ፍሬዋ ጣፋጭ ነው>
<ከእኔ አትራቅ >
ወዘተ ብዙ ጥቅሶችን ይደረድራሉ
በዚህ ከ98% በላይ የገንዘብ ድሀ የሆኑ ኢትዮጵያውፓን ወንዶች ውስጥ ከ67% ያህሉ ድሀ እንደሆኑም ይሞታሉ።
5. ምንም ሳይዙ አፈቀርኩ ብለው ይሟዘዛሉ
በማያገኙዋት ሴት ፍቅር ይጃጃላሉ ብዙ ህይላቸውም ይበላል። ይህም ለብዙ ድሀ ኢትዮጵያውያን ወንዶች ብዙወቹን የሚያጃጅል የሂወታቸው አንዱ ገፅታ ነው።
@ልጅ አቤል

❤13👍6👎6👏3😁3
#የራስህ_ጠላት_ራስህ_ነህ!!!
#1_የራስህ_ጠላት_ራስህ_ነህ!
ሕይወትህ ፊልም ሆኖ ቢሰራ ያንተ እውነተኛ ተቀናቃኝ የሚሆነው ሌላ ማንም ሳይሆን አንተ ራስህ ነህ። ራስህን የምትጠልፈው፣ የምታሰቃየው፣ የምታዋርደው፣ የምትገድለው አንተው ራስህ ነህ።
ለራስህ ጠላት የሆንክበት ለሰዎች ሐሳብ በመጨነቅ፣ ምን ይሉኛል በማለት እና ሌሎችን በማስቀደም ለራስህ፣ እንደ ራስህ ባለመኖር ነው።
አዎ፣ ሕይወትህ ፊልም ሆኖ ቢሰራ ያንተ ዋነኛ ጠላት ሌላ ሳይሆን አንተ ራስህ ነህ!
#2_የሰዎች_ስሜት_አይንዳህ!
ሁሉም ነገርህ ሰዎች የሰጡህ፣ ሌሎች የመረጡልህ ነው። የተማርከው ቤተሰብህ የሚወደውን፣ ሰዎች ያበላል ያሉህን ወይም መንግስት የመደበልህን ነው። ልብስና ጫማ እንኳ የምትገዛው ጓደኞችህን አስመርጠህ ነው። ምንም ነገር የምታደርገው ይወዱታል እንጂ እወደዋለሁ ብለህ አይደለም። ከዚያ ግን ይደብርሃል። በተማርከው ደስ ብሎህ አትሰራም። በሰዎች ግፊት በገባህበት ትዳር ትነጫነጫለህ። የገዛሃቸው ልብሶችና ጫማዎች ቶሎ ይሰለቹሀል። ሙሉ ሕይወትህ እንደባከነ ይሰማሃል። ሲከፋህ ከጎንህ እነዛ ሰዎች የሉም። ትምህርትህን የመረጠልህ መንግስት ስራ እንኳ ሳይሰጥ ረስቶሃል።
ግን አልፈረደም ወዳጄ! ዛሬ ለራስህ በራስህ ተነሳሽነት አንተ የምትፈልገውን ማድረግ ትችላለህ። በቀላሉ የምትወደውን በመልበስ ጀምር። በልብህ የምትወደውን ያስቀመጠ ፈጣሪ መንገዱንም ይሰጥሃልና ከፈጣሪህ ጋር ሕልምህን ተከተል።
#3_ራስህን_ተቀበል_ከሌሎች_ጋር_በማወዳደር_አትሰቃይ!
ራስህን እንጂ ማንንም መሆን አትችልም። እንትና ፋሽን ስለቀያየረ፣ እገሌ መኪና ስለገዛ፣ እንትና ደግሞ ቤት ስለገዛ እንደ እሱ እሆናለሁ ብለህ በማወዳደር አትሰቃይ። አንተም የራስህ ጉዞና መንገድ ይኑርህ። በዚህ ሄጄ፣ እንደዚህ አድርጌ ከዚህ እደርሳለሁ የምትለውና እሱ እኮ እንዲህ ነው የምትባልበት መንገድና መድረሻ ይኑርህ።
ንጽጽር ደስታን ይሰርቃል። ውድድር ሰላምን ይነሳል። አንተ መሆን የምትችለው አንተን ብቻ ነው!!!
#4_አንተ_ያቀለልከውን_ማን_ያክብድልህ?
አንተ ራስህን የምትቀበልበት መንገድ ሰዎች አንተን የሚቀበሉበትን መንገድ ይወስናል። ራስህን ትጠላዋለህ? ማን ይውደድልህ ታዲያ! ራስህን ትንቀዋለህ? ማን ያክብርልህ ታዲያ! ራስህን በአግባቡ አትቀበለውም? ማን ይቀበልልህ ታዲያ! ሰዎች አንተን አያውቁህም፤ እንዲያውቁህ በፈቀድክላቸው መንገድ ደግሞ ያውቁሀል። አንተ ያላከበርከውን አንተን ማንም እንዲያከብርልህ አትጠብቅ። ሁልጊዜም ይህን የአባቶችህን ተረት አስታውስ "ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ፣ ባለ ዕዳ አይሸከመውም።"
#5_ስትሞት_አይደለም_ስትታመም_ትረሳለህ!
ብዙ ጊዜ ስትሞት ትረሳለህ ሲባል ሰምተሃል። እሱ የአባት ነው፤ ይግረምህና የአልጋ ቁራኛ መሆንህ ሲታቅ ራሱ ወዲያው ትረሳለህ። እንደማይጠቅም ነገር ትተዋለህ። ሰዎች ካንተ የአልጋ ቁራኛ መሆን በላይ ነገ ለሚለብሱት ጫማ ይጨነቃሉ፤ ካንተ ጤና በላይ መች እንደምትሞትና የለቅሶው ምስር ወጥ ያሳስባቸዋል። ከሞትክም አንተን ቀብረው ተመልሰው የእዝን ንፍሮ እየበሉና ካርታ እየተጫወቱ ይስቃሉ እንጂ አብረውህ አይሞቱም።
ሰው ወደደኝ አልወደደኝ፣ ተቀበለኝ አልተቀበለኝ ብለህ የምትጨነቅበት ጊዜ አይደለም። የምትወደውን፣ ትክክል ነው የምትለውን፣ ጠቃሚውን ለማድረግና ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ራስህን አድምጥ። ስትሞት አይደለም የአልጋ ቁራኛ ስትሆን እራሱ ትረሳለህና ሕይወትህን በራስህ መንገድ ኑር!!!

❤20👍4😢1
#ይሉኝታ
እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ተነቦ ሼር ይደረግ ።
#ይሉኝታ_ምንድን_ነው?
የሰዎችን ደስታና ሃዘን መካፈል፤ ለሰዎች በችግራቸው ጊዜ ያአቅምን ማድረግ አብዛኞቻችን ያስደስተናል፤ እርካታም ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዴ ሰዎች በይሉኝታ ሲታሰሩና ከፍላጎታቸው እና ከአቅማቸው በላይ ጊዜያቸውን፤ ገንዘባቸውን፤ ሃሳባቸውን ለሌሎች ሰዎች ደስታ ሲያውሉ ይታያል፡፡ ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት፡፡
#ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች
✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ? ብሎ መጠየቅ
✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ
✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ
✿የተበላሻ ነገር ስናይ ዝም በማለት ሳይኾን በግልጽ ፊት ለፊት በቅንነት መናገርና ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት
✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ
✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር
✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር
✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል
©zepsychology
Telegram Channel www.tg-me.com/Psychoet

Telegram
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷♂
| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!
የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

👍12❤10😢1
#ተሰሚነት
Telegram www.tg-me.com/psychoet
ለብዙዎቻችን ጠቃሚ ክህሎት ስለሆነ ሌሎችም እንዲማሩ አንብበን #Share እናርገው
“የሰው ውበቱ አንደበቱ ነው” ይላል አንድ ወዳጄ፡፡ አንደበት ውበት ብቻ ሳይሆን ሃብት፣ ስልጣን፣ እና ጉልበትም ነው፡፡ ሃሳባቸውን በሚገባ አደራጅተው አሳማኝ በሆነ መንገድ መግለጽ የሚችሉ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ተደማጭ ናቸው፡፡ ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ጥሪ ቢያቀርቡ ተከታይ ያገኛሉ፤ በንግዱ ዓለምም ቢሆን የተሻለ አትራፊ ነጋዴ ናቸው፡፡ ለዚህ ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስም “ሰው የአንደበቱን ፍሬ ይበላል”የሚለው፡፡
ይህንን ክህሎት የተወሰኑ ሰዎች ሲፈጥራቸውም የታደሉት ሊሆኑ ይችላል፡፡ በሌላ መልኩ ግን በልምምድ እና ውስን ስልቶችን ጠንቅቆ በማወቅ አንደበተ ርቱዕ ሰው መሆንም ይቻላል፡፡የተወሰኑ ጠቃሚ የምላቸውን ስልቶችን ላጋራችሁ፡፡
✍ቅለት
ማስተላለፍ የምትፈልጉትን መልዕክት ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር አድርጉ፡፡ የተራዘመ መልዕክት በአንድ በኩል አሰልቺ ነው፡፡ የሚፈለገውን ግብም አይመታም፡፡ አጥብቆ ለሚጠራጠረም ይህ ሁሉ እኔን ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ከጀርባው ሌላ የተሸፈነ ፍላጎት አለ ወይ የሚል ሃሳብም እንዲያድርበት በር ሊከፍት ይችላል፡፡የዓለማችን ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል መስራች ስቲቭ ጆብስ “አንድን ነገር ቀላል በሆነ መንገድ መግለጽ መቻል ትልቅ ጥበብ ነው” (Simplicity is the ultimate sophistication) ይላል፡፡
✍ሌሎች ሊያገኙ የሚችሉት ጥቅም ላይ ትኩረት ማድረግ
“እኔ ምን አገኝበታለሁ?(What’s in it for me?) ”የተለመደ ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ባይናገሩ እንኳን በውስጣቸው ይህንን ስሌት ከመስራት ወደ ኋላ አይሉም፡፡ በመሆኑም ለዚህ ወሳኝ ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ማቅረብ መቻል በቀላሉ ሃሳባችንን ሰዎች እንዲገዙን ያደርጋል፡፡
✍በራስ መተማመን
አንዳንዴ እውነታው ከምናስተውለው የተለየ እንደሆነ ውስጣችን እያወቀ የተናጋሪው በራስ መተማመን ውሳኔያችንን ሊያስለውጥ፣ ሃሳባችንን ሊያስቀይር ወዘተ ይችላል፡፡ የምንናገረውን ነገር እንደምንተማመንበት ሁለመናችን ሊያስረዳ ይገባል፡፡ በሰዎች መካከል በሚደረግ የእርስ በእርስ ግንኙነት ውስጥ ቃላዊ ባልሆነ መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች በቃል ከሚተላለፉት ያልተናነሰ ጉልበት አላቸው፡፡
✍በሌሎች ዓይን ማየት
ከሚመስሉን ሰዎች ጋር መስራት እንፈልጋለን፡፡ የጋራ ታሪክ አለን ብለን የምናስብ ከሆነ፣ ሃሳባችን ከተመሳሰለ፣ ምርጫች ከገጠመ ወዘተ ውስጣችን ፍላጎት በቀላሉ ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ይህንን የአንድነት መንፈስ ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮችን ማድረግ የማሳመን ኃይላችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ በቀጥታ የዓይን ግንኙነት መፍጠር፣ በትኩረት ማዳመጥ፣ ግንባርን አልፎ አልፎ ዝቅ ከፍ ማድረግ የመሳሰሉት ስልቶች እየተባለ የሚገኘው ነገር እየገባን እንደሚገኝ የሚጠቁሙ ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን የማሳመን አቅማችንንም እንዲሁ በዛው ልክ ከፍ እንዲል ያደርጋሉ፡፡በወደደው ሰው ተጽእኖ ጥላ ስር በቀላሉ ያልወደቀ መቼም አይጠፋም፡፡
✍ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ትምህርት ቤት እያለሁ አንድ መጽሔት ዝግጅት ውስጥ ተሳትፎ አደርግ ነበር፡፡ አንዱን ዕትማችንን በምናዘጋጅበት ወቀት አንድ ቢሮ በተደጋጋሚ መሄድ ነበረብኝ፡፡ በወቅቱ ሳላስተውል፣ይህ ስልት ሰዎችን ሊያሳምን እንደሚችል ሳላስብበትም ነበር አደርገው የነበረው፡፡ በስተመጨረሻ የመስሪያ ቤቱ ኃላፊ የስፖንስርሺፕ ደብዳቤያችን ላይ ከመራበት በኋላ “ይህንን ያደረጉት ተስፋ አልቆርጥ ስላልከኝ ነው”እንዳለኝ ትዝ ይለኛል፡፡ እንደየ ሁኔታው ያለ ማቋረጥ ጥረት ማድረግም ሰዎች ሃሳባችንን ሃሳባቸው እንዲያርጉ ይረዳል፡፡
✍እጥረትን መፍጠር
ዋልያ የሀገር ኩራት ምንጭ፣ የንግድ ስያሜ መጠሪያ፣ የብሔራዊ ቡድናችን አርማ ወዘተ መሆን የቻለው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በመገኘቱ ነው፡፡ በሌላ ቋንቋ ብርቅዬ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በተለያየ መልኩ መሸጥ የምንፈልገው ሃሳብም ይሁን ቁስ ከሌላው በምን መልኩ እንደሚለይ፣ በምን እንደሚሻል ወዘተ ማስረዳት ያስፈልጋል፡፡ እዚህም እዚያም እንደ ልብ ለሚገኝ ነገር ፍላጎታችን እምብዛም ነው፡፡
✍ዝግጅት
ስለምንናገረው ነገር ጠንቅቀን ማወቅ፣ አስቀድመን የቤት ሥራችንን በሚገባ መስራት ማሳመን የምንፈልገውን አካል ለማሳመን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በራስ መተማመናችንንም ይገነባል፡፡
ለሌሎችም #Share በማድረግ መልዕክቱን እናድርስ
በቴሌግራም ይቀላቀሉን www.tg-me.com/psychoet

❤11👍3
ዶ/ር ፕራቲክ ጆሺ ላለፉት ስድስት ዓመታት በለንደን ኖሯል። በህንድ ቆይታውም ለሚስቱ እና ለሶስቱ ትንንሽ ልጆቹ የተሻለ የወደፊት እድል የመገንባት ህልም ነበረው። ከዓመታት እቅድ፣ ወረቀት እና ትዕግስት በኋላ ያ ህልም በመጨረሻ እውን ሆነ። ልክ ከሁለት ቀናት በፊትም ባለቤቱ ዶ/ር ኮሚ ቪያስ
በህንድ ከምትሰራው ከህክምና ስራዋ መልቀቂያ ወሰደች። ሁሉም የቤተሰብ አባላት ቦርሳዎቻቸውን በእቃዎቻቸው አጭቀውና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ተሰናብተው የወደፊቱን አዲስ ህይወታቸውን ለመጀመር ጉዟቸውን ወደ እንግሊዝ አቀኑ። አምስቱም በተስፋ፣ በደስታ እና በእቅድ ተሞልተው በኤር ኢንዲያ በረራ 171 የአንድ መንገድ ጉዞ ቆርጠው ወደ እንግሊዝ ለንደን ተሳፈሩ። በፕሌኑ ውስጥም እንደገቡ ይህን ፎቶ ተነስተው ለማስታወሻ በማለት ለቅርብ ዘመዶች ላኩላቸው።
ግን በፍጹም ወደ አዲሱ መኖሪያቸው እንግሊዝ አልደረሱም። አውሮፕላኑ እንደተነሳ ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ተከሰከሰ። በአንዴም የሁሉም የህይወት ዘመን ህልም ወደ አመድነት ተቀየረ።😢😢😢
አያችሁ አንዳንዴ ሕይወት እንደዚህ ነች። የምንገነባው ሁሉ፣ የምንጠብቀው፣ የምንወደው፣ ሁሉም ነገር በክር የተንጠለጠለ ነው። መቼ እንደሚበጠስና እንደሚቆረጥ አናውቅም። ስለዚህ አሁን በሕይወት ሳለን ፈጣሪን ስለሰጠን ሕይወት እናመስግን።
ለሌሎችም #Share በማድረግ መልዕክቱን እናድርስ
በቴሌግራም ይቀላቀሉን www.tg-me.com/psychoet
😢13❤2
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ (ዶ/ር) 🤷♂
Photo
በጣም ጠቃሚ ምክር ስለሆነ ለሌሎችም ሼር አድርጉላቸው፣ ፔጁንም ፎሎ ያድርጉ
1. ተስፋ አድራጊ መሆን ረጅም ርቀት ይዞህ ይሄዳል፡፡
በጣም አስከፊ በሆኑ ጊዜያት እንኳ ተስፋ ባለመቁረጥ ችግሮችን መጋፈጥና ለመቀየር መቁረጥ የመፍትሄ መላ እንዲመጣልን ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ፣ ጨለምተኛ አትሁን፡፡ከፈተና ባሻገር የሚገኘውን ድል አስብ።
2. መርህ፣ አቋም፣ ያመንክበት ጉዳይ ይኑርህ ነገር ግን ለመስተካከል ቦታ ይኑርህ፡፡
በደረስክበት እውቀት መሰረት በነገሮች ላይ አቋም ሊኖርህ ይገባል፡፡ ነገር ግን የህይወት ዘመን ሁሉ ተማሪ ከሆንክ በአንድ ወቅት የያዝከው አቋም ትክክል እንዳልሆነ ስትረዳ ያመንክበትን ጉዳይ ማስተካከል ይኖርብሃል፡፡
3. አዋዋልህን እና ጓደኞችህን ምረጥ፡፡
አስተሳሰብህን እና ድርጊትህን በገንቢ ጎን ከሚተቹና ከሚገነቡ ሰዎች ጋር የምታደርግ ከሆነ በየጊዜው እየተሻሻልክ የምትሄድ ሰው ትሆናለህ፡፡ ባህሪህ እና ህይወትህ እያደር የሚመስለው የጓደኞችህን ነው፡፡
4. መሆን የምትፈልገውንና መስራት የምትፈልገውን በጊዜ አውቀህ ጀምር፡፡
በወጣትነት ጀምረህ መርጠህ የምትሄበት መንገድ እያደር አንተንም እየቀረፀህ ስለሚሄድ በዛው የመቀጠል እድል ይጨምርልሃል፣ አይቻልም ለሚሉህ በቀላሉ ላትሸነፍ ትችላለህ፣ በእድሜህ ብዙ ሳትገፋ ስኬታማ እና ብዙ ተፅእኖ አምጪ ትሆናለህ፡፡ የራስህን ራእይ የማትገነባ ከሆነ ሌሎች ቀጥረውህ ራእያቸውን እንድትገነባላቸው ያደርጉሃል፡፡
5. ከሌሎች ጎበዞች ጋር በጥምረት ስራ፡፡
ከጎበዞች ጋር በጥምረት ስትሰራ አንተ የማታውቃቸውን ነገሮች ያሳውቁሃል፣ አንተ ልታገኛቸው የማትችላቸውን ሰዎች እንድታገኝ እድል ይከፍቱልሃል፣ ይበልጥ ወደፊት ያራምዱሃል፡፡
6. በቅፅበት ከፍተኛ ደረጃ እደርሳለሁ አትበል፡፡
ከትምህርት ቤት አንደወጣህ ወዲያው ሃብታም፣ ባለስልጣን፣ ወይም ስኬታማ እሆናለሁ ብለህ አትጠብቅ፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ቢኖርህ እንኳ ስኬታማ ለመሆን ብዙ ልምድ ያስፈልግሃል፡፡
7. ስለ ስህተቶችህ ሌሎችን ሳይሆን ራስህን ውቀስ ተማርባቸው፡፡
ስህተቶች እንድንቆጭባቸው ሳይሆን እንድንማርባቸው ካደረግን ደግመን አንሰራቸውም፡፡
8. ምርጡ ትምህርት ቤት ኮሌጅ ሳይሆን ህይወት ነው፡፡
ምንም ያህል መፅሀፎች ብታነብ፣ ፈተናዎችን ብትወስድና ብታልፍ፣ በህይወት ሂደት የምትማረውን ያህል ብቁ አያደርጉህም፡፡ ስራዎች እና የስራ ሃላፊዎች ያስተምሩሃል፣ ያበቁሃል፡፡
9. ህይወት ሁሌም የቀና አይደለም፡፡
በህይወት ጉዞህ ትገጫለህ ትወድቃለህ፡፡ ኑሮ ፈተና ነው፣ ጌም መሳይ ነው፣ ተነስተህ እስኪሳካልህ ጉዞህን ቀጥል፡፡
10. ለስኬታማነት ትእግስት እና ጠንክሮ መስራት ያስፈልግሃል፡፡ በአቋራጭ የሚመጣ ዘላቂ ስኬት የለም፡፡
11. ለራስህ ክብር ይኑርህ፣ በማንነትህ ኩራ፡፡
እያንዳንዳችን የተለያየን ስለሆንን ራስህን ከሌላው ጋር እያወዳደርክ ዝቅተኝነት አይሰማህ፡፡ በሌላው ውስጥ የሌለ አንተ ውስጥ ያለ ችሎታ ስላለ ፈልገህ አግኘው፣ ተቀበለው፣ እዛ ላይ አተኩር፣ አዳብረው፣ በራስህ ተማመን፡፡ ስኬታማ የምትሆነው በዚህ መንገድ ነው፡፡
12. ራስህን አታሳብጥ፡፡
ስኬታማና ታላቅ የመሆን ራእይ መሰነቅ ተገቢ ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ላይ ብትወጣ ነገ ደግሞ ታች መውረድ ሊገጥምህ ይችላል፡፡ ላይ መውጣትህ የብዙ ነገሮች ጥምር ውጤት ስለሆነ ራስህን አይነኬና ልዩ ፍጡር አድርገህ አታስብ፡፡
13. "ደሃ ሆነህ ተወልደህ ከሆነ ጥፋቱ የአንተ አይደለም፤ደሃ ሆነህ ልትሞት ከሆነ ግን ጥፋቱ የአንተ ነው"።
#ኢትዮጵያዊነት#
ፔጁን Follow ማድረግ እንዳትረሱ
ለሌሎችም ሼር አድርጉላቸው

❤15👍4👏3😢1
በህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለማሸነፍ የሚረዱ 10 መንገዶች
1. እቅድ ያውጡ/Make a Plan/
ለወደፊቱ ምን እንደሚሆን ባያውቁም ፣ ሁል ጊዜ አስቀድመው ማቀድ ይችላሉ። በሕይወትዎ ውስጥ ያሉትን ቅጦች ይመልከቱ እና ምን ፈተናዎችን እንደታገሉ ይመልከቱ። እጅግ በጣም ጥሩ ውጤቶችን ይገምግሙ እና እንዴት እነሱን ለማሳካት እቅድ ያውጡ።
የሆነ ቦታ ከሠሩ እና ሊያጋጥሙዎት የሚችሉትን የችግሮች ዓይነቶች መገመት ከቻሉ ከዚያ አስቀድመው ማቀድ ይችላሉ። በትምህርት ቤት ላሉ ተማሪዎች ይህ ተመሳሳይ ነው። ተግዳሮት የጊዜ አያያዝ ከሆነ ፣ ለምሳሌ የቀን መቁጠሪያ አስተዳደርን መማር እና ማቀድ ይችላሉ ፣ ለምሳሌ።
2. እርስዎ ብቻዎን እንዳልሆኑ ይወቁ/Know You’re Not Alone/
በዚህ ዓለም ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ሰው ዝቅተኛ ነጥቦቹ አሉት። አንዳንዶች ከሌሎቹ በተሻለ ሊይዙት ወይም ሊደብቁት ይችላሉ። እውነታው ግን እርስዎ የሚያጋጥሙትን ሁሉ ፣ ሌሎች በእሱ ውስጥ ያለፉም አሉ። ብቻሕን አይደለህም. ወደ ማህበረሰብዎ እና አውታረ መረብዎ ለመድረስ ይሞክሩ። በሁሉም የሕይወትዎ ቅንብሮች ውስጥ ስሜትዎን ይናገሩ እና ስጋቶችዎን ይግለጹ።
3. ለእርዳታ ይጠይቁ /Ask For Help/
እርስዎ ብቻዎን አይደሉም ፣ ስለዚህ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። እርዳታ በመጠየቁ ማፈር አያስፈልግም። በሚወዱት ሰው ፣ በማያውቁት ፣ በአማካሪ ወይም በጓደኛዎ ላይ መታመንን ቢመርጡ ፣ እርስዎ እንዲሳኩ ሊረዱዎት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ።
4. ስሜትዎን ይሰማዎት /Feel Your Feelings/
ስሜትዎን በመደበቅ እነሱ አይሄዱም። ይልቁንም ፣ ስሜቶች ተይዘው ኃይል ይሆናሉ እና ችላ በሚባሉበት ጊዜ አሉታዊ የጤና መዘዞች ሊያስከትሉ ይችላሉ። የሚሰማዎትን ለመሰማት ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ። ይህ በማሰላሰል መልክ ሊመጣ ይችላል። ወይም ፣ እርስዎ የሚሰማዎትን ለመፃፍ ከፈለጉ ፣ መጻፍ የህክምና እና ካታሪክ ተሞክሮ ሊሆን ይችላል።
ስሜትዎን ሲሰማዎት እና ሲያጋሩ ፣ ሁኔታዎን በአዲስ ብርሃን ማየት ይችሉ ይሆናል። ይህ መልመጃ ልብ ወለድ መፍትሄዎችን ለማምጣት እና ማንኛውንም ተግዳሮት ለማሸነፍ ሊያመራዎት ይችላል።
5. ድጋፍን ይቀበሉ /Accept Support/
እርዳታ መጠየቅ የሳንቲሙ አንድ ጎን ብቻ ነው። በሳንቲሙ በሌላ በኩል ድጋፍን ለመቀበል ክፍት እና ፈቃደኛ መሆን አለብዎት። እርስዎን ለመርዳት የሚመጡ ሰዎች ስለእርስዎ ያስባሉ። በሚፈልጉበት ጊዜ እርዳታ ለመቀበል ክፍት ይሁኑ።
6. ሌሎችን መርዳት /Help Others/
አሮጌው አባባል “እርስዎ የሚሰጡት ያገኙት ነው” ይላል። እርስዎ በአንድ ሁኔታ ውስጥ ከገቡ ወይም እርስዎ በከባድ ጊዜ ውስጥ ለሚያልፈው ሰው ምክር ካለዎት መርዳቱን ያረጋግጡ! ሌሎችን መርዳት እነሱን ብቻ ይጠቅማል ፣ ግን እርስዎ እራስዎ የበለጠ ደስተኛ እንዲሆኑ ይረዳዎታል።
7. ትልቅ አስብ /Think Big/
ውድቀትን በመፍራት ፣ ወይም ውሳኔ ከማድረግ ፍርሃት የተነሳ እራስዎን ትንሽ እንዲያስቡ ማድረግ ቀላል ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ፣ በህይወት ውስጥ ታላላቅ ነገሮችን ለማከናወን ፣ አደጋዎችን ለመውሰድ ክፍት መሆን አለብዎት። በማንኛውም ተግዳሮቶች ሊከሰቱ ይችላሉ ፣ ሁል ጊዜ ያስቡ እና ትልቅ ይሁኑ። በዚህ መንገድ እርስዎ ከመገመትዎ በላይ ብዙ ያገኙታል። ሀሳቦችዎ በራስዎ መንገድ እንዳይገቡ ለማድረግ ይሞክሩ።
8. አዎንታዊ አስተሳሰብ /Positive Mindset/
እርስዎ የሚያስቡት የእርስዎ እውነታ ይሆናል። በአዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲያስቡ አእምሮዎን ያሠለጥኑ። ይህ ሁለቱንም ጊዜ እና ልምምድ ይጠይቃል። በአእምሮ ግንዛቤ ይጀምራል። በአስተሳሰብ ዘዴዎች እና በማሰላሰል ግንዛቤን መለማመድ ይችላሉ። ሀሳቦችዎን እውቅና በመስጠት እና እንዲያልፉ ሲፈቅዱ ፣ አሉታዊ ሀሳቦችን በመንገዳቸው ላይ ማቆም ይችላሉ።
9. ተስፋ አትቁረጡ /Don’t Give Up/
ተፈታታኝ ሁኔታ ሲፈጠር ፣ በትምህርት ቤት ውስጥ ትልቅ ፈተና ይሁን ወይም መጪው የሩጫ ውድድር ፣ ተስፋ አይቁረጡ! ተግዳሮቶችን ለማሸነፍ ጽናት ትልቅ ቁልፍ ነው። ተስፋ መቁረጥ ማለት ተግዳሮቱን ማሸነፍ ወይም ከእሱ መማር አይችሉም ማለት ነው። ድጋፍን በመጠየቅ ፣ ስሜትዎን በመሰማትና ወደ ውስጥ ለመግባት እቅድ በማውጣት በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ኃይልን ይስጡ።
10. ስራዎች በብልሀት ይስሩ ብልጥ /Work Smart, Not Hard/
በአጠቃላይ አንድ ነገር ለማከናወን ከአንድ በላይ መንገዶች አሉ። ሆኖም ፣ ሁል ጊዜ አንድ ጥሩ መንገድ ፣ ወይም እሱን ለማድረግ በጣም ጥሩው መንገድ አለ። ግብዎን ይዘርዝሩ እና ይግለጹ። ከዚያ እንዴት እዚያ እንደሚደርሱ ሂደቱን ያቅዱ። ከእርስዎ በፊት የመጡ ሌሎች ሰዎች እንዴት እንዳደረጉት ለማየት ምርምር ያካሂዱ። በተሻለ ሁኔታ እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ የራስዎን ችሎታዎች እና ሀሳቦች ይቁጥሩ።

👍7❤3
የስኬታማ ሰዎች ባህርያት
▫▫▫
ሰብአውያን ተዋሪዎች (humanistic theorists) የሰው ልጅ ባዶ ሆኖ ሳይሆን ከእምቅ ችሎታ ጋር ወደ እዚህ ምድር መጥቷል ብለው ያምናሉ። አብርሃም ማስሎ (Abraham Maslow) የሚባል አሜሪካዊ ተዋሪ እጅግ ስኬታማ የነበሩ ግለሰቦችን (ለምሳሌ፦ አብርሃም ሊንከን፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ መሀተማ ጋንዲ..ወዘተ) ሕይወት ከተለያዩ ፅሁፎች በማሰባሰብ አጠና።
የጥናቱ ሳይንሳዊነት አጠያያቀመ ቢሆንም፣ በጥናቱ መሠረት እጅግ ስኬታማ የሆኑ እነዚህ ት
ታላልቅ ሰዎች አያሌ የጋራ ባህርያት ነበራቸው። ከእነዚህ ውስጥ "ጤናማ" የሚላቸውን 8 ባህርያት እንመልከት፦
⏩ አወንታዊነት (optimism)
ስኬታማ ሰዎች ህይወትን አጨልመው ሳይሆን በበጎ አይን ይመለከታሉ። እነዚህ ሰዎች እንቅፋት ሲገጥማቸው እንኳ እንደ ማደጊያ መንገድ ይወስዱታል እንጂ በትንሽ በትልቁ አያላዝኑም።
⏩ ጨዋታ አዋቂነት (sense of humor)
እነዚህ ሰዎች በህይወታቸው ችክ ያሉ ደረቆች ሳይሆኑ ጨዋታ የሚያውቁና ፈገግታ ከፊታቸው የማይጠፋ ናቸው።
⏩ ክፍትነት (open to new experience)
ጤናማ ሰው አዲስ አስተሳሰብ ሲሰማ ደስ ይለዋል እንጂ ቱግ አይልም። ክፍትነት ለአዲስ ሰው፣ አሰራር፣ እምነት፣ አስተሳሰብ፣ እና ቴክኖሎጂ ጉጉ መሆንን ያጠቃልላል።
⏩ ራስን ማወቅ (self-awareness)
ጤናማና ስኬታማ ሰዎች ድካማቸውን፣ ብርታታቸውን፣ እንዲሁም የሚጠሉትን ወይም የሚወዱትን ጠንቅቀው የሚያውቁ ግለሰቦች ናቸው።
⏩ ራስን መቀበል (self-acceptance)
በምድር ላይ ማንም ያለ ጉድለት የተፈጠረ የለም። ጠንካራ ሰዎች ድካማቸውን አውቀው ራሳቸውን ተቀብለው ይኖራሉ ነገር ግን ደካሞች ጉድለታቸውን እያዩ ዘወትር እዬዬ ባዮችና አጉረምራሚዎች ናቸው።
⏩ አዎንታዊ ግንኙነት (positive relationship)
አዳጊ ሰዎች ከብዙ የይምሰል ጓደኝነት ይልቅ ጥቂት የልብ ጓደኞች አሏቸው። ከሚስቱ እና ከጓደኞቹ ጋር ጥሩ ጓደኝነት የሌለው ለውድቀት የቀረበ ዕድለቢስ ነው።
⏩ ፍቅርና እክብካቤ (loving and caring)
በአለማችን ላይ የተነሱ ታላላቅ ሰዎች የፍቅር ሰዎች ነበሩ፤ ግባቸው የሌሎች ስኬት ነበር፤ በህይወት ዘመናቸው ለሰው ኖረው ነበር ለሰው የሞቱት። በተቃራኒው፣ በህይወት መሰላል ላይ ከታች የቀሩ ሰዎች ለራስ ኖረው ለራሳቸው የሞቱ ስግብግብ ግለሰቦች ናቸው፤ ሰው አይወዱም፤ አይራሩም እንዲሁም ለሰው ግድ የላቸውም ወይም አልነበራቸውም።
⏩ በሰዎች አስተያየት አይሰበሩም (not paralyzed by other's opinion)
ስኬታማ ሰዎች የራሳቸውን እንዲሁም የሌሎችን ችሎታ እንዲሁም ደካማ ጎን ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ከሌሎች የሚመጡ ትችቶችን ሰምተው የሚሰበሩ ሸምበቆዎች ግን አይደሉም። በህይወት መንገዳቸው የተለያዩ ሰዎች በትችት ከመንገዳቸው ሊያደናቅፏቸው ይሞክራሉ ነገር ግን እንደ ብረት ፅኑ ስለሆኑ ከጉዞአቸው ለአፍታም ቆም የሚሉ አይደሉም።
መደምደሚያ
ጤናማ እና የሚያድግ ሰው የሚጫወት፣ ሰው የሚወድ፣ ቀና አሳቢ፣ ለራሱ ጥሩ ግምት ያለው ነው።
ቸር ሁኑልን።

❤9👍6