Telegram Web Link
እኔ ግን እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ፤ አዳኜ የሆነውን አምላክ እጠብቃለሁ፤ አምላኬ ይሰማኛል። ሚክያስ 7፥7
Hope. Wait. Pray.
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዚህ አጭር የጥሞና መጽሐፍ የክርስቶስን ውልደት እንደ አዲስ እንቃኝ። ከታሕሳስ 5 እስከ ታሕሳስ 29 በየቀኑ 10 ደቂቃ በመስጠት፣ ስለ ኢየሱስ እንድናሰላስል እና እንድናወድሰው ያግዘናል።

አድራሻ፦
1) በጃዕፈር መጽሐፍት መደብር (ለገሃር)
2) አዲስ አበባ መሠረተ ክርስቶስ መጽሐፍት መደብር (ስቴዲየም ዙሪያ ቀይ መስቀል ፊት ለፊት)
2) ጉርድ ሾላ፣ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት፣ ሜርሲ ፕላዛ 13ኛ ፎቅ ላይ ያገኙታል።
ከአዲስ አበባ ውጪና በብዛት ለሚፈልጉ ከታች በዚህ ስልክ ይደውሉ።
+251 90 574 6765
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Learn much of the Lord Jesus. For every look at yourself take 10 looks at Christ. He is altogether lovely. Live much in the smiles of God , bask in his beams feel his all seeing eye settle on you in love and Repose in his Almighty arms.
ታሕሳስ 5 | መንገዱን አቅኑ (ቀን 1)

ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል። እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል። የሉቃስ ወንጌል 1፥16-17

መጥምቁ ዮሐንስ ለእስራኤል የሠራውን ሥራ፣ የገና ወቅትም ለእኛ ሊሠራልን ይችላል። በዚህ ዓመት ሳትዘጋጁ የገና በዓል እንዳይደርስባችሁ። ይህንን ስል፣ መንፈሳዊ በሆነ መዘጋጀት ሳትዘጋጁ እንዳይደርስባችሁ ማለቴ ነው። የኢየሱስ የልደት በዓልን በመንፈሳዊ ዝግጅት ተዘጋጅታችሁ ካከበራችሁት፣ ደስታችሁም ሆነ ውጤቱ ዕጥፍ ድርብ ይሆናል!

ስለዚህ፣ ትዘጋጁ ዘንድ…

አንደኛ፣ ምን ያህል አዳኝ እንደሚያስፈልገን አሰላስሉ። የልደት በዓል ታላቅ ደስታ ከመሆኑ በፊት የክስ ደብዳቤ ነው። “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና” (ሉቃስ ወንጌል 2፥11)። አዳኝ ባያስፈልጋችሁ ኖሮ፣ ኢየሱስ መወለዱም ሆነ የልደት በዓል ባላስፈለገ ነበር። የሚያድነን አዳኝ ምን ያህል እንደሚያስፈልገን እስካልተረዳን ድረስ የልደት በዓል የተፈለገውን ያህል ፍሬ አያፈራም። እነዚህ አጫጭር የገና ሰሞን ጥሞናዎች፣ ስለ አዳኝ አስፈላጊነት በልባችሁ ውስጥ ጣፋጭም መራራም ስሜት ይፍጠሩባችሁ።

ሁለተኛ፣ በሰከነ መንገድ ራሳችሁን መርምሩ። የአርባ (ሁዳዴ) ፆም ለፋሲካ በዓል እንደሆነው ሁሉ የገና ወር ለኢየሱስ ልደት ነው። “አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም ዕወቅ፤ ፈትነኝ መንገዴንም ዕወቅ፤ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ” (መዝሙረ ዳዊት 139፥23-24)። እያንዳንዱ ልብ ቤቱን በማጽዳት ለጌታ ክፍል ያዘጋጅለት!

ሦስተኛ፣ እግዚአብሔር ላይ የተመሠረተ ጉጉት፣ ናፍቆት፣ እና መነቃቃት ቤታችሁን ይሙላ! በተለይ ደግሞ ልጆች ካሏችሁ፣ እናንተ ለክርስቶስ ጉጉታችሁ ከጨመረ፣ እነርሱም ይከተሏችኋል። ሆኖም ግን የልደት በዓልን ምድራዊ በሆኑ ዕቃዎች ብቻ ካከበርነው፣ ልጆቻችን እንዴት እግዚአብሔርን ይጠማሉ? የንጉሡ መምጣት በልጆቻችሁ በግልጽ ይታወቅ ዘንድ አስተሳሰባችሁን አስፉት!

አራተኛ፣ ታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በቃላችሁ በማጥናት እና በመሸምደድ ራሳችሁን ቃሉ ውስጥ ንከሩ! “በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድንጋዩንም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር” (ትንቢተ ኤርሚያስ 23፥29)። በበረዶ ወቅት ሰዎች በእሳት ዙሪያ ክብ ሰርተው እንደሚሞቁ፣ እናንተም በዚህ በጸጋ ቀለማት ባሸበረቀው የልደት ወር ዙሪያ ተቀምጣችሁ እንድትሞቁ ትጋበዛላችሁ! ለሺህ ስብራቶች በዚያ ፈውስ አለ። ለድቅድቅ ሌሊቶች ብርሃን ይሆናል።

Telegram
| YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | Website

#ለዛሬ
አታጉረምርሙ / Do not complain!

ማንኛውንም ነገር ሳታጒረመርሙና ሳትከራከሩ አድርጉ፤ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው። (ፊል 2:14-15)

በዚህ ምድር ስንኖር ያሰብነው ነገር ሁሉ እንዳሰብነው አይሆንልንም። ክርስቲያን መሆን ይህን እውነታ ባይሽረውም ነገር ግን እንቅፋት ለሆነብን ነገር የምንሰጠውን ምላሽ መቀየር አለበት። ማንኛውም ሰው የማጉረምረም መብት ያለው ይመስለዋል። ምንም እንኳን ሰዎች ፍጡር ስለሆንን ከፈጣሪያችን ምንም ነገር demand የማድረግ መብት ባይኖረንም አማኙም የማያምነውም ተግቶ ፈጣሪን ያማርራል። ክርስቲያን ደግሞ ይባሱኑ ስለጌታ ሲል ስለከፈለው ዋጋ ፣ ጌታን በማገልገሉ ይሆንልኛል ብሎ ስለቀረበት ነገር ፣ መታዘዝ ስላለበት ነገር አብዝቶ ያጉረመርማል። ፀሎቶቻችን ስለእግዚአብሔር ያለንን አመለካከት ያንፀባርቃሉ። ስለዚህ እንፀልያለን ብለን ስላልገባን ነገር complain አድርገን ከተነሳን ስለምናመልከው አምላክ ያለን መረዳት የሆነ ቦታ ላይ ችግር እንዳለበት ያመላክታል። የሆነ ነገር አልሆነም ብሎ ማጉረምረም ጌታ ያን ነገር ሊያደርግ እንዳልቻለ ወይ ደግሞ አባታችን ለእኛ በጎውን እንደማያስብ ሁሉ ይህ ነገር ለምን ተፈጠረ እያሉ ማጉረምረም ሀጥያት ነው (በግልጽ የተሰጠን ትእዛዝ መተላለፍ ነው፡፡ ጌታን ያሳዝነዋል)።

ክርክር ባዶ ንትርክ ወይንም ንዝንዝ በሚል ሳይሆን እዚህ ጋር የተጠቀሰው ምክኒያታዊ ሙግት (rational argument) ለሁሉም ነገር እንዳናነሳ የሚያዝ ክፍል ነው። ይህ ማለት በሞኝነት እንኑር ማለት ሳይሆን ጌታ ያስቀመጠን ቦታ ላይ እርሱን ስንታዘዝ እንደተፈጥሯዊ ሰው የትኛው አማራጭ ይበልጥ እንደሚጠቅመን አገናዝበን አይደለም። ጌታን ለመታዘዝ ምንም አይነት ቅድመሁኔታ ሊኖረን አይገባም። sense የማይሰጥ ለአለም እንደሞኝነት የሚቆጠር ነገርም ቢሆን ያለክርክር ነገሮችን እንፈፅም። ሌላው ደግሞ የራሳችንን ስህተት justify ለማድረግ የምናደርገው ክርክር ነው። ለዚህ አለማመን መድሀኒቱ ንስሀና በጌታ ፊት ራስን ማዋረድ ነው።

በምናየው ቦታ ሁሉ ስህተት ፈላጊዎች አንሁን። የክርስትና ህይወት ጌታ ላይ ካለን እምነት የተነሳ የፍስሀ ሊሆን ይገባል። ማጉረምረም ደስታን ይዘርፋል ክርክር እምነትን ይሸረሽራል። ይህ ብቻ አይደለም አታጉረምርሙ የተባልንበት ምክኒያት ለማያምኑ ሰዎች የበራልንን የወንጌል ብርሀን እንድናንፀባርቅ ነው። ባለማጉረምረማችን የእግዚአብሔርን ጥበብና ፍቅር ላይ ያለን እምነት እንደብርሀን ሆኖ ለማያምኑ ሰዎች ምስክርነት ይሆነናል። ለዚህም ነው አባቶች ከማጉረምረም ዱዳ መሆን ይሻላል የሚሉት። ስለዚህ ለማጉረምረም በምንፈተንበት ጊዜ ሁሉ አመስጋኞች እንሁን። በእርግጥ ከጌታ ብዙ ተቀብለናል። Piper እንደሚል አሁን እንኳን እኛ የማናውቀውን 1000+ ነገር ጌታ በህይወታችን እየሰራ ነውና ልባችንን በእርሱ አሳርፈን በረከታችንን እንቁጠር።

ለጋሱ አባቴና አምላኬ እግዚያብሄር ቸርነትህን የምገልጥበት ቋንቋ እጅግ ያነሰ ነው። አንተ ሰላሜ ነህ ፤ እንደሸንበቆ ተሰብረህ ትጥለኛለህ ብዬ የማልሰጋብህ አለቴ ፤ ለዘለዓለም የምትምረኝ ፣ ለዘለዓለም የምትጠብቀኝ! ጥበቃህ ደግሞ ከማውቀውም ከማላውቀውም ክፉ ሁሉ! ከራሴ ጥበብ ከሰይጣን ተንኮል ሁሉ ሰውረኸኝ ለዛሬ በቃሁ። ለአፍታ ለራሴ ብትተወኝ ጠፊ ነኝ።በቃኝ ከዚህ ወዲህ አልምርሽም ብትልስ? የትኛው ፅድቄ ወደ አንተ ? ፀጋህን በኔ ላይ አገነንህ ፤ ምስጋናህ ብዙ ። መግቦትህ ለአፍታ አልተለየኝም። በደጋግ ሰዎች ባርከኸኛል የእለት እንጀራዬን አላሳጣኸኝም። እንቅልፍና ጤናም ካንተ ዘንድ ናቸው። ስለኔ የተሰቀልህ ክርስቶስ ከማስተውለው በላይ ውለታህ አለብኝና ለዘለዐለም አመሰግንሃለሁ እንጂ ቀኔን በማጉረምረም አልጀምርም!
🙏
ትምክህቴ ላይ ከባድ ጉዳት ሰንዝረህ ጣዖት አድርጌ ያቆምኩት እኔነት ፈራርሶ በፊትህ ተበትኗል። በምትኩ እውነተኛውን ጌታ ልጅህን ክርስቶስን ሾምክልኝ። አሁን ልቤ ወደ ቅድስናህ ዘንበል ብላለች። (Prayers from Valley of Visions)
ኑዛዜ

በተለምዶው "እግዚአብሔር ያውቃል" ስል የሚሰማኝ እፎይታ ከየት እንደመጣ አላውቅም። ብቻ ስገምት የተማርኩት ወይ ያየሁት ነገር እንጂ የአንተ ሁሉን አወቅነት በእርግጥም በቂ ሆኖ አግኝቼው ማብራርያ ሳልፈልግ አንተ ካወቅክ ይበቃል የሚል አዕምሮ እንደሌለኝ ግን አውቃለው። እንደዛም ሆኖ አስቤ አስቤ ልፈታ ያልቻልኩትን ቋጠሮ አንተ ታውቃለህ በማለት ነው የምገላገለው።

በእርግጥም አንተ ሁሉን ታውቃለህ። ሁሉን በምታውቀው በአንተ መታወቅ እንዴት አስፈሪ ነገር ነው? የዕውቀትህ exhaustiveness ሽራፊውም አይታየኝም። ዝርዝሩና ጥልቀቱ አይታየኝም። ሁሉ ነገሬን ስለምታውቅ ለአንተ የማብራራው context የለኝም። Misunderstand እንዳታደርገኝ አልሰጋም። እኔ የማይገባኝ ባህሪዬ ሳይቀር ለአንተ በግልፅ ይታይሀል። ከአንተ የተሰወረ ምን አለኝ? እንዲህ በአደባባይ እንድወጣ የገፋኝ motive ለአንተ ክፍት ነው። እኔ እንኳን ገና አልደረስኩበትም። ኑዛዜ ትዕቢት ይሁን ትህትና እስከአሁን እንዳወዛገበኝ አለሁ።

አንተ ግን ሁሉን ስለምታውቅ ሳይገባኝም እናዘዛለው። የምታውቀኝን ያህል አንተን ማወቅ በሰው አቅም የሚቻል ባይሆንም አንተን እንድናውቅህ በፈቀድከው ልክ ለማወቅ አለመትጋቴ ድካሜ ነው።

የሚጠቅምሽ ይሄ ነው የሚሉትን ድምፆች ሁሉ እየሰማሁ ከንቱ እውቀት ስቃርም እከርምና "እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን፤ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን" ለማወቅ እደክማለሁ። የዘላለም ህይወት ግን ቃልህ እንደሚለው ይሄው ነው። Thats what life is all about at the end of the day.

ይሄንን የከበረ ዕድል፣ ይሄንን የዘላለም ህይወት የማያገኙ ብዙዎች አሉ። እውነተኛ የሆንከውን አንተን እንድናውቅ ቃልህ እንደሚል ልቦና የሰጠኸን አንተ ነህ። ራስህን ባትገልጥ ፣ አይናችንን ባታበራ እንዴት እናይሀለን?

ህያው ቃልህን ተንፍሰህ ባትፅፍልን፣ በመግቦትህ ጠብቀኸው ዘመናትን ተሻግሮ ለእኛ ባይደርስ ምስክርነትህን እንዴት እናነባለን? ዛሬ እንደቀላል የሆነብን አንተን ባናውቅ የማይኖረን በረከት እጅግ ብዙ ነው። አውቀነዋል ብለን ተዘልለን እንዳንቀመጥ ደግሞ የሚያደርግ በቂ mysteriousness አለህ።

አንተን የማወቅ ክቡርነት የገባቸው ሰዎች አኗኗር ይለያል። Its more focused. ሐዋርያው እንዳለው ነው። ወደር የሌለውን ክርስቶስን ከማወቅ አንፃር አለ የሚባል የምድር ክብር ሁሉ ጉድፍ ነው። Everything pales in comparison. ከርቀት አይተን የምናከብረውን ሰው ቀረብ ስንል አወቅኩሽ ናቅኩሽ ይመጣል። ሰው ነዋ። የሚደብር ነገር አይጠፋውም። በደህና የስነልቦና ምሁር ታግዘን የself awareness journey ውስጥ ብንገባም ከራሳችን የሚያጣላ አሸን እንከን አናጣም።

አንተን ለማወቅ ቆርጠው የተነሱ ሰዎች ግን ሲፀፀቱ አላየንም። ባወቁህ ልክ ሲወዱህ..በቀረቡህ ልክ ሲማረኩ። የበለጠ ለማወቅ ረሀባቸው ሲያይልና ህይወት ያሉትን ነገር ጥለው በአንተ consume ሲደረጉ ነው የማውቀው። Thats why puritans used to use the term of being possessed by you.

ቃልህን ሲያነቡ ያላቸው መሰጠትና ቆራጥነት ይሄን ያሳብቃል። በስንፍናና በመሰላቸት የሆነ እቅድን ለማሳካት፣ አንብቤያለው ብሎ tick ለማድረግ ሳይሆን የሆነ የከበረ ድንጋይ ወይ ማዕድን እንደሚቆፍር ታታሪ ሰራተኛ ያላቸውን ምርጥ ጊዜና ጉልበት ሰጥተው፣ ተሰጥተው ያጠናሉ።በቃላቸው ይሸመድዳሉ። ቃሎቼ ህይወታችሁ ናቸው ብለሀላ! Thats their life. They breath it because they believe it has your breath. ቃልህ ውስጥ ድምፅህን ስለሚሰሙት ለስልጣኑ በመገዛት መንፈስ በአክብሮትና የሚወዱትን ሙሽራቸውን ሲናፍቁት ድምፁን እንደሚሰሙበት መሳርያ ቶሎ ቶሎ ይከልሱታል።

ፀሎት ለእነርሱ chore አይደለም። ጌታ በምድር ሳለ ከጋጋታው ገለል ለማለት እንደ እረፍት ቦታው ወደአባቱ ለመፀለይ ዞር እንደሚለው..ከአለም ዝለት ለማረፍ፣ ፈታ ለማለት፣ ጭንቀትን ለማራገፍ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመጋደልና ለመዋጋት፣ ለማመስገን፣ ለመናዘዝ ዘወትር "ሳያቋርጡ" ይፀልያሉ። ከራሳቸው አልፈው የወዳጆቻቸውን ሸክም ይዘው፣ ስለሀገራቸው፣ ስለ አለም፣ ስለሚስዮናውያን ሁሉ ይማልዳሉ።

አንተን የሚያውቅ ሰው እንዲህ ነው።

ማንነትህን ያየ። የገባኸው። ሁሉ በሁሉነትህን የተረዳ። ባህሪህን የሚያጠና። አፍቃሪነትህን፣ ሉዓላዊነትህን፣ ፃዲቅ መሆንህን፣ ዘለዓለማዊነትን፣ አለመለወጥህን፣ የማትሞት መሆንህ፣ ቸር አባትና ለጋስ መጋቢነትህን፣  ትዕግስትህና የምህረትህን ባለጠግነት፣ ቁጣህ፣ ቅድስናህን አይቶ የሚያመልክህ..

ልጅህን ልከህ ከዘላለም ሞት የተቤዠኸው፣ በደል መተላለፉን ይቅር ያልከው፣ ሞቱን የወሰድክለት፣ ህይወት ያበዛህለት፣ ምህረት የገነነለት፣ ትዕግስትህ የጠበቀው፣ እንደልጅ ወራሽ የሆነ፣ መግቦትህ የሚያኖረው ውለታውን እየቆጠረ የሚያመሰግንህ ሰው አንተን ከማወቅ ውጪ ምን ግብ ይኖረዋል?

Whats the chief end of man? ለሚለው ጥያቄ የአባቶች መልስ "Glorifying God and Enjoying Him forever." ፓይፐር እንደሚለው ደግሞ ሁለቱ የሚነጣጠሉ ሁለት የተለያዩ ድርጊቶች አይደሉም። በአንተ መደሰት ነው አንተን የሚያከብርህ። You are most glorified in us when we're most satisfied in You. የህይወት ዋና ግብ (my cheif end) በአንተ መርካትና በአንተ መደሰት ከሆነ በእርግጥም ዋናው ግብሬ መሆን ያለበት አንተን ለማወቅ መትጋት ላይ ነው። አንተን አውቆ በአንተ አለመደሰት፣ በአንተ አለመርካት፣ አንተንም አለማክበር አይቻልምና።

ኑዛዜዬ ይሄ ነው። ብዙ ያከማቸሁት ከንቱ ዕውቀት አለኝ። የምመካበት። I'm a psuedo intellectual with an ego way bigger than my ability to comprehend ideas. Thats why I keep trying to figure you out like one of the other concepts I like thinking about instead of getting to know You as a Person.

አንተን ለማወቅ የሚጠበቅብኝ ትህትና እና አላውቅም ማለት ከብዶኝ ነው የተቸገርኩት። ስለአንተ ማወቅ አንተን ማወቅን አስረስቶኛል። አንዳንዴ ትምህርት ትሆንብኛለህ። አየር ላይ ብቻ ያለህ ሀሳብ። ለዛሬ የኢትዮጵያ ህይወቴ ምንም አንድምታ የሌለህ ቀኖናና የተለያዩ አመለካከቶች ጥርቅም። አንዳንዴ ደግሞ ለህይወት ትልልቅ ገፅታዎች እንጂ ለአዘቦት ቀን ህመሞች ምንም ፋይዳ የሌለህ አድርጌ እየወሰድኩህ የማይመለከቱህ" የመሰሉኝን ችግሮች ብቻዬን እታገላለሁ። እንደምትወደኝ፣ እንደምታስብልኝ፣ እንደአባት ለኔ ያለህን ልብ አለማወቄ ስንት ዋጋ እንዳስከፈለኝ ታውቃለህ። ደግሞ እኮ አንተን ማወቅ ህይወት እንደሆነ ሳላውቅ ቀርቼ ቢሆን እሺ...I know for certain that this is what life is all about.

Please, remind me of the emptiness in the world. So grant me the mind of a student. Remove pretentious pride from my heart and let me see you and be thrilled with unexplainable privilege of knowing you.
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መክብብ 4:13-16 (Part 8)

ቁጥር 13 የሚጀምረው የታወረ መሪነትን ማለትም ምክርን መቀበል የሚባለው ሀሳብ እንግዳ የሚሆንበት ፣ መቼ ከሀላፊነቱ ዘወር ማለት እንዳለበት ለማወቅ እንዳይችል ጉድለቱ የማይታየው ሰው ከወጣት፣ ጠቢብና ውጤታማ ሆኖ ግን ከማይመሰገን መሪ ጋር በማነፃፀር ነው። የመጀመርያው መሪ በሁለተኛው ይተካል።

የሽግግሩ ሰሞን አዲሱ መሪ ተቀባይነቱ ከፍተኛ ነው። ሁሉ ይከተሉታል። ነገርግን ከጊዜ በኋላ በሚመጡት ሰዎች ፊት ሞገስ ያጣል። ከእርሱ በኋላ የሚመጡ አይደሰቱበትም። ይህንንም ከንቱ ነው ይለዋል ሰባኪው። The injustice here is becoming unappreciated.

The conclusion could be something along the lines of.. good leaders can be forgotten. Popularity and giftedness aren't things we can actually rely on to have a great legacy. Todays hero can be tomorrows beggar. No one is fully safe from such brutal betrayal.

Unless our motivation for being great surpasses the desire to make a name for ourselves , gain acceptance, recognition and noteriety, we are setting ourselves up for a huge disappointment.

ዝም ብላችሁ አስቡት... ብዙ የሚገራርም ስራ የሰሩ፣ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው፣ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ የተወጡ ፣ ከሚጠበቅባቸው አልፈው የሚኖሩ ሰዎች በዙርያችን አሉ። መሪነት ከፖለቲካዊ አስተዳደር ስለሚያልፍ እነዚህ ሰዎች በተፅዕኖ አኳያ ለተነካኳቸው ሁሉ በጎ ለውጥ የሚያመጡ መሪዎችና ምሳሌዎች ሆነው ሳለ የትኛውም መፅሄት ፎቷቸውን cover አያደርግም። ማንም አይዘፍንላቸውም። ለክብራቸው የተሰራ documenteryም ሆነ biography የለም።

ታማኝነታቸውና ትጋታቸው አልታየም ወይንም recognition አላገኘም ማለት ግን ውጤታማ አልነበሩም ማለት አይደለም የሚለው ሀሳብ ከነዚህ አጭር ቁጥሮች የምንወስደው ትልቅ ትምህርት ይመስለኛል። This is incredibly liberating in how we conceptualize effectiveness in whatever God has called us to do. ምስጋናና ክብር ከሰው መፈለግ ከንቱ ነው። በተለይ ደግሞ የምናደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር የምናደርግ ከሆነ!

ይሄ ሀሳብ የሚያስታውሰኝ ስለነአናንያና ሰጲራ የተሰበክነው ስብከት አለ። በርናባስ 'የመፅናናት ልጅ' ተብሎ ስም ሲሰጠውና ሲመሰገን ማየታቸው የተለየ ክብርንና impressive መስሎ መታየትን እንዲፈልጉ ስላደረጋቸው ነው የዋሹት ብንል የተሳሳተ ግምት አይመስለኝም (የሰውን የውስጥ motive 100% ማወቅ ባንችልም)

እና የአንዳንድ ሰዎች በአደባባይ መመስገን በ'ተራው ማህበረሰብ' ውስጥ  እንዲህ አይነት መርዝ የሚያጋባ ከሆነ recognition መስጠት ከነአካቴው ቢቀርስ ብለን እንድንጠይቅ ሊያደርገን ይችላል። ነገርግን ሰው ለሰራው ስራ መመስገኑ መልካም ነው። እንደ ተራ ሰው ደግሞ የክርስትና ህይወት ውስጥ ያሉ imparatives (ትዕዛዞች) በመስቀሉ ከተቀበልነው/ ከምንቀበለው ጉልበትና ፀጋ የተነሳ የሚቻሉ (possible) እንደሆኑ የሚመሰገኑ ስም ያላቸው ህያው ምስክሮች ያስፈልጉናል ብዬ አስባለው።

ምናልባት ቅናትን risk እናደርግ ይሆናል። ነገርግን ከኮረጅንም ውጤታማ እንዲሆኑ ያስቻላው background ስራ ላይ ትኩረት በማድረግ ለሰዎች genuinely መደሰት የምንችል ይመስለኛል። በተለይ ደግሞ እንደክርስቲያን ስናስብ we worship a God who made Himself of no reputation. ከኢየሱስ ክርስቶስ በላይ low key የኖረ የለም።

ምስጋናና ክብር እየተገባው ሙሉ ትኩረቱን የተላከበት ስራ ላይ አድርጎ የተገፋና በገዛ ወገኖቹ ለሞት የተሰጠ አምላክ ነው ያለን። ምንባቡ ላይ እንዳለው ተተኪ ወጣት እንጀራን ሲያበዛ የተንጋጉት ደጋፊዎች ሁሉ eventually ተበትነዋል። እንኳን አድናቂ ወዳጅ ብሎ ያስጠጋቸው ደቀመዛሙርቱ ሳይቀር ከድተውታል።
Pursuing Holiness
መክብብ 4:13-16 (Part 8) ቁጥር 13 የሚጀምረው የታወረ መሪነትን ማለትም ምክርን መቀበል የሚባለው ሀሳብ እንግዳ የሚሆንበት ፣ መቼ ከሀላፊነቱ ዘወር ማለት እንዳለበት ለማወቅ እንዳይችል ጉድለቱ የማይታየው ሰው ከወጣት፣ ጠቢብና ውጤታማ ሆኖ ግን ከማይመሰገን መሪ ጋር በማነፃፀር ነው። የመጀመርያው መሪ በሁለተኛው ይተካል። የሽግግሩ ሰሞን አዲሱ መሪ ተቀባይነቱ ከፍተኛ ነው። ሁሉ ይከተሉታል።…
ጠቢቡ እግዚአብሔር ሆይ አስተዳዳሪነትህ እንዴት ድንቅ ነው? መሪነትን ከአንተ በላይ ማን ማስተማር ይችላል? You miss nothing. No detail is too small. Nothing is overlooked. ቸል ብለኸው ለአንተ ማን ምን ያስታውስሀል? አማካሪ ሳያሻህ ብቻህን ሁሉን ትገዛለህ። አትሳሳትም። እንከን ስለሌለብህ ከአንተ የተሻለ መሪ መጥቶ ዙፋንህን አይሽረውም።መንግስትህ ዘለዓለማዊ እና ፅኑ ነው።

በተለያየ ምህዳር የሚመሩን መሪዎች ግን እንዲህ አይደሉም። እንደሰው ያለባቸውን ጉድለት አገናዝበው አይመከሩም። ሀላፊነታቸውን አለመወጣት ብቻም ሳይሆን በውል ገና አልተረዱትም። በተለይ ይሄ በቤተክርስቲያን ሲሆን እንዴት ያሳዝንህ ይሆን? ምስጋናና ክብር ከሰው በመፈለግና በስልጣን ወዳድነት የሚከሰተውን ቀውስ ታያለህ!

ጥበብ ለጎደላቸው መሪዎቻችን ውጤታማ የሆነ አማካሪ አዘጋጅ። Grant that they have teachable heart that can take constructive criticism. Don't let them chase popularity at the expense of neglecting their duties.

የዝናን ከንቱነት በሚገባቸው መንገድ አስረዳቸው። መረሳት የህይወት አይቀሬ እውነት መሆኑን በመረዳት የዕለትተለት ስራቸው ላይ ትኩረት ማድረግ እንዲችሉ ከምንም በላይ በአንተ ዘንድ በልጅህ በክርስቶስ በኩል ያላቸውን ተቀባይነት treasure በማድረግ ከዚህ ከንቱ pursuit ነፃ አውጣቸው። For whatever reason ታዋቂ የሆኑን ደግሞ ያንን ዝና በአግባቡ handle ማድረግ የሚችሉበትን ጥበብ አንተ ስጣቸው።

ደግሞ ጌታ ሆይ ሰውን ለበጎ የሚያነቃቁ.. በትጋት ስራቸውን የሚወጡ፣ ማድረግ ከሚገባቸው over and beyond በማለፍ የሚታትሩ ሰዎች እንዲሸለሙ እንፀልያለን። ስማቸውን ረስተው የሚያደርጉትን ሁሉ ለአንተ ክብር dedicate አድርገው low key የሚኖሩ ውብ ነፍሶች ተስፋ እንዳይቆርጡ እነርሱን የሚያበረታታ ሰው አስነሳላቸው። ሁላችንም በዙርያችን ያሉትን እነዚህን ሰዎች notice ማድረግ እንድንችል አይናችንን ክፈት።

Just because they forget their names, it doesn't mean we should we forget theirs! ምስክርነታቸውን በማድነቅና acknowledge በማድረግ ውስጥ ያለው በረከት ብዙ ነው። የእነሱ ልብ አይወድቅም። (If we do it in a way that doesn't awake pride) እኛም ደግሞ ለራሳችን ጥሪ የሚጠቅመንን ህያው ነፍስ ያለው ምሳሌ እናገኝበታለን።

ቅናት የሚባለውን መርዝ ከውስጣችን አሟጠህ አስወግድ። ማርከሻውን ትህትና አስተምረን። አንተ እንኳን ራስህን ዝቅ አድርገህ reputation አጥተሀል። ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለ ስም ያለህ አምላክ መበለቶችንና የተናቁትን ሰዎች ለማየት፣ recognition ለመስጠትና ለማድነቅ አልከበደህም!

የትኛው ክብራችን ነው ታድያ እኛ በዙርያችን ውጤታማ የሆኑ ወገኖቻችንን እንዳናሞግስ እንቅፋት የሚሆንብን? በተለይ የእምነት ወንድሞቻችን ስኬት የእኛ እንደሆነ ሁሉ በእነሱ ድል እንድንደሰት በአንተ ተሳስረናል። Credit ፍለጋ አጉል እንዳንባክን grant that we have the ability to genuinely celebrate people without deifying them lest they're tempted to be prideful.

በመጨረሻም ወጣቱ ባጨበጨቡለት ሰው ተከድቷል። This is the bitter truth everyone comes to terms with eventually. ፈቃድህ ቢሆን ከከሀዲ አጨብጫቢዎች ሰውረን። Don't let our hearts be accustomed to their attention. Inevitable እጣፈንታችን ሆኖ ወዳጅ፣ ወንድም፣ ደጋፊ ያልናቸው ሰዎች ከከዱን ደግሞ በአንተ ታማኝነት የተሰበረ ልባችን እንዲጠገን እንለምንሃለን።
Audio
ብርሃንህ ፡ ብርሃኔ ፡ ለእኔ ፡ ሆኖ
በመንገዴ ፡ አንተን ፡ እያየሁ
ያወጅኩትን ፡ ሞትህን ፡ ቀምሼ
በትንሳኤ ፡ ልምሰልህ ፡ እርዳኝ

ላይህ ፡ እናፍቃለሁ ጌታ ፡ እናፍቃለሁ
ላይህ ፡ እናፍቃለሁ ፡ ጌታዬ
የእጆችህን ፡ ቁስል የእግሮችህን ፡ ቁስል
የተወጋው ፡ የቀኝ ፡ ጐንህን

እንባዬ ፡ ይሰማህ ፡ ከዙፋንህ
ብሩህ ፡ ሗህንም ፡ ሰንጥቆ
ነፍሴ ፡ የምታርፍበት ፡ አጣች ፡ ጌታ
መቼ ፡ ነው ፡ የማይህ ፡ ስትመጣ

ሁሉን ፡ ለመፈጸም ፡ ጌታ ፡ ሲታይ
ክብሩን ፡ አንሠራፍቶ ፡ በሰማይ
ልጆቹን ፡ ለመንጠቅ ፡ ሲልክ ፡ እጁን
ምን ፡ ስሰራ ፡ ያገኘኝ ፡ ይሆን?

በተጠራ ፡ ጊዜ ፡ ቃሌን ፡ ሰምቶ
ያልጠበቀኝ ፡ በጊዜው ፡ ነቅቶ
ዕድሉን ፡ ያጐድላል ፡ ብሏልና
ነፍሴ ፡ ሳትደክም ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ና
እውነተኛ ደስታ ከወሲብ ኀጢአት ነፃ አወጣው

የርካሽ ፍቅሮች መፍያ አፍላል

አውግስጢኖስ የተወለደው እ.ኤ.አ. ሕዳር 13፣ 354 አሁን ላይ አልጄሪያ በመባል በምትታወቀው ታጋስቴ በምትባል ስፍራ ነበር። ታጋስቴ ሂፖ በምትባለው ከተማ አቅራቢያ ያለች ከተማ ነች። መካከለኛ ገቢ የነበረውና በግብርና ሥራ ይተዳደር የነበረው አባቱ ፓትሪሺየስ፣ ልጃቸው አውግስጢኖስ በንግግር ጥበብ ሊያገኝ የሚችለውን የላቀ ትምህርት ሁሉ እንዲያገኝ ጠንክረው ይሠሩ ነበር። ዕድሜው ከዐሥራ አንድ እስከ ዐሥራ አምስት አመት ሳለ ከሚኖርበት ስፍራ ሠላሳ ሁለት ኪሎ ሜትር የሚያክል ርቃ በምትገኝ ማዳውራ በተባለች ከተማ ተማረ። በመቀጠልም አንድ ዓመት ቤት ወስጥ ከቆየ በኋላ ከዐሥራ ሰባት ዓመቱ አንሥቶ ሃያ ዓመት እስኪሞላው በካርቴጅ ትምህርቱን ተከታተለ።

አውግስጢኖስ ለሦስት ዓመት ትምህርት ወደ ካርቴጅ ከመሄዱ በፊት እናቱ ዝሙት እንዳይፈጽም ከምንም በላይ ደግሞ የማንንም ሚስት እንዳያማልል አበክራ አስጠንቅቃው ነበር። ይሁን እንጂ አውግስጢኖስ ከጊዜ በኋላ ኑዛዜ በተሰኘ መጽሐፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ “የርካሽ ፍቅሮች መፍለቅለቂያና መፍያ አፍላል ወደ ሆነው ካርቴጅ መጣሁ… በውስጤ ውስጣዊ ምግብ የሆንከው የአንተ የአምላኬ የማያቋርጥ ራብ ነበር።”[1] በካርቴጅ አንድ ቁባት ይዞ ለዐሥራ አምስት ዓመት አብሯት የኖረ ሲሆን አዲዎዳቱሰ የተባለ አንድ ወንድ ልጅ ከእርሷ ወልዷል።

አውግስጢኖስ ከዐሥራ ዘጠኝ ዓመቱ አንሥቶ እስከ ሠላሳ ዓመቱ ድረስ ለሚቀጥሉት ዐሥራ አንድ ዓመታት የንግግር ጥበብ መምህር በመሆን ያስተምር ነበር።

ተጨማሪ ለማንበብ...

Telegram | YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | Website

#Articles
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ምህረትህን በማለዳ ታማኝነትህንም በለሊት ማወጅ መልካም ነው። (መዝ 92:2)

ሁለት ነገር

እግዚአብሔር መሀሪ ነው። As one preacher put it.. He is so merciful that his seat is literally called a mercy seat. ቆጥረን የማንዘልቀውን ሀጥያታችንን የሚከድን ምህረት.. በተሰበረ ልብ ንስሀ የሚገባውን ጎስቋላ ቀና አድርጎ ያቆማል። ለሀጥያት የሚገባውን ክፍያ ራሱ absorb በማድረግና በክርስቶስ ክቡር ደም በማስተሰረይ ይቅርታን አጊኝተናል። ምህረቱ ፍቅር አለበት። ምህረቱ ታጋሽ ነው። ምህረቱ አይለዋወጥም። ዛሬም እንደቀድሞው ሀጥዓንን restore ያደርጋል። ነፍስን ይመልሳል። በሀጥያታችን ምክኒያት የሚገባንን ቅጣት በማስወገድ ብቻም አያበቃም.. አለን የምንለው በረከት በሙሉ የእግዚአብሔር ምህረት ነው። ያለ ምህረቱ ምንም የለንም። ከአባታችን የምንለምነው ሀሉ የሚሰጠን በእኛ ላይ ከገነነው ምህረት የተነሳ ነው። በማለዳ ምህረቱን እያሰቡ ማመስገን መልካም ነው። ከአላስፈላጊ ፀፀትና ሀፍረት፣ ከሀጥያት ሸክም፣ ከድካምና ከሀዘን ይፈውሳል። በመከራ ውስጥ ብንሆን እንኳን ትናንት ያቆመንን ምህረት ለዛሬም እንድንታመን ድፍረት ይሰጠናል።

2, እግዚአብሔር ታማኝ ነው... እኛ ሳንታመንለትም የማይዋዥቅ ታማኝነቱ- ልብ ይጣልበታል። ጊዜ ስለማይለውጠው አያሰጋም። በታሪክ ውስጥ የማንንም አደራ ሲበላ አልሰማንም። ይሄን ሁሉ ዘመን ሲያስተዳድር የማንም እንባ ዕዳ የለበትም። እንደተናገረው ቃሉን ይፈፅማል። ይዋሽ ዘንድ ሰው አይደለም።  መለወጥ ሳይኖርበት የኖረ .. ያለ.. የሚኖር ነው። ያልተሸነቆረ አስተማማኝ ዓለት ነው። ሲደገፉት እንደሸንበቆ ተሰብሮ አደጋ ላይ የማይጥል ወዳጅ ነው። የወደዳቸውን እስከመጨረሻው የሚወድ። ትናንትን በስውር እጁ አሻግሮ ..ለዛሬ የማይታክት አባት ነው። እንኳን ለዚህኛው ለሚመጣውም አለም ተስፋ ያደረግነው "ተስፋን የሰጠ የታመነ ስለሆነ" ነው። በለሊት ታማኝነቱን ማወጅ ለጭንቀት ማርከሻ ነው። Its the only antidote for anxiety. We can always rely on His words. Great is His faithfulness.
ታሕሳስ 27 | ወደር የሌለው የእግዚአብሔር ስጦታ

የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከእርሱ ጋር ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም! ይህ ብቻ አይደለም። ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ ሐሤት እናደርጋለን። (ሮሜ 5፥10-11)

ዕርቅን ተቀብለን በእግዚአብሔር ልንመካ የምንችለው እንዴት ነው? ይህንን ልናደርግ የምንችለው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ነው። ይህ ማለት በአዲስ ኪዳን በሥራው እና በንግግሩ የተገለጸውን የኢየሱስን ማንነት በእግዚአብሔር የምንደሰትበት ዋነኛው ነገር እናደርገዋለን ማለት ነው። በአዲስ ኪዳን በማንነቱ እና በሥራው በተገለጠው ኢየሱስ አማካኝነት በእግዚአብሔር ሐሴት እናደርጋለን። ክርስቶስን ማዕከላዊ ሳናደርግ በእግዚአብሔር ለመደሰት ብንሞክር ክርስቶስን ሳናከብር እንቀራለን። ክርስቶስ ባልከበረበት ደግሞ እግዚአብሔርም አይከብርም።

በ2ኛ ቆሮንቶስ 4፥4-6 ጳውሎስ በክርስቶስ መለወጥን በሁለት መንገድ ይገልጸዋል። በቁጥር 4 መሠረት የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነውን የክርስቶስን ክብር መመልከት ነው። ቁጥር 6 ላይ ደግሞ በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን ክብር መመልከት እንደሆነ ይነግረናል። በሁለቱም መንገድ ዋና ሐሳቡ ምን እንደሆነ ግልጽ ነው። የእግዚአብሔር መልክ የሆነው ክርስቶስ አለን፤ ከዚያ ደግሞ በክርስቶስ መልክ ውስጥ እግዚአብሔር አለን።

በእግዚአብሔር ሐሴት የምናደርገው በክርስቶስ ኢየሱስ መልክ ውስጥ በምናየው እና በምናውቀው እግዚአብሔር ሐሴት በማድረግ ነው። ይህን ደግሞ በሙላት ልንለማመድ የምንችለው የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ሲፈስ እንደሆነ ሮሜ 5፥5 ይነግረናል። ያ ጣፋጭ የሆነ፣ ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ የእግዚአብሔር ፍቅር የቁጥር 6ን ታሪካዊ እውነተኝነት ስናሰላስል ለእኛ ደግሞ ተግባራዊ ይሆናል። “ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና” (ሮሜ 5፥6)።

የገና ዋና ነጥቡ ይህ ነው። እግዚአብሔር በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዕርቅን ገዛልን ብቻ አይደለም (ሮሜ 5፥10)። እንደገናም ደግሞ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ዕርቅ ማግኘት እንድንችል አደረገን ብቻም አይደለም። ከዚህ ሁሉ በተጨማሪ፣ አሁን ላይ ሆነን በመንፈስ ቅዱስ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በራሱ በእግዚአብሔር ሐሤት ማድረግ ሆኖልናል!

ኢየሱስ ዕርቅን ገዝቶልናል። ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅን አስገኝቶልናል፤ በእርሱ አማካኝነት ስጦታውን መክፈት ሆኖልናል። አምላክ የሆነው ኢየሱስ ራሱ ሥጋ ለብሶ፣ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ስጦታ ሆኖ በፊታችን በመቅረብ፣ በእግዚአብሔር መደሰት እንችል ዘንድ ልባችንን ያቀጣጥላል።

በዚህ ገና ወደ ኢየሱስ ተመልከቱ። በደሙ የገዛውን ዕርቅ ተቀበሉ። የሰጣችሁን ስጦታ እንደታሸገ መደርደሪያ ላይ አታስቀምጡት። ስትከፍቱት ደግሞ በውስጡ ያለው ስጦታ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቂያችን የሆነው ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ አስታውሱ።

በእርሱ ሐሤት አድርጉ። የእርካታችሁ ምንጭ ይሁን። ውዱ ሀብታችሁ አድርጉት።

Telegram | YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | X (Twitter) | Website

#ለዛሬ
Follow Dane on X
ለአማኑኤል...ስጦታዬ!

ከሰው ባህሪ ቅር የሚለኝ ነገር መሀከል አንዱ አስደናቂ ነገሮችን ጭምር ብዙ በረከትና ተዓምራትን ቶሎ መልመዱ ነው። በተለይ ደግሞ  ከልጅነት ስንሰማው ያደግነው ጀብዱ through time we start considering them to be unremarkable. Ordinary. ነገር ግን ቃል ስጋ መሆንህ..አምላክ በመሀከላችን ማደርህ (ዩሐ 1:14)  ነብዩ "የዘለዘለዓለም አባት" ብሎ የተናገረልህ ንጉስ፣ እግዚያብሄር ወልድ ስጋን ለብሰህ (ዕብ 2:17) የትህትናህን ትርጉም ዝቅ በማለት ማሳየትህ (ፊሊ 2:6) ትልቅ ክስተት ነው።

እንደአምላክነትህ ስለማትለወጥ መለኮትነትህ ሳይነካ (ዕብ 13:8) እውነተኛ ሰው ሆነሀል። You're the defining moment in history. የአንተ መወለድ ነው መሀከለኛ ያስገኘልን።  (1 ጢሞ 2:5) አለበለዚያ ወኪል ፍለጋ "በሁለታችንም ላይ እጅ የሚጭን በመካከላችንም የሚዳኝ ቢኖር (ኢዮብ 9:33) እያልን impossible በሆነ አጣብቂኝ ውስጥ በገባን ነበር።

የእግዚአብሄር ልጅ ሆይ መለኮትነትህ የማይካድ እውነታ ነው። የውልደትህ ትርክት እስከነፋይዳው ለዘመናት የተተነበየና የተጠበቀ እውነት ነው። በጊዜ የምትገደብበት የጅማሬህ ልደት የለም። ውልደት አልፈጠረህም። በምድር ስትመላለስ የሰራኸው ጀብዱ ዛሬም መለኮትነትህን ይዘክራል። በተፈጥሮ ላይ ያለህን ጌትነት በድንቅና ተዓምራቶችህ አሳይተኸናል። ሀጥያትን በምድር ሆነህ ይቅር ብለሀል። ሙታንን አስነስተሀል። ማንም ቦታ ለማይሰጣቸው ራርተህ መፍትሄን ሰጥተሀቸዋል። ደካሞችን ልታሳርፍ የምትጠራ የሀጥያተኞች ወዳጅ ነህ። ትንሳኤህም የማይደገም ታላቅ ብርታትህ መገለጫ ነው።  I'm equally blown away by your greatness and lowliness! I love that your attributes compliment eachother so well. አይፎካከሩም።

የገና በዓል ሲመጣ ግን በአፅንዖት ማሰብ የምፈልገው ስብዕናህን ነው። ለረጅም ጊዜ ሰው'ነትህ የይስሙላ ይመስለኝ ነበር። ..እንደሰው መብላት መተኛትህን (ማቲ 4:2) ፤ ሲመቱህ መድማትህን (ዩሐ 19:34) መከፋት መቆጣትህን (ማቲ 26:37, ማር 3:5) ያለው አንድምታ እምብዛም አይታየኝም ነበር። But your incarnation is what makes Christmas joyful!  ሰው መሆንህ ያመጣልን ትሩፋት ተዘርዝሮ አያልቅም! አባቶች impassible የሚሉት የአምላክ አይነኬነት.. መከራን መቀበል አለመቻል ብቸኛ exception የአንተ መወለድ ነው። ሰው ሆነህ ባትመጣ መከራችንን መቀበል አትችልም ነበር።

የዕብራውያን መፅሀፍ እንዳለው በድካማችን የምትራራበት መንገድ ራሱ hypothetical/ anticipatory ብቻ ይሆን ነበር። አሁን ግን ለአንተ ብዙ ሳላብራራ ይገባሀል። ሰው ስለሆንክ ነው ለሰዎች የተሰጠውን ህግ የፈፀምከው።  (ገላ 4:4, ማቲ 5:17) ሰው ስለሆንክ ነው ደምህን ስለሀጥያታችን ስርየት ያፈሰስከው (ዕብ 9:22, 10:5) ደግሞ ሰውም ስትሆን የናዝሬት ሰው መሆንህ shows who you identify with. Your humility is matchless my King!

You're not just a doctrine to me. You're not a paradox for me to figure out. You're a person. You're a person to be known, to be loved, to be treasured , to be marvelled at, to be made much of, to be worshipped, to live and to die for! የሆንነውን ሁሉ የሆነው ከአንተ የተነሳ ነው። ከአንተ ወደማን እንሄዳለን? አንተ (ብቻ) የህይወት ቃል አለህ።

የሀጥያተኞች ወዳጅ ሆነህ ጠላት የነበርነውን የእግዚአብሔር ወዳጆች አደረከን። በራሳቸው የሚተማመኑ ትምክህተኞች በውጫዊ ፅድቃቸው አልሸነገሉህም። የተለሰኑ መቃብር መሆናቸውን አይተህ ቢጤዎቻችንን አህዛብ፣ ቀራጮች፣ ተቅበዝባዥ የጠፉ በጎችን ወደድግስህ ጠርተሀል። ከመለኮታዊ ክብርህ የባዘነውን ፍለጋ የወረድክ መልካም እረኛ ነህ።  (Luke 19:10, Matt 9:13..)

I (actually) owe You everything. Everything I have now was given to me because of You. Apart from you I have no claim, no plea to ask God for anything. You, Yourself are given to me as a gift. The Greatest gift there could ever be! And you have bestowed countless other gifts to me. Christ Jesus, I'm eternally grateful for all your blessings you've given me.

I am especially gratefull today for everything that is a means for me to get to know you more! Because You are the greatest Good and my greatest need. So I don't want to take all the beautiful godly people you've surrounded me with, the providence of having a functioning brain and the luxury of time to pursue you as well as having access to resources that reveal You for granted!

ያንተን መልካምነት የሚያሳየኝ ነገር ብዙ ነው። ጎደለ የምለው ሺህ ነገር ቢሟላ አንተ ከሌለህ ከንቱ መሆኑን ስለምታውቅ ነው በቅድሚያ ራስህን የሰጠኸኝ። ስጦታዬ አማኑኤል ራስህ ነህ። ከስሞች ሁሉ በላይ ስም ያለህ፣ ስልጣን ሁሉ የተሰጠህ ጌታ ኢየሱስ አንተ ሁሉ በሁሉ ነህ። የዘላለም አባት፣ ሀያል አምላክ፣ My wonderful counseler! ምክርህ በእርግጥም ሰው ያደርጋል! የወይኑ ግንድ ሆይ ያለአንተ ምንም ላደርግ እንደማልችል ገብቶኝ ይህች ቀን ከአንተ ጋር የምጣበቅበት ትሁን። My Lord and Savior Jesus Christ, draw me close so I may cleave to You alone.

የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ የሰዉ ልጅ ሆነህ ታላቅ ወንድም ከሆንከኝ ከዚህ በላይ ምን ትምክህት እሻለው? ዛሬ ራሴን define የማደርገው የአንተ ልጅ በመሆኔ ነው። ይህን የከበረ እድል በነፃ ሰጠኸኝ። ከሀጥያተኞች ዋና የሆንኩ እኔ በአንተ እንድፀድቅ ምትኬ ሆንክልኝ። በትዕቢት የወደቅኩትን እኔን ልታነሳ ራስህን አዋረድክ። ከዚህ በላይ ስጦታ ከየት ይገኛል?

አማኑኤል...እግዚአብሔር ከእኛ ጋር። No words can express how much we don't deserve this precious gift. We don't even have to wonder about it.. we are unworthy. But thats the definition and beauty of Grace. And we will do well if we use any excuse to thank God for His amazing grace he has shown us. እንደሰብዓሰገል ይዘን የምንሄደው እጅ መንሻ እንደነዚህ ብዙ ምስጋና ያዘሉ imperfect ደካማ ቃላትና ድሪቶ ሰባራ ልብ ቢሆንም ያለንን ስጦታ እንሰጠው። በበረት የተወለደው ንጉስ በደስታ ይቀበለናል።
"Now we cannot discover our failure to keep God’s law except by trying our very hardest (and then failing). Unless we really try, whatever we say there will always be at the back of our minds the idea that if we try harder next time we shall succeed in being completely good. Thus, in one sense, the road back to God is a road of moral effort, of trying harder and harder. But in another sense it is not trying that is ever going to bring us home. All this trying leads up to the vital moment at which you turn to God and say, “You must do this. I can’t.”
አቅማችንን አሟጠን ሞክረን እስካልተሸነፍን ድረስ ህገ-እግዚአብሄርን መጠበቅ አለመቻላችንን ማወቅ አንችልም ይልቁንም ሁልጊዜ በውስጠታችን ትንሽ ጨምረን ብንጥር ተሳክቶልን ሙሉ ለሙሉ መልካም የምንሆን ይመስለናል። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር የሚመልሰን መንገድ አብዝቶ በፅናት መጣጣርና መሞከር ነው። በርግጥ የኛ ጥረት ብቁ ሆኖ ወደቤት አያደርሰንም ነገርግን መሟሟታችን ወደእግዚአብሔር ዞረን "አንተ ካለወጥከኝ በራሴ አቅም የለኝም" ወደምንልበት ሁነኛ ቦታ ያደርሰናል።
CS Lewis
2025/07/07 11:14:37
Back to Top
HTML Embed Code: