Telegram Web Link
There is this cool insight I got from Dane Ortlund.

በተደጋጋሚ ስለእግዚአብሔርና ስለእስራኤል መስተጋብር ስናነብ በአመፃችሁ ምክኒያት "ቁጣዬን አነሳሳችሁት" ወይንም "ቀሰቀሳችሁት in other words provoke አደረጋችሁት ይላቸውና በተቃራኒው ደግሞ በሚያሳዩት ማንኛውም አይነት የልብ ስብራትና ራስን ማዋረድ ምህረት ለማድረግ ሲቸኩል፣ ቸርነትን ሊያደርግ ወደእነርሱ ቶሎ ሲመለስ እናያለን። ለልጆቹ የሚቀናው መልካምነት ነው። Its easy for Him to be gracious. ቁጣውን በእምቢተኝነታቸው ካልቀሰቀሱት በቀር...

በተቃራኒው እኛ ሰዎች ደግሞ አመፅ ይቀናናል። ሁላችን ለራስወዳድነት የተጋለጥን ነን። የምንቸኩለው ለጥፋት ነው። ቶሎ የምንመለሰው ወዳልገደልነው አለማዊነታችን ነው። This is why it says in hebrews that Hebrews 10:24 "Let us consider one another to provoke unto love and to good works: Not forsaking the assembling of ourselves together, as the manner of some is; but exhorting one another: and so much the more, as ye see the day approaching."

ከቅዱሳን ጋር ባለን ህብረትና በሌሎቹ የፀጋ መሳርያዎች (በቃሉ፣ በፀሎት፣ በጌታ እራት.." ካልተነቃቃን (provoke ካልተደረግን) በስተቀር ከፍቅርና ከመልካም ስራ እጅግ የራቅን ነን። This is why godly friendships are very very crucial. I hope and pray we don't take it for granted.

ምክኒያቱም እንደክርስቲያን አለም አልተገባችንም። ከሷ መወዳጀት ከእውነተኛው ወዳጃችን ጋር ጠላትነት ነው። በደፈናው አማኝ ነን ከሚሉትም መሀከል የኛ ቢጤ ናፍቆት፣ የኛ ቢጤ ጉጉትና መሻት ያላቸውን እንድንፈልግ የሚመራን ደመነፍስ አለ። ሰውን ገንዘብ የምናደርገው የሆነ መስፈርት አውጥተንለት ያንን ስላሟላ ሳይሆን የጋራ አባት፣ የጋራ ታላቅ ወንድምና የጋራ አፅናኝ ስላለን ነው። አብ የመረጣቸው፣ ወልድ የተቤዣቸው፣ መንፈስ ዳግም የወለዳቸው ሁሉ (ወደድንም ጠላን) የኛ ወገን ናቸው። If you have to be tribal, belong and be thrilled that you get to be in that tribe.

እነዚህ ወንድሞቻችን ደግሞ ወደምንወደው ጌታ የሚገፉን፣ ጣርያ ገንጥለው ኢየሱስ ጋር የሚያደርሱን ብቻ ሳይሆኑ አንዳንዴ የሚያቆስሉን አካሎቻችን ናቸው። ምን ያህል ቢያበሽቁን ቆርጠን አንጥላቸውም። ምንም ቢሆን እነርሱ ከበደሉን በላይ እኛ ንፁሁን እግዚአብሔር በድለነዋል። ምንም ቢሆን በአንድ ወቅት በእነርሱ በኩል የምንወደውን ጌታ ድምፅ ሰምተነዋል። ስለዚህ ስለተጠሩበት "ክርስቲያን" የሚል የቤተሰብ ስም፣ ስለምንጋራው እግዚአብሔርን የመምሰል መሻት ስንል ራሳችንን የሁሉ አገልጋይ፣ ይቅር ባይ፣ ሆደ ሰፊ በማድረግ lets treasure our brethren. ምክኒያቱም ያለእነርሱ provocation መልካም የምንሰራ የፍቅር ሰዎች አንሆንም። ፍቅር by definition object ይፈልጋል። ለብቻችን የምንማረው ትምህርት አይደለም። Genuine የሆነ መልካም ስራ ለመስራት የግድ ትክክለኛ የሆነ ጉድለትን የሚያስተውሉ ሩህሩህ አይኖች ያስፈልጉናል። ይህም ለብቻ ምሽግ በመግባት አይመጣም። ለነዚህ ሁሉ በረከት ምንጭ ስለሆኑ ወንድምና እህቶቻችን እግዚአብሔር ይመስገን ለማለት ነው 😊
19👍1
እስራኤል እንዲህ ይበል፦ “ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ። በርግጥ ከልጅነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ አስጨነቁኝ፤ ዳሩ ግን ድል አላደረጉኝም። ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤ ትልማቸውንም አስረዘሙት።
እግዚአብሔር ግን ጻድቅ ነው፤ የክፉዎችን ገመድ በጣጥሶ ጣለው።
ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ፣ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ይሁኑ፤ ደግሞም ለዐጫጅ እጁን፣ ለነዶ ሰብሳቢ ዕቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ። መንገድ ዐላፊዎችም፣ “የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንባርካችኋለን” አይበሉ። (መዝ 129)

ይህ ክፍል ፀረ እግዚአብሔር የሆኑ አሳዳጆች በእግዚአብሔር ህዝብ ላይ ስላስነሱት መከራ ፣ ስለመከራው ፅኑነትና መራርነት፣ በስደቱ ውስጥ ስለነበረው የእግዚአብሔር ታማኝነትና ታዳጊነት እንዲሁም ስሉአሳዳጆች የመጨረሻ እጣፈንታ ያትታል።

የምንኖርበት አለም የእግዚአብሔርን ነገር የሚቃወቀም እንደመሆኑ ደግሞ በፅድቅ ከእግዚአብሔር ጋር የማንወግን ከሆነ የሚኖረን ሌላ አማራጭ ወደድንም ጠላንም ከእርሱ ጋር ተፃራሪ በሆነ system ውስጥ መሰንበት ነው። Unfortunately there is no middle ground. There is no neutrality.

ይሄ ነው እንግዲህ የሰውን ልጅ ህይወት ሰልፍ የሚያበረታው፡፡ የክርስቲያን የመናኝ ጉዞ አሸነፍን ሲሉ ብዙ ጊዜ የሚወድቁበት ፤ አንድ ተራራ ወጣው ሲሉ ያልታየ ሸለቆ ውስጥ የሚወረወሩበት ብዙ ጥጋጥግ አለው፡፡ እረፍትና መረጋጋት በጦርነት ኬላ ስለማይገኝ መባዘን የደከመው ሁሉ ዝለቱን ተሸክሞ ይጋደምና በአዕምሮው ደግሞ እዚ እዛ እያለ ወደሌላ አይነት እንግልት ይሸጋገራል።

የሠራዊት ጌታ የሆንከው እግዚአብሄር፤ አንተ ጣቶችን ለሰይፍ ማስታጠቅ ብቻ ሳይሆን ዘለቄታዊ የሆነ እፎይታ መስጠትን ታውቅበታለህ። ይህን የሚያውቅ ልቤ ነው እንግዲህ አንተን ጌታዬን ትቶ ሊያጠፉኝ የሚመኙ የአንተ ጠላቶች (ገና ከአንተ መንግስት ጋር በአግባቡ መራመድ ሳልጀምር በልጅነቴ ከሚያስጨንቁኝ) ጋር ይላመዳል፣ አንፃራዊ ሰላም ይመሰርታል።

ያም ሆኖ ግን መከራው አልቀረልኝም። ቃልህ እንደሚል መከራ ቃል ከተገቡልን ነገሮች መሀል ነው። መነጫነጭ ለምዶብኝ እንደ self fulfilling prophecy ራሴ ላይ ማመጣው ነገር ቢሆን እንደአንዳንዶች እኔም ችግሬን መካድ እስኪያምረኝ ድረስ ነው የደከመኝ.. አቤቱ ሸክም የደከማቸውን ድኩማን ልታሳርፍ የምትጠራው፣ መንፈሳቸው ለተሰበረ ቅርብ የሆንከው ጌታ ሆይ ፈጥነህ ድረስልኝ፡፡ የማዳንህን ደስታ መልስልኝ እንዳለ ባርያህ ባንተ ረክቼ ደስታህ ሀይል ሆኖኝ ውጊያውን በታደሰ ሀይል ልቀጥል..

ቃልህ እንደሚል አንተን ሊመስል የሚወድ ሁሉ ይሰደዳል፡፡ ታድያ የኔ ስደት እንደአባቶቼ ስለመንግስትህ፣ ስለተሸከምኩት ስምህ ከጠላቶችህ የሚመጣ ሆኖ በመከራዬ ምመካው መቼ ነው? እንዲሁ ከራሴ ጋር ስታገል- ስሸነፍ ለመቀደስ ስፍጨረጨር- ስሰንፍ .. ስጋዊ ምኞቴን መግደል ተስኖኝ ስጋዬ እኔን እያሳደደኝ እኔም እየተሸነፍኩለት እንድኖር ለምን ፈቀድክ? አንድ ወንድሜ እንዳለ ከውጪ ስለስምህ መከራን መቀበል ቅንጦት ሆኖብኝ ይቅር?

በእርግጥ መከራዬ ከምንም በላይ አቅሜን አሳይቶኛል፡፡ እስትፋሱ አፍንጫው ላይ ያለን ሰው አትደገፍ ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው የሚለው ጥቅስ እኮ ስለ ሌላ ምስኪን ስጋ ለባሾች እንጂ ስለኔ አይመስለኝም ነበር.. ትዕቢት ክፉ ነው። ስብዕናንም ያስረሳል፡፡ ህይወቴ ላይ ምንም ስልጣን እንደሌለኝ  ከመከራ በላይ ማን አስረዳኝ?

When things relatively went well I had the illusion that I was in control..ቃልህ እንደሚል ትንፋሽና መንገዴን የያዘው ማን እንደሆነ የተረዳሁትን ግን  በሰላሙ ጊዜ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ እንድመስልህ ያለኝ ፍላጎት ከመከራ የማረፍ ጉጉቴ እንዲበልጥ ልቤን አበርታልኝ፡፡ ልፍስፍስ ምሳሌዎች የሉኝምና አጀግነኝ፡፡

ምስጋናዬን አዘርፌ ድባቴ እንዳይወርሰኝ በምህረትህ በጎነት አገልግለኝ፡፡ አባቴ ነህና የፍቅርህን ልክ ለአፍታም ጥያቄ ውስጥ መክተት አልፈልግም፡፡ ይልቁንስ እንደቀድሞ በአንተ እንድረካ ድምፅህን ወደምሰማበት እግርህ ስር አሳርፈኝ፡፡ የሚያፀናውን ፀጋ ተቀብዬ እንድነሳ እግሮቼን ለመንበርከክ አስቸኩል፡፡

አልታዘዝ ባዩን ልብ መስበር እንደምትችል ምስክር ነኝና ሳስቸግር ገስፀኝ ፤ እንዳላሳዝንህም ጠብቀኝ፡፡ ከአንተ ሌላ ሀብት የሌለኝ ፤ ለዘለዓለሜ የታመንኩህ የምጠብቅህም አለኝታዬ አንተ ብቻ ነህ፡፡ ምድር ልትቸር የምትችላቸውን በረከት ሁሉ ማግኘት ለአንድ ቀን የአንተ ባርያ ከመሆን አይወዳደርም፡፡

አንተ ፍፁም ፃዲቅ ፣ ፍፁም ፍቅር ፣ ፍፁም ታማኝ ፣ ፍፁም በጎ እጅግ ታላቅና ቅዱስ ነህ፡፡ አንተን ማወቅ ራሱ መታደል ነው፡፡ ስምህን መጥራት በረከት ነው፡፡ እንዲቀልብኝና እንድለምደው አልፈልግም፡፡

የከበርከው አምላኬ ሆይ በእኔ ሁኔታ የማይገመት ጥበብ እንዳለህ አውቃለው፡፡
“ብንነቃም ሆነ ብናንቀላፋ ከእርሱ ጋር በሕይወት እንድንኖር" የሞትክልን ኢየሱስ የአንተ እጅ ስለያዘው ህይወቴ አብዝቼ መጨነቄ ከንቱነቱ ገብቶኛል፡፡ እምነቴን አበርታውና ከዚህ በላይ ጥገኛህ ሆኜ ልደገፍህ፡፡ እረፍቴ ፣ ብርታቴ ሰላሜም ቃልኪዳንህን የምትጠብቀው ቸሩ እረኛዬ የነፍሴ ንጉስ ክርስቶስ ነህ፡፡

ከአንተ ጋር ወግኖ መሰደድ ክብር ነው። የአንተ ሰልፍ ውስጥ ገብቶ መቁሰል ትምክህት ነው። ጌታ ሆይ ከሁሉ አስበልጬ መንግስትህን እንድሻና ከዚህ በረከት እንዳልጎድል ጣቶቼን ለሰልፍ አሰልጥን።
20👍1
መከራዬ በአብዛኛው አንተን ከመርሳቴ ይመነጫል። ጥበብህን እየረሳሁ እጨነቃለሁ። ፀጋህን እየረሳሁ እለግማለሁ። ምህረትህን እየረሳሁ ቂም ይዛለሁ። እባክህን ማንነትህ ዘወትር አስታውሰኝ!
34🙏2
በርጠሚዮስ ነኝ አይነ ስውር ሚስኪን
ከሩቅ የሰማሁኝ የጌታዬን ድምፁን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሀል
የክርስቶስ ድምፁ ከሩቅ ይሰማኛል..

የከበበውን ሰው ገለል በሉ እያለ
በደሌን በደሙ ዋጋ እየከፈለ
ስለኔ የሞተው ኢየሱስ ይመጣል
የልቦናዬን አይን ገልጦ ያሳየኛል..

አብዝቼ እጮሃለው ጌታ ማረኝ ብዬ
በግልፅ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
በውስጤ  በደልስ ህይወቴ ዝላለች
ባምላኬ ቸርነት ህይወት ካላገኘች!
ይልማ 🎶


ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዐይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።

እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በሰማ ጊዜ፣ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር።

ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤

እርሱ ግን፣ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ።

ኢየሱስም ቆም ብሎ፣ “ጥሩት” አላቸው።

እነርሱም ዐይነ ስውሩን፣ “አይዞህ፤ ተነሥ፤ ይጠራሃል!” አሉት። እርሱም ልብሱን ጥሎ ብድግ በማለት፣ ተነሥቶ ወደ ኢየሱስ መጣ።

ኢየሱስም፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው።

ዐይነ ስውሩም፣ “መምህር ሆይ፤ እንዳይ እፈልጋለሁ” አለው።

ኢየሱስም፣ “ሂድ፣ እምነትህ አድኖሃል” አለው።

ወዲያውም ዐይኑ በራለት፤ በመንገድም ኢየሱስን ተከትሎት ሄደ።
ማርቆስ 10:46
17
Original_song_Yosef_Ayalew_koterkegni_Ende_Balemareg(256k)
<unknown>
ቆጠርከኝ እንደባለማዕረግ
ሳልለፋ ምንም ሳላደርግ
ምህረትህ በዝቶልኝ በላዬ
ኸረ ደግ እኮ ነህ ጌታዬ!
ልናገር እኔስ ቸርነትህን
አላውቅም ክፉ መሆንህን..

እኔማ ይገርመኛል ሁልጊዜ ይደንቀኛል
እኔማ ይገርመኛል ሳስበው ይደንቀኛል

ሹመት ሆኖልኝ ነው ከአብ የተወሰነ
ማንም የማይቀያይረው ከላይ የሆነ
ልጄ ነህ ብሎኛል ምን ልበል ይህ ማዕረጌ ነው
ውስጤን መደነቅ ሞልቶታል ለእኔ በሆነው

በህልሜ በእውኔም አስቤ የማላውቀውን
ብዙ አድርገህልኛል ያልጠበኩትን
ልዘምር በገናዬን ላንሳ ቅኔን ልደርድር
ግሩምና ድንቅ የሆነውን ስራህን ልናገር

አይቆጠር እንዲሁ አይባል ቸርነትህ
የማይለወጠው ፍቅር የአባትነትህ
ኧረ እንዴት ብዬ እገልጸዋለው ያረክልኝን
ከቁጥር በላይ የበዛው የዋልክልኝን
11
Psalms 136 (Sermon Notes)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
The focus of this psalm isn't hard to find. Its repeatedly emphasized with the phrase "His love endures forever." The word translated as love is the hebrew word chêçêd. Its an incredibly hard word to translate due to its wide range of possible meanings. The main ones can be summarized with these ways.
1, Steadfast Love: ፅኑ፣ የማይወድቅ ፍቅር
2, Indescribable tenderness: motherly softness and gentleness
3, Heart melting faithfulness and loyalty : ተስፋ የማይቆርጥ፣ አስተማማኝ ታማኝነት
4, Astonishing magnanimity: generosity and mercy that the victorious side of war shows to the defeated. (ከሚጠብቃቸው አደጋ ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ምህረት)

This is the love this psalm tells us to count on. It presents it as an indispensable part of the picture of God we see revealed in scripture. Being believers on the other side of the cross, we have more evidence of His love and mercy. This chêçêd wasn't substituted by grace in the New Testament. Jesus is the chêçêd of God. Jesus is the love of God made visible and concrete for us. If we miss this when we see God we have a distorted view of God.

Who is this God (Verse 1-4)

¹ Give thanks to the Lord, for he is good. His love endures forever.
² Give thanks to the God of gods. His love endures forever.
³ Give thanks to the Lord of lords: His love endures forever.
⁴ to him who alone does great wonders, His love endures forever.

The Lord is Good and The Lord is Great. He is the first of all beings. He alone does miracles and wonders. Though we see more details to describe His greatness its significant that His goodness was mentioned first. Its much better to be good than great! How tragic would it be if a great God was anything but good?

How did He show His love?
1, Creation (verse 5-9)
Continuing and unchanging existence of sun, starts, moon and the land we stand on are proof of enduring steadfast love. “Every good and perfect gift is from above, coming down from the Father of the heavenly lights, who does not change like shifting shadows.”Jam 1:17

2, Redemption ( verse 10-24)
The bible tells a story with a pattern of Gods redemption of His people. We can see the story of our salvation in these stories. This section shows us a journey with a fantastic rescue in a challenging pilgrimage despite the opposition of hell.
²³ to the One who remembered us in our low estate His love endures forever.
²⁴ and freed us from our enemies, His love endures forever.
Believers can and should sincerely say this about their own salvation!

3, Providence (verse 25)
“and who gives food to every creature. His love endures forever.”
His providence is His upholding, sustaining and directing of all things for His glory. The one who feeds every creation will surely not deprive His own people.

“Give thanks to the God of heaven. His love endures forever.”Ps 136:26
The phrase "God of heaven" is only mentioned here is the Psalms. Its meant to emphasize on the transcendence of God. The Good and Great God is not of this earth. He is not of our world. Heaven isn't the clouds we see above us. Its a realm where He alone reigns in. Its unseen, immaterial and eternal reality. የመጠቀ እና ከእኛ የተለየ ነው። And yet, He is not too far for us to start doubting the reliability of His love. We can trust that it will not have an expiration date. We know His love endures forever for He is an eternal God.
5👍1🙏1
ደስታ አማራጭ አይደለም

ይሁን እንጂ ደስተኛ አይደለሁም

‘ደስተኞች ሁኑ’ የሚለውን ትእዛዝ፣ አንዳንዶች ‘ይቻላል’ በሚል ስሜት ሲቀበሉት፣ ሌሎች ግን ችግር ሆኖ ይታያቸዋል። ሁለቱም ምላሾች ግን በምክንያት የተደገፉ ናቸው። እኛ ከፍጥረታችን የሞትን ኀጢያተኞች ነን (ኤፌሶን 2፥1-3)። አብዛኛውን ጊዜም፣ ስሜታችን የሚዋዥቅና ለመንፈሳዊ ነገር የደነዘዝን ነን። በክርስቶስ ውስጥ ሆነን እንኳ እያለ፣ ዥዋዥዌ ላይ እንዳለ ሰው፣ በየዕለቱ፣ ከደደነዘዘ ልብ ወደ ተነቃቃ መንፈስ፣ ከዚያም መልሰን ወደ ድርቀት በመሄድ እንዋዥቃለን።

ራሳችንን የምናውቅና እውነታን ተቀብሎ መኖርን እየተማርን ያለን ሰዎች ከሆንን፣ ከልብ ደስተኞች የምንሆንባቸው ጊዜያት ምን ያህል ጥቂት እንደሆኑ በማመን፣ አባታችንን ደግመን ደጋግመን፣ «የማዳንህን ደስታ መልስልኝ» እያልን እንማጸናለን (መዝሙር 51፥12)።

እንደነዚህ ላሉ ሰነፍና ራሳቸውን ለሚያውቁ ሰዎች፣ ደስታ አማራጭ እንዳልሆነ መስማት፣ ‘ይቻላል’ ከሚል ስሜት ይልቅ ኩነኔን ይፈጥርባቸዋል። በብዙ ሸክም ተዳክሞ ባለ ትከሻ ላይ ሌላ ተጨማሪ ቀንበርን እንደመጫን ነው።

ነገር ግን፣ ደስታን ያጡ ሰዎች መሆናችን የታሪኩ መደምደሚያ አይደለም። በስሌቱ ውስጥ አንድ ከመጠን በላይ ዋጋ ያለው ነገር ይቀራል።

ተጨማሪ ለማንበብ...

Telegram
| YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | Website

#Articles
👍3
እንኳን ያንተ ሆንኩኝ አወኩህ እንኳን
እንዳልችል ሆኛለሁ ለሌላ እንዳልሆን
የማምነው እውነት በፍቅር ይዞኛል
ሌላ ሌላ እንዳላይ ውስጤን ሞልተኸዋል
አሰብኩት እራሴን ከአንተ ውጪ
አሰብኩት ወጥቼም ከቤትህ
ባዶ ነኝ ቅብዝብዝ የሌለኝ እረፍት
እኔ አልችልም ሰው አልሆንም በሌለህበት 🎶
20🙏1
ወሰን የሌለው ትዕግሰት..
“ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለምን ሕይወት ለሚቀበሉ ወሰን የሌለው ትዕግሥቱን ከኀጢአተኞች ዋና በሆንሁት በእኔ እንደ ምሳሌ አድርጎ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ።” 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥16

እግዚአብሔርን ስለ ትዕግስቱ ማን አመስግኖት ይዘልቃል? The fact that He waits for us ወደቀልባችን እስክንመለስ.. ከውድቀታችንም ከስኬታችንም ተምረን ያለ እርሱ ህይወት ትርጉም የለሽ መሆኗ ያለጥርጥር እስኪገባን ድረስ መታገሱ..

ስንቅበዘበዝ፣ አትሂዱ ወደተባልንበት ስንደረደር፣ ጎስቁለን ደግሞ እንደጠፋው ልጅ ተስፋ ቆርጦ ወደተስፋችን ቶሎ እንደመመለስ when we try to make it by ourselves until we recover enough to pretend like we can be fine without him.. ያኔም አይ የልጅ ነገር እያለ ይታገሳል፣ ነፍሳችንን የሚመልሳት (restore) የሚያደርጋት እርሱ ብቻ እንደሆነ እንዲገባን ይታገሳል።

Its hard for me to believe that whenever I ask for forgiveness for the millionth time on the same sin, His attitude isn't "ኤጭ..ደግሞ መጣች። አሁንም?... I taught you this lesson በቅርቡ እኮ.. ከመቼው ተመልሰሽ ገባሽበት.."

የእርሱን ትዕግስት በጥሩ ሁኔታ የሚያንፀባርቅ template የለንም። ቤተሰብ ብንል ጓደኛ ትዕግስት መሳይ ነገር ቢኖረውም ገደብ አበጅቶ ነው። ተሟጦ ያለቀ ዕለት ምንም ማስተባበያ የለውም። "ቆረጠልኝ" ካለ አበቃ። እግዚአብሔር በኛ በልጆቹ ቢቆርጥለት ምን ይውጠን ነበር?

ለእኛ extended የሆነው የእግዚአብሔር ቸርነት እራሱ ጌታ ኢየሱስ ነው። ወሰን የለውም። አይነጥፍም። የእስከዛሬው ነው አይደል የሚገርመን? ገና እስከፍፃሜው የሚሸከመን ራሱ ነው።


"ደግሞም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ተናገረ፤ “አንድ ሰው በወይኑ ዕርሻ ቦታ የተተከለች አንዲት የበለስ ተክል ነበረችው፤ እርሱም ፍሬ ሊፈልግባት መጥቶ ምንም አላገኘም። የወይን አትክልት ሠራተኛውንም፣ ‘እነሆ፤ ፍሬ ለማግኘት ልፈልግባት ሦስት ዓመት ወደዚህች በለስ መጥቼ ምንም አላገኘሁም፤ ስለዚህ ቍረጣት፤ ለምን ዐፈሩን በከንቱ ታሟጥጣለች?’ አለው። እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ጌታ ሆይ፤ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፍግ እስከማደርግላት ድረስ ለዘንድሮ ብቻ ተዋት፤ ለከርሞ ካፈራች መልካም ነው፤ አለበለዚያ ትቈርጣታለህ።’ ሉቃስ 13:6-9

በለሲቱን አትቁረጣት
ለአንድ አመት ታገሳት
🎶 ቤቲ ተዘራ
19👍3
ከማይደረስበት
ከቅድስናው ጥግ በሞቱ አድርሶኝ
ፀድቀሻል አለኝ..
ካለሁበት ሸለቆ
ህያው ቃሉን ልኮ ዳግም ሰው አ'ርጎኝ
አንቺ ብርቱ አለኝ...
እዩልኝ እዩልኝ..ደግነቱን እዩልኝ።
አስቱ 💙
18😢4
መክብብ 3: 1-15 ( Part 5)

ጊዜና በጊዜ ላይ የሌለን control

1-8: ለሁሉም ጊዜ አለው

የህይወትን ከንቱነት በምሳሌ ማስረዳቱን ሲቀጥል በቀጥታ ወደጊዜ ትንተና ይገባል።
መቀበል ያለብን 2 ነገሮች: እኛ በጊዜ የተገደብን ነን። እግዚአብሔር ግን አይደለም። እኛ የምንሰራው አስቀድሞ እንዳለው አላፊ ጠፊ ነው። እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ግን ፅኑ ነው (3:14) ስለዚህ አንድ መፅሀፍ ቅዱስ አስተማሪ እንዳለው እድገት ወይንም መብሰል ማለት ትንሽነትን መገንዘብ ነው። "Part of growing up is learning to grow small."

በዚህ ምዕራፍ መጀመርያ የምናገኘው ግጥም በህይወት ውስጥ ያሉ ወቅቶች/ seasons summary ነው። የግጥሙ ጥልቀት አቅም ላለው ብዙ የሚያመራምር ነው። አንዳንዶቹ ቃላት ሆን ተብለው እንደተመረጡ ያስታውቃሉ። ለምሳሌ የመጀመርያው list መወለድና መሞት መሆኑ intentional ነው። ልደትና ሞት የአንድ ሰው ህይወት አጥር ናቸው። ሁሉንም ሰው የማይምሩ እውነታዎች ስለሆኑ የአንባቢን ትኩረት ለመሳብ ያገለግላሉ። የተቀሩት ዝርዝር ቃላት የሚከተሉት ይሄ ነው የሚባል order or pattern ያለ አይመስልም። ሰባኪው በዚያም ውስጥ ሊያስተላልፍ ያሰበው ነገር ያለ ይመስለኛል።

መወለድ መሞት፣ መትከል መንቀል ፣ መግደል ማዳን፣ ማፍረስ መገንባት፣ ማልቀስ መሳቅ ፣ ሀዘን ጭፈራ፣ ድንጋይ መጣል ድንጋይ መሰብሰብ፣ መተቃቀፍ መለያየት፣ መተቃቀፍ መለያየት፣ መፈለግ መተው፣ ማስቀመጥ አውጥቶ መጣል፣ መቅደድ መስፋት፣ ዝምታ መናገር፣ መውደድ መጥላት፣ ጦርነት ሰላም። እነዚህ ሁሉ በሰው ህይወት ውስጥ አይቀሬ ወይንም inevitable የሆኑ፣ በሆነ መንገድ ልንዘጋጅላቸው የማንችል unpredictable ክስተቶች ናቸው።

በአጭሩ ሰባኪው እንድንረዳ የሚፈልገው ነገር ህይወትን የምንቆጣጠር በሚመስለን ልክ ስልጣን እንደሌለን። እንዲሁም ደግሞ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ሁሉም ህይወት የሚከስምበት ወቅት እንዳለ ነው። ህይወት ብቻ ሳይሆን ለመቅደድ ጊዜ አለው ሲል it implies that there will be situations in life where we choose or are forced to move on accepting ‘loss’ saying “Let it be”. ባሉን የቤተሰብ፣ ወዳጅነት ፣ የስራ እና ሌሎች relationships ያለንን አቅም አሟጠን ጨርሰንም ግኑኝነቱን ማከም አንችል ይሆናል። ይህም የህይወት አንዱ እውነታ ነው።

9-11:ጊዜና ዘለዓለም

ከላይ በተነተነው ግጥም ላይ ሁለት ምልከታዎች:

1, The best we can do is simply respond to the inevitable and also the unpredictable events within a finite lifetime. ስለዚህ ሰራተኛ ከጥረቱ የእግዚአብሔርን እቅድ አያስቀይርም። Infact verse 10 makes the point that we have this pressure/ burden to respond to life. በሚያደክም ሁኔታ ጫናውን ከመሸከም ውጪ አማራጭ የለንም። We can't just be passive and do nothing. ትግል እንቀጥላለን እንጂ..

2 , Yes, life is beautiful. በህይወት tragic ነገሮች ሳይቀር የሆነ አይነት ውበት አለ። ነገርግን ሰው ከዚህ ለተሻለ ነገር ተፈጥሯል። ዘለዓለም። ይሄንን ሀቅ መረዳት ህይወትን ያከብዳል እንጂ አያቀለውም (unfortunately). We have this compulsive drive to transcend our mortality. But all we can clearly see is the micro moments of our lives. የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ስራዎች ማወቅም ሆነ መገንዘብ አንችልም።ነገርግን ዘላለማዊነትን በልባችን እግዚአብሄር አኑሯል። ስለዚህ ፍንጭ ቢኖረንም ስለጊዜ እና ስለዘላለም ገና ብዙ ያልገባንና የማይገባን ነገር አለ።

12-15: አሁን: የእግዚአብሔር ስጦታ!

ቁጥር 12&13 ከምዕራፍ 2: 24-26 ጋር ይመሳሰላል። ምላሻችን ስለጊዜ ሞን መሆን አለበት? አሁን የተሰጠንን ህይወት አሁን በደስታና በሀላፊነት መኖር። እና ደግሞ የህይወትን መሰረታዊ ደስታዎች በአመስጋኝነት ማጣጣም አለብን። መብልና መጠጥ በድጋሚ ተጠቅሰዋል። እነዚህ ነገሮች የስጋ ክፉ ምኞት ሳይሆኑ የእግዚአብሔር ችሮታ ናቸው። በድካሙ ርካታን እንዲያገኝ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። This is also stated like a testimony. He knows that these things make life good and that they are Gods gifts. ስጦታ/ ችሮታ ደግሞ earn ያደረግነው ሳይሆን በለጋስነቱ የተሸለምነው common grace ነው።

ቁጥር 14: "እግዚአብሔር ያደረገው ሁሉ ለዘላለም እንደሚኖር ዐውቃለሁ፤ በእርሱ ላይ ምንም አይጨመርም፤ ከእርሱም ምንም አይቀነስም፤ ሰዎች ያከብሩት(ይፈሩት) ዘንድ ይህን አደረገ።” We cant change the way life is, with all its seasons. ምንም ያህል ብንለፋና ብንጥር እግዚአብሔር ህይወትን በዚህ መልኩ ሰፍቶ ወስኖታል። What we can do is bow our souls before Him. Fear God because His deeds are eternal.

እዚህ ላይ ሌላ የምንማረው ነገር የእግዚአብሔር ማንነት ወይ ባህሪ የሚገለጥልን ለሆነ አላማ መሆኑን ነው። Who God is evokes human response. ዘለዓለማዊነቱና የአላማው ፅኑነት እንድንፈራው ሊያደርገን ይገባል።

ቁጥር 15“አሁን ያለው ከዚህ በፊት የነበረው ነው፤ ወደ ፊት የሚሆነውም ቀድሞ የነበረ ነው፤ እግዚአብሔርም ያለፈውን መልሶ ይሻዋል።” ሰው የማይፈልጋቸውን ነገሮች ከህይወቱ ለማጥፋት ይጣጣራል። ለአፍታ ይሳካለትም ይሆናል። ግን እግዚአብሔር በጊዜው የሚመልሳቸው እንደሞት አይነት አይቀሬ ክስተቶች አሉ። የእግዚአብሔርን መኖር ላለመቀበል ሰው ምንም ያህል አኩኩሉ ቢጫወት፣ የክርስቶስን ምስክሮች ወይ ደግሞ የእግዚአብሔርን መልዕክተኞች እየሸሸ ቢኖር፣ በፍጥረት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን እውነት ቢያፍን..ለጊዜው ነው። There will come a time, when God will require an account.
11👍4
Pursuing Holiness
መክብብ 3: 1-15 ( Part 5) ጊዜና በጊዜ ላይ የሌለን control 1-8: ለሁሉም ጊዜ አለው የህይወትን ከንቱነት በምሳሌ ማስረዳቱን ሲቀጥል በቀጥታ ወደጊዜ ትንተና ይገባል። መቀበል ያለብን 2 ነገሮች: እኛ በጊዜ የተገደብን ነን። እግዚአብሔር ግን አይደለም። እኛ የምንሰራው አስቀድሞ እንዳለው አላፊ ጠፊ ነው። እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ግን ፅኑ ነው (3:14) ስለዚህ አንድ መፅሀፍ…
እግዚአብሔር ሆይ አንተ ብቻ ከጊዜ ውጪ ትኖራለህ። ለሁሉ ጊዜ አለው። ከአንተ በቀር። አንተ ዘለዓለማዊ ስለሆንክ ስራህም እንደራስህ የፀና ነው። ጊዜ በአንተ ላይ ተፅዕኖ ስለሌለው ግን እርግፍ አድርገህ አልተውከውም. You pick and choose the best time to do your will. Your timing is perfect. Even when I fail to notice it in the moment.

ምንም ያህል ብጥር የአንተን እቅድ መለወጥ እንደማልችል ገብቶኛል። ትንሽነቴን አሁንም በውሉ በመረዳት እንዳድግ እርዳኝ። ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርገህ የምትሰራውን አንተን እንዳምን እርዳኝ። በኔ ጊዜ ካልሆነ ብዬ ትዕግስት ሳጣ ታግሰኸኛል። አሁንም የአንተን ጊዜ በሚያስረሳ መንገድ ከሰዎች የሚሰበክልኝን "ጊዜው የ....ነው" ልፈፋ እንዳልሰማ አድርገኝ።

በዚህ ጊዜ መሆን የነበረብኝ እያሉ ከንቱ ቁጭት ውስጥ ከመግባት ጠብቀኝ። Helo me to trust and rest in Your timing.

ከሰው ህይወት የማይቀሩ ክስተቶች ሲገጥሙኝ ለምን እንደምበረግግ አላውቅም። ሰው መሆንን በሚገባ ገና embrace አላደረኩትም መሰለኝ። ሞትን አለመድኩትም፣ የደስታና ሀዘን መፈራረቅ ያነጫንጨኛል። የተለየሁትን እስከመጨረሻው መቅደድና መለየት ገና ምን እንደሆነ አልገባኝም። ከስንቱ ትናንት ጋር እንደተሰፋሁ አለሁ። በጦርነት ከመከበቤ የተነሳ የሰላምን ጠዓም ዘንግቼዋለው። ሰው ብቻ'ነቴ እንዳልገባኝ ሁሉ ላልታሰቡ ክስተቶች መዘጋጀት አለመቻሌ እስካሁን ያበሽቀኛል።

ህይወት በእርግጥም ከኔ ቁጥጥር ውጪ ሆና አየር ላይ ብትቀር አሳሳቢ ነበር። That would actually justify my anxiety. ነገር ግን አንተ አለህ። ሁሉን በስርህ የምታስተዳድር ሉዓላዊው ንጉስ ከዘለዓለም እስከዘላለሙ ብቻህን ጊዜንና በጊዜ ውስጥ የሚያልፉትን ሁሉ ትቆጣጠራለህ። So why do I worry about anything? ያንተን ጥበብና ረቂቅነት እንደሚያውቅ ሰው መንግስትህን እንዳስብ አድርገኝ። ወደ እረፍቴ ውሀ ምራኝ።

You have given me a sense of eternity. That brings its own burden and blessings to my life. በየዕለቱ ያሉትን ጥቃቅን moments ስኖር ዘላለማዊ ህይወቴ ላይ ያላቸውን አንድምታ እንዳገናዝብ አግዘኝ። Routine ከመሰለኝ ተራ ድርጊቶች በስተጀርባ ብዙ እየተሰራ ያለ እውነታ እንዳለ በማሰብ እንዳልሰንፍ ትጋትን ጨምርልኝ።

በምደክምበትና በምኖረው ህይወት ውስጥ ያሉትን ጥቃቅን ደስታዎች እንዳጣጥም ፍቀድ።ደስታ የአንተ ችሮታ ነው። ያለአንተ ፈቃድ ተድላን የቀመሰ የለም። በልፋት ሀሴት ማድረግ የአንተ ስጦታ ነው። በቀኝህ ፍስሀ አለና grant your joy to me. Help me to enjoy the simple things in life.

እንዳከብርህ፣ እንድፈራህ ስለራስህ የሆነ ባህሪይ ስትገልጥ ለገባኝ መረዳት ተገቢውን ምላሽ መስጠትን አስተምረኝ። አንተ አንተን ነህ። አትቀየርም። አትለወጥም። ህይወት እንድትቀጥል ያሰብክበትን ዕቅድ ከኔ ጋር ተማክረህ አታሻሽለውም። የኔ ምላሽ ይልቁንም መሆን ያለበት በገባኸኝ በተገለጥክልኝ ልክ ዝቅ ማለትና የሚገባህን መፈራትና ክብር መስጠት ነው። ዘላለማዊነትህ ደግሞ ትልቅ በረከት ነው። ልትወደስበትም ይገባል። Because it means that all your graces and mercies to me are eternal. ሀሳብህን ቀይረህ አትተዋቸውም። ተመስገን።

You are a righteous judge. ተጠያቂነት ስለሚባለው ፅንሰሀሳብ አንተ ባትኖር አናውቅም ነበር። ማንም ለማንም የማይመልስበት ምድር ውስጥ ስላላኖርከን ተመስገን። ከአንተ ጋር አኩኩሉ ተጫውቶ የማይገኝ የለም። በጊዜው የምትሻውን ሁሉ መልሰህ በማምጣት የሸሸ የመሰለውን ትይዘዋለህ። በዚህ መረዳትም አሳርፈኝ። ፍትህ ምን እንደሆነ ካልገባቸው ዳኞች ፅድቅን በመጠበቅ disappointed ከመሆን አድነኝ።
15👍3
ወንድሞች ሆይ፤ በተጠራችሁ ጊዜ ምን እንደ ነበራችሁ እስቲ አስቡ። በሰው መስፈርት ከእናንተ ብዙዎቻችሁ ዐዋቂዎች አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ኀያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከትልቅ ቤተ ሰብ አልተ ወለዳችሁም።

ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔር ብርቱዎችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ። እግዚአብሔር የተከበረውን እንደሌለ ለማድረግ፣ በዚህ ዓለም ዝቅ ያለውንና የተናቀውን ነገር፣ ቦታም ያልተሰጠውን ነገር መረጠ፤ ይኸውም ማንም ሰው በእርሱ ፊት እንዳይመካ ነው።

በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኖአል። እንግዲህ፣ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፤ “የሚመካ በጌታ ይመካ።
1 ቆሮ 1:26-31
22🙏3👍2👏1
ሀጥያት ማለት መጥፎ/የተከለከለን ነገር መስራት ብቻ አይደለም። ሀጥያት በመሰረቱ ሀይል ወይንም አገዛዝ እንጂ የሆኑ የወንጀል/ vice ክልክል ድርጊቶች ብቻ አይደለም። ማምለክ እንደሚገባን አላመለክንም.. ለእርሱ ሊኖረን የሚገባ መሰጠት የለንም...በእርሱ መደሰት ሲገባን ሀሴትን ፍለጋ ሌላ ሌላ ጋር እንቅበዘበዛለን (አሁንም)....ካሰብንበት መናዘዝ ያለብን የሀጥያት መገለጫዎች መሀል የሚገዝፈው ያደረግነው ስህተት ዘይ ጥፋት ሳይሆን ያላደረግነውና ያልኖርነው ህይወት ይመስለኛል....
13👍7🙏1
10
Why a Shepard put oil on His sheep? Psalm 23

Sheep can get their head caught in briers and die trying to get untangled. There are horrid little flies that like to torment sheep by laying eggs in their nostrils which turn into worms and drive the sheep to beat their head against a rock, sometimes to death. Their ears and eyes are also susceptible to tormenting insects. So the shepherd anoints their whole head with oil. Then there is peace. That oil forms a barrier of protection against the evil that tries to destroy the sheep. Do you have times of mental torment? Do the worrisome thoughts invade your mind over and over? Do you beat your head against a wall trying to stop them? Have you ever asked God to anoint your head with oil? He has an endless supply! His oil protects and makes it possible for you to fix your heart, mind, and eyes on Him today and always! There is peace in the valley!

@Mahi_Yoni
24👍2
አምላክ ሆይ፤ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ስምህ ቅርብ ነውና.. መዝሙር 75፥1
13
መክብብ 3:16-22 (Part 6)

የፍትህ መጓደልና የሚጠበቅብን ምላሽ

"ከፀሓይ በታችም ሌላ ነገር አየሁ፤ በፍርድ ቦታ ዐመፅ ነበር፤ በፍትሕ ቦታ ግፍ ነበር።"

አለማችን በሚያሳዝን ሁኔታ በክፋትና በተዛባ ፍትህ የተሞላ ነው። ይህን ሀቅ መቀበል በእርግጥ ከባድ ነው። Its unsettling. የተበደለ ሰው መፍትሄ ፍለጋ የሚሄድበት ፍርድቤት የበዳዮች ማጎርያ ሲሆን መሄጃ ማጣት ሰውን ይከበዋል። ለነገሩ ፈራጅ መሆን ለፈላጭ ቆራጭነት ያጋልጣል። የህግ የበላይነት አስከብራለው ብሎ የማለ ሰው ከህግ በላይ ሆኖ በሰው ቁስል ላይ እንጨት ይሰድዳል። ሀይ ባይ የለም። "የዳኛ ነፃነት" እና "ገለልተኛነት" በተባሉ መርሆች ከተጠያቂነት ያመለጡ ብዙ ወንበዴዎች አሉ።

"እኔም በልቤ “ለማንኛውም ድርጊት፣ ለማንኛውም ተግባር ጊዜ ስላለው፣ እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጢአተኛውን ወደ ፍርድ ያመጣቸዋል” ብዬ አሰብሁ።"

ነገርግን ምንም ያህል ሰው ከህግ በላይ ሆኖ ፍትህን እንደፈለገ ቢያጣምም ወደ እውነተኛው ዳኛ ፊት የሚቀርብበት ጊዜ አለ። አስባችሁታል? ማንኛውም ድርጊት! No exceptions. Every deed will be judged. ስለፍርድ ሲነሳ metaphor እንጂ እውነታዊ ትዕይንት የማይመስለን ሰዎች እንኖር ይሆናል። መፅሀፍ ቅዱስ እንዲህ በግልፅ ስለፍርድ ቀን ሲያወራ ግን ለትርጉም ክፍት የሚያደርገው አይመስለኝም። እዚህ ላይ ቆም ብለን ስለእኛ በፍርድ ቀን የሚታይልንን ምትካችንን ኢየሱስ ማመስገን ተገቢ ነው። ያ ብቻ ሳይሆን የእኛን ሞት ሞቶ ፅድቁን እንዳስቆጠረልን ያመንን ሁሉ የእምነታችንን እውነተኛነት የሚመሰክረውን ፍሬ በማፍራት ለፍርድ ቀን የማናፍር ፃድቃን ለመሆንም መትጋት አለብን።

እንዲህም ብዬ አሰብሁ፤ “ሰዎች፣ እንደ እንስሳት መሆናቸውን ያዩ ዘንድ እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል። የሰው ዕድል ፈንታ እንደ እንስሳት ነው፤ ሁለቱም ዕጣ ፈንታቸው አንድ ነው፤ አንዱ እንደሚሞት፣ ሌላውም እንዲሁ ይሞታል። ሁሉ አንድ ዐይነት እስትንፋስ አላቸው፤ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነው። ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄዳሉ፤ ሁሉም ከዐፈር እንደሆኑ፣ ተመልሰው ወደ ዐፈር ይሄዳሉ።የሰው መንፈስ ወደ ላይ መውጣቱን፣ የእንስሳ እስትንፋስ ደግሞ ወደ ታች ወደ ምድር መውረዱን ማን ያውቃል?”

ሞት equalizer ነው። እዚህ ጋር የምናየው የዘገየውን ፍርድ ነው። እንደእንስሳ የሰው ልጅ act የሚያደርግባቸው ቅፅበቶች በርካታ ናቸው። ይሄንን ሁሉ ሰው አያስተውልም። እግዚአብሔር ሰውን በገዛ አይኑ የወደደውን እንዲያደርግ የሚለቀውና ፣ የሚገድብ እጁን የሚከለክልበት ጊዜ አለ። በዚያን ጊዜ ሰው ምን ያህል መዝቀጥ እንደሚችል ይገንዘብ። ያንን የራሱን ወራዳነት በማየትም በዙሪያው ያሉት ሰዎች ለራሳቸው ሲተው ጊዜ ምን ያህል እንደሚወርዱና እንዴት ሊበድሉት እንደሚችሉ ሊያስብ ይገባል። እንደእንስሳ የሚኖሩና ግፍ የሚፈፅሙ ሰዎች አስተሳሰብ 'ወደላይ' ከፍ አይልም። As if all there is to life is earth ነው የሚኖሩት። እዚህ ጋር አኗኗር ወይንም የኑሮ ዘይቤንና ድርጊትን ከሀሳብና እውቀት ነጥለን ማየት እንደሌለብን እንማራለን። ሰባኪው የሚገልጣቸው ሰዎች ከእንስሳ ብልጫ እንደሌላቸው ስለሚኖሩ መንፈሳቸው ወደላይ ትውጣ አትውጣ አያውቁም። የመጨረሻው ሀረግ "Who of them knows/ከእነርሱ መሀከል ማን ያውቃል?" ተብሎ መተርጎም ይችላል። ስለዚህ ሰባኪው የሰውን ዘላለማዊነት እየተጠራጠረ ሳይሆን የእነርሱን ignorance እያሳየን ነው።

ስለዚህ ለሰው ዕጣ ፈንታው ስለ ሆነ፣ በሥራው ከመደሰት የተሻለ ነገር እንደሌለው አየሁ፤ ከእርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ተመልሶ እንዲያይ የሚያደርገው ማን ነው?

ለዚህ ምላሻችን ሊሆን የሚገባው ምንድነው? ዕጣ ፈንታችንን አለመጣላት። እግዚአብሔር ከሰጠን ሀላፊነት ጋር አለመጋጨት። በደስታ በስራችን መፅናት። ደግሞም ነገሮች ለወደፊት ከዚህ ይሻሻሉ አይሻሻሉ የምናውቀው ነገር ስለሌለ ነብይ ፍለጋ አንድከም። ነገን እስክንደርስበት የሚያሳየን የለም። ይልቅስ የተቸረን ዛሬ ላይ ሆነን የምናደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሆን እንበርታ። Live in the moment ተራ ቱሪናፋ አይደለም። የጠቢብ motto ነው። አንዴ ትናንት አንዴ ነገ ላይ መንጦልጦል ትርፉ የአዕምሮ ዝለት ነው። አስተዋይ በህልም ቅዠትና በማይጨበጥ ትዝታ ሳይሆን ዛሬ ላይ በእጁ ባለው ይደሰታል።
7👏2
Father, what we know not, teach us; what we have not, give us; what we are not, make us for the sake of your Son our savior. (Old Anglican Prayer)
21
2025/07/09 02:23:31
Back to Top
HTML Embed Code: