Telegram Web Link
Forwarded from BØØĶ ČËÑŢËŘ📚 (Haymanot)
እግረ መንገዱንም የዛፎቹ ቅርንጫፍ፣ ቅጠላቅጠል እየረገፈ ከረጢቱ ውስጥ የሚገባውን ወስዶ ደግሞ ዛፎቹ ሲያረጁ ቅጠሎቹ ወደ መሬት ሲረግፉ የሚመጣውን ንጥረ ነገር እና ዑደት (Nutrient Cycling) ለመረዳት ያስችላል።

ይህን ጥናት ለማድረግ በስምንት አብያተ ክርስቲያናት ቁጥራቸው የታወቀ ከረጢቶችን በስርዓት አስቀምጬ በየሳምንቱ እየተመላለስኩ ከረጢት ውስጥ የገባውን እየገለበጥኩ ወደ ላቦራቶሪ እየወሰድኩ አንድ ዓመት ሉ መሥራት ነበረብኝ# አንዳንዱ ከረጢት ባዶውን ሊገኝ ይችላል። ያ ግን የምርምሩ አካል እንጂ ችግር አይደለም።

ከስምንቱ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት በአንዱ የአብነት ተማሪዎች የሚማሩትና የሚያስተምሩት ደኑ/ካው ውስጥ ስለነበረ ምናልባት ከውጭ ሰው መጥቶ ከረጢቶቹን እንዳይወስዳቸው ተማሪዎቹ እንዲከታተሉልኝ መርጌታውን አደራ ብዬ ተስማምተን ሄድኩኝ።

መርጌታውን ስለምርምሩ በበቂ መጠን አላስረዳኋቸውም ነበር# ብቻ በየሳምንቱ እየመጣሁ ዘሩን እንደምወስድ ነግሬአቸዋለሁ። በዚህ መሠረት አንድ ወር ያክል በየሳምንቱ እየሄድኩኝ ዘሩን እየገለበጥኩ ስመለስ ይመለከታሉ። እኔም ሰላም እላቸዋለሁ እሳቸውም ሰላም እያሉኝ ከረጢቶቹን ስገለብጥ ያያሉ። እንድ ቀን፡...

#ከ_መጸሐፉ_የተወሰደ
@books_centerr
@books_centerr
Forwarded from BØØĶ ČËÑŢËŘ📚 (Haymanot)
“እንዲያው እንደዚህ ዓመት ትዘልቀዋለህ?” አሉኝ በሐዘኔታ

“አዎ አንድ ዓመት እመላለሳለሁ። ከዚህ ከረጢት ውስ የገባውን ዘር ስለምፈልግ በየሳምንቱ መምጣቴ ግዴታ ነው" አልኳቸው።

በዚህ መሠረት አንድ ሁለት ወር ተመላለስኩኝ። ስምንት ጊዜ ማለት ነው" በዘጠነኛው እንደተለመደው ከረጢቱ ውስጥ የገባውን ዘርና ቅጠላቅጠል ለመገልበጥ ስሄድ ደኑ ውስጥ ያስቀመጥኳቸው ከረጢቶች በሉ ከአፍ አስከ ገደፋቸው በዘር እና በቅጠል ተሞልተዋል። ይሕ ለእኔ የሚገመትም የሚጠበቅም አልነበረም# ምክንያቱም ያን ያክል በከረጢቱ የሚሞላ ሀር የሚገኝ ከሆነ ተአምር እንደማለት ነውና በጣም ተደንቄ ይሄ ሊሆን አይችልም? እንዴት ይህን ያክል ዘርና ቅጠል በሳምንት ይረግፋል? እያልኩ ከራሴ ጋር በጥያቄ ስፋጠጥ ድምጼን ሰምተውኝ ኖሮ እኒህ መርጌታ ተማሪዎቻቸውን አስከትለው መጡ። ሰላምታ ከሰጡኝ በኋላ መገረሜን ሲያዩ “ምነው?"

አለኝ። “አይ ደንቆኝ ነው" ይህን ያክል ዘር እንዴት ተገኘ ብዬ እያሰብኩ ነው" ስላቸው:

“እ ነው?" አሉና “እኔማ እንዲያው በየሳምንቱ መንከራተትህ ሲያሳዝነኝ ጊዜ ለምን እኛ አንሰበስብለትም ብዬ ተማሪዎችን...

#ከ_መጸሐፉ_የተወሰደ
@books_centerr
@books_centerr
Forwarded from BØØĶ ČËÑŢËŘ📚 (Haymanot)
በየዛፉ አሰማርቼ ሽምጥጠን ከመሬት ያለውንም እያፈስን እኛ ሞልተንልህ እኮ ነው አሌኝ።

ይህን ስሰማ ብው አልኩ። ለወዲያው የምይዘውን የምጨብጠውን አጣሁ" ምክንያቱም ያዚያን ሳምንት ምርምር አውጥቼ መድፋት ስለሚኖርብኝ ነው" የዛን ሳምንት መረጃ ለማግኘት ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት በዛችው ወቅት መጠበቅ ሊኖርብኝ ነው" ወይም ሁለተኛው ደካማ አማራጭ የዚህን ሳምንት መረጃ መተው ይሆናል" ለማንኛውም በምርምሬ ሥራ ላይ ትልቅ ጥፋት ትልቅ በደል ነበር።

እርሳቸውም ቀጠል አደረጉና

“መቼም የሚበቃህ ይመስለኛል ተንግዲህ አትመላለስም "

አሌኝ።

እሳቸው በደግነታቸው ለእኔ ያደረጉት እርዳታ የእኔን የምርምር ሥራ የሚያጠፋና የሚያወድም እንደሆነ አልተረዱትም ነበር። ተግባራቸው ለእኔ ጥፋት እንደሆነ ብረዳም ይህን ያደረጉት ደግሞ እኔን ለማገዝ ለእኔ ባላቸው ሐዘኔታ በመሆኑ የእሳቸው ደግነትና የምርምር ሥራዬ ላይ የደረሰው ጥፋት አንድ ላይ አዕምሮዬ ውስጥ ገብቶ ጭንቅላቴን ናጠው።

“በዓለም ላይ ትልልቅ ጥፋቶች የተፈጸሙት በጎ ሓሳብ ባላቸው ሰዎች ነው የሚባለው ለዚህ ይሆን? በጎና ቅን ሓሳብ በዕውቀት በጥበብና አርቆ በማዬት ካልታሰበ መጨረሻው ጥፋት ሊሆን ይችላል። ወደ ገሃነም የሚወስደው መንገድ...

#ከ_መጸሐፉ_የተወሰደ
@books_centerr
@books_centerr
Forwarded from BØØĶ ČËÑŢËŘ📚 (Haymanot)
በቅንነትና በየዋህነት የተገነባ ነው የሚባለው ለዚህ ነ እያልኩ ብዙ ተብሰከሰኩ።

ሰከን ብዬ ሳስብ ደግሞ በተንኮል ከመነጨው የይሁዳ መሳም

ይልቅ በቅንነት የሆነው የሙሴ መግደል ይሻላል የሚለው አባባል ሞገተኝ። እንዲያውም ኢማኑኤል ካንት የተባለው ፈላሰፋ ስለ ደግነትና

ሞራሊቲ ሲገልጽ፣

“ደግነትና ሞራሊቲ የሚለካው በሚያመጣው ወይም በሚያስከትለው ውጤት ሳይሆን ድርጊቱ በተፈጸመበት መንፈስ ብቻ ነው በጎ ሐሳብ ውጢት ባይኖረው እንኳን እንደ እንቄ ያበራል። በጎ ሐሳብ በራሱ መልካም ነውና።

Moral worth of an action depends on motive. A good will isn't good because of what it effects or accom plishes, it's good in itself. Evenif by atmost effort the good will accomplishes nothing it would still shine like a jewel for its own sake as something which has its full value in itself enA

እንደ ካንት አባባል በበጎ የታሳበን፡ መጥፎ ውጢት አያባላሸውም፤ በሌላ በኩል መጥፍ እሳቤን፡ መልካም ውጤት አያስተካክለውም ነው" ምሳሌ ሲሰጥ...

#ከ_መጸሐፉ_የተወሰደ
@books_centerr
@books_centerr
Forwarded from BØØĶ ČËÑŢËŘ📚 (Haymanot)
“አንድ ባለሱቅ በርካሽ የሚሽጥን እቃ ተመሳሳይ ከሆነና በውድ ከሚሸጥ ዕቃ ጋር ቀላቅሎ ለመሸጥ አስቦ ድንገት ደንበኞቼ ዕቃውን ለይተው ቢያውቁት ለወደፊቱ ደንበኝነታቸውን ያቋርጡብኝና ገቢዬ ይቀንሳል› ብሎ ማጭበርበሩን ቢተዎው የተወበት ምክንያት ከራስ ወዳድነት አንጻር በመሆኑ ውጤቱ መልካም ቢሆንም አያስመሰግነውም” ይላል።

ተረጋግቼ ይህን ሁሉ ሳስበው ከእርሳቸው ደግነት የሚበልጥ ጉዳይ እንደሌለኝ ተረዳሁና መቀየሜን ተውኩት። ራሴን እንደምንም አረጋጋሁና የምፈልገው ዝም ብሎ ዘር ብቻ ሳይሆን እራሱ በተፈጥሮ የሚገባውን እንደሆነ ለወደፊቱ እንዲያ እንዳያደርጉ የምርምሩን ሐሳብ አስረዳኋቸሁ። በዚህ ሂደት የራሴ ጥፋት ወለል ብሎ ታየኝ" ይህን ገለጻ ቀደም ብዬ ማድረግ ነበረብኝ። የሀገራችን ተመራማሪዎች የተለመደ ተራ ስህተት ነበር። እርሳቸውም ሁኔታውን ሲረዱ በአድራጎታቸው ተጸጽተው “አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል ማለት ይኼ አይደል?" አለኝ ደጉ መርጌታ!
#ከ_መጸሐፉ_የተወሰደ

📚

______________________________________________
@books_centerr
@books_centerr
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@realitysensation
@realitysensation
Forwarded from BØØĶ ČËÑŢËŘ📚 (Haymanot)
...የሀገር መሪዎች፣ የሃይማኖት እና የእምነት መሪዎች፣ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችº አንቃዒና አንቃሂ ሊሆኑ ይገባቸዋል። አንቃዒ ሕዝቡን የሚያነቃ፣ ንቅሐተ ሊና የእስተሳሰብ ንቃትን የሚፈጥር፣ ቅንነትና መልካምነትን አፍላቂ ነው ለመልካም _ አስተሳሰብ መንገድ ሠንጣቂ፣ መንገዱን የሚያውቅ፣ በመንገዱም የሚሄድና ለሌሎችም ቅን የሆነውን መንገድ አንቅቶ የሚያሳይ ነው። ይህ ይፈጸም ዘንድ መሪዎች በኣንቃዒነት ላይ አንቃሂነትን መደረብ አለባቸው: አንቃሂነት የተኛውን መቀስቀስ ነው የሞተውንም ማስነሳት ነው ሕዝብ አስነሺ ይሻል። በሐሳብ እንዳይሞት አንቅሆ ያስፈልገዋል። የመሪዎች፣ የአስተዳዳሪዎች ብሎም የመምህራን ኃላፊነት ሕዝብ የትናንት ማንነቱን ረስቶ በዛሬ ከንቱነት ፈዝዞ የነገ አሳቢ እንዳይሆን ከያዘው የኅሊና እንቅልፍ ይነሣ ዘንድ hንቃሐን መሆን ይገባቸዋል። ይልቁንም ለዛሬይቱ ኢትዮጵያና ሕዝቧ ይህ የግድ ነው።

#ከ_መጽሐፉ_ውስጥ_ገጽ_የተወሰደ

📚
_____________________________________________
@books_centerr
@books_centerr
🥀

ᴇᴠᴇʀʏᴛʜɪɴɢ ʜᴀᴘᴘᴇɴѕ ғᴏʀ ᴀ ʀᴇᴀѕᴏɴ, ʙᴜᴛ ѕᴏᴍᴇᴛɪᴍᴇѕ ᴛʜᴇ ʀᴇᴀѕᴏɴ ɪѕ, ᴛʜᴀᴛ ʏᴏᴜ'ʀᴇ ѕᴛᴜᴘɪᴅ ᴀɴᴅ ʏᴏᴜ ᴍᴀᴋᴇ a ʙᴀᴅ ᴅᴇᴄɪѕɪon

@realitysensation
@realitysensation
💙🤍💜

ዛሬ የተሰጠን ቀን ከነገ የተሻለ ነው።

@realitysensation
@realitysensation
🐾

YOU ARE THE CREATOR OF YOUR OWN DESTINY'S.


@REALITYSENSATION
@REALITYSENSATION
🐾

When you are the owner of your smile,
No one can make you cry:)

@realitysensation
@realitysensation
-💖

They are always special,
But can't bring them back🖤
____________________________
@realitysensation
@realitysensation
-💖

YOU CAN'T BUY LOVE,BUT YOU CAN PAY HEAVILY FOR IT.
_____________________________________
@REALITYSENSATION
@REALITYSENASTION
🐳

SILENCE IS THE BEST RESPONCE TO A FOOL.
WE DON'T HAVE TO ALWAYS EXPLAIN OURSELVES.
_________________________________
@realitysensation
@realitysensation
2025/07/05 16:00:20
Back to Top
HTML Embed Code: