Telegram Web Link
Pursuing Holiness
መክብብ 3:16-22 (Part 6) የፍትህ መጓደልና ፤ የሚጠበቅብን ምላሽ "ከፀሓይ በታችም ሌላ ነገር አየሁ፤ በፍርድ ቦታ ዐመፅ ነበር፤ በፍትሕ ቦታ ግፍ ነበር።" አለማችን በሚያሳዝን ሁኔታ በክፋትና በተዛባ ፍትህ የተሞላ ነው። ይህን ሀቅ መቀበል በእርግጥ ከባድ ነው። Its unsettling. የተበደለ ሰው መፍትሄ ፍለጋ የሚሄድበት ፍርድቤት የበዳዮች ማጎርያ ሲሆን መሄጃ ማጣት ሰውን ይከበዋል።…
እግዚአብሔር ሆይ

በፍትህ ጉዳይ ያለን ብቸኛ መፅናኛ እንደ ዳኞች ፍርደገምድለት ቢሆን ጥንት በጠፋን ነበር። ነገርግን የክፋትን ሀይል የሚገድብ ሉዓላዊ እጅህና በዘመን ፍፃሜ ሁሉን የሚያስተካክለው ምጡቅ ፍርድህን በመታመን እንፅናናለን። እንጂማ objective ሆኖቹ ህጉን በመተርጎም ፍረዱ የተባሉት ግፍና አመፅ በርክቷል። ሀይ ባይ ያጡ ብዙ የህግ የበላዮች አሉ። አንዳንዶቹ ለገንዘብ በተሸጠ ህሊና ሌሎቹ ደግሞ አንተ ብቻ በምትረዳው የስልጣን ስካር ምክኒያት ንፁሀንን ይበድላሉ። በዳዮችን ነፃነት ይሸልማሉ።

ይሄንን በቅርበት እንደሚመለከት ሰው ቃልህ እንደሚለው ለማንኛውም ድርጊት፣ ለማንኛውም ተግባር ጊዜ እንደተቀጠረለትና በፃዲቁ በአንተ ፊት ሁሉ እንደሚቀርብ ዘወትር አስታውሰን። መርማሪ አይኖችህንና ሁሉን አወቅ ችሎትህን የሚረታ ፍርደገምድል የዛኔ አይኖርም። ስለዚህም ተመስገን። እስከዚያው ድረስ ለእውነት የተቻለውን ዋጋ ሁሉ መክፈል እንድችል አበርታን። ቆራጦች አድርገን። አንተ ሁልጊዜ ከሀቀኞች ጋር ትቆማለህና ተጠያቂነታችን በዋናነት ለአንተ ይሁን።

ጌታዬና ጠበቃዬ ክርስቶስ ፤ በፍርድ ቀን የምትታይልኝ ፅድቄ፣ የአመፄን ዋጋ ከፍለህ አመፃዬን የከደንክልኝ ዋሴ። ብዙ ምስጋና ለአንተ ይገባሀል። ዘለዓለም አንተነሰ የማወድስበት መዝሙር ይሄ ነው። ታርደሀልና! ዋጅተኸኛልና! I pray that I die before I take this for granted. ይሄን ተዓምር ከመልመድ ጠብቀኝ።

ደግሞም በአንተ ለመዋጀቴ evidence የሚሆን መልካምን ስራ በህይወቴ ይብዛ። ጣቶቼን ለዚህ አሰልጥናቸው። ለፅድቅ ስራዎች ወይንም ለመንፈስ ፍሬዎች የሚያስፈልገኝን ordinary means of grace ወይንም ፀጋህን የምቀበልበት መሳርያዎች ሰጥተኸኛል። ፀሎት፣ የቃል ጥናት፣ የቅዱሳን ህብረት፣ የጌታ እራት ና ሌሎችንም መንገዶች አሳድጄ በመጠቀም በየዕለቱ የምኖረውን ህይወት እንዲቀይረው እማፀንሀለው። በፍርድ ቀን vindicate የምደረግበት፣ አንተን የማስደስትበት ምስክርነቴ ይብዛልኝ።

ጌታ ሆይ: የምንኖርበት አለም ሁሉ በአይኑ መልካም እንደመሰለው የሚኖርበት፣ አንድ አስከፊ ግፍ አይተን ይሄ ነው የክፋት መጨረሻ ስንል ከዚያ በእጥፍ ወደሚብስ ማጥ ውስጥ የሚከት አይነት አዙሪት ነው። እንደእንስሳ በደመነፍስ የሚኖሩ ሰዎች ህይወት በዚህ ምድር ብቻ እንደምታበቃ ሁሉ ክፋትን እንደውሀ ይጨልጣሉ። ዳኞችን በሀይልም ሆነ በገንዘብ መግዛት ስለቻሉ ብቻ ከፍርድ ያመለጡ መስሏቸው በ'ሰላም' ይኖራሉ። ከእነርሱ መሀል ስለነፍሳቸው eternal state የሚያስተውል የለም። ጌታ ሆይ ይሄን ማስተዋል ስጣቸው። የሚጠብቃቸው ፍርድ እንዳለ እንዲገነዘቡ። ሞት የሚባል ለሁሉ የማይቀር ክስተት መሸጋገርያ እንደሆነ የሚነግራቸው የሚሰሙትን ሰው አስነሳ። ፈቃድህ ከሆነ ለክፋት የተጉትን ያክል በአንተ ተዋጅተው የፅድቅ መሳርያዎች አድርጋቸው። አልያም ከክፋታቸው የሚገቱበትን መንገድ አንተ ፍጠር።

በዚህ ሁሉ ውስጥ ለሁላችንም የሰጠኸንን ሀላፊነት በአግባቡ እንድንወጣ እርዳን። ጌታ ሆይ ነገን ዛሬ ላይ ለማወቅም ሆነ ለመቆጣጠር ከመድከም ሰውረን። የሰጠኸንን የዛሬ ቀን በደስታ፣ በትጋት to its fullest መኖር ይሁንልን። በፍርድ ቀን የምንጠየቀው ስለእቅዳችን ሳይሆን ባለን ጊዜ ስለሰራነው ስራ ነውና ስንፍናችንን ገስፀው። ደስታችን በአንተ ነውና ለከት ያለፈ ሀዘናችንን አንሳልን። የምናደርገውን ነገር ሁሉ including our joy ለአንተ ክብር ማድረግን አስተምረን።
አንድ አለ። አንድና ብቸኛ የሆነ በዚህ ምድር ላይ ማንንም መበደል የማይችል ቅዱስ አምላክ አለ። የማይስት፣ የማይሳሳት። ፍፁም የሆነ። እንከን የለሽና ነውር አልባ ነው። እርሱ ሀጥያትን ሊያደርግ አይቻለውም። ስለዚህ ይበድለኝ ይሆን ብሎ ስጋት የለም እርሱ ዘንድ። ቅድስናው አስተማማኝ ነውና ያሳርፋል። አለት ነው። ቀላል ያስደግፋችኋል! ነገር ሲዘባረቅባችሁ ራሱ በጭፍን ብትከተሉት በወጀቡ አሳልፎ ማንነቱን ይገልጥላችኋል እንጂ በማዕበል ስትጠፉ ዝም አይልም።

አባት ነው። አባትነት ሁሉ የሚሰየምበት። በምድር ላይ አሉ የሚባሉ ደጋግ አባቶች ጫፉ ጋር የማይደርሱበት ቸር ነው። ቁጣም ቅጣትም ፍቅርም መግቦትም ትዕግስትም ሁሉ የማይነጥፈው ሳትለምኑት የሚያስፈልጋቹን የሚረዳ

የልቡ ስፋትና ለልጆቹ ያለው ፍቅር ተብራርቶ የማያልቅ ደግ ነው። እንጥፍጣፊ ታክል ክፋት የለበትም። የሚበልጠው የለምና ቅንዓትም ሆነ ፉክክር አያጠቃውም። ሰው አይደለምና አይዋሽም። እውነት ነው። ህይወት ነው።

እመኑት ብቻ እንጂ እርሱ ለዘለዓለም ታማኝ ነው። አንድንም ሰው አሳፍሮ ፣ ከድቶ አያውቅም። አሉ የሚባሉ ብረት መዝጊያ ባሎች ከርሱ ጋር ሲነፃፀሩ ይወይባሉ። እርሱ ለወደደው ራሱን ሳይሰስት ይሰጣል። የወደዳቸውን እስከመጨረሻ ይወዳል። ዘለዓለማዊ ምህረቱ የማይሸፍነው ጉድ የለም።

እንደርሱ ያለ ማንም የለም። ምሳሌ የለውም። እርሱ እርሱ ነው። ከማን ታወዳድሩታላችሁ? ይሄ ሲገባችሁ ብቻ ነው በእንባ "ከአንተ ወደማን እንሄዳለን?" የምትሉት። እግዚአብሔርን ማወቅ ነው ህይወት። እርሱን በማወቅ የሚገኘውን ደስታ የሚተካከል ምንም የለም። ለዚህ የከበረ እድል ብዙ ዋጋ ተከፍሎልናል። ተራ በሆነ ከንቱ ወሬ ጉብዝናችንን አናባክነው።
Focus.
Look at God.
Look at God as He is revealed in His word.
“እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤ የጽድቅ ሥራም ይወዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።”
— መዝሙር 11፥7

Glorious incentive and motivation for holiness.
Jesus Christ and his ways are better than silver and gold, rubies, and all desirable things.

The glory of his Deity,
the excellency of his person, his
all-conquering desirableness,
ineffable love,
wonderful undertaking,
unspeakable condescensions,
effectual mediation,
complete righteousness,
lie in their eyes,
ravish their hearts,
fill their affections,
and possess their souls.

Owen
በየማለዳ
እንደንቁህ ተማሪ በተዘጋጀ ልብ፣ የአለምና የስጋ ጩኸት ባታከተውና አንተን ለመስማት በናፈቀ ጆሮ እንጠብቅህ። በቃልህ ውስጥ የተገለጥከውን አንተን ለማየት የሚጓጉ አይኖችን ስጠን። በፍርፋሪ የማይጠግብ..ግቡ አንተና አንተ ብቻ የሆነ ቁርጠኛ ፈላጊዎች አድርገን። እረፍትንና ሀይል የሚሆነንን ፀጋ ልትሰጠን በክርስቶስ በኩል አንዴ ፈቅደሀልና አቤቱ ስንፍናችንን ገስፀህ አንተን ከአንተ እንድማር ቀልባችንን ወደእግርህ ስር ዘንበል አድርገው።

“ልዑል እግዚአብሔር ...በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።”ኢሳይያስ 50፥4

Gracious Father, since our whole salvation depends on our true understanding of your holy word, grant that our hearts freed from worldly affairs may hear and understand your holy word with diligence and faith so that we may rightly discern your gracious will, cherish it and live by it with all earnestness to your praise and honor. (Martin Bucer)
This world is not my home, I’m just a-passing through,
My treasures are laid up somewhere beyond the blue;
The angels beckon me from heaven’s open door,
And I can’t feel at home in this world anymore.

O Lord, You know I have no friend like You,
If heaven’s not my home, then, Lord, what will I do?
The angels beckon me from heaven’s open door,
And I can’t feel at home in this world anymore.

They’re all expecting me, and that’s one thing I know—
My Savior pardoned me, and now I onward go;
I know He’ll take me through though I am weak and poor,
And I can’t feel at home in this world anymore.

I have a loving Savior up in glory-land,
I don’t expect to stop until I with Him stand;
He’s waiting now for me in heaven’s open door,
And I can’t feel at home in this world anymore.

Just up in glory-land we’ll live eternally,
The saints on every hand are shouting victory,
Their songs of sweetest praise drift back from heaven’s shore,
And I can’t feel at home in this world anymore. 🎶
የማለዳ ረሀብ: Lesson from George Mueller

የሰው ልጅ ተኝቶ ሲነቃ ይርበዋል። አካላዊ ረሀብ ለሁሉም ሰው ሁሌ የሚኖር ባይሆንም ግን ነፍስ ይሄ ነው ማትለው ጠኔ እንዲኖራት አድርጎ እግዚአብሔር ሰርቷቷል። የምንፈልጋቸው ነገሮች ማለቂያ የላቸውም- one after the other we want and want and want and want. ስልክ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ እንቅልፍ፣ ቁርስ ፣ ወሬ..

George Mueller ከአስር ሺህ በላይ ወላጅ ያጡ ህፃናትን የተንከባከበ ጀግና ነው። በሚፅፈው journal ላይ በ 1841 May 7, ያስተዋለው ሀሳብ እጅግ ጠቃሚና በተደጋጋሚ መነበብ ያለበት ነው። በአጭሩ ሀሳቡ ይህ ነው " በየዕለቱ ቀኔን ስጀምር ታላቁና ቅድሚያ የምሰጠው ስራዬ ነፍሴን በእግዚአብሔር ማስደሰት ነው።" መደሰትን እንደ ስራ ለማናይ ሰዎች እንግዳ ሀሳብ ሊሆን ይችላል።

ምናልባትም ቅድሚያ በመስጠት እኖርለታለው የምንለውን ጥሪ ይቃረንብን ይሆናል። እግዚአብሔርን ማገልገል፣ ወንጌል መመስከር፣ የተጨነቁትን ማፅናናት፣ በጨለመው አለም እንደ ብርሀን ልጆች መመላለስና የመሳሰሉት መንፈሳዊ ጥሪዎችና ብዙ በጎነት የሞላባቸው አላማ ብለን የምንኖርላቸው ነገሮች አሉ። But none of these are “the first and the primary thing. Filling up is more important than pouring out. በቅድሚያ ነፍስ በእግዚአብሔር ተደስታ ረሀቧ ጋብ ማለት አለበት።

ረሀብ እንዴት ወደ ፍስሀ ይወስደናል ካልን ደግሞ መብላችንን እራሱ እግዚአብሔር በማድረግ ነው። በዚህ መረዳት ወደእግዚአብሔር የሚመጣ ሰው ከእግዚአብሔር ለመቀበል ተዘጋጅቶ ይቀርባል። ሰው በባህሪው ስራን በማሳካትና በማጠናቀቅ ይረካል። We enjoy achieving even small things. እግዚአብሔር ጋር ስንመጣ ግን ረሀብተኛ ሆነን እርሱን በመቀበልና በማጣጣም እንድንረካ ይፈልጋል።

Mueller “The first thing the child of God has to do morning by morning is to obtain food for his inner man.” ሲል ምግብ የሚሰጠውን ተፈጥሯዊ ጥቅሞች የሚገልፁ ቃላትን ማሰብ አለብን። ጥሩ ምግብ ሀይልና ሙቀት ይሰጣል። It brings nourishment and refreshment. ይሄንን የነፍስ መብል ደግሞ ከቃሉ ነው የምናገኘው።

“What is the food for the inner man? Not prayer, but the word of God. Every verse, to get blessing out of it . . . for the sake of obtaining food for my own soul. Having chewed on one bite and savored it, I go on to the next words or verse, turning all, as I go on, into prayer for myself or others, as the word may lead to it, but still continuously keeping before me that food for my own soul is the object of my meditation. “not the simple reading of the word of God, so that it only passes through our minds, just as water runs through a pipe, but considering what we read, pondering over it, and applying it to our hearts.”

እንደዚህ የተረጋጋ፣ ያልተጣደፈ፣ የተብሰለሰለ የቃል ጥናት በራሱ ወደፀሎት ይመራናል።ፀሎት ለእግዚአብሔር ቃል የምንሰጠው ምላሽ ነው።

“I speak to my Father and to my Friend about the things that he has brought before me in his precious word. Meditation soon leads to a response. Now, having heard our Father’s voice all the way down into our souls, we find ourselves able to really pray and to actually commune with God.

እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል በሰራልን ስራ ምክኒያት የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን we can have a communion woth God.God speaks first in his word, and we receive his words with the hunger, delight, and unhurried pace that fits the word of our Father and divine Friend. Then we speak humbly yet boldly in response, adoring our God, confessing our sins, thanking him for his grace and mercy, and petitioning him for ourselves, our loved ones, and even those who seem like enemies.

ይሄ ህብረት ሰዎችን ለማገልገል የሚደረግ ዝግጅት አይደለም። ምናልባት እግዚአብሔር leftover እንዲኖር ከፈቀደ ካጣጣምነው ውስጥ ለሌሎች እናካፍል ይሆናል ግን ለማካፈል ብለን አይደለም የምንበላው። The point, and prayer, is soul-satisfying communion with Christ.

Mueller testifies that this gave him the help and strength, “to pass in peace through deeper trials, in various ways, than I had ever had before.” When days turn out to be the worst of days in many ways we can say with Mueller “How different when the soul is refreshed and made happy early in the morning!”

(From Desiring God Article)
የእግዚአብሔር እጅ የያዘው ነገር
እንዳይወድቅ አይፈራም
እንዳይጠፋ አይፈራም

How unspeakably wonderful to know that all our concerns are held in hands that bled for us?!
Newton
መክብብ 4:1-12 (Part 7)

4:1-3: ጭቆናና መገለል
ምዕራፍ 3 የጀመረው የተዛባ ፍትህ theme ይቀጥላል። እዚህ ላይ የምናየው political ጭቆናና መገለልን ነው። ያሉበትን ሁኔታ የሚያባብሰው ደግሞ ከመጨቆናቸው ባለፈ የሚያፅናናቸው አለመኖሩ ነው። ካሉበት ሁኔታ መዳንን እርሱት። መፅናኛም የላቸውም። በዚህ ልክ suffer ከማድረግ ሞት ይሻላል። ከነአካቴው አለመወለድ ደግሞ ይመረጣል።

ይሄ የማያምን ሰው ተስፋ ሲቆርጥ ያመጣው ሀሳብ አይደለም። realistic የሆነ የርህራሄ ልብ የሚለው ነገር ነው። ኢየሱስ ስለይሁዳ ሲናገር ይሁዳ ባይወለድ ይሻለው ነበር ማለቱን ስናስታውስ በእርግጥም innocent ሆነው የሚሰቃዩና ያ ህመማቸው notice የማይደረጉ ሰዎች ርህራሄ exist አለማድረግ ቢፈልጉ ምንም እንደማይገርም እንረዳለን።

4: 4-6: ስግብግብነት ፣ ስንፍና እና መርካት

ይህ ክፍል የሚያነፃፅራቸው ነገሮች
(a) ድካም/ ፍጋት እያለ እርካታን ማጣት (ንፋስን መከተል) ከዛ ደግሞ በቅናት የተጫረ ambition
(b) የማይሸማቀቅ ግን ራስን አደጋ ላይ የሚጥል ግድየለሽነት።
ሁለቱም ፅድቅ አይደሉም። የእግዚአብሔርን እቅድ ለመቀበል በሚያስቸግር ልክ መልፋትም ሆነ መስነፍ ትክክል አይደለም። ሊበረታታ የሚገባው virtue quiet contentment እንጂ ከገደብ ያለፈ ፍጋትም ሆነ ስንፍና አይደለም።

4: 7-12: ብቸኝነት፣ ድካምና ስግብግብነት ይቀጥላል።

በጣም ከሚያሳዝኑ realities መሀል አንዱ በብልጥግና circle ውስጭ ያለ የተገለሉ ሰዎች ራሳቸውን በስራ እየገደሉ መቼም የማይረኩበትን መጠን ገንዘብ እያገኙም ራሳቸውን ደስታ የሚነፍጉ ናቸው። ሁልጊዜ ተጨማሪ ለማግኘት መጣጣር ሰውን የማወር አቅም አለው። ለማን ነው የምለፋው? በዚህ ልክ ከደስታ የምታቀበው ለምንድነው ብለው አይጠይቁም። ለማንም ሀላፊነት አይሰማቸውም።ልፋታቸው ለማንም ምንም ትርጉም የለውም። ራስን ብቻ ማሰብ ሲጀምር በጣም አድካሚ ነው።

መገለላቸው ደግሞ በራሳቸው የመጣ ነው። የሚሰሩት ሌላ ስለሌለ ለብቻቸው ይሰራሉ። ስራቸውን ብቻ በሰሩ ቁጥር ከማህበራዊ ህይወት መገለላቸው ይቀጥላል። This proves the importance of companions.
አንደኛ “ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል ሲል በቀጥታ ሌሎች ሰዎች የሚሰጡን እገዛ የሚጨምርልንን ውጤታማነት ያመለክታል።
ሁለተኛ ደግሞ በመሰረታዊ ፍላጎት ጊዜ ለሙቀትና ለደህንነት እንኳን ከአንድ በላይ መሆን አስፈላጊ ነው። ሁልጊዜ ራሳችንን መከላከል አንችልም። ሁልጊዜ በራሳችን መፅናናትም ሆነ ምቾትን ማግኘት አንችልም። ጓደኛ ማፍራት ካለው value መካከል አንዱ ይሄ ነው።
"If we were diligent in casting out all that filthiness and superfluity of naughtiness which corrupts our affections and disposes the mind to abound in vain imaginations..
Were our hearts more taken off from the love of the world which is exclusive of a sense of divine love..
If we meditated more on Christ and His glory..
We would frequently enjoy these overwhelming visits of His love much more than we do."
Owen
Be still, and know that I am God” (Ps 46:10).

“Be still”
• Think less of yourself.
• Shrink down to size.

“and know”
• Acknowledge
• Have confidence in

“that I am God.”
• The I AM
• Three in One and One in Three

Now what is it that you think God can't handle? (Dustin Benge X)
When things of God become burdensome and grievous to us we think to ourselves " I can't wait till Sabbath is over so I can actually relax." This attitude is unsuitable to Christ. If our soul refuses to be refreshed by the unspeakable joy , the eternal and abiding consolation that our Lord graciously offers and instead find the temporary pleasures of this world more satisfying we grieve the Spirit of Christ. This is why our daily work should be to get our hearts to crucified to the world and its pleasures so that our living affections aren't set on dying things. Ask yourself..do I have a special regard to Lord Jesus? Is He continually in my thoughts ? Does His love, His life and death , His kindness and Mercy constrain me to live for Him? ( Owen - Paraphrased)
እንደ ምሕረትህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ፤ የአፍህንም ምስክር እጠብቃለሁ:: In your unfailing love preserve my life, that I may obey the statutes of your mouth. (Ps119:88)
Pursuing Holiness
እንደ ምሕረትህ መልሰህ ሕያው አድርገኝ፤ የአፍህንም ምስክር እጠብቃለሁ:: In your unfailing love preserve my life, that I may obey the statutes of your mouth. (Ps119:88)
Has it occurred to you that part of how God keeps us saved is by reviving us from slumber that happens to be so deep that we need to be revived by the One who gave us life? The second half of this line can be taken as a rededicating of oneself or a declaration of a desire even in a season of what seems to be deadly sleep that requires resuscitation. This is encouraging cause it means we get to depend on Him to sustain us when we are thriving in obedience but also rely on Him to revive us when our life turns out to be series of failures. Its always a good news to remember that we are called for a higher calling which demands everything from us AND that God has a stake in our obedience and surrender that He will providentially enable us to be who we were meant to be. I remember reading somewhere a line that said something like "When God called you for a certain thing, He factored in your stupidity" 😊 So we can take comfort in His inability to be surprised by our weakness and His willingness to grant us grace and help.
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Pursuing Holiness
Its impossible to be grateful and entitled at the same time. If we are preoccupied with the notion that just because we belong to God we deserve to be free from all troubles, we rob ourselves from thankfulness, peace and joy.

No matter what the ups and downs were.. you made it here. Safe. God has been faithful. He has preserved your faith. Time and time again, He saved you. As Piper says, its impossible to know all that he's doing in our lives but we do know that we can trust his intentions.

You could be in the sort of darkness Psalm 88 describes. Remember how Heman addresses God at the beginning of that prayer? God of my salvation: The God who saves me. Thats who He immutably is to us. This is a cause for praise. We shouldn't take for granted how many times God showed up to save us from the enemy, from ourselves, from this world, from sin and from the mundane troubles of life.

በሕይወት ጐዳና ፈተና ቢበዛም ጌታን እየጠራ ንጹህ ሰው አይጠፋም
እጄን ያዘኝ ብሎ ሲጮህ ይሰማዋል ከረግረግ አውጥቶ በድል ይመራዋል
ችግረኛውን ሊውጥ ጠላት ሲገዳደር በሚያስፈራራ ቃል በትዕቢት ሲናገር
ደርሶ የሚታደግ እግዚአብሔር ብቻ ነው በሰው መታመን ግን የከንቱ ከንቱ ነው
ያለውን ተነጥቆ ሁሉን ነገር አጥቶ ከአጠገቡ የሚቆም ጌታ ብቻ ቀርቶ
በእንግድነት አገር ተገፍቶ ለሚያልፈው ተስፋው መሰረቱ አምላኩ ብቻ ነው
የቅዱሳን ረድኤት ከሰማይ ይመጣል ዘመናትን ቆጥሮ ጌታ ይመለሳል
የልጆቹን እንባ ከዓይናቸው ያብሳል ክብርና ምሥጋና ለሥሙ ይሆናል
እግዚአብሔር ሲረዳ 🩵🎶
2025/07/08 05:01:33
Back to Top
HTML Embed Code: