Telegram Web Link
Forwarded from Mahlet Mesfin
https://m.youtube.com/watch?v=XgsMIF6-yMg

በሁሉም የህይወት ጎዳና “ስኬትን” ማግኘት (A very rare or unlikely scenario when living in this broken world but let’s assume that) እኔን ችሎ በእረፍት የማኖር ጉልበት የለውም::

በአጭሩ "ስኬት" እኔን አይችለኝም:: እኔን ችሎ በእርጋታ ሊያኖረኝ የሚችለው የእግዚአብሔር ሀልዎት ነው::

ህይወትን, ነገን face ለማድረግ አቅም የማገኘው , ያለምንም ደባል ንፁህ ደስታና እረፍት የሚሰጠኝን እርሱን ሳስብና ስከተል ብቻ ነው::

ስኬት must be redefined!

ስኬት ከእግዚአብሔር ጋር መራመድ ነው:: ስኬት የእኛን ትንሽነት ተቀብሎ እርሱን መስማት ነው::

ስኬት እዚአብሔርን በፍፁም ልብ በፍፁም ነፍስ በፍፁም ሀይል መውደድ መቻል ነው::

ስኬት በፀጋው መደገፍ ነው::

ስኬት ሰው የመሆንን ታላቅ ትንሽነት እና ታላቅነት በመረዳት መኖር ነው:: (If we think about it, we are unable to control anything in this world. we are so ምስኪን But at the same time we are also እጅግ ታላቅ because unlike many mighty creatures, He created us in His image as a result of which we shared many of His characters. Not only that, He loved us in a way that cannot make sense ኤፌ 3:18)
9👍2
Forwarded from The Truth (Mintesnot Meskele)
“Put on therefore, as the elect of God, holy and beloved, bowels of mercies, kindness, humbleness of mind, meekness, longsuffering;”
— Colossians 3፥12 (KJV)
10
Elizabeth 💙
16
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Flood this heart with assurance of Your mercy
Fill this mind with knowledge of Your love

Hold me fast through the deep and steady current
How long, how long ‘till these tears are gone?

Every hour, awake me to Your presence
Shine Your light, brighter than the dawn
Send Your joy, illuminate the darkness
How long, how long ‘till these tears are gone?

I'll fix my eyes on eternity above
Where every lie, is uncovered by Your love
Where every lie, every shadow is uncovered by Your love
4
የዳንኤል ፀሎት

በዘመነ መንግሥቱ በመጀመሪያው ዓመት፣ እኔ ዳንኤል ለነቢዩ ለኤርምያስ በተሰጠው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት፣ የኢየሩሳሌም መፈራረስ ሰባ ዓመት እንደሚቈይ ከቅዱሳት መጻሕፍት አስተዋልሁ።
( Daniel is mourning with the reality of his situation, seeking answer in Gods revelation which is divine ግን ደግሞ ለእርሱ የተሰጠው በመገለጥ ሳይሆን የተገለጠላቸው የፃፉትን በማስተዋል ነው።)

ስለዚህ ማቅ ለብሼ፣ በራሴም ላይ ዐመድ ነስንሼ፣ በጾምና በጸሎት፣ በምልጃም ፊቴን ወደ ጌታ አምላክ አቀናሁ። ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፤ ተናዘዝሁም"
(ያስተዋለው እውቀት በቀጥታ ወደሆነ ድርጊት አመራው። Unlike what we see these days እውቀቱ የሚያስታብይ ሳይሆን ትሁት የሚያደርግ ነበር። ማቅ መልበስ፣ ዐመድ መነስነስ፣ ፆም፣ ፀሎት፣ ምልጃ፣ ፊትን ወደ አምላክ ማቅናተ፣ መናዘዝ የሚሉት ቃላት በአውዳቸው ቢተነተኑ የተሸከሙት ብዙ ሀሳብ አለ። ብቻ መፍትሄ ወዳለው ትልቁ እግዚአብሔር ላይ የተዋረደን ራስ መጣል መልካም ነው።)
Look at how he addresses God in prayer:

ከሚወዱህና ትእዛዝህን ከሚፈጽሙ ሁሉ ጋር የፍቅር ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅ፣ ታላቅና የተፈራህ አምላክ፤ ጌታ ሆይ
(የእግዚአብሔርን ታላቅነት ከቃልኪዳን ታማኝነቱና ፍቅሩ ጋር አቆራኝተን አለማየታችን ምን ያህል የፀሎታችንን quality እንዳወረደው ይህ ማሳያ ነው። We run on extremes. We either use overly friendly casual words of affection fit for loved ones or fathers. Or we use words fit for a king that we tremble to approach. This reminds us that we always need both. ቀሪው ፀሎቱ ላስተዋለ እጅግ በጣም አስተማሪ ነው። ሀጥያተኛ ሊኖረው ስለሚገባ ስነመለኮት..ኑዛዜ ሊኖረው ስለሚገባ full accountability. ሰበብ አስባብ የሌለው ሀላፊነትን ወደሌላ ለማላከክ ጣት የማይጠቁም ከወዴት እንደሳተ የተረዳ ሰው ስለሚለምነው ልመና ያስተምረናል። He doesn't minimize his guilt. He doesn't lower Gods standards. ሀጥያታቸውን በስሙ ይጠራዋል እንጂ አደባብሶ አያሳልፍም። Its filled with emotional language. Pay attention to the pronouns. The verbs. The adjectives He uses for God.

እኛ ኀጢአት ሠርተናል፤ በድለናልም፤ ክፋትን አድርገናል፤ ዐምፀናልም፤ ከትእዛዝህና ከሕግህ ዘወር ብለናል። ለንጉሦቻችን፣ ለልዑሎቻችንና ለአባቶቻችን እንዲሁም ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በአንተ ስም የተናገሩትን አገልጋዮችህን ነቢያትን አልሰማንም

ጌታ ሆይ፤ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ለአንተ ታማኞች ባለመሆናችን እኛን በበተንህባቸው አገሮች ሁሉ የምንገኝ የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምና የመላው እስራኤል ሕዝብ፣ በሩቅም ሆነ በቅርብ ያለን በዚህ ቀን በኀፍረት ተከናንበናል። እግዚአብሔር ሆይ፤ እኛና ንጉሦቻችን፣ ልዑሎቻችንና አባቶቻችን በአንተ ላይ ኀጢአት ስለ ሠራን በኀፍረት ተከናንበናል።
ምንም እንኳ በእርሱ ላይ ያመፅን ብንሆን፣ ጌታ አምላካችን ይቅር ባይና መሓሪ ነው።
እግዚአብሔር አምላካችንን አልታዘዝነውም፤ ደግሞም በአገልጋዮቹ በነቢያት በኩል የሰጠንን ሕግ አልጠበቅንምመላው እስራኤል አንተን ባለመታዘዝ ሕግህን ተላልፎአል፤ ዘወርም ብሎአል። “በአንተ ላይ ኀጢአትን ስለ ሠራን፣ በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ ሕግ የተጻፈው መሓላና ርግማን ፈሰሰብን። ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ በማምጣት፣ በእኛና በገዦቻችን ላይ የተነገረውን ቃል ፈጸምህብን፤ በኢየሩሳሌም ላይ የተደረገውን የሚያህል ከሰማይ በታች ከቶ የለም። በሙሴም ሕግ እንደ ተጻፈው፣ ይህ ሁሉ ጥፋት በእኛ ላይ ደረሰ፤

ሆኖም ከኀጢአታችን በመመለስና እውነትህን በመከተል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ምሕረትን አልፈለግንም

አምላካችን እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ ጻድቅ ነውና፣ በእኛ ላይ እግዚአብሔር ጥፋት ከማምጣት አልተመለሰም፤ እኛም አልታዘዝነውም

አሁንም ሕዝብህን ከግብፅ ምድር በብርቱ እጅ ያወጣህ፣ እስከዚህም ቀን ድረስ ስምህ እንዲታወቅ ያደረግህ፣ ጌታ አምላካችን ሆይ፤

እኛ ኀጢአትን ሠርተናል፤ አንተንም በድለናል። ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ እንዳደረግኸው የጽድቅ ሥራህ ሁሉ፣ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም፣ ከቅዱሱም ተራራህ ቊጣህን መልስ፤ በእኛ ኀጢአትና በአባቶቻችን በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ባሉት ዘንድ መሣለቂያ ሆነዋል።

አሁንም አምላካችን ሆይ፤ የአገልጋይህን ጸሎትና ልመና ስማ። ጌታ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል ፊትህን ወደ ፈረሰው መቅደስ መልስ። አምላክ ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፤ ዐይንህን ገልጠህ መጥፋታችንንና ስምህ የተጠራበትን ከተማ ተመልከት

ልመናችንን የምናቀርበው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን፣ ስለ ታላቅ ምሕረትህ ነው
ጌታ ሆይ፤ አድምጥ!
ጌታ ሆይ፤ ይቅር በል!
ጌታ ሆይ፤ ስማ!
አድርግም፤
ስምህ በከተማህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና አምላኬ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል አትዘግይ።
(ዳንኤል 9)
10👍3🙏1
ንጉስን በለሊት ለሚጠጣ ውሃ ሊያነቃ የሚችለው ጨቅላ ልጁ ብቻ ነው። በክርስቶስ በኩል ለእኛም ያ ልጅነት ተሰጥቶናል። "በረባ ባልረባው" ሳንለምነው የሚያስፈልገንን ሁሉ ወደሚያውቀው አምላክ በፀሎት ለመቅረብ አንስነፍ። If anything it solidifies our intimacy. And as long as what we ask for is in His will, He will answer.
18👍1
“እግዚአብሔርን መታመኛው ያደረገ፣ ወደ ትዕቢተኞች የማይመለከት፣ የሐሰት አማልክትን ወደሚከተሉት የማያይ፣ ሰው ብፁዕ ነው።”
“Blessed is the man who makes the Lord his trust, who does not look to the proud, to those who turn aside to false gods.”
Psalms 40:4
9
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Don't despise your suffering because without it you could never be like the one who came to this world to suffer and save you 💙
ዕዝራ የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናትና በማድረግ፣ ለእስራኤልም ሥርዐቱንና ሕጉን በማስተማር ራሱን ፈጽሞ ሰጥቶ ነበር።

For Ezra had devoted himself to the study and observance of the Law of the Lord, and to teaching its decrees and laws in Israel.
— Ezr 7:10
10
Pursuing Holiness
ዕዝራ የእግዚአብሔርን ሕግ በማጥናትና በማድረግ፣ ለእስራኤልም ሥርዐቱንና ሕጉን በማስተማር ራሱን ፈጽሞ ሰጥቶ ነበር። For Ezra had devoted himself to the study and observance of the Law of the Lord, and to teaching its decrees and laws in Israel. — Ezr 7:10
What we need are these types of men instead of the toxic masculine or fragile feminine men among us.

የእግዚአብሔርን ህግ
1, ለማጥናት
2, ለማድረግ
3, ለማስተማር
ራሳቸውን ፈፅመው የሰጡትን ያብዛልን። ያሉትንም እንድንለይ ጥበብ ይስጠን።
15👏1
መጽሐፈ መክብብ ጥናት (Part 1)

የመጽሐፉ ዓላማ
የመክብብ መፅሀፍ በይዘቱ ምክኒያት ከጥበብ መፅሀፍቶች መሀል ብዙ ጊዜ misunderstood የሆነ ወይንም ደግሞ ከነአካቴው ቸል የተባለ መፅሀፍ ነው።Joy is the underlying theme of the book. Its not as cynical or fatalistic as people assume. እውነታን ያለማደባበስ ይመረምራል እንጂ ድባቴንና ጨለምተኝነትን የሚያበረታታ መፅሀፍ አይደለም። አንባቢያኑ ከጸሐይ በታች (በምድር ላይ) የሕይወት ትርጉምን ከእግዚአብሔር ውጪ በመፈለግ እንዳይባዝኑ ፀሀፊው በሄደበት መንገድ ተጉዘው ከራስ ልፋት ከመማር ጥበብን ከእግዚአብሔር ሕግ እንዲማሩና እና ለመጨረሻው ፍርድ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የሚሞግት ውብ መፅሀፍ ነው። በአጠቃላይ አንድ ሙሉ ሰው ስለራሱ ሊኖረው ስለሚገባ ግምት፣ እግዚአብሔር መፍራት ማለት በተግባር፣ በስሜት ፣ በስለመለኮታዊ እምነት ምን እንደሆነ ፣ ከእግዚአብሔር ውጪ ያለው ነገር ሁሉ ከንቱ/ አላፊ እንደሆነ ፣ የስራንና የደስታን ግኑኝነት አጭቆ ይዟል።

Some commentaters read it as a tract for other nations. This explains why he didn't go into the detail of the law or use the covenantal name of God 'Yahweh' and used the title Elohim to refer to the God who is exalted. Because Solomon had diplomatic relationships with plenty of nations its plausible that his correspondence and conversations inspired some of the themes he raised. Nations heard that Israel was successful and blessed beyond others which might create curiosity to learn about the living and exalted God who had blessed Israel with wealth and wisdom.

ጸሐፊው
ሰለሞን መሆኑን ብዙ አያሻማም ራሱን “በኢየሩሳሌም የነገሠው የዳዊት ልጅ” ብሎ ስለሚያስተዋውቅ። ነገርግን በመፅሀፉ ጥንቅር ወቅት ቢያንስ መግቢያና መደምደሚያው በኋላ የታከለ የመሆን እድሉ ከፍ ያለ ነው። ስለዚህ እግዚአብሄርን በለጋነቱ ጥበብ የለመነው ሰለሞን ምናልባትም በእድሜው ማምሻ የፃፈው መፅሀፍ ነው።

አንባቢ
“ሰባኪውም ጠቢብ ስለ ሆነ ለሕዝቡ እውቀትን አስተማረ..”
12፥9 ሲል በግልፅ ተደራስያኑ የተወሰኑ ሰዎች ሳይሆኑ በጠቅላላው ህዝብ ናቸው ማለት እንችላለን። በተጨማሪ ደግሞ በተደጋጋሚ “ልጄ ሆይ” እያለ ስለሚፅፍ ለተማሩ ታዳጊ ወጣቶች ትኩረት የሰጠ መፅሀፍ ነው ማለት እንችላለን። አንዳንድ ምክሮቹ በቀጥታ ወጣት ወንዶችን address የሚያደርግ ስለሆነ ምናልባት ለእስራኤል ቀጣይ ተተኪ ተስፋ ለሆኑና ለመሪነት ለሚታሰቡ ወጣቶች ምክርን እንደሰነቀ መረዳት እንችላለን።

የተፃፈበት ጊዜ
- ከ 10ኛው - 3ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይገመታል፡፡

ክርስቶስ በመክብብ ውስጥ

መክብብ ከፈጣሪው የተለየ ሰው ስለሚኖርበት ባዶነትና ውስጣዊ ሰቆቃ የሚከትብ መፅሀፍ ነው።ጨሀቀኛ የሆኑ ጥርጣሬዎች፣ ተስፋና ፍርሃቶች አሉት። ዘላለማዊነትን በልባችን ያኖረው አምላክ ወደዚህ ፍጥረቱ የገባው ለዚህ ነው። Ultimate የሆነ እርካታ ጥበብና ፍስሀ የሚገኘው በክርስቶስ ብቻ እንደሆነ in hindsight በመገንዘብ ማኖበብ እንችላለን። መፅሀፋ ውስጥ ሰባኪው ታትሮ የሚፈልገውን መልካም (the chief good) በአዲስኪዳን እንዳለን አማኞች በክርስቶስ ውስጥ እንደሚገኝም እንማርበታለን።

ማውጫ
1, መግቢያ ።(1:1-11)
2, በጥበብና በደስታ ውስጥ መልካም የሆነውን መፈለግ
2.1 ጥበብና ደስታን ፍለጋ 1:12-2:11
2.2 የጥበብና የደስታ ንፅፅር 2:12-26
3,በንግድና በስራ ውስጥ መልካም የሆነውን መፈለግ
3.1 በፍለጋው ላይ ያለው የእግዚአብሔር ውሳኔ (3:1-15)
3:2 የሰው ፍትህአልባነትና perversity (3:16-4:3)
3.3 የሰው ጠላቶች (4:4-8)
3.4 የተሻለው የትብብር መንገድ 5 ምሳሌዎች (4:9-16)
3.5 አምልኮተ እግዚአብሔር (5:1-7)
3.6 በእግዚአብሔር መታመን (5:8-20)
4, በሀብት ውስጥ መልካም የሆነውን መፈለግ
4:1 ብልጥግናን ማሳደድ (6:1-12)
4:2 ሚዛናዊነትን መፈለግ (7-8:15)
5, Conclusion of search for the chief good
5:1 የጥበብ ከንቱነት (8:16-9:6)
5:2 የደስታ ከንቱነት (9:7-12)
5:3 የንግድና ትርፉ ከንቱነት (9:13-10:20)
5:4 The good in wise use and enjoyment of life (11:1-8)
5:5 The chief good in a faith in the life to come (11:9-12:8)
6, መደምደሚያ (12:9-14)
10👍2
Question 1
What is your only comfort in life and in death?

Answer
That I am not my own, but belong - body and soul, in life and in death - to my faithful saviour Jesus Christ.
He has fully paid for all my sins with His precious blood and has set me free from the tyranny of the devil. He also watches over me in such a way that  not a hair can fall from my head without the will of my Father in Heaven.
Infact all things work together for my salvation. Because I belong to Him, Christ, by His Holy Spirit [He] assures me of eternal life and makes me wholeheartedly willing and ready from now on to live for Him.
ይህ የHeidelberg Catechism መግቢያ ጥያቄ ብቻ ባፕቲስትነትን የሚያስኮበልል ውበት አለው 😊
አለም ላይ ምቾት ሊሰጡ ቃል የሚገቡ ብዙ ነገሮች ቢኖሩም ቃሉ እንደሚለው ኑሮ በምድር ውስጥ ብርቱ ሰልፍ ነውና ትግል የሞላውን ህይወት፣ እንዲሁም ሞት ለመጋፈጥ የሚያበቃ አስተማማኝ የሆነ security ሊሰጥ የሚችል ምንም ነገር የለም ።

አባቶቻችን ስደትና ሞትን በደስታ የተቀበሉበት መረዳት ግን ይሄ ነው፡የራሳችን አይደለንም! ብለው ራሳቸውን effectively abandon አድርገውት ነበር። "Don't set a goal to seek whats expedient for you. Forget yourself and all that is yours. You belong to God. Live and die for Him!" John Calvin

የምንኖርለትን አላማና መኖርያችንን ለባለቤታችን ከሰጠን ያለርሱ ፈቃድ ምንም ስለማይሆን በህይወትም ሆነ በሞት ሳንበረግግ በኛ ላይ ሉዐላዊ ስልጣን ባለው አባታችን ባረፍን ነበር።

ምንም እንኳ የእጁ ስራ ስለሆንን አስቀድሞም በኛ ላይ መብት ቢኖረውም ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ በጌታ ኢየሱስ ክቡር ደም ገዛን ፤ በቤዛነቱም የሀጥያት ይቅርታ አገኘን። የጌታ መሆን እንዴት መታደል ነው? ከእርሱ የሚያመልጥ ምን detail አለ? ያለእርሱ ፈቃድ ምንም አንሆንም። አለምን የሚያሸብረው ሞት ቢመጣ እንኳ ወደላቀ ክብርና ወደአባታችን ዕቅፍ እንደምንገባ መንፈሱ ለመንፈሳችን ይመሰክርልናል! ስለዚህ ከሚያስፈራው ሞት ፣ ከሰይጣን እንዲሁም ከነበርንበት የሀጥያት ባርነት ነፃ ስለወጣን በውስጣችን ያደረው መንፈስ ለጌታ እንድንኖር ያበረታናል።

This is our ONLY comfort in life and in death. As Kevin Deyoung said Comfort isn't the absence of pain its the certainty we feel after understanding that there is a greater joy from anticipated suffering we may face. We can rest in the fact that we will live as long as God wants us to live and He will provide what we need to do what He wants us to do for His fame and glory because WE BELONG TO HIM.

ሉቃስ 12:6-7, 23-31, ማቲ 6:25-33
9👍1
“.. የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።” ሮሜ 12፥16
“በዓይናቸው ጥበበኞች በነፍሳቸውም አስተዋዮች ለሆኑ ወዮላቸው!” ኢሳይያስ 5፥21
“አቤቱ፥ ልቤ አይታበይብኝ፥ ዓይኖቼም ከፍ ከፍ አይበሉብኝ፤ ከትልልቆች ጋር፥ ከእኔም ይበልጥ ከሚከበሩ ጋር አልሄድሁም።” መዝሙር 131፥1

Pride is the beginning of sin. And what is pride but the craving for undue exaltation? And this undue exaltation- when the soul abandons Him whom it ought to cleave as its end, and becomes a kind of end to itself. St Augestine

ትዕቢት የሀጥያት አሀዱ ነው። ያልተገባንን ልህቀት ከመቋመጥ ይልቅ ብቻውን ምጡቅ የሆነውን የሙጥኝ በማለት ቦታችንን እንያዝ። "እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔርም ፊት ቃልን ይናገር ዘንድ ልብህ አይቸኵል፤ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።” መክብብ 5፥2
2
“ጻድቃንና ጠቢባን ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፤ ፍቅር ወይም ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም ሁሉ ወደ ፊታቸው ነው።”
“So I reflected on all this and concluded that the righteous and the wise and what they do are in God's hands, but no man knows whether love or hate awaits him.”
— መክብብ 9፥1

ህይወቴን በእጁ የያዘ..መንገዴን የሚቀይሰው
አምላኬ እርሱ ብቻ ነው 🎶
8
እግዚአብሔር ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁ፤ አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፤ እባክህ አታሳፍረኝ፤ ጠላቶቼም አይዘባነኑብኝ።አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ ከቶ አያፍሩም፤ ነገር ግን እንዲያው ያለ ምክንያት፣ ተንኰለኞች የሆኑ ያፍራሉ።

እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝአንተ አዳኜ፣ አምላኬም ነህና፣ በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።

እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህንና ፍቅርህን አስብ፤ እነዚህ ከጥንት የነበሩ ናቸውና። የልጅነቴን ኀጢአት፣ መተላለፌንም አታስብብኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣ እንደ ምሕረትህም መጠን ዐስበኝ

እግዚአብሔር መልካምና ቅን ነው፤ ስለዚህ ኀጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋልዝቅ ያሉትን በፍትሕ ይመራቸዋል፤ ለትሑታንም መንገዱን ያስተምራቸዋል። ኪዳኑንና ሥርዐቱን ለሚጠብቁ፣ የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ናቸው

እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአቴ ታላቅ ነውና፣ ስለ ስምህ ይቅር በልልኝ

እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በተመረጠለት መንገድ ያስተምረዋል። ዘመኑን በተድላ ደስታ ያሳልፋል፤ ዘሩም ምድርን ይወርሳል። እግዚአብሔር ምስጢሩን ከሚፈሩት ወዳጆቹ አይሰውርም፤ ኪዳኑንም ይገልጥላቸዋል።

ዐይኖቼ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤ እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነውና።

እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ። የልቤ መከራ በዝቶአል፤ ከጭንቀቴ ገላግለኝ። ጭንቀቴንና መከራዬን ተመልከት፤ ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።

ጠላቶቼ እንዴት እንደበዙ ተመልከት፤ እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ እይ። ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም፤ መጠጊያዬ ነህና አታሳፍረኝ።አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ። አምላክ ሆይ፤ እስራኤልን፣ ከመከራው ሁሉ አድነው
መዝሙር 25
9
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Are you still under the illusion that Jesus is merely a part of your life that you chose? Where else do you think you can go to replace everything Christ is to you and all that He has done for you?

If we are indeed His disciples, our pilgrim journey must begin with acknowledging that we have no where else to go. በሰማይ አለን የምንለው ማነው? በምድርም ከእርሱ በላይ ልንሻው የተገባ የለም።

This is beautiful and painful moment of christians where they empty themselves of all their egos and submit. Let us now confess that all we have is Christ..የህይወት ቃል ያለው እርሱ ህይወታችን ነው። He is the one we trusted for our eternity. He's the one revealed in all the scriptures we read.

ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ህይወት ቃል አለህ። አንተ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደሆንህ አምነናል አውቀናልም። (ዩሃ6:68)
6👍2
Forwarded from Mahlet Mesfin
ቅድስና ለእግዚአብሔር

ቅድስና ለእኛ አይደለም 🙂:: የአእምሮ እረፍት የውስጥ ደስታ ማግኘት የቅድስና ቱሩፋቶች ናቸው:: ልክ የሀጢያት ቱሩፋት ከሞት በተጨማሪ ድብርት ፍርሀት ሀዘን እንደሆነው ሁሉ ማለት ነው::

ነገር ግን በቱሩፋቶቹ ብቻ inspired በመሆን መቀደስ ጣጣ አለው:: እያንዳዳችን ለራሳችን ከባድ ወይም አስቀያሚ የምንለው ሀጢያት ይኖረናል … ማለት ምርር አርገን የምንጠላው ሀጢያት ልንገልፀው እንችላለን :: ከዚህም የተነሳ በፍፁም በዚህ ነገር መያዝ የለብንም ብለን እጅግ ቆራጥ ውሳኔ የምናደርግበትና ስተን ስንገኝም እጅግ የምንፀፀትበት አልቅሰን ይቅርታ የምንጠይቅበት ማለት ነው:: ይህ በራሱ ጥሩ ነገር ነው:: ግን ቆራጥ የምንሆንበት ዋናው ምክንያት ጌታን ለማስደሰት ሳይሆን ሀጢያቱ ከእኛ value መውረድ/መጋጨት ጋር መያያዙ እና የሚያስከትላቸው ደስ የማያሰኙ ስሜቶችን እንጂ እግዚአብሔርን እንደበደልነው ገብቶን ካልሆነ ultimately ለመቀደስ እየጣርን ያለነው ለራሳችን ነው:: የዚህ አስተሳሰብ ሌላኛው መዘዝ ደግሞ ለእኛ ያን ያህል የማያሳስቡና የሚያስጠሉን ግን still ሀጢያት የሆኑ ነገሮችን ችላ ብለን በጣም በብዙ ሀጢያት ሳናውቀው ህይወታችን ይታሰራል:: ቅድስና ግን primarily ስለእኛ መደሰት ወይም mental satisfaction እይደለም ለእግዚአብሔር መስዋዕት ስለመሆን ነው:: የምንቀደሰው ለእግዚአብሔር ነው::
13
Forwarded from Mahlet Mesfin
መዝ 23(6) - እንዴት ነው ምህረቱና ቸርነቱ የሚከተሉን?

Chad Bird የተባለ ፀሐፊ "ይከተሉኛል" የሚለውን ቃል የትኛውንም አይነት ተራ መከተልን ከማመልከት ያለፈ ትርጉም እንዳለው ያብራራል።

"ይከተሉኛል" ተብሎ የተተረጎመው ቃል በእብራይስጥ "Radaph" ነው። ይኼም አንድን እጅግ ተፈላጊ ሰው እንዳይጠፋ ከኋላ ኋላው ማሳደድን ያመለክታል። እዚህ ጋር የሲ. አይ. ኤ ወይም ሞሳድ ወይም ኬጂቢ የስላለ ድርጅቶች አንድን እጅግ ተፈላጊ ሰው ጂፒኤስ፣ ድሮንና ዘመናዊ መሳሪያዎች ተጠቅመው ደብዛው እንዳይጠፋ የገባበት እየገቡ በጥብቅ መከታተልን የሚመስል ጥልቅ ትርጉም አለው። ይኼም ምናልባትም "ጥብቅ ክትትል ማድረግ" ከሚለው የስላላው ዓለም ሀሳብ ጋር ተስማሚ ነው!!

እናም Chad ይላል፦ "ቸርነቱና ምህረቱ እንደ ተጎታች የቤት ውሻ ከኋላ ኋላችን አይከተሉንም። ወደየገባንበት ሰርጥና ጉራንጉር ሁሉ በእሳት ሰረገላ እያሳደዱ ይከተሉናል።

ወንጀለኞችን ለማደን እንደ ሰለጠነ ውሻ በለያችን ያለውን ሰማያዊ ጠረን እያሸተቱ ያሳድዱናል። ከእግራችን ዱካ አይርቁም፤ ኮቴያችንን አይለቁም።

ቸርነቱና ምህረቱ ወደ ሰማይ ደጅና አባታችን እቅፍ እስክንገባ ከኋላ ኋላችን ያሳድዱናል።"

አንዳንድ ቅጂዎች ደግሞ "በእግዚአብሔር ቤት ለዘላለም እኖራለሁ" በሚለው ሀሳብ "እኖራለሁ" የሚለውን "ወደ መኖር እመለሳለሁ" ["Shall return to dwell" ESV Study Bible footnote] ይላሉ። ይኼም በቸርነትና ምህረቱ ክትትል ከተቅበዘበዘበት ተነድቶ በመመለስ ወደ ዘላለም ዕረፍት መግባትን ያመለክታል።
15
2025/07/14 15:33:54
Back to Top
HTML Embed Code: