Telegram Web Link
Tell-me-the-old-old-story
<unknown>
Tell me the old, old story, of unseen things above
Of Jesus and His glory, of Jesus and His love;
Tell me the story simply, as to a little child,
For I am weak and weary and helpless and defiled.

Tell me the old, old story, Tell me the old, old story
Of Jesus and His love.


Tell me the story slowly, that I may take it in
That wonderful redemption God’s remedy for sin;
Tell me the story often, for I forget so soon
The “early dew” of morning has passed away at noon.

Tell me the story softly, with earnest tones and grave;
Remember I’m the sinner whom Jesus came to save;
Tell me the story always, if you would really be,
In any time of trouble, a comforter to me.

Tell me the same old story, when you have cause to fear
That this world’s empty glory is costing me too dear;
And when the Lord’s bright glory is dawning on my soul,
Tell me the old, old story: “Christ Jesus makes thee whole.”
Thank you for the series of events that made You my only hope in heaven , my greatest desire on earth and my most prized treasure. Thank you for my feeble heart and flesh that consistently fails which made me rely on You, my strength. In You I have found, Every good thing. You yourself are the greatest good. And I get to call you my eternal portion :)
መክብብ 5:1-7 (Part 9)

ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ።
የእግዚአብሔር ቤት በራሱ ሰፊ የሆነ ሀሳብን የተሸከመ ሀረግ ቢሆንም በዚህ አውድ የአምልኮ ስፍራን የሚወክል ይመስለኛል። ሰባኪው አምልኮን ለማቅረብ ስንሄድ / ስናቀርብ behave እንድናደርግ እያስጠነቀቀ ነው። እግር ደግሞ ስብዕናን የሚመስል ቃል ነው። Creatureliness or humanity የሚል ሀሳብን በውስጡ ያዘለ ነው። ይህ ማለት ሰው'ነታችን ጌታ ጋር እንዳንቀርብ ይከለክለናል ሳይሆን we should keep in mind that we are flawed humans and act accordingly. Guard your steps, keep your mind on how you approach አይነት ነው ትዕዛዙ።

ለመስማት መቅረብ የሞኞችን መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤ እነርሱ ክፉ እንደሚሠሩ አያውቁምና።
አስቀድሞም ለሰጠው ማስጠንቀቂያ ምክኒያት ከዚህ እናገኛለን። አምልኮን ማቅረብ በጎ ተግባር ነው። ወደእግዚአብሔር ቤት መሄድም እንደዚሁ መልካም ነው። But we should not do the right things for a wrong reason or in a wrong manner
ስለዚህ በስንፍና ከመሰዋት ይልቅ ለመስማት (ብቻ) መቅረብ ይሻላል።

በአፍህ አትፍጠን፤ በአምላክም ፊት ማንኛውንም ነገር ለመናገር፣ በልብህ አትቸኵል፤ አምላክ በሰማይ፣ አንተ ደግሞ በምድር ነህ፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።

አስቀድሞ ሰው መሆንህን አስብ ማለቱ በጣም ጠቃሚ ይሐስለኛል እየዚህን ቁጥሮች ለመረዳች። የሆነ ነገር ለማግኘት የቸኮለ ልብና እንደሰው ያለበትን ገደብ የማያገናዝብ ሰው ምላሽ ወደእግዚአብሔር ሀልዎት እንደገባ የሚዘባርቀው ነገር ብዙ ነው። ይሄንን እንደቀላል ነገር እናየው ይሆናል afterall who cares how a person prays or what he says in his prayer የሚል unspoken sentiment አለ በዘመናችን። ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ትክክለኛ ቦታውን ያውቃል። እግዚአብሔር በሰማይ ነው። እኛ በምድር ነን። ሰባኪው ደጋግሞ ስለ "ከፀሀይ በታች" ማውራቱ ይሄን ሊያስታውሰን ይገባል። እይታችን፣ እወሸቀታችን፣ ሀይላችን ውስን መሆኑን ከግምት ውስጥ ያስገባ ንግግር ነው በአምላክ ፊት የሚቀርበው። በዚህ መርህ ሲሆን by default ንግግራችን ይመጠናል።

በሥራ ብዛት ሕልም እንደሚታይ፣ ብዙ ቃል ባለበትም የሞኝ ንግግር ይገለጣል።
Afterall what we do matters more than the promises we make. Good intention ብቻውን ጥቅም የለውም። በስራ የማይታይ ንግግር ሁሉ ከንቱ ነው። የሚሰሩ ሰዎች የሚያገኙትን ክብር እሰራለው ብሎ በመፎከር ብቻ ማግኘት ሞኝነት ነው። አንድ ነገር የምር ህልማችን መሆኑን የምናውቀው actively pursue ካደረግነው ብቻ ነው።

ለአምላክ ስእለትን በተሳልህ ጊዜ ለመፈጸም አትዘግይ፤ በሞኞች ደስ አይለውምና፤ ስእለትህን ፈጽም። ስእለት ተስሎ ካለመፈጸም፣ አለመሳል ይሻላል።አንደበትህ ወደ ኀጢአት እንዲመራህ አትፍቀድ፤ ለቤተ መቅደስ መልእክተኛም፣ “የተሳልሁት በስሕተት ነበር” አትበል። አምላክ በተናገርኸው ተቈጥቶ የእጅህን ሥራ ለምን ያጥፋ?

Not much I can say on this. Its very clear and direct. በኛ ዘመን የስዕለት ሀሳብ ቸል የተባለ ይመስለኛል ነገርግን ዘዳ 23:21, ሐዋ 5..ሌሎችም ብዙ ቦታዎች ላይ ያለ ሀሳብ ነው። የወደፊቱን ስለማናውቅ lets say there might come a time የምንሳልበት.. የዛኔ መፈፀም ብቻ ሳይሆን ሳይዘገዩ፣ ሰበብ ሳያበዙ መፈፀም ነው መርሁ። አንደበት ወደዚህ እግዚአብሔርን ወደሚያስቆጣ ሀጥያት መከልከል ቀላል ነው። እንደማናደርግ የምናውቀውን ነገር አደርጋለው አለማለት። በሰው ፊት ስዕለታችንን አውጀን አድናቆት ለጊዜው እንሰርቅ ይሆናል እንጂ እግዚአብሔር አይሸነገልም።

ብዙ ሕልምና ብዙ ቃል ከንቱ ነው፤ ስለዚህ አምላክን ፍራ።
የዚህ section መዝጊያ ከመግቢያው ጋር በደንብ fit ያደርጋል። ሰው ብቻ ነን። ማድረግ የምንችለው ነገር የተወሰነ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ በብዙ ህልም የምንሸልል እና የምንለፍፍ ከመሆን እንጠበቅ። God actually sees our hearts which is both comforting and terrifying. If we fear God we will think twice before we attempt to bribe or impress him with empty promises.

ሀይማኖተኛ መስለን እንታይ ይሆናል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት አምልኳችን ከንቱ የው። የውሸት ነው። ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ ማዳመጥን ማስቀደም፣ ስንናገርም ደግሞ ቃል ስለምንገባው ነገር መጠንቀቅ አለብን። God sees religious pretense and hypocrisy for what they are.
Yared-Maru-Ethiopian-Protestant-Old-Gospel-Song
<unknown>
ለጊዜው ከሚገኝ ፡ ከኃጢአት ደስታ
የዓለምን ትርፍ ፡ ንቆ ራሱን የገታ
እንደመርደክዮስ ፡ በደጁ የተጋ
ከጌታው ሚቀበለው ፡ አለ ብዙ ዋጋ

አርቆ ዋጋውን ተምኖ
ብድራቱን ያየ ትኩር ብሎ
ተጥሎ አይቀርም ፤ በአምላኩ ይታሰባል
እንዳለፈ ውሃ
መከራውን ይረሳል..
እግዚአብሔርን የምትወድዱ ክፋትን ጥሉ ፤ እርሱ የታማኞቹን ነፍስ ይጠብቃልና፤ ከዐመፀኞችም እጅ ይታደጋቸዋል። ብርሃን ለጻድቃን፣ ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።
እናንተ ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ።

መዝሙር 97:10-12
Pursuing Holiness
መክብብ 5:1-7 (Part 9) ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ። የእግዚአብሔር ቤት በራሱ ሰፊ የሆነ ሀሳብን የተሸከመ ሀረግ ቢሆንም በዚህ አውድ የአምልኮ ስፍራን የሚወክል ይመስለኛል። ሰባኪው አምልኮን ለማቅረብ ስንሄድ / ስናቀርብ behave እንድናደርግ እያስጠነቀቀ ነው። እግር ደግሞ ስብዕናን የሚመስል ቃል ነው። Creatureliness or humanity የሚል ሀሳብን በውስጡ ያዘለ…
ወደአድራሻህ ላለመቅረብ ሰበብ የሚያበዛ ሰው መች እግሩን ይጠብቃል? እዚም እዛም ስንት አልባሌ ቦታን የረገጠ እግር በንስሀ እንባ ሳይነፃ እየተንፏቀቀ እፊትህ ሲያደርሰኝ ከሰነፍ መስዋዕት ውጪ ምን ላቀርብልህ እችላለሁ? ለነገስታት ንጉስ አምልኮን ማቅረብ እንዴት እንደቀለለብኝ እንጃ። አንተው ባዘዝከው መንገድ ብቻ የሚገባህን ባለኝ አቅም ሁሉ ልሰጥበት የሚገባ ስፍራ ነው። ወደሀልዎትህ casually ከመግባት ጠብቀኝ። ለአንተ የማደርገውን ነገር ሁሉ with intention እንዳደርገው አሰልጥነኝ። በእርግጥ ሰው ብቻ ነኝ። Thats how you made me. ወደአንተ ስመጣ እንደመልዓክ አልሆንም። ስለዚህ ብዙ እንከን ያለብኝ ልጅህ እንደሆንኩ act ማድረግ እንድችል እርዳኝ። መብረር በሚያቃጣኝ ሰዓት አካሄዴን ጠብቅ።

እውነታውን ስናዘዝ በነዚያ ወቅቶች የቀረብኩህ ራሱ ልሰማህ ሳይሆን የማያባራውን ብሶቴን ሰምተህ መፍትሄ እንድትሰጠኝ ነው፡፡ ራሴን ከእኔው ክፋት ፤ አረማመዴን ከወደቀችው አለም ፈተና ሳልጠብቅ.. ቅዱሳን መላዕክት ፊታቸውን ሳይሸፍኑ የማይቀርቡትን ሀልዎት በስልቹ ሽምደዳ ፀሎት ዘው ብዬ መግባቴን ስንቴ ከፅድቅ ቆጥሬው ይሆን? በምድር ላይ ካሉ ፍስሀዎች ሁሉ አንተን ከማምለክ ጋር የሚስተካከል የለም። ይሄ እውነት ነው። አንተንም ደስ የሚያሰኝህና የሚያከብርህ ተግባር ነው። ነገርግን ትክክለኛውን ነገር ለነሳሳተ ምክኒያት ወይንም በተሳሳተ መንገድ ከማድረግ ጠብቀኝ።

ስንፍና ከመስዋዕቴ ይወገድ። ይልቁንም አንተን ለመስማት መጓጓት እንድችል እርዳኝ። ቃልህ እንደሚል የስንፍናን መስዋዕት አቅራቢ በፊትህ ክፉን እንደሚሰራ አያውቅምና ተላላ ነው፡፡ የራሱን ትከሻ እየመታ በደሉን እያበረታታ መኖሩን ማን ደፍሮ ይነግረዋል (ከቃልህ ውጪ..)  ሰይፍ በሆነው ቃልህ ስንፍናዬን ገስፅልኝና አንተን ለመስማት ልቅረብህ! አንተ እኮ የህይወት ቃል አለህ!

ከሰማሁህም በኀላ ምላሽ ስሰጥ ስሜታዊነት በችኮላ ያንደረደረው ድንፋታዬ አሸማቆኛል! መልካምነትህን ስሰማ እኔም ልመስልህ ወድጄ ስንቱን ሸጋ ነገር አደርጋለሁ ለማለት ልቤ እንደሚቸኩል ታውቃለህ.. አንደበቴም ያልተብላላን ምኞት ሲተፋ አይሰክንም ለመደመጥ ይፈጥናል እንጂ፡፡

ድፍረቱን ከየት አመጣሁት ቆይ? አንተ በሰማይ ምትኖር አምላክ እኔ ደግሞ በምድር ያለው ፍጡር ነኝ.. ምናልባት "ሩቅ" ስለሆንኩ ቃልአባይነቴ consequence የለውም ብዬ ይሆናል.. ተላላነቴን ይቅር በል፡፡ ለሰው እንኳን ቃል ገብቶ መካድ ያስጠይቅ የለ? አንተ ደግሞ በሰማይ ነህ..ገና ሽለላዬን ስደነፋ የልቤን ቆራጥነት ፣ የውሳኔዬን intention፣ የችኮላዬን ምክኒያት እንዳትረዳ የፉከራዬ ድምፅ መች ይከልልሀል? ታውቀኝ የለ? እራሴን ከምረዳው በላይ የምታነበኝ በሰማይ ከፍ ብለህ አለህ፡፡
ሰው ከመሆን ጋር አብረው ያሉትን ውስንነቶች እንዳስብ እርዳኝ። የሆነ ነገር ለማግኘት እንደቸኮለ ሰው ያልተገናዘበን ምላሽ ወደሀልዎትህ እያቀረብኩ እንዳልዘባርቅ እርዳኝ።  አንተ በልጅህ ስም የሚፀለይን ፀሎት በሙሉ እኔደምትሰማ አምናለሁ። በእርግጥ ፀሎቴ ሁልጊዜ inperfect ኘው። እያረምክ ስለምትሰማኝ እንጂ ብዙ ስህተት አለው። ምን እንደምለምን አላውቅም። የሚበጀኝን የምታውቀው አንተ.. እንደአንተ ሁሉን ባውቅ የምፀልየውን ፀሎት እንደምትመልስልኝ ምስክሮቼ ሳልለምን የሰጠኸኝ በረከቶች ናቸው። አሁንም አባት ሆይ አንተን መፍራት አስተምረኝ።  ትክክለኛ ቦታዬን ልወቅ። እግዚአብሔር በሰማይ ነህ። እኔ በምድር ነኝ። እይታዬ፣ እውቀቴ፣ ሀይሌ ውስን መሆኑን እንዳልረሳ አደራ።

ስለዚህ ቃሌን ጥቂት አድርግልኝና ውርደቴን ማርልኝ፡፡ በምድር እንደሚኖር ሰው መማልን አስተምረኝ.. ህልምን የሚገልጠው ስራ ነው.. የኔ ስራ የሚያሳብቀው ደሞ ህልሜ ነው ብዬ የምፎክረው ቅዱስ ህይወት አይደለምና ብዙ ልፈፋዬ "የሞኝ ንግግር" ብቻ ሆኗል፡፡
Afterall what I do matters more than the promises I make. Good intention ብቻውን ጥቅም የለውም። በስራ ያልተገለጡ ንግግሮቼ ሁሉ ያሸማቅቁኛል። በትጋት የሚሰሩ ሰዎች የሚያገኙትን ክብር እሰራለው ብሎ በመፎከር ብቻ ማግኘት ሞኝነት ብቻ ሳይሆን ቃልአባይነት ነው። ምህረትህ ይብዛልኝ።

ሁለት ነገር ልለምንህ.. የተሳልኩትን ስዕለት ለመፈፀም ስንፍና እንዳያዘገየኝ እርዳኝ.. የማልፈፅመውን ነገር አደርጋለሁ ብሎ ከመሳል ጠብቀኝ፡፡ በእርጥም አንተን ለመዋሸት ከመሞከር ቃል አለመግባት ብልህነት ነው፡፡ የልብን ስለምታይ አንደበት ልብ ያላመነበትንና እሰራለው ብሎ ያላቀደበትን ነገር በችኮላ እንዳይለፍፍ ልጓም አበጅለት፡፡

አንደበቴ ወደ ሀጥያት ለመራኝ እልፍ ጊዜያት ሁሉ የሚያኖረኝ ምህረትህ ይግነንልኝ ፤ ከቁጣህም አድነኝ፡፡ የወደፊቱን አላውቅም። ብሳል እንኳን ሳልዘገይ፣ ሰበብ ሳላበዛ እንድፈፀም እርዳኝ። አንደበቴን ከከንቱ ፉከራ መከልከል አስተምረኝ። እንደማላደርግ የማውቀውን ነገር አደርጋለው ከማለት ጠብቀኝ። አንተ እግዚአብሔር አትሸነገልም። ለእንደኔ ያለ ደካማ ብዙ ቃል ከንቱ ነው። ይልቅ ጆሮዬን አንተን ለመስማት የፈጠነ ይሁንልኝ፡፡

The fact that you see my heart is both comforting and terrifying. Its comforting cause you understand me completely. All the good, the bad and the ugly. You see it all. Its terrifying cause I can't fool you. I can't impress you with my convincing performance. Rid me of any religious pretense and hypocrisy.

ከሆንኩት ነገር ውጪ ምንም ነገርን መስዬ አልታይ። አምልኮ ህይወት አይደል? እውነተኛ ህይወት፣ እውነተኛ አምልኮ ይኑረኝ።  አንተ የምትቀበለው ደስ የሚያሰኝህ መስዋዕት ይሁንልኝ። የየዕለት to-do ሊስቴ ላይ የማይቀር ተግባር እሱ ይሁን። ከትህትናህና የተነሳ እንዳትቀልብኝ .. ወደ አንተ ስመጣም ደግሞ "ባልተጠበቀ እግር" ባልተገራ እኔነት እንዳይሆን ፈሪሀ እግዚአብሄርን አስተምረኝ፡፡ The concept of fearing you, በኑሮ ነው የሚገለጠው። አንተ የሚገባህን ቦታ ስትይዝ ሁሉ ይስተካከላል። ሁሉን የምታውቀውን አንተን መፎገር አለመቻል ውስጥ ያለው በረከት ብዙ ነው። ራሴን በመሆን የምህረትህን ኪዳን የጌታዬን ደም ታምኜ ድካሜን እንድናዘዝ ድፍረት ይሆነኛል። ስለዚህም አመሰግንሃለሁ።
በምድር ያሉ ውድ ሀብቶች ሁሉ "ህይወትህን ስጥና ግዛኝ" ይላሉ። ህይወቱን ሰጥቶ የገዛን ብቸኛው ውድ ሀብት ኢየሱስ ነው።
Track 05 Filegaw Aderege...
Aster Abebe Official
እንደገናን ባያውቅ ዳግም ዕድል ባይሰጥ
ማን ይችል ነበረ የጌታ ደጅ ሊረግጥ
እየተደገፈ በማይሰፈር ፀጋው
እንደኔ የቆመ ስንቱን ቤት ይቁጠረው
ስንቱን ቤት ይቁጠረው

ደጋግሞ የተፈተነ እምነቴ
እንዳይንኮታኮት አልቆለት እንዳይወድቅ
እንደስንዴ ሊያበጥረኝ የወጣውን ፈታኝ
በ ‘አይቻልም’ ሲሰድ

የአንደበቴን ሳይሆን ያወቀ የልቤን
እንደተመኘሁት ልሆን ያለመቻሌን
እስኪቆሙ እግሮቼ በብዙ አገዘኝ
ሃይልን እስክቀበል አይዞሽ በርቺ እያለኝ
ያለቀልኝ መስሎት ለሳቀብኝ ጠላት
ማልዶ ማለደልኝ ጉልበቴን አጸናት

ክህደት መሃላዬን አላውቀውም ማለቴን
ዶሮ ሶስቴ እስኪጮህ አልፎ መጨመሬን
ከትንሳኤው ማግስት ብርቱዎች እያሉ
ከሰነፎች ተርታ እንደኔ ያልዋሉ
ፍለጋው አረገኝ መጣ ወዳለሁበት
ሊቀጥለኝ ዳግም ከተቆረጥኩበት

በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
በማለዳ ምስጋናዬ ይኸው
በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
ለተቤዠኝ ምስጋናዬ ይኸው
በማይጠቅሙት መጠቀም ልማዱ ለሆነው
ሳላቋርጥ ምስጋናዬ ይኸው

በትንሽ አዕምሮዬ ስላሰብኩት ነገር
ብዕሬን ይዣለው ቃላትን ቀምሬ በዜማ ልናገር
አልችልም ልደብቅ የውስጥ ደስታዬን
እሱ በኔ ሆኖ ነውሬን አስወግዶ ከሰው መቆጠሬን
ዝም ይባላል እንዴ ደግሞስ ያስችላል ወይ
አትረፍርፎ አድርጎልኝ ረድኤቱን ከላይ
የቃላትን ድንበር ጥሶ ያለፈ መውደድ
አንድ ልጁን ሰጥቶ የራሱ የሚያደርግ

አጽናንቶኛል ባድማ ህይወቴን በመልካምነቱ ሞልቶ
አስደሰተኝ በረሃ ህይወቴን እንደ ኤደን አድርጎ
ተድላ አደለኝ የደስታ የቅኔ ድምጽ ወጣ ከቤቴ
መራቄ ቀርቶ ቀርቤአለሁ አብ ሆኖኝ አባቴ
📌
የመንፈስ ድህነት

ፓይፐር ከስብከቱ በኋላ አንድ ተማሪ መጥቶ
Isn’t Christianity a crutch for people who can’t make it on their own?” ሲለው በአጭሩ አዎ ብሎ መመለሱን ይናገራል። ማንም ለአካላዊ አንካሳነት የተሰሩ ክራንቾችን አይነቅፍም። ክርስትናን ግን እንደዛ ለድጋፍ እንደሚሆን መንገድ ማሰብ የማይፈለግበት ምክኒያት ያ አማኞችን አንካሳና ደካማ ማድረጉ ነው።

በራሴ ብቁ ነኝ ብሎ ለሚመካ ሰው offensive ነው። ኢየሱስ ደግሞ ለህመምተኞች እንጂ ለጤነኞች እንዳልመጣ ተናግሯል። ይህ ማለት ጌታን የሚያገኙት መንፈሳዊ በሽታቸውን የተረዱ ብቻ ናቸው።  ይሄንን ታድያ ሰው ለምን መቀበል አይፈልግም? እውነተኛ ፍስሀና እርካታ በራስ ከመደገፍ፣ በራስ በመተማመን የሚመጣ ስለሚመስለን ነው። We're so obsessed with self-esteem.  በራሳችን ከመደገፍ ይልቅ እንደህፃናት በሆነ ትሁት ልብ እግዚአብሔር ላይ መደገፍን አንፈልግም። Unworthy ሆነን የወደደንን ከማድነቅ ይልቅ ተወዳጅ የመሆንን self esteem እናሳድዳለን።

እነ አዳምን የጣላቸውም ይሄው ነው። እንደእግዚአብሔር በመሆን ውስጥ ያዩት ነፃነት አለ። ጌታ ደግሞ በተራራው ስብከቱ "በመንፈስ ድሀ የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግስተ ሰማይ የእነርሱ ናትና" ሲል የምንጠላውን ምስኪንነት፣ ጎስቋላነት፣ ረድኤት አልባነት ወስዶ የመንግስቱ መግቢያ መዳረሻ ያደርገዋል።

ቃሉም ይህን ያስረግጥልናል። እግዚአብሔር የሚቀበለው መስዋዕት የተሰበረን ልብ ነው።
ይህን ስንል ደግሞ እንደዳዊት በሀጥያት ፀፀት ስለመሰበር ብቻ አይደለም። በመልካሙም ጊዜ አማኝ የልቡ ቅኝት መሆን ያለበት “ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና፥ ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ችለን ልናቀርብልህ እኔ ማን ነኝ?...”(1 ዜና 29፥14) Who is qualified for this?

አብርሃም፣ ሙሴ፣ ዳዊት፣ ኢዮብ፣ ኢሳይያስ ታላላቅ አባቶች እና ታላላቅ ነብያቶች ሁሉ የሚያመሳስላቸው ነገር ይህ ነው። የእግዚአብሔርን ዋጋ በመረዳት ለራሳቸው ትልቅ ግምት ከመስጠት የተፈወሱ ትሁታን ነበሩ። ሲስቱም ይታደሳሉ ፤ በስኬታቸውም አይታበዩም ነበር። They don't base their identity on their success or failures.

ከሴት ከተወለዱት ሁሉ የሚልቅ የተባለው መጥምቁ ዩሃንስ ማንም አይሁዳዊ የማያደርገውን እንደባርያ የኢየሱስን ጫማ ለመፍታት እንኳ ብቁ አይደለሁም ሲል እናገኘዋለን። He is saying that he is not worthy to be a slave. እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ሲል በቁጭት አይደለም። የራሱን ዋጋ የሚያስረሳ ዕንቁነትን ጌታ ላይ ስላየ ነው።

ምናልባትም ከተፃፉልን ብዙ ፀሎቶች አጭሩና በአስፈላጊነቱ ሁልጊዜ relevant የሆነው ፀሎት የምንሰማው ከቀረጥ ሰብሳቢው ነው። "ጌታ ሆይ፤ እኔን ሀጥያተኛውን ማረኝ።" አለ። ፀደቀ። Its so simple that we often miss it. እግዚአብሔር እንደሚመልስ እርግጠኛ መሆን የምንችለው ፀሎት ይህ ነው። በተገላቢጦሹ እራሱ ጴጥሮስ ከእኔ ተለይ እኔ ሀጥያተኛ ነኝ ሲል እያለ ያለው ምን እንደሆነ አውቆ  (as tim keller says God often corrects our prayers and answers what we should've asked for if we knew what he knows) ጠላት ሊፈትነው ብዙ እየጣረም ultimately ግን እንዳይወድቅ እምነቱን በመጠበቅና አብሮት በመሆን መልሶለታል።

የሀጥያተኞች ዋና ብሎ ራሱን የሚጠራው ጳውሎስም የከበረውን መዝገብ የተቀበለ ሸክላ አድርጎ ነው ራሱን የሚቆጥረው። ለበጎ ትጋቱ ሁሉ "በእኔ የሚሰራው ክርስቶስ ነው" እያለ credit ሲሰጥና በድካሙ ሲመካ እናገኘዋለን።

This is how piper defines spiritual poverty
• It is a sense of powerlessness in ourselves.
• It is a sense of spiritual bankruptcy and helplessness before God.
• It is a sense of moral uncleanness and personal unworthiness before God.
• It is a sense that if there is to be any life or joy or usefulness, it will have to be all of God and all of grace.

ከሁሉም በፊት "Sense" የሚል ቃል ያስገባበት ምክኒያት ፣ እንደዚህ ተሰማንም አልተሰማንም በእግዚአብሔር ፊት ግን እውነታው ያ ስለሆነ ነው። ከክርስቶስ ውጪ ሁላችንን የሚገልጥ መገለጫ ነው መንፈሳዊ ድህነት።

"Blessed are the poor in spirit who mourn. Blessed are the people who feel keenly their inadequacies and their guilt and their failures and their helplessness and their unworthiness and their emptiness — who don’t try to hide these things under a cloak of self-sufficiency, but who are honest about them and grieved and driven to the grace of God."
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
CityAlight - My God is A...
CityAlight
Dark, dark is the valley
Faint, the light at my feet
But whatever may face me
My God is all I need.

Bright, bright are the treasures
Life may offer to me
But whatever the pleasure
My God is all I need.

He is my strength, when I cannot go on
Peace, when all my power is gone
Hope, although the night is long and deep


He is my song, for He has rescued me
Joy, now He has set me free
Praise, praise to my Father be
My God is all I need
.

Brief, brief are my days here
Soon my journey complete
But I look to my Savior
Where God has met my need
Yes, He has met my need.

My God is so big,
So strong, and so mighty
There's nothing my God cannot do.
The mountains are His,
The valleys are His,
The stars are His handiwork too.
📌
Melt the clouds of sin and sadness
Drive the dark of doubt away
Giver of immortal gladness
Fill us with light of day

Henry Van Dyke (1907)
Pursuing Holiness
ኑዛዜ... ጌታ ሆይ እኔን ሀጥያተኛዋን ማረኝ "....የሚያመካኙትን አጡ" የተባሉት ሰዎች እጅግ ያሳዝኑኝ ነበረ። ምክንያቱም እድሜዬን ሙሉ ለራሴ ጥብቅና በመቆምና በመከራከር ስላሳለፍኩ ማመካኛ ሰበብና defence ያላቸውን ሚና አበክሬ አውቀዋለሁ... I try to rationalize my actions and why I do what I do...to a point where selfcriticism swallows…
..ቀረጥ ሰብሳቢው ግን በርቀት ቆሞ፣ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ማየት እንኳ አልፈለገም፤ ነገር ግን ደረቱን እየደቃ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ኀጢአተኛውን ማረኝ’ ይል ነበር...እላችኋለሁ፤ ከፈሪሳዊው ይልቅ ይህኛው በእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ጻድቅ ተቈጥሮ ወደ ቤቱ ተመለሰ። Luke 18፥13
...ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ" ዮናስ 2:7
2025/07/06 08:18:44
Back to Top
HTML Embed Code: